ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Ko'proq ko'rsatish606
Obunachilar
-224 soatlar
-57 kun
-1430 kun
Postlar arxiv
+9
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
በትላንትናው ዕለት የደብረ ታቦር በዓል በደማቅ ሁኔታ በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ተከብሮ አልፏል።
ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል
ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!!
💥💥💥 አቤል ለታ💥💥💥
"ታቦር እና አርሞንኤም በስምህ
ደስ ይላቸዋል፤ስምህን ያመሰግናሉ"
መዝ 88:12
📣እንኳን ለበዓለ ደብረታቦር አደረሳችሁ አደረሰን🙏
✍ኪነ_ጥበብ ክፍል
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ጌታችን_ልክ_በደብረ_ታቦር ለእነ #ቅዱስ_ጴጥሮስ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጠላቸው ሁሉ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት ለአባታችን #ለአቡነ_ሊቃኖስም እንዲሁ በበዓታቸው #በደብረ_ቆናጽል_ገዳም ሳሉ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ ለአሳያቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በሀገራችን በሚገኘው በደብረ ቆናጽል ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል። የተገለጠውም እንደነ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ፋንታ የለተሰወሩት ለአቡነ ሊቃኖስ ነው።
❤ አቡነ ሊቃኖስ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡ ይህንንም ገድለ አቡነ አረጋዊ "ቆመው ጸሎት በሚጸልዩበት ጊዜ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶችና ዓሥሩ የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና የሚያበሩበትና እንደመብረቅ የሚብለጨልጩበት ጊዜ አለ" በማለት ይገልጸዋል፡፡ በሥዕላቸውም ላይ ይህንኑ ለማሳየት አባቶቻችን የራሳቸውን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡
❤ የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል አክሱም ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፡፡ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፡፡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡
❤ ጌታችን ነሐሴ 13 ቀን ልክ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በዚህ በፎቶው ላይ በሚታየው በአቡነ ሊቃኖስ ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል።
❤ አቡነ ሊቃኖስ በደረቅ ጭንጫ ላይ ውሃ በተአምራት አፍልቀው ለቅዳሴ ማይ ጸሎት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ አቡነ ሊቃኖስም እንደ መሴ ከጭንጫ ላይ ያፈለቁትን ውሃ በወንፊት አድርገው ለአቡነ ገሪማና ለአቡነ ጰንጠሌዎን ይልኩላቸዋል፡፡ ከዳግማዊው ሙሴ ከአቡነ ሊቃኖስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ። ወይሴብሑ ለስምከ። መዝራዕትከ ምስለ ኃይል"። መዝ 88፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥23-30፣ 2 ጴጥ 1፥15-ፍ.ም እና የሐ ሥራ 7፥44-54። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥28-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላችን_ለመድኃኒታች #ለኢየሱስ_ለክርስቶስ_ከዘጠኙ_ዐበይት በዐል ለአንዱ ለሆነው #በደብረ_ታቦር_ተራራ ላይ ለቅዱስሙሴ ለቅዱስ ኤልያስ ለሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ለቅዱስ ያዕቆብና ለለቅድስጨዮሐንስ ብርሃነ መለኮቱ ለገለጠበት በዐልና እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና ቀጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ነቢያት_ከቅዱስ_ሙሴ ከልደቱ፣ #ከብንያምም ከመታሰቢያው፣ ከተጋዳይ #ከአባ_ጋልዮን ከዕረፍቱና በሰማዕትነት ከዐረፈች #ከቅድስት_ኦፍራ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን ክብር ይግባውና #የጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ታላቅና_ክቡር_በዓል ነው። በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን #ቅዱሳን_ጴጥሮስ_ያዕቆብንና_ዮሐንስን_ይዞ_ወደ_ታቦር_ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
❤ ስለ እነርሱም ጌታችን "የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ" አለ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
❤ ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው "አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ለአንተ አንድ ለሙሴ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ"። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት።
❤ ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና እራሱን የሚሰውርበት ቤት ይሠራለት ዘንድ የተጋገረው ነገር ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። እራሱንና ባልጀሮቹን ሐዋርያት እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ስለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያ ጊዜ ፍፁማን አልሆኑምና።
❤ እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ አነሆ ደመና ጋረዳቸው። የጌታችንን ጌትነነቱ የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት"።
❤ ሙሴና ኤልያስም ከእነርሱ ጋር ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
❤ ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያ ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሳው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያወጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ስልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ያስነሳቸው ማንም አይችልም።
❤ ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይ እና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና።
❤ የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደሙታን ሆኑ ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስ ወደ ቦታው ተመለሱ።
❤ ሐዋርያትን በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የደዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
❤ እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ድንግል ማርያም በአበሠራት ጊዜ "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው" እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ "ለመግሥቱ ፍጻሜ የለውም" እንዴት አላት። ሰው ካልሆ በበረት እንዴት አስተኙት አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው "ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው" እያሉ እንዴት አመሰገኑ።
❤ ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውሃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆ አልዓዛር ከመቃብር እንዴት ሊያስነሳው ቻለ።
❤ ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለመለየት አንድ አካል አንድ ባሕሪ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሁልጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬ ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ተጋዳይ_አባ_ጋልዮስ፦ ይህም በቀንና በሌሊት ጸሎት የማይታክት ተጋዳይ ሆነ ጎልማሳ ሆኖ ሳለ ከመነኰሰም ጀምሮ እስከ ሸመገለ ድረስ ከበአቱ ቅጽር ውጪ አልወጣም ከማህበር ጸሎት ጊዜ በቀር ከመነኰሳቱ ማንም አያየውም።
❤ ሰይጣናትም ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ መነኰሳትን ተመስለው ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ገብተው እንዲህ አሉት "እኛ ተሰውረን የምንኖር ገዳማውያን ነን ከእኛ አንዱ በሞት ስለተለየ ከእኛ ጋር ልንወስድህ ወደን ወደ አንተ መጣን" ለእርሱም ቃላቸው እውነት መስሎት ልብስና ሲሳይ ወደ ማይገኝበት ጠፍ ወደ ሆነ ተራራ ላይ እስከ አደረሱት ድረስ አብሯቸው ሔደ።
❤ ሲጠቃቀሱበትም በአየ ጊዜ ሰይጣናት መሆናቸውን አውቆ በላያቸው በመስቀል ምልክት በአማተበ ጊዜ ተበተኑ። በሚመለስም ጊዜ በወዲያም በወዲህም መንገድ አጣ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታችን ጸለየ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም የሚዘዋወሩ ከአባ ሲኖዳ ገዳም የሆኑ መነኰሳት ተገለጡለት እነርሱም የዳዊት መዝሙር ያገቡ ነበር ስለ ሥራው ጠየቁቱ በእርሱ ላይ የደረሰውን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ከእነርሳቸው ጋር ወስደውት በፀሐይ የበሰለ ዓሣ እየተመገበ ከእርሳቸው ጋር አንዲት ዓመት ሙሉ ኖረ።
❤ ያመነኰሰው መምህሩ አባ ይስሐቅም ወሬውን በአጣ ጊዜ ፊቱን ያሳየው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አባ ጋልዮንም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ርሱ መጣ አባ ይስሐቅም በአየው ጊዜ በእርሱ ደስ አለው "ወዴት ነበርክ" አለው እርሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ነገረው።
❤ ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሶ ነሐሴ 13 ቀን በሰላም ዐረፈ። መነኰሳቱም በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጋልዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ የነሐሴ 13 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ጸርሐ_አብ_ኪያከ_በውዳሴ። ወበርእስከ ጸለለ መንፈስ ቅዳሴ። አመ ገበርከ በታቦር እግዚኦ ምስለ ሐዋርያት ክናሴ። ኤልያስ መንገለ ቆመ ወኀበ ሀለወ ሙሴ። ዘመለኮትከ ወልደ ከሠትከ ሥላሴ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_13።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል። ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉአን። ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ። መዝ 67፥15-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥1-14።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለጾመ_ፍልሰታ_ሁለተኛ_ሳምንት ለዕለተ እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ በ፪ ሃሌ ሉያ "ዛቲ ይእቲ #ማርያም_ማኅደረ_መለኮት እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን #በከመ_ይቤ_ዳዊት በመዝሙር አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር አድባረ ድኁኃን ተሰማየት #ዛቲ_ይእቲ_ቅድስት_ድንግል ተዓቢ እምኵሉ ፍጥረት ኢያውዐያ እሳት መለኮት"። ትርጉም፦ ሰንበተ ክርስቲያን የተሰኘችው #የመለኮት_ማደሪያ_ይህቺ_ማርያም_ናት። #ዳዊት_በመዝሙር ዐይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ (አቀናሁ) ብሎ እንደተናገረው ያቺ ተራራ የተራሮች ራስ ይህቺ #ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ናት፤ እርሷም ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች የመለኮት እሳት አላቃጠላትም። #ሊቁ_ቅዱስ ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ ኃረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም"። መዝ 131፥13-14 ወይም 120፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-19፣ 2ኛ ዮሐ 1፥1-8፣ የሐዋ ሥራ 27፥31-38። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39፥47። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የፆም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል ወደ #ንግሥት_ቅድስት_ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ ለተላከበት ለእርሱም ጠላቶቹን አሸንፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ለሰጠበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓሉ በሰላምና በጤና አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰበው፦ ከንጉሥ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ_ወደ_ሮሜ ከተማ ከገባበትና በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ከነገሠበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ የከበረ #የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ እሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስካሸነፍቸው መንግሥቱን እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው።
❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እንድናደርግ አዘዙን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚችም ቀን #ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮች ሁሉ ላይ ነገሠ። ዜናውንም መጋቢት ሃያ ስምንት ቀን ላይ ጽፈናል። ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 12 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_መልአከ_ኪዳኑ_ወምክሩ። ለእግዚአብሔር ልዑል ዘግሩም ግብሩ። በረድኤትከ ረዋጺ ዘአሠረ ነፋስ አሠሩ። ሶበ ላዕሌየ እኩየ መከሩ። ጉባኤ ፀርየ #ሚካኤል ዝሩ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_12።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ማኅሌቱ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስመከ። መዝ137፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥31-ፍ.ም።
+6
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያክ ፲፪ኛ ዓመት የዕረፍተ ሥጋ የመታሰቢያ ጸሎተ ፍትሐት ብፁዕ አቡነ አብርሐም የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን #ለአውሲም_አገር_ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ሞይስስ_ለዕረፍትና ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ለሆነ #ለቅዱስ_አብጥልማዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በሰማዕትነት ከአረፉ በአንጾኪያ ከተማ የሠራዊት አለቃ #ከነበረው_ከቅዱስ_ፋሲለደስ በሰማዕትነት ከዐረፉ ማኅበሮች #ከሦስት_መቶ ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአውሲም_አገር_ኤጲስቆጶስ_አባ_ሞይስስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ድንግልም ነበረ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትንም ሁሉ ተምሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገባ። በአንድ ጻድቅ ሰው ዘንድም መነኰሰ በዚያም እያገለገለ በጠባብዋ መንገድም ተጠምዶ ያለመብልና መጠጥ ያለእንቅልፍም እየተጋደለ ዐሥራ ስምንት ዓመት ኖረ።
❤ ከብዙ ፍቅርና ትሕትና ጋር ዘወትር በጾምና በጸሎት ይተጋ ነበር። ትሩፋቱም በበዛ ጊዜ ከአባ ገሞስ በኋላ በአውሲም ከተማ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው። ይህም አባ ሞይስስ በተሾመ ጊዜ ትሩፋት መሥራትን አብዝቶ ጨመረ ስለ እነርሱም በጸሎት እየተጋ መንጋዎቹን ነጣቂዎች ከሆኑ ከዲያብሎስ ተኲላዎች ጠበቀ።
❤ በሕይወቱም ዘመን ሁሉ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ የሚሰበስብ አልነበረም። አባ ሚካኤልም በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜና ደሙ ሳይፈስ ሰማዕት በሆነ ጊዜ ይህ አባ ሞይስስ በእሥር ቤት ከእርሱ ጋር ነበር ብዙ ስለገረፉት እግሮቹንም ለረጅም ጊዜ በእግር ብረት አሥረው ስለ አሠቃዩት ብዙ መከራ ደረሰበት።
❤ በዚህ አባት ሞይስስ እጅም እግዚአብሔር ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ የሚያውቁትም በተአምራቶቹ ደግነቱንና ትሩፋቱን ተረዱ። ዳግመኛም ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ከመሆኑም በፊት ብዙ ነገርን ተናገረ እንደተናገረውም ይሆን ነበር። የምስር ኤጲስቆጶስ ስለሆነው ስለ አባ ቴዎድሮስ ከሔደበት እንደማይመለስ ትንቢት ተናግሮበት እንዲሁ ተፈጸመበት።
❤ ዳግመኛም ሀብተ ፈውስ ተሰጥቶት ነበር። ብዙዎች ሕሙማንንም ፈወሳቸው። ገድሉንም በመልካም ሽምግልና ፈጸመ። እግዘአብሔርንም አገልግሎ ጥቂት ታመመ የሚያርፍበትንም ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና ባረካቸው በቀናች ሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ነሐሴ 11 ቀን ዐረፈ። አለቀሱ ለትም ለኤጲስቆጶሳትም እንደሚገባ በዝማሬና በማኀሌት በታላቅ ክብር ገንዘው ቀበሩት ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም የሚሆን ፈውስ ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋነ ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት በአባ ሞይስስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_አብጥልማዎስ፦ ይህም ቅዱስ ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ነው። ቅዱሱንም ክርስቲያን እንደሆነ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። መኰንኑም በአስቀረበው ጊዜ በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃይቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
❤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አብጥልማዎስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ዕብል_ለሞይስስ_ፍጹም። ኤጲስቆጶስ ዘብሔረ አውሲም። ለጸሎት ዘተግሀ ወተጋደለ በጾም። አመ ርሥእናሁ በንስቲት ሕማም። እምፃማ ዓለም አዕረፈ ዮም"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ(አርኬ) #የነሐሴ_11።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ። ወትሠይም(ሚ)ዮሙ መላእክተ በኵሉ ምድር። ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ"። መዝ 44፥16-17። የሚነበቡት መልክታት 1ኛ ቆሮ 5፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥14-20 እና የሐ ሥራ 12፥18-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥20-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለቢካቦስ_ዘኮኖሙ_ተበያጼ። ለተስዓቱ ወኃምስቱ ሰማዕታተ ክርስቶስ እንበለ ግጋፄ። ጣዖታተ ይዝልፍ ወንጉሠ ዐማፄ። ለዝ ጥቡዕ ኢመጽኦ ድንጋፄ። እስከ መተሩ ሥጋሁ በማሕፄ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ_የነሐሴ_10።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "በማኅበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር። ወለአምላክነ በአንቅዕተ እስራኤል። ህየ ብንያም ወሬዛ በኃይሉ"። መዝ 67፥26-27። የሚነበበው ወንጌል ማር 11፥23-27።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ፡፡ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ። ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ"። መዝ 73፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥22-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥7-13 እና የሐዋ ሥራ 4፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳ #ለማኅበረ_በኵር_መታሰቢያ_በዓል፣ በእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት #በቅዱስ_ድሜጥሮስ ዘመንና በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመነ መግሥት ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_መጥራ ለዕረፍት በዓል፣ በከሀዲ መክስምያኖስ እጅ ሰማዕት ለሆነ #ለቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ ለዕረፍት በዓል፣ እስሙናይን ከሚባል አገር ለሆኑ ለከበሩ #ለቅዱሳን_ከቢካቦስና_ዮሐንስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ_ጋር_ሰማዕትነት_ከተቀበሉ_ከሠላሳ_ሺህ_ማኅበርተኞቹ_ሰማዕታት፣ ከቅዱሳን #ከቢካቦስና_ዮሐንስ_ከእነርሱ_ጋር_ሰማዕትነት ከተቀበሉ #ከዘጠና_አምስት_ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ በዚህችም ቀን #የማኅበረ_በኲር በዓልን እንዲከበር የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓት ሠሩ እነዚህም #ከአቤል_ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲሁም እስከ ምጽአት #ስለጽድቅ_ደማቸውን_ስለሚያፈሱ እና #ደስተኞች_ስለ_ሆኑት_አዕላፍ_መላእክትም ሁሉ። እግዚአብሔር በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መጥራ፦ ይህም ቅዱስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖት መስገድን የሚያዝ የንጉሡን ደብዳቤ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ ወዲያውኑ ሒዶ ከወርቅ የተሠራ የአጵሎንን ክንድ ሰረቀ በየጥቂቱም ሰባብሮና ቆራርጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው።
❤ የጣዖቱም አገልጋዮች ክንዱ ተቆርጦ አጵሎንን በአገኙት ጊዜ ስለርሱ ብዙዎችን ሰዎች ያዟቸው። በዚያንም ጊዜ ወደ መኰንኑ ቀርቦ ክርስቲያን እንደሆነ በፊቱ ታመነ ሁለተኛም "የአጵሎንን የወርቅ ክንድ የወሰድኩ እኔ ነኝ ለድኆችና ለችግረኞችም ሰጠኋቸው" አለው። መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ አስጨናቂ የሆነ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤና አወጣው።
❤ ከዚህም በኋላ እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ ብዙ ደም ከአፍንጫው ወደ ምድር እስከ ሚወርድ ዘቅዝቀው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ቅዱስ መጥራንን ፈታው ከተሰቀለበትም አውርዶ በመዳሠሥ አዳነው። አንድ ዕውር ሰውም መጣ ከአፍንጫው ከወረደውም ደም ወስዶ ዐይኖቹን ቀባ ወዲያውኑ አየ። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ መጥራ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ፦ ይህም ቅዱስ በንጉሥ መክስምያኖስ ፊት በአቆሙት ጊዜ "ለአማልክት ሠዋ" አለው። የከበረ ሐርስጥፎሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ ለእርሱም እሠዋለሁ"። ንጉሡም ተቆጥቶ ሥጋው ተቆራርጦ በምድር ላይ እስቲወድቅ በበትር ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ወህኒ ቤት ጣሉት በላህያቸውም እንዲአስቱት ሁለት ሴቶችን ንጉሡ ወደርሱ ላከ ቅዱሱ ግን የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራቸው የዛሬ የሆነ የዚህንም ዓለም ኃላፊነት አስገነዘባቸው ወደ መክስምያኖስም በተመለሱ ጊዜ "እንዴት አደረጋችሁ" አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት "በከበረ ሐርስጥፎሮስ አምላክ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ እኛ እናምናለን" ንጉሡም ሰምቶ አንዲቱን በዕንጨት ላይ ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ሁለተኛዋን በአንገቷ ደንጊያ አንጠልጥለው ቊልቊል እንዲሰቅሏት አዘዘና ምስክርነታቸውን እንዲህ ፈጸሙ።
❤ ከዚህም በኋላ ዕንጨቶችን ሰብስበው በማንደጃው ውስጥ አድርገው አነደዱ የከበረ ሐርስጥፎሮስን እጅና እግሩ እንደ ታሠረ ከውስጡ ጨመሩት ያን ጊዜም "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" አለ እሳቱ ከቶ ምንም አልነካውም። ሕዝቡም ይህን አይተው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ዐሥር ሺህ ያህል ሰዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።
❤ ሁለተኛም የብረት ሠሌዳዎችን በእሳት አግለው አመጡ ቅዱሱንም በላያቸው በአስተኙት ጊዜ ምንም ምን የነካው የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃያ ሺህ አንድ መቶ ሰዎችና አርባ ሕፃናት አምነው ምስክር ሁነው ሞቱ።
❤ ንጉሥ መክስምያኖስም አይቶ እጅግ ተቆጣ የቅዱስ ሐርስጥፎሮስንም ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።ከንጉሡም ዘንድ በወጣ ጊዜ ጸሎትን አደረገ ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ ከዚህም በኋላ ምስክርነቱን ፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ቢካቦስና_ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ቢካቦስ ክርስቲያን ሲሆን በሥውር ወታደር ሆነ። አንጥያኮስ ለሚባል መኰንንም ስለ ዮሐንስና ስለ ኤጲስቆጶስ አባ አክሎግ ከተርሴስ አገር ስለ ናሕር ስለ አባ ፊልጶስም እነርሱ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ነገር ሠሩባቸው።
❤ መኰንኑም እነርሱን አቅርቦ "እናንት ክርስቲያኖች ናችሁን?" አላቸው "እኛ በእውነት ክርስቲያን ነን በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን" አሉት። መኰንኑም "ይህን ነገር ትታችሁ ለአማልክት ሠዉ" አላቸው። ቅዱሳኑም እንዲህ ብለው መለሱለት "እኛስ ለረከሱና ለተናቁ አማልክት አንሠዋም ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከጌታችን ኢየሱስ በቀር"። መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ምስክርነታቸውንም እስከፈጸሙ ድረስ አሠቃያቸው።
❤ ቅዱስ ቢካቦስን ግን ከአሠቃየው በኋላ አሠረውና ከመንኰራኲር ውስጥ ጨመረው ዘቅዝቆም ሰቀለው ሕዋሳቱንም ቆራረጠው ጌታችንም ያስታግሠውና ያበረታው ነበር ያለ ጉዳትም ጤናማ አድርጎ አስነሳው።
❤ ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ከብዙዎች ሰማዕታት ጋራ ላከው በመርከብም ውስጥ እህልና ውኃ ሳይቀምሱ ሃያ ስድስት ቀኖች ኖሩ። በርሙን ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይተው በምሳር ቆረጡት የምስክርነቱንም ተጋድሎ ፈጸመ መንግሥተ ሰማያትም አክሊልን ተቀበለ።
❤ ከሀገረ በርሙን ሹማምንቶችም አንድ ባለ ጸጋ ሰው መጥቶ የቅዱስ ቢካቦስን ሥጋ ወስዶ በአማሩ ልብሶች ገነዘው ወደ አገሩ እስሙናይንም ላከው። በመከራውም ወራት ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ ከእርሱም ጋራ የተገደሉ ዘጠና አምስት ሰዎች ናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ለቅዱሱ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ቢካቦስና ዮሐንስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ይድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 10 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_እብል_ኪያክሙ_ማኅበረ። እምነቢያት ቅድመ ወእምወንጌላውን አኅረ። ፍሡሐን አእላፍ #እለተሳተፍክሙ_በኲረ። #ጽዮንሃ በጺሐክሙ ሀገረ። በጸሎትክሙ ቅድስት ዝክሩነ ወትረ"።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊ_ጻድቅ ለአባታችን #ለአቡነ_ለዓቢየ_እግዚእ ተከዜ ወንዝ እንደ ባሕረ ኤርትራን ከፍለው ለተሻገሩበትና ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብን ላሳመኑበት ዓመታዊ ለተአምር በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ዓቢየ_እግዚእ_ያደረጉት_ተአምር_ይህ ነው፦ አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ ዐሥር ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ።
❤ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይሕም ዘወትር ነሐሴ ዐሥር ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል። ከአባታች አቡነ ዓቢየ እግዚእ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳዮስ አበበ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን #ለአባታች_ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል (በዚች ቀን አባታችን እስትፋሰ ክርስቶስ ከሰማይ የወረደውን የቊርባን ኅብስት ተቀብለው ያቀበሉበት ነው ብሎ ገድላቸው ይናገራል)ና ስጥኑፍ ከሚባል አገር ለሆኑ ለሰማዕቱ ለካህኑ #አባ_ኦር ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ጳጳስ_አባ_ጲላጦስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ ስጥኑፍ ከሚባል አገር የሆነ የከበረ #ቄስ_አባ_ኦሪ፦ ይህ ቅዱስ ብዙ ርኅራኄ ያለው በሥጋው በነፍሱም ንጹሕ የሆነ ነው ብዙ ጊዜም አምላካዊ ራእይን ያያል። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት።
❤ ከዚህም በኋላ የአባ ኦሪ ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ ተሰማ ወደርሱም አስቀርቦ "ለአማልክት ዕጣን አቅርብ" አለው እርሱም "ለረከሱና ለተሠሩ አማልክት አልሠዋም" ብሎ እምቢ አለው። መኰንኑም ተቆጥቶ በብዙ ሥራ አስፈራራው ቅዱስ ኦሪም ሥቃዩን ምንም ምን አልፈራውም ጹኑ ሥቃይንም አሠቃየው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ አገር ላከው በዚያም ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃይተው በወህኒ ቤት ጣሉት። በዚያም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ በሽተኞችን ፈወሳቸው ። ዜናውም በተሰማ ጊዜ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ከየአገሩ ብዙዎች ሰዎች ወደርሱ መጥተው አዳናቸው። ይህንንም መኰንኑ ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ።
❤ ከዚህም በኋላ የከበረ ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ ገንዘው ወደ ሀገሩ ስጥኑፍም ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በማመንም ለሚመጡ በሽተኞች ሁሉ ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ ኦሪ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 9 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 1፥12-24፣ 2ኛ ዮሐ 1፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥19-25። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን #ለካህኑ_ቅዱስ_አልዓዛርና_ለሚስቱ #ቅድስት_ለሰሎሜ ለሰባቱ ልጆቻቸው #አንኤም፣ #አንጦኒኃስ_ዖዝያ_አልዓዛር_አስዮና_ስሙና #መርካሎት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_አሞን ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ካህኑ_ቅዱስ_አልዓዛርና_ሚስቱ_ሰሎሜ ሰባቱ ልጆቻቸው #አንኤም_አንጦኒኃስ_ዖዝያ_አልዓዛር፣ #አስዮና_ስሙና_መርካሎስ፦ ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት።
❤ የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው። ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኰል እንዲገባ አደረጉት።
❤ በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የእሊም ቅዱሳንም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ። ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ። ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ"። መዝ 57፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥24-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 7፥12-26። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከሰባቱ ከዋክብትን አንዱ ለሆኑት ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ በመሔድ ታላቁ ገዳም ደጋ እስጢፋኖስን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ_ዘጣና፡- ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኵስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡
❤ አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ "ዓቃቤ ሰዓት" እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
❤ ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡
❤ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ "ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ" ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ "ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት (ገንፎ)" ብለው በመናገር ምላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡
❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡
❤ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡
❤ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡
❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ከአቡነ ኂሩተ አምላክ ረድኤት በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
#ነሐሴ ሰባት ጽንሰታ ለማርያም ድንግል
#ጴጥርቃ እና #ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ፡፡
አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን ፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ #ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ #ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ #7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ #ጨረቃዋም #ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧችኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ #ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ #የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደችውን ሃናን ወለደች ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቧት::
እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡-
ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ::
ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተእግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።
ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው፤ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው፡፡
ሃናም እኔም አየሁ አለችው ምን አየሽ ቢላት ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ነጭነቱ ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው::
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ ነሐሴ ሰባት በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሏችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡:
ለአባ ሕርያቆስ ,ለቅዱስ ኤፍሬም ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ጾሙን ጾመ ሥርየት ጾመ መድኃኒት ያድርግልን አሜን!
#ጾመ ፍልሰታ
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፮ (6) ቀን።
❤ እንኳን #ጌታችን_ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ላወጣላት #ከ36_ቅዱሳት_አንስት አንዷ ለሆነችው ለእናታች #ለቅድስት_መግደላዊት_ማርያም_ለዕረፍት በዐል መታሰቢያና #ከቂሳርያና_ከቀጰዶቅያ አገር ለሆነች ለከበረች #ለቅድስት_ኢየሉጣ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰበው፦ #ከአባ_ሲኖዳ_ረድእ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዊፃ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_መግደላዊት_ማርያም፦ ይችም ቅድስት ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ ያገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ የነበረች እስከ ቀበሩትም ድረስ ያልተለየች እናት ነች።
❤ በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች። መልአኩም "እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል" አላቸው ። ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት "ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው" አላት። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው።
❤ ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀብላለች።
❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት። ተጋድሎዋንም ፈጽማ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ። እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በቅድስት መግደላዊት ማርያም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #ከቂሳርያና_ከቀጰዶቅያ አገር የሆነች #ቅድስት_ኢየሉጣ፦ ይቺም ቅድስት ከወላጆቿ ብዙ ገንዘብ ወረሰች ከታጋዮችንም አንዱ በግፍ ተነስቶ ጥሪቷን ሁሉ ወንዶች ሴቶች ባሮቿን ለዳኛ መማለጃ በመስጠት ነጠቃት።
❤ ይህም ዐመፀኛ እንደምትከሰውና ሐሰቱንም እንደምትገልጥበት በአወቀ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ገዢ ሒዶ ክርስቲያን እንደ ሆነች ወነጀላት። በልቧም እንዲህ አለች "የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ አይደለምን እነሆ እርሱን ነጠቁኝ የሰማይ ድልብን ገንዘብ ካደረግሁ ማንም ከእኔ ነጥቆ ሊወስድብኝ አይችልም"።
❤ ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ቀረበች በፊቱም ቁማ እንዲህ አለች "እኔ ክርስቲያዊት ነኝ ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ"። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ወደ እሳትም ውስጥ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ነፍሷንም ነሐሴ 6 ቀን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች።
❤ ነገር ግን እሳቱ አልነካትም ምንም ምን አላቃጠላትም ከውኃ ውስጥ እንደሚወጣም ከእሳት ውስጥ አወጧት። ስለ ገንዘቧና ስለ ጥሪቷም የማያልፍ የሰማይ መንግሥትን ወረሰች። ቅዱስ ባስልዮስም ብዙ ወድሷታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአባ_ሲኖዳ_ረድእ_ቅዱስ_አባ_ዊፃ፦ እርሱም ከእግዚአብሔር ብዙ ምሥጢራትን የሰማ የአባ ሲኖዳንም ገድል እንደ አየና እደንሰማ የጻፈ ነው። መልካም አካሔዱንም እንዴት እንደፈጸመ ከእርሱ ከአባ ሲኖዳ ሰማ እግዚአብሔርም አገልግሎ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም ዐረፈ። እግዚአብሔር በአባ ዊፃ ጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 6 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለኢየሉጣ_እንበይነ_ምግባር_ሠናይ። በውስተ እቶን ዘእብዋእ በውዴተ ብእሲ እኩይ። እንዘ ኢሀሎ ላዕሌሃ አሠረ ዋዕይ። ወጽአት እምእሳት ከመ ዘወጽአ እማይ። አምሳለ ፍቱን ወርቅ ወብሩር ጽሩይ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ_ነሐሴ 6።
+ + +
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ። ወለገጽኪ ይትመሀለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሴቦን"። መዝ 44፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥10-22፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማር 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፮ (6) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዓሣ ከሰማይ ለሚዘንብላቸው ለመናኔ መንግሥት #አቡነ_ኢዮስያስ_ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #መናኔ_መንግሥት_አቡነ_ኢዮስያስ፡- ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የንጉሥ ዓምደ ጽዮን ልጅ ናቸው፡፡ ጥር 6 ቀን ሲወለዱ ቅዱሳን መላእክት ከበዋቸው ታይተዋል፡፡የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በዓለም ነግሠው መኖርን ንቀው በመመነን በመጀመሪያ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ገቡ፡፡ አቡነ ኢዮስያስ በሐይቅ ገዳም ለ14 ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በዚያም ብሉይንና ሐዲስን፣ መጽሐፈ መነኰሳትንና መጽሐፈ ሊቃውንትን አጠናቀው ተምረዋል፡፡ በኋላም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ትግራይ ደብረ በንኰል ገዳም ሄዱ፡፡ በደብረ በንኰልም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በታላቁ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ መነኰሱ፡፡ ቆብ የተቀበሉት ግን ከአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡
❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ሰባት ዓመት ከእሳቸው ጋር ካቆዩአቸው በኋላ አቡነ ኢዮስያስን ወንጌልን ዞረው እንዲሰብኩና ገዳም እንዲገድሙ በማዘዝ መርቀው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢዮስያስም ወደ አዱዋ አውራጃ ዛሬ በስማቸው ወደተጠራው ገዳም ሄደው በቦታው ላይ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ገዳሙንም ከገደሙት በኋላ በርካታ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ ያፈለቁት ጠበል በፈዋሽነቱ የታወቀ ነው፡፡ በየዓመቱ በዕረፍታቸው ዕለት ነሐሴ 6 ቀን ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ ይዘንባል፡፡ ይህ አሁንም ድረስ በየዓመቱ ነሐሴ 6 ቀን በግልጽ እየታየ ይገኛል፡፡
❤ አቡነ ኢዮስያስን ከሃዲያን የሆኑ አረማውያን ቢያስቸግሯቸው ጻድቁም በጸሎት ቢያመለክቱ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ነጭ የንብ መንጋ መጥቶ አረማውያኑን አንጥፍቶላቸዋል፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው አራት ሙታንን በአንድ ጊዜ ከሞት ያስነሡ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በገዳማቸው ውስጥ በበዓላቸው ቀን ገድላቸው ሲነበብ አጋንንት ከሰው ልቡና እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፡፡
❤ ጻድቁን እንደ ረድእ ሆኖ የሚያገለግላቸው አንበሳ ነበራቸው፡፡ ወደ ገዳማቸው መጥቶ መካነ ዐፅማቸውን የተሳለመውን እስከ 14 ትውልድ ድረስ እንደሚምርላቸው ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ልጁን በስማቸው የሰየመ ቢኖር የሰይጣንን ፊት ፈጽሞ እንደማያይ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከአቡነ ኢዮስያስ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
➩** ለምን ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና አላት ቢሉ ?
ትርጓሜው :*
ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን አእምሮውን ጥበቡን በልቦናችን ሳዪልን አሳድሪልን፡፡
#ቅድስት አለ ንጽሕት ጽንዕት ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡
#ንጽሕት አለ :- ሌሎች ሴቶች ቢነጹ ከነቢብ(ከቃል ከመናገር)፣ ከገቢር(ከሥራ ከድርጊት) ነው ከሐልዮ (ከሐሳብ)አይነጹም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ(ከቃል ከመናገር) ከገቢር(ከሥራ ከድርጊት) ከሐልዮ (ከሐሳብ) ንጽሕት ናትና፡፡
#ጽንዕትም አለ :- ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፡፡ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ(ከመፀነሷ በፊት) ጊዜ ፀኒስ(በፀነሰች ጊዜ) ድኅረ ፀኒስ(ከፀነሰች በኋላ) ቅድመ ወሊድ(ከመውለዷ በፊት) ጊዜ ወሊድ(በወለደች ጊዜ) ድኅረ ወሊድ(ከወለደች በኋላ) ፅንዕት በድንግልና ናትና፡፡
#ክብርትም አለ:- ሌሎች ሴቶችን ብናከብራቸው ጸድቃን ሰማዕታትን፤ ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳትን፤ ቀሳውስት ዲያቆናትን፤ ነገሥታት መኳንንትን ወልዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ፣ እመ አምላክ፣ እመ ብርሃን ብለን ነውና፡፡
#ልዩም አለ:- እናትነት ከድንግልና አስተባብራ የተገኘች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችም ወደፊትም አትኖርምና ፡፡
#ሰአሊ/ሰዓሊ ለነ አለ፡፡
ዐይኑ ‹ዓ› ነው ያሉ እንደሆነ (ሰዓሊ ለነ) አእመሮውን ለብዎውን ሳይብን አሳድሪብን ማለት ነው፡፡ አልፋው ‹አ› ያሉ እንደሆነ (ሰአሊ ለነ) ለምኚልን ማለት ነው፡፡
