cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
211
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

​​​​​. 🌺 🖤ተስፋ_ያጣች_ሴት🖤 🌺 ╰═════════════╯ ​ 💟እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💟 #ክፍል\_17 ...🖊ሀና ከኪሩቤል ጋር ማደሯ እጅግ በጣም ነበር ያስደነገጣት ፈፅሞ ይህ እንዲፈጠር አልፈለገችም ነበር በዚም ምክንያት ጧት ላይ ቀድሟት ነቅቶ ቁርስ እየሰራ ስታየው እራሷን አንቃ ብትገል ደስ ባላት ነበር ኪሩቤልን እንደገደለችው ተሰማት። አሁን አብረው አድረዋል ይህም ማለት ወደ ጀርመን የመመለስ እድል አይኖረውም ይህ ደግሞ በሷ ምክንያት መሆኑ ህሊናዋን እረፍት አሳጣት "ኪሩ እባክህ ይቅር በለኝ" አለች ከየት መጣ የማይባል እምባ ጉንጯን አልፎ በቅጡ ያልተሸፈኑ ጡቶቿን እያራሰ... "ያለፈው አልፏል ውዴ አትጨናነቂ ደግሞ ሰክረሽ እንደምታፈቅሪኝ ነግረሽኛል ስለዚ ካፈቀርሽኝ ለኔ በቂዬ ነው!" አለ በደስታ ፈገግ ብሎ ስስ ፀጉሮቿን እያሻሸ... ሀና እንባዋ እየባሰ መጣ ኪሩቤልን ከማጣቷ በላይ በሷ ምክንያት የሚጎዳው ጉዳት አሳሰባት... ኪሩቤል ደረቱ ላይ ልጥፍ አርጓት እረጅም ሰአት ቢቆይም ሀና ግን ልትናገረው የምትፈልገውን ነገር ለማውጣት ከራሷ ጋር ሙግት ገጥማ ነበር ይሄኔ "ሀኒ" አለ ኪሩቤል ፍርሃት ጭንቀትና እንባ በወረሱት አይኖቿ ተመለከተችው "እባክሽ በመሃላችን ስለነበረው መራራቅና ክፍተት እርሺ ከዛም ፍቅራችንን ብቻ እናዳምጥ ሀኒዬ አይናችንን ባይናችን እንይ አሁኑኑ አግቢኝ!! ከዛ ከፈለግሽ እዛ አወስድሻለው ካልፈለግሽ ደግሞ ሀገርሽ ላይ እንደንግስት እንከባከብሻለሁ... " አለ በአይኖቹ እየተማፀናት... ሀናም ይህን ስትሰማ ድሮ ቢሆን ምን ያህል በደስታ እንደምትሰክር አሰበች አሁን ግን ባዶ ተስፋ ሆነባት እናም ኪሩቤልን ከላይዋ ላይ ገፋ እያደረገች ... "በቃህ ይሄ ሁላ ከንቱ ምኞት ነው ስለኔ ብዙ የማታውቀው ጉድ አለ... አንተጋ ለመምጣት ፕሮሰስ ጀምሬ ተስፋ በሰነኩበት ሰአት ቅዱስ የሚባል አውሬ በደካማ ጎኔ ገብቶ ህይወቴን አመሰቃቀለው ከዛም ወደ ሴተኛ አዳሪነቴ ተመለስኩ... ይህን ያረኩት ከሀገር ለመውጣት በቂ ገንዘብ ስላልነበረኝ ላጠራቅም ነበር ግን ፈጣሪ ያኔ ገና ቴዎድሮስ ልጅነቴን ሲነጥቀኝ እረስቶኝ ነበርና (H I V )ኤች አይ ቪ በደምሽ ውስጥ አለ ተባልኩ እናም ያንቺ እጣ ሴተኛ አዳሪነት ነው ብለው ፈረዱብኝ... በቃ ወንዱን ሁሉ በተለይ ሀብታምና ባለስልጣን እየመረጥኩ ስበቀል ኖርኩ ግን በስተመጨረሻ ወላጅ አባቴ ፀጋዬ ገ/ማርያም አንሶላ ተጋፈፈኝ... " አለች ይህን ስትናገር በስሜት ጮክ ብላ ነበር ሀናን ለሚሰማት ልብ ወለድ ትረካ እንጂ እውነት የሷ ታሪክ አይመስልም ነበር ... ኪሩቤል ይህን ሁሉ ጉድ ሲሰማ እራሱን አለመሳቱ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ ያሳያል ... ሀና ንግግሯን ቀጠለች "እሺ አሁን ይሄን ሁሉ ጉዴን ሰምተሃል በላ ዝም አትበል እንደመጀመርያህ ያላንቺ አልኖርም... ምናምን በለኝ እ ዝም አትበለኝ ኪሩ አሁንስ አግብተኸኝ መኖር ትፈልጋለህ?" ኪሩቤል መቋቋም ተሳነው ምንም ሳይመልስላት ወጥቶ ሄደ... ኪሩቤል ከወጣ 2ወር ሆነው ስለሱ ምንም ሰምታ አታውቅም ስልኩም ዝግ ነበር ሀና ስለኪሩቤል ብዙ ትጨነቃለች ስለሱ ምንም ባለመስማቷ ደግሞ ጭንትቷን እጥፍ አርጎባታል ይህ በንዲህ እንዳለ ሀና የወር አበባዋ ቀረ ለዚህም በመጠራጠር ሆስፒታል ስትሄድ የ2 ወር ነብሰ ጡር መሆኗን አረጋገጠች ከዚህ የባሰው ለሀና ያስደነገጣት ነገር ግን ከኤች አይ ቪ ነፃ ነሽ መባሏ ነበር... ይሄ ለሀና ተአምር ነበር... አላምን ብላ 3 ሀኪም ቤት ሄደች ግን ለውጥ የለውም ሀና ነፃ ናት... ግን አሁን እረፍዷል ኪሩቤል ጥሏት ሄዷል ይሄ ደግሞ ልጁን እንዳትወልደው ያደርጋታል ምክንያቱም ሀና ያለ አባት ልጅ ላታሳድግ ያለፈ ህይወቷ ያስገድዳታል... ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 18 ከ150♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ❥..................🍃⚘🍃...................❥ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,, ••●◉Join us share◉●•• https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

​​​​​. 🌺 🖤ተስፋ_ያጣች_ሴት🖤 🌺 ╰═════════════╯ ​ 💟እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💟 #ክፍል\_16 ...🖊ኪሩቤልና ቅዱስ በሩን ቢያንኳኩም ሀና ግን ለመክፈት ፍቃደኛ አልነበረችም እንዲያውም ፖሊስ ሳልጠራ ሂዱ እያለች መጮህ ጀመረች ይሄኔ ቅዱስ ኪሩቤልን እንደምንም አሳምኖትና ተመልሰው ስትረጋጋ እንደሚመጡ ነግሮት ይዞት ሄደ ኪሩቤል በጣም ነበር ያዘነው ... በ3ኛው ቀን ኪሩቤል ለብቻው መጣና ሀና ሳታየው ወደ ፀጉር ቤቷ ገባ ይሄኔ ሀና ድንገት ስትዞር ኪሩቤል ገብቶ በሩን ሲዘጋው ተመለከተች ኪሩቤልም ስታየው ትጮሃለች ብሎ ስለፈራ "እባክሽ ሀና አንዴ ስሚኝ ከዛ እሄድልሻለው ግን አዳምጪኝ ወደ ጀርመን ልመለስ ጥቂት ቀን ነው የቀረኝ ሁለት ወር ሙሉ ፈልጌሻለሁ ግን አጣሁሽ ስልክሽንም አጥፍተሽዋል ቅዱስ ነው ንፅህናሽን የነገረኝ በድርጊቱ በጣም ተፀፅቷል..." ሲል ንግግሩን አቋርጣ... "የሱ መፀፀት ምን ይጠቅመኛል? የትኛውን የተበላሸ ማንነቴን ያቃናዋል? የትኛውን ሀጥያትና ጥፋቴን ያርምልኛል? ንገረኝ ከየትኛው የህሊና ቁስል ይፈውሰኛል ?..." ሀና እንባ እየተናነቃት ንግግሯን እንኳ መቋጨት አቅቷት ጭንቅላቷን ይዛ እናቱን እንደቀበረ ሰው ተንሰቅስቃ አለቀሰች ... ሀና የእውነትም በቫይረሱ ከመያዝ ጀምሮ ከአባቷ ጋር እስከማደር ያደረሳት በቅዱስ ጥፋት ተስፋ በመቁረጧ ነው! ኪሩቤልም እንባውን መንታ መንታ እያዘነበ "እባክሽ ይቅር በይኝ ያኔ ያየሁትን ማመን አልነበረብኝም ካንደበትሽ መስማት ነበረብኝ ..." አለ ፀፀትና ቁጭት እየታገለው ሀናም ለደቂቃዎች ዝምታን ከመረጠች ቡሃላ እራሷን በራሷ ሁሌም እንደምታረገው እያረጋጋች "ኪሩ ምንም ጥፋት የለብህም የኔ እድልና እጣ ፈንታ የተፃፈው በዚ መልኩ ስለሆነ ነው... እናም እስካሁን ከማውቃቸው ወደፊትም ከምተዋወቃቸው ሁሉ በልቤ ትልቅ ስፍራ ያለህ ብቸኛ ሰው ነህ! አንተን መጥላትም መቀየምም ለኔ ሀጥያት ይመስለኛል እና ግን ኪሩ በቃ ሂድ ዳግም እኔጋር እንዳትመጣ!!..." ይህን ስትናገር ሀዘኗን ለመሸሸግ እየሞከረች እንደነበር ፊቷ ላይ በደንብ ይነበባል...ኪርቤልም በአባባሏ ግራ እየተጋባ "የኔ ውድ በጣም አፈቅርሻለሁኮ ያላንቺ ሁሉም ነገር አስጠልቶኛል እባክሽ አትግፊኝ" አለ ሀናም አፈቅርሻለሁ የምትለዋን ቃል ስትሰማ ልቧ ምቱ የጨመረ መሰላት ግን ቀጥ ብላ ልታየው አልደፈረችም አይኖቹን ስታይ ያኔ ድሮ ልጅ ሆና ያሳለፈችው የታፈነ ፍቅር ይመጣባታል... ሀና ኪሩቤልን በቆሸሸው ማንነቷ መቀበል አልፈለገችም ያሳለፈችውን ታሪክ ደግሞ ብትነግረው እንደሚጠላት አልፎም እንደሚጎዳ ታውቃለች ለዚም ሀና የሷን ፍቅር አፍና እሱ ተስፋ ቆርጦ ወደ ጀርመን እንዲሄድ ብዙ ደከመች ነገር ግን ኪሩቤል ከሷ ውጪ ፈፅሞ ማፍቀርም ማግባትም እንደማይፈልግ አስረግጦ ነገራት። ስለዚህ የነበራት አማራጭ ያሳለፈችውን ሳትደብቅ መንገር ይህን ለማድረግም አቅም እንዲሆናት እቤቷ እራት ጋብዛው መጠጥ መጠጣት ጀመረች "ሆድ ያባውን..." አይደል አባባሉ... ያን አስባ ነበር መጠጣቷ ግን ያሰበችው ሳይሆን እንዲሆን የማትፈልገው ነገር ተከሰተ ሀናና ኪሩቤል ያለጥንቃቄ አብረው አደሩ... ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 17 ከ150♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ❥..................🍃⚘🍃...................❥ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,, ••●◉Join us share◉●•• https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

​​​. 🌺 🖤 ተስፋ_ያጣች_ሴት🖤 🌺 ╰═════════════╯ ​ 💟እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💟 #ክፍል\_15 ...🖊ሀና አሰበች ይሄ ሰውዬ ሳይነቃ ከቤት መውጣት እንዳለባት በመገንዘብ በፍጥነት ልብሷን ለበሰች ያን ሰአት አባቷ ሴተኛ አዳሪ ይዞ ማደሩ ያውም የትም ወልዶ የጣላት ልጁ መሆኗ አንተ ልክስክስ ...ብላ በህዝብ ፊት ብታሸማቅቀውና ብታዋርደው ምን ያህል ደስ ባላት ግን ሀና ለብዙ ግዜ ለፍታ ያሳደገቻትን እናቷን አስታወሰች እናም ለዚች ምስኪን እናቷ ምላሽ ይህን ማድረግ እናቷን ማዋረድ እንደሆነ በመገመት አባቷ ሳይነቃ ጥላው ወታ ሄደች ኪሱ ውስጥ የነበሩትን ፎቶዎችና አስተካክላ ያልቆጠረችውን ገንዘቡንም ይዛበት ነበር የሄደችው.... ሀና ከዛን ቀን ቡሃላ ወደ ሴተኛ አዳሪነቷ ላትመለስ በምትወዳት እናቷ ስም ለራሷ ቃል ገባች ምክንያቷ ደግሞ ስትበደልና ስትገፋ ኖራ የወደፊት ትስፋ የሌላት ቢሆንም እሷም ባቅሟ ብዙ ሃጥያትን ሰርታለች ይሄኔ ያላትን ብር ባንክ ከተተችና ወደ ትንሽ ገዳም ሄደች እዛም መንፈሷን ካረጋጋች በኋላ የነብስ አባት ይዛ ሀትያቷን ተናዘዘች ... ይቅር ባዩ ጌታ ይቅር ይላት ዘንድም ፆምና ፀሎት ጀመረች ሀና ከሁሉም የሚቆጫትና አልረሳ ያላት ከአባቷ ጋር አንሶላ መጋፈፏ ነበር ግን እየቆየች እራሷን ማረጋጋት ጀመረች ፀሎትና ፆሟንም ጨርሳ በአዲስ መንፈስ ወደተከራየቻት ትንሽ ጎጆ በመመለስ ቤቷን ዘግታ ባላት ገንዘብ ምን ሰርታ መለወጥ እንዳለባት ማሰብ ጀመረች... ሀና ሱስ ማቆሟ ፈተና ሆኖባት ነበር ሁሌም ስታየው ያሰኛታል ግን በጥንካሬ እራሷን አሸነፈች ... ሀና በቅድሚያ አንድ መኝታ ኮንዶሚኒየም ገዛች ቀጥላም የፀጉር ሞያ ለ6ወር በመማር የሴቶች የውበት ሳሎን ከፈተች... ሀናን ለሚያውቋት ይሄ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበር ... ይህን አድርጋ ትንሽ ከተረጋጋች ቡሃላም እናቷን ይቅርታ ለመጠየቅ ድፍረት ፈጣሪዋን መለመን ጀመረች እናቷን ሁሌም ከሩቅ ታያት ነበር እናት ግን ልጇን ካየች አመታት አልፈዋል እናቷ አፀደ ሰዎች ስለሀና ሲጠይቋት"ልጄ ሀና አንድ ቀን እንደምታኮራኝ አውቃለው አሁን በቅርብ አገኛታለሁ.." ነበር መልሷ ታድያ ቴድሮስ ይህን ስትል ሁሌም ይስቅባት ነበር .... ሀና እናቷን በልቧ ነቅሳት እድሜ ልኳን ኖራለች ሁሌም ግጥም ስትፅፍ ስለእናቷ የምትፅፈው ይበዛል ታድያ ግጥም ስትፅፍ ላነበበላት ወይንም ስታነብ ለሰማት ትልቅ ስፍራን ሳይመኝላት አያልፍም!! ሀና ምንም እንኳ ያለፈ ታሪኳን መርሳት ብትፈልግ ሊረሳት ግን አልቻለም ሁሌ የእናቷን ቤት ጥላ ለመሄድ መወሰኗ ይፀፅታታል ... በዚ ግዜ ለሀና ህልም የሚመስል እውነት ተከሰተ ሀና ምንም እንኳ ስልኳንና አድራሻዋን አጥፍታ ብትጠፋም ኪሩቤል ግን ይፈልጋት ነበር... ሀና ብዙ ደምበኞች ነበሯት ከነዚህም አንዷ ትግስት ፀጉሯን ለመሰራት ሀናጋ ደውላ ለጠዋት ቀጥራት ነበር ሀናም ለሷ ስትል ያለወትሮዋ በጥዋት ተነስታ ፀጉር ቤቷን ስትከፍት ቅዱስ ድንገት በሚመስል መልኩ መጣ ሀናም ትንሽ ደንገጥ ብላ "እንዴ ቅዱስ ምን ልሰራ መጣህ ተሳስተህ መሆን አለበት እንጂ ፈፅሞ ልታየኝ አትደፍርም!" አለችው ቅዱስም "ሀኒ አንቺ እንጂ አይተሽኝ የማታውቂው እኔ ሁሌም አይሽ ነበር ሆቴል ስትሰሪ ስራሽን በግልፅ ባላውቅም እኔ ከሩቅ እጠብቅሽ ነበር" አለ... ሀናም በምፀት ፈገግታ ፈገግ ብላ እያየችው የቱርክ ፊልም አክተር ትአሁንብኝ ብላ በሩን ልዘጋው ስትል ሀኒ አለ ከፈት አርጋው ቅዱስ ትውስታዬን አትቀስቅስብኝ ካለዛ እገልሃለው ... ብላ ንግግሯን ገታ ከማድረጓ ኪሩ ነኝ አለ ከቅዱስ ጀርባ ሆኖ ቅዱስን ወደኋላው ጎተት እያረገ ይሄኔ ሀና ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት እግሮቿ የከዷት መሰላት ... ኪሩቤል ከጀርመን መቶ ሀናን ብሎ ይሄው ከፊለፊቷ ተገኘ ቅዱስም ሀና እሮጣ ኪሩቤል ላይ ትጠመጠማለች ብሎ ሲጠብቅ እሷ ግን በተቃራኒው ሁለታችሁም ጥፉልኝ ከፊቴ ሀና በሁለት እግሮቿ ልትቆም ነው ሲሏቹ ዳግም ልትጥሉኝና ልታዋርዱኝ ህይወቴን ልትበጠብጡ መጣቹ?? ይህን አልፈቅድም ! ብላ በሩን ከውስጥ ቆለፈችውና እንዳትወድቅ በቀስታ ወለሉ ላይ ተቀመጠች... ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 16 ከ150♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ❥..................🍃⚘🍃...................❥ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,, ••●◉Join us share◉●•• https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

​​​​​. 🌺 🖤ተስፋ_ያጣች_ሴት🖤 🌺 ╰═════════════╯ ​ 💟እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💟 #ክፍል\_14 ...🖊ሀና ኤች አይ ቪ በደሟ ውስጥ መኖሩን ስታውቅ እራሷን ከሳተች ከሁለት ቀን ቡሃላ ነቃች ስትነቃ እንድ ክፍል ውስጥ ብቻዋን አልጋ ይዛ ተኝታ ነበር ዞር ዞር ብላ ተመለከተች ለመነሳትም ፈለገች ግን አቃታት እራሷን በጣም አሟታል ይሄኔ እዛ ክፍል ከመግባቷ በፊት ስለተፈጠረው ነገር ለማስታወስ ጥረት ማድረግ ጀመረች ይሄኔ ስለጉዞዋ አሰበች በዚ ግዜ ነበር ኤች አይ ቪ / HIV/ የምትለዋን የዶክተሩ ንግግር ትዝ ያላት ሃና በቅፅበት አይሆንም መኖር የለብኝም አለችና የተሰካላትን ጉልኮስ ነቀለችው ይሄኔ አንድ ወጣት ዶክተር ወደክፍሉ በመግባት "የኔ እህት ተረጋጊ" አላት ሀና ግን እንደ እብድ አረጋት "እኔ መትረፍ የለብኝም" እያለች ጮኸች ዶክተሩም ከብዙ ጥረት ቡሃላ አሳምኖ እንድትረጋጋ አደረጋት ... ሀና ከሀኪም ቤት እንደወጣች ቤተክርስትያን በመሄድ ለፈጣሪዋ አነባች ግን ሀና ስታለቅስ እንጂ የውስጧን ፍላጎትም ሆነ ምን ብላ እንደምትለምነው አታውቅም ነበር ግን ደጋግማ አንድ ነገር አለች "ግን ለምን በኔ ላይ ይህን ሁሉ መከራ ፈረድክ ምንስ ነው ሀጥያቴ?የማንንስ እዳ ነው እየከፈልኩ ያለሁት? " እያለች ትጠይቃለች የፈጣሪ መልስ ግን ምን ግዜም በተግባር ስለሆነ ያን ሰአት ምንም መልስ አላገኘችም! አልቅሳ ስትጨርስ ቤቷ ገባች ቁጭ ብላ ካሰበች ቡሃላም አንድ ነገር ልታደርግ ወሰነች እዛው ትሰራበት የነበረው ሆቴል ተመልሳ ወንዶችን መበቀል ... ሀና መድሃኒቷን/ማራዘምያ/ መውሰድ ጀመረች እራሷንም ከድሮው በበለጠ ትጠብቃለች ውበቷ እንደ አደይ ፈካ እድሜዋም ህፃን ስለነበረች ወንዶችን ማጥመድ ለሷ ቀላል ነበር ይህ በእንዲህ እንዳለ የመጀመርያ ወጥመዷ የሆቴሉን ባለቤት አደረገችው ሆን ብላ እንዲደፍራት አደረገች እንደፈለገችውም ተሳክቶላት ያለምንም ጥንቃቄ ወሲብ ፈፀሙ ሁለተኛው ስራዋ "...እንደደፈርከኝ ለሚስትህ እንዳልናገር 50,000 ብር ስጠኝና ከሆቴልህ ልጥፋ" የሚል ነበር ይሄም እንዳሰበችው ተሳካላትና ሀና ጥላ በመውጣት ሌላ ሆቴል ተቀጠረች ... ሀና ፈፅሞ አትፀፀትም አንድ ሰው በበከለች ቁጥር የመንፈስ እርካታ ይሰማታል... በዚ ሁኔታዋ አንድ አመት ቆየች ከነጭ እስከ ጥቁር ከኢትዮጵያዊ እስከ እንግሊዛዊ የበቀል መርዟን እረጭታባቸዋለች... አንድ ቀን አዳር ከአንድ ባለሀብት ጋር ካደረች ቡሃላ እንቅልፉን ሲተኛ ኪሱን መበርበር ጀመረች ይሄኔ ግን ያልጠበቀችው ጉድ ነበር የገጠማት ሀና ምንግዜም ቢሆን ማታ ከስራ በፊት አልኮልና አደንዛዥ እፅ ስለምትወስድ ምንም አታስተውልም ዛሬም እንደለመደችው ሰውየውን ገንዘቡን ለመስረቅ ኪሱን ስትበረብር መንጃ ፍቃዱ እጇ ውስጥ ገባ ይሄኔ ስሙን ስታነብ መቼም ልትገምት የማትችለው ዱብዳ ነበር የገጠማት የሰውየው ሙሉ ስም አቶ ፀጋዬ ገ/ማርያም ይላል እሷ ስሟ ሀና ፀጋዬ ገ/ማርያም እንደሆነ ታውቃለች ይህ ሰው በአካል የማታውቀው ወላጅ አባቷ ነው አባቷ የወጣለት ሴሰኛ መሆኑን ብታውቅም በሀብቱ አማሎ ሴት ይይዛል እንጂ ሴተኛ አዳሪ ጋር ይሄዳል ብላ አስባም አታውቅ ግን ሆነ ለማረጋገጥ ዋሌቱን ፈተሸችው የወንድሟ ያስራና ሌሎች የማታውቃቸው ወንድምና እህቶችዋ ፎቶ አለ ሀና ግራ ተጋባች... ይቀጥላል...] ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 15 ከ150♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ❥..................🍃⚘🍃...................❥ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,, ••●◉Join us share◉●•• https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

​​​​​. 🌺 🖤ተስፋ_ያጣች_ሴት🖤 🌺 ╰═════════════╯ ​ 💟እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💟 #ክፍል13 ...🖊ኪሩቤል ሀናን ጀርመን የመውሰድ ሃሳቡን በመተው ሀና ህይወት ያበቃች መሰላት በተለይ ደግሞ ለምን የሚለውን ጥያቄ መልስ አለማግኘቷ ዳግም ወደ ተወችው ሱስ መለሳት ሀና ታጨሳለች ትቅማለች ትጠጣለች ... ቅዱስም እሷን የሱ ለማድረግ ብዙ ቢለፋም አቃተው... አንድ ቀን ሀና ዋትሳፕ ላይ ለኪሩቤል የድምፅ መልክት ላከችለት "ኪሩ ሰላም ባለህበት ግን ኪሩ እኔ ካንተ ይሄን አልጠበኩም ነበር ... እራስህ ተስፋ ሰጠኸኝ ግን መልሰህ ወሰድከው እኔ ላንተ ትልቅ ቦታ ነበረኝ ግን ከዳኸኝ ይሄን ያደረከው አንተ ባትሆን ብዬ ተመኘው ያኔ እንደተጠፋፋን ብንቀርም ብያለው... ግን አንድ ነገር እወቅ እኔን ያስከፋኝ ጀርመን መቅረቴ አይደለም ባንተ መከዳቴ እንጂ..." ይሄን ስትናገር የእንባዋን መዝነብ ሳያያት ድምፅዋን ለሰማ በራሱ ግልፅ ነበር... ሀና ለላከችው መልክት ኪሩቤል መልስ ለመስጠት አልዘገየም ነበር ወድያው ፎቶዎች ላከላት... ሀና ይህን ማማን ተሳናት እራሷን መካድ ፈለገች እርቃኗን አልጋ ላይ ከቅዱስ ጋር ሲሳሳሙና ሲጎራረሱ... ያሳያል ፎቶውን አይታ አፍዋን ከፍታ ቀረች በፍፁም ይሄ ሲሆን እራስዋን አታውቅም ከፎቶው ውጪ ስለተፈጠረው ነገርም አታውቅም ! ቅዱስ በቁሟ እንደቀበራት ያህል ተሰማት ጠብቃም ልክ ሲገባ አናቱን በጠርሙስ ብላ ልትገለው ወሰነች ... ሰአታት አለፉ ለኪሩቤል ምንም መልስ ስላጣች ዝምታን መረጠች ቅዱስን ገላ እስር ቤት ብትገባም አይቆጫት ግን ቅዱስ ያን ቀን ቤት አላደረም ከቤት ውጪ አድሮ ስለማያውቅ ብላም አልተጨነቀችም ቀን ሁለት ቀን ሳምንት ሞላው ... ቅዱስ ከቤት ከወጣ 15ኛ ቀን ላይ አንድ ደብዳቤ በሰው ላከላት ደብዳቤውን ገልጣ ማንበብ ጀመረች ... "ሀኒ በጣም ስለማፈቅርሽ ከጎኔ ስትርቂ ማየት ስላልፈለኩ ነው ይሄን ያረኩት ግን ከሆነ ቡሃላ በራሴ አፈርኩ የጅል ስራ እንደነበርም ተረዳሁ ይቅር እንደማትይኝ አውቃለው ሀኒ ግን እመኚኝ ለፍቅር ስል ነው !" ይላል ሀና ይህን ስታነብ በቅዱስ ሳይሆን በራሷ እድል ማልቀስ ጀመረች ... ከዚ ቡሃላ ስልኳን ዘጋችውና ሰፈር ቀየረች ... ልክ በወሯ ደላላጋ ሄዳ በባህር ስደት ለመሄድ መዘጋጀት ጀመረች በቅድሚያ አረብ ሀገር ልትሄድ አስባ ነበር ግን አረብ ሀገር ሲባል በጣም ትጠላ ስለነበር በሊቢያ አቋርጣ ጣሊያን ለመግባት ወሰነች ሀና ምንግዜም ሞት አትፈራም "ወይ ሀብታም መሆን አልያም መሞት ይሻላል!!" ትላለች ... ሀና ለጉዞው ብዙ ገንዘብ ስለተጠየቀች ወደ ሴተኛ አዳሪነቷ ተመልሳ ገንዘብ ማጠራቀም ጀመረች... ያላትን ሸጣና ከምትጠላቸው ሰዎች አንሶላ ተጋፋ እንዲሁም ከሰከሩት ላይ እየሰረቀች 80,000 ብር አጠራቀመች ይሄኔ የምርመራ ወረቀት አስገብታ መሄድ እንደምትችል ተገለፀላት ሀና ይህን ለማድረግ ጤና ጣብያ ሄዳ ስትመረመር ግን ያልጠበቀችው ውጤት ነበር የገጠማት ዶክተሩ ትንሽ ምክር ቢጤ ካስተላለፈ ቡሃላ "ይቅርታ ሀና በጣም አዝናለው ኤች አይ ቪ HIV በደምሽ ውስጥ አለ!" አላት ሀና ይህን ለማመን አይደለም ለመስማት አቅም ስላልነበራት በቁሟ ወደቀች... ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 14 ከ150♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ❥..................🍃⚘🍃...................❥ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,, ••●◉Join us share◉●•• https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

​​😔😔😔😔😔ልናወራቸው እምንፈልጋቸው ብዙ ሰዋች አሉ👦👧፤ግን አናውራቸውም፤ምክንያቱም እነሱ ባይፈልጉስ🤦‍♀እየረበሽናቸው ቢሆንስ🤦‍♂ብለን እየፈራን ልናወራቸው የነበረውን ነገር በልባችን ይዘን🙊ዝም እንላላን፤ግን ምን አለ🙍እንዲሰሙን የምንፈልጋቸው ቢሰሙን👂እንዲኖሩልን እምንፈልጋቸው ካጠገባችን ቢኖሩልን:: https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

​​❝በህይወት መንገድ አታርፍድ..ድንገት ከረፈደብህም አትቅር..ምክንያቱም ስታረፍድ ትቀጣለህ..ስትቀር ግን ታጣለህ።❞ ─━━━━❤️⊱✿⊰❤️━━━━━─ https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

​​​​​. 🌺 🖤ተስፋ_ያጣች_ሴት🖤 🌺 ╰═════════════╯ ​ 💟እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💟 #ክፍል\_12 ...🖊መመረቅ አንዴ ነው እንዲሉ የሀና እድል ስትወለድ ጀምሮ መከራና ስቃይ አቅምና ሁኔታውን እየቀያየረ ያሰቃያታል፤ ያለፈው ፈተናዋን ስታልፍ ሌላ ፈተና ይገጥማታል፤ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ዘመድ በሌለበትና አንድም ሰው በማታውቅበት ቦታ አበደች በርግጥ ሀናን በረንዳ ማደሯንና ብቻዋን መለፍለፏን ላላየ ጤነኛ ትመስላለች ምክንያቱም ጨርቋን አልጣለችም ...ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሀና ፍቅር ይዞት የነበረ እሷ ሴተኛ አዳሪ የነበረችበት ሆቴል በሼፍነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ፀበል ወሰዳት... ይሄኔ ነበር በቅናት መንፈስ ተነሳስተው ሀናን ለእብደት የዳረጓት አብረዋት ይሰሩ የነበሩት ሴቶች እንደሆኑ የታወቀው ... ከ3 ወር ቡሃላ ሀና ትሽሏት ሀዋሳን ለቃ በድጋሚ አዲስ አበባ ተመለሰች ይሄኔ ፀበል ወስዶ እንድትድን የረዳት ቅዱስ አብሯት ነበር ሀና ቅዱስን እንደወንድም ወደደችው እሱ ግን ያፈቅራታል ነገር ግን ፍቅሩን አልገለፀላትም ነበር እሷም ከዛ ቀን ቡሃላ ገላዋን ሽጣ መኖር አልፈለገችም ነበርና በቅዱስ እርዳታ ቤት ተከራይታ መኖር ጀመረች ግን ሁሌ የሱን እጅ ማየት ስላሳፈራት ከእናቷ ቤት አካባቢ የሚገኝ የቡና መልቀምያ ድርጅት ውስጥ ተቀጠረች በዚ ግዜ ስለእናቷም ወሬ ታጠያይቅ ነበር የሰማችው ዜና ግን ሀናን በሰአቱ በጣም ረብሿት ነበር ... እናቷ አፀደ የምታውቀው ልጇ ውጪ ሀገር ማለትም አረብ ሀገር እንደሄደች ነው ይህን እንድታስብ ያሳመናት ደግሞ የሀና እንጀራ አባት መሆኑንም ሰምታለች ... ታድያ አንድ የተባረከ ቀን የሀና ስልክ ጠራ የውጭ ስልክ ነበር አንስታም "ሀሎ" ስትል ይደውላል ብላ ያልጠበቀችው ሰው ነበር ሀና ልቧ ስንጥቅ አለ ይሄ ድምፅ ከረጅም ግዜ በፊት ልክ እንዳሁኑ ስትሰማው ሌላ ስሜት ይሰማት ነበር ኪሩቤል ነው ማመን ተሳናት ኪሩቤልን ባሳለፈቻቸው ግዜያቶች ሁሉ ከ100 ቢያንስ 95ቱን ቀናት ታስበው ነበር ሳታስበው እምባ ተናነቃት ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላም "ሀኒ አፈቅርሻለሁ!! ብዙ ጠብቄሽም ነበር በኔ ምክንያት ፀንሰሽ ... ህይወትሽ እንደተበላሸና ከቤት እንደጠፋሽ ሰምቻለው ግን ፈልጌ አጣሁሽ ይቅር በይኝ እባክሽ..." አለ እንባ እየተናነቀው እንዳወራ ድምፁ ያሳብቅ ነበር ሀናም መናገር አቃታት እንባዋ ያለገደብ ፈሰሰ ምንም መልስ ሳትሰጠውም ዘጋችበት... ቅዱስ ተቀምጦ ያያት ስለነበር ልክ ስልኩ ሲቋረጥ ነገሩን ለማወቅ እንደጓጓ ሁሉ የሀናን አይኖች እየጠራረገ ጠየቃት... ሀናም እንደምንም እራሷን አረጋግታ ስለኪሩቤል ነገረችው ቅዱስም ያፈቅራት ስለነበር በኪሩቤል ቀና ግራ በሚያጋባ አኳኋንም "...ታፈቅሪዋለሽ ማለት ነው?" ሲል ጠየቀ ሃናም የረጠቡ አይኖቿን እያደራረቀች "አላውቅም እኔ የማውቀው አሁን ከጎኔ ቢሆን ደስተኛ እንደምሆን ብቻ ነው" አለች። ኪሩቤል ከሰአታት ቡሃላ ደግሞ ሲደውል ሀናም ተረጋግታ ስለነበር በደምብ አወሩ እሱም ጀርመን እንደሄደ ነገራት ... ከዛ ቡሃላ ሁሌም ይደውላል ልጁን በማስወረዷ እንደተናደደባት ደጋግሞ ይነግራታል ሀና ግን ከሱ ቡሃላ በጌታቸው ስለመደፈሯም ሆነ ስለ ሴተኛ አዳሪነት ህይወቷ ፈፅሞ አልነገረችውም ታማ ፀበል እንዳሻላት ብቻ ነግራው አዝኖ ነበር ... ከዛም ሀናን ፓስፖርት እንድታወጣ ነገራት ሀናም ፓስፖርት አውጥታ ወደ ኪሩቤል ጀርመን ለመሄድ ፕሮሰስ ጀመረች ቅዱስንም የግሉ ቤት እንዲፈልግ ነገረችው ቅዱስ ግን "እስካለሽ አብሬሽ እሆናለው" አላት ሀናም ቅዱስ ውለታ ስለዋለላት እንደወንድሟ ትወደዋለች እንደሚያፈቅራት ግን እስካሁን አልገለፀላትም ይሁንና ቅዱስ የሀናን መሄድ አልወደደውምና እንድትቀር ለማድረግ እንቅፋት ያዘጋጅ ጀመር... ኪሩቤል ስለቅዱስ ምንም አያውቅም ቅዱስ ግን ስለኪሩቤል ሁሌም ይሰማ ነበር ሀናም ይህችን ሀገር ተሰናብታ የምትሄድበትን ግዜ በጉጉት ትጠባበቅ ነበር ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ምሽት ቅዱስ ሀና ኢንባሲ ሄዳ እስክትመጣ ቤቱን አሰማምሮ እራትና የወይን መጠጥ አዘጋጅቶ ጠበቃት ሀናም ይህን ማሰቡ ደስ እያላት በሉ ከዛም ወይን ቀድቶ ሰጣት... ሀና የመጠጥ ልምድ ነበራት ማለትም ቶሎ አሰክርም ነበር ያን ቀን ግን አንድ ብርጭቆ ሳትጨርስ ሰከረች ይህንም አጋጣሚ ቅዱስ ተጠቀመበት... ሲነጋ ሀና እራሷን አሟት ነበር ኪሩቤል ይደውላል ብላ ቅትጠብቀው ሳይደውል ቀረ ያ ቀን እንደምንም ነጋ... ግን ኪሩቤል አልደወለም በሳምንቷ እራሷ ካርድ ሞልታ ደወለች ኪሩቤል ግን "ሁለተኛ እንዳትደውይ" ብቻ ብሎ ዘጋባት... ሀና ይህን ማመን ተሳናት ኪሩ ይህን ለምን አረገ ብላ እራሷን ጠየቀች ግን ምንም መልስ አጣች ሀና ተስፋዋ ባንዴ ድራሹ ጠፋ... ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 13 ከ150♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ❥..................🍃⚘🍃...................❥ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,, ••●◉Join us share◉●•• https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

🎵💋😘🎵 እስኪ ቆንጆ ሙዚቃ ልጋብዛችሁ ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢ @loveferst 👈 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢ @loveferst 👈 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢ @loveferst 👈 💌✽̶»̶̥🌹📥 @mamlove13 🌹»̶̥✽̶💌 🌹📥 @seyajo3 🌹
Hammasini ko'rsatish...
3.13 KB
​​​​​. 🌺 🖤ተስፋ_ያጣች_ሴት🖤 🌺 ╰═════════════╯ ​ 💟እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💟 #ክፍል\_11 ...🖊ሀና በሀዋሳ ለ3 ቀን በረንዳ ላይ ከጎዳና ልጆች ጋር ካደረች ቡሃላ ብርዱንና ፀሀዩን እንዲሁም ርሃቡን ስላልቻለችው የነበራት የመኖር ተስፋ በሙሉ ተሟጠጠባት እናቷን ስታስብ ህይወት ቅፍፍ ትላታለች ለዚም ሀና ይህን ለመርሳት የአልኮል መጠጦችንና አደንዛዥ እፆችን መጠቀም ጀመረች ... ሀና ከድሮም አንድ ልምድ አላት ሁሌም የቀን ውሎዋንና ለየት ያሉ አጋጣሚዎቿን ትፅፋለች ግጥም በጣም ትወድ ስለነበር የመግጠም ችሎታም ነበራት ሀና በዚ በከፋት ግዜም ዲያሪዋን(ማስታወሻ ደብተሯን) ትገልጥና ከኪሩቤል ጋር የነበራትን ግዜና ግንኙነት ታነባቸዋለች ከዛም እንባዎቿን በጉንጮቿ ያለገደብ ታዘንባቸዋለች ከዛም የእንጀራ አባቷን ታስታውሳለች እሱ ሲጫወትባት ከኖረው በላይ ለጌታቸው ያስደፈራት እንድትበቀለው ይገፋፋታል ...ሀና ተቀምጣ ስታስብ ከቆየች ቡሃላ አባቷን ጌታቸውን እና የእንጀራ አባቷን ለመበቀል ጥርሷን ነከሰች... አንድ ቀን ሀና ተቀምጣ ግጥም ስትፅፍ አንዲት ወጣት ሴት ጠራቻትና "ማን ነበር ስምሽ?" አለቻት ሀናም የልጅቷ አጠያየቅ ፈገግ እያስባላት "ሀና" አለች "ይሄን ውበትና አቋም ይዘሽ ጎዳና ላይ በነፃ ከማንም ጋር ከምትጋደሚ ለምን ስራ ላይ አታውይውም" አለች ሀናም በልጅቷ ንግግር በንዴት እየጋለች "ምናገባሽ ስጋደም አየሽኝ እብድ" አለችና ትታት ስትሄድ ለራስሽ ብዬ ነው አለቻት ሀናም በቀስታ በአስፓልቱ ዳር እየሄደች የልጅቷን ሁኔታና ግልፀኝነት አስባ ብቻዋን መሳቅ ጀመረች ሀናን በዛ ቅፅበት ላያት እብድ ትመስል ነበር ... ሀና ከብዙ ሀሳብ ቡሃላ ጎዳና ላይ መለወጥ እንደማይታሰብ እራሷን አሳምና ልጅቷ ልክ ነበረች ስትል ለራሷ ነገረችው ከዛም እዛው ሀዋሳ በአንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ ሰራተኛ እንደሚፈልጉ ሰምታ በአስተናጋጅነት ለመቀጠር ወስና ስትጠይቃቸው ልምድ ከሌላት እንደማይፈልጉ ነገርዋት ሀናም አማራጮች ስላለቁባት እዛው ሆቴል በሴተኛ አዳሪነት ስራ ጀመረች የመጀመርያዎቹ ቀናትና ሳምንታት ለሀና ፈታኝ ነበሩ ... ሀና እራሷን እንድትረሳ በሚል የጀመረቻቸው አጓጓል ሱሶች አሁን ላይ መደበኛ ሆነዋል ሀና ለስራዋ ስትል ትለብሳለች እራሷን ትጠብቃለች ይሄም ሀናን አይቶ ማለፍ ለወንዶች ፈተና ነበር ... ሀናም ከለት ወደለት ስራው ላይ ጠልቃ ገባች ገና የ19 አመት ልጅ ብትሆንም ያላየችው ፈተና ግን አልነበረም ... ሀና ሀዋሳ ከገባች 8 ወር የሴተኛ አዳሪነትን ህይወት ከጀመረች ደግሞ ድፍን 4 ወር ሞላት ሀና ከሆቴሉ ሰራተኞች ጋር በፍቅር ነበር የምትኖረው የሷን አይነት ስራ የሚሰሩት ሁለት ሴቶች ግን ሀናን ጠምደው ያዝዋት ምክንያታቸው ደግሞ የሀና በብዙ ወንዶች መፈለግ ነው ... ይህ በንዲህ እንዳለ የሆቴሉ ባለቤት ሚስቱ አሜሪካ ሄደች ይሄኔ ሰውየው ሀናን ቅምጡ ማድረግ ፈልጎ ጠየቃት ሀና ግን ይህን ማድረግ እንደማትፈልግ ነገረችው ይሄኔ ሰውየው አብረዋት የሚሰሩትን ሴቶች እንዲያሳምኑለት ነገራቸው ሀና ግን አቋሟ አንድ ነበር "እኔም እናት አለችኝ ባልዋ ከሌላ ሴት እንዲማግጥ አልፈቅድም እኔ የማልፈቅደውን ደግሞ ሰው ላይ አላደርግም!!" ትላለች ሴቶቹ ግን ከነሱ እንድትርቅ ስለፈለጉ ብቻ እሷ የሰውየው ብቻ መሆን ካልፈለገች ሌላ ወጥመድ ይዘጋጅላታል ብለው ተመካከሩ... ይህ በሆነ በወሩ ሀና ከአንድ ሀብታም ጋር አዳር ተስማምታ በመጨፈር ላይ ሳሉ ድንገት ተዘረረች እንደምንም አንስተው ሆስፒታል ቢወስዷትም ምንም በሽታ እንደሌለባት ተነገራትና ተመለሰች ይሁን እንጂ ሀና ከቀን ወደቀን እራሷን መጣል ጀመረች ... ልክ ይህ በሆነ በወሯ ሀና አበደች... ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 12 ከ150♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ❥..................🍃⚘🍃...................❥ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,, ••●◉Join us share◉●•• https://t.me/loveferst አሳብ አስታዬት 📥@seyajo3 📥@mamlove13
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር❤️መንገድ

╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━~ ¯ 💃𝐂𝐫𝐚𝐳𝐲💃 Iɴ ᴛʜɪs ᴄʜᴀɴɴᴇʟ ✨New music 🎼 ✨Lovely Profile pic😍 ✨Filling's ✨Love pics ❤ ✨Funny video's 😉 If u like the channel plz share 🙏 ✔️ @seyajo3 @manlove13

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.