cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሞትን አስታውስ (تذكر الموت)

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
189
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

AUD-20200725-WA0214.mp39.34 KB
ሰዎችን ተዋቸው!! ነገ ግርዶሹ ይነሳል፣ የተደበቁ ነገሮችም በሙሉ ይወጣሉ፣ ምስጥሮችም ይጋለጣሉ። ⚡ወንጀልህን ከምትደብቀው በላይ መልካም ስራህን ደብቅ ብቻህን እንደተወለድከው ሁሉ የምትሞተውም ብቻህን እንደሆነ እወቅ ሰዎችን ተዋቸው ❗ አይደለም ላንተ አላህ ከቀደረላቸው ውጪ ለራሳቸውም ምንም ማድረግ አይችሉም ☄ሁሌም ህያው በሆነው በአርሹ ባለቤት ተመካ✅ ከጭቃ የተፈጠሩና ነገም ወደዛው የሚመለሱ ደካማ የሰው ልጆችን ተስፋ አታድርግ፣የነርሱ መራቅና መቅረብ መውደድና መጥላታቸውም አንተ ዘንድ እኩል ይሁኑ ✅ ⏳ለዲንህና ለዱኒያህ የሚበጅህን ነገር አውቀህ እዛ ላይ ፅና! ጨለማው ሲወገድ ያለቀሱት ካለቃቀሱት ይለያሉ፣ ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩና ዓላማ ቢስ የሆኑ ሰዎች ካሰቡት ለመድረስ ቀን ከሌሊት ይለፉ የነበሩ ሰዎችን ተሳክቶላቸው ሲያዩ በቁጭት አለንጋ እራሳቸውን ይገርፋሉ ☞የሙእሚን ግቡ አላህን ማስደሰትና ጀነትን መውረስ ነውና ሳትደርስ የደረሰክ መስሎህ ከመንገድ እንዳትቀር፣ ☞ከወዳጅ ነጥሎ ከሰፊው ቤት አውጥቶ ጨለማና ጠባቡ ጉርጓድ ላይ ወስዶ ሊጥልህ በድንገት የሚመጣውን ሞት ዘወትር በልብህ አስታውስ❗ ☞በዚህ በጣም ከባድና አስቸጋሪ በሆነው የጘርጘራ ሰዓት ላይና ከዛም በኋላ የሚጠቅምህ ስራህ ነውና መልካም ስራ ላይ በርታ ፣የምትሰራው ስራም ኢኽላስ ይኑረው፣ ☞ሰው ምን ይለኛል ብለህ መልካምን ስራ አትተው፣ ወንጀልንም አትዳፈር❗ ሰዎችን ተዋቸው‼️ https://t.me/rememberdeth
Hammasini ko'rsatish...
◼️ መሞት መጥፋት መስሎኝ◼️ መሞት መጥፋት መስሎኝ፣ አካሌ በስብሶ በዛው ይቀር መስሎኝ፣ የወንጀል መርማሪ ሚዛን የለ መስሎኝ፣ ትርፉና ኪሳራው አይበጠር መስሎኝ፣ ከሞትኩኝ በኋላ መሞት ማረፍ መስሎኝ፣ እራሴን ስሸውድ ሳታልለው ኑሬ፣ በወንጀል መኣበል እራሴ ዘፍቄ፣፣ ካአላህ ፊት እንዳልቆም ከወራዶች ሁኔ፣ እራሴን ላስተካክል ሳይደርስብኝ ሞቴ። ያረቢ የአላህ ባንተ መንገድ ምራኝ ዱኒያ አሄራዬን በተውሂድ አስውበኝ። https://t.me/rememberdeth
Hammasini ko'rsatish...
02:27
Video unavailableShow in Telegram
4.57 MB
የአላህ መልእክተኛ አላህ ከሰማያት ከዐርሽ በላይ መሆኑን በማያሻማ መልኩ ገልፀዋል፤ አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ከሚያረጋግጡ የሀዲስ ማስረጃዎች በጥቂቱ እንመልከት፡ قَال النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَلاَ تَأْمَنُونِي وَأَنَا أَمِينُ مَنْ فِي السَّمَاءِ›› صحيح البخاري4351 ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ በሰማይ ያለው(አላህ) አምኖኝ ሳለ አታምኑኝምን››ቡኻሪ 4351 ሙዓውያ ኢብኑ ሀከም ፍየሎችን የምትጠብቅለት አገልጋይ ነበረችው እና ተኩላ በላባት ተበሳጭቶ መታት፤ ይህም ለነብዩ صلى الله عليه وسلم ነገራቸው በዚህም ነብዩ صلى الله عليه وسلم አከበዱበት… قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ أَفَلَا أُعْتِقُهَا؟ قَالَ: «ائْتِنِي بِهَا» فَأَتَيْتُهُ بِهَا، فَقَالَ لَهَا: «أَيْنَ اللهُ؟» قَالَتْ: فِي السَّمَاءِ، قَالَ: «مَنْ أَنَا؟» قَالَتْ: أَنْتَ رَسُولُ اللهِ، قَالَ: «أَعْتِقْهَا، فَإِنَّهَا مُؤْمِنَةٌ» مسلم 1/381 ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ ነፃ ላውጣትን›› አልኳቸው እሳቸውም‹‹ ወደኔ አምጣት አሉኝ›› ወደ እሳቸው አመጠኋት እና እንዲህ አሏት ‹‹አላህ የት ነው›› እሷም ‹‹በስማይ›› አለች እሳቸዉም ‹‹እኔ ማነኝ አሏት›› እሷም ‹‹ አንቱ የአላህ መልእክተኛ ናቹህ›› አሳቸው እንዲህ አሉ‹‹ ነፃ አውጣት እሷ ሙእሚን ነች››ሙስሊም ዘግበዉታል 1/381 ከሀዲሱ እንደምንረዳው የአላህ መልእክተኛ እምነቷን ካረጋገጡበት አንዱ አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን መመስከሯ ነው፤በዚህ ዘመን አላህ የት ነው አይባልም በሚል ለሚሞግት ሰው በቂ ማስተማሪያ ነው! ልብ ካላቸው!! አላህ በስማይ ነው ስንል በሰማይ ዉስጥ ሳይሆን ከሰማያት በላይ መሆኑን እና ‹ፊ› የሚትለዋ ፊደል በላይ የሚል ትርጉም እንዳላት ከላይ ስለተመለከትን የሚያወዛግበን አይመስለኝም፡፡ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَمَّا قَضَى اللَّهُ الخَلْقَ كَتَبَ فِي كِتَابِهِ فَهُوَ عِنْدَهُ فَوْقَ العَرْشِ إِنَّ رَحْمَتِي غَلَبَتْ غَضَبِي»صحيح البخاري 3194 የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ አላህ ፍጥረታትን(ፈጥሮ) እንደጨረሰ እሱ ዘንድ ከዓርሽ በላይ ካለው መፅሓፉ እዝነቴ ቁጣዬን ቀድማለች ብሎ ፃፈ፡፡›› ሶሂህ አል-ቡኻሪ 3194 ከዚህ ሀዲስ በማያሻማ መልኩ የምንረዳው አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ነው፡፡ عَنْ أَنَسٍ قَالَ: فَكَانَتْ زَيْنَبُ تَفْخَرُ عَلَى أَزْوَاجِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ تَقُولُ: زَوَّجَكُنَّ أَهَالِيكُنَّ، وَزَوَّجَنِي اللَّهُ تَعَالَى مِنْ فَوْقِ سَبْعِ سَمَوَاتٍ.‹‹صحيح البخاري 7420 አነስ (ረድየሏሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት፡ ዘይነብ በነብዩ ሚስቶች ላይ ስትፈክር ነበር እንዲህም ትላለች‹‹ እናንተን የዳሯቹህ ቤተሰቦቻቹህ ናቸው እኔን ግን ከሰባት ሰማያት በላይ(ያለው) አላህ ነው የዳረኝ፡፡›› ሶሂህ አል-ቡኻሪ 7420 በሌላ የቲርሚዚ ዘገባ ደግሞ፡ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الْآيَةُ فِي زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ {فَلَمَّا قَضَى زَيْدٌ مِنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَاكَهَا} [الأحزاب: 37] አነስ(ረድየሏሁ አንሁ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ እርሷን አጋባንህ፡፡›› ይህ የቁርአን አንቀፅ በዘይነብ ቢንት ጀሕሽ በወረደ ግዜ ዘይነብ በነብዩ ሚስቶች ላይ ስትፈክር ነበር እንዲህም ትላለች‹‹ እናንተን የዳሯቹህ ቤተሰቦቻቹህ ናቸው እኔን ግን ከሰባት ሰማያት በላይ(ያለው) አላህ ነው የዳረኝ፡፡›› ቲርሚዚ 3213 عَنْ أَبِي حَازِمٍ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، مَا مِنْ رَجُلٍ يَدْعُو امْرَأَتَهُ إِلَى فِرَاشِهَا، فَتَأْبَى عَلَيْهِ، إِلَّا كَانَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ سَاخِطًا عَلَيْهَا حَتَّى يَرْضَى عَنْهَا» مسلم 1436 አቡ ሁረይራ(ረድየሏሁ አንሁ) እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ ነብሴ በእጁ በሆነው እምላለው አንድ ወንድ ሚስቱን ለምኝታ ጋብዟት እምቢ አትለውም ፤ ያበሰማይ ያለው በሷ ላይ የተቆጣባት ቢሆን እንጂ እሱ(ባሏ) ከእርሷ እስኪወድ ድረስ፡፡›› عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «الرَّاحِمُونَ يَرْحَمُهُمُ الرَّحْمَنُ، ارْحَمُوا مَنْ فِي الأَرْضِ يَرْحَمْكُمْ مَنْ فِي السَّمَاءِ، …»:الترمذي 1924 حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ አብደላህ ኢብኑ ኡመር(ረድየሏሁ አንሁማ) እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ አዛኞችን አር-ራህማን(አዛኙ አላህ) ያዝንላቸዋል፤ በመሬት ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው(አላህ) ያዝንላችኋል››ቲርሚ ዘግበዉታል 1924 ሀዲሱ ሶሂህ ነው ብዙ ሀዲሶችን መጥቀስ ቢቻልም ፅሁፉ እንዳይረዝም ከላይ የጠቀስናቸው ሶሂህ ሀዲሶች አላህ ከሰማያት በላይ ከዓርሽ በላይ መሆኑን ያረጋግጣሉ፤ አላህ ያጠመመው ቢሆን እንጂ ይህንንም የሚያስተባብል የለም፡፡ ኢንሻ አላህ ይቀጥላል Please sher & invite channal https://t.me/rememberdeth
Hammasini ko'rsatish...
ቁርአንን የተረዳ እና የተገነዘበ ሰው አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን በግልፅ እና በማያሻማ መልኩ በቁርአን ሰፍሮ እንደሚገኝ ያውቃል፡፡በቁርአን አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች በአላህ ፍቃድ ጥቂቱን እንመለከታለን፡፡ አላህ በሰባት ቦታዎች አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን በግልፅ ነግሮናል፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ‹‹ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡››አል-አዕራፍ 54፣ ዩኑስ 3፣ ፉርቃን 59፣ አስ-ሰጅዳ 4፣ አል-ሐዲድ 4 اللَّهُ الَّذِي رَفَعَ السَّمَاوَاتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا ۖ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ‹‹አላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋት አዕማድ ሳትኖር ያነሳት ከዚያም ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡››አር-ራዕድ 3 الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ ‹‹አልረሕማን ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡›› ጠሀ 5 የጥሜት ባለቤቶች ‹‹ኢስተዋ›› የሚለውን አላህ ያልተናገረዉን፣ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ያላስተማሩትን እና ሶሀቦች የማያውቁትን ትርጉም ለመስጠት ተሕሪፍ በማድረግ ‹‹ኢስተውላ›› ለማለት ነው ይላሉ፤ ትርጉሙም ተቆጣጠረ ማለት ነው፡፡ እነሱ እንደሚሉት ከተተረጎመ ‹‹ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ዐርሹን ‹‹ተቆጣጠረ››፡፡›› ይሆናል ይህም አላህ ዓርሽን የተቆጣጠረው ሰማይ እና መሬትን ከፈጠረ ቡኃላ ነው የሚለዉን ያስይዛል ይህም አላህን ማሳነስ ነው፡፡ ስለዚህ ኢስተውላ ብሎ መተርጎም የአላህ ስልጣንን መገደብ ነው፤ በዚህ መልኩ የአላህ ባህሪን መተርጎም ክህደት ነው፡፡ سئل الإمام مالك بن أنس رحمه الله فقيل: يا أبا عبد الله {الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى} كيف استوى؟ فقال: الاستواء غير مجهول، والكيف غير معقول، والإيمان به واجب، والسؤال عنه بدعة. ثم أمر بالرجل فأخرج. الأسماء والصفات للبيهقي2/305 ታላቁ ኢማም ማሊክ ተጠየቁ‹‹ የአባ አብዲላህ ‹‹አራህማን ከዓርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡›› እንዴት ከፍ አለ ተብለው ተጠየቁ እሳቸዉም እንዲህ አሉ‹‹ አል-ኢስቲዋእ(ከፍ ማለቱ) የማይታወቅ ነገር አይደለም(ግልፅ ነው)፣ እንዴት የሚለው አእመሮ ሊደርስበት የማይችል ነው፣ በእርሱ ማመን ግዴታ ነው፣ ስለዚህ(እንዴት) ብሎ መጠየቅ ቢድዓ ነው፡፡›› ሰውየው እንዲወጣ አዘዙ እና አስወጡት፡፡አል-አስማእ ወሲፋት ሊልበይሀቂ 2/305 ኢማሙ ማሊክ በአላህ ባህሪ ዙርያ የነበራቸው አቋም እንደተመለከትነው የአላህ ባህሪዎችን እንደወረዱ ማፅደቅ እንጂ መፈላሰፍ እንደለለብን እንገነዘባለን፡፡አላህ በዛቱ ከፉጡራኑ በላይ መሆኑን የሚያመላክቱ የቁርአን አንቀፆች እንመለከታልን يَا عِيسَى إنِّي مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إلَيَّ ‹‹ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡›› አል-ዒምራን 55 አላህ አንሺህ ነኝ ሲል ወደ ላይ አነሳህ አለው ማለት ነው ወደ እኔ ሲል ደግሞ አላህ ከላይ መሆኑን ይገልፃል፡፡ بَل رَّفَعَهُ اللَّهُ إلَيْهِ ‹‹ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው፡፡›› አን-ኒሳእ 158ከዚህ የቁርአን አንቀፅ አላህ ከላይ መሆኑን እንረዳልን፡፡ አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን የሚያስረዱ የቁርአን አንቀፆችን እንመለከታለን፡፡ أَأَمِنتُم مَّن فِي السَّمَاءِ أَن يَخْسِفَ بِكُمُ الْأَرْضَ فَإِذَا هِيَ تَمُورُۖأَمْ أَمِنتُم مَّن فِي السَّمَاءِ أَن يُرْسِلَ عَلَيْكُمْ حَاصِبًا ۖ فَسَتَعْلَمُونَ كَيْفَ نَذِيرِ ‹‹ከሰማይ በላይ ያለው (አላህ) በእናንተ ምድርን ቢደርብባችሁ ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ ብትኾን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?)፡፡ ወይም በሰማይ ያለው(አላህ) በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደኾነ ወደፊት ታውቃላችሁ፡፡››አል-ሙልክ 16-17 የሚገርመው ሙስሊም ነን ባይ የጥመት ተከታዮች የማያውቁትን ፊርዓውን እኔ ጌታቹህ ነኝ ያለው ካፊር እንኳ አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን ያውቃል፡፡ وَقَالَ فِرْعَوْنُ يَا هَامَانُ ابْنِ لِي صَرْحًا لَّعَلِّي أَبْلُغُ الْأَسْبَابَأَسْبَابَ السَّمَاوَاتِ فَأَطَّلِعَ إِلَىٰ إِلَٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّي لَأَظُنُّهُ كَاذِبًا ‹‹ፈርዖንም አለ «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዢም ሕንጻን ለእኔ ገንባልኝ፡፡ «የሰማያትን መንገዶችን (እደርስ ዘንድ)፣ ወደ ሙሳም አምላክ እመለከት ዘንድ፡፡ እኔ ውሸታም ነው ብዬ በእርግጥ እጠረጥረዋለሁ»(አለ)፡፡››ጋፊር 36-37 ከዚህ የቁርአን አንቀፅ የምንረዳው ሙሳ አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን ለፊርዓውን እንደነገሩት እና ፊርዓውንም እንዳላመነ እንንረዳለን ኢማሙ አጥ-ጠበሪ ይህን አንቀፅ ሲያብራሩት እንዲህ ይላሉ وقوله: (وَإِنِّي لأظُنُّهُ كَاذِبًا) يقول: وإني لأظنّ موسى كاذبا فيما يقول ويدّعي من أن له في السماء ربا أرسله إلينا. ‹‹እኔም ውሸታም ነው ብዬ በእርግጥ እጠረጥረዋለሁ» በሚለው ንግግር (ፊርዐውን) እንዲህ ይላል፡- ሙሳ በሚናገረው፣ ለእርሱም ከሰማይ ጌታ እንዳለው እና ወደኛ እንደላከው በሚለው ነገር በዉሸት እጠረጥረው አለሁ፡፡››የኢማም አጥ-ጠበሪ ተፍሲር 21/387 ከዚህ እንደምንረዳው አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን ነብዩ ሙሳ ማስተማረቸው እና በዚህም ሲያምኑ እንደነበር ነው፡፡ እኒዚህ የቁርአን አንቀፆች እና አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን የሚያስረዱ ማስረጃ ሲቀርብላቸው አላህ ስንት ነው እንዴ? አንዴ ሰማይ አንዴ ከአርሽ በላይ ነው የምትሉት በተጨማሪምفِي «ፊ›› የሚለው የአረብኛ ፊደል ውስጥ ያለን ነገር ለመግለፅ ነው የሚጠቅመው እናም አላህ እንዴት ሰማይ ላይ ነው ሌላም ግዜ አርሽ ላይ ነው እምትሉት ለሚለው ጥያቄ!! አላህ ቀጥተኛው መንገድ ይምራን እና እወቅ/ እወቂ «ፊ» የሚለው የአረብኛ ፊደል ሐርፍ አል- ጀር ሲትሆን على «ዓላ» ማለትም ‹‹ዉስጥ›› ከሚለው ትርጉም በተጨማሪ ከ‹‹ላይ›› የሚል ትርጉም አላት፡፡ ለምሳሌ አላህ ያለውን እንመልከት وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً
Hammasini ko'rsatish...
ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡›› አል-በቀራህ 30 አላህ እኛን በምድር ላይ ለማድረግ እንደፈለገ ለመግለፅ ‹‹ፊ›› የሚለው ቃል ተጠቅሟል ስለዚህ ‹‹ፊ›› የሚለው ቃል ዉስጥ ብቻ ተብሎ የሚተረጎም ከሆነ እኛ አላህ ያኖረን ከመሬት ላይ ሳይሆን ከመሬት ዉስጥ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ከእውነታው ጋር የሚስማማ አይደለም ምክንያቱም እኛ እየኖርን ያለነው ከመሬት ላይ እንጂ መሬት ዉስጥ ክረስት(crest) ወይም ኮር ላይ አይደለም!! ስለዚህ ‹‹ፊ›› የሚለው ቃል በላይ የሚለው ትርጉም እንዳለው ተረዳን ማለት ነው፡፡ ሌላ ምሳሌ እንጨምር وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ فِي جُذُوعِ النَّخْلِ ‹‹በዘምባባም ግንዶች ለይ እሰቅላችኋለሁ፡፡››ጠሀ 71 እሰቅላችኋለሁ ሲል ‹‹ፊ›› የሚለውን ቃል ተጠቅሟል ስለዚህ ‹‹ዉስጥ›› ብለን ብንተረጉመው ሰው የሚሰቀለው ዛፍ ተስንጥቆ ዉስጥ ላይ ነው ማለት ነው? በግልፅ እንደምናውቀው ሰው የሚሰቀለው ከዛፍ ላይ እንጂ ዛፍ ውስጥ አይደለም ስለዚህ ‹‹ፊ›› የሚለው ከላይ የሚል ትርጉም አለው ማለት ነው፡፡ስለዚህ ‹‹ፊ ሰማእ›› የሚለው ሰማይ ዉስጥ ሳይሆን አላህ ከሰማይ በላይ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡ ይቀጥላል https://t.me/rememberdeth
Hammasini ko'rsatish...
አላህ የት ነዉ? ኢስላምን አልቆ ሽርክን ዝቅ ላደረገው አላህ ምስጋና ይገባው፤ የአላህ ዉዳሴ እና ሰላም በነብዩ ላይ ይስፈን፡፡ አላህ የት ነው? የሚለው ጉዳይ ብዙዎቹ ግራ የተጋቡበት፤የተለያዩ ፊርቃዎች(ቡድኖች) የራሳቸውን አመለካከት የሚያራምዱበት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህም ነው ለብቻው ርዕስ ተሰጥቶት እንዲዘጋጅ የተፈለገው፤ የፁሁፉ አላማ እውነታዉን ለማያውቁት ማሳወቅ፣ለሚጠራጠሩ ደግሞ እርግጠኝነትን ለማረጋገጥ፣ የተሳሳተ አመለካከት የያዘ ሰው ደግሞ እንዲመለስ ታስቦ የተዘጋጀ ፅሁፍ ነው! ወደ ዋናው ርዕሰ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት በአላህ ባህርያቶች ዙርያ ሊኖረን የሚገባው እምነት ምን መምሰል እንዳለበት አስቀድመን እንመለከታለን ምክንያቱም እነዚህን አራት መርሆዎች በአላህ ባህሪ ዙርያ ትክክለኛ አቋም እንዲኖረን ያደርጋሉ፡፡አህለ ሱና ወልጀምዓ የአላህ ባህሪን፡ 1. ተህሪፍ አያደርጉም፡-ማለትም የአላህ ባህሪን እንደወረደ ያፀድቃሉ፣ ስለ አላህ የሚናገሩ የቁርአን አንቀፆችም ሆኑ ሶሂህ ሀዲሶችን ባሉበት ያፀድቃሉ ትርጉሙን ሳያዛቡ፡፡ 2. ተዕጢል አያደርጉም፡- ማለትም የአላህ ባህሪን አይገባዉም በሚል ወድቅ አያደርጉም በሁሉም የአላህ ባህሪዎች ያምናሉ፡፡ 3. ተክይፍ አያደርጉም፡-ማለትም የአላህ ባህሪዎችን ሲያፀድቁ ሁኔታዎችን አይዘረዝሩም አላህ እና መልእክተኛው የተናገሩትን ብቻ ያፀድቃሉ፡፡ 4. ተምሲል አያደርጉም፡-ማለትም የአላህ ባህሪ ከፉጡራን ባህሪ ጋር አያመሳስሉም፤ አላህን የሚመመስል አንዳች ነገር የለም፡፡ አላህ ይሰማል ስንል መስማቱ እንደኛ አይደለም በሌሎች ባህሪዎቹም እንደዛው፡፡ የአህለ ሱና ወልጀምዓ በአላህ ባህሪዎች ዙርያ ያለን እምነት ይህንን ይመስላል፡፡አላህ የት ነው የሚለዉን እውነታ ለማወቅ በአላህ ፍቃድ ከቁርአን፣ከሶሂህ ሀዲሶች እና ከሰለፎች ንግግር ማስረጃዎችን እንመለከታልን፡፡ ሰለፎቻችን በአላህ ባህሪ ዙርያ የነበራቸውን አቋምእንመልከት ኢማም አሽ-ሻፊዒ እንዲህ ይላሉ፡ قال الإمام أبو عبد الله محمد بن إدريس الشافعي رضي الله عنه: آمنت بالله وبما جاء عن الله، على مراد الله، وآمنت برسول الله، وبما جاء عن رسول الله على مراد رسول الله. ‹‹በአላህﷻ አምኛለሁ ከአላህﷻ በመጣዉም አላህﷻ በሚፈልገዉ መልኩ፡፡ በአላህﷻ መልዕክተኛ አምኛለሁ ከመልዕክተኛዉ በመጣዉም ነገር አምኛለሁ፤ በሚፈልጉት መልኩ አምኛልሁ፡፡››ሉምዓት አል-ኢዕቲቃድ 7 قال الإمام أبو عبد الله أحمد بن محمد بن حنبل رضي الله عنه في قول النبي صلى الله عليه وسلم: «إن الله ينزل إلى سماء الدنيا» ، أو «إن الله يرى في القيامة» ، وما أشبه هذه الأحاديث نؤمن بها، ونصدق بها بلا كيف، ولا معنى، ولا نرد شيئا منها، ونعلم أن ما جاء به الرسول حق، ولا نرد على رسول الله صلى الله عليه وسلم، ولا نصف الله بأكثر مما وصف به نفسه بلا حد ولا غاية {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} [الشورى: 11] ونقول كما قال، ونصفه بما وصف به نفسه، لا نتعدى ذلك، ولا يبلغه وصف الواصفين... ኢማሙ አህመድ ኢብን ሐንበል :አላህﷻ ይዘንላቸዉና ‹‹ አላህﷻ ለዱኒያ ቅርብ ወደሆነችው ሰማይ ይወርዳል፣አላህﷻ የዉመል ቂያማ ይታያል እና በመሳሰሉት ሀዲሶች ላይ በእርሷ እናምናለን ሁኔታዎችን ሳንዘረዝር እውነት ነው እንላለን፣ከትክክለኛው ትርጉም ዉጭ ሌላ ትርጉም አንሰጥም፤ ከእርሷም ምንም ነገር አንመልስም(አናስተባብልም)፡፡ ነብዩ ﷺ የመጡበት መንገድ ሃቅ መሆኑን እናዉቃለን ንግግራችዉም ሆነ አስተምህሮታቸዉን አንመልስባቸዉም እንቀበላቸዋለን፡፡ አላህንም ﷻደግሞ ያለ ገደብ እና ያለመጨረሻ እርሱ እራሱን ከገለጸበት በላይ አንገልጸዉም፡፡ አላህﷻ እንዲህ ይላል (እርሱን የሚመስል ምንም የለም እርሱ ሰሚና ተመልካች ነዉ(አሽ-ሹራ 11) አላህ እንዳለው እንላለን፤ ራሱን በገለፀበት እንገልፃለን በዚህም ላይ ድንበር አናልፍም፤ የገላጮች ገለፃም አይደርሰዉም፡፡…››ሉምዓት አል-ኢዕቲቃድ 7 ቀደምቶቻችን በአላህ ባህሪ ዙርያ የነበራቸውን አቋም እንደተመለከትነው አላህ ራሱን በገለፀበት እንደሚገልፁ እና ራሱን የገለፀበትን አይገባዉም በሚል እንደማያስተባብሉ ተመልክተናል ይህም አሁን እኛ ከምናምንበት ጋር የሚስማማ እና የማይቃረን መሆኑን እንረዳለን፡፡ ይህን የሚያስተባብሉ ቡዱኖች አህባሽን ይመስል የሰለፎችን መንገድ እንደማይከተሉ በግልፅ እንረዳለን፡፡ ይቀጥላል https://t.me/rememberdeth
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.