cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አርከለዲስ | Arkeledis Media

√ ይህ የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካውንት ነው። 1000057909769 ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ እያላችሁ የቻላችሁትን አበርክቱ። 🔗 https://www.youtube.com/@Arkeledis_21 🔗 https://www.facebook.com/Arkeledis21 @Arkeledis_21

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 415
Obunachilar
+124 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † † ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፴ † † አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት † =>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሠላሳ በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ሚካኤል አረፈ። ይህም አባት የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ስለ ተማረ አዋቂ ነበር። በልቡም አጠናቸው በቃሉም አጠናቸው። ከዚህም በኋላ ንጽሕት ሰውነቱ ከአምላክ በተገኘ የምንኵስና መንገድ በመጋደል ክብር ይግባውና የክርስቶስ ጭፍራ ልትሆን ወደደች። ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በውስጡ ብዙ ዓመታት ኖረ ቅስናም ተሾመ። ከዚህም በኋላ በግብጽ አገር ወደ አለ ወደ ሠንጋር ወጣ በዚያም በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አድርጎ አርባ ዓመት ኖረ ከዚያም የሚበዛ ኖረ በዚያም ዋሻ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ። የትሩፋቱ የጽድቁና የዕውቀቱ ወሬ በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ኤጲስቆጶሳት ተስማው ወዲያውኑ ይዘው በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በተሾመም ጊዜ በጎ አካሔድን ሔደ የዚህን ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ ተወ። ከሚገባው ከሚአመጡለት ገጸ በረከት አንድ ዲናር ወይም አላድ ጥሪት አድርጎ አላኖረም። ከእርሱ በየጥቂት እየተመገበ የቀረውን ለድኃና ለጦም አዳሪ ይሰጣል ለአብያተ ክርስቲያናትም ለንዋየ ቅድሳትና ለቅዱሳት መጻሕፍት መግዣ ያደርገዋል። ሕዝቡንም ያስተምራቸውና ይገሥጻቸው ይመክራቸውም ነበር። አንድ ጊዜ ከመጻሕፍት አንድ ጊዜም ከቃሉ። መልካም አገልገሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ከዚህ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው የሕይወትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ሊሰጠው ወዶ የአንዲት ቀንና የአንዲት ሌሊት ሕመም በላዩ አመጣ። ከቶ አልተናገረም በሚሞትበትም ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን አመሰገነው ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ። ነፍሱንም ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መላ ዕድሜውም ዘጠና ዓመት ከስምንት ወር ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለሚካኤል እግዚአብሔር ዘንዕዶ። ሶበ አሥመሮ ፈድፋደ እንዘ ይጸመዶ። በመጽሐፍ ወቃል ልበ ምእመናን ምዒዶ። አዕረፈ ዮም ቅድመ እለ ይቀውሙ ዐውዶ። በአርአያ መስቀል ቅዱስ እንዘ ይሰፍሕ እዶ። ፨፨፨ =>በዚችም ዕለት ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያ ቆሮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጌታችን በሚያስተምርበት ወራት ሦስት ዓመት አገልግሎታል ከዕርገቱ በኋላም ሐዋርያትን አገልግሏቸዋል ከእሳቸውም ጋራ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ። ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ጳውሎስ ጋራ በመሆን መልእክቶቹንም ወደ ብዙ አገሮች ተሸክሞ በመውሰድ አገለገለው። ከአይሁድና ከአሕዛብም ብዙዎቹን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ከዚህ በኋላም በምሥራቅ ወዳሉ አገሮች ሔደ ከመኵራቦችም ብዙ መከራ ደርሶበት አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለቆሮስ ለወልደ ማርያም ዘተልእኮ። መጠነ ፫ቱ ዓመት በኢያውክኮ። ወእምድኅረዝ ዐርገ ካዕበ ምስለ ጳውሎስ ተወሲኮ። እምነ ሥቃይ ዘረከቦ ወእምንዳቤ ዘሆኮ። አመ ፍጻሜ ወርኅ አዕረፈ በሠናይ አምልኮ። ፨፨፨ =>በዚችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ፍትወተ ሥጋን ድል ያደረገች በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘች ቅድስት አርዋ አረፈች። በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለአርዋ እንበለ ትግበር ጌጋየ። በስምዐ ሐሰት ተቀቲላ እንተ ተንሥአት ጥዑየ። ምስሌሃ ለሰኪብ አመ ብእሲ ሐለየ። እግዚአብሔር መሠጣ ኀበ ትረክብ ናህየ። ከመ በጸሎት ትቤ ተመጠው ነፍስየ። ፨፨፨ =>በዚህችም ዕለት የሰማዕት ዲማዲስ መታሰቢያው ነው በረከቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን። የግንቦት ወር ንባብ ተፈጸመ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ለመንግሥተ ሰማያት የተዘጋጀን ያድርገን ለዘላለሙ አሜን። =>ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት አርዋ እናታችን 2.ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት 4.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት 2.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ 3.አባ ሣሉሲ ክቡር 4.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት 5.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት =>+"+ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: +"+ (ምሳሌ. 31፥29) ፨፨፨፨ ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ፨፨፨፨ ( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።) ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። የግንቦት ወር ስንክሳር ተፈፀመ
Hammasini ko'rsatish...
ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ
Hammasini ko'rsatish...
AUD-20240603-WA0182.mp38.82 MB
ወንድማችን እንኳን ደሕና መጣሕ ምን ሖኑ አባታችን 🥲🥲🥲 ኑእስኪ ተወዳጆች ሊንኩን ነክተን እንግባ
Hammasini ko'rsatish...
*አቡነ_ሀብተ_ማርያም* ፡- አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቴና የሚባሉ በሕገ እግዚአብሔር፣ በሃይማኖት፣ በትሩፋትና በምግባር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡ አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፡- *1/ መብረቅ፣* *2/ ቸነፈር፣* *3/ ረሃብ፣* *4/ ወረርሽኝ፣* *5/ የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡* አቡነ ሀብተ ማርያምን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ‹‹አምስት መቅሰፍታት እንዲጠፉ በደጄ በደብረ ሊባኖስ ተቀበርልኝ›› ብለው የለመኗቸው ታላቅ አባት ናቸው ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለነበር ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በጻድቁ መቃብር ቅዱስ አጽማቸው አርፏል፡፡ የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከተ ረድኤት ምልጃቸው ከሁላችን ጋር ይሁን። ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ፎቶ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ
Hammasini ko'rsatish...
Glob 94,742,361.94 92,025,026.50 89,956,096.55 89,956,096.55 92,202,766.75 93,031,057.29 92,211,591.77 Nib 860,837,000 860,603,000 846,349,000 914,605,000 915,927,000 893,390,000 Awash 3,466,340,480.63 3,429,272,559.49 3,398,787,293.31 3,662,429,069.29 3,562,159,625.09 3,513,555,292.59 Cbe 16,536,348,612.20 16,754,153,428.44 16,037,648,281.68 16,037,648,281.68 16,771,081,390.94 17,170,580,540.78 17,527,414,248.67 Enat 396,755,536.09 401,275,427.71 422,171,331.66 456,497,728.08 465,489,655.80 465,120,336.03 Zb 607,475,442.19 596,826,694.66 586,524,997.79 586,524,997.79 598,924,471.78 595,264,158.51 612,706,864.79 Hb 1,694,604,622.51 1,691,266,220.45 1,734,010,568.26 1,827,300,874.74 1,785,562,455.64 1,737,697,666.36 Dbe 28,554,607.16 28,484,647.30 28,364,301.64 28,364,301.64 29,663,449.82 30,737,239.20 29,363,978.51 Wb 1,364,885,123.55 1,266,014,775.36 1,278,761,466.91 1,361,421,375.55 1,377,459,196.05 1,295,615,758.02 Coop 3,629,991,569.52 3,588,961,861.92 3,479,591,164.72 3,479,591,164.72 3,588,093,048.07 4,644,870,622.68 3,615,480,561.73 Adib 371,722,263.02 370,094,325.90- 375,606,800.25 374,865,200.25 378,368,040.66 378,980,059.12 373,478,004.81 Lib 1,170,182,565.69 1,181,062,553.11 1,189,623,437.66 1,189,623,437.66 1,184,555,352.09 1,248,951,267.55 1,301,888,346.51 Db 3,927,146,433.13 3,952,570,354.69 3,842,220,379.87 3,842,220,379.87 4,265,638,962.59 4,294,710,564.07 4,239,143,408.22 Goh 8,384,693.90 9,578,754.42 8,096,227.27 8,096,227.27 9,968,627.54 10,720,620.18 9,242,939.59 Oib Թ 1,364,334,196.67 1,329,695,143.06 1,328,840,665.43 1,426,460,577.34 1,412,942,623.11 1,437,916,485.44 1,383,364,948.51 Abay 2,258,815,979.44 2,266,015,140.54 2,264,529,684.24 2,361,745,881.13 2,370,108,646.10 2,426,652,857.07 Brib 1,529,939,087.57 1,514,414,054.40 1,495,019,208.13 1,489,366,808.13 1,560,963,781.17 1,598,373,324.65 1,587,260,394.19 Bib 1,215,159,900.81 1,139,917,722.45 1,101,818,011.16 1,101,818,011.16 1,160,654,420.36 1,151,446,861.14 1,149,214, 104.86 Boa 5,530,457,798.40 5,479,003,332.51 5,288,637,976.55 5,288,637,976.55 5,511,388,067.55 5,471,232,129.64 5,580,979,999.87 Amara 416,150,268.29 401,383,637.89 406,345,756.87 450,795,468.11 448,303,511.90 432,821,256.56 Tsehay 134,918,121.66 132,002,027.72 132,206,295.11 132,206,295.11 144,267,312.65 143,553,606.26 143,532,532.36
Hammasini ko'rsatish...
ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ
Hammasini ko'rsatish...
AUD-20240531-WA0134.amr5.59 MB
Photo unavailableShow in Telegram
📌 ያልተሰጠህን አትሻ ❖ የተሰጠህን ጸጋ እንዳታጣ ያልተሰጠህን አትሻ፤ ወደ ጸጋ ወደ ክብር ለመድረስ እግዚአብሔር ቢያበቃህ ያሳየህን እይ ያላሰየህን አያለሁ አትበል፤ አንድም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፣ በተሰጠህ ጸጋ ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ማር አብዝቶ መመገብ እንዳይመች እንደዚህም ሁሉ ያልተሰጠውን መሻት አይገባም አያስመስግንም፡፡ ❖ ነፍስ ያልተሰጣትን ጸጋ በመሻት እንዳትደክም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፤ የምታየው ማየት ቢኖር እውነተኛውን ምትሐት ሆኖ ታየዋለህ ፤ ሕሊና ያልሰጡትን ጸጋ በመሻት በማውጣት፣ በማውረድ የተሰጠውን ያጣል፡፡ ❖ ሰሎሞን መልካም ነገር ተናገረ ‹‹በሰጡት ጸጋ የማይኖር ሰው ቅጽር የሌላትን አገር ይመስላል›› ብሎ ያን ማንም እየገባ እንዲዘረፈው እሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል ፤ አንተ ብሩህ አእምሮ ሰውነትህን ያልተሰጣትን ጸጋ እንዳትሻ ከልክላት፡፡ ❖ ከቁመተ ሥጋ የወጣ አብዝቶ መገበርን ከአንተ አርቅ ያልተሰጠህን መሻት ከአንተ አርቅ፤ ባልተሰጠህና በተሰጠህ ጸጋ መካከል ትሕትናህን፣ ንጽሕናህን መጋረጃ አርጋቸው፤ አንድም በተሰጠህ ጸጋ ላይ ያልተሰጠህን ጋርደው በንጽሕና፣ በትሕትና፣ በልቡናህ የምታስበውን መንፈሳዊ ክብር ታገኛለህ። 📌ምንጭ 📚ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ
Hammasini ko'rsatish...