cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Aksum university student's union

This is the official telegram channel of Aksum university student's union office @goiteomhailu----0949745846 @Aksum_University_Student_Union -President

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
719
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ለሁሉም በተለያየ ምክንያት በግዚያችሁ ወደ አክሱም ዩኒቨርስቲ ሪፖርት ያላረጋችሁ ተማሪዎች የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ከዩኒቨርሲቲው የማናጅመንት አካላት በመመካከር እስከ ሰኔ 6/2013 ዓ/ም ድረስ ወደ ካምፓስ ሪፖርት ማረግ ለሚችሉ ተማሪዎች ለመጨረሻ ግዜ ከነበሩበት ባች(የት/ት ዓመት ) ሚቀጥሉበት ዕድል ወስነዋል። ከተባለው ግዜ ዘግይቶ የመጣ ተማሪ ግን ሓምሌ 11 ከነበረበት ባች አንድ አመት ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ባች የሚቀጥሉ መሆናቸውን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ join @akumk
Hammasini ko'rsatish...
"አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመጪው ምርጫ በኋላ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የየሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ከምርጫው በኋላ ሰኔ 21 ሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ነባር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመጪው ምርጫ ወደደቤተሰቦቻቸው በመሄድ በምርጫው ይሳተፋሉ ብለዋል። "#የተማሪዎቹ #መሄድ #ግዴታ #አይደለም" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ፤ መምረጥ ለሚፈልጉ ነባር ተማሪዎች እንዲመች ከምርጫው በፊትና በኋላ ያሉ ቀናት የዕረፍት ጊዜ እንደሚሆኑ ገልፀዋል። "#ምርጫ #ማድረግ #መብት #እንደመሆኑ፤ #መምረጥ #የማይፈልጉ #ነባር #ተማሪዎች #በያሉበት #ዩኒቨርሲቲ #መቆየት #ይችላሉ" ብለዋል። ነባር ተማሪዎቹ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ባዘጋጀው የበይነ መረብ የመራጭነት መመዝገቢያ አማካኝነት በምርጫው ለመሳተፍ የመራጭነት ምዝገባ አድርገዋል። ተማሪዎቹ ወደየመጡበት አካባቢ በመሄድ በምርጫው እንዲሳተፉ ምርጫ ቦርዱ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል። @Akumk
Hammasini ko'rsatish...
ለዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፤ የመግቢያ ቀን በአንድ ሳምንት ስለመራዘሙ ውድ ተማሪዎቻችን፤ አንዳንድ ያልተሟሉ ግብዓቶችን በበቂ ለማቅረብ ሲባል መጋቢት 28-30 የነበረው ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የመግቢያ ቀን ወደ ሚያዝያ 5-7/2013 የተራዘመ መሆኑን እናስታውቃለን። ከሰላምታ ጋር!!! የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ረጂስትራር To all Adigrat University students: Reporting Date Extended by One Week!!! The University Registrar announces that the Reporting Date to our University is extended to Miazia 5 - 7/2013 E.C. (April 13-15/2021). Best Regards, Office of the Registrar, Adigrat University.
Hammasini ko'rsatish...
ሀገር አቀፍ የወጣቶች ካውንስልን ለመመስረት ውይይት ተካሄደ፡፡ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የወጣቶች ካውንስልን ለመመስረት ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች፣ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች እና ከሁሉም ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ጋር የዉይይት መድረክ አካሂዷል፡፡ በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችው ንግግር ያደረጉት የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ኢትዮጲያ የአፍሪካ ሀገራት መዲና እንደመሆንዋ መጠን መሰራት ያለበትን ስራ አልሰራንም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በ2004ዓ.ም የወጣቶች ፖሊሲ ሲጸድቅ የወጣቶች ካውንስል በፌደራል ደረጃና በክልል ደረጃ እንደሚሰራ የተካተተ ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት ስራዎች አልተሰሩም፤ ነገርግን አሁንም ጊዜው አልረፈደም ሲሉ አክለዋል። ሚኒስትሯ የወጣቶችን ካውንስል መስርተን ትልቅ ለውጦችን ማምጣት እንችላለን፤ ወጣቱ የራሱን ጉዳይ በራሱ መወሰን የሚችልበት እድል ነው ሲሉ በዕለቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የወጣቶች ካውንስልን ለመመስረት አላማውንና አስፈላጊነቱን በተመለከተ የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ለወደፊቱም ሊካተቱ የሚችሉ ሀሳቦችን በግብዓት መልኩ በመውሰድ የወጣቶችን ካውንስል ለመመስረት የሚያስችል ሁኔታዎች ላይ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ውድ የ2013 ዓ/ም ተመራቂዎች በመጀመርያ የ15/17 ዓመት ልፋታችሁ ውጤት የሆነውን የምርቃት ስነ-ስርዓታችሁ ላይ በአካል ባለመገኘቴ ይቅርታ እየጠየኩኝ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ያንን ብዙ መሰናክል እና የህይወት ውጣ ውረድ ኣልፋችሁ ለዚሁ የምረቃችሁ በዓል በመድረሳችሁ በራሴ እና በአክሱም ተማሪዎች ስም "እንኳን ደስ ያላችሁ"ለማለት እወዳለሁኝ፡፡ እንዲሁም በቀጣይ በምትሄዱበት እና በምትሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ መልካሙን ነገር እንዲገጥማችሁ እየተመኘሁኝ በድጋሜ "እንኳን ደስ ያላችሁ" ለማለት እወዳለሁኝ። Congrajulations!!! ጎይተኦም ሃይሉ የአክ/ዩ/ተ/ሕብረት ፕረዚደንት
Hammasini ko'rsatish...
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ተማሪዎቹን በራሱ ዩኒቨርሲቲ ሊጠራ መሆኑን አሳወቀ ! በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ዝርፊያና ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ ዛሬ በነበረው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ስነስርዓት ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ዩኒቨርሲቲውን ወደነበረበት የቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ያሳወቁት ፕሮፌሰሩ የሁሉም አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን አጠናቆ ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ እንደሚጠራቸው ፕ/ር ገብረእየሱስ አሳውቀዋል። በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ላይ በደረሰው ውድመት እና ዝርፊያ ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው ለ12ኛ ጊዜ ያስመረቃቸው ተማሪዎች ያላጠናቀቁትን ትምህርት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በመማር ነው አጠናቀው የተመረቁት።
Hammasini ko'rsatish...
Entrance Exam Time Table
Hammasini ko'rsatish...
ለሁሉም ተመራቂ ላልሆናችሁ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፥ የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኮረና ቫይረስ እንዲሁም በክልሉ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በዩኒቨርስቲያችን ውስጥ መማር ማስተማር ተቋርጦ ለ11 ወራት ያህል ከትምህርት ገበታ እንደራቃችሁ እና ይሀን አልበቃ ብሎ ስለዩኒቨርስትያችን አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታ እናዩኒቨርስቲዉን ስለሚያወጣቸው አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያሳውቅ አካል አጥታችሁ ስትቸገሩ እና ስትጉላሉ መቆየታችሁ የሚታወቅ ነው። በ "ኢንተርኔት"እና "ኔትዎርክ" መዘጋት ምክንያት ስለዩኒቨርስቲያችን ወቅታዊ ጉዳዮች እና አዳዲስ መረጃዎች በአግባቡ ተከታትለን ስላላሳወቅናችሁ ይቅርታ እየጠየቅን የግቢ መግብያ ቀን በተመለከተ በቅርበት እየተከታተልነው እና በተቻለ መጠን እንዲፈጥን እየሰራን መሆናችን እና ዩኒቨርስርቲው በጦርነቱ ምክንያት የወደሞውን ንብረት በመተካት ተማሪ ለመቀበል የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ መሆኑን ላበስራችሁ እወዳለሁኝ።ስለዚህ የተከበራችሁ ተማሪዎቻችን ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ግቢ የሚገቡበት ቀን አስመልክቶ በመገናኛ ብዙሃን እስክያሳውቅ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁ እጠይቃለሁኝ። "በሰላም ያገናኘን" ጎይተኦም ሃይሉ የአክ/ዩኒ/ተማ/ሕብረት ፕረዚዳንት
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.