uz
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Ko'proq ko'rsatish
603
Obunachilar
-224 soatlar
-57 kun
-1430 kun
Postlar arxiv
.....ወር በገባ በ22 ...... የከበረና የገነነ የመነኮሳት ሁሉ አባት ፤ ኮከበ ገዳም ማኅቶተ ገድል ፨ በገዳም ለሚኖሩም ሁሉ ተገድሎው እንደ ኮከብ የሚያበራላቸው የ አባ_አንጦንስ ረድኤት በረከ
.....ወር በገባ በ22  ...... የከበረና የገነነ የመነኮሳት ሁሉ አባት ፤ ኮከበ ገዳም ማኅቶተ ገድል ፨  በገዳም ለሚኖሩም ሁሉ ተገድሎው እንደ ኮከብ የሚያበራላቸው የ አባ_አንጦንስ ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደር ።          " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን_መንግሥት_ጽድቁንም_ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ_ክፋቱ_ይበቃዋል። ማቴ 6 ፥ 33 - 34/

❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤️              ❤️ #ሰኔ_፳፪ 22 ቀን። ❤️ እንኳን #ለመነኰሳት_መጀመሪያቸው_ለሆነ ለከበረ #አባ_እንጦንስ_ረድእ ለነበረው ለየዋህ #ለቅዱስ_ጳውሎስ ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከከበሩ_ቅዱሳን_ከቆዝሞስና #ከድምያኖስ_ከእናታቸውና_ከወንድሞቻቸው ከበዐላቸው መታሰቢያና ቤተ ክርስቲያናቸውም ከከበረችበት ተአምራታቸውም ከተገለጠበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                               ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የአባ_እንጦስ_ረድእ_የዋህ_ቅዱስ_ጳውሎስ፦ ይህም ጳውሎስ በረኸኛና እጅግ የዋህ ነበር ደም ግቧቷ ውብ ሥራዋ ግን ክፉ የሆነ ሚስት አገባ ከእርሱም ልጆችን ወለደች። በአንዲትም ቀን ከእርሻው በተመለሰ ጊዜ ከሎሌው ጋራ ስታመነዝር አገኛት በአያቸውም ጊዜ ሣቀ ያንን ሎሌውንም እንዲህ አለው "ከልጆቿ ከቤቷና ከንብረቷ ጋራ ውሰዳት እኔ ምንም አላዝንም እግዚአብሔርም ወደ ፈቀደልኝ እሔዳለሁ" አለው። ❤️ ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አባ እንጦንስ ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ የአባ እንጦንስንም ሥራ ተከተለ። በደዌያትና በሰይጣናት ላይ ጸጋና ኃይል እስከተሰጠው ድረስ በጾምና በጸሎት ተጋደለ። ❤️ በአንዲት ዕለትም ጋኔን የያዘውን ሰው ያድነው ዘንድ ወደ አባ እንጦንስ አመጡ። አባ እንጦንስም ይፈውሰው ዘንድ ረድኡ ጳውሊን አዘዘው ጳውሊም ጋኔናሙን ሰው ወስዶ "አባቴ እንጦንስ ውጣ ይልሃል" አለው ሰይጣኑ ግን መውጣትን እምቢ አለ። እርሱንም እንጦንስንም ተሳደበ። ጳውሊም "ካልወጣህስ ለእንጦስ እነግረዋለሁ እንደሚቀጣህም ታያለህ" አለ። ይህንንም ብሎ በቀትር ጊዜ ወጥቶ ፀሐይ በአጋለው ደንጊያ ላይ ቁሞ "ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው እስኪድን ድረስ ከዚህ አለት እንዳልወርድ እንዳልበላና እንዳልጠጣ ሕያው እግዚአብሔር" አለ። በዚያንም ጊዜ ጋኔኑ ጮኸ በታላቅ ዘንዶ አምሳልም ከሰውዬው ላይ ወጥቶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ገባ። ❤️ ይህም የዋህ ጳውሊ የሰዎችን ሥራ ሁሉ እያየ ስለ ኃጥአን ያለቅስ ነበር ስለ እነርሱም ይማልድ ነበር። በመልካም እርጅናም ሰኔ 22 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ የዋህ በቅዱስ ጳውሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 22 ስንክሳር።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ "#ሰላም_ዕብል_ለጳውሎስ_ሊሉይ። እምነ ብእሲት ዘማ ሠናይተ ላህይ። ቀዊሞ ወዓለ እንበለ ናህይ። በመልዕልተ ኰኵሕ እንተ አርሰኖ ፀሐይ። እስከ እምጋኔን ሐይወ ብእሲ ድውይ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_22።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወኢትቅናእ ላዕለ ዘይዴሎ በሕይወቱ። ወላዕለ ሰብእ ዘይገብር ዐመፃ። ኅድጋ ለመዓት ወግድፋ ለቊጥዓ"። መዝ 36፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥6-ፍ.ም፣ ያዕ 5፥14-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥44-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥39-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️                ❤️ #ሰኔ ፳፩ (21) ቀን። ❤️ እንኳን #ለአዳም_ለዘር_ሁሉ_ድኅነት ለተደረገባት #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም በስሟ የተሠራችው የመጀመርያ #ቤተ_ክርስቲያን_በልጇ_በወዳጇ_እጅ #ለተቀደሰችበት_ለከበረችበት_ዓመታዊ_በዐሏና በዓለም ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዐል፣ #እመቤታችን_ለቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሣርያ ለተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ለነገረችውና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ላደረገች፣ ለሐዋርያው #ቅዱስ_ቶማስ በመሸታ ቤት ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ በዐል፣ ለምስር አገር ለሆነ #ለቅዱስ_ጢሞቴዎስ_ሰማዕትነት_ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለእስክድርያ_አራተኛ_ሊቀ_ጳጳስ #ለአባ_ከላድያኖስ_ለዕረፍት_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ሜሮን_ከተገኘችበትና_የአስታፍን_ዐፅም ከተገኘችበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                     ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #በዚች_ዕለት_የአዳምና_የዘሩ_ድኅነት የተደረገባት #አምላክን_የወለደች_የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች። ❤️ ይኸውም ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ቅዱሳን ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ። ሐዋርያትም እንዲ ብለው መለሱላቸው "ክብር ይግባውና ያለ ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው" እንዲህም አዘዙአቸው። ❤️ በሱባኤውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾላቸው ሐዋርያትም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዩስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ቅዱሳን ጳውሎስና በርባስ ነበሩ ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲናት እንዲታነፁ የፈቀድኩባት ናት"። ይህንንም ብሎ በከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኵል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈጸመ ድረስ ሦስቱ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበር ጌታችንም ንዋየ ቅዱሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ። ❤️ ከዚህም በኋላ ጌታችን እጁን በቅዱስ ጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማዕዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም ሊቀ ጳጳሳት ማለት ነው "ለሐዋርያት አለቃ ለቅዱስ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል" እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ። ❤️ ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ መድኃኒታችን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው "በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው"። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያች ቀን ጀምሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያንሳንፁ ሆኑ።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #በቂሣርያው_ሊቀ_ጳጳሳት_በአባ_ባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት። ❤️ ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ፤ ባለጸጋውም "ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው" አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና ዕንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት። ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዒሊ ሰጠው። ❤️ እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛም ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው። ❤️ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳችው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው። ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ ጠበል አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ። እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ዘር በሃያ አንድ ቀን ነው። ❤️ በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም "ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ" አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና። ❤️ እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኞች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል ስለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሁኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው። እርሷን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እንድትወልደው ላደረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእርሷ በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

ጻድቁ ንጉስ አጼ ካሌብ ወርኀዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው ። + ንጉሡ አጼ ካሌብ + ❖ ይህ ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚፈራውና በፍጹም ልቡ የሚወደው ሃይማኖቱም የቀና ነው፤ በናግራን አገር ያሉ ክርስቲያኖችን አይሁድ እንደሚገድሏቸው በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ መንፈሳዊ ቅናትንም ቀና። ❖ ከዚህም በኋላ ተነሣ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብቶ በመሠዊያው ፊት ቆመ ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ ብሎ ጸለየ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ሆይ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠርህ መላእክት ሁሉ አእላፈ አእላፋት አንተን የሚያመሰግኑህ ለአንተም የሚገዙ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆነ ኪሩቤል ክንፎቻቸው ስድስት የሆነ ሱራፌልም ጽኑዕ ክቡር ልዩ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር በቅዱሳን የሚመሰገን እያሉ ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑህ፣ ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጐናጸፍ የክብር ባለቤት ለሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔር ሆይ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ የጠፉ በጎችን ይመልሳቸው ዘንድ ልጅህን ይኸውም ቃልህ ነው በፈቃድህ የላክኸው አንተ ነህ። ❖ ተናጋሪ በግ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳትለይ ከሰማይ የወረድክና ስለ እኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆንክ ከጨለማም ከድንቁርናም አውጥተህ ወደ ብርሃን ወደ ሕይወት ወደ ዕውቀት የመራኸን፤ አሁንም ከሀዲ ወንጀለኛ ፊንሐስ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች እንደ በጎች በማረድ እንደ ገደላቸው በእሳትም አቃጥሎ የወገኖችህንና የርስትህን ልጆች እንዳጠፋቸው እይ። ❖ እነሆ አብ ሆይ እኔ አመንሁብህ በአንድ ልጅህም በሕያው ቅዱስ መንፈስህም በመሠዊያህ ክብርም ተማፅኛለሁ በሃይማኖትህም ጸንቼአለሁ እነሆ ስለ አምልኮትህና ስለ ምእመናን ወንድሞቼ ስለ ቀናሁ በአንድ ልጅህ መስቀል ጠላቶችህን ልዋጋቸው እወጣለሁና ከአለኝታዬ እንዳታሳፍረኝ የማያውቁህም አምላካቸው ወዴት ነው እንዳይሉ። ❖ ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴም ጸሎቴን የማትሰማ ልመናዬንም ንቀህ የምትተው ከሆነ በዚሁ ቦታ ብትገድለኝ ይሻለኛል፤ አቤቱ መሐሪ ይቅር ባይ ርኅሩህ ርስትህ የሆኑ ምእመናንን በከሀድያን ጠላቶችህ እጅ አሳልፈህ አትስጥ። እኛ ወገኖችህና የርስትህ መንጋዎች ስለሆን ለአንተም ምስጋና እናቀርባለን ምስጋና ገንዘብህ ነውና ለዘላለሙ። ❖ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ካሌብ ከሀገረ መንግሥቱ ወጥቶ ሔደ የናግራንን ሀገር ያጠፉአት አይሁድን ገደላቸው ብዙ ተአምራትም አድርጎ ስለ አደረገለት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ሀገረ መንግሥቱ በታላቅ ክብር በታላቅም ደስታ ተመለሰ፤ ለእግዚአብሔር ምን ዋጋ እከፍለዋለሁ ለጌትነቱና ፍጹም ለሆነ ገናናነቱ መባ አድርጌ ነፍሴንና ሥጋዬን ከማቀርብለት በቀር አለ። ❖ ከዚህም በኋላ ይህን ዓለም ንቆ መንግሥቱንም ትቶ ወጣ ደጋጎች መነኰሳት ወደሚኖሩበት ወደ አባ ጰንጠሌዎን በተራራ ላይ ወደ አለ ገዳም እስከ ደረሰ በእግሩ ሔደ፤ ወደ ዋሻ ውስጥም ገብቶ ሰውም እንዳያየው የዋሻውን በር ዘግቶ በዚያ ውስጥ ኖረ ከዚያችም ወጥቶ ዳግመኛ ዓለምን እንዳያይ ማለ። ❖ ከእርሱ ጋራም ያገባው ዕቃ የለም ከምንጣፍ ከሸክላ ጽዋ ከለበሳት የምንኲስና ልብስ በቀር ምግቡም አምባሻና ጨው የሚጠጣውም ውኃ ነው፤ የክብር ባለቤት ከሆነ ከእግዚአብሔር ቃል መቃብር መስኮት ላይ ይሰቅልለት ዘንድ የኢየሩሳሌሙን ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስን እየለመነው ዋጋው ብዙ የሆነ የነገሠበትን ዘውድ ላከ፤ ወደ ዋሻውም ከገባ በኋላ ከማንም ጋራ አልተነጋገረም እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ በፍቅር አንድነት አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

🕊 [  †  እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ [ ሕንጸታ ] በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †  ] †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊   †   በዓለ ሕንጸታ    †   🕊 †  በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" [አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ] [ማቴ.፳፰፥፲፱] (28:19) ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና [ዮሐ.፮፥፶፮] (6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ:: በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: [ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::] ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ:: በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ:: ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው:: እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል:: ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን:: † አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን:: 🕊 [  † ሰኔ ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፫. ቅዱሳን ሐዋርያት ፬. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ ዕረፍቱ ] [    † ወርኀዊ በዓላት     ] ፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት] ፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ ፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ ንጉሠ ኢትዮጵያ ] ፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና ፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት † " በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: " † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር †

❤️ ከዚህ በኋላ በዚያች ቀንና በዚያች ሌሊት በሥጋው ላይ እሳትን አነደዱ እሳቱም በላዩ እየነደደ ምንም ምን አልነካውም ወስደውም በገበያ ውስጥ ጣሉት ከዚያም አንሥተው በባሕር ውስጥ ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ ደሴቱ ወደብ ዳር ደረሰ እናቱም ጠብቃው ነበርና ወስዳ ገነዘችው ለጥቂት ወራትም በቤቷ ውስጥ ሸሸገችው። ❤️ ከዚህም በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሥጋውንም በውጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅና ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በሐዲስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #አባ_ብሶይ_አኖብ፦ የስሙ ትርጓሜውም የጠራ ወርቅ ማለት ነው። ይህም ቅዱስ ከድምያጥ አውራጃ ስሟ ባኖስ ከሚባል አገር ከአቅራብ መኰንን ከቆጵርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ ከከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ልጆች ወገን ነበር በዚህም ቅዱስ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። ቅዱሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በፊቱ ታመነ። ❤️ ወደ እንዴናውም ወሰዱት በመኰንኑ አርያኖስ ፊት ቁሞ በጌታችን ታመነ አርያኖስም በእርሱ ላይ ተቆጣ "ለአማልክትም ሠዋ" አለው። አልታዘዘለትም ሥቃዩንም አልፈራም መኰንኑም ወስዶ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚያም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ ወደሚገድሉበት ቦታም ሊወስዱት አወጡት ብዙ ሕዝብም ይከተሉት ነበር እነሆ ከዚያም የአርያኖስ መኰንን አንበሶች ነበሩ። የሚጠብቃቸውም ሰው ነበር እነርሱም በብረት ሰንሰለት ታሥረው ነበር ከእነርሱም አንዱ አንበሳ የብረት ሰንሰለቱን በጥሶ ሩጦ ወደ ቅዱስ ደረሰ። የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱሱን በአንበሳው ጀርባ ላይ አወጣውና ዐይነ ፀሐይ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሰው በረረበት ቅዱሱ ግን ዐይኑን ሸፍኖ ስለ ነበር ውዴት እንዳለ አላወቀም በዚያም ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ብሶይ አኖብ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 19 ስንክሳር።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ "#ሰላም_ለጻድቃን_እለ_በቋዓት"። ትርጉም፦ በቋዓት ያሉ ለኾኑ #ጻድቃን_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን ላይ።                                                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 1፥1-8፣ 1ኛ ዮሐ 2፥14-20 እና የሐዋ ሥራ 19፥11-18። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥8-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ወይም የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️               ❤️ #ሰኔ ፲፱ (19) ቀን። ❤️ እንኳን #ለሰማዕቱ_ሐዲስ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ፣ #ለአባ_ብሶይ_አኖብ ሰማዕትነት ለተቀበሉት #ለዕረፍታቸው_በዓልና_ለአምስት_ጭፍሮች እሊህም #ለአርሶፎኒስ_ለጴጥሮስ_ለአስኪርዮን #ለአርጌንዮስ_ለቢልፍዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት #ለዕረፍታቸው_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከደብረ_ቋዓት ቅዱሳን አባቶቻችን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #አምስቱ_ጭፍሮች፦ እሊህም ስማቸው አርሶፎኒስ፣ ጴጥሮስ፣ አስኪርዮስ፣ አርጌንዮስና ቢልፍዮስ ነው። በዲዮስጲልዮስ ቅጽር ውስጥ ይኖሩ ነበር። መኰንኑም ለጣዖታት እንዲሠው በአስገደዳቸው ጊዜ "እኛስ የንጉሣችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝ እንፈጽማለን ለእርሱም እንሰዋለን" አሉት መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ በአንድ ቤት ውስጥም እንዲዘጉባቸውና እስከ ሁለት ቀን ያህል ውኃ እንዳይሰጧቸው አዘዘ። ❤️ ከዚህም በኋላ እንዲያመጧቸው አዘዘ በፊቱም በቆሙ ጊዜ "ለአማልክት ሠዉ" አላቸው እነርሱም በአንድ ቃል "እኛስ ለፈጣሪያችን ለክርስቶስ እንሠዋለን ለረከሱ አጋንንትን ግን አንሠዋም" አሉት። አንገታቸውንም አሥረው ወደ ሌላ አገር ይወስዱአቸው ዘንድ አዘዘ። አርጌንዮስም ወንድሞቹን "እኔ እውነትን እነግራችኋለሁ የእግዚአብሔር መልአክ አምስታችንንም በስማችን ሲጠራን ሸምቼዋለሁና" አላቸው። ❤️ ዳክስ ወደሚባል መኰንንም በአደረሷቸው ጊዜ መኰንኑ አስቀድሞ አርሶፎኒስን ወስዶ "ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ በአለውም ጊዜ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው በከተማ ውስጥ እንዲጎትቱትና እንዲአዞሩት አዘዘ። በመለሱትም ጊዜ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ፊቱን እንዲአጠወልጉት አዘዘ ሁለተኛም እስከ ሚጨነቅ ድረስ በሠረገላ ውስጥ አሥረው ቊልቊል ሰቀሉት ሃይማኖቱንም ጠብቆ ክብር ይግባውና ለጌታችን ነፍሱ ሰጠ። ❤️ ሁለተኛም ጴጥሮስን አቀረቡት ዳክስም "ለአማልክት ሠዋ" አለው ትእዛዙንም ባልተቀበለው ጊዜ እንዲአሠቃዩትና እንጨት ተክለው ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ ሁለተኛም ምድሩን ቆፍረው ከትከሻው በታች ቀብረው በቅሎዎችን በላዩ እንዲነዱበት አዘዘ ይህንንም እግዚአብሔር እየረዳው ታገሠ ከጉድጓድም በአወጡት ጊዜ ከሥቃዩ ብዛት የተነሣ ሥጋው ጠወለገ መናገርም ተሣነው በግንድ ውስጥም አሥረው ጣሉት። ❤️ ከዚህም በኋላ አርጌንዮስን አቀረቡት ዳክስም "ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ያለ መብልና መጠጥም በተበሳ ግንድ ውስጥ አሥረው ዘቅዝቀው ሰቀሉት። ❤️ ዳግመኛም አስኪርዮንን አቀረቡት ዳክስም "ለራስህ እዘን በክፉ አሟሟትም እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እንዲሰነጥቁት አዘዘ ወታደሮችም ተረከቡትና በጽኑ ሥቃይ አሠቃዩት በትዕግሥቱም በአሸነፋቸው ጊዜ ለመኰንኑ ነገሩት በረኃብና በጽም ይሞት ዘንድ በግንድ ውስጥ አሥረው በባዶ ቤት እንዲዘጉበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። ❤️ ደግመው ዲያቆን ቢፍዮስን አቀረቡት መኰንን ዳክስሞ "እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ" አለው ባልሰማውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ ሥጋውን ሠነጣጥቀው በከተማው አደባባይ ጎተቱት እንጨት ተክለውም ቊልቊል ሰቀሉት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠለጠሉ ከሃይማኖቱም ባልተናወጸ ጊዜ በረኃብና በጽምዕ እንዲሞት በግንድ ውስጥ አሥረው በላዩ መዝጊያ ሠርተው ዘጉበት። በየዕለቱም ወንድሞች ምእመናን ከውጭ ሆነው ይጎበኙት ነበር ጳሔን የተባለው የሰኔ ወር በባተ በሠላሳ ጴጥሮስ ነፍሱን ሰጠ። እርሱንም አውጥተው ደጁን በሌሎቹ ላይ ዘጉ። ❤️ የከበረ አርጌንዮስም ከአምስት ቀን በኋላ ዐረፈ እርሱን አውጥተው በቀሩት ላይ ደጁን ዘጉ። ብፁዕ አስኪርዮንም ከዐሥራ ሁለት ቀን በኋላ ዐረፈ። እርሱንም አውጥተው በቅዱስ ቢልፍዮስ ላይ ደጃፍ ሠርተው ዘጉበት እርሱም የሚያርፍባት ቀን ስትደርስ ወንድሞቼ ታገሡኝ በዚች ሌሊት እወጣለሁና አላቸው። ከዐሥራ ዘጠኝ ቀን በኋላ በዚያች ልሊት ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ገድለኞች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #ሰማዕቱ_ሐዲስ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መዛሕዝም ነው ትርጓሜውም ድንገተኛ ማለት ነው። እርሱም እስላም ነበር ከግብጽ ደቡብ ድምራ ከሚባል አገር ክርስቲያን ሴት አግብቶ ከእርሷም ሦስት ልጆችን ወለደ ከሦስቱም አንዱ ይህ ቅዱስ ነው። ከእናቱም ጋራ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሔድ ነበር ቅዱስ ቁርባንንም ይቀበል ዘንድ እናቱን ለመናት እርሷም ማንም የክርስትናን ጥምቀት ሳይጠመቅና ንጹሕ ሳይሆን ቁርባን ሊቀበል አይችልም አለችው። ❤️ ከዚህም በኋላም ከተረፈ መሥዋዕቱ ሰጠችው በጎረሳትም ጊዜ ጣዕሟ በአፉ ውስጥ እንደ ማር ሆነ "የዚች የቁራሿ ጣዕም በአፌ ውስጥ እንዲህ የሆነ የዋናው የቁርባኑ ኅብስት ጣዕም ምን ያህል ይሆን" ብሎ በልቡ አሰበ ከዚች ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ። ❤️ በአደገም ጊዜ ክርስቲያን ሴት አገባ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ መፈለጉንም ነገራት እርሷም ወደሌላ አገር ሒዶ የክርስትናን ጥምቀት እንዲጠመቅ መከረችው እርሱም ወደ ሌላ አገር ሒዶ ተጠመቀ ስሙንም ለውጦ ጊዮርጊስ ተባለ። እስላሞችም በአዩት ጊዜ ይዘው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ከዚያም አምልጦ ሳፍጥ ወደሚባል አገር ሸሸ በዚያም ሦስት ዓመት ኖረ። ወሬውም በተገለጠ ጊዜ ቀጡር ወደ ሚባል አገር ሒዶ የልዳዊው ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን እያገለገለ ኖረ። ❤️ ከዚህ በኋላ ወደ አገሩ ድምራ ተመለሰ እስላሞችም ሰሙ ይዘውም ለመኰንኑ ሰጡት የመኰንኑም ሚስት ክርስቲያን ነበረች ለመኰንኑም "አታሠቃየው" አለችው መኰንኑም አሥሮ በወህኒ ቤት ዘጋበት። እስላሞችም ተሰብሰቡ የወህኒ ቤቱንም ደጅ ሰብረው ታላቅ ግርፋት ገረፉት አካላቱም ቈራርጠው በሕይወትና በሞት መካከል ጣሉት። ሲነጋም ክርስቲያኖች የሞተ መስሏቸዋልና ሊቀብሩት መጡ ነገር ግን በሕይወት አገኙት። ❤️ ከዚህም በኋላ እስላሞች ተሰብስበው "ከዚህ ምክርህ ካልተመለስክ እኛ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተን እንገድልሃለን" አሉት የመዛሕዝም ልጅ የከበረ ጊዮርጊስም "ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም የፈለጋችሁትን አድርጉ" አላቸው። እጅግም ተቆጡ በመርከብ ምሰሶ ላይም ሰቅለው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት መኰንኑም ከስቅላት አውርደው በእሥር ቤት እንዲአሥሩት አዘዘ እንደዚሁም አደረጉ። ሚስቱም ታጽናናውና እንዲታገሥ ታደርገው ነበር ሰይጣንም እንዳያስተውና የደከመበትን ዋጋ እንዳያጣ በልቡ ወደ ክርስቶስ ያስብ ዘንድ ትመክረው ነበር። ❤️ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና አረጋጋው አበረታታውም ከሰማዕታትም ጋራ እንደ ተቈጠረ በማግሥቱም ራሱን በሰይፍ እንደሚቆርጡት ነገረው። በነጋም ጊዜ እስላሞች ወደ መኰንኑ ተሰብስበው ጊዮርጊስን ይሰጣቸው ዘንድ ፈለጉ መኰንኑም የወደዱትን ያደርጉበት ዘንድ እንዲሰጧቸው አዘዘ። ❤️ ከዚህም በኋላ ከእሥር ቤት አወጡት ድምራ በምትባል አገር በከበረ የመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ራሱን በሰይፍ ሰኔ 19 ቀን ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ_፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_አርባ_አምስተኛው ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ድምያኖስ_ለዕረፍት_በዐል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰው፦ #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ኤስድሮስ መታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_ድምያኖስ፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ነው። በአስቄጥስ በአባ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም ከታናሽነቱ ጀምሮ መነኰሰ ዐሥራ ሰባት ዓመት ያህልም እየተጋደለ ኑሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ በታርን ወደተባለ ገዳም ሔደ ይኸውም የአባቶች ገዳም ማለት ነው እርሱም በእስክንድርያ ምዕራብ ያለ ነው። እንደ ገዳመውያንም ገድል በውስጡ ተጠምዶ እየተጋደለ ኖረ። ❤ ከእርሱ አስቀድሞ የነበረው አባ ጴጥሮስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ በሊቀ ጵጵስናው ሥራ የሚረዳውና በሥራው ሁሉ የሚአማክረው ስለ ቤተ ክርስቲያን ጥበቃ አዋቂ ሰው ፈለገ ይህንንም አባ ድምያኖስን ሰዎች በበጎ ሥራ ሁሉና በዕውቀቱ ያመሰግኑታል። ስለዚህም ወደርሱ ወሰደውና በሊቀ ጵጵስናው ሥራ እየተራዳው ከእርሱ ጋራ እንዲቀመጥ አደረገው እርሱም ትእዛዙን ተቀብሎ ከእርሱ ጋር ተቀምጠ ሰዎችም ሁሉ ወደዱት። ❤ አባ ጴጥሮስም በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳትና አዋቂዎች ሊቃውንት በአንድ ምክር ተስማምተው በእስክንድርያ ከተማ ይህን አባ ድምያኖስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ለአገልግሎትም ፅሙድ ሆነ በመልካም ሥራ ሁሉ ጸንቶ ኖረ። ሁሉጊዜም ድርሰቶችንና መልክቶችን እየጻፈ ወደ አገሩ ሁሉና ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ይልክ ነበር። ❤ በአስቄጥስም ገዳም በአባ መቃርስ ደብር ከነጣቂው ከሀዲ ወገን የሆኑ አርሲሳን የሚሉአቸው መናፍቃን ነበሩ እነርሱም በሚቆርቡበት ቀን ሌሊት ወይን ይጠጣሉ በማግሥቱም ቅዱስ ቁርባንን ይቀበላሉ። እነርሱ ጌታችን በመጀመሪያ ኅብስቱን ከመፈተቱ በፊት በኋላም ኅብስቱን ከሰጣቸው በኋላ ሁለት ጊዜ ጽዋን እንደሰጣቸው በሉቃስ ወንጌል ተጽፎ ያለውን ምክንያት ያደርጋሉና። ይህም አባት አባ ድምያኖስ ስሕተታቸውን ገለጠላቸው የፊተኛው ጽዋ የአለፈው ኦሪት ፋሳካ ምሳሌ እንደ ሆነም አስረዳቸው አዲሱ የአባቶቻችን ሐዋርያት ቀኖና ሕግ ግን የመድኃኒታችንን ሥጋውንና ደሙን የሚቀበል ሁሉ ከመብልና ከመጠጥ ይጠበቅ ዘንድ ከቁርባንም አስቀድሞ ምንም ምን እንዳይቀምስ ያዝዛል። ከእርሳቸውም ውስጥ ከስሕተታቸው ተመልሰው ንስሐ የገቡና የታዘዙለት አሉ ያልተመለሱትን ግን አውግዞ ከምእመናን አንድነት ለይቶ አባረራቸው። ❤ በዚህ በአባ ድምያኖስ ዘመንም የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎድሮስ ዐረፈ። በእርሱ ፈንታም የሥላሴን ስም ፈጽሞ የማያወሳ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ይላል እንጂ በልዩ ሦስትነት የማያምን መናፍቅ ሰው ተሾመ የከፋች ሃይማኖቱንም የምትገልጽ መልእክት ወደዚህ አባት ድምያኖስ ላከ። አባ ድምያኖስም በአነበባት ጊዜ እጅግ አዘነ በመልክቱ ውስጥ እግዚአብሔር አንድ ገጽ ብቻ እንደ ሆነ ያወሳል እንጂ የልዩ ሦስትነትን ስም የሚያወሳ አላገኘምና። ❤ ይህም አባት ድምያኖስ የሥላሴን በመለኮት አንድነታቸውን በገጽ በአካልና በግብር ሦስትነታቸውን ከቅዱሳን መጻሕፍትም ጠቅሶ ለዚህም መናፍቅ መልእክት ጻፈለት ደግሞም እንዲ አለው "ለእግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋራ የነበረ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው አካላዊ ቃል አካላዊ ሕይወት አለው"። ይህችንም ምሥጢርንና ዕውቀትን የተመላች መልእክት ለአንጾኪያ ሊቀ ጵጵስና ወደ ተሾመ ወደዚያ መናፍቅ በደረሰች ጊዜ ትርጓሜዋን ያውቅ ዘንድ የልቡ ድንቁርና የአእምሮው ጉድለት አለቀቀውም። ነገር ግን በክህደቱ ጸና። አባ ድምያኖስም ከዚህ መናፍቅ አንድነት ተለየ ማኅበሩንም በቅዳሴና በጸሎት ጊዜ ይህ ከሀዲ እስኪሞት ድረስ ለሃያ ዓመት ስሙን እንዳይጠሩት አዘዛቸው። ❤ ይህም አባት ድምያኖስ በተግሣጾቹና በመልክቶቹ መንጋውን እየጠበቀ አርባ ሦስት ዓመታት ያህል ከኖረና ወደ በጎ እርጅና ከደረሰ እግዚአብሔርንም ከአገለገለ በኋላ ሰኔ 18 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ድምያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 18 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለሊቀ_ጳጳሳት_ድምያኖስ_አቡነ። ለተልእኮ ምሥዋዕ ዘጽሐቀ ወዘአስተንተነ። ለእለ አመክነየ ሰብእ በፍስሐ ሐሙስ ዘኮነ። ገሠጾሙ ወአውገዞሙ ኢይትመጠዉ ቁርባነ። በኑኅ ሌሊት ሰትዮሙ ወይነ። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_18።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ሠርከ ወነግሀ ወመዓልተ እነግር። አየድዕ ወኢሰምዑኒ ቃልየ። አድኅና በሰላም ለነፍስየ እምእለ ይትቃረኑኒ"። መዝ 54፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 2፥1-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 2፥9-14 እና የሐዋ ሥራ 17፥5-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥15-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ_፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_አርባ_አምስተኛው ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ድምያኖስ_ለዕረፍት_በዐል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰው፦ #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ኤስድሮስ መታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_ድምያኖስ፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ነው። በአስቄጥስ በአባ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም ከታናሽነቱ ጀምሮ መነኰሰ ዐሥራ ሰባት ዓመት ያህልም እየተጋደለ ኑሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ በታርን ወደተባለ ገዳም ሔደ ይኸውም የአባቶች ገዳም ማለት ነው እርሱም በእስክንድርያ ምዕራብ ያለ ነው። እንደ ገዳመውያንም ገድል በውስጡ ተጠምዶ እየተጋደለ ኖረ። ❤ ከእርሱ አስቀድሞ የነበረው አባ ጴጥሮስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ በሊቀ ጵጵስናው ሥራ የሚረዳውና በሥራው ሁሉ የሚአማክረው ስለ ቤተ ክርስቲያን ጥበቃ አዋቂ ሰው ፈለገ ይህንንም አባ ድምያኖስን ሰዎች በበጎ ሥራ ሁሉና በዕውቀቱ ያመሰግኑታል። ስለዚህም ወደርሱ ወሰደውና በሊቀ ጵጵስናው ሥራ እየተራዳው ከእርሱ ጋራ እንዲቀመጥ አደረገው እርሱም ትእዛዙን ተቀብሎ ከእርሱ ጋር ተቀምጠ ሰዎችም ሁሉ ወደዱት። ❤ አባ ጴጥሮስም በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳትና አዋቂዎች ሊቃውንት በአንድ ምክር ተስማምተው በእስክንድርያ ከተማ ይህን አባ ድምያኖስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ለአገልግሎትም ፅሙድ ሆነ በመልካም ሥራ ሁሉ ጸንቶ ኖረ። ሁሉጊዜም ድርሰቶችንና መልክቶችን እየጻፈ ወደ አገሩ ሁሉና ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ይልክ ነበር። ❤ በአስቄጥስም ገዳም በአባ መቃርስ ደብር ከነጣቂው ከሀዲ ወገን የሆኑ አርሲሳን የሚሉአቸው መናፍቃን ነበሩ እነርሱም በሚቆርቡበት ቀን ሌሊት ወይን ይጠጣሉ በማግሥቱም ቅዱስ ቁርባንን ይቀበላሉ። እነርሱ ጌታችን በመጀመሪያ ኅብስቱን ከመፈተቱ በፊት በኋላም ኅብስቱን ከሰጣቸው በኋላ ሁለት ጊዜ ጽዋን እንደሰጣቸው በሉቃስ ወንጌል ተጽፎ ያለውን ምክንያት ያደርጋሉና። ይህም አባት አባ ድምያኖስ ስሕተታቸውን ገለጠላቸው የፊተኛው ጽዋ የአለፈው ኦሪት ፋሳካ ምሳሌ እንደ ሆነም አስረዳቸው አዲሱ የአባቶቻችን ሐዋርያት ቀኖና ሕግ ግን የመድኃኒታችንን ሥጋውንና ደሙን የሚቀበል ሁሉ ከመብልና ከመጠጥ ይጠበቅ ዘንድ ከቁርባንም አስቀድሞ ምንም ምን እንዳይቀምስ ያዝዛል። ከእርሳቸውም ውስጥ ከስሕተታቸው ተመልሰው ንስሐ የገቡና የታዘዙለት አሉ ያልተመለሱትን ግን አውግዞ ከምእመናን አንድነት ለይቶ አባረራቸው። ❤ በዚህ በአባ ድምያኖስ ዘመንም የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎድሮስ ዐረፈ። በእርሱ ፈንታም የሥላሴን ስም ፈጽሞ የማያወሳ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ይላል እንጂ በልዩ ሦስትነት የማያምን መናፍቅ ሰው ተሾመ የከፋች ሃይማኖቱንም የምትገልጽ መልእክት ወደዚህ አባት ድምያኖስ ላከ። አባ ድምያኖስም በአነበባት ጊዜ እጅግ አዘነ በመልክቱ ውስጥ እግዚአብሔር አንድ ገጽ ብቻ እንደ ሆነ ያወሳል እንጂ የልዩ ሦስትነትን ስም የሚያወሳ አላገኘምና። ❤ ይህም አባት ድምያኖስ የሥላሴን በመለኮት አንድነታቸውን በገጽ በአካልና በግብር ሦስትነታቸውን ከቅዱሳን መጻሕፍትም ጠቅሶ ለዚህም መናፍቅ መልእክት ጻፈለት ደግሞም እንዲ አለው "ለእግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋራ የነበረ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው አካላዊ ቃል አካላዊ ሕይወት አለው"። ይህችንም ምሥጢርንና ዕውቀትን የተመላች መልእክት ለአንጾኪያ ሊቀ ጵጵስና ወደ ተሾመ ወደዚያ መናፍቅ በደረሰች ጊዜ ትርጓሜዋን ያውቅ ዘንድ የልቡ ድንቁርና የአእምሮው ጉድለት አለቀቀውም። ነገር ግን በክህደቱ ጸና። አባ ድምያኖስም ከዚህ መናፍቅ አንድነት ተለየ ማኅበሩንም በቅዳሴና በጸሎት ጊዜ ይህ ከሀዲ እስኪሞት ድረስ ለሃያ ዓመት ስሙን እንዳይጠሩት አዘዛቸው። ❤ ይህም አባት ድምያኖስ በተግሣጾቹና በመልክቶቹ መንጋውን እየጠበቀ አርባ ሦስት ዓመታት ያህል ከኖረና ወደ በጎ እርጅና ከደረሰ እግዚአብሔርንም ከአገለገለ በኋላ ሰኔ 18 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ድምያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 18 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለሊቀ_ጳጳሳት_ድምያኖስ_አቡነ። ለተልእኮ ምሥዋዕ ዘጽሐቀ ወዘአስተንተነ። ለእለ አመክነየ ሰብእ በፍስሐ ሐሙስ ዘኮነ። ገሠጾሙ ወአውገዞሙ ኢይትመጠዉ ቁርባነ። በኑኅ ሌሊት ሰትዮሙ ወይነ። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_18።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ሠርከ ወነግሀ ወመዓልተ እነግር። አየድዕ ወኢሰምዑኒ ቃልየ። አድኅና በሰላም ለነፍስየ እምእለ ይትቃረኑኒ"። መዝ 54፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 2፥1-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 2፥9-14 እና የሐዋ ሥራ 17፥5-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥15-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።

Repost from N/a
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 በትላንትናው ዕለት
+8
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 በትላንትናው ዕለት የፍኖተ ብርሃን ህፃናት ክፍል ፲፪ ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እንዲህ ባለ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል በእለቱም ህፅበተ እግር ለህፃናት ተደርጓል መዝሙር፣ኪናዊ ዝግጅት እንዲሁም መንፈሳዊ ፊልም ጥያቄና መልስ ተካሂዶ በግሩም ሁኔታ ተከብሮ አልፏል ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን።

❤️ ከሰባት ቀኖች በኋላ አባ ጰላሞን ከረኀብና ከውኃ ጥም የተነሣ ከመሬት ላይ ወደቀ፤ ለሞትም የደረሰ ሆነ፡፡ ሰውን ወዳድ የሆነ ጌታችንም እንዲጠፋ አልተወውምና ሰይጣንን ከእርሱ አርቆ አሳደደው፡፡ አባ ጰላሞን በእርሱ ላይ የሆነውን ባወቀ ጊዜ ወደ ጌታን ጮኸ፡፡ ወዲያውም "ጰላሞን ሆይ አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ጠላት በአንተ ላይ ክፉ ሊሠራ አይልችም፡፡ ነገር ግን ተነሥተህ ወደ ደቡብ ጥቂት ተጓዝ በዚያም በተራራው አጠገብ የሚኖር ስሙ ለትጹን የሚባል ሽማግሌ ጻድቅ ሰው ታገኛለህ፣ እርሱ ስለ ስሜ ብዙ መከራ የተቀበለ ነው፡፡ ያደረከውንም ሁሉ ሰይጣንም እንዴት እንዳሳተህ ንገረው፣ እርሱ ኃጢአትህ እስኪሠረይ ስለ አንተ ይጸልያልና" የሚል ቃልን ሰማ፡፡አባ ጰላሞንም እየጸለየ ቃሉ ወዳመለከተው ወደ አባ ለትጹን በዓት ደረሰ፡፡ አባ ጰላሞንም ባየው ጊዜ በደስታ ተቀብሎ ሰላምታ ሰጠው፡፡ ወደ ተራራውም ወጥተው ከጸለዩ በኋላ ተቀምጡ፡፡ አባ ጰላሞንም የመረረ ልቅሶን እያለቀሰ ሰይጣን በፈተናው እንደጣለው ለአባ ለትጹን ይነግረው ጀመረ፡፡ እንዲህም አለው፡- "በአንዲት ዕለት የእጅ ሥራዬን ለመሸጥ በግብፅ ገበያ መንገድ ስጓዝ ሰይጣን መጥቶ ልቤን አዘነጋት፤ መድኃኒት የሚሆነኝን የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እጠራ ዘንድ አልተወኝም፡፡ ዳግመኛም እንደ ንጉሥ ከተማ የታነፀች ውኃዎችና ተክሎች መልካም ዛፎችም ያሏት ከተማን አሳየኝ፡፡ የእጅ ሥራዬንም ልሸጥ ሳስብ ባሏ ብዙ ገንዘብ ትቶላት ሙቶ በምታዝን ሴት አምሳል ታየኝ፡፡ "የእጅ ሥራህን እኔ እገዛሃለሁ" ብለኝ ወደ አዳራሽ አስገባችኝ፡፡ እንቅቦቹንም ከላዬ አውርዳ አኖረች፣ እግሮቼንም አጠበች፣ አሽከሮቿንም ምግብ ያቀርቡ ዘንድ አዘዘቻቸው፡፡ ከእርሷ ጋርም እበላ ዘንድ ብዙ ማለደችኝ፣ በልተን ጠጥተን ሰከርን፡፡ ስንጨዋወትም አሽከሮቿ ሁሉም ወጡና ሁለታችን ብቻችንን ቀረን፡፡ ያንጊዜም ልቤ በዝሙት እሳት ተቃጠለ፡፡ እግዚአብሔርንም መላእክቶቹንም ቢሆን አላሰብኩም በእርግጥ ከእርሷ ጋር እንደሚተኛ ሆንኩ፡፡ ❤️ ከዚህ በኋላ በነቃሁ ጊዜ ብመለከት ምንም ነገር አላገኘሁም፡፡ ሴትም ቤትም ማዕድም አትክልትም ቢሆን አላገኘሁም፡፡ ነገር ግን ራሴን ከተራራው በታች አገኘሁት፡፡ ምንም እንዳልበላና እንዳልጠጣም ሰው ሆንኩ፡፡ እጅግም አለቀስኩ፡፡ ሰይጣንም በሩቁ ቆሞ "መጻተኛ ጰላሞን ሆይ ወዮልህ እንደወፍ ላጠምድህ በአንተ ላይ በርትቻለሁና…" እያለ ሲዘብትብኝ አየሁት፡፡ ነገሩንም ሰምቼ በመስቀል ምልክት በላዩ አማተብኩ፣ ከእኔም ሸሸ፡፡ "አሁንም አባቴ ለትጹን ሆይ በደሌን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንልኝ በቅድስናህ ተማፅኛለሁ" አለው፡፡ ቅዱስ አባ ጰላሞንም "አይዞህ እግዚአብሔር ኃጢአትህን ይቅር እንደሚልህ አምናሁ" ብሎ አጽናናው፡፡ ከዚህም በኋላ ተነሥቶ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ጸለየ፡፡ ወደ እነርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡- "የታመናችሁ አገልጋዮቼ አትፍሩ ከእንግዲህ ወዲህ ጠላት በእናንተ ላይ አይበረታታም፡፡ ጰላሞንም የሠራውን ኃጢአት በራሱ በሰይጣን ላይ አደረግሁ፣ የጰላሞንን ኃጢአት ብቻ አይደለም ነገር ግን የሚፈትናቸውን ሰዎች ሁሉ ኃጢአታቸውን በሰይጣን በራሱ ላይ እመልሳለሁ"፡፡ ❤️ ከዚህም በኋላ አባ ጰላሞን ከአባ ለትጹን በረከትን ተቀብሎ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ በዓቱ ሄደ፡፡ ተጋድሎውንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፡- የሰኔ 17 ስንክሳር።                                + + + ❤️ "#ሰላም_ለአባ_ለትጹን_እስከ_ፍጻሜ_ዘክህለ። ከመ ያውጽእ እምደይን ብእሴ ህጉለ። ለለ መዋዕል ሰዱስ እንዘ ይበልዕ ቈጽለ። በትርሕምት ዐቢይ እምብዝኀ ተጋደለ ገድለ። በአምሳለ ዖፍ ኮነ ሥጋሁ ቀሊለ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_17።                                + + + ❤️ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ኀይልየኒ ወዝክርየኒ እግዚአብሔር። ወውእቱ ኮነኒ መድኃንየ። ቃለ ትፍሥሕት ውስተ አብያቲሆሙ ለጻድቃን"። መዝ 117፥14። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 17፥5-11።                                 + + + ❤️ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አኮ ከመዝ ኃጥአንሰ አኮ ከመዝ። ዳዕሙ ከመ መሬት ዘይግሕፎ ነፋስ እምገጸ ምድር። ወበእንተዝ ኢይትነሥኡ ረሲዓን እምደይን"። መዝ 1፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 1፥1-10፣ ያዕ 5፥14-17 እና የሐዋ ሥራ 13፥44-49። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥20-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ገሪማ ከሞት የተሰወሩበት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️             ❤️ #ሰኔ ፲፯ (17) ቀን። ❤️ እንኳን #ለታላቁ_አባት እናቱን በዝሙት አስረግዞ ፅንሱንም መርዝ አጠጥቶ በማኅፀኗ የገደለውን ርጉም ሰው ከዘላለማዊው ሥቃይና ኩነኔ ለታደጉት #ለአባ_ለትጹንና #ፍፁም_መናኒ_ለሆነ ለመጻተኛ ከሰው ጋር ተነጋግሮ ለማያውቀውና በተራራ ላይ ብቻውን በገድል ተጠምዶ ሲኖር የጌታችንን መከራ እያሰበ ቀንና ሌሊት ያለቅስ ለነበረው ለባሕታዊ #አባ_ጰላሞን ለዕረፍታቸው_መታሰቢያ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕታት #ከነአኮራን፣ #ከበርተሎሜዎስ፣ #ከእለስክንድርያ፣ #ከእለስክንድሮስ፣ #ከዮሴፍና_ከጻድቂቱ_አርሴማ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤️# አባ_ለትጹን፦ ይህም አባት ከብህንሳ አገር ነበር ጎልማሳ በነበረ ጊዜም "ነፍሱን ስለ እኔ የጣላትም ያገኛታል ለዘላለም ሕይወትንም ይጠብቃታል" የሚለውን በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጻፈውን የሕያው ንጉሥን ቃል ሰማ ወዲያውኑ ልቡ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ዘላለማዊ ተድላ እንደ እሳት ነደደ። ቅዱስ ቁርባንንም ተቀብሎ እስዋሕት ወደ ሚባል ገዳም ሔደ በጾም በጸሎትና በስግደት ታላቅ ተጋድሎን ያለ ማቋረጥ ይጋደል ጀመር ሰባት ሰባት ቀንም ይጾም ነበር። ❤️ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና የምንኲስና ልብስን ዘንድ ወደ አባ ኤስድሮስ እንዲሔድ አዘዘው እርሱም መልአኩ እንዳዘዘው ሔደ አባ ኤስድሮስም በልብሱና በአስኬማው ላይ አርባ ቀኖች ጸለየ ከዚያም በኋላ ልብሱንና አስኬማውን አለበሰው በገድል መጠመድን ጨመረ። ❤️ ከዚያም መምህሩንም አስፈቅዶ ወጥቶ ብቻውን መጋደል ጀመረ፡፡ በአቅራቢያውም አንድ ገዳም ነበረና አንድ ቀን አበ ምኔቱ ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው፡፡ መነኰሳትም ዙሪያውን ከበውት ሲያለቅሱት አገኛቸው፡፡ እንዲሁም የሰይጣን ሠራዊትም አበ ምኔቱን ከበውት ደስ ሲሰኙ አያቸውና ደንግጦ "አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድነው?" ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው፡፡ እርሱም መነኰሳቱን ከእርሱ እንዲርቁ ካደረገ በኋላ የሠራውን በደሉን እንዲህ ብሎ ነገረው "እኔ ካሁን በፊት ማንም ያልሠራውን ኃጢአት ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ፡፡ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ ሀገር ሄድኩ፡፡ "ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል" ብዬ በድፍረት በቁርባን ላይ የምቀድስ ሆንኩ፡፡ ለጠላሁትም በቁርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ እሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል፡፡ ከእናቴም ጋራ ዓሥር ጊዜ ተኝቻለሁ፣ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆዷ ውስጥ ገደልኩት፡፡ ኃጢአቴ ብዙ ነውና ተነግሮ አያልቅም፡፡ ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም፡፡ ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና" ብሎ ለአባ ለትጹን ነገረው፡፡ ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ፤ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲያሠቃዩዋት አባ ለትጹን ተመለከታት፡፡ ❤️ በዚህም አባ ለትጹን የመረረ ልቅሶን አለቀሰ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ለትጹን "ስለ ወዳጆቹ ነፍሱን አሳልፎ የሚሰጥ ያለ ከሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" የሚለውን የቅዱስ ወንጌልን ቃል አስቦ ስለዚያ ኃጥእ ሰው ነፍስ ወደ ጌታችን እየለመነ አምስት ጊዜ እስከሚሞት ሰውነቱን ሊያሠቃያት ጀመረ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መትቶ አስነሣውና እንዲህ አለው "ስለዚያ ኃጢአተኛ ነፍስ ነፍስህን አትግደል ምሕረት አይገባውምና፡፡ እግዚአብሔር እውነት ፈራጅ ስለሆነ በደሉ አይሠረይለትም"፡፡ ❤️ አባ ለትጹን ግን መሐሪ ይቅር ባይ ወደሆነ እግዚአብሔር ስለዚያ ኃጢአተኛ እየለመነ ራሱን ማሠቃየት አልተወም፡፡ ከዚህም በኋላ ራሱን በባሕር አስጥሞ ሞተ፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን መጥቶ በባሕሩ ዳር ተቀመጠና ከባሕሩ ውስጥ አውጥቶ ከሞት ያድነው ዘንድ ሚካኤልን አዘዘው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም አባ ለትጹንን ከባሕሩ አውጥቶ ከሞት አድኖ ቤታችን ፊት አቆመው፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንም "የመጥኩህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለሆነ በደሉም ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ሰው ብዙ ጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ?" አለው፡፡ አባ ለትጹንም "መሐሪና ይቅር ባይ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ግን የእኔንም ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት" ብሎ ጌታችንን ለመነው፡፡ ❤️ ከዚህም በኋላ ጌታችን የዚያን ኃጥእ ነፍስ ያመጣት ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘውና አመጣት፡፡ ጌታችንም በከበሩ እጆቹ ዳሰሳትና እንዳልተፈጠረች አደረጋት፡፡ ወዲያውም "ይህቺ ነፍስ አፈር ትሁን እንጂ ለሥቃይ ወይም ለሕይወት አትሁን" አለ፡፡ አባ ለትጹንም ስለይቅርታውና ስለቸርነቱ ገናናነት መድኃኒታችንን ፈጽሞ አመሰገነው፡፡ ❤️ ከዚህም በኋላ ጌታችን አባ ለትጹንን "የመጥኩህ ለትጹን ሆይ በእውነት እነግርሃለሁ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ በስምህ መባ ለሚያስገባ ወይም የተራበ ለሚያበላ የተጠማ ለሚያጠጣ የተራቆተ ለሚያለብስ ገድልህን ለሚጽፍ እኔ የሁሉንም ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፣ ስማቸውንም በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ፣ በጎ ዋጋቸውንም እሰጣቸዋለሁ" የሚል ቃልኪዳን ሰጥቶት ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ አባ ለትጹንም እጅግ ደስ ብሎት ወደ በዓቱ በመመለስ ብዙ ከተጋደለ በኋላ ገድሉን ፈጽሞ ሰኔ 17 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ለትጹን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትጉር ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #ባሕታዊ_አባ_ጰላሞን፦ ከተጋድሎው የተነሣ ሰይጣን እስከ ደከመ ድረስ በተራራ ላይ እግዚአብሔርን እያገለገለ በገድል ተጠምዶ ሲኖር ቀንና ሌሊት ያለቅስ ነበር፡፡ ከሰው ጋር ሳይነጋገር ብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ ሰይጣን የሚያስቅ ነገርንና ጨዋታን እያመጣበት ይፈትነው ነበር፡፡ ነገር ግን አባ ጰላሞን የጌታችንን መከራ እያሰበ ይተክዝ ያለቅስ ነበር፡፡ ሰይጣንም በዚህ ተቆጥቶ አንበሳ ሚዳቋን እንደሚያድን አባ ጰላሞንን ያድነው ነበር፡፡ በአንዲት ቀንም አባ ጰላሞን የእጅ ሥራውን ሊሸጥ ተነሠቶ ወደ ገበያ ሲጓዝ ሰይጣን ጎዳናውን አሳተው፣ ልቡንም መሰጠው እንጂ የሚያደርገውን ያውቅ ዘንድ አልተወውም፡፡