cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

እኔና ቤቴ ግጥም የህያው ስሜት መግለጫ ከብቸኝነት ግዞት ማምለጫ መሆኑን እናምናለን፡፡ እኔና ቤቴ ግጥም ከቃላት ስደራ በላይ የእውነትና የእምነት ውጤት መሆኑን የነቆራ እና የምስጢር ዋሻ መሆኑን እናምናለን፡፡ አምነንም እነንፅፋለን! አባላችን ይሁኑ! ° ° ° @mr_trump_poems ግጥሞትን ለመላክ እና ለማንኛውም አስተያየት @termo_dynamics ን ይጫኑ።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
1 934
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
በአቢላማ የቴአትር እና የፊልም ፕሮዳክሽን እየተዘጋጀ #በየወሩ ወደናንተ የሚደርሰው ምርጥ የግጥም ምሽት #ስር በተሰኘ ርዕስ ግንቦት 28/2014 ዓ.ም በ ማሜ ሆቴል ከቀኑ 9:00 ሰዐት ጀምሮ ይካሄዳል። #4ኛ ምሽታችንን ለመታደም ቀጠሮዎን ከእኛ ጋር ያድርጉ።በዕለቱም የተለያዩ ገጣሚያን ተወዳጅ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ። 🦋ያስታውሱ ⏰ @abilam @abilam ለበለጠ መረጃ @sew19 ላይ አናግሩን
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
እንዳትቀሩ 😍🙏
Hammasini ko'rsatish...
የገዘፈው ፍቅርሽ ያሸነፈው ገፅሽ ፣ የመራኝ በመንገድ ከገደል ወደኩኝ እንዲያው ስንገዳገድ። ያለ ዘርዐ አንቺ :በልቤ ፀንሼሽ፣ ህልወቴን ንቄ በድፍረት አምልኬሽ፣ ምን ይሉታል አሁን ያንቺ ከእኔ መሸሽ?። ያላግባብ ያለ ህግ መንታ አንቺን ለመውለድ እየጓጓ ልቤ፣ ምን ነክቶሽ ይሆነው ማቶኝ እንዳሳቤ?። እንደ ደጀ ሰላም : እየተሳለምኩሽ፣ አንቀልባ ሳልሸክፍ :እየተሸከምኩሽ፣ እኔ ጦሬሽ ሳለ ስለምን ደከመሽ?። አየሽ የእኔን ሁሉን ላንቺ ማለት ስላንቻ ማሰቤ ስለእኔ በመርሳት። ካንቺነትሽ በላይ የእኔ አንቺን ማሰብ:ሲያሞሽ መዋተቴ፣ በፈለግሽኝ ልክ በዝቼ መምጣቴ፣ እሱ ነው አደለ ያራቀሽ ከህይወቴ?። ይሁና ግድ የለም "ፍቅር ፍቅር ያለ የማይሆነው የለም። #ፍሬው @yene_eyta
Hammasini ko'rsatish...
ሆሳዕና ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ ~ ባማልክቱ ክብር የገነትን ደጃፍ እንድትከፋፍቱ በዘንባባው ንጋት ከስጋት ተፈቱ። እንግዲህ… በቁም መታሰርህ ፤ የገባው እረኛ ፤ በቁምህ ሲፈታህ ሕማማቱ ገብቶ ፤ ሕመምህ ሊፈወስ ፤ ሲደቅልህ ጌታህ የምጥ ሕይወት አልፎን ወጋገኑ ተርፎን ከጭንቀት ተነቅቶ ፤ በእውን ሲታለም፤ መነሣትን አውቀው መቃብር መግባትን ፤ የመሰለ የለም። : የሆሳዕና 'ለት የምትረሰርሱ በፍትሃት ውሆች፤ እሑድ ልትነሡ ዛሬ 'ምትሞቱ እናንተ የዋሆች፤ እንደዚህ እመኑ : በዛ በመቅደሱ እናንተ ልትከብሩ ፤ ክበሩ ይፈተታል፤ ከዚህ ከሞት ወህኒ አሳሪም ታሳሪም ፤ ባንድ ቀን ፟ይፈታል፡፡ በዚህ ምስጢር ዕለት ኀጢአቱ ሲፈታ ነውር ተጎንጉኖ ሕዝቡም "አሜን" ይላል እንደሞተ አምኖ። … ከደጀ ሰላሙ በየዓመቱ መጥቶ ፍትሃት ሊፈታ እያቀረቀረ፤ አንዳንዱ ለምዶበት በሬሳነት ቀረ። : ያልታደለ!!!
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ታድያስ እንኳን ወደፊልም ዞን በደህና መጡ። ዛሬ ማታ 3 ሰዓት ላይ፣ በ2021 ለእይታ የበቃውን፣ አውት ኦቭ ዴይዝ ወይም ወደኛ ስንመልሰው ከሞት ውጪ የተሰኘውን አክሽን ትሪለር ፊልም በአጭሩ እናስመለክታችኋለን። በዚ ቪድዮ ላይም ቻናላችን 10ሺ ተከታዮችን በማፍራቱ እናንተን ውድ ቤተሰቦቻችንን እያመሰገንን #የ200 ብር ካርድ ሽልማትን አዘጋጅተንላችኋል። አብራችሁን ቆዩ! https://www.youtube.com/channel/UClsth2dZRGxrtati4MB00Gw/
Hammasini ko'rsatish...
ዓለም ምድር ሰማይ ሰማይ ኮከብ ፀሐይ ፀሐይ ጀንበር ንጋት ንጋት ብርታት ስጋት ስጋት ያንቺ ፍቅር ኤድያ! ሰው መሆን ይቅር! (ስለዚ ልመለስ) ፍቅር ያንቺ ስጋት ስጋት ብርታት ንጋት ንጋት ጀንበር ጸሐይ ጸሐይ ኮከብ ሰማይ ሰማይ ምድር ዓለም (በዘላለምሽ ውስጥ) ያንቺ እንጂ የኔ ቀን የለም። ✍️ ዳዊት
Hammasini ko'rsatish...
(እግረ መንገድ) ሰምተሽ ካለምሻቸው የፍቅር ክስተቶች እመኚኝ ያምራሉ የኔና አንቺ ነብሶች የዚች ህይወት 'ሚሏት ምናምንቴ ነገር ባይገባኝም ልኳ ጉድፍ መሳይ ጸዳል በጠገበው መልኳ አንቺን ቀብቷት ነው የካሳት አምላኳ ብዬ ስቀባጥር ብዬ ስቀባጥር በናፍቆት ብርንዶስ በትዝታ ናርዶስ በሐሳብ ሰባሰገል ተሰበርኩ እንደገል ልሰበር ልቀንጠስ የምትመጪበትን ቀንሽን ልነቀስ "ፍቅር ይበልጣል" የሚል የጴጥሮስን ቃል ከመጽሐፌ ልጥቀስ ቀስ ቀስ ቀስ ልፋለም ከሳቅሽ ስጪኝ ትንሽ ከንፈር አፈሬን ነይ ባርኪው መልሽኝ ወደ አፈር እሰይ እሰይ እሰይ ወደዘላለሜ ዘላለም ቶሎ ነይ። ✍️ ዳዊት
Hammasini ko'rsatish...
ሰባት የቃል እሳት በልቶት ያንቺን ናፍቆት፤ በመቅረዝ ልቤ ላይ የለም ሰይጣን ሰርቆት። (ይኸዋ ረክሼ) ለሰባት ጠንቋይ ልጅ ለደብተራ ውላጅ፤ ይዤ ስመላለስ የጨርቅሽን ጉማጅ፤ (ይኸው እድሜ ላንቺ) አንቺን ለመሳለም መናፍስት አብረው፤ ምን ይባላል እቴ አስፈቅራት ብዬ ግብር የጣልኩለት አፍቅሮሽ ባገኘው? (እድሜ ለጠረንሽ) ወዛም ቀጫም ወንዱን ለሚያንበረክከው፤ እንዳትገረሚ ረቢዬን ክጄ ገጽሽን ባመልከው፨ ✍️ ዳዊት
Hammasini ko'rsatish...
ነ - ፃ - ነ - ት ትልሜ ..... የትላንት የዛሬ የነገዬ በመኖሬ ጥግ ሰማይ አድማሴ ምት'ወጪ ምትታዪ ለኔ ብቻ ለህልም ፍችዬ ተስፋ መቀነቻ ልቤ ላይ ተስለሽ የቀረሽ ከደረቴ ላይ ያዋልኩሽ እንደ ድርሳነ ዑራኤል ማንገቻ ይኸው ከኔ ላንቺ ብቻ...... (ከዚያ ከነጠላሽ)....... 'ራሴን ከጠመጠምኩበት ወዝሽ ከወዜ ከተዋሀደበት እርሱ ላይ ነው በደሜ አቅልሜ ከነፃነት ሞት ድግስ ተሰይሜ በጣር ቃላት ተራቅቄ ተቀኝቼ አድምቄ ከተብኩሽ በትኩስ ደሜ ከመቃብር አፋፍ ላይ ቆሜ ነው ምፅፈው ላንቺ አለሜ! (ይህን ስልሽ).......... ማቅ ለብሰሽ አመድ ነስንሰሽ ወድቀሽ ፤ አዝነሽ አልቅሰሽ ፤ አንብተሽ በናፍቆት ሲቃ ስቅቅ ብለሽ ደረት እየደቃሽ ከሰውነት ወርደሽ በዋይታ ሰቀቀን እንባ ሲያንቅሽ ኩርትም፤ ኩስስ ልጉም፤ ዝም፤ ድርግም ብለሽ እንባሽ አልቆ ደም ካነባሽ አጥንቴ ይፋረድሽ ላንቺ የከሰከስኩት ደሜ ጣርሽን ያብዛው ላንቺ ያፈሰስኩት አፅሜ እሾህ ሆኖ ይውጋሽ ላንቺ የሰበርኩት ስሚኝ አለሜ ለደስታሽ ነው መውደቄ በሰላም ለመኖርሽ ነው እኔ መድቀቄ ለመተንፈስሽ ነው ማለቄ ተራራ ተደግፌ ከአፈር መደበቄ ለክብርሽ ለክብሬ ለእምነት ማህተቤ ለሐገሬ ለነፃነት ስል ነው ዘገር መነቅነቄ ለሞት መዋከቤ እመ አምላክን ! ወላዲቷን ነው የምልሽ ! ሚሽቴን ሐገሬን ለሚነሳኝ ዕርስት ሀብቴን ለሚቀማኝ እንዴት አስችሎኝ ሲገዛኝ በባርነት ለጉሞ ሲጋልበኝ ይኼ እኮ ነው ....... ሰይፌን አስወልውሎ ጋሻ ያስጨበጠኝ ጦር አስነቅንቆ ሽምጥ ያስጋለበኝ በዕለተ ጊዮርጊስ በአድዋ ሰማይ በአድዋ ጉያ በሰፊው ሜዳ ላይ ምድር ምድጃ ሆና የአድዋን ተራራ ጉልቻ ሰርታ ንግስት ፊት መርታ ፋሽስቱን ጥቁር ብረት ምጣድ ላይ እያገላበጠ ሲቆላ ከታች ወደላይ እቴጌ ታጥቀው ሲያስተናብሩ ዋሉ አደግድገው ወዲህ ና ተመለስ እያሉ ንጉስ ከጠሩት የጦር ድግስ እኔም መገኜቴ ከአደዋ ዳስ ብሩህ ነገን ለማየት ነፃነትን ለመቅመስ እንጂማ ...... እንጂማ.... ለመሞት አይደለም ለመላቀስ ከፋሽስት ጋር የምዳቆስ ሐገር ሚሽቴን ለማኖር ነው ደረቴን ለጥይት የምሰጠው እንቢ ....እንቢ.... እንቢ... የምለው.................... አታልቅሺ .........አታልቅሺ ብያለው ትልሜ .......የትላንት የዛሬ የነገዬ በመኖሬ ጥግ ሰማይ አድማሴ ምት'ወጪ የምትታዪ ለኔ ብቻ ለህልም ፍችዬ ተስፋ መቀነቻ ልቤ ላይ ተስለሽ የቀረሽ ከደረቴ ላይ ያዋልኩሽ እንደ ድርሳነ ዑራኤል ማንገቻ ይኸው ከኔ ላንቺ ብቻ! ያብራክ ክፋያችን ገና በማህፀን ያለውን ወንድ ይሁን ሴት አምላክ ብቻ የሚያውቀውን ማን ብለሽ ሰየምሽው ?? ብዬ የምጠይቀው ላፍታ አንተ ምን አልክ ? ካልሺኝ ? አባቱን እኔን ከጠየቅሽኝ በጣር ድምፅ በደከመው በጣቱ የሞት በርን ከሚያንኳኳው ለማቆም ሲል ከወደቀው ለማኖር ሲል ከሚሞተው ከአንቺው ባል ከእኔ መልስ በገዛ ደሜ አቅልሜ የምፅፈው ለልጄ ለአብራኬ ክፋይ የማወርሰው እየሞትኩ ለሚኖረው የምሰጠው ያወጣውለትን ስም ነፃነትን ነው ። ነ-ፃ-ነ-ት የሟች ስያሜ የፅንስ መጠሪያ የእንቡጥ አበባ ማበቢያ ለሐላፊው የደም ዋጋ ክፍያ . . . . . . . . . . . . በኤልያስ ሽመልስ ከምሽቱ ፦ 12:25 - 4:00 ዘ የካቲት 11/06/2014 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#መቅረት_አይታሰብም!💪 #አቢላማ (ጊዜ) 📆 መጋቢት 11 📍 ናዝሬት ማሜ ሆቴል 🕰 ዘጠኝ ሰአት
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.