cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

መንፈሳዊ ጥያቄዎች - spiritual questions

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ይካሄዳል ሁላችሁ ተሳተፉ ጥያቄ ና አስተያየት ካላችሁ በዚህ ላኩ ና አናግሩን 👇👇👇👇👇 @ortodox_mezmur2 " ስለዚህ በሰው ፊት #ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው #በአባቴ ፊት #እመሰክርለታለሁ፤"" (የማቴዎስ ወንጌል 10:32) 👇👇 ለሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ ይደርስ ዘንድ በቅንነት share አድርጉ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
148
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

8⃣9⃣.ሳኦል ጳውሎስን የጌታ ብርሀን ሲገለጥለት ወዴት ከተማ እየሄደ ነበር? ⚪️ኢያሪኮ ⚫️ሰማርያ 🔴ደማስቆ 🔵ኢጣሊያ @habmisbot Join channel👇 @spiritualquestions በዩቲዩብ ጥያቄ ለመግኘት⬇️⬇️⬇️⬇️ https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
Hammasini ko'rsatish...
❣በ❤️❤️❤️ፍቅር❣ ❣ ❣ ❣ ❣ ❣ ❣ ❣ መጪው የፋሲካ በአል የይቅርታ እና የምስጋና ቀን ነው ስለሆነም ❣ሳላዉቅ በስህት❣ 💙አውቄ በድፍረት💔 አስቀይሜ አሳዝኜ አስከፍቼ 💜ከሆነ ከጉልበቴ በርከክ ብዬ💗 💞ይ 💞ቅ 💞ር 💞ታ ጠይቃለው💕 🖤በችግሬ በሃዘኔ ስከፋ በመከፋት ሳዝን በማዘን💘 💖በደስታዬ ተደስተህ/ሽ ሃሳቤን በመካፈል መፍትሄ ለሰጠከኝ/ሺኝ❣ 💚ስሜታዊ ሆኜም 💙መታገስን ላስተማርከኝ/ሺኝ💜💗 💖💕💞በዙሪያዬ 💓💗💖ስላለህ/ሽ 💝አ 💝መ 💝ሰ 💝 ግ 💝ና 💝ለ 💝ው እስኪ ለምትወደው/ጂው ሰው ይህን መልእክት ላክለት/ላክላት ❣💝💞💞💞💞💓💓 💘 for best friend💘 💛💚💙💜❤❤❤ @mezmur_tewahdo1
Hammasini ko'rsatish...
​​👉 ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46) 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34) 3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43) 4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27) 5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28) 6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46) 7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30) 👉 ሰባቱ ተዐምራት ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት 1. ፀሐይ ጨልሟል 2. ጨረቃ ደም ሆነ 3. ከዋክብት ረገፉ 4. ዐለቶች ተሠነጠቁ 5. መቃብራት ተከፈቱ 6. ሙታን ተነሡ 7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ 👉 አምስቱ ችንካሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች 1. ሳዶር ፦ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት 2. አላዶር ፦ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት 3. ዳናት ፦ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት 4. አዴራ ፦ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት 5. ሮዳስ ፦ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት
Hammasini ko'rsatish...

Hammasini ko'rsatish...
መንፈሳዊ ጥያቄዎች - spiritual questions

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ይካሄዳል ሁላችሁ ተሳተፉ ጥያቄ ና አስተያየት ካላችሁ በዚህ ላኩ ና አናግሩን 👇👇👇👇👇 @SendSpiritualquestionBot " ስለዚህ በሰው ፊት #ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው #በአባቴ ፊት #እመሰክርለታለሁ፤"" (የማቴዎስ ወንጌል 10:32) 👇👇 ለሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ ይደርስ ዘንድ በቅንነት share አድርጉ

​​✟ በፍቅሩ አሸንፏል ✟ ምን አይነት ፍቅር ነው ምን አይነት መውደድ ንጉሱን ከሰማይ ከዙፋን የሚያወርድ እስኪ የትኛው ነው የትኛው ስራችን እስከሞት ውለታ የሚከፈልልን ፍፁም ይገርመኛል ከአይምሮ በላይ ነው ስለአንዱ በግ ብሎ መንጋውን የተወው ፍፁም ፍቅር አየን ፍፁም ትህትና አምላክ ስለ ሰው ልጅ ከላይ ወርዷልና እንዲ ለዋለልን ለታላቁ ጌታ ለፍቅር ባለቤት ሞትን ደገስንለት በአይሁዶች እጅ ተሰቃይቶ እንዲሞት አምላክና ወንበዴ አንድላይ አቁመን ወንበዴውን ፈታን ከአምላክ አስበለጠን ይህን ክፋት አይቶ ከቶ መች እራቀን እሱ አቀርቅሮ እኛን ቀና አረገን ድንጋዩ ልባችንን መች ፍቅሩ ሰበረው ገንዘብ አስበልጠን በ 30 ዲናር ለጠላት ሰጠነው ንፁህ ሆኖ ሳለ ሀጥያት የሌለበት በሀሰት ተከሶ ሞት ተፈረደበት አኛ እየሸጥነው ወዳጄ ይለናል የፍቅር አምላክ መሆኑን በግልፅ አሳይቷል መስቀል አሸክመን ቀራኒዮ ሰደድነው እራሱ ፍቅር በሀሰት ልንሰቅለው እሁንም ፍቅር ነው አሁንም ዝምታ ለጠላቶቹ ነው የሚያዝነው ጌታ እንዲህ እየወደደን እኛ መች ወደድነው ቀትር 6 ሰዓት ከመስቀል አኖርነው አሁንስ ይገርማ በእውነት ድንቅ ነው መስቀል ላይም ሆኖ ማራቸው ነው ሚለው ቁስላችንን ሊያድን ስለኛ ቆሰለ ከሞት ሊያነሳን ሞቶ ተቀበረ እጅግ ቢበረታም የኛ በደላችን በፍቅሩ አሸንፏል ኢየሱስ ጌታችን ✍ ዳዊት ፳፫ አዘጋጅ : ንጋት የአማርኛ ጥቅሶች
Hammasini ko'rsatish...

የሰው እግር አጠበ የሚለውን መዝሙር አዳም @mezmur_tewahdo1 እባክዎ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ለሌሎች ወገኖቻችንም ያካፍሉ
Hammasini ko'rsatish...
የሰው እግር አጠበ ..መዝሙር .mp31.40 MB
እንኳን አደረሳችሁ:- ለጸሎተ ሐሙስ ይህንን እንጸልይ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለተወደደ ጌትነትህ እጅ እነሳለሁ። አንተ በአርያም ሰማይ በአባትህ ቀኝ ተቀምጠሃል። ደግሞም ከጣሪያዬ በታች ኑሮዬን ትመራለህ። የሃጢአተኞች ወዳጅ የተባልክ ሆይ መመኪያዬ ና ሮጬ የማመልጥብህ የዓለት ቤቴ ሆነሃል። እኔን መክሰስ በቃኝ ከማይል ጠላቴ ታድነኝ ዘንድ ደምህ መስቀል ላይ ፈሰሰ። ቀና ስል ሰማዩን በብርሃን ድምቀት ሞልተኸው አያለሁ። ዝቅ ስል እግሬን ስታጥብ ደግሞ አይሃለሁ። በጸሎቴ ጌታዬ ብዬ እጠራሃለሁ። ደግሞ ስታገለግለኝ አይሃለሁ። ዓይነስውሩን ጭቃ በቀባኸው ጊዜ አይኖቹ እንደተከፈቱ የኔንም ዓይኖች ክፈት። አያለሁ ብዬ የሮጥኩበት መንገድ የእሾህ አጥር ሆኖ አይቼዋለሁና። የክብርህ መዝገብ የተቀመጠበት ሸክላህ አድርገኝ። ከአጥናፍ አጥናፍ የሚሰበክ ወንጌልህ እኔንና ቤቴን፣ ሃገሬንና ወገኔን የሚፈውስ አድርግልኝ። ከአፍህ የሚወጣ ጣፋጭ ወንጌል አልጫነቴን የሚያጣፍጥ ጨው ይሁንልኝ። ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የተመላለሱ እግሮችህ በልቤ ተራራ ላይ ይራመዱ። ክብርህን አይቶ ተራራዬ ዝቅ ይበል። የኔ የዋህ ጌታ አንተ ያልሰጠኸኝ ስኬትና ደስታ ከፊቴ ተጠቅልሎ ይጥፋ። የኔ የዋህ ጌታ አንተ የሰራኸው ቤቴን ይሙላ። አንተ የከበርክበት ኑሮ በፊቴ ይኑር። ምስጋናና ክብር ከሰማያዊ አባትህና ከመንፈስ ቅዱስ ጋ ለዘለዓለም ላንተ ይሁን። አሜን። አቡነ ዘበሰማያት እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት @mezmur_tewahdo1
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
መዝሙር ተዋህዶ

ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን የህይወት ቃል ጌታ እግዚአብሔር በገለጠልን ፀጋ መጠን የምንካፈልበት ሲሆን! " ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤"ቲቶ 2÷11 ስለዚህ ፀጋ ያየነውን የዳሰስነውን በስልጣን ቃል ለትውልድ ሁሉ በእምነት እናውጃለን!! ቤተሰባችን ስለሆናችሁ በክርስቶስ ፍቅር እንወዳችኃለን!! /ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን የጠበቁ መዝሙሮች ና የቅዱሳን ገድል ይገኙበታል

ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተበት ወይም ራሱ ምስጢረ ቁርባንን የጀመረበት ቀን በመሆኑ የምስጢር ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡ 📌 ይኸውም የሰው ልጆች ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡《ማቴ.26-26-29》፡፡ ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮ ✥ @mezmur_tewahdo1 ✥ ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯ ✍️ መዝሙር ተዋህዶ መንፈሳዊ ምስሎች
Hammasini ko'rsatish...
ማክሰኞ ይህንን አብረን እንጸልይ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከሰማያዊ አባትህና ከሕያው መንፈስህ ጋ ሰላም እልሃለሁ፡፡ አንተ የህልውናዬ ባለቤት እና ሰሪ ነህ፡ የውስጥ ቤቴ አስተካካይ ነህ፡፡ በተስፋ ቃልህ ደግፈህ ያቆምከኝ ነህ፡፡ እስከ ዓለም ፍጻሜ ካንተ ጋ ነኝ ያልከኝ ነህ፡፡ እናት አባት እንደ ሌለው ልጅ አልተዋችሁም ያለክ ነህ፡፡ በልብህ ትሁት የዋህ ወዳጄ ነህ፡፡ ወደህ የማትከዳ ነህ። ቃልህን ሽረህ አታውቅም። ስለዚህ በማለዳ ከልቤ አመሰግንሃለሁ፡፡ ደግሜ ደጋግሜ አብረኧኝ እንድትሆን እለምንሃለሁ፡፡ ወደ እኔ እንድትመጣ በናፍቆት እጠራሃለሁ፡፡ ወደ ልቤ እንድትገባ እጋብዝሃለሁ። ለኔ ብቻ በሰጠኸኝ መብቴ ላይ አንተም እንድትሰራ እፈቅዳለሁ። በውስጤ ያደሩትን ክፉዎች ውደ ውጭ ስደዳቸው፡፡ በቤተልሄም በረት የተኛህበትን ትንሽ አልጋ አድርገኝ፡፡ ለእንግድነትህ ቦታ ባልተገኘ ጊዜ ከዮሴፍና ከእናትህ ጋ እኔ ውስጥ እደር፡፡ አንተ ውስጥ ገብቼ ልኑር፡፡ ጌታዬ ሆይ ሙሽራህ ነኝ፡፡ ገነቴ በሆነው መስቀለህ ላይ እንደሄዋን ከጎንህ ቀዳዳ አውጥተኧኛል፡፡ ሁሌ ነጭ አልብሰኝ፡፡ ያንተን ሙሽራ አይብረዳት፡፡ ልብሷ አይደፍባት፡፡ ዓይነርግቤ ሳይገፈፍ ይኑር፡፡ ጸጉሬ ለእግር ማበሻ፣ እንባዬ ለእንግድነትህ ውሃ፣ ሽቶዬ ለራስህ ይሁን፡፡ እጅህን እያየሁ ልኑር፡፡ እንደቶማስ ጌታዬ አምላኬ እያልኩ ጠዋትና ማታ ልጩህ፡፡ ሰው ድንጋይ ነው ቢለኝም ውሃ የሚመነጭበትን የቃዴስ ዓለት አድርገኝ፡፡ ሕይወቴ ወደ ውጭ ይፍሰስ፡፡ ዘይቴን እየጨመርክ መብራቴን የበራ እንዲሆን እርዳኝ፡፡ መድሃኒቴ ሆይ ካንተ ጋር ውዬ ጋንተ ጋ ልደር፡፡ እድሜዬ ቅዱስ ስጦታዬ ይሁንልህ፡፡ ትኩር ብዬ እያየሁህ ለልቤ እየተናገርክ አሸምግለኝ፡፡ የኔ ወዳጅ ሁሌ ስለምትሰማኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስለምትወደኝ ክበር እልሃለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስምህ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ይሁንልህ፡፡ አቡነ ዘ በሰማያት እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት @ortodox_mezmur2
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.