cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Addis News

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
461
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
-230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
♦ ከግፍ እስር ተፈቷል! ከበርካታ ወራት የግፍ እስራት በኋላ በላይ በቀለ ወያ ከእስር ተፈቷል!
Hammasini ko'rsatish...
🔴🔴🔴 ፋኖ በከባድ መሳሪያ ታጅቦ በአራት አቅጣጫ የመጣውን የብልፅግና ጦር መጨረሱን ይፋ አደረገ። በደቡብ ጎንደር በአምስት ግንባሮች እየተደረገ በሚገኘው ከባድ ውጊያ ፋኖ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን አስታውቋል። በደብረታቦር ማህደረ ማርያም ፣ በጭስ አባይ ፣ በአንዳቤቴ ፣ በእስቴና በደራ ዓርብ ገበያ ልጫ ግንባሮች እየተደረገ በሚገኘው ውጊያ ነው ድል ማስመዝገባቸውን የተናገሩት። ከፍተኛ ቀጠና ሸፍኗል በተባለው ውጊያ የብልፅግናው መንግስት የመጨረሻውን ከፍተኛ ሃይል ይዞ ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል። በጎንደርና በጎጃም ፋኖዎች ጥምረት እየተደረገ የሚገኘውን ውጊያ መቋቋም ያቃተው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ከባህር ዳር ከፍተኛ ሃይል በ16 ወታደራዊ መኪና ጭኖ እያንቀሳቀሰ መሆኑን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። 🔴🔴🔴 በባህር ዳር ዙሪያ ዘንዘልማ ከተማ ውጊያ ተካሂዶ እንደነበርም ተነግሯል። ለሰባት ሰዓት ተደርጓል በተባለው ውጊያ ከ10 በላይ የብልፅግናው መንግስት ወታደሮች መገደላቸው ሲነገር 4ቱ መቁሰላቸውና 10 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በፋኖዎች መማረካቸው ተገልፃል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘንዘልማ ካምፓስ ድረስ ተኩሱ ይሰማ ነበር ያሉት ምንጮቻችን ውጊያው ከእኩለ ቀን በኋላ ረገብ ማለቱን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ በአካባቢው አሁንም ድረስ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ ተነግሯል። በተመሳሳይ በጎጃም ጎዛመን ወረዳ የቦቅላ የሚደረገው ውጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ተነግሯል። ከአምስት ወራት በላይ ፋኖዎችን ቀልባችኋል የተባሉ የኩብራ ከተማ ነዋሪዎች መገደላቸው የገለፁት ምንጮቻችን በአማኑኤል ቤተክርስቲያን መሽጎ የሚገኘው የብልፅግና ጦር ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ንፁሃን እየጨፈጨፈ መሆኑ ተነግሯል። በወረዳው ቀኝ አቦ በተባለው ቦታም ከባድ ውጊያ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልፃል። ውጊያ እንደከዚህ ቀደሙ የደፈጣ ሳይሆን የእጅ በእጅና የጨበጣም ነው ብለዋል። ሞገሴ ሽፈራው
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 129.7 ሚሊዮን መድረሱን አስታወቀ ኢትዮጵያ የሚገኘው የተመድ የሥነ ሕዝብ ፈንድ ድርጅት እ.ኤ.አ. የ2024 የኢትዮጵያን የሥነ ሕዝብ ሪፖርት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተመድና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተገኙበት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቋጥር ዘንድሮ 129.7 ሚሊዮን መድረሱንና ቁጥሩም በ28 ዓመት ውስጥ ራሱን እጥፍ እንደሚያደርግ አመልክቷል። ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከ0 እስከ 14 ዕድሜ 39 በመቶ፣ ከ10 እስከ 19 ዕድሜ 23 በመቶ፣ ከ10 እስከ 24 ዕድሜ 32 በመቶ፣ እንዲሁም ከ15 እስከ 64 ዕድሜ ክልል 55 በመቶ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ዓመታዊ ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ ከአገሪቱ ሕዝብ ሦስት በመቶው 65 እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ዜጎች ሲሆኑ፣ የአገሪቱ የውልደት መጠን 3.9 በመቶ እና የመኖሪያ ዕድሜ ጣሪያ ወንዶች 64 እንዲሁም ሴቶች 70 መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
🔴🔴🔴 ሰኔ 2/2016 ዓ.ም 1) የደፈጣ ጥቃቶች 1.1) ጎንደር ዙሪያ ድንዛዝ በተባለ ቦታ  በመንግሥት ኃይሎች ላይ በተፈጸመ ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደረሰ። 1.2) አሰቃቂ ዕልቂት ያደረሰ የተባለው የደፈጣ ጥቃት የተፈጸመው በደቡብ ወሎ ዞን  መካነ ሠላም  ከተማ አቅራቢያ መነዩ ማርያም በተባለ ቦታ ነው። በዚህ ጥቃት  ቁጥራቸው ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ የመንግሥት ኃይሎች ሳይጎዱ አይቀርም የሚሉት ምንጮች ሦስት ወታደራዊ  ኮንቮይዎች ሲወድሙ አንዱ ደግሞ ገደል ገብቷል ብለዋል። ይህን የመሰለ እልቂት አላየንም የሚሉት የዓይን እማኞች አስክሬን የማንሳቱ ሥራ እንደቀጠለ ነው ብለዋል። 1.3) ከወልዲያ ከተማ በቅርብ እርቀት በሚገኙ ሦስት ቦታዎች የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሟል። ጋ×ላ ጊዎርጊስ እዜት በር ወጠጥ በተባሉ አካባቢዎች የተፈጸመው ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት አድርሷል። 🔴በ መርሃ ቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ አልማዝ ሜዳ ሞያ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሁም አዲሱ ገበያ በተባሉ ሁለት ቦታዎች በሌሊት በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት የሚሊሺያ አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። 🔴የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ከተፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት አመለጡ! Belete Kasse
Hammasini ko'rsatish...
🔴🔴🔴ዜናዎች 🔴የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ከተዳከመ የዋጋ ንረት እንደሚባባስና የነዳጅና ማዳበሪያ ዋጋ እንደሚጨምር ማስጠንቀቁን ከአንድ የድርጅቱ ሰነድ ላይ መመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል። መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች በአስመጭነትና ላኪነት እና በችርቻሮና ጅምላ ንግድ እንዲሳተፉ የፈቀደው፣ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት ሲል ሊኾን እንደሚችል ሰነዱ ማመልከቱን ዘገባው ጠቅሷል። ኹለቱ ተቋማት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም እንደሚፈልጉና የእስካኹኑን የዋጋ ንረት ከአለመረጋጋትና ከዓለማቀፍ የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ጋር እንደሚያያይዙት ሰነዱ ያብራራል ተብሏል። ብሄራዊ ባንክ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ማብቂያ የመደበኛውንና የጥቁር ገበያውን የምንዛሬ ልዩነት ልዩነት ለማጥበብና ለ7 ወራት የሚበቃውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ወደ አንድ ወር ለማሳደግ ማቀዱን ሰነዱ ይጠቅሳል ያለው ዘገባው፣ ባንኩ በቀጣዩ ዓመት ሰኔ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱን ወደ ኹለት ወር ለማሳደግ ማሰቡንም እንደጠቆመ አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ከእያንዳንዳቸው 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት። 🔴ባለፈው ረቡዕ ታጣቂዎች በኦሮሚያው ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ ዴይቸቨለ ዘግቧል። በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች መካከል፣ አንድ መምህር እንደሚገኝበት ዘገባው አመልክቷል። ጥቃቱን ያደረሱት፣ በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ እና በአጎራባቹ የምሥራቅ ወለጋ ዞኑ ኪረሙ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደኾኑ የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች መናገራቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል። በኡሙሩ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፈጽሟቸው ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከ40 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተፈናቅለውበት የነበረ አካባቢ ነው። 🔴የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ኩመር እና አውላላ ከተባሉ የተመድ የስደተኞች መጠለያዎች ለቀው የወጡ ሱዳናዊያን ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር እንቅስቃሴ እያደረኩ ነው ማለቱን ቪኦኤ ዘግቧል። የተቋሙ ሃላፊዎች፣ ሱዳናዊያኑን ስደተኞች በዞኑ ውስጥ ወደሚገኝ አፍጥጥ የተባለ ቦታ የማዛወሩ ሂደት እንደተጀመረ መግለጣቸውን እንደገለጡ ዘገባው አመልክቷል። ተቋሙ፣ በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ኹኔታ ለማሻሻል እየሠራ እንደኾነም ገልጧል ተብሏል። በሺዎች የሚቆጠሩት ስደተኞች ከመጠለያዎቹ አቅራቢያ መንገድ ዳር የከተሙት፣ ታጣቂዎች በመጠለያዎቹ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ስላደርሱ፣ ተደጋጋሚ እገታዎችን ስለፈጸሙና አገልግሎቶች በማሽቆልቆላቸው እንደኾነ መናገራቸውን የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን መግለጡ ይታወሳል። ስደተኞቹ በበኩላቸው፣ ተመድ በሦስተኛ አገር እንዲያሠፍራቸው ይፈልጋሉ ተብሏል። መንገድ ዳር የከተሙት ስደተኞች አኹንም የጥቃት ሰለባ እየኾኑ እንደሚገኙ መናገራቸውን ሮይተርስ ትናንት ዘግቦ ነበር። 🔴የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የመኖሪያ ቤት የአከራይና ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል። የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አከራዮችንና ተከራዮችን የውል ምዝገባ በኹሉም ክፍለ ከተሞች የጀመረው፣ የከተማዋ አስተዳደር ያወጣውን የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ነው። አዋጁ፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ ከሚወስነው የኪራይ ጣሪያ በላይ ኪራይ ከመጨመርና ተከራዮችን በግዳጅ ከማስወጣት የሚከለክል ነው። አስተዳደሩ አዋጁን ያወጣው፣ ተከራዮች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል እምነት እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል። 🔴ዓለም ባንክ፣ በአውሮፓዊያኑ 2023 የዓለም የወደቦች የብቃት መለኪያ ለሶማሊላንዱ በርበራ ወደብ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ወደቦች ቀዳሚውን ደረጃ ሰጥቶታል። በድርጅቱ የደረጃ ምደባ መሠረት፣ በርበራ የካርጎ መርከቦችን በማስተናገድ አቅሙ ከዓለም 348 ወደቦች 106ኛ ደረጃ አግኝቷል። ጅቡቲ ወደብ በዓለም 379ኛ ደረጃ የተሰጠው ሲኾን፣ የኬንያው ሞምባሳ ወደብ ደሞ 328ኛ ደረጃ አግኝቷል። የጅቡቲ መንግሥት፣ ለጅቡቲ ወደብ የተሰጠውን ደረጃ "አድሏዊ" በማለት ውድቅ አድርጎታል። ዓለም ባንክ፣ የዓለም ወደቦችን ለማወዳደር የተጠቀመው መስፈርት፣ ካርጎ ጫኝ መርከቦች ወደቦች ላይ ጭነታቸውን ለማራገፍ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
♦ በአልሞ ተኳሾች የአዲስ አበባ ወጣት መሰዋዕትነት !! የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የወጣቶች ደምና ሰቆቃ ፣ የእናቶችን ዋይታና ለቅሶ ያስተናገዱበት መቼም የማይረሳ ጥቁር ቀን ! የምርጫ 1997 ውጤት መሰረቁን ተከትሎ፣ ሰኔ 1/1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ ህዛባዊ እንቅስቃሴ እና ተቃውሞ ተካሂዶአል፡፡የምርጫው መሰረቅ ለመቃወም አደባባይ የወጡት ዜጎቻችን ላይ ፋሽስታዊ እርምጃ በአገዛዙ ስርዓት ጠባቂዎች አማካኝነት ተወስዶባቸዋል፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ ወታደራዊ ትጥቅ የታጠቁ ወታደሮች ፣አደባባይ ባዶ እጃቸውን በወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ በአልሞ ተኳሾች የተወሰደው እርምጃ የስርዓቱ ልኬለሽ አምባገነን ባህሪ ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ በወቅቱ የነበረው አስከፊ ጭፍጨፋ የአገዛዙ ስርዓት ዋና መሪ የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ፣ የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በሙሉ በአንድ ዕዝ ሰንሰለት ሥር ገብቶ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለእሳቸው እንደሆነ፣ በሬዲዮና በቴሌቭዥን መመሪያና አዋጅ ማስነገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ የእሳቸው እና የመንግስታቸውን ጥሪ የተቀበለው በልዩ ስሙ የአጋአዚ ጦር የሚባለው፣ በአዲስ አበባ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሰው ሕይወት ቀጠፈ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነፃነት ጠያቂዎች በአገዛዙ ሥርዓት አገልጋዮች አማካኝነት ወደተለያየ የማጎሪያ ስፍራ በመውሰድ በዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እንዲደርስባቸው አደረጉ ። ሰኔ 1 ቀን 1997 ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ፤ ሁሌም የማንረሰው ዛሬም ድርስ በሁላችን ህሊና የሚታወሰው ነው፡፡ በተለይ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ፊት ለፊት ግንባሯን በጥይት ተመታ የተገደለችው የ18 አመቷ ወጣት ሽብሬ ደሳለኝ፤ቀድሞ በተተኮሰ ጥይት የወደቀውን ወንድሙን አብረሃም ይልማ አስከሬን ታቅፎ ያለቅስ የነበረው በጥይት ተበሳስቶ የተገደለው የፈቃዱ ይልማ አሟሟት እንዴት ይረሳል ? የ14 አመቱ ነብዩ አለማየሁ ደብተሩን ይዞ ከትምህረት ቤት ሲመለስ አልሞ ተኳሽ በሆኑ ወታደሮች መገደሉ እና የወላጅ እናቱ የይድረሱልኝ እሮሮና ለቅሶ ዛሬም ድረስ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ የተቀመጠ ሐዘን ነው፡፡ ውድ ህይወታቸውን መሰዋዕትነት የከፈሉ ወገኖቻችንን መቼም አንረሳቸሁም ! ክብር ለሠኔ 1/1997 ዓ.ም.እና ለጥቅምት 22/1998 የአዲስ አበባ የነፃነት እና ዴሞክራሲ ሰማእታት 🙏 ይድነቃቸው ከበደ
Hammasini ko'rsatish...
🔴🔴🔴 ግንቦት 29/2016 ዓ.ም 1) ለሌሎች ኢትዮጵያውን ያልተፈቀደ  ለኦሮሞ ተወላጆች ብቻ የተፈቀደ ሆኗል። ይህን የሚሉት የመረጃ ምንጮች ባለፉት አስር ወራት ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች በርካታ ስራተኞች በሹመትና በዝውውር ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደርገዋል። በሲቪል ሰርቪስ በፖሊስ እና በደህንነት ተቋማት እንዲመደቡ የተደረጉት በከንቲባ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ነው ተብሏል። የከተማ አስተዳደሩ በጀት የለኝም በሚል የከተማዋ ተወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ባገለለ መንገድ ይህንን ማድረጉ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል ሲሉ የመረጃ ምንጮች ገልፀዋል። የከተማ አስተዳደሩን ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም። 2) በሰሜን ጎንደር ወገራ ቆላ እና በደባት ቆላማ ቦታዎች በተደረገው ውጊያ የዳባት ወረዳ ሚሊሺያ አባላት ሙሉ በሙሉ አልቀዋል። የወረዳው ምድብተኛ የዐድማ ብተና አባላትም እንዲሁ አልቀዋል። በአጅሬ ጃኖራ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ሚሊሺያ ዐድማ ብተና አባላት ከፋኖ ኃይሎች ጋር ባደረጉት ከባድ ውጊያ ነው 133 በላይ የሚሊሺያ እና የዐድማ ብተና አባላት የተገደሉት ተብሏል። 3) ጋዜጠኛና ደራሲ ታዲዮስ ታንቱ በተመለከተ ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኙት አዛውንቱ ጋዜጠኛ ከእስር ተለቀዋል ተብሎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዘገባ ስህተት ነው ተብሏል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ፀጋ ለ Ethio News- ለኢትዮ ኒውስ ቻናል 2 እንዳረጋገጡት ባለቤታቸው አለመፈታታቸውን ለቀጣዩ ሰኔ 4/16 ዓ.ም የመጨረሻ ምስክሮች ለማሰማት ቀጠሮ መኖሩን ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ በቂሊንጦ የቀጠሮ ማቆሚያ እስር ቤት ይገኛሉ። 4)ግንቦት 29/2016 ዓ.ም በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን  በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ በደርጌ ኮትቻ ቀበሌ በመከላከያ 4 የአንድ በተሰው አባላት ተረሽናዋል። በዚሁ ወረዳ አማራውን ለስብሰባ እንፈልጋችኋለን በማለት 170 የአማራ አርሶአደሮችን  በአሊቦ ከተማ እስርቤት ያለምግብና እና በቂ ጥበቃ አስረዋቸዋል። ፖሊሶቹ እነዚህን እስረኞች በሸኔ ታጣቂዎች ለማስጠቃት ዕቅድ አላቸው ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ስጋታቸውን ገልፀዋል። ሆን ተብሎ ጠንካራ አማራዎች መሣሪያ ተነጥቀው በአንድ እስር ቤት የታጎሩት በተቀነባበረ የአካባቢው አስተዳደር እና የሸኔ ታጣቂዎች ዕቅድ ነው የሚሉት ቤተሰቦቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። Belete kassa
Hammasini ko'rsatish...
♦ ከወራት በፊት ለዐቢይ አሕመድ መወድስ አቅርበው የነበሩት ቄስ ወንድም አማረ በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ! "ከሕዝቡ እና ከቤተክርስቲያኗ ምዕመን ጋር ካጣሉኝ በኋላ ቃል የገቡልኝ ሳይፈፅሙልኝ ተጠቅመው ጥለውኛል " ዐቢይ አሕመድ ከወራት በፊት በየአከባቢው የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ እሳቸውና ስለሚመሩት ፓርቲ መወድስ ያቀረቡት ከደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ ተወክለው የሄዱት ቀሲስ ወንድም አማረ በጉና ክ/ጦር ፋኖዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ድምፅ ሚድያ ዘግቧል። በወቅቱ ቀሲስ ወንድም አማረ፤ ዐብይ አህመድ ለሚመሩት ፓርቲ የዜማ መወድስ ማቅረባቸውን ተከትሎ "እንዴት አማራ ሆነው የአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀን የአገዛዝ ስርዓት ያወድሳሉ? ህፃናትና ነፍሰ ጡር እናቶችን ሳይቀር የአማራን ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገድል መከላከያ ሰራዊትን ያሰማሩ ጠቅላይ ሚኒስትርን እንዴት ያሞግሳሉ? በርካታ ካህናትና ምዕመናን በቤተ መቅደስ እንዳሉ በታጣቂዎች ሲገደሉ ምንም አይነት ምላሽ ለማይሰጥ መንግስት እንዴት ክህነታቸውን ተጠቅመው የዜማ መወድስ ያቀርባሉ?" በሚል በርካታ ሰዎች ማህበራዊ ትስስር ገፃቸውን በመጠቀም ትችታቸውን ሲሰነዝሩ እንደነበር ይታወሳል። "በዞኑ ተወክየ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጠሩት ውይይት ለመሄድ ስዘጋጅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እና የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ይርጋ በዞንናችን አመራሮች በኩል አስጠርተውኝ እውቀትህን ተጠቅመህ ለመንግስት የዜማ መወድስ ካቀረብ የከተማ ቦታ እንሰጥኃለን በሚል ቃል ገብተውልኝ ነበር" ያሉት ቀሲስ ወንድም ፤ ነገር ግን ከሕዝቡ እና ከቤተክርስቲያኗ ምዕመን ጋር ካጣሉኝ በኋላ ቃል የገቡልኝ ሳይፈፅሙልኝ ተጠቅመው ጥለውኛል ማለታቸውን የፋኖ ደህንነት አባላቱ ለአማራ ድምፅ ሚዲያ ገልፀዋል።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram