cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ቤተ ክርስቲያናችን እንወቅ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
174
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው:: ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአሔር ይገሥጽህ!" አለው:: (ይሁ 1:9) እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ? መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም:: የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌላው ሲሾም አዲሱ ተሿሚ ስለወደቀው ምን እንደሚል እናውቃለን:: አንደበቱ ስድብ በመናገር ያልረከሰው ቅዱስ ሚካኤል ግን ወድቆ በማያርፈው ዲያቢሎስ ላይ የስድብን ቃል አልተናገረም:: @Afe_Werk
Hammasini ko'rsatish...
🌺 አንተ ሰው !!! 🌺 📝 ቃለ እግዚአብሔርን ተማር ! ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር ! ኹልጊዜ ተማር ! ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር! ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፡፡ ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡ ይህች #የንስሐ_በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ #ንስሐ ትመራሃለች !!! #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ .....🙏🙏 ለተጨማሪ 👇 🇨🇬👉 @Afe_Werk ላይ ይቀላቀሉን።
Hammasini ko'rsatish...
ክፍል ፪፦ 📚.በኪሩቤልና በሱራፌል እጅ የተሠሩ በ፱ ሺ፮፻ ከፊ(B.C) 📖.በኪሩቤል እና በሱራፌል እጅ የተሰሩ የፒራሚድ ከተሞች ደግሞ ከዞብል ራማ ሐዳር፣በአሰብ አፋር እስከ ጅቡቲ ድረስ የሚገኙ ሲሆንቁጥራቸውም ፫ት ናቸው ። የእነዚህ ፒራሚዶች ሥራ ቅጥልጥል የሌለባቸው አንድ ወጥ የሆነ ዕብነ በረድ የሚመስል ሲሆን በጣም ሰፋፊ ናቸው ። ቀለማቸውም የወይን ጠጅ ፣ ውሃ ሰማያዊ ፣ ጥቁር ሲሆኑ በኪሩቤልና ሱራፌል የሚታዘዙ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ነገደ መላእክት በገዛ ኃይላቸው እንዳይቃጠሉ የመሬት ስበት የሚያገኙባቸው ከተሞች ናቸው ። ለምን ድንጋይ አስፈለጋቸው የሚል ሰው ቢኖር መላእክት ተፈጥሯቸው ከእሳትና ከነፋስ ነው ። እንደ ሌላው ፍጥረት ሁሉ የመሬት ስበት ያስፈልጋቸዋል ። ይህ ባይሆን ግን በገዛ ኃይላቸው ይቃጠላሉ ። ስለዚህ ለዘለዓለም መኖር እንዲችሉ ስበት ያስፈልጋቸዋል ፤ ማለትም ቅዱሳን የሆኑ መናፍስትና መላእክት ወደ ተቀደሰ ሰውና ሥፍራከፍተኛ ፍጥነት ወርደው በዚህ ዓለም የሚገኙ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሁም ክፋትና ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች በመጐብኘት ከፍተኛ የሆነ የድጋፍ ኃይል ያገኛሉ ። ለቦታውና ለሰውም የበለጠ ቅድስና ይሰጠታል ፤ በአንፃሩ ደግሞ ርኩሳን የሆኑ መናፍስትና ኃይላትም ወደዚህ ዓለም ወርደው የረከሰ ሥፍራና የረከሱ ሰዎችን በመገናኘትኃይላቸውን ያድሳሉ ። 📚.የረከሱ ሰዎችና የረከሰ ሥፍራ ማለትም ያለማቋረጥ አመጽና ግድያን የሚፈጽሙ በውሸት ሰውን የሚያጣሉና የሚያጋድሉ ሲሆኑ የረከሰ ሥፍራም ፳፬ ሰዓት ሙሉ ጭፈራና ዝሙት የሚፈጸምበት ወይም ዳንስ ቤት ነው ። መናፍስት ርኩሳኑም ለረከሱ ሰዎችና ለረከሰ ሥፍራ በፊት ከነበራቸው በይበልጥ የባሰና የከፋ ርክስናን ይሰጧቸዋል ማለት ነው ይላል መጽሐፈ ምስጢር ። ✡.ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አማን። @Ethiopia7980 @Ethiopia7980 @Ethiopia7980
Hammasini ko'rsatish...
✥እንኳን፡ለብርሃነ፡መሥቀሉ፡በሠላም፡በጤና፡አደረሣችሁ።✥ ✥የመስቀሉ፡ቃል፡ለሚጠፉት፡ሞኝነት፥ለእኛ፡ለምንድን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ኀይል፡ነውና።✥ ፩ኛ ቆሮንጦስ ፩÷፲፰ ✥ ✥ ✥ ✥✥✥✥✥✥ ✥ ✥ ✥ ✥መልካም በዓል✥ https://t.me/tmhrteorthodox
Hammasini ko'rsatish...
🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox

🤔😳እናንተ ኦርቶዶክሶች? እንኳን ለጌታችን የዕርገት በዐል በሰላም አደረሳችሁ ይህን መልክት ❗‼‼‼📨 •➢#ሼር // SHARE •➢#ሼር // SHARE •➢#ሼር // SHARE 🤔😳እናንተ ኦርቶዶክሶች ግን ቆይ እርሱን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት አርጋችሁ እንደው ምን ብላችሁ ነው ምታመልኩት 😊እኛማኢየሱስ ክርስቶስን እንዲህ እናምናለን እንታመንማለን 👉እርሱ የአለም ብርሀን ነው ዮሐ ፰፡፲፪ 👉እርሱ ሕይወታችን እውነታችንና መንገዳችን ነው ዮሐ ፲፬፡፮ 👉እርሱ ሰላማችን ነው ዮሐ ፲፬፡፳፯ 👉እርሱ ትንሳኤያችን ነው ዮሐ ፲፩፡፳፭ 👉እርሱ የህወታችን ውሀ ነው ዮሐ ፯፡፴፯ 👉እርሱ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራችን ነው ዮሐ ፮፡፶፩ 👉እርሱ የጽድቅ በራችን ነው ዮሐ ፲፩፡፱ 👉እርሱ ቸር እረኛችን ነው ዮሐ ፲፡፲፩ 👉እርሱ የወይን ግንድ ነው ዮሐ ፲፭፡፭ 👉እርሱ የጌቶች ጌታ የንጉሶችም ንጉሥ ነው ራዕይ ፲፯፡፲፬ 👉እርሱ የአብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ ነው ሉቃ ፳፡፴፯ 👉እርሱ እረፍታችን ነው ማቴ ፲፩፡፳፰ 👉እርሱ ፍቅር ነው ፩ዮሐ ፬፡፰-- 👉እርሱ የዋህ ነው ማቴ ፲፩፡፳፱ 👉እርሱ ትሁት ነው ማቴ ፲፩፡፳፱ 👉እርሱ የዓለምን ሀጢዓት ያስወገደ በግ ነው ዮሐ ፩፡፳፱ 👉እርሱ የእኛ የበጎቹ በር ነው ዮሐ ፲፡፯ 👉እርሱ ህማማችንን የተሸከመ አምላክ ነው ኢሳ ፶፫፡፭ 👉እርሱ ስለብዙዎች ኃጢአት የተሰዋው ፍሪዳ ነው፤እርሱ መሥዋዕትን የሚያቀርብ፤መሥዋዕት ተቀባይም ነው ዕብ ፫፡፩ 👉እርሱ ስለኛ መከራን የተቀበለ ስለኛም የራራልን ነው ፩ጴጥ ፬፡፩-፪ 👉እርሱ ሙሽራ ነው፤እርሱ ራሱ ሙሽሪትም ነው ሉቃ ፭፡፴፬ 👉እርሱ የሰርጉ ቤት ነው፤እርሱ ራሱ የሰርግ ቤቱ አሳላፊ ነው ማቴ ፱፡፲፭ 👉እርሱ ገነት ነው፤እርሱ ራሱ የሕይወት ዛፍ ነው ራዕ ፲፪፡፲፬ 👉እርሱ ሰማያዊ ኢየሩሳሌም ነው፤እርሱ ራሱ መቅደሳችንና ቅድስተ ቅዱሳናችን ነው 👉እርሱ ምግባችን ነው፤እርሱ ራሱ የሚመግበን መጋቢያችን ነው 👉እርሱ ሕያው የሆነ ህብስት ነው፤እርሱ ራሱ የደስታ ወይናችን ነው 👉እርሱ ዕንቋችን ነው፤እርሱ ራሱ መዛግብታችን ነው 👉እርሱ የጦር መሣሪያችን ነው፤እርሱ ራሱ ድል የሚነሣ ነው 👉እርሱ የቅዱሳን ህብረት ለሆነችው ቤተክርስቲያን ራስ ነው፤እርሱ መልካም የስንዴ ቅንጣት ነው 👉እርሱ የወይን እርሻችን ነው፤እርሱ ራሱ የእርሻው ባለቤት ነው 👉እርሱ ግርማችን ነው፤እርሱ እምነታችን ነው 👉እርሱ ሰርጋችን ነው፤እርሱ ራሱ የሰርግ ልብሳችን ነው 👉እርሱ የሕይወት መንገዳችን ነው፤እርሱ ራሱ በራችን ነው 👉እርሱ የጽድቅ ፀሐያችን ነው፤እርሱ ራሱ የነፍሳችን ብርሃን ነው 👉እርሱ ሞታችንን በሞቱ የገደለ ንጹህና ሀያል አምላክ ነው 👉እርሱ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋና ኦሜጋ ነው 📖ኧረ እርሱ እግዚአብሔር ነው! ምንተብሎ በየትኛው ቃል ይገላጻል?እርሱ ሁሉ ነገራችን ነው!እንደ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ትምህርት ከሄድን ገና ስለክርስቶስ ጫፉንም አልገለጽኩም!ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያናችን ከምታስተምረው ገና አንዱንም ገጽ ሙሉ አልገለጽኩም! አንዳንድምስኪኖች እኛ ሮሜ ፰፡፴፬ን ዮሐ ፲፬፡፮ን ዕብ ፯፡፳፬ን ፩ጢሞ ፪፡፭ን....ማንቀበልናማናምን ይመስላቸዋል!እኛ ከትርጉማቸው እንጂ ከቃሉ ችግር የለብንም!ኦርቶዶክስ የሆነ ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማያምነው ቃል የለም!እኛ መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው የምናምነውን ለመፈለግ ሳይሆን የምናነበውን ለማመን ነው!ስለዚህ ከየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጋር የምስኪኖች አተረጓጎም እንጂ ቃሉ አያጣላንም! ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE t.me/sratebetkrstyane
Hammasini ko'rsatish...
✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️

እንኳን ወደዚህ ቻናል በሰላም መጡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት ደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ። share share share

🕊 🍒 🕊 የማይጠገበው የአባቶቻችን የቅዱሳን ትምህርትና ምክር ! በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ [ ፍኖተ ሕይወት - ፸፮ - ] [ መጀመር ሳይኾን .......... ] 🍒 " ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እምነት በተናገረበት አንቀጽ በዘመነ ብሉይ የነበሩትን ጻድቃን አበው ይዘረዝርልናል [ዕብ.፲፩]፡፡ እነዚህ አበው ጻድቃን ምንም እንኳን በሚኖሩባት ምድር ቤት ሠርተው ፣ ቤተ ሰብ መሥርተው ሲኖሩ የነበሩ ቢኾኑም ራሳቸውን በምድሪቱ ላይ እንግዶችና መጻተኞች እንደ ኾኑ ይቆጥሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ ልበ አምላክ ዳዊትን ብንመለከት ምንም እንኳን ንጉሥ ቢኾንም ፣ ምንም እንኳን ነቢይ ቢኾንም ፣ ምንም እንኳን መላ ዘመኑን በምርኮ ሳይኾን በገዛ ሀገሩ በእስራኤል የኖረ ቢኾንም "እኔ በምድር መጻተኛ ነኝ ፤ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ" ይል ነበር (መዝ.፴፱፥፲፪) " መጻተኛና እንግዳ መኾናቸው በምንድን ነው? " የሚል ጥያቄ ይከተል ዘንድ አግባብ ነው፡፡ ክቡር ዳዊት "መጻተኛና እንግዳ ነኝ" ሲል "በእርግጥ ሀገር (እስራኤል) አለች ፤ ነገር ግን እውነተኛይቱ ሀገራችን ይህቺ ምድራዊቷ እስራኤል አይደለችም፡፡" ማለቱ ነበር፡፡ ስለዚህ ዳዊት ብቻ ሳይሆን እኛም በዚህች ምድር እንግዶችና መጻተኞች ነን ማለት ነው፡፡ "እንደ አባቶቼ እንግዳ ነኝ፡፡" እንዲል፡፡ እንኪያስ "እግዚአብሔር አምላካችን" ተብሎ መጠራትን እንዳያፍርብን በዚህች ምድር እንደ አባቶቻችን እንግዶችና መጻተኞች ኾነን ልንኖር ይገባናል፡፡ በክፉዎች ስም መጠራት ለእግዚአብሔር ሐፍረት ነውና ፥ በበጎዎች ስም መጠራትንም ክብሩ ነውና አባታችን እንዳያፍርብን እንግዶችና መጻተኞች ኾነን ልንኖር ይገባናል፡፡ እንኳንስ ልዑል እግዚአብሔር ይቅርና ፍጡራን የምንኾን እኛም በክፉዎች ሠራተኞቻችን ስም መጠራትን የምናፍር ነን፡፡ አንድ ሰው መጥቶ "እገሌ የተባለ ሰው እጅግ ብዙ ክፉ ሥራ ሠራ ፤ የአንተ ሠራተኛ ነውን?" ብሎ ቢጠይቀን ፈጥነን "ኧረ በፍጹም!" ብለን ራሳችንን ከሐፍረት ለማራቅ የምንሞክር አይደለምን? ይህስ የሠራተኛው ክብር ከአሠሪው ክብር ጋር ፣ የሠራተኛው ክፉ ሥራም ከአሠሪው ሐፍረት ጋር እንደሚያያዝ የሚያስረዳ አይደለምን?" [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ] 🕊 🍒 🕊
Hammasini ko'rsatish...
#የክህነት_አመሰራረት ክህነት የተጀመረ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው:: እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ፈጥሮ በልጅነቱ አክብሮ ነቢይ ካህን አድርጎ ስለሾመው በኦሪት በወንጌል ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከተ አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን÷ ክህነትን ከቅዱስ መንፈሱ እየተቀበሉ (እየተሾሙ)÷ በነቢይነታቸው ያለፈውን የሚመጣውን ሲገልጡ ሲያስተምሩ÷ በክህነታቸው መሥዋዕት ሲያቀርቡ÷ በፀሎታቸው አምላካቸውን ሲጠሩና ቃል በቃል ሲነጋገሩ ኖረዋል:: አዳም ከገነት በወጣ በማግስቱ በሠራው ኃጢአት ተጸጽቶ እያዘነና እያለቀሰ ቸርነት ምህረት የባሕርዩ ከሆነው አምላክ ምህረት ለመጠየቅ የመዓዛ መሥዋዕት አቀረበ:: #ምሥጢረ_ክህነት ምሥጢረ ክህነት ከፍ ያለ ምስጢር ነው:: የማሠር የመፍታት ሥልጣን ያለው ሌሎችንም የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ለመቀደስ ለማክበር ለመፈጸም ችሎታ ያለው ክርስቶስ የመሠረተው የሠራው ከእርሱም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያለማቋረጥ የሚሰጥ ጸጋ ነው:: ይህንንም ሥልጣን ክርስቶስ ለሐዋርያት በንፍሐት በአንብሮተ እድ ሰጥቶዋቸዋል (ዮሐ 20÷21-23 / ሉቃ 24÷50):: ሐዋርያትም ለተከታዮቻቸው በአንብሮተ እድ እያስተላለፉ እስከ ዛሬ ደርሰዋል:: (ማስረጃ የሐዋርያት ስራ 6÷3-7 /ሐዋ 14-23/ 1ኛ ጢሞቲዎስ 4÷14/ 1ኛ ጢሞ 1÷7/ ቲቶ1-3) እስከ ምጽአትም እንዲሁ ያለማቋረጥ እንደሚሰጥ የተረጋገጠ ነው:: ለምሥጢረ ክህነት የሚታይ አገልግሎት የማይታይ ሀብት አለው:: የሚታየው አገልግልት ጳጳሱ በአንብሮተ እድ ሲሾም የተለየ ጸሎት ሲጸለይ ክህነት የሚቀበለውም በሰቂለ ሕሊና በሰፊሐ እድ በእንቃዕድም አዕይንት በአድንኖ በተመስጦ ሲጸልይ ይታያል:: ይህ የሚታይ አገልግሎት ይባላል:: ሆኖም ስልጣነ ክህነት ጸጋ ሀብት የማሠር የመፍታት የማንጻትና የማጽናት የማዳን ስልጣን ሲሰጥ አይታይም:: ይህ የማይታይ ሀብት ይባላል:: ክህነት ለሁሉ አይሰጥም በምእመናን ለተመረጡ ሰውች ብቻ ነው:: ሢመተ ክህነተ አይደገምም በየደረጃው አንድ ጊዜ ብቻ ነው:: ሹመቱ የሚሰጠው ከፈረሰ ይቀራል አይታደስም አይጠገንም:: #ይቀጥላል.......... ቻናላችንን_ለመቀላቀል_ከዚህ–በታች_ያለውን_ሊንክ_በመንካት_Join_ይበሉት:: 👇 👇 👇 @betkrstiyanachinenwek @betkrstiyanachinenwek @betkrstiyanachinenwek
Hammasini ko'rsatish...
📖ኦሪት ዘፍጥረት 2፥4-7📖 ⛔ከዚህ በኋላ ያለው የጸሐፊው(ነቢዩ ሙሴ) ሙሉ ትኩረት ወደ ሰው ልጅ ያደርጋል ይተነትናል❗ 4.“እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት(ትውልድ) ይህ ነው።” #የሰማይና_የምድር_ልደት : - እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ባከናወነ በፈጠረ ጊዜ ካለ በኋላ ተመልሶ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው የሚለው ስለሌላ እንጂ በቁሙ ስለ ሰማይና ምድር ልደት እንዳልሆነ እናስተውል!! ምክንያቱም ስለሰማይ ልደት በምዕራፍ አንድ ከጠቀሰው ጋር የሚመሳሰል ምንም አይተነትንም ስለምድርም ልደት ቢሆን ምንም አይገልፅም። በሰማይና(ፀሐይ፡ጨረቃ፡ከዋክብት ወዘተ) በምድር(እንስሳት፡ዕፅዋት፡ ወዘተ) ተፈጠሩ ያለውን ፍጥረታት ትውልድ በመጀመርያው ምዕራፍ ስለገለጠው አሁን መድገምም አያስፈልገውም። የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው የሚለን ስለማን ነው ካልን ግን ስለ ሰው ነው። ከፍጥረታት ከሰማይም ከምድርም ባሕርይ የሚካፈል ከሰው ልጅ በቀር ማንንም አናገኝም።የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መልክ መፈጠሩ(ነፍሱ) ሰማያዊ፤ ከምድር በሆነው ግዙፍ አካሉ(ስጋው) ደግሞ ምድራዊ ነው።ስለዚህ ከሰማይና ከምድር የሆነ ባሕርይ ስላለው ብቸኛው ፍጡር ሊያብራራ ርእሱ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው አለ።ምክንያቱም በምዕራፍ1፥27 ሰው በእግዚአብሔር መልክ መፈጠሩና ወንድና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው እንጂ እንዴት እንደነበረ አፈጣጠራቸው አልገለፀም ነበር።አሁን ግን ገና ከጅምሩ ይህን ሊተነትን ነው። 5.“የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም ነበር፣ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤” ቅዱስ ኤፍሬም ይህንን ሲያብራራው “በምድር የሚፈጠረው ሁሉ ከውሃና ከአፈር ጥምረት ነው ሙሴም ሊያሳይ የፈለገው ይህንን ነው የሜዳ ቁጥቋጦና ቡቃያ አልበቀሉም ምክንያቱም እግዚአብሔር ገና ስላላዘነበ። ”ይላል። ለሰው ልጅ ምግብ ይሆኑ ዘንድ አትክልት ሳይፈጠሩ ምድርን ያርሳትና ያለማት ዘንድ ሰውም ገና አልተፈጠረም ነበር። 6.“ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር።” 🌫ጉም ከምድር ወጥታ የብሱን ሁሉ አጠጣችው አረሰረሰችው ስለዚህ አትክልቱ በዋናነት ደግሞ የሰው ልጅ ይፈጠሩባት ዘንድ ዝግጁ ሆነች።አትክልቱ እንዴት እንደተፈጠሩ በምዕራፍ1 ስለገለጠው እዚህ ላይ አይደግመውም ዋና ትኩረቱ የሰው ልጅ አፈጣጠር ላይ ነውና። 7.“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።” #ከምድር_አፈር_አበጀው : - አፈር ሲል ደረቅ አፈር ላለመሆኑ ጉም ምድሪቱን እንዳረጠበቻት ነግሮናል ስለዚህ የሰው ልጅ ግዙፉ አካል(ስጋ) ከጭቃ እንደተሰራ እንረዳለን። “እኛ #ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።”— ኢሳይያስ 64፥8 “እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ እኔ ደግሞ #ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ።”— ኢዮብ 33፥6 በምዕራፍ1 እንዳየነው ሰው በዚህ ተፈጥሮው ባሉት ስጋዊ(ምድራዊ) ባሕርያት እንስሳትን ይመስላል። #ሰውም_ሕያው_ነፍስ_ያለው_ሆነ :- ሕያዋን ፣ሕያው ነፍስ ያላቸው ብሎ በምዕራፍ 1 ለእንስሳት ከተጠቀመበት አገላለፅ ፍፁም የተለየ ነው። ምክንያቱም የእንስሳቱ ተፈጥሮ “ታስገኝ፥ታውጣ” ብሎ ምድርን በቃሉ በማዘዝ ብቻ ነው የተፈጠሩት በዚህም ሕይወታቸው ከምድር ነው ደማዊ ነፍስ ነው ያላቸው ማለትም ነፍሳቸው ደማቸው ነው። ደማቸው ከፈሰሰ ወይም በሌላ ምክንያት ከሞቱ ደግሞ በቃ ሞቱ ነው።ሰው ግን ከእግዚአብሔር ባሕርይ የተከፈለች የእግዚአብሔር መልክ ሰማያዊነት ተሰጠችው። ይህችም #ነፍስ ነች።እንደ እንስሳቱ አካሉ ከምድር በተሰራ ጊዜ ሕያው አልሆነም ሰማያዊ ማንነት የእግዚአብሔር መልክ ባሕርይ በተካፈለ ጊዜ እንጂ።እግዚአብሔር ዘለአለማዊና ሕያው እንደሆነ የሰው ልጅም እንደ እንስሳት ሞቶ የማይቀር ሕያው ነው ነፍሱ አትሞትም ስጋውም ሕይወት የሚኖራት ከነፍሱ የተነሳ ነው። 📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎 “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።”— መዝሙር 139፥14 📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.