ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Ko'proq ko'rsatish603
Obunachilar
-224 soatlar
-57 kun
-1430 kun
Postlar arxiv
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
ሐምሌ 14 የሰንበት ትምህርት ቤታችንን 12ኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቶቻችንን አጠናቀን እናንተ ወንድም እህቶቻችንን በመጠባበቅ እንገኛለን በዕለቱም ሁላችንም ነጭ በመልበስ 7:00 ሰዓት በሰንበት ትምህርት ቤታችን በመገኘት እንድናከብር እና በተለያዩ ምክንያት ለራቁን ወንድም እህቶቻችን ባሉበት ድረስ ሄደን በመጥራት በመንገር አብረን እንድንመጣ በሰዓት እንድንገኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
ሐምሌ 14 የሰንበት ትምህርት ቤታችንን 12ኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቶቻችንን አጠናቀን እናንተ ወንድም እህቶቻችንን በመጠባበቅ እንገኛለን በዕለቱም ሁላችንም ነጭ በመልበስ 7:00 ሰዓት በሰንበት ትምህርት ቤታችን በመገኘት እንድናከብር እና በተለያዩ ምክንያት ለራቁን ወንድም እህቶቻችን በመንገር በሰዓት እንድንገኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
ለሚሰማው ሁሉ መጽናኛ ይሆን ዘንድ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉና ወደ ገዳማትም ላክሁ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ኪሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ሚሳኤል፦ ይህም አባት አባ ኪሮስ የቀበረው የንጉሥ ልጅ ድኃ የነበረ ነው። ዜናውም እንዲህ ነው። አባ ኪሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሳት ገዳም ሔደ። ከዚያም ደርሶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተሳለማት በዚያም አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ሥዕል አየ። ከዐይኖቹም ዕንባ እያፈሰሰ "እመቤቴ ሆይ አስቢኝ" አላት ሥዕሊቱም "ኪሮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው ከዚህም አትለፍ የአባትህን ዐፅም ትጠብቅ ዘንድ ወደ ማደሪያህ ተመለስ እንጂ" አለችው። አባ ኪሮስም ይህን ሰምቶ ከሥዕሏ ፊት ሰባት መቶ ሰግደትን ሰገደ። በዕብራይስጥም ቋንቋ "እንግዳ ነህና በቃህ በምሕረት መዝገብም ተመዝግቦልሃል" የሚለውን ቃል ሰማ።
❤ ከዚያም በአለፈ ጊዜ መነኰሳቱ መልኩ የተዋበ ሁለመናውም ያማረ እንደሆነ ተመለከቱ። እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ "ይህ መነኵሴ ከመንግሥት ከተማ ከግብጽ አገር የመጣ ነው ሰውነቱ በጾምና በጸሎት አልጠወለገምና"። እጅግም ነቀፉት አልተቀበሉትም።ነገር ግን ወደ ሌላ ወደሚንቁት ቦታ ሰደዱት።
❤ በዚያም መስፈርስ በሚባል ሕማም ለብዙ ጊዜ የታመመና በምድር ላይ የተጣለ ድኃ ሰውን አገኘ። በራስጌውም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በግርጌው ቅዱስ ገብርኤልን በቀኙም ቅዱስ ሩፋኤልን በግራውም ቅዱስ ሰዳካኤልን አየ። እነርሱም በክንፋቸው ጋርደውት ነበር ከሰውም ያለርሱ ያያቸው አልነበረም። "በገዳዩች ፊት ሞትን የማይፈራ ጐበዝ እንዴት ነህ" ብለው ሰላምታ ሰጡት። አባ ኪሮስም አደነቀ "በልዕልና ነዋሪዎች ሆይ ከዚህ ለምን ተቀመጣችሁ" አላቸው "ይህንን ድኃ እንድንጠብቀው ከእግዚአብሔር ታዘናል" አሉት አባ ኪሮስም "እስከ መቼ ነው" አላቸው። "ከዚህ ድካም እስከሚአሳርፈው ድረስ ነው" አሉት።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ታመመው ደኃ ተመልሶ "በዚህ ቦታ ከኖርህ ምን ያህል ዘመን ነው" አለው በሽተኛውም "ሠላሳ አምስት ዓመት ነው" አለው ሁለተኛም "ከታመምክ ስንት ዓመት ነው" አለው "ሃያ ዓመት ነው" ብሎ መለሰ። "አበ ምኔቱና የገዳሙ መነኰሳት ይጐበኙሃልን" ብሎ ጠየቀው በሽተኛውም "አባቴ ሆይ የለም አይጐበኙኝም ፊታቸውን ከአየሁ ዓሥራ አምስት ዓመት ይሆናል" ብሎ መለሰ።
❤ አባ ኪሮስም "ና ንገረኝ አባትህ ማነው እናትህስ ማናት" አለው በሽተኛውም እንዲህ ብሎ መለሰ "አባቴ የኬልቄዶን ንጉሥ እናቴም የራሕራሕ ንጉሥ ልጅ ናት። አባቴ ኪሮስ ሆይ እውነት እልሃለሁ በአባቴ ቤት ያሉ ሰዎች ወርቁንና ብሩን ቀጭኑንም ልብስ በእግሮቻቸው ይረግጡአቸዋል"። አባ ኪሮስም "ወደዚች ገዳም ማን አደረሰህ" አለው ድውዩም "እንዳንተ ያሉ ሁለት ሰዎች ወደ አባቴ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ። እኩለ ሌሊትም ሲሆን ፊቱ ብሩህ የሆነ ሰውም ወደኔ መጣ "ሚሳኤል ብሎ ጠርቶ ሲነጋ ተነሥተህ ከእነዚህ ቅዱሳን ጋራ ሒድ" አለኝ በእንዲህ ያለ ሥራ ወጥቼ ወደዚህ ቦታ ደረስሁ ምንም በጎ ሥራ ሳልሠራም እንደ እነርሱ ሆንሁ"።
❤ አባ ኪሮስም "እኔ አጽናናሃለሁና ወንድሜ ሆይ ስማ ስሙ በብኑዳ የሚባል አንድ እጅግ ድኃ የሆነ በበረሃ የሚኖር መነኵሴ ነበረ። የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ወደርሱ መጥቶ አሳተው እግዚአብሔርም ሥጋውን ለአንበሳና ለሰማይ ወፎች ሰጠ እርሱም በወገን የከበረ ከሮም ንገሥ በታች የሚገዛ የኬፋዝ ንጉሥ ልጅ ነበረ"። ሁለተኛም እነግርሃለሁ "የሮሜ ንጉሥ ልጅ የሆነ አንድ ድኃ ነበረ። እርሱም ከበትር ብቻ በቀር ከአባቱ ቤት ምንም ሳይዝ በቀስታ ወጣ ያንንም ሰው እኔ እጅግ አውቀዋለሁ። ከገዳም ወደ ገዳም ከተራራም ወደ ተራራ ይዞር ነበር ሞቱንም አላስተዋልኩም ሕይወቱንም አላወቅሁም"።
❤ ዳግመኛም "አንድ የንጉሥ ልጅ ድኃ ነበረ። እርሱም በሰንበታት እነጂ በሌላ ቀን ምንም ሳይቀምስ ማቅ ለብሶ በቀንና በሌሊት ለጸሎት ይተጋ ነበር። በእንዲህ ያለ ሥራም ኑሮ አረፈ የብርሃን መላእክትም ነፍሱን ወስደው በመንግሥተ ሰማያት አኖሯት። አሁንም ወንድሜ የምነግርህን ስማ። የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አታድንቅ የወደደውን ይገሥጻልና" ያም በሽተኛ ድኃ መነኰስ "እውነት ነው ለእኔ ይገባኛል ስለ ኃጢአቴም ይህን ተቀበልሁ" ብሎ መለሰ። ይህንንም ብሎ ዝም አለ።
❤ በዚያች ሰዓትም ያን በሽተኛ በሞት ያሰናብተው ዘንድ አባ ኪሮስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በድንገት መጣ። እልፍ አእላፋት መላእክትም በዙሪያው ሆነው ከእርሱ ጋር ነበሩ ለጻድቃን ሞገሳቸውና ንጉሣቸው የሆነ አምላካችንን እናመስግነው ለችግረኞችም ተስፋ የሆነ አምላካችንን እናመስግነው እያሉ ይዘምሩ ነበር። በዚህ ዓለም በገድል የደከሙ በእርሱ ደስ ይላቸዋል።
❤ አባ ኪሮስም በአየ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ "ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ወደዚህ ምን አመጣህ" አለ ጌታችንም "ስለ ጠራኸኝ መጣሁ" አለው። አባ ኪሮስም "ይህ ሰው ፃዕር በዝቶበታልና ያርፍ ዘንድ አሰናብተው" አለው። ጌታችንም "ምን ያህል እንደምወድህ የመላእክት ሠራዊት ያዩና ያውቁ ዘንድ ይቺን የገነት ተክል አበባ ከእጄ ወስደህ በዚህ በሽተኛ በፊቱ ላይ ጣል" አለው። አባ ኪሮስም ያንን የገነት ተክል አበባ ከጌታችን እጅ ተቀብሎ በበሽተኛው ፊት ላይ አኖረ ያን ጊዜም ነፍሱ ያለ ፃዕር በፍጥነት ወጣች መድኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ከእርሱም ጋር በብርሃን ሠረገላ ውስጥ አስቀመጣት አውጥቶም በሰማያዊ ክብር አኖራት።
❤ አባ ኪሮስም እያደነቀ አለቀሰ ከዚህም በኋላ ወደ አበምኔቱ ሔዶ "እነሆ ያ ድኃ ስለ አረፈ መቃብር ቆፍረው ይቀበሩት ዘንድ ከመነኰሳቱ እዘዝ" አለው አበ ምኔቱም "ምን ግዴታ አለብኝ" አለው አባ ኪሮስም ትኩር ብሎ ተመለከተውና "ይህ የሰይጣን ሥራ እንጂ የሰው ሥራ አይደለም" አለው። ሰለ አስጨነቀውም ሰባት መነኰሳትን አዘዘለት እነርሱም ማዕጠንታቸውን ይዘው ተነሡ አባ ኪሮስም "የሚአጥኑት አሉና የረከሱ ማዕጠንቶቻችሁን አስወግዱ። በቦታቸውም ተዉአቸው ነገር ግን ቅበሩት" ብሎ አማላቸው።
❤ ያን ጊዜም አራቱ የመላእክት አለቆች ሥጋውን በከርቤና በሚዓ አጠኑ መዓዛውም ያንን በዓት "መላው እነዚህ መነኰሳትም የሚያሸተን ምንድነው ይህመነኰስ ሥራይን ያውቅ ይሆን" ተባባሉ። ከዚህም በኋላ ሥጋውን ወስደው በዚያው ገዳም በእንግዳ መቃብር ቀበሩት ከመቃብሩም ጥሩ ውኃ ፈልቆ ለበሽተኞች ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ሚሳኤል በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 8 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለሚሳኤል ሶበ አዕረፈ እምተጽዕሮ። እደ ኪሮስ ድኅረ ቀበሮ። ለእለ መነንዎ ቅድመ ወኢሐወጹ ማኅደሮ። ያቅልል ለክሙ ይቤሎሙ ለጌጋይክሙ ፆሮ። እስመ በግፍዕክሙ ቦእኩ ለክርስቶስ ሀገሮ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_8።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ_፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን #ጌታችን_በአረጀ_መነኲሴ አምሳል ለተገለጸላቸ በጀርባቸው ላዘሉት የሚነድ መለኮት በከንፈራቸው ለሳሙ ለአባታችን #ለአቡነ_ኪሮስ ለዓመታዊ ለዕረፍታቸው በዓላቸው፣ አባ ኪሮስ ለቀበረው ለንጉሥ ልጅ ድኃ ለነበረው #ለአባ_ሚሳኤል ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልእግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ኪሮስ፦ ይህም ቅዱስ የታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ወንድሙ ነበር በከተማ ውስጥ የሚሠራውን ዐመፅ በአየ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ትቶ ከሀገሩ ወጣ። ጌታቸንም መርቶ ወደዚች ምዕራባዊት በረሀ አደረሰው በውስጧም ብዙ ዘመናት ብቻውን ኖረ ከሰው ማንም አላየውም በዚህ ሁሉ ዘመን የዱር አራዊትም ቢሆኑ።
❤ በአስቄጥስም ገዳም ስሙ አባ ባውማ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ እርሱም የንጉሥ ዘይኑን ልጅ ቅድስት ኢላርያን ሥጋዋን የገነዘ ነው። እርሱም እንዲህ አለ በቤተ ክርስቲያን ወስጥ እያለሁ "አባ ባውማ ሆይ ተነሥ ወደ በረሀው ውስጥ ገብተህ ወደ ፀሐይ መግቢያ ሒድ ከቅዱሳን ሁሉ አብዝቶ ፈቃዴን የፈጸመውን የአንድ ገዳማዊ ሥጋ ትገንዝ ዘንድ የሚለኝን ቃል ከሰማይ ሰማሁ"። ያን ጊዜም ደስ ብሎኝ ተነሣሁ በበረሀውም ውስጥ ሦስት ቀን ተጉዤ ከአንድ ገዳማዊ በዓት ደርሼ ደጁን አንኳኳሁ አንድ ሽማግሌ ገዳማዊም ከፈተልኝና እርስ በርሳችን ሰላምታ ተለዋወጥን "በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን?" ብዬ ጠየቅሁት "አዎን" አለኝ። ሁለተኛም "ስምህ ማነው አባቴ ሆይ በዚችስ በረሀ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ኖርክ አልሁት" "ስሜ ስምዖን ነው በዚች በረሀ የኖርኩትም ሰባ ዓመታት ነው" አለኝ።
❤ ከእርሱ ዘንድም ወጥቼ ሦስት ቀን ተጓዝኩ ሁለተኛም ስሙ ባሞን የሚባል ገዳማዊ አገኘሁ ሰላምታም ሰጠሁትና "በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን?" አልሁት "አዎን አለ" አለኝ። አራት ቀንም ተጓዝኩ ወደ አባ ኪሮስ በዓት ደረስኩ "ቅዱስ አባት ሆይ ባርከኝ" እያልኩ ደጁን አንኳኳሁ "አባ ባውማ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው" ብሎ ከውስጥ ተናገረኝ። "እግዚአብሔር ያከበረህ ሰው በሰላም በፍቅር ወደእኔ ግባ" አለኝ ያን ጊዜ ገብቼ ከእርሱ ተባረክሁ በፊቱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ክብር አየሁ የራሱ ጠጉርና ጽሕሙ እንደ በረድ የነጣ ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ተቀመጥሁ በብብቻውም አቀፈኝ እንዲህም አለኝ "እነሆ ይችን ሰዓት እየጠበቅኋት በዚች በዓት ሃምሳ ሰባት ዓመት ኖርኩ" ይህንንም ሲል ጥቂት ታመመና ተኛ እየደነገጠ ያቺን ሌሊት አደረ ሲነጋም በበዓቱ ውስጥ ታላቅ ብርሃን በራ ብርሃናዊ ሰውም ገባ በእጁም የብርሃን መስቀል አለ በአባ ኪሮስ አጠገብም ተቀምጦ ሳመዉ ባረከውም አጽናናው ሰላምን ፍቅርን አንድነትን አደረገለት ከእርሱም ተሠወረ እኔም ፈራሁ "እንዲህ የሚበራ ይህን ክብር የተጐናጸፈ ይህ ማነው" አልሁት።
❤ እርሱም "ልጄ ሆይ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ልማዱ ስለ ሆነ ሁልጊዜ ይመጣል ያጽናናኛልም" አለኝ። "በቀዳሚት ሰንበት ዕለትም ዘጠኝ ሰዓት በሆነ ጊዜ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላቅ ጩኸትን ሰማሁ ከጩኸታቸውም ኃይል የተነሣ ምድር ተናወጸች። እኔም "ይህ የምሰማው ጩኸት ምንድነው ብዬ ጠየቅሁት እርሱም ልጄ ሆይ ይህ በሲኦል የሚኖሩ የኃጥአን ጩኸት ነው ስለ ቅድስት ትንሣኤው የእሑድ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ እግዚአብሔር ያሳርፋቸዋልና ስለዚህም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል" አለኝ"። በዚችም ዕለት ሐምሌ ሰባት ቀን ቅዱስ አባ ኪሮስ ጩኾ አለቀሰ ዛሬ "በግብጽ አገር ታላቅ ምሰሶ ወደቀ ይኸውም የገዳማውያን አለቃ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ነው" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ እሑድ ሌሊት እጅግ ደነገጠ በበዓቱም ውስጥ እነሆ ታላቅ ብርሃን በራ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ገብቶ በአባ ኪሮስ ራስ አጠገብ ተቀመጠ። አባ ኪሮስም መድኃኒታችንን "ጌታዬ ሆይ ይህን ሰው ባርከው" አለው መድኃኒታችንም "የመረጥሁህ አባ ባውማ ሆይ ጽና አትፍራም ሰላሜ በረከቴም ከአንተ ጋራ ይኑር። አሁንም ታማኝ አገልጋዬ የሆነ የዚህን የቅዱስ ኪሮስን ያየኸውንና የሰማኸውን ወደፊትም ዳግመኛ የምታየውንና የምትሰማውን ገድሉን ጻፍ" አለኝ።
❤ ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን አባ ኪሮስን እንዲህ አለው "እነሆ አንተ ትሞታለህና አትዘን ሞትህ ሞት አይደለም የዘላለም ሕይወት ነው እንጂ። የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን የሚሰማውንም ሁሉ በምድርም መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሽህ ዓመት በዓል ምሳ ከእኔ ጋር ይቀመጥ ዘንድ አደርገዋለሁ ከቅዱሳኖቼም ጋራ እቆጥረዋለሁ። የኃጢአቱንም መጽሐፍ ቀድጄ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ። ለመሥዋዕት የሚገባውንም ዕጣኑንና ወይኑን መብራቱንም መባ አድርጎ ለሚሰጥም በስምህም ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ለሚያደርግ ዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልቡናም ያልታሰበውን በጎ ዋጋ እኔ እጥፍ ድርብ አድርጌ እሰጠዋለሁ። በበኵር ቤተ ክርስቲያንም ሥጋዬንና ደሜን አቀብላቸዋለሁ በዚህም ዓለም ቤታቸውን እባርካለሁ። ልጆቻቸውን አሳድጋለሁ ከበጎ ነገር ሁሉ ምንም ምን አያጡም። አሁንም ከዚህ ዓለም ድካም ወደ ዕረፍት የዘላለም ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደ ብርሃን ቦታ እወስድህ ዘንድ ጊዜው ደረሰ" መድኃኒታችንም ይህን ሲናገር እነሆ ነቢዩና ዘማሪው ዳዊት መጣ መሰንቆውም ከእርሱ ጋራ ነበረች። "ይቺ ዕለት በእርሷ ፈጽሞ ሐሤት እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር የሠራት ናት" እያለ አመሰገነባት።
❤ መድኃኒታችንም አባ ኪሮስን "እነሆ ዘማሪው ዳዊት መጥቷልና ይዘምርልህ ዘንድ የምትሻውን ንገር" አለው። ዳዊትም ቅዱስ አባ ኪሮስን "በየትኛው አውታር እንድዘምርልህ ትሻለህ ደግሞስ በየትኛው ዜማ በየትኛው ስልት በመጀመሪያው ነውን ወይስ በሁለተኛው ወይስ በሦስተኛው" አለው። ቅዱስ አባ "ኪሮስም በዐሥሩም አውታር በየስልታቸውና በየዜማቸው ልሰማ እሻለሁ" አለ። ያን ጊዜ ዳዊት መሰንቆውን አዘጋጅቶ "የጻድቅ ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው" አለ ዳግመኛም "ጐለመስሁ አረጀሁም የሚወድቅ ጻድቅን አላየሁም" አለ። ዳዊትም ድምፁን አሣምሮ ዘመረ መሰንቆውንም በስልት መታት። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ ኪሮስ ነፍሱ ወጣች ኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤልም ሰጣት።
❤ እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ሥጋውን ቀበርኩ ከበዓቱም በወጣሁ ጊዜ በረሀው በሰማይ ሠራዊት ተመልቶ አየሁ መድኃኒታችንም የቅዱስ አባ ኪሮስ ሥጋው ባለበት በዓት ላይ መስቀሉን አኑሮ ዘጋት። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለኔ ሰላምታ ሰጥቶኝ መላእክትና የመላእክት አለቆች በፊቱ እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ዐረገ። የቅዱስ አባ ኪሮስን ነፍስ ከመድኃኒታችን ጋራ እንደዚህ አሳረጓት። እርሷም በተሰጣት ክብር ደስ እያላት ዐረገች።
❤ እኔም አባ ባውማ በዚያ ቦታ ብቻዬን ቀረሁ ተመልሼም ወደ አባ አሞን በዓት ደረስሁ። ከዚያም የሦስት ቀን መንገድ ተጉዤ ወደ አባ ስምዖን በዓት ደረስሁ። ከዚያም ሦስት ቀን ተጉዤ ወደ ቦታዬ ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረስሁ። ለመነኰሳቱም ሁሉ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ስለ አባ ሲኖዳም ዕረፍት ትንቢት እንደ ተናገረ ነገርኋቸው። መነኰሳቱም ሰምተው እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ጽፌ ለሚያነበውና
✝ ✝ ✝
❤ #የሮሜ_ከተማ_ሊቀ_ጳጳሳት_አቡነ_አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፦ እርሱም ከቅዱስ ጴጥሮስ በኋላ በከሀዲው ንጉሥ በጠራብያኖስ ዘመን ሆነ። ይህም ንጉሥ ስለ አባት አግናጥዮስ የጣዖት አምልኮን እንደሚአቃልል ሕዝቡንም ሁሉ እንደሚያስተምር ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን እንደሚያስገባቸው በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ "ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ" አለው ቅዱሱም "እኔ ለረከሱ ጣዖታት አልሠዋም" ብሎ መለሰለት።
❤ ንጉሡም ብዙ ቃል ኪዳኖችን በመግባት አባበለው በአልተቀበለውም ጊዜ ለአንበሳ ሰጠው ያን ጊዜም ቅዱስ አግናጥዮስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ ቀርቦ አንገቱን ያዘው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ። ከዚህ በኋላ ያ አንበሳ ወደ ሥጋው አልቀረበም ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በመልካም ቦታም አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ አግናጥዮስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 7 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለአግናጥዮስ_ለመንበረ_ጴጥሮስ ዘወረሳ። እምነ መናብርት ኵሉ ዘተለዓለ ሞገሳ። ለመሥዋዕተ ጣዖት ምንንት እንዘ ያረኵሳ። በፍጻሜ ስምዑ ቀተሎ አንበሳ። ወእምድኅረዝ ኢቀርበ ለሥጋሁ ይግሥሣ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_7።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ። ወበቃለ እግዚአብሔር ፀንዐ ሰማያት። ወእምእስትንፋሰ አፋሁ ኵሉ ኃይሎሙ"። መዝ 32፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥1-6
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወኀሠሥኩ ገጸከ። ገጸ ዚአከ አኀሥሥ እግዚኦ። ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ"። መዝ 26፥8-9። የሚነበበው መልዕክታት ሮሜ 9፥1-17፣ 1ኛ ዮሐ 4፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥11-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥51-59። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአጋእዝተ ዓለም የቅድስት ሥላሴ በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፯ (7) ቀን።
❤ እንኳን #ለአጋእዝተ_ዓለም_ለቅድስት_ሥላሴ ወደ #አብርሃም_ቤት_ለገቡበት_የይስሐቅን_መወለድ_ለአበሰሩበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለሮሜ ሊቀ ጳጳስ ለሐዋርያው #ለቅዱስ_አግናጥዮ_ምጥው_ለአንበሳ_ለዕረፍት_በዓልና ለባሕታውያን አለቃ ለሆነ ለመስተጋድል #አባ_ሲኖዳ_ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ መቃቢስ፣ ከአግራጥም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት (#አጋዝእተ_ዓለም_ሥላሴ) በኦሪት መጽሐፍ እንደተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገብ ያቀረበላቸውን ተመገቡ የይስሐቅንም ልደት አሠሰሩት ባረኩት አከበሩትም። ለእግዚአብሔር ይስጋና ይሁን በአባታችን በቅዱስ አብርሃም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ታሪኩን በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 18 ላይ ያንብቡ።
✝ ✝ ✝
❤ #የባሕታውያን_አለቃ_የሆነ_መስተጋድል_አባ_ሲኖዳ፦ ይህም ቅዱስ በግብጽና በአክሚም አውራጃ ስሟ ስንላል ከምትባል ሀገር ከላይኛው ግብጽ ነበር። ስለእርሱም የመላእክት አምሳል የሆነ አባ ሐርስዮስ ትንቢት ተናገረለት። እርሱም ስለ ገዳም አገልግሎት ከመነኰሳት ጋር ሲሔድ የዚህን የቅዱስ ሲኖዳን እናት ውኃ ለመቅዳት ወጥታ አገኛት። ወደርሷ ሒዶ ሦስት ጊዜ ራሷን ሳማትና እንዲህ አላት "ዜናው በዓለሙ ሁሉ የሚሰማ የስሙ መዓዛ ከሽቱ የሚጥም የሆነ የሆድሽን ፍሬ እግዚአብሔር ይባርክ"።
❤ እነዚያ መነኰሳትም በአዩት ጊዜ አድንቀው "አባታችን አንተ የሴት ፊት ማየት ከቶ አትሻም ነበር ዛሬ ግን ከሴት ጋራ ትነጋገራለህ" አሉት። "ልጆቼ ሆይ ሕያው እግዚአብሔርን የእግዚአብሔርን ምሕረት ተስፋ የሚያደርግ ዓለሙ ሁሉ የሚጣፍጥበት ከዚች ሴት የሚወጣ የጨው ቅንጣት አለ" አላቸው።
❤ አንድ በገድል የጸና ጻድቅ ሰው መነኰስ ነበረ እርሱም መልሶ አባ ሐርስዮስን እንዲህ አለው "እግዚአብሔር ሕያው ነው አንተ ራሷን ትስም ዘንድ ወደዚያች ሴት በቀረብክ ጊዜ በእጁ የእሳት ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ በዙሪያዋ አየሁት። ራሷንም በሳምካት ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ሲልህ ደግሞም ከዚች ሴት የሚወለደው የተመረጡ ቅዱሳንን ሁሉ ልባቸውን ደስ ያሰኛል ወልደ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋር ብዙ ጊዜ ይነጋገር ነበር ሲል ሰማሁት" አለ።
❤ በግንቦት ሰባት ቀን ይህ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ተወለደ በአደገም ጊዜ አባቱ በጎች ስለነበሩት ለልጁ ለሲኖዳ እንዲጠብቃቸው ሰጠው ይህ ሲኖዳም ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር። በሌሊትም ከውኃ ዐዘቅት ውስጥ ወርዶ በዚያ ቁሞ እስቲነጋ ድረስ ሲጸልይ ያድር ነበር። በክረምትም ሆነ በቊር ሰዓት እንዲሁ ያደርግ ነበር። አባቱም የሲኖዳ እናት ወንድም ወደ ሆነው ወደ አባ አብጎል እጁን በላዩ ጭኖ ይባርከው ዘንድ ወሰደው። አባ አብጎልም በአየው ጊዜ የሕፃኑን እጅ አንሥቶ በራሱ ላይ አድርጎ "ሲኖዳ ሆይ ባርከኝ ለብዙ ሕዝብ ታላቅ አባት ትሆን ዘንድ የሚገባህ ሁነሃልና" አለው። አባቱም በአባ አብጎል ዘንድ ተወው።
❤ ከዕለታትም በአንዲቱ ቀን አባ አብጎል እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ "እነሆ ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ አርሲመትሪዳ የባሕታውያን አለቃ ሁኖ ተሾመ"። ይህም ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን እስከሚሆን በበጎ አምልኮ ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት በስግደትና በመትጋት ታላቅ ተጋድሎ መጋደልን ጀመረ።
❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ለአባ አብጎል የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና የኤልያስን አስኬማ የሠለስቱ ደቂቅን ቆብና የመጥምቁ ዮሐንስን ቅናት አመጣለት። እንዲህም አለው "እንድትጸልይና የምንኵስና ልብስ ለሲኖዳ እንድታለብሰው እግዚአብሔር አዝዞሃል"። ያን ጊዜም አባ አብጎል ተነሥቶ ጸለየ የምንኵስና ልብስንም አለበሰው።
❤ ከዚህም በኋላ ተጋድሎውን አበዛ። ለመነኰሳት፣ ለመኳንንት፣ ለሕዝባውያንና ለሴቶች ለሰዎች ሁሉ መመሪያ የሚሆን ሥራትን ሠራ። በኤፌሶንም የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በተደረገ ጊዜ ከማኅበሩ አባት ከሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ጋራ ወደ ጉባኤው ሔደ ንስጥሮስም ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው አሳደዱት።
❤ ከዚህ በኋላም ወደ ሀገራቸው በመመለሻቸው ጊዜ መርከበኞች ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋራ አትሳፈርም ብለው አባ ሲኖዳን ከለከሉት እርሱም ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ማለደ። ወዲያውኑም ደመና መጥታ ተሸከመችውና አባ ቄርሎስ በመርከቡ ውስጥ እያለ በበላዩ በአንጻሩ አደረሰችው። "አባቴ ሆይ ሰላም ለአንተ ከአንተ ጋራ ላሉትም ይሁን" ብሎ ሰላምታ አቀረበ። በመርከብ ያሉት ሁሉም "ላንተም ሰላም ይሁን በጸሎትህም አትርሳን" አሉት። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ያህል ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
❤ ወደ ገዳሙም ደርሶ ከልጆቹ መነኰሳት ጋራ የመንፈቀ ሌሊትን ጸሎት አደረገ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ጊዜ ወደርሱ እየመጣ ያነጋግረው ነበር። እርሱም የመድኃኒታችንን እግሩን ያጥበው ነበር እጣቢውንም ይጠጣ ነበር ጌታችንም ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት ትንቢቶችንም ተናገረ።
❤ ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ ሐምሌ ሰባት ቀን ተኛ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መጥቶ እያረጋጋው በእርሱ ዘንድ ተቀመጠ። ብፁዕ አባ ሲኖዳም ጌታችንን እንዲህ አለው "ጌታዬ ፈጣሪዬ ልዩ ሦስትነትህንና ጌትነትህን ስለሚነቅፉ ከሀድያን ወደ ጉባኤው እሔድ ዘንድ እንዲጠሩኝ ሊቀ ጳጳሳቱ ወደ እኔ ልኳልና እንደቀድሞው ታጸናኛለህን?"። ጌታችንም በጸጋና በጥዑም ቃል እንዲህ ብሎ መለሰለት "ወዳጄ ሲኖዳ ሆይ ሌላ ዕድሜ ትሻለህን?። እነሆ ዕድሜህ ሁሉ መቶ ሃያ ዓመት ከሁለት ወር ሁኖሃል ዕድሜህ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን አስኬማን ለበስኽ ከዚያ በኋላ መቶ ዐሥራ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ኖርኽ አሁንስ ድካምህ ይብቃህ" ይህንንም ብሎ ጌታችን በክብር ዐረገ።
❤ በዚያንም ጊዜም የቅዱሳን አንድነት ማኅበር ወደርሱ መጡ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ዳግመኛ አየው ልጆቹንም ክብር ይግባውና "ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ እሰግድ ዘንድ አንሱኝ" አላቸው አንሥተውትም ሰገደለት። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አላቸው "ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠብቅኋችሁ ነፍሴም ከዚህ ከደካማው ሥጋዬ የምትለይበት ጊዜ ደርሷል እኔም ለአባታችሁ ለዊዳ እንድትታዘዙ አዝዛችኋለሁ ከእኔ በኋላ ጠባቂያችሁ እርሱ ነውና" አላቸው።
❤ ለልጆቹም ይህን በተናገረ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "የመረጥሁህ ሲኖዳ ሆይ ብፁዕ ነህ ቸርነቴም ይደረግልሃል በሕይወትህ ዘመን ሁሉ አንተ የምወደውን ሥራ ሠርተሃልና እንግዲህ ወደ ዘለዓለም ተድላ ታርፍ ዘንድ ወደእኔ ና" አለው። ያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ሲኖዳ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❖ ይህም እንዲህ ነው ይቺ ቅድስት ልጇ አብሮኮሮንዮስን ክርስቲያን ነው ብለው እንደወነጀሉትና ለሞት እስቲደርስ ጽኑዕ ሥቃይን እንዳሠቃዩት ሰማች፤ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያች ሌሊት ተገለጠለት ከሥቃዩም አዳነው ያለ ምንም ጉዳት ጤናማ ሆነ።
❖ እኒህ ሁለቱ መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች ከእናቱ ጋር በአዩት ጊዜ እጅግ አደነቁ እንዲህ ብለውም ጮኹ እኛ በአብሮኮሮንዮስ አምላክ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእኒህ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ ሰላም ዕብል ለቴዎዳስያ በጽዋዔ። ጥብዓተ ወልዳ ነጺራ እንበለ ምማዔ። እንተ ኮነት ስምዐ ለተስፋ ትንሣኤ። ወሰላም ዕብል ለዘዚአሃ ጉባዔ። ምስለ ካዕበተ ስሱ አንስት ወመኳንንት ክልኤ።
ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ ፮
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ ርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን የዕዝራ ዕርገት ሆነ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ይህም ነቢይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚጽፍ ነበረ እርሱም ከሌዊ ወገን ነበረ፤ ከእግዚአብሔርም ጋራ ግሩም የሆነ ነገርን መናገር ጀመረ እንዲህም አለ ምድርን በፈጠርካት ጊዜ አዳምን ታስገኝ ዘንድ አዘዝካት አስገኘችውም።
❖"ሁለተኛው የጥፋት ውኃ በጊዜው እንደ መጣና ሁሉን እንዳጠፋ ተናገረ ኖኅ አብርሃምና ዳዊት እንዴት እንደ ተመረጡ ደግሞ ተናገረ፤ ዳግመኛም ነፍስ ከሥጋዋ እንደምትወጣና ሰባት ቀኖች እንደምትዞር ከዚያም በኋላ እንደ ሥራዋ ወደተዘጋጀላት ቦታዋ እንደምትገባ ተናገረ።
❖ ከዚያም ስለ ፍርድ ቀን ተናገረ፤ ከእግዚአብሔር ከጌትነቱ ብርሃን በቀር ፀሐይና ጨረቃ መብራትና ብርሃንም እንደሌሉ ተናገረ፤ ዳግመኛም በልቧ እጅግ በምትጨነቅ በምታዝንና በምትተክዝ ሴት አምሳል ጽዮንን አያት ልብሶቿም የተቀደዱ ነበሩ ልጇም ወደ ጫጕላው ቤት በገባበት ቀን እንደሞተ ነገረችው፤ ከዚህም በኋላ እርሷን ከማየቱ የተነሣ ፈርቶ በድንጋፄ እስከ ወደቀ ድረስ ፊቷ በድንገት እንደ መብረቅ በራ።
❖ ደግሞም ዐሥራ ሁለት ክንፎችና ሦስት ራሶች ያሉት ንስር ከባሕር ሲወጣ ከክንፎቹም ውስጥ ራሶች ሲወጡ አየ እኒህም በየዘመናቸው ገዝተው የጠፉ ነገሥታት ናቸው፤ ደግሞም ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስ መወለድ ተናገረ እንዲህም አለ፤ አንበሳ እያገሣ ከበረሀ ወጣ በሰው አንደበትም ሲናገር ንስሩንም ሲገሥጸው ሰማሁት አለ።
❖ ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ፤ በሌሊት ታላቅ ነፋስ ከባሕር ሲወጣ አየሁ ከማዕበሉ የተነሣ ባሕሩ ይታወክ ነበር ነፋሱም እንደ ሰው አምሳል ሁኖ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ደግሞም ከብዙ ኃይልና ክብር ጋር በሰማይ ደመና ማረጉን በአብ ቀኝ መቀመጡንም አይቶ ተናገረ።
❖ ዳግመኛም በፈሳሹ ማዶ ያኖራቸው ዘጠኙ ነገድ እንደሚሰበሰቡ ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ የነቢያት መጻሕፍትና የአባቶችን ትውልድ የያዙ መጻሕፍት ተደምስሰው መጥፋታቸውን በአሰበ ጊዜ ወደ በረሀ ገብቶ በጾምና በጸሎት ምሕላ ያዘ፤ ከእርሱም ጋር አምስት ጠቢባን ጸሐፊዎችን ወሰደ።
❖ ከዕንጨቱም አንጻር ቃል ጠርቶት ዕዝራ አፍህን ክፈት ብሎ ኅብሩ እሳት የሚመስል ውኃን የተመላ ጽዋን ሰጠው፤ ያንንም ጽዋ ጠጣ ያን ጊዜም ልቡናው ጥበብን አገሣ፤ ተገልጾለትም መጻሕፍትን ሁሉ ሰበሰበ ለእነዚያም ሰዎች ልዑል አምላክ ዕውቀትን ሰጣቸው፤ መጻሕፍትንም ሁሉ በየተራቸው ጻፉ፤ በዚያም አርባ ቀን ኖሩ እነዚያ ግን ቀን ቀን ይጽፋሉ ማታ ማታም ይመገባሉ እርሱ ግን ቀን ይጽፋል ማታም ዝም አይልም በእነዚያ አርባ ቀኖችም ሁሉ መጻሕፍት ተጻፉ።
❖ ከዚህም በኋላ ልዑል እንዲህ ሲል ተናገረው የዕውቀት ምሥጢር የጥበብም ምሥጢር እንደ ፈሳሽ ውኃም ያለ ዕውቀት ላላቸው ታስተምራቸው ዘንድ ይህን ተመልከት እንዳለውም አደረገ፤ በአራተኛውም ዘመን ከሚቈጠሩ ከብዙ ሱባዔ በአምስተኛው ሱባዔ ይህ ዓለም ከተፈጠረ ከአምስት ሺ ዘመን በኋላ ጨረቃ ሠርቅ አድርጋ ጨለማዋን ባጣች በአሥረኛው ቀን በሦስተኛው ወር በዘጠና አንድ እንደእርሱ ያሉ ደጋግ ሰዎች ወዳሉበት ዕዝራን ወሰዱት።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለከ ተረፈ ነቢያት ሱቱኤል። ድኅረ ማእረር ወቀስም ከመ አሀዱ አስካል። ሶበ አናኅከ ማኅሠሠ ቃል። ምክረ ስብሐቲሁ ለእግዚአብሔር ልዑል። እሳተ ድሉ ይቤለከ እመ አንተ ትክል።
በዚችም ዕለት ቅድስት ንስተሮኒን አረፈች፤ እርሷም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ውስጥ ነበረች፤ እርሷም አስቀድማ ኃጢአተኛ ነበረች ከዚያም በኋላ ንስሓ ገብታ ወደ እግዚአብሔር በተቃጠለ ልብ ተመለሰች የሥጋን ፍላጐቶች ሁሉ ናቀች እመምኔት እስከ ሆነች ድረስ በበጎ ሥራ ሁሉ ትሩፋትንና ተጋድሎን አበዛች።
❖ እኅቶችም ከገድል ብዛትና ምግብን ከመተው የተነሣ ሥጋዋ እንዳለቀ አይተው ሥጋሽን እንድትረጂ ጥቂት እህል በወጥ ብዪ አሏት፤ አብዝተውም ግድ ባሏት ጊዜ ልጆቼ ሆይ ወደ ቀድሞ ልማዴ እንዳልመለስ ጥቂት ወጥ ስለመብላት አትድከሙ ስለዚህ ወጥ አልበላም አለቻቸው፤ ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈች።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለንስተሮኒን እንተ ኀልቀ አባላ። እምበዝኀ ፃማሃ ወገድላ። ሶበ ሰአላሃ አኃት ከመ ትብላዕ ዘየአክላ። ኢይኩን ተመይጦትየ ኀበ ኃጢአት ኲላ። ወበእንተዝ አዐቢ ትቤሎን ለእላ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ቅዱስ መርቄሎስ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ዕለት ጳውሎስ የተባለ ቅዱስ መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ፤ ይህም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ ነው፤ እርሱም ሐዋርያትን አገልግሎአቸዋል፤ ወንጌልንም ለመስበክ ከእነርሱ ጋር ሔደ፤ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስን መልእክቶች አደረሰ በመከራውም ጊዜ አገለገለው፤ ከእርሱም ጋር መከራ ተቀበለ ከእርሱም አልተለየም።
❖ ወደ ሮሜ አገርም ከርሱ ጋር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን አስተማረ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን ከአረማውያን ብዙዎቹን መለሳቸው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ይህ ረድእ መርቄሎስ መጥቶ ከመስቀል ላይ አወረደው በከበሩ ልብሶችም ከሽቱ ጋር ገነዘው፤ በሣጥንም አድርጎ ከምእመናን በአንዱ ቤት አኖረው።
❖ የሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙርም እንደሆነ በኔሮን ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ አቅርቦ ጠየቀው እርሱም ለሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ አመነ ደግሞም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ ታመነ፤ ስለዚህም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ገረፈውም ዘቅዝቀው ሰቅለውም ከበታቹ ጢስን አጤሱበት።
❖ ከዚህም በኋላ ንጉሡ እንዴት ሁነህ መሞት ትሻለህ በምን አይነት ሞት ልግደልህ ንገረኝ አለው፤ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰ እኔ ሕይወት በሆነ በክርስቶስ ስም መሞት እሻለሁ አንተ ግን በፈለግኸው ዓይነት ግደለኝ ፈጥነህም ወደ ፈለግኸው አድርሰኝ፤ ያን ጊዜም ንጉሡ ኔሮን እንዲገርፉትና እንደ መምህሩ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። የሰማዕታትንና የሐዋርያትን አክሊል ተቀበለ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያት በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለመርቄሎስ ጳውሎስሃ ዘተሰምየ። እንተ ገነዞ ለጴጥሮስ ግንዘተ ሠናየ። ሶበ መኮንን ይቤሎ እመ ትፈርህ ሥቃየ። ንግረኒ ዘትፈቅድ መዊተ አየ። ይቤሎ በዘትፈቅድ ቅትለኒ ኪያየ።
በዚችም ዕለት ከሐዋርያት የበርተሎሜዎስ የአንድ ሽህ ሰማዕታትና ከማርቆስ ዘጠነኛ የሚሆን የሊቀ ጳጳሳት ከላድያኑ መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ቴዎዳስያ ሰማዕት
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ቀን የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት ገድለኛዋ ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች ከእርሷ ጋርም ሁለት መኳንንቶችና አሥራ ሁለት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ።
❤ ከዚህም በኋላ እልዋሪቆን ወደ ምትባል ታላቅ አገር እስከሚደርስ በብዙ አገሮች ውስጥ ተመላለሰ በዚያም የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት አረጋጋችው ረዳችውም በመጋቢት ሃያ ዘጠኝ እንደጻፍነው የአገሩን ሰዎች እንዲያጠምቃቸውና እንዲያስተምራቸው አዘዘችው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገብቶ በውስጧ ሰበከ በስብከቱም ብዙዎች ሰዎች አምነው የክርስትናን ጥምቀትን አጠመቃቸው። በመጻፍትነት የታወቁ ዐሥራ አራት መልክቶችን ጻፈ የመጀመሪያ መልክቱም ለሮሜ የተጻፈችው ናት።
❤ መልካም ሩጫውን ከፈጸመ በኋላ ንጉሥ ኔሮን ይዞ ጽኑ ሥቃይ አሰቃየው። ራሱንም በሠይፍ እንዲቆርጡት ለሠያፊ ሰጠው ከሠያፊውም ጋር አልፎ ሲሆድ ከንጉሥ ኔሮን ዘመዶች ወገን የሆች አንዲት ብቴና አገኘችው እርሷም ክብር ይግባውና በጌታችን ያመነች ነበረች ስለእርሱ አለቀሰች። እርሱ ግን "መጎናጸፍያሽ ስጭኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ" አላት። እርሷም መጎናጸፍያዋን ሰጠችውና ራስ ወደሚቆርጡበት ቦታ ሔደ። ለሠያፊው ራሱ በዘነገበለለት ጊዜ በመጎናጸፍያዋ ፍቱን ሸፈነ ሠያፊው የቅዱስ ጳዌሎስ ራስ ሐምሌ 5 ቀን ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፍያ እንደተሸፈነ ጣለው።
❤ ሠያፊው ጳውሎስን እንደገደለው ለንጉሥ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችው "ያ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ አለ" አለችው። ራስ በሚቆርጥበት ቦታ ወድቋል ራሱም በመጎናጸፍያሽ ተሸፍኗል" አላት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት "ዋሽተሃል እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ ዘንድ አልፈው ሔዱ እነርሱም የመንግሥት ልስን ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ በእንቊ የተጌጡ አይንን የሚበዘብዙ አክሊላትን አድርገዋል። መጎናጸፍያየም ሰጡኝ። እርሷም እነኋት ተመልከታት" ብላ ለዛያ ሠያፊ አሳየችው። ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው። አይተውም አደነቁ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።
❤ ለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተአምራቶች ቁጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅዱስ ጳውሎስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎና ከአባ ማትያስ ከሁሉ ሊቃነ ጳጳሳት እና የቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያ ልጆች ጋር ይኑር ለዘለላሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 5 ሰንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ጴጥሮስ_ተልሚድ። ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ፡፡ እንዘ ትረውጽ ጥቡዕ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልደ። አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ። ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_5።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 15፥1-17።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ 138፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 1፥4፥-13-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 23፥10-16። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 21፥15-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱሳን የጴጥሮሰና የጳውሎስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ ከዚህም በኋላ እልዋሪቆን ወደ ምትባል ታላቅ አገር እስከሚደርስ በብዙ አገሮች ውስጥ ተመላለሰ በዚያም የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት አረጋጋችው ረዳችውም በመጋቢት ሃያ ዘጠኝ እንደጻፍነው የአገሩን ሰዎች እንዲያጠምቃቸውና እንዲያስተምራቸው አዘዘችው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገብቶ በውስጧ ሰበከ በስብከቱም ብዙዎች ሰዎች አምነው የክርስትናን ጥምቀትን አጠመቃቸው። በመጻፍትነት የታወቁ ዐሥራ አራት መልክቶችን ጻፈ የመጀመሪያ መልክቱም ለሮሜ የተጻፈችው ናት።
❤ መልካም ሩጫውን ከፈጸመ በኋላ ንጉሥ ኔሮን ይዞ ጽኑ ሥቃይ አሰቃየው። ራሱንም በሠይፍ እንዲቆርጡት ለሠያፊ ሰጠው ከሠያፊውም ጋር አልፎ ሲሆድ ከንጉሥ ኔሮን ዘመዶች ወገን የሆች አንዲት ብቴና አገኘችው እርሷም ክብር ይግባውና በጌታችን ያመነች ነበረች ስለእርሱ አለቀሰች። እርሱ ግን "መጎናጸፍያሽ ስጭኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ" አላት። እርሷም መጎናጸፍያዋን ሰጠችውና ራስ ወደሚቆርጡበት ቦታ ሔደ። ለሠያፊው ራሱ በዘነገበለለት ጊዜ በመጎናጸፍያዋ ፍቱን ሸፈነ ሠያፊው የቅዱስ ጳዌሎስ ራስ ሐምሌ 5 ቀን ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፍያ እንደተሸፈነ ጣለው።
❤ ሠያፊው ጳውሎስን እንደገደለው ለንጉሥ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችው "ያ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ አለ" አለችው። ራስ በሚቆርጥበት ቦታ ወድቋል ራሱም በመጎናጸፍያሽ ተሸፍኗል" አላት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት "ዋሽተሃል እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ ዘንድ አልፈው ሔዱ እነርሱም የመንግሥት ልስን ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ በእንቊ የተጌጡ አይንን የሚበዘብዙ አክሊላትን አድርገዋል። መጎናጸፍያየም ሰጡኝ። እርሷም እነኋት ተመልከታት" ብላ ለዛያ ሠያፊ አሳየችው። ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው። አይተውም አደነቁ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።
❤ ለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተአምራቶች ቁጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅዱስ ጳውሎስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎና ከአባ ማትያስ ከሁሉ ሊቃነ ጳጳሳት እና የቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያ ልጆች ጋር ይኑር ለዘለላሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 5 ሰንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ጴጥሮስ_ተልሚድ። ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ፡፡ እንዘ ትረውጽ ጥቡዕ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልደ። አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ። ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_5።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 15፥1-17።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ 138፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 1፥4፥-13-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 23፥10-16። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 21፥15-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱሳን የጴጥሮሰና የጳውሎስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ ሳውልም ከምድር ተነሣ ዐይኖቹንም ተገልጠው ሳሉ አያይም ነበር እየመሩም ወደ ደማስቆ አስገቡት በዚያም ሳያይ ሳይበላና ሳይጠጣ ሦስት ቀን ሰነበተ። በዚያም በደማስቆ ከደቀ መዛሙርት ወገን ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ጌታም በራዕይ ተገለጠለትና ሐናንያ ብሎ ጠራው እርሱም "አቤቱ ጌታዬ እነሆኝ" አለ። ጌታም "ተነሥና ቀጥተኛ ወደምትባለው መንገድ ሒድ በይሁዳ ቤትም ጠርሴስ ከሚባል አገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ እርሱ አሁን ይጸልያልና" አለው።
❤ ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ "አቤቱ ስለዚያ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ ወደዚህም ከካህናቱ አለቃ አስፈቅዶ የመጣ ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ሊአሥር ነው"። ጌታችንም "ተነሥና ሒድ በአሕዛብና በነገሥታት በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና። እኔም ስለ ስሜ መከራ ይቀበል ዘንድ እንዳለው አሳየዋለሁ"።
❤ ያን ጊዜም ሐናንያ ሔደ ወደ ቤትም ገባ "ወንድሜ ሳውል በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ታይ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ ይሞላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል" አለው። ያን ጊዜም የሸረሪት ድር የመሰለ ከዐይኖቹም ተገለጡ። ወዲያውም አየ ተነሥቶም ተጠመቀ እህልም በልቶ በረታ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር በደማስቆ ጥቂት ቀን ሰነበተ። በዚያው ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰበከ አስተማረም። የሰሙትም ሁሉ አደነቁ እንዲህም አሉ "በኢየሩሳሌም ይህም ስም የሚጠሩትን ሁሉ ያሳድድ የነበረ ይህ አልነበረምን ወደዚህስ የመጣው እያሠረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን"።
❤ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም አደረበት እውነተኛንም ሃይማኖት ግልጽ አድርጎ አስተማረ። ለኦሪት ሕግ የሚቀና እንደ ነበረ እንዲሁ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሠራት ሕግ ወንጌል ዕጽፍ ድርብ ቅንዓትን የሚቀና ሆነ። ከዚህም በኋላ በአገሮች ሁሉ ዞሮ ሰበከ በጌታችንም ስም ሰበከ። ድንቆችንና ተአምራትንም አደረገ። ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም አሳመናቸው ነገር ግን ብዙ ጊዜ በመገረፍ በመደብደብና በመታሠር ብዙ መከራ ደረሰበት መከራውንም ሁሉ ታግሶ በሁሉ ቦታ አስተማረ።
❤ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደተጻፈ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙና ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ "እኔ እነርሱን ለመረጥሁለት ሥራ ሳውልና በርናባስ ለዩልኝ" አላቸው። ከዚህም በኋላ ጾመውና ጸልየው እጃቸውንም በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሙአቸው ከመንፈስ ቅዱስም ተሹመው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ።
❤ በደሴቱም ሁሉ ሲዘዋወሩ ጳፋ ወደ ምትባል አገር ደረሱ። በዚያም ሐሰተኛ ነቢይ የሆነ ስሙ በርያሱስ የሚባል አንድ ሥራየኛ አይሁዳዊ ሰው አገኙ እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባል ብልህ ሰው ከሆነ አገረ ገዥ ዘንድ የነበረ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ወዶ በርናባስንና ሳውልን ጠራቸው። የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ነበርና ኤልማስ የሚሉት ያ ሥራየኛ ሰው ይከራከራቸው ነበር ገዥውንም ማመንን ሊከለክለው ወዶ ነበር።
❤ ጳውሎስ በተባለው ሳውል ላይም መንፈስ ቅዱስ መላበት። አተኵሮም ተመለከተው "ኃጢአትንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሰይጣን ልጅ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ እያመጣመምኽ ተው ብትባል እምቢ አልኽ እነሆ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ተቃጥታለች ትታወራለህ እስከ እድሜ ልክህም ፀሐይን አታይም" አለው። ወዲያውኑም ታወረ ጨለማም ዋጠው የሚመራውንም ፈለገ አገረ ገዥውም የሆነውን አይቶ ደነገጠ በጌታችንም አመነ።
❤ ከዚህ በኋላ ሒደው ወደ ሊቆኦንያ ከዚያም ወደ ልስጥራንና ደርቤን ከተማ ወደ አውራጃውም ሁሉ ገብተው አስተማሩ። በልስጥራን ከተማም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እግሩ ልምሾ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ተቀምጦ ይኖር ነበረ እንጂ ልምሾ ከሆነ ጀምሮ ቁሞ አልሔደም። ቅዱስ ጳውሎስንም ሲያስተምር አደመጠው ጳውሎስ ተመልክቶ ሃይማኖት እንዳለው እንደሚድንም ተረዳ። ድምፁንም ከፍ አድርጎ "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ቀጥ ብለህ ቁም እልሀለሁ" አለው ወዲያውኑ ተነሥቶ ሔደ። አሕዛብም ቅዱስ ጳውሎስ ያደረውን አይተው በጌታች አመኑ...።
❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ፊሊጶስ ጋር ወደ ሁለት አገሮች በአንድነት ሔዱ ከዚያም በጌታችን ስም ሰበኩ የአገሩም አለቆች ያዟቸው እጆቻቸውንና እግሮቻቸው አሰሯቸው በአንገቶቻቸውም የብረት ሰንሰለቶችን አስገቡ እራሳቸውንም የሸፋን የብር ቆብን ሰሉላቸው ዳግመኛም በእጅና በሐል እጅ በጣቶችም ምሳሌ ሰሩ በእጆቻቸውና በክንዶቻቸው እያንዳንዱን የብረት እጅ ጨመሩ። ከብረቶችም ጋር ቸነከሯቸው።
❤ ሁለተኛም እስከ አንገት የሚደርስ በትከሻ አምሳል ሰሩ በፊትና በኋላም ቸነከሯቸው ደግሞም መላ አካላቸውን የሚከብና ከአካላቸው ምንም እንዳይታይ የሚሸፍን የብረት ሰሌዳ ሰሩ ከወገቦቻቸው ጋራ ቸነከሯቸው ችንካሮችም ተረከዛቸውን ነድለው ወደ ጭኖቻቸው እስከሚደርሱና እስከሚያቆስሏቸው ድረስ የብረት ጫማ ሰርተው እግሮቻቸውን ቸነከሩ። ደግሞ በመሸፈኛ አምሳል የብረት ሰናፊል ሠሩ ቀማሚዎችም መጡ አንድ መክሊት የሚመዝን እርሳስንም አመጡ ታላቅ የብረት ጋንንም ሰባት ልጥር የሰሊጥ ቅባት አመጡ። ስቡንና አደሮ ማሩን የእሳቱን ኃይል አብዝቶ የሚያነደውን ቅመሙን ከሙጫውና ከድኙ ጋር ቀላቀሉት ከዋርካና ከቁልቋል ከቅንጭብም ደም ሰባት ልጥር አንድ ወይን ሐረግንና ቅባት ያለቸውን እንጨቶች ሁሉ አመጡ።
❤ በጋን ውስጥ ያበሰሉትንና ያሟሙትን ልዩ ልዩ ቅመምን አምጥተው ከሥጋቸው እስሚጣበቅ በቅዱሳን ሐዋርያት ሥጋ ላይ ባሉት ሠሌዳዎች ውስጥ ጨመሩት። ከእግራቸው እስከ ራሳቸው ከፍ ከፍ እስከሚል ድረስ በእሳት ያቀለጡትን ያንን እርሳስ ጨመሩት። ርዝመቱ ዐሥራ አምስት ክንድ በሆነ ወፍራም የጥድ ምሰሶ ላይም አቆማቸውና ከበታቻቸው ፍሬ በሌለው በወይን ሐረግና በተልባ እሳቱን አቀጣጥለው አነደዱ። የእሳቱም ነበልባልም ከሥጋቸው በላይ ከፍ ከፍ አለ ሐዋርያትን ግን ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር።
❤ ከመኳንቱም በአንዱ ልብ ርኅራኄ አሳደረና እንዲፈቷቸው አዝዞ ፈቷቸው። በፈቷቸውና ሠሌዳው ከሥጋቸው ላይ ባስወገዱ ጊዜ ቆዳቸው ተገፈፈና ከብረቱ ሠሌዳዎች ጋር ወጣ። ብዙ ደምም ከሥጋቸው ፈሰሰ።
❤ ሰይጣንም በከተማው ሰዎች ልብ አደረና ሐዋርያትን ወደ እሳት ውስጥ መለሷቸው ያን ጊዜ ጌታች ወርዶ የእሳቱ ነበልባል አጠፋው። ዝናብን የተሞላች ብርሕት ደመና መጥታ ቅዱሳን ሐዋርያት ከበበቻቸው በዚያም አገር አንድ ጊዜ በደንጊያ በመወገር አንድ ጊዜም በፍላጻ በመንደፍ ብዙ ተሰቃዩ።
❤ ከዚህም በኋላ ሙታንን በአነሱ ጊዜ የከተማው ሰዎች ሁሉ አመኑ አጠመቋቸው። ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው ካህናትንም ሾሙላቸው በቀናች ሃይማኖት እስኪጸኑ አስተማሯቸው። ከዚያም ወጥተው ጌታችን ወደ አዘዛቸው ወደ ሌላ አገር ሔዱ።
❤ ክብር ይግባውና ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጳውሎስ ተገለጠለትና "የመረጥኩህ ጳውሎስ ሆይ ስላም ላንተ ይሁን። መታሰቢያህን የሚደርገውን፣ በስምህ ቤተ ክርስቲያን የሚሰራውንና የሚጸልየውን፣ ስለትንና መባንም የሚሰጠውን፣ በመታሰቢያህም ቀን ለድኆች የሚመጸውተውን ሁሉ ከአንተ ጋር በመንግሥተ ሰማያት አኖራቸዋለሁ" አለው። "በስምህ የታነጹትም አብያተ ቤተ ክርስቲያናት መላእክቶቼን እንዲጠብቋቸው አደርጋቸዋለሁ" ቡዙ ቃል ኪዳንም ሰጠው። በመለኮታዊ አፉ አፉን ሳመውና ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በክብ ዐረገ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ከቅዱ ዮሐንስ ጋር ጌታችን እንደአዘዛቸው ወደ አንጾኪያ ከተማ ገቡ የአገሪቱንም ሁኔታ ይጠይቅ ዘንድ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ዮሐንስን ላከው ሰዎችንም አግኝቶ ክፉ ነገርን ተናገሩት። ሊገድሉትም ፈለጉ እያለቀሰም ተመለሰ ሰውነቱም ተበሳጨች ጴጥሮስንም አለው "አባቴ ሆይ የእሊህ ጎስቋሎች ክፍታቸው እንዲህ ከሆነ ወደ ነገሥታቱና ወደ መኳንንቱ ገብተን በጌታችን ስም በሰበክን ጊዜ ምን እንሆ ይሆን እንዴትስ ሃይማኖትን እናስተምራለን"። ቅዱስ ጴጥሮስም "ወዳጄ ሆይ የሃያውን ቀን መንገድ በአንዲት ሌሊት ያመጣን እርሱ ሥራችንን መልካም ያደርግልናል አትፍራ አትዘን" አለው።
✝ ከዚህም በኋላ ወደ ከተማ መካከል ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ሰበኩ የከተማውም ሰዎችና የጣዖታቱ አገልጋዮችም በእነርሱ ላይ ተሰበሰቡ ታላቅ ድብደባንም ደበደቧቸው አጎሳቋሏቸውም ግማሽ የእራስ ጠጉራቸውን ላጭተው ተዘባበቱባቸው አሥረውም በግንብ ውስጥ ጣሏቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ተነሥተው ይረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ወደያውን ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኪሩቤልና ሱራፊል እያጀቡት ተገለጠላቸውና እንዲህ አላቸው "የመረጥኳችሁ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሆይ በዘመኑ ሁሉ እኔ ከእናንተ ጋር እኖራለሁና አትፍሩ አትዘኑም"። ለመዘባባቻም በራሷችሁ መኳካከል ስለላጩአችሁ አታድንቁ ይህም መመኪያና ክብርን የክህነት ሥርአትና ምልክትንም ይሆናችኋል ካህን የሚሆን ሁሉ ያለዝህ ምክንያት ሥጋዬንና ደሜን ማቀበል አልችልም። ይህ መልእክት እያለው የሚሞት ካህምን ኃጢያቱም ይሰረይለታል" ይህን ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ዘንድ በክብር ዐረገ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን ተገናኘው "የዚህ አገር ሰዎች ያደረጉብህ ምንድን ነው" አለው እርሱም "ስለ እኔ አታድንቅ የሐዋርያትን አለቃ በእኔ ላይ ባደረጉት አምሳል አድርገውበታልና" አለው። ቅዱስ ጳውሎስ አጽናናቸው እንዲህ አላቸው "እኔ በጌታችን ፍቃድ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቼ እናንተንም አስገባቸዋለሁ"።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሒዶ ምክንያትን ፈጠረ ጣዖታቸውንም እንደሚያመልክ መስሎ ሐዋርያትን እንዲያቀርቡለትና ስለ ሥራቸውም እንዲይቃቸው የከተማውን መኳንን አነጋገራቸው። መኳንንቱም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲያቀርቧቸው አዘዙ በቀረቡም ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ ስለሥራቸው ጠየቃቸው። እነርሱም "ድንቆችንና ተአምራቶችን የሚያደርግ ለክርስቶስ ወደ መዛሙርቶቹ እንደሆኑ ነገሩት። ዳግመኛም "እናንተ እንደርሱ ማድረግ ትችላላችሁ" አለቸው እነርሱም "አዋ በእርሱ ስም ሁሉን ሥራ መሥራት እንችላለን" አሉት።
❤ ከዚህም በኋላ ከእናቱ ማኅፀን እውር ሁኖ የተወለደውን አይኑን አበሩ። የንጉሡንም ልጅ ከሞተ በሦስት ወሩ ሥጋውን ከተባላሸ በኋላ ከመቃብር አሥነሱት። ንጉሡና የከተማ ሠዎች ሁሉ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ጴጥሮስም ምድሩን ረግጦ ውሃን አፈለቀ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አደረጓቸው።
❤ ከዚህም በኋላ በሎዶቅያ ያሉ ምእመናን የቂሳሮስ ባሕር ከወሰኑ አልፎ ቡዙ ሰዎችን ከአትክልት ቦታዎቻቸውና ከከቡቶቻቸው እንዳሰጠማቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላኩ ጴጥሮስም ተወዳጅ ቅዱስ ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላከ ዮሐንስም ወደ እነርሱም ሲጓዝ በጎዳና በግ አገኘ በጉንም እንዲህ ብሎ ላከው "ወደ ቂሳሮስም ወንዝ ሒደ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ወደ አንተ ልኮኛል ወደ ቀድሞው ወሰንህ ተመልሰህ ትገባ ዘንድ አንተ በእግዚአብሔር ቃል የታሰርክ ነህ ብሎሀል በለው"። ያን ጊዜ በጉ ሒዶ እንደአዘዘው አደረገ ወንዙም ሸሽቶ ወደ ቦታው ተመለሰ ቁጥር የሌላቸው ቡዙዎች የከተማ ሰዎችም ይህን አይተው በጌታ አመኑ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ አልፎ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በዚያም ሥራ መሠሪው ሲሞን ተቃወመው እርሱንም ከአየር አውርዶ ጥሎ አጠፍው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ብዙዎች ሕዝቦች አመኑ። የከተማው ገዢ የአክሮጶስ ቊባቶችም የቅዱስ ጴጥሮስን ትምህርት ተቀበሉ ሌሎችም የከበሩ ቡዙዎች ሴቶች ትምህርቱን በመቀበል ከባሎቻቸው እርቀው ንጽሕናቸውን ጠበቁ። ስለዚህም ነገር ቅዱስ ጴጥሮስ ሊገድሉት የሮሜ መኳንንት ተማከሩ። የአልታብዮስ ሚስትም እንዳይገሉት ከሮሜ ከተማ ወጥቶ እንዲሆድ ወደ ቅዱ ጴጥሮስ ላከች ምእመናን ወንድሞችም ውጣ አሉት እርሱም ቃላቸውን ተቀበለ ትጥቁንም ለውጦ ከከተማ ወጣ። በሚወጣበትም ጊዜ መስቀል ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲገባ ጌታችንን አገኘውና "አቤቱ ጌታዬ ወዲት ትሆዳለህ" አለው ጌታዬም "ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እህሔዳለሁ" ብሎ መለሰለት። ቅዱስ ጴጥሮስ "አቤቱ ዳግመኛ ትሰቀላለህን?" አለው።
❤ ያን ጊዜም "ጎልማሳ ሳለህ ወገብህ በገዛ እጅህ ታጥቀህ ወደ ወደድከው ትሔዳለህ በሸመገልክ ጊዜ ግን እጅህን ታነሳና ሌላ ያስታጥቅሃል ወደ ማትወደው ይወስድሃል" ያለውን የጌታችንን ቃል አሰበ አስተዋለውም። ያን ጊዜም ወደ ከተማው ተመልሶ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ለወንድሞች ነገራቸው እነርሱም እጅ አዘኑ።
❤ ንጉሥ ኔሮንም ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲሰቅሉት አዘዘ ሊሰቅሉት በያዙት ጊዜ ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ለመናቸው "የክብር ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ላይ ሁኖ ስለተሰቀለ እኔ ቊልቊል ልሰቀል ይገባኛል"። ወዲያውንም እንደነገራቸውም ሰቀሉት። ተሰቅሎም ሳለ ለምእመናን የሕይወትን ቃል አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ ሐምሌ 5 ቀን ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታች በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረ በረከቱም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘለላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ፦ ይህም ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራ ይኸውም ልሳነ ዕረፍት፣ የክርስቶስ አንደበት፤ የዕውቀት አዘቅት፤ የቤተ ክርስቲያን መብራት፤ እንደ ስሙም ትርጓሜ መሪ አመስጋኝ ወደብ ጸጥታ ነው።
❤ ይህም ጳውሎስ አስቀድሞ በክርስቶስ ያመኑትን የሚያሳድድ ነበር፤ እርሱም ከብንያም ወገን የፈሳሪሳዊ ልጅ ነው። ወላጆቹም ሳውል ብለው ስም አወጡለት ትርጓሜውም ስጦታ ማለት ነው። ቁመቱ ቀጥ ያለ መልኩ ያማረ ፊቱ ብሩህ ቅላቱ እንደ ሮማን ቅርፍት ደበብ ያለ ዐይኑም የተኳለ የሚመስል አፍንጫው ቀጥ ያለ ሸንጎበታም ጉንጩ እንደ ጽጌ ረዳ ነበር።
❤ እርሱም ሕገ ኦሪትን አዋቂ ነበረ። ለሕጉም ቀናተኛ ሆኖ ምእመናን አሳዳጅ ነበረ። ወደ ሊቀ ካህናቱም ሔዶ መንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንና ሴቶችን እንደ ታሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመልሳቸው ዘንድ ለደማስቆ ከተማና ለምኵራቦች የፈቃድ ደብዳቤ ለመነ። ሲሔድም ወደ ደማስቆ ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጊዜ ድንገት ከሰማ መብረቅ ብልጭ አለበት በምድር ላይም ወደቀ ወዲያውም "ሳውል ሳውል ለምን" ታሳድደኛለህ የሚለውን ቃል ሰማ።
❤ ሳውልም "አቤቱ አንተ ማነህ" አለው "አንተ የምሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ በሾለው ብረት ላይ ብትረግጥ አንተን ይጎዳሃል" አለው። እየተንቀጠቀጠም አደነቀ "አቤቱ ምን እንዳደርግ ትሻለህ" አለው ጌታም "ተነሥና ወደ ከተማ ግባ ልታደርግ የሚገባህን ከዚያ ይነግሩሃል" አለው። ከርሱ ጋራ ቁመው የነበሩ ሰዎችም ንግግሩን ይሰሙ ነበር ነገር ግን የሚያዩት አልነበረም።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፭ (5) ቀን።
❤ እንኳን #ለብርሃናተ_ዓለም_ለቅዱስ_ጴጥሮስ፣ #ቅዱስ_ጳውሎስ_በጫካኙ ንጉሥ በኔሮን ቄሳር እጅ ሰማትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሳቁኤል_ለበዓሉ መታሰቢያ፣ #ለሰባ_ሁለቱ_አርድእት_ለመታሰቢያቸው_በዓላቸው፣ #ለአባታችን_ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓላቸውና ለሐዋርያት (ለሰኔ) ፆም ፍቺ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ፡በዚች ከሚታሰቡ፦ በጋዛ ሰማዕት ከሆነ #ከይስሐቅና_ከደብረ_ዓሣ_ጻድቃንም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የሐዋርያት_አለቃ_ቅዱስ_ጴጥሮስ፦ ይህም ጴጥሮስ ከቤተ ሳይዳ የነበረ ዓሣ አጥማጅም ነበረ ጌታችንም ከተጠመቀባት ዕለት ማግስት አግኝቶ መረጠው ከእርሱ አስቀድሞም ወንድሙ እንድርያስን አግኝቶ መረጠው። መድኀኒታችንንም እስከ መከራው ጊዜ ሲያገለግለው ኖሩ ፍጹም ሃይማኖት ለጌታውም ቅንዓትና ፍቅር ነበረው። ስለዚህም በሐዋርያት ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው።
❤ ጌታችን ም ሰዎች ማን እንደሆነ ማንም እንደሚሉት ስለ ራሱ በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎች "ኤርምያስ ይሉሃል ወይም ኤልያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት። ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለ። ጌታችንም "የሃይማኖት አለት የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ነህ" ብሎ ብፅዕና ሰጠው "የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ" አለው።
❤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ከተበቀለ በኋላ ተናገሪዎች ከሆኑ በዚህ ዓለም ተኲላዎች መካከል ገባ በውስጣቸውም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም መልሶ የዋሆች ምእመናን አደረጋቸው። ጌታችንም የማይቈጠሩ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችን በእጆቹ አደረገ ጥቅም ያላቸው ሦስት መልእክቶችንም ጽፎ ለምእመናን ላከቸው። ለማርቆስም ወንጌሉን ተርጒሞ አጽፎታል።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ የከተማው መኳንንት ወደሚሰበሰቡበት ወደታላቁ የጨዋታ ቦታም ሔዶ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብሎ ተናገረ "የሚራሩ ብፁዓን ናቸው ለርሳቸውም ይራሩላቸዋልና" የዚህንም ተከታታይ ቃሎች ተናገረ። በዚያም ከዚያ የነበሩ አራት የደንጊያ ምሰሶዎችም በሚያስፈራ ድምፅ "አሜን" አሉ የተሰበሰቡትም ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ። ከሰባ ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያደረበት አንድ ሰው ነበረ ከእነዚያ ድንጋዮች ቃልን ስለ ሰማ ያን ጊዜ ጋኔኑ ጣለው ከእርሱም ወጥቶ ሔደ። መኳንንቱም ፈርተዋልና ስለዚህ ነገር እያደነቁ ወደ ቤታቸው ገቡ።
❤ ከከተማ መኳንንቶችም ቀውስጦስ የሚባል አንዱ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ስሟ አክሮስያ የምትባል ሚስቱ ዓለምን ስለ መተው ለድኆችም ስመራራትና የመሳሰለውን ቃል ቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት እንዳስተማረ ነገራት። እርሷም በሰማች ጊዜ በልቧ ነቃታ "ይህ ገገር መልካምና ድንቅ ነው" አለች። ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተማረውንም ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ከዚህም በኋላ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድኆች ሰጡ ከዕለት ራት በቀር ምንም አላስቀሩም።
❤ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ንጉሡ ስለ መንግሥት ሥራ ከርሱ ጋራ ለመማከር በቶሎ እንዲደርስ ወደርሱ መልክትን ላከ። ቀውስጦስም ይህ በሰማ ጊዜ ገንዘብ ስላልነበረው ፈርቶ ደነገጠ ተጨነቀም። ምክንያትም አመካኝቶ ይሰወር ዘንድ ከሚስቱ ጋራ ተማከረ። እርሷ ግን "ምክንያት አታድር ነገር ግን ወደ ንጉሥ ሒድ የቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን ጎዳናህን ያቅናልህ" አለች። እርሱም ነገሯን ተቀብሎ ወደ ንጉሡ ሔደ በመንገድም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ብዙ በረከትን አገኘ ወደ ንጉሡም ደረሰ ንጉም በደስታና በክብር ተቀበለው።
❤ ከሦስት ዓመት በኋላም ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሁለቱ ልጆቹ የተመረዘ ውሃ ጠጥተው እነሆ ሞተው ነበር ሚስቱም ለእርሱ መንገርን ፈራች ብዙ ምሳሌዎችን ከመሰለችለት በኋላ ነገረችው። በሰማ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ። ሚስቱም እንዲህ አለችው "ጌታዬ ሆይ ልባችን የሚጽናናበትን እርሱ ያደርግልናል የቅዱስ ጴጥሮስ ፈጣሪ እግዚአብሔርን እንለምነው"። ሊጸልዩም በጀመሩ ጊዜ ቀወስጦስና አክሮስያ "የደቀ መዝሙሬ የጴጥሮስ ቃል ስለሰማችሁና ስለተቀበላችሁት ስለዚህ ልጆቻችሁን በሕይወታቸው እሰጣቸዋለሁ" የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ ያን ጊዜም ልጆቻቸው ድነው ተነሱ ቀውስጦስና ሚስቱም ደስ አላቸው የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
❤ እሊህም ከሞት የተነሱ ልጆች ለቅዱስ ጴጥሮስ ቀደ መዝሙሮቹ ሆኑ የአንዱ ስሙ ቀሌምንጦስ ነው እርሱም ቅዱስ ጴጥሮስ ያየውንና ጌታች በሥጋ ወደ ሰማይ በሚያርግ ጊዜ የገለጠለትን ምስጢር ሁሉ የነገረው ነው ሰዎች ሊያዪአቸው የማይገባቸውን መጻሕፍትን አስረከበው። ይህንም ቀሌምጦስን ሊቀ ከጵጵስና ወንድሙንም ዲቁና ሾማቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን የወለደች የንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ክብራን በምሳሌ አየ። በቀስት አምሳል ደመናን አይቷልና በላዪዋም የብርሃን ድንኳን ነበር በድንኳን ውስጥም አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ተቀምጣለች። በእጆቻቸው ውስጥ የነበልባል ጦሮችና ሰይፈችን ያያዙ መላክትና የመላእክት አለቆች በዙሪያዋ ነበር። እንዲህም እያሉ ያመሰግኗት ነበር። "ከእርሷ የደኅንነት ፍሬ የተገኘ የሰመረች የወይን ተክል አንቺ ነሽ ማኅፀንስሽም የእግዚአብሔር በግ የተሸከመ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ"።
❤ ሁለተኛም እንዲህ ይሏት ነበር " የብርሃን እናቱ ሆይ የምሕረት መገኛ ሆይ ደስ ይበልሽ የአማልክት አምላክ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆነ የመድኅን ዙፋን ሆይ ደስ ይበልሽ ክብርና ምስጋናን የተመላሽ የፍጥረት ሁሉ እመቤት ደስ ይበልሽ"። መላእክት ምስጋናዋንና ሰላምታዋን ባደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርስዋ ተገልጦ ከእርሷ በቀር ማንም ሊያውቀው የማይቻል ነገርን ነገራት ወዲያውኑም ምድር ተናገወች ሊነገር የማይቻል ምሥጢራትንም ገለጠላት።
❤ ከዚህም በኋላ መድኀኒታችን ለአገሩ ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ቅዱስ ጴሮስን አዘዘው ቅዱስ ጴጥሮስም መጥቶ ሔደ ኢዮጴም ወደምትባል የባሕር ዳርቻና ልድያ ወደምትባል አገር ደረሰ። በአንዲት ዕለትም በኢዮጴ ሳለ ብርሕት ደመና ዞረችው። እነሆም ሰፊ መጋረጃ ወደርሱ ወረደች በውስጧም የእንስሳት የምድረ በዳ አውሬዎችና የሰማይ አዕዋፍ አምሳል ነበር። "ጴጥሮስ ሆይ ተነሥና አርደህ ብላ" የሚል ቃልም ከሰማይ ጠራው። ቅዱስ ጴጥሮስም "አቤቱ አይገባኝም እርኲስ ነገር አልበላም ወደ አፌም ከቶ አልገባም" አለ። ያም ቃል ዳግመኛ ጠራውና እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገው አንተ ርኲስ ነው አትበል" አለው ያም ቃል ሦስት ጊዜ መላልሶ እንዲህ ነገረው። በየንግግሩም ወደ እሪያዎች፣ ወደ አራዊትና ወደ አእዎፍ ሥዕሎች ጣት ያመለክተው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ያቺ መጋረጃ ወደ ሰማይ ተመለሰች። ቅዱስ ጴጥሮስም ስለ አየው ራእይ አደነቀ ይህም ራእይ ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር የሚመለሱ አሕዛብን ስለመቀበል እንደሆነ አስተዋለ። ለወንድሞቹ ሐዋርያትም አሕዛብ የእግዚአብሔር ቃል እንደተቀበሉ የመቶ አለቃ ቆርኔሎስንም ከወገኖቹ ጋር እንዳጠመቀው ነገራቸው።
