cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ውብ ታሪኮች®

“ማወቅ መልካም ነው ያወቁት ማሳወቅ ይበልጥ መልካምነት ነው።” ውብ ታሪኮች 𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋 𝐏𝐀𝐆𝐄® ለሃሳብ አስተያየታችሁ👉 @Jemseidbot

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 092
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ዝሙት የሚያሳድዳት ጉብል‼ ====================            አንድ ገና ሃያዎቹን ያልደፈነች ጉብል ወደኔ ስልክ መታች። ሠላምታ አቅርባልኝ ስታበቃ ምን እንደማግዛት ስጠይቃት እንባዋ ማቆሚያ አላገኘም። በጣም እየተንዘፈዘፈች አንብታ እስክትረጋጋ ጠበቅኋት። በልቤም ይህችን ወጣት ታግሼ በማዳመጥ ከቻልኩ ችግሯን በመካፈል ምንዳ ከጌታየ ለማግኘች ከጃይ ሆንኩ።            በነገራችን ላይ እንደ ክረምት ዳመና ልውረድ ልውረድ የሚል እንባቸውን ለማራገፍ የሚሹ ሰዎችን መታገስ ችግራቸውን የመቅረፍ አንዱ አካል እንደሆነ የሥነ ልቡና ጠቢባን ይገልጣሉ።እናም እኔም ያደረግኹት ያንን ነው። እርግጥ ነው ጀሊሉ ፊት ተንበርክኮ ማልቀሱ ከሁሉም በላይ አዋጪና ፍቱን ነው።ግና አንዳንድ ችግሮች መውጪያቸው ሲገድ ደግሞ ሰውን(ወንድምን፣ እህትን) ማማከር ግድ ይሆናል።………            ወጣቷ በመጨረሻ ተረጋግታ ሰዓቴን እየፈጀችብኝ በመሆኑ ይቅርታ ጠየቀችኝ። ለዚህ ምንም እንዳይሰማትና ሃጃዋን ለማዳመጥ መዘጋጀቴን ገልጬ አረጋጋኋት። ጉዳዩዋ ባጭሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ መሆኗን፣ ከት/ቤት መልስ የቤተሰብን ሱቅ እየጠበቀች ትምህርቷን እንደምታጠና ነገረችኝ። ሂጃቧን አሳምራ እንደምትለብስ፣ በሶላቷ እንደማትደራደር፣ ሱቋ ውስጥ ሆና ከጥናቷ ጎን ለጎን የተወዳጅ ዑስታዞችን ዳዕዋ በስልኳ እያዳመጠች ኢማኗን እንደምትጠብቅ፣ ሌላው ቀርቶ ያን ያክል የሴት ጓደኞች እንኳን እንደሌሏት አወጋችኝ።           ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን አንድ የሌላ ዕምነት ተከታይ ወጣት ሱቋ እየመጣ እቃ በመግዛት ሰላም እንደሚላት፣ እዚያው ቆም እያለ በመጫዎት ልቧን እንዳሸፈተው፣ እየቆየ ሲሄድ ለረዥም ጊዜያት በስልክ እንደሚያወሩ፣ ቀስበቀስም የት/ት ሰዓቷን እየሰዋች ከርሱ ጋር ጭልጥ ወዳለ ዝሙት መግባቷን ተናገረች። በዚሁ መሃል በሳግ የታጀበ እንባዋን በኃይል ታወርደዋለች። ከወጣቱ ጋር ዉላ ስትመለስ ታጥባ ሶላቷን ከሰገደች በኋላ ተውበት አድርጋ ሁለተኛ ከርሱ ጋር እንደማትሆን፣ ስልኩን  እንደማታነሳ ትወስንና ግና ወጣቱ ሲደውል፣ ወይም በአካል ሲመጣ ያንን ለማድረግ አቅም እንደሚያንሳት አጫወተችኝ። ባጭሩ ልጁን እንዳፈቀረችው አልደበቀችኝም።           በመጨረሻም "ዑስታዝ አሁን እኔን አላህ ይምረኛል? ያውም ከካፊር ወንድ ጋር እንዲህ እየተጨማለቅሁ? እባክህ መላ ካለህ ንገረኝ" ብላ ምርር ወዳለ ለቅሶዋ ተመለሰች።           *       *      **           ሰፊ ከሆነው ምክሬ በፊት አላህ እርሷን እንደሚምራት ምንም እንዳትጠራጠር አበክሬ አሳወቅኋት። አንቺንማ በደንብ ነውንጂ የሚምርሽ! ምክኒያቱም ይህ እንባሽኮ የተውበት ምልክት፣ ከጌታሽ ጋር ለመታረቅ የምታቀርቢው ቁርባን ነው በማለት አባሸርኳት።  አሉ አይደለም እንዴ በሺህ ሳይሆን በመቶ ሺህ ምናልባትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝሙትን ሃላል አድርገው የያዙ ሙስሊም እህቶች! ያሉበት ሁኔታ የማያስደነግጣቸው፣ ገንዘብ በማሳደድ፣ ለፋሽን፣ ለተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ለመኪና፣ ብሎም መኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ገንዘብ ሳይቀር ከሃብታም ሹገር ዳዲዎች እየቀፈሉ ዘንጠው ወጣ ገባ እያሉ የሚኖሩ። ዘመድ ጎረቤት ውጭ ሃገር ሳይሄዱ፣ ሳይወጡና ሰይወርዱ ይህን ያህል ገንዘብ ከወዴት እንደሚያመጡ ግራ እስኪገባው ድረስ ያነጠጡ፣ የተገማሸሩ!            አንቺ ግና ተግባርሽ ትክክል ያለመሆኑን፣ የጌታሽን ቁጣ እንደሚያመጣብሽ በማወቅሽ ነው ይህን ያህል ማንባትሽ። ባይሆን ከዚህ በኋላ የምር ተውበት አድርጊ፣ ከልጁ ጋር ተቆራረጭ፣ ስልኩን አታንሺ ብቻ ሳይሆን ስልክሽን ላልተወሰኑ ጊዜያት ዝጊ፣ ሱቅ አትግቢ፣ ቤትሽ መጥቶ ካስጠራሽ አትውጪ፣ ት/ቤት ስትሄጂ መንገድ ላይ እንደይረብሽሽ ኢማን ካላቸው የሰፈር እህቶች ጋር ጓደኝነት አብጂ ወዘተ… ……             አንድ የማልደብቃችሁ ጉዳይ ውጤቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ መደወል ሲኖርብኝ ሥራ በዝቶብኝ አልደወልኩላትም፣ እርሷ ግን አንድ ቀን ደውላ ሁኔታዎች ጥሩ እየሆኑ እንደሆነ አጫወተችኝ። በዚሁ መሃል አራት ኪሎ ለታክሲ ስጋፋ ስልኬን ጎበዞቹ ሊያስቀምጡልኝ( ኪኪኪኪ) ስለወሰዱት ግንኙነታችን ተቋረጠ።         ይህን ያወጋሁዋችሁ በዚህ አባዜ የተያዛችሁ እህቶች እንድትጠነቀቁ፣ ከአላህ እዝነት ተስፋ እንዳትቆርጡና ዝሙትን አቅልላችሁ እንዳታዩት ነው።ወጣት ሴቶች ሆይ!  ወላሂ ዝሙት ከመሥራት ለአንዱ ጠባየ ሸጋ ሙስሊም 3ኛ ወይም 4ኛ ሚስት መሆን በላጭና ለጀነት የሚያበቃችሁ መሆኑን ልብ በሉ። ልጅቷ ልጁ ካፊር መሆኑ ነበር ይበልጥ ያስጨነቃት። ካፊር ሆነ ሙስሊም ያለችበትን ሁኔታ ከዝሙትነት አያወጣውም።        ………እናም የጋብቻን መንገድ አቅልሉ፣ ሠርግ፣ ጂኒ እያላችሁ የሚወዳችሁን አታሽሹ። ሃብት ይመጣል ወላሂ። የወላጆቻችሁን ታሪክ አስተውሉ፣ ብዙዎቹ በአንዲት ጠባብ ክፍል ለሃያና ሰላሳ ዓመት ተቀምጠው እናንተን ወይም ታላላቆቻችሁን ወልደው ነው አሁን ለሚገኙበት ማለፊያ ህይወት የበቁት። አደራ ከዝሙት ባቡር እንዳትሳፈሩ፣ አንዴ ከገባችሁበት ማቆሚያ የለውምና። እንዲያው መቅዘፍ፣ መጃጃል፣ ከአላህና ከሰው ዓይን መውደቅ፣ ሲገፋም ሁስነል ኺታም እስከማጣት አደጋ አለው ጓዶች! © አቡ ቢላል #ሼር_በማድረግ_ለሌሎች_ያካፍሉ Join 👇👇👇👇 @wub_Tarikoch @wub_Tarikoch
Hammasini ko'rsatish...
👍 11
በቲክቶክ ፎሎው አድርጉ👆 አጫጭር ዳዕዋ ምክሮችና አዝካሮች የቁርአን አንቀፆችን ያገኛሉ
Hammasini ko'rsatish...
3
Photo unavailableShow in Telegram
01:13
Video unavailableShow in Telegram
በጊዜ ለመነሳት ደግሞ በጊዜ ተኙ። ዕድሜያችሁን ለዉድ ነገር አታዉሉ። ቲክቶክ ይቅርባችሁ ። ቻትም እንደው ዝምብሎ መድከም እኮ ነው። እኔ ትናንሽ ንግድ አልሠራም እንደሚለው ኩሩ ነጋዴ ከፍ ከፍ ያሉ በጎ ሥራዎችን መርጣችሁ ሥሩ። ዉዱእ አድርጉና፣ ሱናችሁን ስገዱና፣ ዚክራችሁን አድርጉና ነፍሳችሁን ለፈጠራችሁ ጌታ አስረክቡና፣ የአላህን ጥበቃ እመኑና ጥቅልል ብላችሁ ተኙ። ያኔ ሌሊታችሁ ያምራል ፤ ህልማችሁም ጥሩ ይሆናል። ኢንሻአላህ ። ቲስበሑ ወዳጆጄ #ሼር_ማድረግ_እንዳትረሱ Join 👇👇👇👇 @wub_Tarikoch @wub_Tarikoch
Hammasini ko'rsatish...
👍 7
02:05
Video unavailableShow in Telegram
👍 1 1
00:42
Video unavailableShow in Telegram
04:25
Video unavailableShow in Telegram
👍 1🥰 1
00:25
Video unavailableShow in Telegram
አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላህ #ሼር_ማድረግ_እንዳትረሱ Join 👇👇👇👇 @wub_Tarikoch @wub_Tarikoch
Hammasini ko'rsatish...
1