cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

✞Semayawi~tesfa✞

Semayawi~tesfa 👉የዚህገጵዋናአላማ:-መልእክቶች:መጽሀፍቶች:ትምህርቶች:የቅዱሳን ታሪኮቻቸው እንዲሁም ሌሎችንም በተዘጋጁበት ቋንቋ ጥራት እና መጠን ሁሉ በ1ቦታ እንዲገኙ ለማድረግ ነው◈

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
189
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

""✝ የጾመ ፍልሠታ ትምህርት✝  "" ወላዲተ  አምላክ በገድለ ጻድቃን ኢትዮጵያውያን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  2011  ክፍል  9⃣  ቀን ፲(10)         ❇️መልከአ ኤዶም ትርጓሜ❇️ ✝በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር። " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn 🛑የ2011
Hammasini ko'rsatish...
††† እንኳን ለቅዱስ አባ ሞይስስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አባ ሞይስስ ጻድቅ ††† ††† ቅዱሱ በኋላ ዘመን ከተነሱ አበው አንዱ ሲሆን ትውልዱ: ነገዱ ከግብፅ ነው:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ ቢሆንም ክርስቲያኖች ጠንካሮች ነበሩ:: አባ ሞይስስ ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: ገና በልጅነት ወደ ትምህርት ቤት ገብቷል:: ††† የዘመኑ ትምሕርት ሁለት ወገን ሲሆን 1ኛው የሃይማኖት ትምሕርት: 2ኛው ደግሞ ፍልስፍና ነበር:: የጻድቁ ምርጫው የቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ነበርና ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: እንደሚገባ ተምሮ ስለ ነበርም ዲቁናን ሹመውት ተግቶ አገልግሏል:: ከጥቂት ዘመናት በኋላም በተሻለው ጐዳና እግዚአብሔርን ሊያገለግል ተመኘ:: ይህቺን ዓለምም ይንቃት ዘንድ ወደደ:: መልካም ምኞትን መፈጸም ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና የልቡናውን ተምኔት ፈጸመለት:: ከከተማ ወጥቶ: ቁራጭ ጨርቅ ለብሶ ገዳም ገባ:: በዚያም በረድእነት ያገለግል ገባ:: በፍጹም ልቡ በትሕትና እግዚአብሔርን ደስ አሰኘ:: በጉብዝናው ወራት ይህንን መርጧልና:: ገዳሙንም ሲያገለግል ዕረፍትም አልነበረውምና በመነኮሳት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው:: ከጊዜም በኋላ "በቅተሃል" ብለው አበው ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና: ከምንኩስና ወደ አስኬማ አሸጋግረውታል:: እርሱም ለአሥራ ስምንት ዓመታት አገልግሎቱን ሳያስታጉል: ወጥቶ ወርዶ ገዳሙን ረድቷል:: በእነዚህ ጊዜያት በጸሎት: በጾምና በስግደት ይጋደል ነበር:: በጠባዩም ትእግስትን: ትሕትናን: ተፋቅሮን የሚያዘወትር ነበር:: ጐን ለጐንም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ይፋጠን ነበር:: በዘመኑ የግብፅ ፓትርያርክ አባ ሚካኤል ይባሉ ነበር:: አውሲም በምትባል አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ዐርፎባቸው "ማንን ልሹም" እያሉ ይጨነቁ ነበርና እግዚአብሔር ስለ አባ ሞይስስ ገለጠላቸው:: አባ ሚካኤልም "ለሕዝቤ የሚጠቅም መልካም እረኛ አገኘሁ" ብሎ ደስ አለው:: ጊዜ ሳጠፋም እርሱን አስጠርቶ "ተሾም" አለው:: አበው ትሕትና ሙያቸው ነውና "አይቻለኝም: ተወኝ ይቅርብኝ" ሲል መለሰ:: አባ ሚካኤል ግን "የምሾምህ መቼ በሰው ፈቃድ ሆነና: በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ" ብሎ ዕለቱኑ ሹመውታል:: እርሱም የአውሲም ጳጳስ ሆኗል:: ቅዱሱ አባ ሞይስስም ወደ ሃገረ ስብከቱ ሔዶ አገልግሎቱን ጀመረ:: በጵጵስና ዘመኑ እንደ ከተማ ሰው መኖርን: የሥጋ ምቾትን አልፈለገምና ጠባቡን መንገድ መርጧል:: በገዳም ሲሰራው ከነበረው ተግባር መካከል ያቋረጠው አልነበረም:: ከብቃቱ የተነሳ ለወደፊት የሚደረገውን ያውቅ ነበር:: እርሱ የተነበየው ሁሉ ተፈጽሟልና:: ሕዝቡን ይመራቸው ዘንድም ተግቶ ያስምራቸው ነበር:: ዘወትርም ከክፋት: ከኃጢአት ይጠብቃቸው ዘንድ ይጸልይላቸው ነበር:: ያዘኑትን ሲያጽናና: በደለኞችን ሲገስጽ ዘመናት አለፉ:: አንድ ወቅት ላይም ስለ ሃይማኖቱ ታሥሮ በረሃብ ተቀጥቷል: ግርፋትንም ታግሷል:: ጻድቁ ጳጳስ አባ ሞይስስ እንዲህ ተመላልሶ የሚያርፍበት ቀን ቢደርስ ሕዝቡን ሰበሰባቸው:: "እኔ ወደ ፈጣሪዬ እሔዳለሁና ሃይማኖታችሁንና ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ" ብሏቸው በትእምርተ መስቀል አማትቦ ዐረፈ:: ምዕመናንም በብዙ እንባና ምስጋና ቀብረውታል:: ከተቀደሰ ሥጋውና ከመቃብሩም ብዙ ተአምራት ታይተዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ አባት በረከት ይክፈለን:: ††† ነሐሴ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ሞይስስ 2.ቅዱስ አብጥልማዎስ 3.ሦስት መቶ ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማኅበር) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን 2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና 4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ 5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት ††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" ††† (ሐዋ. ፳፥፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Hammasini ko'rsatish...
✝እንኳን አደረሳችሁ!✝ ✝ከፋሌ ባሕረ ተከዚ አቡነ ዓቢየ እግዚእ! ☞መንስኤ ሙታን ☞ፈዋሴ ዱያን ☞መምህር ዘበአማን ☞ምዑዝ ከመ እጣን . . . ❀ተከዜን በየብስ የተሻገራት፥ ፱፻፵፩ አሕዛብን ያጠመቀ፥ ጎንደርን ከአራዊት ይታደጋት ዘንድ ቃል ኪዳንን የተቀበለ! በረከቱ ይደርብን! (ስዕሉ ከጥንታውያኑ አንዱ ነው) https://t.me/zikirekdusn
Hammasini ko'rsatish...
✝✝✝ እንኳን ለቅዱሳን #ማኅበረበኲር ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ ✝✝✝ ☞ማኅበረ በኲር (ዕብ. ፲፪:፳፫) ማለት ከዓለም ፍጥረት እስከ መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ድረስ የተነሱ/የሚነሱ ቅዱሳን ሁሉ የጋራ መጠሪያ ነው፡፡ ☞እነዚህም አበው፡ ነቢያት፡ ሐዋርያት፡ ጻድቃን፡ ሰማዕታት፡ ደናግል፡ መነኮሳት፡ ባሕታውያን፡ ሊቃውንት፡ ጳጳሳት፡ ካህናት፡ ዲያቆናት፡ ነገሥታት እና ምዕመናን ናቸው፡፡ ☞ታቦታቸው/ቤተክርስቲያናቸው ታች አርማጭሆ #ደብረመጉና (ሞጊና) ውስጥ ይገኛል፡፡ ☞ነሐሴ10 ደገኛ በዓላቸው ነው፡፡ <<< በረከታቸው በዝታ ትደርብን፡፡ >>> ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊትጉባኤ ዘጎንደር✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Hammasini ko'rsatish...
✝✝✝††† እንኳን ለታላቁ ጻድቅና ገዳማዊ አባ ዓቢየ እግዚእ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††✝✝✝ ††† ✝✝✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ✝✝✝ጻድቅና ገዳማዊ አባ ዓቢየ እግዚእ †††✝✝✝ ††† አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው "ዓቢየ እግዚእ" ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ጳጳስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም 'በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው' ማለት ነው:: ዓቢየ እግዚእ በሕፃንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ (ደብረ በንኮል) ሔደው መንኩሰዋል:: በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በአርባ ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር:: ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ:: ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል:: ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል:: ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው:: እንኳን በወርኀዊ በዓላቸው (በ19) ይቅርና በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት 19, ነሐሴ 10) እንኳ ለንግስ የሚመጣው ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል:: አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: ሦስት ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በመቶ አርባ ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እናስባቸው:: ይህች ዕለት ባሕረ ተከዜን ከፍለው ሕዝቡን ያሻገሩባት: አሕዛብንም ያጠመቁባት ናትና በገዳማቸው: ጐንደር ውስጥ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያናቸውም ይከበራል:: በረከታቸው ይደርብን:: ††† ✝✝✝ቅዱስ መጥራ ሰማዕት †††✝✝✝ ††† ቅዱሱ በዘመነ ሰማዕታት በድፍረቱ ይታወቅ ነበር:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" እያሉ ሲያስቸግሯቸው በሌሊት ወደ ቤተ ጣዖቱ ገብቶ የአጵሎንን (የጣዖት ስም ነው) ቀኝ እጁን ገንጥሎ: (ወርቅ ነውና) ለነዳያን መጽውቶታል:: አሕዛብ በዚህ ተበሳጭተው በብዙ ስቃይ ገድለውታል:: †††✝✝✝ ቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ሰማዕት✝✝✝ ††† ††† በወጣትነቱ መከራን ሲቀበል አሕዛብ ሊያስቱት ሁለት ዘማ ሴቶችን ላኩበት:: እርሱ ግን አስተምሮ ክርስቲያን አደረጋቸው:: ለሰማዕትነትም በቁ:: በየጊዜው ሲያሰቃዩት ብዙ ተአምራትን ይሠራ ነበርና ከሰላሳ ሺ በላይ አሕዛብ በክርስቶስ አምነው አብረውት ተሰይፈዋል:: ††† አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን:: አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅርና በረከት ያብዛልን:: ††† ነሐሴ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ዓቢየ እግዚእ ኢትዮጵያዊ (ተአምራትን ያደረጉበት) 2.ቅዱስ መጥራ ሰማዕት 3.ቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ሰማዕት 4.ሰላሳ ሺ ሰማዕታት (የሐርስጥፎሮስ ማኅበር) 5.ቅዱሳን ቢካቦስና ዮሐንስ (ሰማዕታት) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 5.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት 6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል 7.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ††† " ኑ የእግዚአብሔርንም ድንቅ ሥራ እዩ:: ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር ግሩም ነው:: ባሕርን የብስ አደረጋት:: ወንዙንም በእግር ተሻገሩ:: በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል:: በኃይሉ ለዘለዓለም ይገዛል::" ††† (መዝ. ፷፭፥፭) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Hammasini ko'rsatish...