cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethiopian Law Network-የኢትዮጵያ ህግ አውታር-Neetworkii Seera Itoophiyaa

WH of the Law!

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
237
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+47 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

"Legislative Framework Applicable Legislation 2. What legislation applies to arbitration? To what extent has your jurisdiction adopted the UNCITRAL Model Law on International Commercial Arbitration 1985 (UNCITRAL Model Law)?" https://uk.practicallaw.thomsonreuters.com/4-502-1378?transitionType=Default&contextData=(sc.Default)#:~:text=Legislative%20Framework,UNCITRAL%20Model%20Law)%3F
Hammasini ko'rsatish...
Arbitration Procedures and Practice in the UK (England and Wales): Overview | Practical Law

የውክልና አይነቶች በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::    1ኛ.ጠቅላላ ውከልና ይህ ውክልና በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ነው፡፡ ጠቅላላ ውክልና ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2204 የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት ምን ምን አይነት ስራዎች እንደ ሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም፡- • የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ፣ መጠበቅ • ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት • በብድር የተሰጠውን ሀብት መሰብሰብ  • ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ ማስቀመጥ • ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ መስጠት • ሰብሎችን መሸጥ • ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሽጥ የአስተዳደር ስራዎች ናቸው፡፡ 2ኛ ልዩ ውክልና ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ውጪ ተወካይ የተለየ ተግባር እንዲፈፅምለት በመግለፅ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው፡- • የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ • አስይዞ መበደር • ካፒታሎችን ኢንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በማሕበር የመግባት • ስጦታን ማድረግ • በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡ የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች የፍትሐብሔር ህጉ በቁጥር 2208 እና ተከታዮቹ መሰረት ተወካይ በርካታ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት ተወካይ ለወካይ በሚሰራበት ወቅት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እና በውክልና በተሰጠው አደራ ላይ ልክ አንድ የቤተሰብ አባት እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መከወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ተወካዩ በሚሰራበት ወቅት ለወካዩ ጥቅም ማሰብ እና ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን የሚጠበቅበት ሲሆን ወካዩ ሳያውቅ በወኪልነቱ ምክንያት ከሚሰራው ስራ አንዳችም ጥቅም መውሰድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ ሁሉ የስራውን አካሄድ፣ መግለጫ እና ሂሳብ በየጊዜው ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በውክልናው ምክንያት የሚያገኛቸውን መረጃዎችም የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡  በሌላ በኩል ወካዩም ግዴታዎች እንዳሉበት ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2219 እና ተከታዮቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዋናነትም ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ ለመክፈል ውል ገብቶ ከሆነ ወይም ተወካዩ በውክልና የፈፀመው በሙያ ውስጥ በተመለከተ የግል ሥራው ከሆነ ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ የውክልናው ሥራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የሚጠበቅበት ሲሆን ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልና ስራው መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከሚገባው የውል ግዴታ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡     የውክልና ጥቅም ውክልና ለወካይ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ የሚያስፈልገው ስራ በወኪሉ በኩል ማከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸውም እንደ ተፈጥሯዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆናቸው በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ምክንያት ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም እድሜቸው ለአካለመጠን ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ የሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ውክልና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ ስለውክልና መቅረት ውክልና ከተሰጠ በኋላ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል ማለት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ሊሆንባቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች በህጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ሁኔታዎች መካከል ውክልናን መሻር፣ የውክልና ስልጣንን መተው፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት ስልጣንን ቀሪ ከሚያረጉ ሁኔታዎች መካካል ናቸው፡፡ ውክልናን መሻር ወካይ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን መሻር እና ለተወካይ የሰጠውን የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካለት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል አላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም፡፡ የወኪል የውክልና ስልጣኑን መተው ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን ለመተው የሚችል ሲሆን የውክልና ሥራውን መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልና ስራውን መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍፁም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ እና ከመካከላቸው አንድኛው የውክልና ስራውን ለመቀጠል በአንድ ምክንያት ያልቻለ እንደሆነና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎቹንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡     ማጠቃለያ በአጠቃልይ ውክልና ጊዜን፣ ገንዘብን እና አቅምን በመቆጣብ በዋናነት ወካዩን የሚጠቅም በመሆኑ የታለመለትን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ወገኖች የውክልና ስምምነት በህጉ ላይ የተቀመጡለትን መስፈርቶች እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማሟላት አለባቸው፡፡ FDRE  MINISTRY OF JUSTICE                   በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Hammasini ko'rsatish...
Adil Lawyer | ሕግ አገልግሎት

የቻናሉ አላማ ህግ እና ህግ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተሸለ እዉቀትን ለማዳበር የተከፈተ ቻናል እና ግሩፕ ሲሆን፣ የሀገር ዉስጥ እና አለም አቀፍ የህግ መፅሀፍትንና የተለያዩ የህግ የምርምር ስራዎችን ያገኙበታል። Ethiopia

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎች በቅርቡ ባሳተመው ቅፅ 25 ላይ የገጠር መሬትን በተመለከተ ምን አዲስ እይታ ይዞ መጣ? **** 1. የገጠር መሬትን በተመለከተ ሁለት ዳኝነቶች በአንድ ላይ ተጣምረው ሲቀርቡ የፍርድ ቤት ስልጣን በተመለከተ በመሬት አዋጁ፣ በስነ-ስርዓት ህጉ እና የክልል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መካከል ግጭት ካለ የመሬት አዋጁ ልዩ ህግ በመሆኑ በቀዳሚነት ሊተገበር ይገባል (Special prevails over the geberal)። የሰበር መ/ቁ. 191968 2. ወራሽነትን ቀድሞ በማረጋገጥ የገጠር መሬትን ቀድሞ መያዝ ልዩ የወራሽነት መብትን የማያጎናፅፍ በመሆኑ ሌሎች ወራሾችን ድርሻቸውን ከመጠየቅ አይገድብም። የሰበር መ/ቁ. 181643 3. የገጠር መሬት አዋጁ ላይ የገጠር መሬትን በሽያጭ ዉል ማስተላለፍ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ መሬቱ ላይ ቤት ቢኖርበትም ባይኖርበትም ዉሉ ህግን ያለተከተለ ሰለሆነ አይፀናም። የሰበር መ/ቁ. 186431 4. የገጠር መሬት ስጦታ ተደርጎል ተብሎ የሚመዘነው በጊዜው በነበረው የገጠር መሬት ህግ እንጅ ከስጦታው በኋላ ተሻሽሎ በወጣው ህግ አይደለም። (Principle of non-retroactivity) የሰበር መ/ቁ. 185848 5. የገጠር መሬት ስጦታን በተመለከተ የመሬት አዋጆቹ ስራ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ ወይም ደግሞ በህጎቹ ባልተሸፈኑ ጉዳዪች ላይ የፍ/ህጉ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ስለሚተላለፍበት ሁኔታ የተዘረዘሩት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሊሆኑ ይገባል። (Common approach of the Cassation using the 1960 Civil Code provisions as a gap feeling to rural land matters) የሰበር መ/ቁ. 188853 6. ከሚመለከተው የመንግስት አካል በስተቀር አንድ ግለሰብ የያዘውን መሬት አያያዙ በህገ-ወጥ መንገድ በሚል አስለቅቆ መያዝ አይችልም። (No one can take justice by his own hand) የሰበር መ/ቁ. 187618 7. የገጠር መሬት ኪራይ ይርጋ ጋር በተያያዘ የመሬት አዋጁ በግልፅ ካላስቀመጠ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ የፍ/ህ/ቁ. 1845 ነው። የሰበር መ/ቁ. 187484 8. ትዳር በሞት ምክንያት ከፈረሰ በሌላኛው ተገቢ የተያዘ የገጠር መሬት እንዲመለስ በወራሾች የሚቀርብ ጥያቄ በጋብቸ የተፈራ የንብረት ክፍፍል ጥየቄ ስለሆነ ሰበር ቀደም ብሎ በቅፅ 4 የመ/ቁ. 17937 በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል። የሰበር መ/ቁ. 186461. Credit to #Ayalew Asfaw
Hammasini ko'rsatish...
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎች በቅርቡ ባሳተመው ቅፅ 25 ላይ የገጠር መሬትን በተመለከተ ምን አዲስ እይታ ይዞ መጣ? **** 1. የገጠር መሬትን በተመለከተ ሁለት ዳኝነቶች በአንድ ላይ ተጣምረው ሲቀርቡ የፍርድ ቤት ስልጣን በተመለከተ በመሬት አዋጁ፣ በስነ-ስርዓት ህጉ እና የክልል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መካከል ግጭት ካለ የመሬት አዋጁ ልዩ ህግ በመሆኑ በቀዳሚነት ሊተገበር ይገባል (Special prevails over the geberal)። የሰበር መ/ቁ. 191968 2. ወራሽነትን ቀድሞ በማረጋገጥ የገጠር መሬትን ቀድሞ መያዝ ልዩ የወራሽነት መብትን የማያጎናፅፍ በመሆኑ ሌሎች ወራሾችን ድርሻቸውን ከመጠየቅ አይገድብም። የሰበር መ/ቁ. 181643 3. የገጠር መሬት አዋጁ ላይ የገጠር መሬትን በሽያጭ ዉል ማስተላለፍ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ መሬቱ ላይ ቤት ቢኖርበትም ባይኖርበትም ዉሉ ህግን ያለተከተለ ሰለሆነ አይፀናም። የሰበር መ/ቁ. 186431 4. የገጠር መሬት ስጦታ ተደርጎል ተብሎ የሚመዘነው በጊዜው በነበረው የገጠር መሬት ህግ እንጅ ከስጦታው በኋላ ተሻሽሎ በወጣው ህግ አይደለም። (Principle of non-retroactivity) የሰበር መ/ቁ. 185848 5. የገጠር መሬት ስጦታን በተመለከተ የመሬት አዋጆቹ ስራ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ ወይም ደግሞ በህጎቹ ባልተሸፈኑ ጉዳዪች ላይ የፍ/ህጉ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ስለሚተላለፍበት ሁኔታ የተዘረዘሩት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሊሆኑ ይገባል። (Common approach of the Cassation using the 1960 Civil Code provisions as a gap feeling to rural land matters) የሰበር መ/ቁ. 188853 6. ከሚመለከተው የመንግስት አካል በስተቀር አንድ ግለሰብ የያዘውን መሬት አያያዙ  በህገ-ወጥ መንገድ በሚል አስለቅቆ መያዝ አይችልም። (No one can take justice by his own hand) የሰበር መ/ቁ. 187618 7. የገጠር መሬት ኪራይ ይርጋ ጋር በተያያዘ የመሬት አዋጁ በግልፅ ካላስቀመጠ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ የፍ/ህ/ቁ. 1845 ነው። የሰበር መ/ቁ. 187484 8. ትዳር በሞት ምክንያት ከፈረሰ በሌላኛው ተገቢ የተያዘ የገጠር መሬት እንዲመለስ በወራሾች የሚቀርብ ጥያቄ በጋብቸ የተፈራ የንብረት ክፍፍል ጥየቄ ስለሆነ ሰበር ቀደም ብሎ በቅፅ 4 የመ/ቁ. 17937 በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል። የሰበር መ/ቁ. 186461.
Hammasini ko'rsatish...
Share Qajeelfama Shaggar Lak.17-2015.pdf
Hammasini ko'rsatish...
Qajeelfama Shaggar Lak.17.pdf13.31 MB
የፍትሐብሔር ክስ እና የዳኝነት ጥያቄ አቀራረብ ሰዎች በየዕለቱ በሚኖራቸው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ፍትሐብሔራዊ አለመግባባቶች ሲከሰቱ እና ዳኝነት ፍለጋ ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ ይታያል፡፡ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ለማቅረብ ደግሞ የክስ ማመልከቻ መዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡  ሆኖም አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ ሊኖረው ሚገባውን ይዘት በተመለከተ ያለው ግንዛቤ ውስን በመሆኑ ሲቸገር ይስተዋላል። በዚህ አጭር ፅሁፍ አንድ ሰው ክስ ሲመሰርት ክሱ ሊኖረው ስለሚገባው ይዘት እንመለከታለን።   የፍትሐብሔር ክስ ማመልከቻ ይዘት መብትና ጥቅሜ ተነክቷል የሚል ማንኛውም ሰው የደረሰበትን ጉዳት በመግለፅ አቤቱታውን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። በ1958 በወጣው የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርአት ህግ ቁጥር 222 መሰረት አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ሲመሰርት የክሱ ይዘት የሚከተሉትን መሰረታዊና አስገዳጅ ነገሮች ማካተት ይኖርበታል፡፡  ክሱ የሚቀርብበት ፍርድ ቤት ስም፣ የሚያስችልበትን ቦታና ስም የፍርድ ቤቱ ስም መገለፁ ክሱ ለቀረበለት ፍርድ ቤት ተደራሽ እንዲሆን ከማድረጉ በተጨማሪም ተከራካሪ ወገኖች ጉዳዩ የቀረበበት ፍርድ ቤት የሚያስችልበትን ቦታ እንዲያውቁ ያደርጋል።  የክሱ አርዕስት፡    የክሱ አርዕስት የሚባለው የክሱን ምንነት በአጭሩ የሚገልፅ ነው፡፡  የከሳሽና ተከሳሽን ስም፣ የሚኖሩበትን አድራሻ እና መጥሪያ የሚደርስበትን አድራሻ       የከሳሽና ተከሳሽ አድራሻ ያስፈለገበት ምክንያት አንድም የፍርድ ቤት ስልጣንን       ለመወሰን ሲሆን ሌላው ደግሞ የመጥርያ አደራረስን ለመወሰንና የተከራካሪዎችን       ማንነት በተገቢው ሁኔታ ለመለየት እንዲቻል ነው።      ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በህግ ችሎታ የሌለው ከሆነ ይሄው በክሱ ላይ መገለፅ ይኖርበታል    ተከራካሪ ወገኖች ህጋዊ ተግባራትን እንዳያከናውኑ በህግ ክልከላ የተደረገባቸው ከሆነ    ለምሳሌ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ክርክሩ የሚካሄድበትን ሁኔታ    ለመወሰን እንዲያመቸው በክሱ ላይ መገለፅ ይኖርበታል።  ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ ያለውን ስልጣን     ክሱን ያቀረበው አካል ነገረፈጅ ወይም ጠበቃ ወይም ወኪል ከሆነ ይህን መግለፅና    ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።    ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮችና የተፈጠሩበትን ጊዜና ቦታ እንዲሁም ተከሳሽ ተጠሪ የሆነበትን ምክንያት፡ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ነገር መቼ፣ የት እና እንዴት እንደተፈጠረ፣ ከሳሽ በጉዳዩ ላይ መብት ያለው መሆኑ እንዲሁም ከተከሳሽ ለጉዳዩ ሀላፊ የሆነበት ምክንያት እና ከሳሽ ከተከሳሽ ላይ ምን እንደሚፈልግ መገለፅ አለበት፡፡  ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ጉዳይ የማየት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ  አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር ግምት በክስ ውስጥ መካተት ያለባቸው ናቸው፡፡ ከሳሽ ለክሱ ምክንያት የሆኑን ምክንያቶች ሁሉ በክሱ ማመልከቻ ላይ አጠቃሎ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በዚህ መሰረትም ከሳሽ ክስ ሊመሰርትበት ሲችል ሆነ ብሎ ባስቀረው ጉዳይ ላይ በድጋሚ አዲስ ክስ ሊመሰርት እንደማይችልና ከሳሽ ያቀረበው ክስ በአንድ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ ሆኖ የሚጠይቀው ዳኝነት ግን ከአንድ በላይ ዳኝነት መጠየቅ ሲችል ቀንሶ ባስቀረው መብት ላይ በድጋሚ ክስ ሊያቀርብበት እንደማይችል በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 216(2፣3፣4) ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል። የማስረጃ አቀራረብ አንድ ክስ ለፍርድ ቤት በሚቀርብበት ጊዜ የቀረበውን ክስ ሊያስረዱ የሚችሉ የተለያዩ ማስረጃዎች ከክሱ ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው። በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 223 መሰረት ከሳሽ ከሚያቀርበው የክስ ማመልከቻ ጋር የሚከተሉትን ነገሮች አያይዞ ማቅረብ አለበት። • የምስክሮችን ስም ዝርዝር ከነ ሙሉ አድራሻቸውና ምስክሮቹ የሚቀርቡበት ምክንያት • ለክሱ መነሻ ወይም መሰረት የሆነውን ሰነድ ዋናውን ወይም ትክክለኛ ግልባጩ • ማስረጃ ይሆናሉ የተባሉ ጽሁፎችን በከሳሽ እጅ የማይገኙ ከሆነ በማን እጅ እና የት እንደሚገኙ • የሚያቀርበው ምስክር ወይም የፁሁፍ ሰነድ የሌለው ከሆነ ይህንኑ መግለፅ ይጠበቅበታል፡፡ ከክሱ ጋር ተያይዞ የሚቀርበው የማስረጃ ዝርዘር የፍርድ ቤቱን ስም፣ የከሳሽና ተከሳሽን ስምና አድራሻ የያዘ መሆን አለበት።    የሚጠየቀውን ዳኝነት በዝርዘር ስለማቅረብ ከስ ያቀረበ ወገን በክስ ማመልከቻው ላይ በተለየ ወይም በምትክ ወይም በተለዋዋጭ የሚጠይቀውን ዳኝነት በግልፅ መጠየቅ አለበት። ከዚህ በተጨማሪ ከሳሽ ክስ የመሰረተው በብዙ ጉዳዮች ወይም በተለያዩ ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ የሚጠይቀውን ዳኝነት በግልጽ ማስቀመጥ እንዳለበት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 224 ላይ ተደንግጎ ይገኛል። ማንኛውም መብትና ጥቅሙ የተነካበት ሰው መብቱን ለማስከበርም ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻ ሲያቀርብ ክሱ የሚቀርብበት ፍርድ ቤት ስም፣ የሚያስችልበትን ቦታና ስም፣ የከሳሽና ተከሳሽን ስም እና መጥሪያ የሚደርስበትን አድራሻ፣ የክሱ አርዕስት፣ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮችና የተፈጠሩበትን ጊዜና ቦታ መገለፅ ይኖርበታል። በተጨማሪም የፍትሐብሔር ክስ ሲቀርብ መጠየቅ ያለበት ዳኝነት ሁሉ ለፍርድ ቤቱ መቅረብ አለበት፡፡ ክሱ ተጠቃሎ ሳይቀርብ ቀርቶ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ነገር ውሳኔ ከተሰጠ ግን በድጋሚ አዲስ ክስ ሊቀርብበት አይችልም። ስለሆነም በፍትሐብሔር ጉዳይ ክስ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ክሱን በሚያቀርብበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።                                                                                                               #በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Hammasini ko'rsatish...
ሰ/መ/ቁጥር 220553 ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም ከተሽከርካሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ ጉድለት ያለበትን ተሽከርካሪ ስላስረከበኝ በተሽከርካሪዉ ሰርቼ ማግኘት ያለብኝን ገቢ እንዲከፍለኛና ውሉ እንዲሰረዝ ነዉ በሚል በከሳሽ የተጠየቀ ዳኝነት እንደውሉ ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት ካሳ እንዲከፈልና እና ውሉ እንዲሰረዝ (actions for cancellation of a contract and damage) የቀረበ ክስ በመሆኑ በክሱ ላይ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር የተደነገገዉ የ 10 ዓመት የይርጋ ጊዜ እንጂ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2298 ስር የተደነገገዉ አይደለም።
Hammasini ko'rsatish...
👉የህንጻ ግንባታ ላይ የሚታዩ ችግሮች /Defects in Building Construction/ 🚧የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለሚታዩ ችግሮች ዋና ዋና የመከሰቻ ምክንያቶች: /Major Causes of defects in construction/ 🌟1ኛ.ጥራታቸውን ያልጠበቁ የግንባታ ግብዓቶችን መጠቀም ⏺ከአመራረት፣ ከአያያዝ ችግር ወይም የአገልግሎት ጊዜያቸው በማለፉ ምክንያት ጥራታቸው የጎደለ የግንባታ ግብዓቶችን መጠቀም በግንባታ ስራው ላይ የተለያዩ ከቀላል እስከ አደገኛ ችግር የሚያመጣ ይሆናል። 🌟2ኛ.ቸልተኝነት ወይም ደካማ የስራ ቁጥጥር ⏺ሁሉም ነገር በተሟላበት ሁኔታ የተቆጣጣሪ ባለሞያዎች ለስራ ቁጥጥሩ ካላቸው ደካማ አቀራረብ የተነሳ በታችኛው የሰው ሃይል የተሰሩ ስህተቶችን በጊዜው ማረም ሳይቻል ቀርቶ በሂደት ችግሮቹ ስር ሰደው እስከ የከፋ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ይሆናል። 🌟3ኛ. ከባለሞያዎች የብቃት/ልምድ ማነስ ምክንያት ችግሮች ይከሰታሉ። ⏺በተወሰነ መጠን ስልጠና ካላቸው ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ ስልጠና ያላቸው ባለሞያዎች ስራን የመረዳት አቅማቸው ደካማ ከመሆኑ ወይም ከሚሰሩት ስራ ጋር ተዛማጅ የሆነ በቂ የሆነ የስራ ልምድ የሌላቸው ሲሆንና ስራን በነሲብ/በግምት በመስራት ምክንያት ስህተቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። 🌟4ኛ. ከዲዛይን ስህተት ⏺ስህተት ያለበትን ዲዛይን አስቀድሞ በሚገባ ሳይታይና ጥያቄ ሳይቀርብበትና ማስተካከያ ሳይደረጋበት /Without Clarification and design Modification/ወደ ስራ ትግበራ መግባት ስራው ከጠናቀቀ በኋላ የእርምት ርምጃ መውሰድ ባብዛኛው አዳጋች ስለሚሆን በሂደት አደገኛ ችግር ያመጣል። 🌟5ኛ. ለስራ ምቹ ባልሆነ የአየር ጠባይ መስራት ⏺አንድአንድ የግንባታ ስራዎችን ለማከናወን የተመቸ የአየር ጸባይን መጠበቅ ግድ የሚሆንበት አስተዳጅ ምክንያቶች አሉ። ▶️ለምሳሌ ዝናብ እየዘነበ የኮንክሪት ሙሊት ስራን ማከናወን በተለይ እንደ የወለል ስላብ ፣ደረጃና ራምፕ ያሉ horizontal structural members /በቀጣይ ክፍሎች የምንመለከታቸው/የተለያዩ የኮንክሪት ችግሮችን ያመጣሉ። 🌟6ኛ. ማጭበርበር ⏺ላልተገባ ጥቅም ሲባል በ ባለሞያዎች፣በተቋራጮች፣ወይም በተቆጣጣሪ ባለሞያዎች አሻጥር ጥራታቸው የጎደለ የግንባታ ግብዓቶችን በመጠቀም፣ ወይም ከተቀመጠ የስራ ጥራት ደረጃ ልክ/Standard/ በታች  ስራው እንዲሰራ ማድረግ በቀጣይ ችግሮች እንዲከሰት የሚያደርግ ይሆናል። ▶️ለምሳሌ: ከደረጃ በታች የሆነ የሙሊት አፈርን ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ስራ ላይ እንዲውል መፍቀድ ቀጣይ የህንጻው አጠቃላይ ደህንነት ላይ የሚያመጣውን ችግር መገመት አይከብድም። 🌟7ኛ. ከተፈቀደው በላይ የሚመጣ ጫና ⏺ህንጻው ሊቋቋም ከሚችለው ጫና መጠን/Design loads/ በላይ ህንጻው ላይ የሚመጡ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ ጫናዎች የህንጻው ደህንነት ላይ እስከ ከፋ ችግሮችን ሊያመጡ ይችላሉ።
Hammasini ko'rsatish...
45ቱ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት Webs 1 AA SCI. & TECH UNIVERSITY http://www.aastu.edu.et/ 2 Adama science & technology University http://www.astu.edu.et/ 3 Addis Ababa University http://www.aau.edu.et/ 4 Adigrat University http://www.adu.edu.et/ 5 Ambo University http://www.ambou.academia.edu/ 6 Arba Minch University http://www.amu.edu.et/ 7Arsi University https://www.arsiun.edu.et/ 8 ASOSSA UNIVERSITY http://www.asu.edu.et/ 9 Axum University http://www.aku.edu.et/ 10 Bahir Dar University http://www.bdu.edu.et/ 11 BONGA UNIVERSITY http://www.bongau.edu.et/ 12 BULE HORRA UNIVERSITY http://www.bhu.edu.et/ 13 DEBARK UNIVERSITY http://www.dku.edu.et 14 Debrebirhan University http://www.dbu.edu.et/ 15 Debremarkos University http://www.dmu.edu.et/ 16 DEBRETABOR UNIVERSITY http://www.dtu.edu.et/ 17 DEMBI DOLO UNIVERSITY http://www.dedu.edu.et 18 Dilla University http://www.du.edu.et/ 19 Dire Dawa University http://www.ddu.edu.et/ 20 Gambella University http://www.gmu.edu.et 21 Gondar University http://www.uog.edu.et/en/ 22 Haramaya University http://www.haramaya.edu.et/ 23 Hawassa University http://www.hu.edu.et/hu/ 24 INJIBARA UNIVERSITY http://www.inu.edu.et/ 25 Jigjiga University https://www.jju.edu.et/ 26 Jimma University https://www.ju.edu.et/ 27 JINKA UNIVERSITY http://www.jnu.et/ 28 KEBRI DEHAR UNIVERSITY http://www.kdu.edu.et/ 29 Kotebe Metropolitan University http://www.kmu.edu.et/ 30 Meda Welabu University http://www.mwu.edu.et/ 31 Mekelle University http://www.mu.edu.et/ 32 MEKIDELA AMBA UNIVERSITY http://www.mau.education/ 33 METU UNIVERSITY http://www.meu.edu.et/ 34 Mizan-Tepi University http://www.mtu.edu.et/ 35 Oda Bultum http://www.odabultum.edu.et 36 RAYA UNIVERSITY http://www.rayu.org/ 37 Selale University http://www.seu.edu.et 38 Semera University https://www.su.edu.et/ 39 WACHAMO UNIVERSITY http://www.wachemouniversity.academia.edu/ 40 Welketie UNIVERSITY http://www.wku.edu.et 41 WERABE UNIVERSITY http://www.edu.et/ 42 Wolayita Sodo University http://www.wsu.edu.et/ 43 Woldiya University http://www.fh2web.academia.edu/ 44 Wollega University http://www.wuni.academia.edu/ 45 Wollo University http://www.wollo.academia.edu/
Hammasini ko'rsatish...
Adama Science and Technology University - Adama Science and Technology University

Welcome to Adama Science and Technology University

#የውክልና #አይነቶች በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ:: 1ኛ.ጠቅላላ ውከልና ይህ ውክልና በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ነው፡፡ ጠቅላላ ውክልና ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2204 የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት ምን ምን አይነት ስራዎች እንደ ሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም፡- • የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ፣ መጠበቅ • ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት • በብድር የተሰጠውን ሀብት መሰብሰብ • ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ ማስቀመጥ • ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ መስጠት • ሰብሎችን መሸጥ • ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሽጥ የአስተዳደር ስራዎች ናቸው፡፡ 2ኛ ልዩ ውክልና ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ውጪ ተወካይ የተለየ ተግባር እንዲፈፅምለት በመግለፅ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው፡- • የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ • አስይዞ መበደር • ካፒታሎችን ኢንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በማሕበር የመግባት • ስጦታን ማድረግ • በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡ የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች የፍትሐብሔር ህጉ በቁጥር 2208 እና ተከታዮቹ መሰረት ተወካይ በርካታ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት ተወካይ ለወካይ በሚሰራበት ወቅት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እና በውክልና በተሰጠው አደራ ላይ ልክ አንድ የቤተሰብ አባት እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መከወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ተወካዩ በሚሰራበት ወቅት ለወካዩ ጥቅም ማሰብ እና ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን የሚጠበቅበት ሲሆን ወካዩ ሳያውቅ በወኪልነቱ ምክንያት ከሚሰራው ስራ አንዳችም ጥቅም መውሰድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ ሁሉ የስራውን አካሄድ፣ መግለጫ እና ሂሳብ በየጊዜው ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በውክልናው ምክንያት የሚያገኛቸውን መረጃዎችም የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡ በሌላ በኩል ወካዩም ግዴታዎች እንዳሉበት ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2219 እና ተከታዮቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዋናነትም ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ ለመክፈል ውል ገብቶ ከሆነ ወይም ተወካዩ በውክልና የፈፀመው በሙያ ውስጥ በተመለከተ የግል ሥራው ከሆነ ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ የውክልናው ሥራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የሚጠበቅበት ሲሆን ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልና ስራው መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከሚገባው የውል ግዴታ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡ የውክልና ጥቅም ውክልና ለወካይ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ የሚያስፈልገው ስራ በወኪሉ በኩል ማከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸውም እንደ ተፈጥሯዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆናቸው በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ምክንያት ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም እድሜቸው ለአካለመጠን ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ የሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ውክልና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ ስለውክልና መቅረት ውክልና ከተሰጠ በኋላ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል ማለት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ሊሆንባቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች በህጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ሁኔታዎች መካከል ውክልናን መሻር፣ የውክልና ስልጣንን መተው፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት ስልጣንን ቀሪ ከሚያረጉ ሁኔታዎች መካካል ናቸው፡፡ ውክልናን መሻር ወካይ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን መሻር እና ለተወካይ የሰጠውን የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካለት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል አላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም፡፡ የወኪል የውክልና ስልጣኑን መተው ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን ለመተው የሚችል ሲሆን የውክልና ሥራውን መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልና ስራውን መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍፁም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ እና ከመካከላቸው አንድኛው የውክልና ስራውን ለመቀጠል በአንድ ምክንያት ያልቻለ እንደሆነና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎቹንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡ ማጠቃለያ በአጠቃልይ ውክልና ጊዜን፣ ገንዘብን እና አቅምን በመቆጣብ በዋናነት ወካዩን የሚጠቅም በመሆኑ የታለመለትን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ወገኖች የውክልና ስምምነት በህጉ ላይ የተቀመጡለትን መስፈርቶች እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማሟላት አለባቸው፡፡ በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ https://t.me/lawsocieties
Hammasini ko'rsatish...
አለ_ህግ🔵Ale_Hig

#አለ_ህግ🔵Ale_Hig ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች፣

https://www.youtube.com/@Lawsocieties

ሁሉንም ሕጎችና ባለሙያዎች እዚሁ ያገኛሉ🔴 All in one, for All. መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው @LawsocietiesBot / [email protected]