cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Islamic Knowledge👈

"ዳመና የውሃን ክብደት መሸከም ሲያቅተው ዝናብ ይጥላል። ልብም የውስጡን ህመም መሸከም ሲሳነው አይን እንባ ያፈሳል። ስሜትህ ሲጎዳ ፣ ልብህ ሲሰበርና ሲጨንቅህ እጅህን ወደላይ ከፍፍ አድርግና ጌታህን ለምነው። እርሱ የለመኑትን አያሳፍርምና!" እናማ በዱዐ በርታ እኛንም አትርሳን አደራአለመርሳትህን share በማድረግ አሳየን😉 @Islamicknowledgechanal ለአስተያየት @Yuttiii

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
279
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
-430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ጠቃሚ መልእክት!!! የሚቀጥሉት 72 ሰዓታት ለፍልስጤም በተለይም ለጋዛ ወሳኝ ናቸው። እስራኤል ጋዛን እና ሃማስን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት 100,000 ወታደሮችን ከተጨማሪ 200,000 መጠባበቂያዎች ጋር አሰባስባለች። መላው ኡማ ከዚህ በታች ያለውን ዱዓ እንድታነብ ተጠየቀ።  በሚቀጥሉት 72 ሰአታት ውስጥ እያንዳንዱን ዱአ 10 ሚሊዮን ጊዜ በህብረት ለማንበብ አላማ አለን። حَسْبُنَا اللَّهُ وَ نِعْمَ الْوَ كِيلُ اَللّٰهُمَّ إِنَّا نَجْعَلُكَ فِي نُحُوْرِهِمْ وَنَعُوذُ بِكَ مِنْ شُرُورِهِمْ ይህንን መልእክት ለሁሉም ይላኩ እና 10 ሚሊዮን ኢላማ ላይ ለመድረስ የበኩላችሁን ተወጡ።  ጠላት ያሴራል አላህ በላጭ እቅድ አውጪ ነው። ጀዛክአላህ https://t.me/Islamicknowledgechanal
Hammasini ko'rsatish...
Islamic Knowledge👈

"ዳመና የውሃን ክብደት መሸከም ሲያቅተው ዝናብ ይጥላል። ልብም የውስጡን ህመም መሸከም ሲሳነው አይን እንባ ያፈሳል። ስሜትህ ሲጎዳ ፣ ልብህ ሲሰበርና ሲጨንቅህ እጅህን ወደላይ ከፍፍ አድርግና ጌታህን ለምነው። እርሱ የለመኑትን አያሳፍርምና!" እናማ በዱዐ በርታ እኛንም አትርሳን አደራአለመርሳትህን share በማድረግ አሳየን😉 @Islamicknowledgechanal ለአስተያየት @Yuttiii

ጥሩ ሰዎች በየሄዱበት መልካም ነገር ነው ምያጋጥማቸው ነገ ርግን አንድም ቀን መጥፎ ነገር ሳይሰሩ ቀርተው አይደለም ከመጥፎ ስራቸው ይልቅ ጥሩ ስራቸው ስለምያመዝን ነው።          
Hammasini ko'rsatish...
✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 በእናቱ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቀ። ዕድሜው ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናቱን ቀበረ። ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 በስምንት ዓመቱ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጉት አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው። እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት። ያ ፈታኝ ጊዜ "የሀዘን ዓመት" ተብሎ ተሰየመ። ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 ይባስ ብሎ ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት። ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ። ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው። ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች። ታሪክ ክስተቱን በደማቅ ፃፈ። ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 ግንባሩን ከመሬት ሰይሞ ከፈጣሪው ጋር በለሆሳስ ሲያወጋ የመካ ሙሽሪኮች በትከሻዎቹ መሃል የግመል አንጀት ከደም ጋር ቀላቅለው ሲያፈሱበት ግንባሩን ከመሬት ለአፍታ አላነሳ።   ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር ይቅር ባይነት የዘወትር ስንቁ ነበር። ስቃይ በተሸከመው አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ለሊቱን በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል።  ✨اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد 🌹 ልቦቻችን ውሃ እንዳጣ የዓረቢያ ምድረ በዳ ስንጥቅ በዝቶባቸዋልና ፈለግህን በመከተል በፍቅር ይረሰርሱልህ ዘንድ ደጋግመህ ሰለዋት አውርድ። ✨✨🌹🥀》♡🍀🍁🍀♡《🥀🌹✨✨ ሰለዋቱ ረቢ ወተስሊማቱሁ ዓለይሂ የአላ አሊሂ ወሰህቢሂ ወሰለም
Hammasini ko'rsatish...
🌹የጁምዓ ~ ቀን⃝ «የአላህ መልእክተኛ ‏(ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦ 🪧"ፀሀይ ከወጣችበት እለት ሁሉ በላጩ  የጁምዓ ቀን ነው" ➾የጁምዐ ቀን ማለት እኮ°°°> ✅:አባታችን አደም(ዓለይሂ ሰላም)የተፈጠረበት ነው! ✅:ወደ ጀነት የገባበት ቀን ነው! ✅:ከሷም ከጀነት የወጣበት ነው! ✅:ሙስሊሞች አንድነታቸውን የሚያሳዩበት ቀን ነው። ✅:ዱዐችን በይበልጥ ተቀባይነት የሚኖርበት ቀን ነው። ✅:በነብያችን ﷺ ላይ በብዛት ሰለዋት የምናወርድበት ቀን ነው። ✅:ጁምዐ በሳምንት አንዴ የምትመጣ የደስታ/የኢድ ቀን ናት። ✶⊶⊷⊶⊷⃝❍⊶⊷⊶⊷✶ ➥የትንሳዔ ቀንም በጁምዓ ቀን ቢሆን እንጂ አትቆምም።” 📒(ሙስሊም ዘግበውታል ‍‌8‌5‌4‌📚 ✿صلواعلي الحبيبﷺ↔ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ ●اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ 👉👉ነገ  ጁመዓ ነዉ ኢንሻ አላህ እንተዋወስ ሰለዋት አለ ነብይ ﷺ ያለው ጥቅም ሰለዋትን ማውረድ #ሙስሊም የሆነ ሰው #በነብዩ ላይ ሰለዋት (የአክብሮት እዝነት) ማውረድን ማብዛት ይጠበቅበታል። በተለይ ስማቸው በሚወሳበት ጊዜ። #አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይለናል፡- إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا (ሱረቱ አል- አሕዛብ - 56) አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ قال صلى الله عليه وسلم « مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا » ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት‘መን ሶላ ዓለየ ሶላተን ሶለልሏሁ ዐለይሂ ቢሃ ዐሸራ’ ‹‹በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል›› وقال صلى الله عليه وسلم : « لاَ تَجْعَلُوْا قَبْرِي عِيْدًا وَصَلُّوْا عَلَيَّ؛ فَإِنَّ صَلاَتَكَ تَبْلُغُنِي حَيْثُ كُنْتُمْ » ሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት: ‘‹‹መቃብሬን የባዕል ማዕከል አታድርጉት ፡፡በኔ ላይም ሶለዋት አውርዱ፡፡ የትም ሆናቸሁ ሶለዋት ብታወርዱ ይደርሰኛል፡፡›› ’ وقال صلى الله عليه وسلم : « الْبَخِيْلُ مَنْ ذُكِرْتُ عِنْدَهُ فَلَمْ يُصَلِّ عَلَيَّ » የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል፡-‹‹ስስታም ማለት ከእርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው፡፡››’ وقال صلى الله عليه وسلم : « إِنَّ لِلَّهِ مَلاَئِكَةً سَيَّاحِيْنَ فِي اْلأَرْضِ يُبَلِّغُوْنِي مِنْ أُمَّتِي السَّلاَمَ » እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል: “ለአላህ ተጓዥ መላኢኮች አሉት፡፡ ምድር ላይ ከኡመቴ የሚላክልኝን ሰላምታ ለኔ ያደርሳሉ፡፡” وقال صلى الله عليه وسلم : « مَا مِنْ أَحَدٍ يُسَلِّمُ عَلَيَّ إِلاَّ رَدَّ اللهُ عَلَيَّ رُوْحِيَ حَتَّى أَرُدَّ عَلَيْهِ السَّلاَمَ » ነብዩ( ﷺ ) እንዲህ ብለዋል፡: “አንድ ሰው ሰላምታ ሲልክልኝ አላህ ነፍስ ይዝራብኝና ምላሽ እሰጠዋለሁ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
🌹ይነበብ!👌 ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ከአራት የጋብቻ ዓመታት በኋላ.. ሰዎች ስለ ትዳራቸው ማውራት ጀመሩ። "አላህ የልባቸውን ክፋት አይቶ ልጅ ነፈጋቸው" እያሉ ተሳለቁ። ግን ግን ችግሩ ከማን ይሆን? እያሉ ደጋግመው ጠየቁ። የሰፈሩ ሰው ቡና መጣጫ የአላፊ አግዳሚው መባቻ መተረቻ ሆኑ። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿የወሬው ጫና ሲበረታባቸው ወደ ሆስፒታል አቀኑና ችግራቸውን ለዶክተሩ አስረዱት። የምርመራ ውጤቱን እየጠበቁ ከአግዳሚው ወንበር ላይ አረፉ። ውጤቱ ደርሶ ባል ብቻውን ወደ ዶክተሩ ክፍል ገባና ጠየቀ። ሚስቱ መውለድ እንደማትችል ተነገረው። "አትወልድም መሐን ናት" አለው። "እባክህ ባለቤቴን ከመጥራቴ በፊት ...." እንዳለ ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ። ሳግ እየተናነቀው እንደምንም ያለውን አቅም አሟጦ "እባክህ ችግሩ የኔ እንደሆነና መውለድ እንደማልችል አርገህ ለሚስቴ ንገራት" እያለ ለመነው። ችክ ብሎ አጥብቆ ጠየቀው። ቀልቡ ራራለትና ተስማማ። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ባል ሚስቱን ከሴቶች ማቆያ ክፍል ጠርቶ ተያይዘው ዶክተሩ ዘንድ ገቡ። "ባልሽ መሀን ነው" ሲል አረዳት። "የመውለድ ተስፋም የለውም" አላት። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ተቃቅፈው እየተላቀሱ ወደ ቤት ተመለሱ። ቀናት ቀናትን እየተኩ ሳምንታት አለፉ። ወሬው በአካባቢው ተሰራጨ። መንደርተኛው እየተጠቋቆመ መሳለቂያ አደረገው። በዚህ ሁኔታ ዘጠኝ ዓመታት ተቆጠሩ። ያቺ ቅጽበት እስክትመጣ ጥንዶቹ በትዕግስት የአላህን ምላሹ ጠበቁ። ሚስት በባሏ ተስፋ የቆረጠችበት ቅፅበት ደረሰ "ሞከርኩ አቃተኝ ለድፍን ዘጠኝ አመታት ታገስኩ አሁን ግን በቃኝ እንድትፈታኝ እፈልጋለሁ" ስትል ጠየቀች። በሰዎች እይታ ባሏን ችላ ተሸክማ የተቀመጠች ጥሩ ሚስት ነበረች።   "ማግባትና ዓይኔን በዓይኔ ማየት እፈልጋለሁ" ስትለው ትንሽ እንድትጠብቀው እያለቀሰ ለመናት። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ከዚህ ንግግሯ፣ ጥቂት ቀናት በኋላ አላህ በኩላሊት በሽታ ፈተናት። ጣቷን ባሏ ላይ እየቀሰረች ትወነጅለው ጀመር። እሱ ነው ሰበቡ እያለች ወቀሰችው። ለምን አይፈታኝም ነበር.. ልጆች መውለድ እንደምፈልግ ነግሬዋለሁ እያለች ተነፋረቀች። ጮኸች አለቀሰችም። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ኦፕራሲዮን ልትደረግ በተዘጋጀችበት ወቅት ባል ለሥራ ወደ ውጭ አገር እንደሚሄድ በቅርቡ ግን እንደሚመለስ የሚገልፅ ቴክስት ላከላት። ኩላሊት የሚለግሳት ሰው ማግኘቱንም ነገራት። በፍጥነት እንደሚመለስ ገልፆ ተሰናበታት። ሚስት በገነች። "ጭራሽ ይህን ሁሉ ጊዜ ተሸክሜው መኖሬ ሳያንስ ሰው በሚያስፈልገኝ ሰዓት ከአጠገቤ ይራቅ?!" እያለች ተብሰለሰለች። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ከቀዶ ጥገናው አንድ ቀን ቀደም ብሎ አንድ ወጣት የሆስፒታሉን ቅጥር አልፎ ከዶክተሩ ክፍል ገባ። ዐረብ ነው ሰላምታ ሰጥቶ ከወንበሩ ተቀመጠ። ኩላሊቱን ይለግሳል የተባለው እርሱ ነበርና ብቻውን ወደ ውስጥ ዘለቀ። በተሳካ ሁኔታ ቀዶ ጥገናው ተደረገ። የኩላሊት ንቅለ ተከላው ወደ ሙሉ ጤንነቷ መለሳት። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ባል ቆይታውን ጨርሶ ሲመለሰ... የድካም ምልክቶች ፊቱ ላይ ይነበብበት ነበር። አእምሮህ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ለምን እንደደከመው ልንገርህ። እሱ ራሱ ነበር ኩላሊቱን የለገሳት ግን ግን እንዳይታወቅበት አረቡን ሰው ላከላት። አዎ ኩላሊቱን ለሚስቱ የሰጣት ባል ነበር። ይህንን መልካምነቱን ከሁሉም ሰው ደብቆ በምስጢርም ሸሸገው። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ቀዶ ጥገናው ተደርጎ ዘጠኝ ወር እንዳለፈ ሚስት አረገዘች። ከሌላ ዘጠኝ ወራት በኋላ የበኩር ልጇን ወልዳ ታቀፈች። በደስታ ቤቱ አነባ። ዘመድ፣ ጎረቤት፣ ባልና ሚስት ሁሉም እየተቃቀፉ ተሳሳቁ። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ባል... በዚያን ወቅት በሸሪዓ ህግ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪውን በማጠናቀቅ ላይ ነበር። ያም ብቻ አይደለም ግርማው የከበረውን በደረጃውም የላቀውን ቁርአንን በቃሉ ሐፍዟል። በሀፍስ የአቀራር ሰንሰለትም ሰነዱን ተቀብሏል። ይህን ሁሉ አብራው የምትኖረው ሚስቱ አታውቅም። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿የእለት እንቅስቃሴውን የሚያሰፍርበትን ደብተር ከዕለታት በአንዱ ቀን ከክፍሉ ጠረጴዛ ላይ እንዳስቀመጠ ረስቶ ከቤት ወጣ። ሚስት አገኘችው። ገልጣም አነበበችው። ደወለችለት ሀሎ ብሎ ሲያነሳው አለቀሰች.. ነገሩ ገባው ደብተሩን እንደረሳ አስታወሰና አነባ። እንዲሁ እየተላቀሱ እንባ ለእንባ ገጥመው እያወሩ ስልኩ ተዘጋ። ክብ ክብ ውሀ መሳይ ጎርፎች ከዓይናቸው ፈልቀው ስሜታቸውን ገለፁላቸውና ቻው ተባባሉ። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ወደቤት እንደተመለሰ አይኗን ከመሬቱ አቀርቅራ ተቀበለችው። ከዚያን ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ወራት በሙሉ ዓይኗ ልታየው ፈራች። ድምጿን እንኳ በቅጡ ማሰማት ቸገራት። ባል እንዲህ ይላል..   "ያለፉትን አስርት አመታት ህመም የተባለን ሁሉ ከዓይነቱ ስጎነጭ እንባዬን የሚጠርግልኝ አቅፎ የሚያባብለኝ አንድም ሰው ከጎኔ አልነበረም። እርሷ ግን ስታለቅስ ፀጉሯን እየዳበስኩ እንባዋን እየጠርግኩ አፅናናታለሁ። በዘመዶቼ ባይተዋር ተደርጌ ስገለል መሸሸጊያዬ እሷ ነበረች። ደግና አዛኝ ሚስት ናት። እኔ ነበርኩ መሐን አሁን መውለድ የቻልኩ" ይላል። እሱን ለመረዳት እንባውና ፍቅሩ በቂ ይመስሉኛል። ብቻ ግን ... እንዲህም ዋጋ ይከፈላል። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿በእነዚህ አስር ዓመታት ላሳየው ትዕግሥት አላህ በተሻለ መነዳው። የአብራኩን ክፋይ ከሚወዳት ሚስቱ ለገሰው። ⚡️አላህ ሆይ  ትዕግስትን ለግሰን!🌹 🌿ታሪኩ በህልም ዓለም ውስጥ በገሀድ የታየ እውነታ እንጂ ልቦለድ አይደለም። የምነግራችሁ ስለ መልካምነት የማወራችሁ ስለትዕግስት በልቤ የተሸከምኩትም አላህ ታጋሾችን የሚክስበትን ተስፋ ነው።  አላህ በእርግጥም በሰብር የተሽሞነሞኑ የችግር ቀናትን በተሻለ ይክሳል።
Hammasini ko'rsatish...
🔎| ወዳጄ ልብ በል❗️|💌 ✅: ጊዜ ፣ ጉልበት እና ገንዘብ በአንድ ጊዜ አይመጡም። 1⃣:#በልጅነትህ ሰፊ ጊዜ እና ጉልበት ይኖረሃል። ገንዘብ ግን አይኖርህም። በልጅነት ጊዜህ ሰፊ ገዜህን እና ጉልበትህን በአግባቡ ተጠቀምበት። ካለፉ አለፉህ ነው ተመልሰው አይመጡም። ከሄዱ ሄዱ ነው አይጠብቁሁም። 2⃣:#በወጣትነትህ ገንዘብ እና ጉልበት ይኖረሃል። ጊዜ ግን ይከደሃል። ገንዘብህና ጉልበትህን በዚህ ውድ ጊዜ(በወጣትነትህ) ላይ በአግባቡ ተጠቀምበት። ገንዘብህን የተቸገርን እርዳበት የተራበን መግብበት ፣ የተራቆተን አልብስበት ፣ ። 3⃣:#በእርጅና ጊዜህ በወጣትነትህ የለፋህበት ገንዘብ እና ሰፊ ጊዜ ይኖረሃል። ጉልበት ግን #ሁለት ጊዜ አጫውቶሃል(በልጅነት ጊዜህና በወጣትነትህ) ፤ ለ3ኛ ጊዜ ግን ተመልሶ ላይመጣ ጥሎህ ይሄዳል። 🔆:በደንብ አስብበት
Hammasini ko'rsatish...
00:54
Video unavailableShow in Telegram
በቃ Allhamdulilah🤌 ሙስሊም ላረገን ጌታ @Strong_iman
Hammasini ko'rsatish...
oUaAZAhRJrzDIhoJAWpHfzSgtFkQHyECIXILUv.mp43.64 MB
የ ረሱልን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አብዛኛውን ሀዲስ የዘገቡት ማናቸው?
Hammasini ko'rsatish...
አነስ ኢብኑ ማሊክ ረ.ዐ
አቢ ሁረይራ ረ.ዐ
አዒሻ ረ.ዐ
ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ
سورة الكهف | ﷽ ዛሬ ጁመአ ነው ሱረቱል ክህፍ የቻለ ይቅራ ያልቻለ ያድምጥ ኮሜንቱን በሰለዎት እኑምላው እስኪ❤️ ﷺ✨ﷺ✨ﷺ✨ﷺ✨ﷺ✨ﷺ
Hammasini ko'rsatish...
018.mp311.89 MB
የሙሀረም 9ነኛ እና 10ኛ ቀናት 9 ሀሙስ 10 ጁምዐ የዓሹራን(10ኛ) ቀን መፆም ያለፈውን አመት ሀጥያት ያስምራል ብዬ አላህን እተማመናለሁ የአላህ ነብይ(ሰ.ዐ.ወ)
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.