cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethioma\ኢትዮማ

ቀላል ነው

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
257
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
-130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

" ያቻት ያቻት ያቻት ያቻት ገሎኛል" የምትለዋን የመጀመሪያ መስመር ብቻ ከዲያሪዋ ላይ አንብቤ ሰላሜ ተነነ።አንድ ዶርም መኖር ከጀመርን መጋቢት አመታችን።ድምጿን ሰምቼው አላውቅም ኧረ ጊቢው ሰምቶት አያውቅም ።የነብስ ጉዳይ ካልሆነ አታወራም ይላሉ ። ተማሪው በሙሉ የማነች ጢባራም ብሎ ሲያያት ይመናቀራል።ባትሪው ሞቷል እምንለው የለም?  charge ካልተደረገ አይሰራም እምንለው እሱን ባትሪ ትመስለኛለች።ፊቷ ላይ ምንም ስሜት አይታየኝም መንፈሷ ሳይቀጠቀጥ አልቀረም።መልከ መልካም ተክለ ቁመናዋም ገዳይ ነው።    ለምንድን ነው ታዲያ ? እየሞተች እንደሆነ የሚሰማኝ።ከትላንት ቤስቲያ እቃዎቿን መነቃቅራ አንዳች ነገር ወሰደችና ያለወትሮዋ እንደተበታተኑ ትታ እየተጣደፈች ወታ ኼደች።      ወረቀቶቿንና ልብሶቿን አጠጥፌ ከጨረስኩ በኋላ አላስችል ሲለኝ ዲያሪዋን አንስቼ ከመሃል ገለጥኩት         "...................ያቻት ገሎኛል" ወዲያው ዝግት አደረኩትና ቦታው መልሼ ወጠሁ።ኢኼው ሁለት ቀን እንቅልፍ አጥ ከሆንኩኝ።     እንደተኛሁ አስመስዬ ፀጥ ብያለሁ።ልብሷን ቀያይራ ወታ ኼደች።ዘልዬ ወረድኩና ዲያሪዋን ወስጄ አገላበጥኩ አገላበጥኩና አገኘሁት።            " . . .   . .  ያቻት . . .ገሎኛል። በአሳር በመከራ ብዙ ሚሊዮን የእንባ ጠብታዎችን አርግፌ አርግፌ አልቀው ሳይሆን አድክሞኝ ማልቀሴን ገታ አድርጌ ከአምስት ወራት በኋላ የእናቴ ልብ በሃዘን ብዛት ቀጥ ከሚል ብዬ ሰባቴ እየወደኩ እየተነሳሁ ሃደራ አበርታኝ ብዬ ፀልዬ ከቤት ብወጣ ? ምነው ባየኋቸው ይኖሩ ይሆን ብዬ በናፍቆታቸው ከተንገበገብኩላቸው ሰዎች አፍ የወጣው የመጀመሪያ ቃል እየተንሾኩ ያቻት ያቻትን ሆነ።በጆሮዬ ባልሰማ በአይኔ ከአፋቸው አነባለሁ። "ከስንት ጊዜ በኋላ ከቤት ወተሽማ እንጋብዝሽ" አሉኝ ጉዋደኞቼ ።          "እሺ" ብዬ ተያይዘን ኼድን።    "አንቺ ምን እሚባልበት ገጠረ ከጓደኞቿ ጋር ሆና በሞተር ሲያልፍ ይዘው አስገብተውት ድፈራት ብለው በቆንጨራ አስገድደው ከደፈራት ኋላ አግባት አሊያ ትታሰራለህ ብለውት ሽማግሌ ልኮ አገባት ካካ.......ቂቂ...... "እኔን አስቀምጠው ተባባሉ ።ከመሃከላቸው ተነስቼ ከዚህ በኋላ ጓደኛ ብዬ ለራሴ እየማልኩ እየተገዘትኩ የተወጋ ልቤን ይዤ ጉዞ ወደ ቤቴ።      ገበያ ደርሼ ስመጣ በስተግራዬ የሚኼዱት "ያቻት ያቻት.......እንዴት እንዴት ሲያደርጋት እንዳልነበር አሰከናት።አሁን ትመናቀራ እንግዲህ ...  ሴት መውለድ ከንቱ ።" በስተቀኜ ያሉት "መኪና ነው የገጨው? ደም አልፈሰሰውም ?.......በቃ ወደ ውስጡ ፈሶ ነው .......ጥሩ አይደለም እኮ ውይ ውይ ልጄን" አሉ ደርባባዋ እናት በሃዘን ደረታቸውን እየመቱ።       "እኔም እኮ ወደ ውስጤ እየደማሁ አመት ሆነኝ አድኑኝ እማማ "አልኳቸው በአይኔ አልሰሙኝም።"   ምን ያህል ነገሮችን በአይኗ ነግራኝ ይሆን? ስንቴ ጮሃ ይሆን ? እንባዬን ለመጥረግ ንባቤን ማቋረጥ ነበረብኝ።     2........ ጫሪ @E_enye 🌈⛅⛅🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...
ኢየሱስ ፈራጅ ነው ወይስ አማላጅ⁉️ . የማቴዎስ ወንጌል ምን ይላል...? ያልተገለጠው ሚስጥር‼️ 👇👇 ማቴ ፤ 24፥ ...       ኢሳ ፤ 33፥ ... ሉቃ ፤ 12፥ ...        ራዕ ፤ 8፥ ... 👇 https://t.me/addlist/k9NjaF5377BkYzQ0 https://t.me/addlist/k9NjaF5377BkYzQ0
Hammasini ko'rsatish...
ኑ የእስራኤላውያንን ቋንቋ ( ዕብራይስጥ ) ተማሩ!! 👇👇 @Hebrewethio @Hebrewethio
Hammasini ko'rsatish...
እንዳለመታደል ታደልኩህ #2 ተቀጣጠርንና ከሶስት ቀናት በኋላ ተገናኘን ።ስለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት ልናወራ የተቃጠርን እስኪመስለኝ አራንባና ቆቦ ወሬዎችን እያወራኝ እስከሰፈር ሸኝቶኝ ተመለሰ።አልከፋኝም እንዲያውም ደስ አለኝ።ሌላ ቀጠሮ ይኖረናል ።ተመስገን ስለቶቼ ሁሉ እየሰመሩልኝ ነው ስል አሰብኩ።ልክ እንደፍላጎቴ በተደጋጋሚ ይቀጥረኝና በወክ ቤቴ ድረስ ሸኝቶኝ ይመለሳል ።በአንደኛው ቀን ምሳ ሰአት ቀጠረኝ።         "ምሳ በልተን አብረን እንውላለን "ቢለኝ ይሁና እንደፍቃድህ አልኩትኝ።ሀገር የሚያውቀኝ በኩራቴ እንዳልነበር ያለኝን ሁሉ እሺ ላለማለት አቅም እስካጣ ተረታሁ። ሲቀርበኝ ባሰብኝና አረፈው።ከምሳ በኋላ ሲያስቀኝ ዋለ።የሚያወራው ነገር  ያስቃል ወይንስ አያስቅም አመዛዝኜ አላውቅም ።ብቻ አጠገቤ መሆኑ ያፍነከንከኛል።ከልቤ እየሳኩኝ በመሃል                          "እኼ ፈገግታሽ እንደሆነ ታውቂያለሽ? ለክፎት ያስቀረው'አለ። አማርኛ ተንሻፎበት ነው ? አይ ስለልቡ እያወራልኝ ይሆናል ብዬ ከማሰቤ የጉዋደኛውን ስም ጠራልኝና "እንደሱ አይነት አፍቃሪ አይቼ አላውቅም ።እንዴት እንደሚንሰፈሰፍልሽ እኮ ብታውቂ "  ድርቅ አልኩ የሆነ ድምጽ የሰማሁም መሰለኝና በአይኔ ለመፈለግ ሞከርኩ ግን ምንም የለም ።          "ህ..............."አልኩኝ ድክም ባለ ድምጽ ። "ከሃያ ስኩል ጀምሮ ያፈቅርሽ ነበር እንዳይነግርሽ ደግሞ አንቺ ትንሽ ታስፈሪያለሽ" የብቻ እየተባልኩ የምበሸቀው ያ ጉዋደኛው እንደዛ ጠርቶኝ ቆሌውን ገፍፌ ነው። ልቤ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሸሽቶ እየኼደ እንደሆነ ይሰማኛል ።እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል ?  አ.....ሃ...... የሰማሁት ድምጽ የልቤ እንቅሽታ ነዋ።ከዚህ በኋላ ልቤ ዳግም አንድ ይሆን ይሆን ? በራሴ ሃሳብ ኼጄ ከዳርቻው ደረስኩ ።እሱ እያወራ ነበር ለካ..... ትከሻዬን ነክቶ ሲነቀንቀኝ ነው የተመለስኩት።ግራ ባጋባው ጊዜ አስሬ "ምን ሆነሽ ነው  .........?" ይለኛል። ውስጤ ጭስስ አለ።እሱ አሁንም ለመቁጠር እስኪከብደኝ "ምን ሆነሻል ደህና ነሽ? "ይለኛል ።እኔ ደግሞ አፌን ከፍቼ እየጨስኩ እንደሆነ ጭስ ወቶ እንዳያውቅ ዝግት ብዬ ጪጭ። ሁለቱን እጆቼን አንድ ላይ በእጆቹ እላይና እታች አድርጎ ያዘና ያለማቋረጥ አይኖቼን አተኩሮ እያየ             "ደህና አይደለሽም ? ምነው ምን ሆንሽ?" አለኝ። ውስጤ መጬስ ሳይሆን ፈልቶ ኖሯል ለካ በሁለቱ አይኖቼ ቀዳዳ ገነፈለ።ወንበሩን አስጠግቶ አጠገቤ ቁጭ አለ። እጁን ትከሻዬ ላይ አሳረፈና ወደ ደረቱ ስቦ አቀፈኝ እንደሁል ጊዜው።መንተክተኬ ብሶ ቲሸርቱን አርጥቤ ለኔ እስኪታወቀኝ ማቆም ዳገት ሆነብኝ ።   እንባዬን ለመጥረግ አስሬ ፊቴን ሲዳብሰኝ ልቤ ቦታዋ እየተመለሰች ዳግም ታፈገፍጋለች።ምናልባትም ለመጨረሻ ጊዜ ይሆናል የሚያቅፈኝ ብዬ ወደ'ሱ ተጠግቼ ይብሱን ልጥፍ አልኩ።ልቤ እየደማ አይኔም እርግፍ እርግፍ  ..........         ይዳኘኝ ያየ ይፍረደኝ ያየ                            ወዶ የጋየ😳      ጫሪ @E_enye 🌈🌈⛅🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
እንዳለመታደል ታደልኩህ " ሄለው ሄለው" ተሳስቶ የደወለ ሰው ይሆን? ለምን አያወራም ብዬ ሳስብ። "የብቻዬ" አለ የደወለው ሰው። የሃይስኩል ተማሪ እያለሁ ጉዋደኞቼ ሊያበሽቁኝ ሲፈልጉ የሚጠሩኝ አጠራር ነበር።"ወዬ" አልኩኝ መቼም ቆየት ያለ የቅርብ ጉዋኛዬ ነው ብዬ "እንዴት ነሽ?" "አለው ........ሰላም ነው?" "ሁሉ ሰላም ስልኩን ኼጄ ላንሳው እንዴ ብዬ ሳስብ እኮ ያነሳሺው" "ውይ እኔ ደግሞ እንዳትደክም ብዬ አነሳሁታ"" "እቺ ታደክመዋለች ብለሽ አሰብሽልኝ ? ድሮም እኮ ከላይ ከላይ እንደሆነ የምትኮሳተሪብኝ እጠረጥራለሁ" "ተው እንጂ" ድምጹ ሲያምር አልኩ በውስጤ። "እኔ ልሙት ዘርዛሪት" ወይኔ ወይኔ !......አምላኬ ድረስ ...........አይ እንዴት ? ቀበዣዠርኩ ለራሴ። "ሄለው ሄለው ......ይሰማሻል?" "እ........አው........አው"ድንዝዝ አልኩ።አለ አይደል በደስታ ደነዘዝኩ እሚሉት አይነት። "አንቺ የት ኼደሽ መጣሽ?".......እሺ አሁን ክላሳቹ በር ላይ ነኝ ውጪ "አለኝ። "'ቤት ነኝኮ ክላስ ጨርሰናል።" "አንዳንድ የምትናፍቂያቸው ሰዎች እንዳሉ አስበሽ ብትመጪ ምነው ግን?" ያዘነ በሚመስል አሹዋፊ ድምጽ አለኝ። "ቢነገረኝ ምናልባት አስብበት ነበር" "ላወራሽ ምፈልገው ቁምነገር አለኝ ።ነገ ደውልልሻለሁ በቃ ሀደራ ደሞ ስልክ አንሺ" "አሁን ቢነገረኝ እወዳለሁ.....የምን ቀጠሮ ነው?"አልኩ ቀልድ አስመስዬ።እንኳን ትምህትርት አልኖረን እንዲ ስፍነከነክ ቢያየኝ ይታዘበኝ ነበር። "እኔ ልሙት የምሬን ነው ።በቃ እራሴን ካልደፋሁልሽ የምቀልድ ነው የሚመስልሽ?" "በቃ የብቻ ትሙት በላ"አልኩት።ለሱ ቀልድ አስመስዬ ብልም እኔ ግን ምኞቴን ነበር ያልኩት ። "የብቻ ከምትሞትስ እኔኑ ይድፋኝ...ይልቅ አላዝግሽ ነገ እደውላለሁ ።ቻው ዘርዛሪት።" ዘርዛሪት ብሎ የሚጠራኝ እሱ ብቻ ነው።የልቤ ፅላት ላይ የታተመው ።በሆነኛው ቀን ክፍል በር ላይ ቆሜ ከጀርባዬ የሌላ ክፍል ተማሪዎች ተሰብስበው ያወራሉ።ትንሽ ቆየት እንዳለ የሆነ የሊቃውንት ዝማሬ የሰማሁ መሰለኝ።ግነት አይደለም! ድምፁ ሲያምር ።ዞሬ አየሁት ዓይን ለዓይን ተጋጨን ። ዓይኔን አልሰበርኩምእንዲያውም ፈዝዤ አረፍኩት።ድሮስ ከዚህ መላክ መሳይ የመላክ ድምጽ ካልሆነ ምን ይወጣ ኖሯል። እሱ ዓይኑን ዞር አደረገና ከጉዋደኞቹ ጋር ወደ ክፍላቸው ገቡ።ከዚያን ቀን አንስቶ እኼው ተለክፌ ቀረው ቀረው።በምግባባው ጉዋደኛው አማካኝነት ተዋወኩት።። ዓይኖቼ ከዓይኖቹ ሲገጣጠሙ እፎይ እላለሁ።የኔ አለመሆኑን እረሳለሁ።በወር አንዴ ፊት ለፊት በቅርበት ከተገናኘን ሰላም ሲለኝ ጥብቅ አርጎ አቅፎኝ ነው።እኔም ባገኘሁት አጋጣሚ ደረቱ ላይ የወር ሙሉ የናፍቆቴን ጥብቅ እላለሁ ። እኼው ከስምንት ወር በኋላ ዛሬ ደወለ። "ምን ሊወራኝ ይሆን?" የብቻ ያለኝ ግን የምርም የብቻው እንድሆን ፈልጎ ይሆን? ወይስ ጉዋደኛው ነግሮት ነው?"ቀበጣጠርኩኝ። ደወለ።ብዙ ካወራን በኋላ "በአካል ላግኝሽና ነው የምነግርሽ በስልክ አይሆንም ።" አለኝ። #2.......        ጫሪ @E_enye ⛅⛅🌈🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...
"  ብሌኔ ትለኝ የል?" "አዎ" "ያላንቺ በድን ነኝም ብለኸኛል" "ነኝኮ" "ታዲያ ትተኸኝ አትኺዳ? በሌን ብቻዋን ምን እርባን ይኖራታል" "እማዬ ሆዴ! አዎን ማያዬ ነሽ።የእናቴ  ቤት እየተቃጠለ ዓይኗን እየጠነቆሉባት ዓይኖችሽን እያየሁ በፍስሃ ልኑር? አተላ ነገር ነው የሚሆነው።" " አንተ ብቻህን ምን ትፈይድላታለህ?" "ለዛ አይደል መኼዴ?   እንደኔ አይነት ብዙ ወዳሉበት"    "የኔ ጌታ እሺ በለኝና አትሂድ....ምንም አልዋጥልሽ እያለኝ ነው" "እእእ አሁንስ?" አላት ከአገጯ ቀና አድርጎ ከንፈሯን ከሳማት ኋላ። ምንም ቃል ሳይወጣት ለደቂቃ አሻቅባ እያየችው ቆየችና ድንገት በሁለቱም ዓይኖቿ እንባዋን ታረግፍ ጀመር "እናት እንዲሁ ከብዶኛል እንባሽ ተጨምሮ አልችለውም " አለና ለራሱ ደረቱ ላይ አጥብቆ አቀፋት። "አንቺን ሲነኩሽ ማሰብ አልችልም ።ያቺ ሰባት ወንዶች የደፈሩዋት .... ተይው ግን እሳቱ የተቀጣጠለበት ኼደን ካላጠፋነው እሱ  መቶ ያቃጥለናል ።" "እግዜሩ ካልቀጣቸው ሰው በምን አቅሙ ያኚን ጋኔን ይመክታል?  አላማረኝም ተው......" "አልተውም 😂"ግንባሩዋን ጉንጮችዋን አገጭዋን አይኖችዋን ከንፈሩዋን ተራ በተራ ስሞ ሲያበቃ " "አንቺን የመሳሰሉ ጥኒኒጥ ልጆቼ አኚህ የሳጥናኤል ተኩላዎች ባሉበት ተወልደው እንዲያድጉ አልፈልግም" አላት በዓይኖቹ ዓይኖቿን አተኩሮ እያየ። ምንም ብል ድካም ነው ብላ አሰበችና ዝምታን መረጠች።  ዓይኖቻቸው እንደተገለጡ እኩለሌሊት ካለፈ ወዲያ እንግላል በተኛበት  ክንዱዋን ደረቱ ላይ አስሞርክዛ ቀና አለችና ቁልቁል ስትመለከተው "ባንቺ አየን ያንድዬን ስራ ያለእቅድ እንደሚሰራ ፈጣሪ ተራቆብሻል ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል"እያለ ማንጎራጎር ጀመረ። "ስሜትህን ለመደበቅ አትጣር ,የእውነት ምን እየተሰማህ ነው?"                  "እስከዛሬ ሽቅብ አይቼሽ አላውቀውም ወይ ቁልቁል አይተሺኝ አታውቂም? መኮሮኒ አፍንጫ አይደለሽ እንዴ"" "ጌታ የምሬን ነው" አለች ቆጣ ብላ። "ጌታን እውነታው ጎራዳ ነሽ" "ታውቃለህ ግን.......ኡፋ እንደውም ተወው በቃ"አለችና ደረቱ ላይ ተኝታ እጇን ፀጉሩ ስር ሰዳ ማሻሸት ጀመረች። " ዎ አትነካኪኝ,  ለሊት መንገደኛ ነኝ ይደክመኛል" "ስድ ! ሂድ ወደዛ" "ነይ ወደዚ😂😂" ከትከት እያለ ሳቀ።ከደረቱ ላይ ተነስታ ጀርባዋን ሰታው ተኛች።እየሳቀ ዞረና ፊቱን አንገቱዋ ስር ሸጉጦ እጁን በወገቡዋ አዙር ሆዷ ላይ አደረገና እቅፍ አደረጋት። ዓይኗን ስትገልጥ ወገግ ብሏል ።ዞር ስትል ብቻዋን ነች።የሌሊት ልብሷን እንደለበሰች ወርዳ ሩጫ ጀመረች።ቦታውጋ ስትደርስ ማንም አልነበረም።ጠጋ አለችና የመስሪያ ቤቱን ጥበቃ "ምልምሎች የሚሳፈሩት ከዚህ አልነበር እንዴ? አባቴ" " አዎን ከዚሁ ነው በለሊት ወጡ እኮ" እጢዋ ዱብ አለ። " አላለቅስም!! ሰው መንገድ ሲኼድ አይለቀስም ሰላም ተመለስ ነው ሚባለው"ብቻዋን እንደእብድ እያወራች ወደ  ቤቷ ገባች።ከዚያች እለት በኋላ ያወቁዋት ሰዎች "ፍንጭታም ነች ወይንም ጭርሱንም ጥርስ የላትም ይሆናል" እያሉ ያሟታል።ቀበሌ የሚሰራ ሰው ቤቷ አቅራቢያ ስታይ ጉልበቷ ይከዳታል በእጃቸው ወረቀት ይዘው ከሆነ ደግሞ ሰው "አበደች?" እስኪላት አሪ እያለች ታለቅሳለች።ቤቷ ሚመጣ ሁሉም ሰው ሊያረዳት የመጣ ይመስላታል ።    የፈሩት ይደርሳል ሚሉት እውነት ይመስላል።ጎህ ሳይቀድ ተሰብስበው በሯን አንኳኩ ።ከፍታ እንዳየቻቸው እንባዋ ረገፈ። ደብዳቤው ምን ይላል አላለችም ።ሃገሬው ለሁለት ተከፍሎ ገሚሱ በሷ የደረሰ በማንም አይድረስ ሲል ሌላው አሟርታ ገደለችው አላት። ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ ሰፈሩ ዳግም በለቅሶ ድብልቅልቅ አለ። መጣ!!! ሞቷል የተባለ ሰው በህይወት ሲመለስ እንዲህ ያስለቅሳል ማለት ነው በማለት እየተገረመ መልሶ መልሶ "የታለች?" ሲላቸው ። "ሞትህን መቋቋም ከብዷት እራሷን አጠፋች" ብለው መለሱለት።ተሰብስቦ የሚያለቅሰውን ሰው እየከፈለ ወቶ ኼደ።አልተመለሰም። ሰብሰብ ብለው ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ እመንገድ ዳር ላይ የተቀመጠውን እብድ እየተመለከቱ "አዪዪ ያን የመሰለ ልጅ እምጽ ...እንዲ ከምያንገላታው በገደለው" ያሻቸውን እንዳሻቸው ፈረዱበት።ስንቱ ይሆን ለነሱ ጋሻ ልሁን ብሎ በተመሰቃቀለ "በገደለውን" ያተረፈ አመድ አፋሽ ።😖😢😢 ጫሪ Enat Kassahun 🌈🌈⛅🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...
አመሻሽ ላይ ቦርሳዬ ናት እምላትን ጥቁር ፌስታሌን አንጠልጥዬ መጥረግ ባዛለው አካሌ ማሰብ መጨነቅ የማይታክተው ጭንቅላቴን ተሸክሜ ስመጣ   <<ፀሀይ ፀሀይ>> ከኔ ወደ'ታች እራቅ ኀብለው ቤቴ አቅራቢያ የቆሙ ጎረቤቶቼ ይጠሩኛል። <<እሜት እቴቴ>>የአንዳቸውን ስም ጮክ ብዬ ጠርቼ መለስኩላቸው ። <<ፍጠኝ ሰው ሁሉ ወቷል >> አሉ።እየተጣደፍኩ ተራምጄ አጠገባቸው ደረስኩ።       <<ምነው የምን ለቅሶ ነው?>> <<ያቺ 'ታችሰፈር የህፃናት መምህሯ እህቷ ሞታ ኼዳ አስቀብራ መታለች . ......በይ ቶሎ ውጪ>>አሉኝ።ወደ ቤቴ ስገባ ስለሽቷቸው እያሰብኩ ነበር።ውስጤ ባፍንጫዬ እየማገ የዋለውን አቡዋራ ለመርሳት ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀበት።የነጠላቸው ንጣት እየፈተኩ የዋልኩት ክምር ልብስ ያደከመኝን ድካም አስረሳኝ።           'ቤት እንደገባሁ ወደ መፀዳጃ ቤት እየኼድኩ ልጆቼን ቀሚስና ነጠላ እንዲያወጡልኝ አዘዝኳቸው። ተመለስኩና ያወጡልኝን ቀሚስ ቀየርኩ። እምያውድ ሽቶ ባይርከፈክፍበትም አቡዋራ አልነበረበትም። ነጠላዬን ያዝኩና ስጣደፍ ወጣሁ ።ነጠላውን ሳየው ጭስ መስሏል ።ሌላው ቢቀር ጫፉ ላይ ያለው ቁጭት መሬት የጠረጉበት ነው እሚመስል።አንድ ለእናቷ የሆነችውን  ነጠላዬን እንባ ባቀረሩ  ዓይኖቼ ተመለከትኳት ። ልከፍት ያልኩትን ያጥር በር ትቼ ወደ ቤት ተመለስኩና ትንሹ ልጄን ለእነቴቴ ኼደህ <<ኺዱ አትጠብቁኝ ከኋላቹ እደርስባቹሃለሁ>> ብላለች በላቸው ብዬ አልጋዬ ላይ ወጥቼ እንደልማዴ ፊቴን ትራሴ ውስጥ ቀበርኩ።        አንድ ላይ ደባል ሆነው ያደጉትን አመል ልተው ቢሉ እሱ አይተውም። የሀይ ስኩል ተማሪ ሳለሁ ት/ቤቱ ግቢው ውስጥ ባሉ ክበባት ከፍተኛ ተሳትፎ ለሚያደርጉ ተማሪዎች ሆቴል የምሳ ግብዣ አዘጋጀና እኔና ጉዋደኞቼም ተጠራንበት ።ነገ በጊዜ ወታቹ ጥሩኝ አብረን እንኼዳለን ተባባልን።በማግስቱ ሊጠሩኝ በሰዓቱ መጡ።እኔ ልብሴን ቀያይሬ ሳልዘገጃጅ ነበር የደረሱት።ጫማና አለባበሳቸውን አይቼ የኔን አሰብኩትና እያመመኝ ስለሆነኺዱ ብዬ ቀረሁ። ልብስና ጫማ ህይወቴ ውስጥ እንደቀልድ ቁምነገር እየሆኑ እንደሆነ  ልብ ያልኩት በቅርቡ ነው።በአለም ላይ ያለኝን ብቸኛው ወንድሜን በደስታው ቀን ብቻውን  የተውኩት 'ለት።የሚስቱ ቤተሰቦች መልስ ጠርተዉት ሲኼድ ያላንቺ ቤተሰብ የለኝም አብረን ነው ምንኼደው ቢለኝ እሺ አልኩትና ቀኑ ተቃርቦ ሳምንት ሲቀረው ካልጋ አልወርድም አሞኛል አልኩ። ቅር እያለው ግድ ሆኖበት ከሚዜዎቹ ጋር ያለቤተሰብ ብቻውን ኼደ። ስለቀረው አልከፋኝም።እኔና ልብሴን አይው ወንድሜን እንዲገምቱብኝ አልፈልግም።    በዚህ ሁሉ መሀል እኔ እራቆቴን ብቆምስ እብድ ነህ ተብዬ ያለው በውቀቱ ሀቅ አለው።        ©Enat Kassahun 🌈🌈⛅🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...
ፍቅር ቢይዘኝና ያፈቀርኩት ልጅ የምጠላትን ሴት እንደሚያፈቅር ብሰማ ምናልባት እሱም ም...ና....ል...ባት ቢያስቀናኝ እንጂ ሌላ ልቀና እምችልበት ምንም ምክንያት ሊኖረኝ ይችላል ብዬ አስቤ አላውቅም።               በሷ ግን ቀናሁባት። በቅናት ግብ ግብ ከማለቴ የተነሳ  "ማን አባትዋ ስለሆነች ነው እንዲ ሚሽቃበጥላት " ሁላ አልኩኝ ልክ እንደሚመለከተው ሰው።ስራ ለመኼድ ስወጣ እሷም ከቤትዋ ስትወጣ እንገጥማለን። አንዴ የሰፈሩ ባለሞተር በሌላኛው ቀን የሰፈሩ ባለባጃጅ ጭራሽ አያት የሆኑት ባለመኪናው ጋሽ ወልዴ        "ህብስቴ ልሸኝሽ?" ይሏታል ተራ በተራ።እኔ በሬ ላይ ቆሜ እያየሁ እርር እላለሁ ። መስሪያ ቤት ስገባ "ህብስት እናንተ ቢሮ ጉዳይ አለኝ ብላኝ ነበር አንቺን አናገረችሽ ?"     "ህብስት የትዋ ?" "እናንተ ሰፈሯ እዚህ ድረስ ከምትደክም ባንቺ ላይ በላከች ነበር" ጎሽ የቀራት እዚህ ነበር እዚህም ደረሰች ብዬ በውስጤ ወደ ስራዬ። ሰፈር ቡና ጠርተውኝ ምኼድበት ሁሉ አላጣትም። ምኗ ነው ህብስት ምስጥ ይመስል የትም አትታጣም።      "አይ ህብስት ሂሂሂሂሂሂሂ ያንቺ ነገር እንደው ቂቂቂቂቂቂ"  ይላል። ሰዉ ሁሉ ቡናውን ትቶ የሷን ወሬ ነው የሚጠጣው።ጓደኞቼ ሳይቀሩ ስለሷ ሲያወሩ ስሰማ አልቻልኩም ቅጥል አልኩ።ቤተሰቦቼ ተደመሩና ጭርሱን  ድብን አረጉኝ።      "እማ ወንድሜ የላከልኝ አዲሱ ጫማስ?" "እእእ ቁጡሩ ያነሰሽን ከሆነ ለህብስቴ ሰጠው" "በስንት ብር?" "የምን ብር እግሯ ላይ ሲያምር ብታይ ሰጠኋት" "እማዬ ጤና የለሽም?"            "ልጅቱ ምን ነካት? .....በእጅሽ ልታደርጊው ነው?" ጭርሱን ቤቴ ገባችልኝ እርፍ!! ማን ስለሆነች ነው ገሚሱ ስሟን እሚዘፍነው ገሚሱ ልጎዝጎዝልሽ እሚላት?  ሀገሬውን አሾረችው እኮ። ሁሌ እንደደበረኝ ብሆንም ይብሱን የደበረኝ ቀን ተነስቼ ቤተክርስቲያን ኼድኩ።በሴቶቹ መሳለሚያ ስፍራ ተሳልሜ ከመቀመጤ የለቅሶ ድምጽ ሰማሁ። "ህቅ......ህቅ... . . . ..ያላንተ ማን አለኝ  .......ህህህህህህ .... .ህህህህህ  .  . ...ያላንተኮ ማንም የለኝም......የኔ ጌታ እባክህ . . . . .ህቅ,...ህቅ  . ..አባቴ ሁሉን እያወክ  ....ህህህህህህ" አልቻልኩም ውስጤ እርብሽብሽ አለ።የልጅቱ አለቃቀስ ሆድ ያባባል። ዓይኔ እንባ አቆረ።አልቅሳ አልተው ስትል ተነስቼ ላባብላት ኼድኩ።   ፊቷን ጉልበቷ ላይ ደፍታ ኩርምት ብላ ቁጭ ብላለች።አቅፌ አባበልኳት።እንባዋን ጠራርጋ ቀና አለች።     ህ...ብ . .  . .ስ....ት !!  ክው አልኩ።ያቺ  ሳቋ ከቀበሌ ቀበሌ እሚሰማው? እኮ ሀገሩ ሙሉ እሚወዳት ህብስት።ከሌላ ሀገር ለስራ መታ ተከራይታ ነው የምትኖረው ።ቤተሰብ እንደሌላት ሲወራ ሰምቻለሁ።ግን እኮ ሳር ቅጠሉ ነው የሚወዳት። "ማን አለኝ?" እንዴት ትላለች? ስሟን በክፉ ሲነሳ ሰምቼ አላውቅም ፊቷም ሁሌ ፋሲካ ነው እንደተፍነከነከ።እራሴን ታዘብኩት።ግን አንድ ነገር ገባኝ እኔ ከፈጣሪ መንገድ ወጥቼ በሰው ተከቦ መኖር መኖር እሚመስለኝ ከንቱ ነኝ። እሷ ግን ፈጣሪዋን ስላስበለጠች ከሰው ሁሉ ከፍ አድርጎ ያኖራታል።በባይዘውያችን ላይ ያን ሁሉ ታሪክ ውሃ በላው።አሁን ህብስቴ የልጄ የክርስትና እናት ነች። ©EnatKassahun 😂😍 🌈🌈⛅🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
የነካኝ የተጠጋኝ  አይደለም ያየኝ ፊቱን ያጨፈግግብኛል። ቢቀርበኝ  መበላሸቱ ሀቅ ነዋ። በእይታ ብቻአይሆኑ ሆኜ መበላሸቴ ከመታወቁም በላይ ሌላውን ማበላሸት መቻሌ አያጠያይቅም ። ቅጥል ክስል ብያለሁ።አብሮኝ የሆነ በጥቁሩ ታሪኬ ይደበዝዛል።     ካለእናትህ በስተቀር እኼን መስቀልህን ሊያግዝህ እሚፈቅድ የለም የለም የለም አይኖርምም ። እንደዛሬው ከሁሉም መሸሽ ከመጀመሬና ሁሉም ከኔ መሸሽ ከመጀመራቸውም  አስቀድሞ ያየኝ ይፈካ  ነበር።ሰላምን የሚፈልግ ሊያርፍ ይጠጋኝ ነበር።አብቤ እማርክ አስደስት ነበር። ከሰዐታት ባንዱ ለሆኑ ያህል ደቂቃዎች እንደዛ ነበርኩ እንደዚህ ሆኜ እንዚህ ሲሆን እንደዛ ቢሆን እንደዚ ሆንኩ አለኝ።ከሌሎቹ የተለየ ነገር አይቼበት አይደለም።ሌሎቹ የሚሆኑልኝን ሩብ ታህል  ልሁንልሽ ብሎኝ አይደለም መከራው አሳዝኖኝ ተሸነፍኩ እንጂ ። ብዙ ባለጸጋ አውቃለሁ ከሀብቱ ብካፈል ብዬ ተመኝቼ አላውቅም ።ግን ግን የተሰበረ ሳይ ብደግፈው እላለሁ ።የታመመ ሳይ ባስታምመው እመኛለሁ ። መከራውን ሲተርክልኝ ላስደስተው እራሴ ለራሴ ማልኩ።ሲፈጥረኝ በቃል አስሮኛል መሰል ለቃል ያለኝ ነገር ፍጹም ነው።ሳቁን ልፈጥርለት ሽቼ ስውተረተር ከልቤ ላይ ተቆረጥኩ።ተሰባብሬ ከጉድጓድ ተከተትኩ ቤንዚል ተርከፍክፎ አፈር ተመለሰብኝ። ከጊዜያት በኋላ አፈሬን አራግፌ ስወጣ ሁሉም እራቀኝ ከስያለሁ።እርባነ ቢስ ሆንኩኛ.............. እያደር አይኔ ቢገለጥ ከሁሉም ሸሸሁ።ከዚህ ሁሉ በኋላም የዋህ እንደሆንኩኝ አስቦ ወደ አመድነት ሊቀይረኝ ዳግም ሲባዝን ሳይ አስቀያሚ ሆንኩኝ እንጂኮ አሁን ብርቱ ነኝ እኼን ሰውዬ ይዤ ላቀጣጥለው እንዴ ያሰኘኛል። አሉ ደግሞ አንዳንድ ብተዋቸው ማይተዉኝ ።ሊቀርቡኝ አይፈልጉም ግን አቃጥለው አቀጣጥለውኝ ሊሞቁብኝ የሚያሻቸው አፍኜ ልገድላቸው እንደምችል ያልገባቸው። 😔እንደወረደ(02/ህዳር/2016) 08:47ቀን 🌈🌈⛅🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌈🌈⛅🌷🌷🌷 🇪🇹👉 @ethioma1
Hammasini ko'rsatish...