cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

እዚህ ቤት

አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም ኢትዮጵያዊ ሆነን—የሚያግባባ አናጣም! ዕወቂው ዐለሜ...! ኢትዮጵያዊ መሆን—የውርስ እንቁጣጣ በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ! |ታመነ መንግሥቴ ውቤ—አባ ወራው| ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል እና ጥበብ እናወጋለን! ጀበናዋ ተጥዳለች! ፍንጃሎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም! ክሕሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ። ትውልድ❤

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
979
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-1230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Repost from N/a
ሩዋንዳ ምርጫ እያካሄደች ነው! ሐምሌ 08 ቀን 2016 ዓ.ም የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ሩዋንዳ ዜጎች ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚመራቸውን መሪ በመምረጥ ላይ ናቸው። 9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሩዋንዳውያን ድምጽ ይሰጡበታል የተባለው ምርጫ ዛሬ ጠዋት የተጀመረ ነው። ሩዋንዳ በዚህ ምርጫ በውጭ የሚኖሩ ዜጎቿም በመራጭነት እንዲሳተፉ አድርጋለች። ሩዋንዳን ለሩብ ክፍለ ዘመን ያስተዳደሩት የ66 ዓመቱ ፖል ካጋሜ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ፖል ካጋሜ ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ሦስት ምርጫዎችን ከ93 በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል። ባሁኑ ምርጫም ለመሪነት ለመወዳደር ከቀረቡ ስምንት ፖለቲከኞች መካከል፣ ስድስቱ በተለያዩ ምክንያቶች ከምርጫው እንዲገለሉ ተደርገዋል። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
1
Repost from N/a
ከአንድ ዓመት በኋላ በአማራ ክልል "ዳታ" የተባለው የኢንተርኔት አገልግሎት መለቀቁን ዘጆርናሊስት ከጎንደር ምንጮቹ አረጋግጧል። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
ከአንድ ዓመት በኋላ በአማራ ክልል ዳታ ተለቅቋል።
Hammasini ko'rsatish...
Repost from N/a
ዶናልድ ትራምፕን ያቆሰላቸው ሰው አልታወቀም! ሐምሌ 7 ቀን 2016 ዓ.ም የአሜሪካውን የቀድሞ ፕሬዚደንት አቁስሎ ሌላ አንድ ሰው የገደለው የ20 ዓመት ወጣት በደኅንነት ሰዎች እንደተገደለ ተገልጿል። በአጠቃላይ አምስት ጥይት የተኮሰው ማንነቱ ያልተለየው ወጣት ተጨማሪ ሁለት ሰዎች አቁስሎ ቢገደልም ማንነቱ እስካሁን አልታወቀም። ትናንት ምሽት ከፔኒስሌቫኒያ የወጡ ዘገባዎች የቀጣዩ ሕዳር የአሜሪካ ፕሬዚደንት ይሆናሉ ተብለው ቅድመ ግምት የተሰጣቸው ትራምፕ ከሞት ተርፈው ሐኪም ቤት መግባታቸው ተገልጿል። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
Repost from N/a
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ አማራ ክልል ይገኛሉ! ሐምሌ 06 ቀን 2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የ"ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክት አካል የሆነውን ጎርጎራ ፕሮጀክት ለማስመረቅ ዛሬ በቦታው መገኘታቸውን በሥፍራው ካሉ ምንጮች ሰምተናል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አማራ ክልል መግባታቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እስካሁን አልዘገቡም። ሆኖም ከትናንት ጀምሮ በጎንደር ከተማ ዙሪያ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እንደሚሰማ ዘጆርናሊስት ከነዋሪዎች ሰምቷል። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
Repost from N/a
የ"ገስት ሐውስ" ተግባራት እንደሚፈትሽ ተገለጸ አርብ ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫው በእንግዳ ማረፊያዎች እና መሠል የውጭ አገር ዜጎች በሚገኙባቸው ቦታዎች ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደረግ መሆኑን አስረድቷል። ለታለመለት እና ለታወቀ ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በእንግዳ ማረፊያዎች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ አካላት በተለያየ አጋጣሚ ከዚህ ውጭ ሲሳተፉ እንደሚገኙ አሳውቋል። እንዲህ ያለውን ሥጋት ለመቀነስ እና የተማከለ የደኅንነት ሥራ ለመከወን ማንኛውም ከውጭ አገር የሚገባ ዜጋ ምን እንደሚሠራ ለማወቅ ጥረት ይደረጋል ተብሏል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሠላማዊት ዳዊት ከመድረክ ተቋማቸው ቁልፍ የደኅንነት ተግባራት ላይ የሚሳተፍ መሆኑን አረጋግጠዋል። በቅርቡ የዚህን ተቋም ተግባራት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጾቻቸው ሲያደንቁ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጨረሻው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቆይታቸው "አንዳንድ"ያሏቸውን አባቶች "ገስት ሐውስ አታጣቡ"ብለዋቸው ነበር። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
1
Repost from N/a
"ጠ/ሚ ዐቢይ ግዛት የማስፋፋት ፍላጎት የተጠናወታቸው ጽንፈኛ አክራሪ ናቸው" አብዲሰይድ ሙሴ አሊ ሐምሌ 05 ቀን 2016 ዓ.ም የቀድሞ የሱማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የፕሬዝዳንቱ የደህንነት አማካሪ የነበሩት አብዲሰይድ ሙሴ አሊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ግዛት የማስፋፋት ፍላጎት የተጠናወታቸው” እና “ጽንፈኛ አክራሪ” ናቸው ሲሉ ኮንነዋል። አማካሪው ከቢቢሲ ሱማሊኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሱማሊያ “በኢትዮጵያ የተቃጣባትን ጥቃት” ለመከላከል ብቸኛው የመከላከያ አማራጯ አልሸባብ ብቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።  አልሸባብን ሽብርተኛ ብሎ መጠራትንም እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Repost from N/a
ጌታቸው ረዳ ከአውሮፓ ሕብረት ልዩ ተወካይ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ ሐምሌ 05 ቀን 2016 ዓ.ም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ከአውሮፓ ሕብረት የአሪፍካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ጋር ትናንት በአዲስ አበባ መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ጽፈዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔት ዌበር ጋር ትናንት ማምሻውን በነበራቸው ቆይታ በፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ላይ ስላሉ ችግሮች ፣ በሱዳን ስለሚገኙ ስደተኞች እንዲሁም ኤርትራን ጨምሮ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት  ባልሆኑ ኃይሎች ስለተያዙ ቦታዎች መወያየታቸውን ገልጸዋል። በውይይቱ ክልሉ ያለበትን አስከፊ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቻለሁ ያሉት ጌታቸው፣ በትግራይ እና በሌሎች ክልሎች የማገገሚያ እና የመልሶ  ግንባታ ጥረቶችን ለማገዝ በፌዴራል አደረጃጀት ውስጥ ቀጥተኛ ውክልና መሰጠት እንዳለበት ገልጸዋል። በክልሉ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታትም ከፌዴራል መንግሥት እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መሥራት እንደሚያስፈልግ ከስምምነት መድረሳቸውን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
😁 2
Repost from N/a
ቱርክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ክልሏ እንዳያልፍ አገደች! ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ቱርክ በትናንትናው ዕለት መነሻውን ከቤልጅየሟ ሌግ ከተማ አድርጎ  ወደ አርመንያ እና ጆርጂያ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በአየር ክልሏ እንዳያልፍ መከልከሏ ታውቋል። የመጀመሪያ መዳረሻውን ወደ አርመንያ ዋና ከተማ የርቫን ያደርገው አውሮፕላኑ ወደ ቱርክ አየር ክልል ሲቃረብ፣ ከቱርክ ባለስልጣናት ፈቃድ እስከሚያገኝ ድረስ በቡልጋሪያ የአየር ክልል ውስጥ በአየር ላይ ሲዞር ቢቆይም፣ ፈቃድ ባለማግኘቱ ወደ ኦስትሪያ ዋና ከተማ ቬና ተመልሶ ለማረፍ ተገዷል። አውሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት የቱርክን የአየር ክልል ለመጠቀም ፈቃድ አግኝቶ የነበረ ሲሆን፣ የቱርክ ባለስልጣናት ግን አውሮፕላኑ ወደ አየር ክልላቸው ሲጠጋ ሃሳብ መቆየራቸው ተነግሯል። ከአውሮፓ ወደ አርመንያ እና ጆርጅያ ሸቀጣሸቀጦችን ለማድረስ ሲበር የነበረው ቦይንግ 777 ኤፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንም፣ የጉዞ መስመሩን በመቆየር በሩስያ በኩል ዳግም ወደ መዳረሻ ከተሞች መድረሱ ነው የተገለጸው። ቱርክ ክልከላውን ያደረገችው በቀጠናው በጭነት አገልግሎት የራሷን አየር መንገድ የሚገዳደርን አካል ለመከላከል ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ሆኖም ቱርክ በፈረንጆች 2020 ማንኛውም የአርመንያ አውሮፕላን በአየር ክልሏ እንዳይበር እገዳ ጥላ ነበር። ይቀላቀሉን 👉  @zejournalist
Hammasini ko'rsatish...
👍 1💔 1
መንግስት ተንኮለኛው እረኛ፥ እኛ ደግሞ በእረኛው ዉሸት የተማረርን መንደርተኛው ማህበረሰብ! "ተንኮለኛው እረኛ" በሚል ከዚህ በፊት የሰማሁት/የሰማነው ተረት አለ። "ተኩላ መጣብኝ፥ በጎቼ ሊበሉ ነው" እያለ በሀሰት እየጮኸ የመንደሩ ሰው ሲሰብሰብ ውሸቴን ነው በሚል የሚመልሳቸው።  ታዲያ በእረኛው ዉሸት የተማረረው መንደርተኛ እውነተኛ ተኩላ የመጣበት ቀን ሳይደርስለት ቀርቷል። "ከታገቱ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውስጥ 21 መለቀቃቸውን እና ቀሪ 6 ተማሪዎችን ለማስለቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።" ይህ ዜና ከአራት ዓመታት በፊት ጥር 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሲመለሱ የታገቱ 27 ተማሪዎችን አስመልክቶ ፋና ያሰራጨው ነበር። ሆኖም ቀሪዎቹ 6ቱ ተማሪዎች ይቅርና ተለቀዋል ከተባሉት 21 ተማሪዎች ዉስጥ እዚህ ቦታ አለሁ የሚል ጠፍቶ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል። ቤተሰቦቻቸውም በሀገራችን ትልቅ ስፍራ ለሚሰጠው "እርም" ሳይታደሉ ቀርተዋል። በተመሳሳይ ከሰሞኑ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ሲመለሱ የታገቱ 167 ተማሪዎችን አስመልክቶ መንግስት ከአራት ዓመቱ መግለጫው ጋር የሚመሳሰል ቃል እነሆኝ ብሏል።
ከቀናት በፊት ከታገቱ  167 የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ  ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ነጻ መውጣታቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ይፋ አድር
ገዋል። ሁለት ጥያቄዎች አሉኝ(ጥያቄን የሚያዳምጥ ጆሮ እንደሌለ ሳይገባኝ ቀርቶ አይደለም)። 1. ቀሪዎቹ 7 ተማሪዎች ከ160ዎቹ እንዴት ተለይተው ተለቀቁ? (ማለቴ ከአራት ዓመት በፊት ቀርተዋል ከተባሉት 6 ተማሪዎች ጋር በተያያዘም ያልገቡኝ ነገሮች ስለነበሩ ነው።) 2. ኤምባሲዎች፥ የዉጭ እና የሀገር ዉስጥ ሚዲያዎች ለጉዳዩ  ከፍተኛ ሽፋን በመስጠታቸዉ ትኩረት ማስቀየሪያ ስላለመሆኑ በምን እርግጠኛ መሆን ይቻላል? (ከዚህ በፊት ከፍተኛ ትኩረት ያገኙ ጉዳዮችን ለማድበስበስ መንግስት ያልፈነቀለው ድንጋይ አለመኖሩ ልብ ይሏል) ከዚህ ጋር ተያይዞ ተለቀቁ የተባሉ ተማሪዎችን እውነተኛነት ማረጋገጥ የጋዜጠኞች ቀጣይ ስራ ቢሆንም፥ ካለፉት ተሞክሮዎቻችን አንጻር ስጋት አለኝ። መንግስት ተንኮለኛው እረኛ፥ እኛ ደግሞ በእረኛው ዉሸት የተማረርን መንደርተኛው ማህበረሰብ!
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.