cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

"ንቁ" የኦርቶዶክስ ልጆች

"ንቁ በሃይማኖት ቁሙ ጎልምሱ ጠንክሩ" 1ኛ ቆሮንጦስ 16 : 13 * ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሀሳብ 💙 @zgebreal19 💙

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
176
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#መልክአ_ገብርኤል ✟የአሸናፊና የኃይል መልአክ ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ከፍጹም ጥፋት እድን ዘንድ ክንፍህን ጋርድልኝ። ✟ወደ ድንግል የተላክ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ ምስራች ተናጋሪ ገብርኤል ሆይ፤ ሰላም ላንተ ይሁን። ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ አብሳሪ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የአካላዊ ቃልን የመጸነስ ብሥራት በማኀፀነ ማርያም ላሳደርክ ሰላም ላንተ ይሁን። ✟በመለአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን አሜን።
Hammasini ko'rsatish...
​​#ጾመ_ነቢያት (የገና ጾም) ኅዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ #ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም: ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡ ምንጭ፡- ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡ ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Hammasini ko'rsatish...

15.97 MB
2.60 MB
2.60 MB
11.93 MB
5.56 MB
​​ውርጃ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን? ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን ተግባርን እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ። 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.