cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሃይማኖታችንስ✞?

✞የኦርቶዶክስ ቻናል✞ > የየዕለቱ ስንክሳር >ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች ከነመልሱ > በቅርብ የጀመረው አስተማሪ ታሪኮች > መንፈሳዊ ዝማሬዎች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ > መንፈሳዊ ፊልሞች > መንፈሳዊ ትምህርቶችና የተለያዩ ፁፎች #ሁሉም_በየእለቱ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
934
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
-430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
                        †                              † [   ያን ጊዜ ጥበብ ትሠወራለች  ] † " ምልክቱስ እነሆ እንዲህ ያለ ወራት ይመጣል ... 🕊 " የሚጣፍጠውም ውሃ ይመራል ፤ ወዳጆችም እንደ ጠላት ድንገት እርስበርሳቸው ይጋደላሉ። ያን ጊዜ ጥበብ ትሠወራለች። ምክርም ወደ ማደሪያዋ ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለች። በብዙ ሰዎች ዘንድ ይፈልጓታል ነገር ግን አያገኟትም። በዚህ ዓለምም ኃጢአት ስንፍና ትበዛለች። ካንዲቱ አገር አቅራቢያዋን አንዲቱን ሀገር በውኑ አንቺ ያለፈ ደግ ሰው አለን ? ወይስ እውነት የሚሠራ ሰው አለን ? ብላ ትጠይቃታለች። ያችም የለም ትላታለች። በነዚያም ወራቶች ሰው ሞትን ይመኛል አያገኝም። " [ ዕዝራ ሱ . ፫ ፥ ፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
Hammasini ko'rsatish...
[ + አልተወኝም + ] .mp35.55 MB
Photo unavailableShow in Telegram
[ + ማርያም አንቲ + ].mp33.33 MB
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊   [  🕊  መዝሙረ ተዋሕዶ   🕊  ]              [  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ] [ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ] 🕊 በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ  እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡ 🍒 ❝ እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ፡፡ ❞ [  እግዚአብሔር በደዌ አልጋ ሳለ ይረዳዋል መኝታውንም በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔም አቤቱ ማረኝ እልሃለሁ፡፡  ] {   መዝ . ፵፥፫   }   †                       †                       † 💖                    🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
🕊 [ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ መርቄሎስ እና ለነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] 🕊  †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!  †  🕊 🕊  † ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ †  🕊 † ቅዱሱ በነገድ እሥራኤላዊ የሆነ የመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ሰው ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሲያስተምር በምሥጢሩና በተአምራቱ ተማርኮ ተከትሎታል:: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ይሆን ዘንድ አድሎታል:: ከጌታችን ሕማማትና ስቅለት በፊትም ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማስወጣት ከቻሉ አርድእትም አንዱ ነው:: ቅዱስ መርቄሎስ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለወንጌል አገልግሎት ተሰማርቷል:: በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሰላሳ አራት ዓመታት በማገልገሉ ሐዋርያት ስሙን "ጳውሎስ" ብለውታል:: ጳውሎስ ማለት ብርሃን ማለት ነውና:: ልክ ሳውል "ጳውሎስ" እንደተባለው ማለት ነው:: ስሙ የግብር [በሥራ የሚገኝ] ስም ነው:: በዚህም ምክንያት ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠራው "ጳውሎስ የተባለው መርቄሎስ" እያለች ነው:: ቅዱስ መርቄሎስ በ፷ [60] ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በሮም ይሰብክ ነበር:: ኔሮን ቄሳር ሊቀ ሐዋርያትን ዘቅዝቆ ሲሰቅለው የተመለከተና ይህንኑ የጻፈ እርሱ ነበር:: ወታደሮቹ ቅዱስ ጴጥሮስን ገድለውት ሲሔዱ ቅዱስ መርቄሎስ እያነባ ቀርቦ: ችንካሮችንም ነቅሎ: ሊቀ ሐዋርያትን ከተሰቀለበት አወረደው:: በፍጥነት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ አምጥቶ በቅዱስ ጴጥሮስ ሥጋ ላይ አፈሰሰና በፍቅርና በክብር ሊገንዘው ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ሊቀ ሐዋርያት አይኑን ግልጥ አድርጎ መርቄሎስን ተመለከተውና አለው:- "ልጄ! ምነው ለእኔ ይህንን ያሕል ሽቱ አባከንክ?" አለውና ተምልሶ ዐረፈ:: ቅዱስ መርቄሎስም እግዚአብሔርን እያመሰገነ በንጹሕ በፍታ ገንዞ እርሱ በሚያውቀው ቦታ ሠወረው:: ሊቀ ሐዋርያትን በመገነዙ የክብር ክብር ተሰጥቶታል:: ቅዱሱ አሁንም ስብከተ ወንጌልን ቀጠለ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እርሱም ተይዞ በኔሮን ፊት ቀረበ:: ኔሮን ቄሳር ቅዱስ መርቄሎስን ጠየቀው:: "እንዴት ባለ አሟሟት ልግደልህ? እንደ መምህርሕ ጴጥሮስ ወይስ ሌላ የምትፈልገው ዓይነት አሟሟት አለህ?" ቅዱስ መርቄሎስ መለሰለት:- "የትኛውም ዓይነት ሞት እኔን አያስፈራኝም:: የምፈልገው ወደ ጌታዬ ቶሎ መሔድ ብቻ ነው::" አለው:: ንጉሡ ኔሮንም ዘቅዝቃችሁ ስቀሉት አላቸው:: ወታደሮቹም በዚህች ዕለት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: 🕊  †   ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ  †   🕊 ከክርስቶስ ልደት በፊት በ፭መቶ [500] ዓመት አካባቢ የነበረ ¤ እሥራኤል ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ መጻሕፍት ተቃጥለው ጠፍተው ነበርና ስለ እነሱ አብዝቶ የለመነ ¤ ጥበብን ሽቷልና እግዚአብሔር ቅዱስ ዑራኤልን የላከለት ¤ በሊቀ መላእክት እጅም ጽዋዐ ልቡናን የጠጣ ¤ ብዙ ምሥጢራት የተገለጡለት ¤ ለአርባ ቀናት ምግብ ሳይበላ አገልጋዮቹ የጠፉ መጻሕፍትን እየነገራቸው የጻፉለት ¤ መጽሐፈ ዕዝራ የተሰኘ መጽሐፍን ያዘጋጀና ¤ በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ዐበይት ነቢያተ ጽድቅ አንዱ የሆነ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው:: † ስለ ቅድስናውም ሞትን አልቀመሰም:: በዚህች ዕለት ቅዱሳን መላእክት ብሔረ ሕያዋን ውስጥ አስገብተውታል:: † እግዚአብሔር ከሐዋርያውና ከነቢዩ በረከትን አይንሳን:: [  † ሐምሌ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት] ፪. ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ ፫. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ ፬. ቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት ፭. ቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሳሌም [  †  ወርኀዊ በዓላት  ] ፩. ቅድስት ደብረ ቁስቋም ፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል ፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ ፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ፯. ቅድስት ሰሎሜ ፰. አባ አርከ ሥሉስ ፱. አባ ጽጌ ድንግል ፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል † " እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን: ሁለተኛም ነቢያትን: ሦስተኛም አስተማሪዎችን: ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን: ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ: እርዳታንም: አገዛዝንም: የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጓል:: ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? . . . ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ:: " † [፩ቆሮ. ፲፪፥፳፰] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
[ ስንክሳር ሐምሌ - ፮ - ] .mp32.66 MB
#ደጋግማችሁ_አታልቅሱ! ሰዎች ወደ አንድ ጠቢብ ሰው እየመጡ ሁልጊዜ ስለአንድ ጉዳይ ያማርሩበታል። ይህ ጠቢብ አንድ ጊዜ ሰዎቹን አስቀምጦ አንድ ቀልድ ነገራቸው። በቀልዱ ሁሉም ሰዎች ከልባቸው በኃይል ሳቁ። ከሁለት ደቂቃ በኋላ ያንኑ ቀልድ ደግሞ ነገራቸው፤ ጥቂት ሰዎች ብቻ ፈገግ አሉ። ያንኑ ተመሳሳይ ቀልድ ለሶስተኛ ጊዜ ሲነግራቸው ግን አንድም ሰው እንኳ ሳይስቅ ቀረ። በዚህ ጊዜ ጠቢብ ሰው ፈገግ ብሎ "በተመሳሳይ ቀልድ ደጋግማችሁ ልትስቁ አትችሉም። ታዲያ በተመሳሳይ ችግር ደጋግማችሁ የምታለቅሱት ለምንድን ነው?" አላቸው! መጨነቅ ችግሮችህን አይፈታልህም፤ ጉልበትህንና ጊዜህን ያባክንብሃል እንጅ። ተንቀሳቀስ! እንደገና ጀምር!  የተሻሉ ነገሮች እየጠበቁህ ነው!
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊 ▷  " የጸጸትና ራስን የመመርመር ሕይወት ! " [    " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "    ] [                        🕊                        ] ----------------------------------------------- ❝ ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም ፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ። .... አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ ፥ ከጣርም ትጠብቀኛለህ ፤ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ። ❞ [  መዝ . ፴፪ ፥ ፭  ] 🕊                        💖                     🕊                              👇
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.