cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡ ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
15 668
Obunachilar
-724 soatlar
-347 kunlar
-3330 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፪ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሰን! "ግቢ ጉባኤያት የአገልግሎት መሠረት" በሚል መሪ ቃል እሑድ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከ7፡00 ሰዓት ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በመገኘት የማኅበራችንን የምሥረታ በዓል በጋራ እናክብር።
Hammasini ko'rsatish...
በበጎች የተመሰሉ መነኮሳት ፡- እንደ በጎች በማኅበር በአንድነት ሳይለያዩ በፍቅር እንደ አንድ አካል ሆነው በማኅበር የሚኖሩ መነኮሳት፣ ባለመለያየት፣ በቅንነት፣ በአንድነት የሚኖሩ ቅዱሳን መነኮሳትን የሚወክሉ መነኮሳትን፣ በርግብ የተመሰሉ መነኮሳት፡- በየዋህነትና በቅንነት በፍቅርና በአንድነት የሚኖሩ፣ ቢጠሏቸው፣ ቢሰድቧቸው፣ ቢጸየፏቸው የማይቀየሙ መነኮሳትን፣ በዋኖስ የተመሰሉ መነኮሳት፡- በጣፈጠና ባማረ ጣዕመ ዜማ ያለ ትዕቢትና ትምክህት በትሕትናና በፈሪሃ እግዚአብሔር በመንቀጥቀጥና እንባቸውን እያፈሰሱ ለፈጣሪያቸው የሚዘምሩና የሚያመሰግኑ መነኮሳትን በዋኖሶች መስሎ አሳይቶታል፤ የዋኖስ ድምፅ ጥዑም ነውና፡፡ በተጨማሪም በንቦች የተመሰሉ መነኮሳት፡- እንደ ንቦች ጠቢባን፣ እንደ ንብ በትጋት የጽድቅ ሥራዎችን ከገድላት የሚቀስሙ መነኮሳትን፣ በፌቆዎች የተመሰሉ መነኮሳትን፡- ያለንዝህላልነትና ያለመታከት በትጋት እንደ ፌቆዎች እየሮጡ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሥራ የሚፋጠኑ መላኩ ለአባ ጳኩሚስ አሳይቶት አባታችንም አይቶ ማድነቁን ሕንፃ መነኮሳት ይነግረናል፡፡ (ሕንፃ መነኮሳት ክፍል ሦስት ቁጥር ፲) ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም አባ ጳኩሚስ ያያቸው ዓይነት መነኮሳትና ማኅበረ መነኮሳት እንደ ምድር አሸዋ፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተውና ደምቀው የነበሩበት መሆኑን የበርካታ ገዳማትና መናንያን ታሪኮች ያስረዱናል፡፡ ለመሆኑ “ክብረ ምንኩስና ዛሬ ምን ሁኔታ ላይ ነው?” የሚለውን በክፍል ሰባት እንዳስሰዋለን ቸር እንሰንብት!
Hammasini ko'rsatish...
ከላይ ከተሰጠው የግእዝ ትርጉም ተነሥተን ስንመረምረው ምንኩስና ማለት ምን ማለት እንደሆነና ምን ያክል ከባድ ኃላፊነት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ዓለሙንና አምሮቱን የናቀ፣ ስለ ጽድቅ ብሎ ራሱን ያደኸየ፣ “እኔ ለዓለም ሙት ነኝ፤ ዓለምም በእኔ ዘንድ ሙት ናት፤ የዓለም የሆነው ሹመቱ፣ ሽልማቱ፣ ሀብቱ፣ ንብረቱ አያስፈልገኝም፤ የሚስት ደስታ የልጅ ተስፋ ይቅርብኝ፤ ንጽሕ ጠብቄ፣ ከሴት ርቄ ራሴን ለመንግሥተ ሰማያት ጃንደረባ አድርጌ በጾም፣ በጸሎት፣ በትሩፋት ተወስኜ እኖራለሁ” ብሎ የወሰነ፣ ራሱን የለየ፣ ቁረንጮ አንጥፎ፣ ጠፍር ታጥቆ፣ ጥሬ ቆርጥሞ ለመኖር የማለ፣ ስለ ጽድቅ ብሎ ራሱን ያስራበ ያሰጠማ መሆኑን ተረድተናል፡፡ (ማቴ.፭፥፮) ‹‹ምንኩስናሰ ጥበበ ሕግ መሲሓዊት›› እንዳሉ ፫፻፣ ምንኩስና በወንጌል የተገኘች መሲሐዊት ሕግ ናት፤ ቀድሞ አልነበረችም፡፡ መነኮሳት በግብራቸው፣ በንጽሕናቸው ሰማያውያን መላእክት ተሰኝተዋልና፡፡ ‹‹መነኮሳት በምድር ያሉ መላእክት በሰማይ ያሉ ሰዎች ናቸው›› ይላል ፍትሐ ነገሥት፡። (ፍት መን አን ፲፥፫፻፵፬) ክርስቶስን የተከተሉ፣ ሐዋርያትን የመሰሉ ናቸውና፡፡ የመጀመሪያው የምንኩስና ሥርዓት ከዘመድ፣ ከእናት አባት መለየት፣ ከሀገር መውጣት ነው፡፡ ምክንያቱም መነኩሴ ማለት ‹‹ምውት ዘተፈልጠ እምዓለም፤ ከዚህ ዓለም የተለየ ሙት›› ማለት ነውና፡፡ ሲሰድቡት የማይሳደብ፣ ሲመቱት የማይማታ፣ ልቡ ክፉ ነገር ቂም በቀል፣ ልብስ ጉርስ የማያስብ ማለት ነው፡፡ የሞተ ሰው ይህ ሁሉ የለበትምና፡፡ ‹‹ልብስ ጉርስ ቢያስብ ጥቂት የሚበቃው ይሁን፡፡ ሰብአ ዓለምን ስንኳ አታስቡ›› ብሏል፡፡ መነኩሴ የነፍሱን ነገር ትቶ እንዴት ልብስ ጉርስ እያለ ያስብ፤ ይህ ምንኩስና አይባልም ከንቱ ነው፡፡ (መጽሐፈ ምዕዳን) እንዳለ፡፡ ምንኩስና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘ ሲሆን ቆቡ የአክሊለ ሶክ፣ ቀሚሱ የከለሜዳ፣ ቅናቱ የሐብል፣ አስኬማው የሰውነቱ ምሳሌ ነው፡፡ (የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻ ዓ.ም) የምንኩስና ዓላማ ምንድን ነው? ምንኩስና የዘለዓለምን መንግሥት ለመውረስ ይቻል ዘንድ ፍጹም ሆኖ መገኘት ነው፡፡ መጽሐፍ እንደሚነግረን የምንኩስና ዓላማ ፍጹም መሆን ነው፡፡ አንድ ሰው “የዘለዓለምን ሕይወት እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ ጌታችን ኢየሱስ ክረስቶስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹ፍጹም ትሆን ዘንድ ትወዳለህን? ያለህን ሁሉ ሂደህ ሽጠህ ለነዳያንም መጽውተህ ና ተከተለኝ›› አለው፡፡ (ማቴ. ፲፱፥፳፩) ሰው ከእግዚአብሔር ይልቅ እናቱን አባቱን፣ ሚስቱን ልጁን ከወደደ እንዲሁም ሀብትና ንብረቱን ከመረጠ መነኩሴ እንደማይሆን ፍጹምም ሊሆን እንደማይችል፣ ፍጹም ሊሆን፣ የዘለዓለምን ሕይወት በምንኩስና ሊወርሳት የሚሻ ደግሞ ሁሉን ትቶ መከተልን፣ መመነንን፣ ከዘመድ አዝማድ መለየትን፣ ከሀገር መውጣትን፣ ራስን መለወጥን የሚፈልግ እንደሆነ ከጥቅሱ እንረዳለን፡፡ የቀደሙ አባቶቻችንም ይህን ሥርዓት አብነት አድርገው ከሀገር ርቀው፣ ከቤተ ሰብ ተደብቀው፣ ራሳቸውን ለውጠው፣ ከቤተ ዘመድ ከሚመጣ ፈተናና ከውዳሴ ከንቱም ተጠብቀው፣ በማይታወቁበት ቦታ በአት አጽንተው በመኖር ሕገ መነከሳትን የጠበቁ ለክብርም የበቁ ብዙዎች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ብቸኛው የሕይወት መንገድ ባይሆንም ምንኩስና ትልቁና ከምድራዊ ዓለም ለይቶ ከሰማያዊ ዓለም የሚቀላቅል፣ ከሰው ተራ አውጥቶ ከመላእክቱ ጋር የሚያዛምድ፣ ሥጋዊ ደማዊ ከሆነው ምድራዊ አስተሳብና አኗኗር ለይቶ ከማኅበረ መላእክት የሚደምር፣ ፍጽም ሆኖ ፍጹም የሚያደርግ አምላካዊ ሕግ መሆኑን ከፍትሐ ነገሥቱም ከወንጌሉም ከሕንፃ መነኮሳቱም የምንረዳው እውነት ነው፡፡ በጥቅሉ የምንኩስና ዓላማው ፍጹም ሆኖ ፍጹም የሆነውን አምላክ ተከትሎ ዘለዓለማዊ ርስቱን (መንግሥቱን) መውረስ መቻል ነው፡፡ ምንኩስና ትናንት፡- ምንኩስና ትናንት በነበረችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ክብሩ እንደ ፀሐይ የሞቀ፣ እንደ ጨረቃ የደመቀ፣ እንደ ከዋክብት የተንቆጠቆጠ ነበር፡፡ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ምድር እንኳን ተራውን ምእመኑን ነገሥታቱን፣ መኳንንቱን መሳፍንቱን፣ የነገሥታቱን እና የባለጸጋዎችን ልጆችና ሚስቶቻቸውን ሳይቀር መማረክ የቻለ፣ ዘውድ አስወልቆ አስኬማ ያስደፋ፣ ልብሰ መንገሥት አስወልቆ ቆዳ መልበስን፣ ሰሌን ማንጠፍን፣ ቅል አንጠልጥሎ፣ ጓዝን ጠቅሎ ገዳም በረሃ መውረድን ያስቻለ ታላቅ ቅቡልነትና ገዥነት የነበረው ሥርዓት እና አስተምህሮ ነበር፡፡ (ግንቦት ፳ ስንክሳር) እንደ ቀድሞዎቹ እንደነ ኤልያስ፣ እንደ ኋለኞቹ እንደነ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ንጽሕናዬን ጠብቄ፣ ከሴት ርቄ እኖራለሁ ብሎ ሰውነቱን ለእግዚአብሔር አደራ በሰጠው አባ እንጦንስ ላይ ያደረው ጸጋ ምንኩስና ያደረባቸው በርካታ መናንያን በኢትዮጵያ ገዳማት ነበሩ፤ አሁንም ጥቂቶች ይኖራሉ፡፡ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክረስቲያን የቅድስና፣ የንጽሕና፣ የመንፈሳዊነት ማሳያ ጥግ ነበር፡ ፡ዘንዶ የሚጫሙ፣ በባሕር ላይ የሚራመዱ፣ አንበሳ የሚጋልቡ፣ ራሳቸውን ከመግዛት አልፈው ተፈጥሮን የገዙ፣ ሃይማኖታቸው የጸና፣ ምግባራቸው የቀና፣ ተባርከው የሚባርኩ የሚያስባርኩ ተቀድሰው የሚቀድሱ የሚያስቀድሱ፣ ትምህርታቸው ሕይወት፣ ጸሎታቸው በረከት የሚያሰጥ፣ በአጽንኦ በአት በቀኖና ገዳማት የጸኑ፣ ሁሉ የሚያከብራቸው የሚያፍራቸው፣ በነገሥታት ሹመት፣ በባለጸጎች ምጽዋት የማይታለሉ፣ የሴት ፊት የአገልግል ፍትፍት የማያውቁ መነኮሳት ነበሩባት፡፡ ‹‹ይሔሶ ለመነኮስ በሊዐ ኅምዝ ዘይቀትል እምይብላ ምስለ ብእሲት እመኒ እኅቱ አው እሙ፤ከሴት ጋር ከመብላት ለመነኩሴ መርዝ ቢበላ ይሻለዋል፤ እኅቱም እናቱም ብትሆን›› እንዳለ አባ ብንያሚን የተባለ አባት(መ/ምዕዳን)፡፡ በእፍኝ ጥሬ፣ በጥርኝ ውኃ የሚኖሩ ግብረ መነኮሳትን፣ ሥርዓተ ገዳማትን ሳያፋልሱ በትጋት ዘመናቸውን የፈጸሙ ብዙ መነኮሳት የነበረባት ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ (ነበረች ስንል አሁን ምንም የለም ለማለት አይደለም መጠኑን ለመግለጽ እንጂ) ምንኩስና ትናንት ትልቅ የበረከት ምክንያት ነበር፡፡ መነኮሳት ትናንት የከተማ ሕይወት፣ የነገሥታት ፊት፣ የአደባባይ ሙግት አያውቁም ነበር፡፡ ለሁሉም ነገር ሰይፋቸው፣ ዘገራቸው ጸሎታቸው ነበር፡፡ የምንኩስና ኑሮ ፈጣሪን ማገልገል፣ ሕገ ምንኩስናን መጠበቅ፣ ከማናቸውም ዓለማዊ ኑሮ መከልከል መሆኑን በደንብ ያውቃሉ፡፡ ምንኩስናን በኢትዮጵያ ካስተዋወቁትና ከአስፋፉት ዘጠኙ ቅዱሳን ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትየጵያ ቤተ ክርስቲያን የክብረ ቤተ ክርስቲያን መታያ፣ የብዙኃን ምኞት የጥቂቶች ስኬትና ኑሮ፣ የክርስትናችን ዓምድ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ቅድስናቸው ከኢትዮጵያ አልፎ በሌሎች ዓለማት የታወቁ፣ ታላላቅ ገዳማትን መሥርተው፣ ደቀ መዛሙርት አፍርተው፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጽፈው፣ ደጉሰው፣ ሃይማኖት እንዲጸና፣ ምግባር እንዲቀና፣ ፍትሕ ርትዕ እንዲሰፍን፣ ፍቅረ እግዚአብሔር ፍቅረ ቢጽ ያስተማሩ፣ ቃላቸው ጦር ጸሎታቸው አጥር ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ በርካታ መነኮሳትን ቤተ ክርስቲያናችን አፍርታለች፡፡ በጥቅሉ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበሩ መነኮሳት የእግዚአብሔር መልአክ ለአባ ጳኩሚስ ያሳየው ዓይነት መነኮሳት ነበሩ፡፡የእግዚአብሔር መላክ ለአባ ጳጉሚስ አምስት መልካም የሆኑ ማኅበራተ መነኮሳትን አሳይቶት ነበር፡፡
Hammasini ko'rsatish...
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ›› ክፍል ስድስት ውድ የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች! እንደምን ሰነበታችሁ? በዚህ ርእስ ቤተ ክርስቲያን ትናንት ለነበራት ድምቀት፣ ዛሬ ለገጠማት ተግዳሮት፣ ነገም ለሚኖራት ማንነት ክብረ ክህነትና ክብረ ምንኩስና የማይተካ አስተዋጽኦ እንዳላቸው እና እነዚህ ሁለት የክብረ ቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ሊወስኑ እንደሚችሉ መንደርደሪያ ሐሳብ አንሥተን በመቀጠልም “ክብረ ክህነት ትናንት እንዴት ነበር? ዛሬስ ምን ሁኔታ ላይ ነው ? ነገስ ምን መሆን አለበት?” የሚሉ ጉዳዮችን ዳስሰን እስከ ክፍል አምስት አብረን ዘልቀናል፡፡ በክፍል ስድስትና ቀጣዮቹ ክፍሎች ደግሞ “ክብረ ምንኩስና ትናንት፣ ዛሬና ነገ ምን ይመስላልና መምሰል አለበት” የሚለውን እናጋራችኋለን፤ አብራችሁን ዝለቁ! መልካም ንባብ! ክብረ ምንኩስና፡- ምንኩስና ምንድን ነው? ‹‹መንኮሰ›› መለኮሰ፣ ተለየ፣ ሞተ፣ ከዓለም፣ ከሕዝብ ተለየ” ማለት እንደሆነ የግእዝ መዝገበ ቃላት ይናገራል፡፡ ‹‹መነኮስ›› ማለት ደግም “መነኩሴ፣ መናኝ፣ ድኻ፣ ከዓለም ከዘመድ የተለየ፣ ለዓለም የማይጨነቅ፣ ጥሬ ቆርጥሞ አዳሪ፣ ለራሱ ጥላ ለእግሩ ጫማ የሌለው” ማለት ሲሆን መናኝ ይህን ዓለም የመነነ፣ የናቀ፣ የተወ ማለትም ነው፡፡ ‹‹መነነ ዘንተ ዓለመ፤ ይህን ዓለም ተወ›› እንዲል፡፡ (ገጽ ፺፱) ‹‹ምንኩስና›› ማለት ደግሞ “ቆብ መድፋት፣ ከዚህ ዓለም መለየት፣ ሥጋዊ ስሜትን መግደል” ማለት ነው፡፡ (ሕያው ልሳን፣ መዝገበ ቃላት ገጽ ፺፰-፻፵፱)
Hammasini ko'rsatish...
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዙ። * ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣ቅዳሴ ቤቱን ለማክበርና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለመባረክ እንዲሁም ምዕመናንን ለማስተማር ዛሬ ማለዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዙ። ቅዱስነታቸው ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑካንን በመምራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና ከቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል። በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራው የልዑካን ቡድን ደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ኦሊቨር ታምቦ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚደርሱበት ጊዜ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የከምባታና ሀላባ፣ ሀዲያና ስልጤ ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ካህናትና ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ያሚያደርጉላቸው ይሆናል። ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Hammasini ko'rsatish...
ኀሙስ ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች (ሉቃ. ፳፬፥፳፭-፵፱)፡፡ ዐርብ የትንሣኤ እሑድ ስድስተኛዋ ዐርብ ደግሞ በክርስቶስ ደም ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቤተ ክርስቲያን› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ ሐዋ. ፳፥፳፰)፡፡ ቀዳሚት ሰንበት በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበያይባት ‹የቁራ ገበያ፣ የገበያ ጥፊያ› ተብላ ትጠራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጕልበታቸው ላገለገሉት፤ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት፤ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት፤ በትንሣኤውም ጌታችንን ከዅሉ ቀድሞ ለማየት ለበቁት ሴቶች መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቅዱሳት አንስት› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፭፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፫፥፳፯-፴፫፤ ፳፬፥፩-፲)፡፡ እሑድ ሰንበት በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤ ሰኞ የትንሣኤው ማግሥት ዕለተ ሰኞ ‹ፀአተ ሲኦል› ወይም ‹ማዕዶት› ትባላለች፡፡ ይህቺውም ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ናት (ዮሐ. ፲፱፥፲፰፤ ሮሜ. ፭፥፲-፲፯)፡፡ ማክሰኞ ይህቺ ዕለት፣ ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቶማስ› ተብላ ትጠራለች፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ በመጣ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት ‹‹ሳላይ አላምንም›› ብሎ ነበር፡፡ በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን በድጋሜ ለሐዋርያት ተገለጸ፡፡ ስለዚህም ይህቺ ዕለት በሐዋርያው ቶማስ ስም ተሰይማለች (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ረቡዕ ጌታችን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላስነሣው ለአልዓዛር መታሰቢያ ናት፡፡ በክርስቶስ ሥልጣን የአልዓዛርን ከሞት መነሣት አይተው ብዙ ሕዝብ በጌታችን ስለ አመኑ ዕለቲቱ (ረቡዕ) ‹አልዓዛር› ተብላ ትታሰባለች (ዮሐ. ፲፩፥፴፰-፵፮)፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ꔰ ꔰꔰእንኳን ለእመቤታችን 2031ኛ ዓመት በዓለ ልደት አደረሳችሁꔰ ꔰꔰ ꔰ  #ልደታ_ለማርያም  ꔰ ꔰ #ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል? ꔰ ሰላም ለልደትኪ እማኀፀነ ድክምት ሥጋ ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ ፠ #የግንቦት_ልደታ_ለማርያም_ክብረ_በዓልና_የእመቤታችን_በዓላት በቀደመዉ ዘመን በዘመነ ብሉይ ‹‹የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል›› ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ /ዮሐ. 10፥22/ በሐዲስ ኪዳን እውነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችዉ እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል፤ ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ. 111፥7በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠዉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 33ት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደዉ በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመዉ እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡ ፠ #ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል?       በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸዉ ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረዉ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ‹‹የንጉሡም የዳዊት የፊተኛዉና የኋለኛዉ ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል›› ይላል፡፡ 1ኛ ዜና 29፥29 ፠ #የእመቤታችን_የልደቷ_ታሪክ የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛዉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ‹‹ሐና››ና ኢያቄም/ዮአኪን በሚለዉ ስም የሚጠሩ ሲሆን ሐና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረዉን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሐና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ እርግብን አይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡ ስለ ሐና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደዉ መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብስራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸዉ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከዉና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረዉ ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡ ፠ #እመቤታችን_የት_ተወለደች? እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሐሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸዉ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸዉ የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሐሳቦች የሚያነሱ ሲሆን፤ አንደኛዉ ‹‹ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች›› የሚል ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ሐሳብ ደግሞ ‹‹ከሦስተኛዉ ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀዉ ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሐና የክሩሲድ ቤ/ክ በታች ነዉ የተወለደችዉ የሚል ነዉ፡፡ የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ በናዝሬት ነዉ ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸዉ ተጠብቀዉ የቆዩ ከመሆናቸዉ አንጻር ተአማኒነታቸዉ የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለዉ ተራራማ ሀገር ነዉ፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፊንቄ በስተምስራቅ ይገኛል፡፡ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ›› መኃ. 4፥7 የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምሥጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸዉ የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት ያስረዳሉ፡፡ ፠ #የልደታ_ለማርያም_በዓል_መቸ_ነዉ? እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነዉ፡፡ በ6ኛዉ ና7ኛዉ መቶ/ክ/ዘመን ነዉ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደዉና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነዉ ይላል፡፡ በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸዉን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸዉ የሚከበረዉም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅ/ ዮሐንስ፤ በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅ/ድንግል ማርያም ልደት ነዉ፡፡ በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባዉና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነዉ፡፡ የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ኬ.ክ በመጋገር፡ የአመቤታችን ትንሽ ሀዉልት በማቆም ዐስር ሻማዎችን በማብራት ያከብራሉ፡፡ #የድንግል_ማርያም_ልደት_ለምን_ይከበራል? * ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅ/ገብርኤል አንደበት‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› በማለት ተነግሯል (ሉቃ 1-14)፤ ምክንያቱም ቅ/ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ፥ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነዉ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ፤ የድንግል ማርያም ልደትማ ምንኛ የሚያስደስት ይሆን!?፡፡ስለሆነም ከጌታ ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነዉ፡፡ * የቀርጤሱ ቅ/እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነዉ፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ፡፡››ብሏል * እመቤታችን  ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፤ በቅድመ አያቶቿ በነ ቴክታና ጰጥሪቃ ሕልም እንደታየችዉ በሌሊት የምታበራ ጨረቃ፤ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰዉ ልጅ ሁሉ ደስታ ነዉ፡፡ * ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት ‹‹መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸዉ››፤ ‹‹ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል››፤ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ነይ››፤ …. ብለዉ የተናገሩላት ቅ/ድ/ማርያም ልደቷ የትንቢታቸዉ ፍፃሜ ነዉና ታላቅ ደስታቸዉ ደስታችንም ነዉ፡፡ (መዝ. 86፥1፣ ኢሳ. 11፥1፣ መኃ. 4፥7)ጂነአ * በዓለም ላይ የብዙ ታዋቂ ሰዎች ልደት ከሞቱም በኋላም ጭምር በታላቅ ድምቀት ይከበራል፤ ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ልደትም እንዲሁ ይታሰባል፡፡ ለሰዉ ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ግን ምንኛ ሊከበር ይገባዉ ይሆን! ፠ #የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር ሐናና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር  እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳውያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ ፣ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ፈንድሻ የሚጥሉ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣  እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡ @ፍኖተ ሕይወት ቀጨኔ መድኃኔ ዓለም
Hammasini ko'rsatish...
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸሎትና የንስሐ መርከብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ++++++++++++++++++++++++ - ቅዱስነታቸዉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሳኤ ስናስብ የእኛን ትንሳኤ እያሰብን ሊሆን ይገባል በማለት ገልፀዋል። - በዕምነት ትንሳኤ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሳኤ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመመላለስ መሆን አለበት ብለዋል። - ቅዱስነታቸዉ ከዚህ በማስቀጠል ከህገ እግዚአብሔር በመራቅ ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ዉጭ በሆነ ዝሙት ምክንያት በኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ የሚሞተዉ ሰዉ ሀገርንና ድንበርን ለመጠበቅ በየጦር ሜዳዉ ከሚያልቀዉ ሰዉ አይተናነስም በማለት ምዕመናን ከዚህ አፀያፊ ተግባት እንዲታቀቡ አባታዊ መልዕክትን አስተላልፈዉ በመላዉ ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን ለ2016 ዓመተ ምህረት የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የቅዱስነታቸዉ በረከት ይደርብን።
Hammasini ko'rsatish...
አለምን ለማዳን ዘማሪ ወንደሰን ክራር ኢዮሲያስ አበራ @krarnadmtsi
Hammasini ko'rsatish...