ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Ko'proq ko'rsatish609
Obunachilar
-124 soatlar
-37 kun
-1130 kun
Postlar arxiv
"እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ።"
ለሰንበት ት/ቤታችን የጥምቀት ዘማርያን በሙሉ
የጥምቀት በዓል ላይ ከጥምቀት ዘማርያን ምን ይጠበቃል?
ቅድመ በዓል
👉ጽ/ቤቱ ባስተላለፈው መሠረት ጸጉር መስተካከል፤ ጥፍር መቆረጥ ፤ የእጅና የጆሮ ጌጥ አለማድረግ፤ የዓይን እና ሌሎች ማስዋቢዎችን አለመጠቀም የግል ንጽህናን መጠበቅ(ሰውነትን መታጠብ)፤ ከውኃ ውጭ አለመጠጣት!
👉ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ አለባበስ መልበስ
👉ልብሰ ስብሐቱ ካጠረን ከረዘመው ጋር መቀያየር
👉ልብሰ ስብሐቱን ከመልበስ በፊት አቡነ ዘበሰማያት መድገም
👉የእኛን ልብሰ ስብሐት ለሌላ ሰው ሰጥተን ማዘመር አይቻልም። መዘመር ካልቻልን ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ እና መመለስ።
ጊዜ በዓል
👉በሥርዓት ሆኖ መዘመር
👉ያለ አስተባባሪው ፈቃድ በዝማሬ የጀመሩበትን ቦታ አለመቀየር እና አቋርጦ አለመውጣት
ድኅረ በዓል
👉መንገድ ላይ እየተራመዱ ልብሰ ስብሐት ማውለቅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
👉ጸበል ጸዲቅ ከተዘጋጀበት ቦታ ምግብ ከበላን በኋላ ንግግራችን መጠን አድርገን፣ ያለመንጓተት እና ያለመላፋት በረከታችንን ወደ ቤታችን ይዘን መሄድ
👉ከዝማሬ በኋላ ልብሰ ስብሐት ይዞ መጠጥ መጠጣት፣ መደባደብ፣ ያልተገባ ንግግር መናገር ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
👉ስንቀመጥም፣ ስንነሳም፣ ስንሄድም፣ ስናስቀምጥም ልብሰ ስብሐቱን በተቻለን አቅም እናክብረው።
ታቦተ ሕጉ ከመንበሩ
ጥር 10፦ 8:00 ስለሚወጣ 6:00 ሰዓት ተገኙ።
ጥር 11፦ 4:00 ስለሚወጣ 3:00 ሰዓት ተገኙ።
ጥር 12፦ 4:00 ስለሚወጣ 3:00 ሰዓት ተገኙ።
ቅዱስ እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይቀበልልን። የበረከት በዓል ያድርግልን።
ከተራ ምንድን ነው?
ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
መልካም የከተራ በዓል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ጥር ፲ /10/በዚችም እለት አባ ታውብንጦስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ አባ ታኡና በሚባል በሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቤት አደገ እርሱም የምንኩስናን ልብስ አለበሰው። መንፈሳዊ እውቀትንና ኃይል እንደተሰጠው አይቶ ከእስክንድርያ አገር ውጪ ስሙ ጤናዲራን በሚባል ቦታ ኤጲስቆጶስነት ሹሞ የገዳም አበመኔት አደረገው በእርሱ ስር ያሉ መነኵሳትም ሰባት መቶ ናቸው። ከዚህም በኋላ ከእርሱ ጋር ላሉ መነኰሳት አለቃ የሆነ ኤጲስቆጶስ ታውብንጦስ ከከሀዲ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ስለሆነው። ሁከት በሰማ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ሲሐት ገዳም ሒዶ እግዚአብሔርን ከምትፈራ ከአንዲት ድንግል ዘንድ ተቀመጠ። በእርሷ ቤትም ብዙ ዘመናት ኖረ በመጀመሪያ ወደርሷ በገባ ጊዜ ግን ንጉሱን ስለመፍራት ጣዖትን ስታመልክ አገኛትና የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳት። ከዚያም ተርኑጥና መርኑስ ወደሚባሉ ገዳማት ሔደ የአብያተ ክርስቲያናትን ወሬ ይሰማ ዘንድ ፈልጎ በፆም በጸሎት ሌሊትም በመትጋት እያገለገለ በአንዲት ገዳም ውስጥ ሁለት ሶስት ቀን ተሰውሮ ያድር ነበር። የመንፈስ ቅዱስም ፀጋ በላዩ እንዳደረ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን እንዳደረገ ከወንበዴዎችና ከዓመፀኞች ብዙዎችን መነኰሳትን አድርጎ ለክርስቶስ ወደ መገዛት እስከ መለሳቸው ድረስ መነኰሳቱ ሁሉም መሰከሩለት። ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ የሚሞትበትን ቀን አወቀ ልጆቹንም የክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ አስተማራቸው ወዲያውኑ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ጥር ፱ /9/በዚች ቀን የከበረ አባት አባ አብርሃም አረፈ። በዚያንም ጊዜ አባ አብርሃም ሔደ በአስቄጥስ በረሀ ውስጥ ተጕዞ በአባ ዮሐንስ አበ ምኔትነት ዘመን ወደ አባ መቃርስ ገዳም ደረሰ ወደርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ገባ ተወዳጅ ልጅንም ሆነለት። በጎ ተጋድሎንም ጀመረ በአንዲት ሌሊትም ራዕይን አየ የበዓቱ ጣሪያ ተሰነጠቀ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ ወደርሱ ሲወርድ አየው ኪሩቤልም ያመሰግኑት ነበር እርሱም ፈርቶ ተንቀጠቀጠ ፈጥኖም ሰገደ ጌታችንም ባረከውና በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ። ጌታችንም የወረደባት በቤቱ ጣሪያ የተሠነጠቀችው ምልክት ሁና እስከ ዛሬ በመታሰቢያነት አለች እርሷም ለመንፈሳዊ አባቱ ለአበ ምኔቱ አባ ዮሐንስ መኖሪያ ቅርብ ናት እርሷም በግቢግ ትባላለች ። የእግዚአብሔርም መልአክ ሁልጊዜ ይጐበኘዋል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥለታል ያስገነዝበዋልም። ከዚህም በኋላ አባ አብርሃም ወደ ደብረ ኀርዮን ሔደ በዚያም አባ ገዐርጊን አግኝቶት ወደ አስቄጥስ ገዳም ከእርሱ ጋር ወሰደውና እስከ ዕረፍታቸው ጊዜ በዚያች በዓት ኖሩ። አበ ምኔቱ አባ ዮሐንስም በአረፈ ጊዜ በአባ አብርሃም ላይ ሰይጣን ታላቅ ደዌ አምጥቶበት ዐሥራ ስምንት ዓመት በዚያ ደዌ ውስጥ ኖረ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የጌታችንን ሥጋና ደም ያቀብሉት ዘንድ ወንድሞችን ለመናቸው ከተቀበለም በኋላ መንፈሳዊ አባቱ አባ ዮሐንስ ወደርሱ መጥቶ እነሆ ወደ ታላቅ ሠርግ እግዚአብሔር ጠርቶሃል አለው። ከዚህም በኋላ ዕድሜው ሰማንያ ዓመት ሁኖት በሰላም አረፈ በዓታቸውም እስከ ዛሬ የታወቀች ሁና ትኖራለች። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
❤ የዚህ አባት እንድራኒቆስ ገድሉ ግን እጅግ ያማረ ነበር እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥር8 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ከዓመተ ሰማዕታት ሦስት መቶ አርባ ሰባት እስላሞች በግብጽ ከመንገሣቸው በፊት በመንበረ ሢመቱ ሰባት ዓመት ኖረ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 8 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለቅዳሴ_ቤትከ_በእደ_ብንያሚን_ዘኮነ። የማነ አምላክ ምስሌሁ እንዘ ይቀብዕ ሜሮነ። ውሳጤ መቅደስከ ዛቲ #መቃርዮስ_አቡነ። ኢይባእ በትእግት ኪሩብ ወሰነ። ዘቦ ትዕቢተ ወዘቦ ህልያነ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥር_ 8።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ። የማነ እግዚአብሔር አልዐለተኒ። የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ"። መዝ 117፥15-16። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 4፥5-14፣ 1ኛ ጴጥ 5፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥36-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥39-52። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የነቢዩ ቅዱስ ሚክያስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ሚክያስ ለመታሰቢያ በዓል፣ #የአባ_መቃርስ_ቤተ_ክርስቲያን በከበረና በተመሰገነ በእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት #በአባ_ብንያሚን እጅ ለከበረችበትና ለእስክድርያ ሠላሳ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ብንያሚን_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ ፦ከእስክንድርያ ሠላሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_እንድራኒቆስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ነቢዩ_ቅዱስ_ሚክያስ፦ የዚህም ነቢይ ከታናሽነቱ ጀምሮ አካሔዱ መልካም ሆነ ስለ ሥራው ማማርና ስለ ጽድቁ ሕዝቡ ሁሉ ያደንቁታል ያከበሩታል ሚክያስም ይሉታል ትርጓሜውም መልአክ ነው ማለት መልኩ እጅግ ያማረ ነውና የሚናገረውም ትንቢት እንደተናገረው ይሆናል የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጾለት ያነጋገረው ነበር ሕዝቡ ግን ያንን መልአክ እያዩትም ድምፁን ግን ይሰማሉ ከእርሳቸውም ያደላቸው የሚያዩት አሉ በመሳፍንት መጽሐፍ እንደተጻፈ። በጎልማሳነቱም አርፎ በአባቶቹ ቦታ ተቀበረ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና እኛን በነቢዩ ቅዱስ ሚክያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ይሁን አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአባ_መቃርስ_ቤተ_ክርስቲያን_በአባ_ብንያሚን_እጅ_መክበር፦ ከዚህም በኋላ መቆቅዝ ከሚባል ዐላዊ መለካዊ በአባ ብንያሚን ላይ መከራ ደረሰበት አባ ቢንያሚንም ሸሽቶ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ ዐሥር ዓመትም እስኪፈጸም በዚያ ኖረ ከዚህም በኋላ ያን ዓላዊ መቆቅዝን እግዚአብሔር አጠፋው ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ ጸጥታ ሰላም ሁኖ አባ ቢንያሚንም ወደ መንበረ ሢመቱ ተመለሰ የአስቆጥስ ገዳም ሽማግሎችና መምህራን ወደርሱ መጡ ወደርሳቸውም ሒዶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን እንዲአከብርላቸው ለመኑት እርሷም የከበረ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ናት። በታላቅ ደስታም ተነሥቶ ከእርሳቸው ጋር ሔደ የቤተ ክርስቲያኒቱንም መባረኪያ ጸሎት ጀመረ።
❤ መሠዊያውንም በሜሮን ሊቀባ በጀመረ ጊዜ የክብር ባለቤት የጌታችን እጅ ከእርሱ ጋር ስትቀባ አየ ከታላቅ ፍርሀት የተነሣ በግምባሩ ፍግም ብሎ ወደቀ። ከኪሩቤልም አንዱ አነሣው እንዲህም አለው "ተነሣ አትፍራ ልዩ የሆነውን ሥርዓት ለዚህ ቦታ ጻፍ ይህ የእግዚአብሔር ምሥጢር የሚፈጸምበት ነውና ማንም በትዕቢት ወይም መማለጃ በመስጠት እንዳይገባ በውስጡ በሚገባ ከሚሾም በቀር የሚደፍርና በውስጡ ከንቱ ነገርን የሚናገር አይኑር የእግዚአብሔር መመስገኛ ቤቱ ነውና ይህም ሥርዓት በዚህ ቦታ እስከ ዘላለሙ የተሠራ ይሆናል። እነሆ ዘመን ይመጣል የአባቶችንም ትእዛዝና ሥርዓት ያፈርሳሉ ይህም የከበረ ቦታ እንደ መሣለቂያ ቦታ ይሆናል"።
❤ አባ ብንያሚንም "ይህች የእግዚአብሔር ቤት የሰማይ ደጅ ናት" አለ ይህንንም ከኪሩብ ጋር ሲነናገር ከቤተ ክርስቲያኒቱ በስተምሥራቅ ተመለከተ አንድ መልኩ የሚያምር ጽሕሙ የረዘመ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት የሚያበራ ሽማግሌ አየ። ለአባ ብንያሚንም ደስ አሰኘውና በልቡ እንዲህ አለ "ከኤጲሰሰቆጶሳት አንዱ ቢሞት በርሱ ፈንታ ይህን ሽማግሌ እሾመዋለሁ"። ኪሩብም እንዲህ አለው "ብንያሚን ሆይ ይህን አባት መቃርዮስን ኤጲስቆጵስን ታደርገዋለህ?"። እርሱ "የሊቃነ ጳጳሳት አባታቸው ነውና ዛሬ ከልጆቹ ጋር ደስ ይለው ዘንድ መጥቷልና ከልጆቹም መንፈሳዊ ሹመት የሚሾም ወይም አለቃ የሚሆን አይታጣም ከገዳማቱም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ አይታጣም"።
❤ አባ ብንያሚንም "ልጆቹ ብፁዓን ናቸው" አለ ኪሩብም እንዲህ አለ "ብፁዓንስ የሚባሉ ትእዛዞቹን ጠብቀው ፍለጋውን ቢከተሉ እነርሱ ከእርሱ ጋር አሁን በአለበት ክብር ውስጥ ይሆናሉ ትእዛዞቹን ቢተላለፋ ግን ከእርሱ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖራቸውም"። አባ ብንያሚንም ኪሩብን እንዲህ አለው "ጌታዬ ሆይ በዚህ ነገር በልጆቼ ላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አትናገር ነገር ግን በሰብል ውስጥ አንዲት ቅንጣት የተረፈች እንደሆነ እግዚአብሔር በውስጥዋ በረከቱን ያደርጋል። እንዲሁም የፍቅር ቅንጣት በውስጣቸው የተገኘ እንደሆነ እግዚአብሔር ከመንግሥቱ እንደማያርቃቸው እኔ አምናለሁ"።
❤ ከአረጋዊው አባ መቃርስ ርኅራኄ የተነሣ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን አደነቀ መልአኩ ኪሩብ እንዳዘዘውም ያንን ሥርዓት ጽፎ ለዘወትር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረው። ዕድሜው በደረሰ ጊዜ ዕረፍቱ በዚች ቀን ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው እንዲሁም ሆነለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቢንያሚን በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_እንድራኒቆስ፡- ይኽም አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሰባተኛ የሆነ ነው። ይህ አባት የሚራራ አዋቂ ሆነ እርሱ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ተምሮአልና እርሱም ለእስክንድር ገዥ የአጎቱ ልጅ ነውና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሊቃነጳጳሳት እንደሚያደርጉት በገዳም አልኖረም፤ ይልቁንም ስለቤቱና ስለክብሩ ታላቅነት በእስክንድርያ ባለው ቤቱ የሚኖር ሆነ፡፡ እርሱም የተሾመው ሕርቃል በነገሠ በ10 ዓመት ከእስክንድር ዘመነ መንግሥት በ933 ዓመት ነው፡፡ በሹመቱም ወራት ፀሐይን የሚያመልክ የፋርስ ንጉሥ ክስራ ተነሣና የሶርያንና የፍልስጤምን ከተሞች ወርሮ ዘረፋቸው፡፡ ወደ ግብጽም መጥቶ እስክንድድርያ ከተማ ደረሰ፡፡ በዙሪዋ በመነኮሳት የተሞሉ ሰባት መቶ ገዳማት ነበሩ፡፡ እነርሱም ገንዘብ ያላቸው በተድላ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ ስለዚህም በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ሥልጣንን ሰጥቶት ገዳማቱን አፈረሰ፡፡ እነርሱንም ሸሽተው ካመለጡት በቀር ሁሉንም ገደላቸው፡፡ ገንዘባቸውንም ሁሉ ማረከ፡፡
❤ የእስክንድርያ ሰዎችም ንጉሥ ክስራ ያደረገውን ባዩ ጊዜ የከተማውን በር ከፈቱለት፡፡ እርሱም "ይህችን አገር በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ አታፍርሳት፣ በውስጧ ያሉትን ብርቱዎች ግደላቸው-ዐመፀኞች ናቸውና" እንደሚለው በሕልሙ አየ፡፡ በዚህም ጊዜ የሀገሩን ንጉሥ ይዞ ካሠረው በኋላ ለሀገሩ ሰዎች "በጦር ሠራዊት አደራጃቸዋለሁና ከ18 ዓመት ጀምሮ ያሉትን ብርታት ያላቸውንም ሁሉ ሰበስቡልኝ፣ ለእያንዳንዳቸው ደመወዛቸውን 20 የወርቅ ዲናር እከፍላለሁ" አላቸው፡፡ ሕዝቡም ሁሉ እውነት ወርቅ የሚቀበሉ መስሏቸው 8 ሺህ ብርቱዎችን ቆጥረውና መዝግበው በሰጡት ጊዜ ንጉሡ ክስራ ሁሉንም በሰይፍ ገደላቸው፡፡ ወደላይኛው ግብጽ በመሄድም ኒቅዮስ ደርሶ ሰባት መቶ በሥራቸው ክፉ የሆኑ መነኮሳትን በሰይፍ ገደላቸው፡፡ የሮም ንጉሥ ሕርቃልም የፋርሱ ንጉሥ ክስራ ያደረገውን በሰማ ጊዜ ሠራዊቱን ሰብስቦ መጥቶ ንጉሥ ክስራን ከነሠራዊቱ ሀገሩንም ጭምር አጠፋቸው፡፡
ጥር ፯ /7/በዚች ቀን የከበረ አባት የሮሜ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት ሶል ጴጥሮስ አረፈ። ይህንንም አባት ስለ ተጋድሎው ገናናነት ስለ አገልግሎቱም ስለ ትሩፋቱ ስለ አዋቂነቱና ስለ ደግነቱ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ መልጥያኖስ ከአረፈ በኋላ መርጠው ሊቀ ጵጵስና በሮሜ ሀገር ላይ ሾሙት። በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የዕሌኒ ልጅ የሆነ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ከከሀድያን ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ምክንያት ገና አልተጠመቀም ነበርና የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ የእግዚአብሔርን አብያተ ክርስቲያናት ሠራቸው። የዚህም አባት የሶል ጴጥሮስ ገድሉ እጅግ ብሩህ የሆነ ነው እርሱ ሁል ጊዜ ሕዝቡን ያስተምራቸዋልና ከልቡናቸውም ከሰይጣን የሆነ ጥርጥርንና ክፉ ሐሳብን ያርቃል። ከእነርሳቸው ሥውር የሆነውንም የመጻሕፍት ምሥጢር ተርጕሞ ያስገነዝባቸዋል። አይሁድንና ዮናናውያንን ሁል ጊዜ ይከራከራቸው ነበር ከእርሳቸውም ብዙዎችን መልሶ ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ስሙም በምእመናን ዘንድ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሆነ። እግዚአብሔርን ስለ ማወቅና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ብዙ ድርሳናትን ደረሰ። በተሾመ በሰባተኛውም ዓመት ስለ አርዮስ በኒቅያ ከተማ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የከበሩ አባቶች የአንድነት ስብሰባ ሆነ ይህም አባት ሶል ጴጥሮስ ከእርሳቸው አንዱ ነበር አርዮስንም ከተከታዮቹ ጋር ረገመው አውግዞም ለየው። በሹመቱም ዐሥራ አንድ ዓመት ኖረ መልካም ተጋድሎውን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፯ (7) ቀን።
❤ እንኳን #ለአጋዕዝተ_ዓለም_ለቅድስት_ሥላሴ የሰናዖር (የባቢሎንን) ቋንቋቸው ለደባለቁበትና የሠሩት ግንብ ላፈረሱበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዘፍ11፥1-9)፣ ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀት ላጠመቀው ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳስ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ሶል_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት #ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ ለመታሰቢያው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰሎሞን፣ #ከጎርጎርዮስ_ከማርቆስ_ከአትያኖስ_ከሉያ፣ #ከመልይን_ከሱስዮስና_ከማርትይ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳስ_አባ_ሶል_ጴጥሮስ፦ ይህንንም አባት ስለ ተጋድሎው ገናናነት ስለ አገልግሎቱም ስለ ትሩፋቱ ስለ አዋቂነቱና ስለ ደግነቱ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ መልጥያኖስ ከዐረፈ በኋላ መርጠው ሊቀ ጵጵስና በሮሜ አገር ላይ ሾሙት። በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የዕሊኒ ልጅ የሆነ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ከከሀድያን ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ምክንያት ገና አልተጠመቀም ነበርና የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ሠራላቸው።
❤ የዚህም አባት ሶል ጴጥሮስ ገድሉ እጅግ ብሩህ የሆነ ነው እርሱ ሁል ጊዜ ሕዝቡን ያስተምራቸዋልና ከልቡናቸውም ከሰይጣን የሆነ ጥርጥርንና ክፉ ሐሳብን ያርቃል። ከእነርሳቸው ሥውር የሆነውንም የመጻሕፍት ምሥጢር ተርጒሞ ያስገነዘባቸው። አይሁድንና ዮናናውያንን ሁል ጊዜ ይከራከራቸው ነበር ከእርሳቸውም ብዙዎችን መልሶ ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ስሙም በምእመናን ዘንድ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሆነ። እግዚአብሔርን ስለ ማወቅና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ብዙ ድርሳናትን ደረሰ።
❤ በተሾመ በሰባተኛውም ዓመት ስለ አርዮስ በኒቅያ ከተማ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የከበሩ አባቶች የአንድነት ስብሰባ ሆነ ይህም አባት ሶል ጴጥሮስ ከእርሳቸው አንዱ ነበር አርዮስንም ከተከታዮቹ ጋር ረገመው አውግዞም ለየው። በሹመቱም ዐሥራ አንድ ዓመት ኖረ መልካም ተጋድሎን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥር7 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሶል ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር7 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ጴጥሮስ_ሶል። መጥምቀ #ቈስጠንጢኖስ ንጉሥ ከሣቴ መስቀል። መዋዕለ ዕብሬትከ ኮነ ዕብሬተ ርትዕ ወሣህል። እስመ ተቀጥቀጠ ዳጎል ወወድቀ ቤል። በከመ ቀዳሜ ኢሳይያስ ይብል"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥር_7።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ። ወበቃለ ለእግዚአብሔር ፀንዐ ሰማያት። ወእስትንፋሰ አፉሁ ኵሉ ኃይሎሙ"። መዝ 32፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 28፥16-20።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 2፥10-16፣ 1ኛ ዮሐ 2፥25-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 22፥7-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥21-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቅድስት ሥላሴ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፮ (6) ቀን።
❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለንዑስ_በዓል ለአንዱ #ለግዝረት_ለኢየሱስ ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #በሥጋው_ወደ_ቤተ_ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ ልሳነ ዕረፍት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ" ብሎ እንደተናገረ። ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር ጌታችን ግን ግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን።
❤ የከበረ ወንጌል "ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት" እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን "እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ" አለችው። ዮሴፍም ሔዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው "እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቆ ያዙት" አላቸው። ሕፃን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልሶ እንዲህ አለው "ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆች መድኃኒት ይሆናል"።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችን ማርያም "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው" አላት።
❤ ሕፃኑም ለዚያ ባለሙያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው "እኔ ነኝ ትገዝረኛለህ ወይስ ተውክ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ" ያም ባለሙያ "የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?" አለው ሕፃን ጌታችንም "አብርሃም፣ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው" ባለሙያውም "እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና" አለው። በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ "አባት ሆይ ለአብርሃም፣ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ" አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች።
❤ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማሕፀን እንደ መውጣቱ የጌታችን ግዝረቱ የማይመረመር ሆነ እንዲሁ ወደ ሐዋርያት በተዘጋ አዳራሽ መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እንዲሁ እንደ ፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ። አዳምንና ልጆቹን ያድናቸው ዘንድ በፈቃዱ ከጐኑ በመስቀል ላይ የሚፈሰው ደምና ውኃ ካልሆነ በቀር ብዙም ሆነ ጥቂት ሊሆን አይችልም እርሱ በፈቃዱ ሕጉ እንዲፈጸም አስቀድሞ አዘዘ እንጂ።
❤ ያም ባለሙያው ገራዥ ይህን ተአምር ባየ ጊዜ የሕፃኑንም ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ሦስት ጊዜ ሰገደና "በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ" አለው። ከዚህም በኋላ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተአምራቱ ያየውንና የሰማውን እየተናገረ ወደ ቦታው ሔደ ለእርሱም ለጌታችን ከቸር አባቱ ጋራ ማሕየዊ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋራ ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 6 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወይከውን ቡሩከ ስሙ ለዓለም። እምቅድመ ፀሐይ ሀሎ ስሙ። ወይትባረኩ ቦቱ ኵሎሙ አሕዛብ ምድር። መዝ 71፥17-18። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥8-22።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ 104፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 15፥8-14፣ 2ኛ ጴጥ 2፥1-9፣ የሐዋ ሥራ 7፥2-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 4፥24-33። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የኢየሱስ ክርስቶስ በዓል፣ የነቢዩ ኤልያስ የዕረገት በዓል፣ የጻድቁ ኖኅ የዕረፍት በዓል፣ የቅዱስ ባስልዮስ የዕረፍት በዓልና የቅዱስ አርሴማ የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
ጥር ፭ /5/
በዚች ቀን በከሀዲው ዑልያኖስ ዘመን የከበረ አውስግንዮስ ምስክር ሁኖ ሞተ።
ይህም ቅዱስ አውስግንዮስ እድሜው መቶ ዐሥር ዐመት እስከ ሆነው ከቈስጠንጢኖስና ከልጆቹ ዘመነ መንግሥት በኋላ እስከ ከሀዲው ዑልያኖስ ዘመን ኖረ።
በአንዲት ዕለትም በአንጾኪያ ከተማ በአደባባይ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲመላለስ ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አግኝቷቸው ሊአስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላም ሊያአደርግ ወዶ አስታረቃቸው በመታረቃቸውም ደስታ አደረጉ እርሱ የከበረ አረጋዊ ሰው ነውና።
ከዚያም አንድ ክፉ ሰው ወደ ንጉሥ ዑልያኖስ ሒዶ ነገር ሠራበት እንዲህም አለው አውስግንዮስ በራሱ ፈቃድ ገዥና ፈራጅ ዳኛ ሆነ። ንጉሥም ይህን ቅዱስ ወደርሱ አቅርቦ ገሠጸው ገዥና ፈራጅ ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማነው አለው።
የከበረ አውስግንዮስ መልሶ ነፍስህ በእጁ የተያዘች የእግዚአብሔርን አምልኮት ትተህ አንተ ለረከሱ ጣዖታት ለምን ሰገድክ ከአንተ በፊት የነበሩ ነገሥታትን ለምን አልተከተልካቸውም እኔም እንዳንተ ወታደር ሁኜ ከቈስጠንጢኖስ ጋር ሃያ ዓመት ኖርኩ ከልጆቹም ጋር ነበርኩ ከእነርሱ ውስጥ እንዳንተ ያለ ጠባየ ክፉ የለም አለው።
ዑልያኖስም በቅዱስ አውስግንዮስ ላይ እጅግ ተቆጣ ይሰቅሉት ዘንድ በጐኖቹም ውስጥ መብራቶችን አስገብተው እንዲለበልቡት አዘዘ እርሱም ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህን ሁሉ ታገሠ።
ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ወታደሮችም ሊቆርጡት በመጡ ጊዜ እስኪጸልይ ይታገሡት ዘንድ ለመናቸው ጸሎቱንም ሲፈጽም የከበረች ራሱን ቆረጡት የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ጥር ፭
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር አምስት በዚህች ዕለት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ የለውጥ በዓል ነው።
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ጥር አምስት በዚህች ዕለት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ የለውጥ በዓል ነው። ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ አሏት። ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ። ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"። እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡
ቅድስት አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ "የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን"አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ዳግመኛም ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን" አለ፡፡
የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ ልደት ታህሳስ 29 በጌታችን ልደት ነው:: ነገር ግን ዕለቱ ትልቅ ሚስጥር የያዘ ነውና አባቶቻችን የጌታ ልደት ዘምረው ጣዕሙ ሳያልቅ ቅዳሴ ይገባሉ:: ስለዚህ የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ከሚቀር ልደታቸው ጥር 5 እንዲከበር ስርዓት ሰርተዋልና በዓለ ልደታቸው በዚህች ቀን ተከብሮ ይውላል፡፡
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፬ (4) ቀን።
❤ እንኳን #ለከበረና_ለተመሰገነ ለታላቁ #ለወንጌላዊው_ለአቡቀለምሲስ_ለቦኤኔርጌስ፣ #ለታኦሎጎስ_ለድንግላዊው_ለቊጹረ_ገጽ፣ #ለፍቊረ_እግዚእ_ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_ለፍልሰቱ (ከሞት ለተሰወረበት) ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦# ከከበረ_ከጊዮርጊስ ከሊቀ ጳጳሳት #ከማርቴና_ከሰማዕት_ታኦድራ_ከአባ_ሊቃኖስና #ቀውስጦስ_ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ፦ ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ አገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀስ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ። ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ወዳለበት ወደ የብስ ባሕሩ ተፋው ስለ መገናኘታቸውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት በዚያን ጊዜም ተነሥተው ወደ ኤፌሶን ከተማ ገቡ ግን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰብኩ ዘንድ አልተቻላቸውም እነዚያ ያገር ሰዎች እጅግ የከፉ ናቸውና። ስለዚህም ምክንያት ፈጥረው ዮሐንስ ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤት እሳትን የሚያነድ ሆነ ረድኡ አብርኮሮስም አጣቢ ሆነ ያች ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ነበር መጻተኞችም ስለሆኑ ታጐሳቁላቸዋለች ትደበድባቸዋለች ትረግማቸዋለች ባሮቿም እንደሆኑ ጽፈውላታልና ከእርሷ ባሮች አደረገቻቸው በዚህ በታላቅ ጒስቊልና ውስጥ ኖሩ።
❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ዕለት ይታጠብ ዘንድ የአገረ ገዥው ልጅ ገባ በዚያም የውሽባ ቤት ከተሠራ ጀምሮ የሰይጣን ኃይል አለ የመኰንኑም ልጅ አንቆ ገደለው በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ለዚያ ለሞተው ሊያለቅሱለት ተሰበሰቡ የከበረ ዮሐንስም እርሳቸው ጋር መጥቶ እንደ ሰው ሁሉ ሊያይ በዚያ ቆመ። ሮምናም በአየችው ጊዜ ረገመችው "አንተ በጌታዬ ልጅ ሞት ደስ ብሎህ ልትዝትብኝ መጣህ" አለችው ቅዱሱ ግን በቅንነት "አይዞሽ አትዘኝ" አላት ይህንንም ብሎ ወደ ሞተው ቀረብ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበበት በፊቱም ላይ እፍ አለበት። በዚያንም ጊዜ ያ የሞተው ድኖ ተነሣ የአገር ሰዎችም ደነገጡ ሮምናም "ወዮልኝ እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን? አለች። እርሱም "አይደለሁም እኔ አገልጋይ ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት በእነርሱ ላይ የሠራችውን በደል ሁሉ ይቅር ይሏት ዘንድ መሪር ልቅሶ በማልቀስ ሐዋርያትን ለመነቻቸው እነርሱም አረጋጓት አጽናኗትም።
❤ ከአገሩም ሰዎች ብዙዎቹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በፊታቸውም ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ይህንንም አይተው የአገሩ ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ። ከጣዖታቱ አገልጋዮች በቀር እነርሱም ሰይጣን በእርሱ ላይ ስለሚያነሣቸው ሊገድሉት ይሹ ነበር ነገር ግን ምርጦቹን እግዚአብሔር ጠበቃቸው። የከበረ ዮሐንስም ሁሉንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከመለሳቸው ድረስ ታላቅ ድካምና ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት። የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ልቡናቸው ደንዳናነት ጣዖታትን ስለመውደዳቸውም ስለ እነርሱ መስክሮአል። እርሱም ቅዱስ ዮሐንስ በታላቅ ድካም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን ሾመላቸው። ከዚህም በኋኋ ከእስያ በዙርያዋ ወዳሉ አገሮች ሁሉ ወጥቶ አስተማረ እግዚአብሔርንም ወደማወቅ መለሰላቸው።
❤ ይህም የከበረ የተመሰገነ ቅዱስ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልጀሮቹ ሐዋርያት በሰይፍ ሞትን አልቀመሰም። ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለምሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልክታትን የጻፈ ነው። ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና "የሚያሲዝህ አቤቱ ማነው?" ያለው ይህ እርሱ ነው። ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም "እነሆ ልጅሽ ያላት" እርሱን ደቀ መዝሙሩንም "እነኋት እናትህ" ያለው ነው።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስርሱ ጌታ ኢየሱስን "አቤቱ ይህስ እንዴት ነው?" ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም "እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደድኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት" ይህ ነው።
❤ የተመሰገነ ቅዱስ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም።
❤ ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለቱን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ። ከኤፊሶንም ከተማ ወጭ ወጣ ጒድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለው ዘንድ አለውና።
❤ ሁለተኛም እንዲህ አላቸው "እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንዲህ ከቶ ፊቶን አታዩኝም"። ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንደር ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጨማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ አባት በሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 4 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ"። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ18፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 4፥17-ፍ.ም።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ 138፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 6፥1-11፣ 1ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 4፥8-24። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 21፥20-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የስዋሬ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፫ (3) ቀን።
❤ እንኳን #ደብረ_ሊባኖስ_ገዳም_በስማቸው ለተሰየመላቸው ከዐለት ጠበል እያፈለቁ ድውያንን ለሚፈውሱት ለተአምረኛው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሊባኖስ (መጣዕ) ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አባ_ሊባኖስ፡- አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ይባላሉ፡፡ እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የበለጸጉ ሮማዊ ናቸው፡፡ ልጃቸውን አባ ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ እርሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ወደጫጉላቤትም መግባትን እምቢ አለ፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም እግዚአብሔር ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና ‹‹ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም›› አላቸው፡፡ አባታችንም "ወዴት እሄዳለሁ? ምንስ ላድርግ?" ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም ለአባ ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን፣ አስኬማ መላእክትን፣ ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ አባ ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና "ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ" አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ፡፡
❤ በአክሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአክሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል "ተራ ውሃ ነው" ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ "አምላከ አባ ሊባኖስ" ብሎ አመሰገነ፡፡ ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው "ምትሃት ነው የሚያሳየው" ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡
❤ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአክሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው "አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን" ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡
ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው "ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኰሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል" አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን "ደብረ ሊባኖስ" ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አክሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም "ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ" አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ "ሊባኖስ ዘመጣዕ" የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው ዐፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡
❤ ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ በዐፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተሰዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡ በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው ጥር 3 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ቀን ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡ ከአባ ሊባኖስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያድለን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለሊባኖስ_እምቤተ_አቡሁ_ዘወጽአ። ከመ ቃለ መልአክ ሰምዐ። ኰኵሐ ዘቢጦ ማየ አንቀዐ። ሰላም ለአድኃኒ ወዓዲ አስትዓ በውስተ ገዳም ምስሌሁ ዘነበሩ ስንዐ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥር_ 3።
