cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

AA Airport Customs branch office /አ.አ ኤርፖርት ጉምሩክ

ራዕይ፡- "በ2022 በአገራችን ደረጃዉን የጠበቀ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደር ተገንብቶ ማየት"

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
3 268
Obunachilar
-224 soatlar
-17 kunlar
+1130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በገቢ፣ በወጪና ተላላፊ ዕቃዎች ላይ ስለሚደረግ የጉምሩክ ቁጥጥር 1. የሚከተሉት ዕቃዎች በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ይሆናሉ፡- ➡️ለአገር ውስጥ ፍጆታ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ጉምሩክ ወደብ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የጉምሩክ ፎርማሊቲ ተከናውኖባቸው እስከሚለቀቁ፣ ➡️ወደ ቦንድድ ጉምሩክ መጋዘን የገቡ ዕቃዎች ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ለተፈቀደላቸው ዓላማ እስከሚለቀቁ ➡️ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ዕቃዎች ወደ ጉምሩክ ወደብ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የጉምሩክ ፎርማሊቲ ተከናውኖባቸው እስከሚላኩ ➡️ተላላፊ ዕቃዎች እንዲንቀሳቀሱ ከተፈቀደበት ጊዜ ጀምሮ ወደተፈቀደው መድረሻ ቦታ እስከሚደርሱ ድረስ፣ ➡️ባለቤት የሌላቸው፣ የተተው፣ የተወረሱ ወይም በኮንትሮባንድ የተያዙ ዕቃዎች እስከሚወገዱ ድረስ፡፡ 2.ማንኛውም ሰው ከኮሚሽኑ ፈቃድ ሳያገኝ በተራ ቁጥር 1 በተገለፀው መሠረት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያሉ ዕቃዎች ወደ ተከማቹበት ሥፍራ መግባት፣ ዕቃዎችን መክፈት ወይም ማናቸውንም ተግባር በዕቃዎቹ ላይ መፈፀም አይችልም፡፡ ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 20/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ አዋጅ 859/2006
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
የጉዞ ዕቃ ክምችትን በሌላ መንገድ አገልግሎት ላይ እንዲውል ስለማድረግ ወደ ጉምሩክ ክልል ውስጥ በገባ አውሮፕላን ወይም ባቡር ላይ የሚገኝ የጉዞ ዕቃ ክምችት፡- ➡️አግባብነት ያላቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ፎርማሊቲዎች መሟላት እንደተጠበቀ ሆኖ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሊለቀቅ ወይም ሌላ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሊፈጸምበት ወይም ➡️ ኮሚሽኑ አስቀድሞ ሲፈቅድ ዓለም አቀፍ ጉዞ ወደ ሚያደርግ ሌላ አውሮፕላን ወይም ባቡር እንደየአግባቡ እንዲተላለፍ ሊደረግ ይችላል። ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 20/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ አዋጅ 859/2006
Hammasini ko'rsatish...
የጉዞ እቃ ክምችት አቅርቦት 1. ወደ ውጭ አገር መጨረሻ መዳረሻ የሚጓዝ አውሮፕላን ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆኖ የሚከተሉትን የጉዞ ዕቃ ክምችቶች ጭኖ ለመሄድ ይችላል፡- ➡️ ኮሚሽኑ የመንገደኞችንና የአውሮፕላኑን ሰራተኞች ቁጥር፣ በረራው የሚሸፍነውን ርቀት እንደዚሁም በአውሮፕላኑ ውስጥ አስቀድሞ የሚገኘውን የጉዞ ዕቃዎች ክምችት መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ ነው ብሎ የሚወስደው የጉዞ ዕቃዎች ክምችት፤ ➡️ በአውሮፕላኑ ውስጥ አስቀድሞ የሚገኘውን የጉዞ ዕቃዎች ክምችት ግምት ውስጥ በማስገባት ለአውሮፕላኑ በረራና ጥገና አገልግሎት ያስፈልጋል ተብሎ የሚገመት መጠን ያለው የጉዞ ዕቃዎች ክምችት፡፡ 2 ወደ ጉምሩክ ክልል የገባ አውሮፕላን በጉምሩክ ክልል ውስጥ ለመጨረሻ መዳረሻ ጉዞው የሚያስፈልገውንና የተጓደለበትን የጉዞ ዕቃ ክምችት ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ማሟላት ይችላል። 3. ወደ ጉምሩክ ክልል የገባ አውሮፕላን በጉምሩክ ክልል ውስጥ በሚቆይበት ወቅት ለሚኖረው ፍጆታ የሚያስፈልገው የጉዞ ዕቃዎች ክምችት ይዞ እንዲገባ በሚፈቀድለት ተመሳሳይ አኳኋን እንዲቀርብለት ኮሚሽኑ ይፈቅድለታል፡፡ 4. ኮሚሽኑ ከጉምሩክ ክልል የሚወጣ አውሮፕላን የጫነውን የጉዞ ዕቃዎች ክምችት በሚመለከት ለጉምሩክ ቁጥጥር የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ብቻ የያዘ ዲክላራሲዮን እንዲያቀርብለት ሊያዝ ይችላል። ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 20/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ አዋጅ 859/200
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
በሚገባ አውሮፕላን ወይም ባቡር ላይ የተጫነ የጉዞ እቃ ክምችት 1. ወደ ጉምሩክ ክልል በገባ አውሮፕላን ወይም ባቡር ላይ የተጫነ ለመንገደኞችና ለማጓጓዣው ሠራተኞች ፍጆታ እንዲውል የተጫነ ዕቃ ወይም ለማጓጓዣው አገልግሎት አሰጣጥ ወይም ጥገና አስፈላጊ የሆነ ዕቃ ከማጓጓዣው ሳይራገፍ እስከቆየ ድረስ ቀረጥና ታክስ አይከፈልበትም፡፡ 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 ቢኖርም በዓለም አቀፍ የባቡር ማጓጓዣ ላይ ለመንገደኞችና ለባቡሩ ሠራተኞች ፍጆታ እንዲውል የተጫነ እቃ፡- ➡️ የተገዛው ባቡሩ ጉዞ ካቋረጣቸው አገራት ከሆነ፣ ➡️ በተገዛበት አገር ተከፋይ የሆነው ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ከሆነ ቀረጥና ታክስ አይከፈልበትም፡፡ 3. ኮሚሽኑ በአውሮፕላኑ ወይም በባቡሩ ላይ ስለተጫነው የጉዞ ዕቃ ክምችት የተለየ ዲክላራሲዮን እንዲቀርብ መጠየቅ የለበትም፡፡ 4. አውሮፕላኑ በጉምሩክ ክልል ውስጥ በሚገኝ አንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ አውሮፕላን ማረፊያ የሚያርፍ ከሆነ በአውሮፕላን ማረፊያው ለሚቆይበትና ከአንዱ ወደ ሌላው ማረፊያ በሚያደርገው በረራ ወቅት ለፍጆታ የሚያስፈልገውን የጉዞ ዕቃ ክምችት ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ እንዲያሟላ ይፈቅድለታል፡፡ 5. አጓጓዡ ዕቃውን ላልተፈቀደ ዓላማ እንዳያውል ለመከላከል እንደ አስፈላጊነቱ ክምችቱን መቆለፍን ጨምሮ አግባብ ያላቸውን እርምጃዎች እንዲወስድ ኮሚሽኑ ሊያዘው ይችላል፡፡ 6. ኮሚሽኑ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አውሮፕላኑ ወይም ባቡሩ በጉምሩክ ክልል በሚቆይበት ወቅት የጉዞ ዕቃ ክምችቱ ተራግፎ በሌላ ቦታ እንዲቆይ ለማዘዝ ይችላል፡፡ ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 20/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ አዋጅ 859/2006
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
የወጪ ዕቃ ትራንዚት ከአገር ዉስጥ ወደ ዉጭ አገር ለሚላክ ዕቃ የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት ላኪዉ ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅርብ አለበት፤ ሀ) የወጪ ዕቃ የትራንዚት ዲክላራሲዩን (EX8) ለ) እንደ አስፈላጊነቱ የተቆጣጣሪ መ/ቤት ፈቃድ፣ የደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ ትራንዚት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 168/201
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
የሀገር ውስጥ ትራንዚት 1/ ከአንድ የጉምሩክ ጣቢያ ወደ ሌላ ጉምሩክ ጣቢያ ለሚተላለፍ ዕቃ የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት አሰመጪዉ ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፤ ሀ) ትራንዚት ዲክላሬሽን (IM8) ፣ ለ) የማጓጓዣ ሰነድ፣ ሐ) ዋስትና፣ የደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ ትራንዚት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 168/2012
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
የተላላፊ ዕቃ ትራንዚት 1/ አገር አቋርጠዉ ወደ ሌላ አገር የሚተላለፍ የትራንዚት ዕቃ ፈቃድ ለማግኘት አስመጪዉ ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፤ ሀ) ዋስትና፣ ለ) ትራንዚት ዲክለሬሽን (IM8) ፣ ሐ) ኮሜርሻል ኢንቮይስ፣ መ) የማጓጓዣ ሰነድ፣ ሠ) ዕቃዉ ከሚደርስበት አገር የተሰጠ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ 2/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ቢኖርም ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የእርዳታ ድርጅቶች ለተላለፊ ዕቃ የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸዉ፤ ሀ) ዋስትና፣ ለ) የማጓጓዣ ሰነድ፣ ሐ) ትራንዚት ዲክለሬሽን (IM8) የደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ ትራንዚት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 168/2012
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
የገቢ ዕቃ ትራንዚት 1/ በዩኒ ሞዳል ትራንስፖርት ተጓጉዞ ወደ ሀገር ለሚገባ ዕቃ በአገር ዉስጥ ካሉ የጉምሩክ ጽ/ቤቶች የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት አስመጪዉ ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፤ ሀ) የትራንዚት ዲክላራሲዮን (IM8) ፣ ለ) ለቀረጥና ታክሰ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ወይም የቀረጥ ነፃ መብት ደብዳቤ፣ ሐ) የማጓጓዣ ሰነድ፣ መ) ዕቃዉ በኮንቴነር የሚጓጓዝ ከሆነ የኮንቴነር ዋስትና 2/ በዩኒ ሞዳል ትራንስፖርት ተጓጉዞ ወደ ሀገር ለሚገባ ዕቃ በጎረቤት አገር ከሚገኝ የጉምሩክ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይም እንደ ሁኔታዉ በጎረቤት አገር ጉመሩክ የትራንዚት ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል 3/ በጎረቤት አገር ከሚገኝ የጉምሩክ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለሚሰጥ የትራንዚት ፈቃድ አስመጪዉ ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፤ ሀ) ኮሜርሻል ኢንቮይስ፣ ለ) የትራንዚት ዲከላራሲዮን (IM8) ሐ) የማጓጓዣ ሰነድ፣ መ) ለቀርጥና ታክስ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ወይም የቀረጥ ነፃ መብት ደብዳቤ፣ 4/ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት በትራንዚት ተጓጉዘዉ ወደ ሀገር ለሚገቡ ዕቃዎች የመልቲ-ሞዳል ትራንስፖርት ኦፕሬተሩ አጠቃላይ ዋስትና ለጉምሩክ ማስያዝ አለበት፡፡ 5/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) እንደተጠበቀ ሆኖ በጎረቤት አገር ጉምሩክ የተሰጠ የትራንዚት ዲክላራሲዮን (IM8) እና የመንገድ ወረቀት (T1) በመግቢያ በር ለሚገኘ ጉምሩክ መቅረብ አለበት፡፡ የደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ ትራንዚት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 168/2012
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.