cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ማህበረ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ

ይህ #ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ማህበር ነው መዝሙር ጥናት የ መፅሀፍ ቅዱስ ጥናት እግዚአብሔርን አክብረው እሱም ላከበራቸው ቅዱሳን ቀናቸውን እና ዜና ገደላቸውን(1-30) የምናይበት የ ተቸገሩ እህት ወንድሞች መረዳት ነዲያንን ማልበስ ና ማብላት ቤተ-ክርስቲያን የሌላቸውን ቅዱስ ነገሮች ማሟላትና ማገዝ እግዚአብሔር በፈቀደው መጠን እንሠራለን

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
353
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kunlar
-930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ለዘመኑ መናፍቃን የሚጎረብጣቸው የቅዱስ ያዕቆብ ተግሳጽ ከሚከተለው አንዱነውAnonymous voting
  • በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው።
  • ለሰው ፊት ግን ብታደሉ ኃጢአትኖ ትሠራላችሁ።
  • እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል።
  • ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
0 votes
†††✝ እንኳን ለቅዱሳኑ ገብርኤል ሊቀ መላእክት: ቂርቆስ ወኢየሉጣ: በጥላን ጠቢብ እና ሰማዕታተ እስና ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝! ††† †††✝ ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ: ወቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††✝ ††† ቅድስት ኢየሉጣ እናታችን በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩና በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳት አንዷ ናት:: በወቅቱ ቅዱስ ቂርቆስ የሚባል ደግ ልጅ ወልዳ ባሏ ባለመኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር:: የዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር ከመነገር በላይ ነው:: በዛው ልክ ደግሞ መከራው በጸጉራቸው ቁጥር ልክ ነበር:: ከሮም ግዛት በአንዱ ከቅዱስ ልጇ ጋር የምትኖረው ቅድስት ኢየሉጣ የስደቱ ዘመን ሲመጣ እርሷም እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ተሰደደች:: እስክንድሮስ የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ግን ያለችበት ድረስ ተከትሎ እንድትያዝና እንድትቀርብ አደረገ:: ወዲያውም "ስምሽ ማን ይባላል?" ቢላት "ክርስቲያን እባላለሁ" አለችው:: ንጉሡ ተቆጣ:: "መዋቲ ስሜን ከፈለክ ኢየሉጣ ይባላል" አለችው:: ንጉሡ መልሶ "አሁን ለጣዖት ካልሠዋሽ ሲጀመር ስቃይ: ቀጥሎም ሞት ይጠብቅሻል" ቢላት ቅድስቲቱ መልሳ "በከተማ ውስጥ የሦስት ዓመት ሕፃን አለና እርሱን አምጣው:: ማንን ማምለክ እንዳለብን ይነግረናል" አለችው:: አስፈልጐ ቅዱስ ቂርቆስን አስመጣው:: "ስምህ ማን ይባላል?" አለ ንጉሡ:: "ከማይደፈርስ ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ ጥሩ ምንጭ ስሜ ክርስቲያን ይባላል:: መዋቲ ስሜን ከፈለግህ ግን ቂርቆስ ይባላል" አለው:: ንጉሡ ሊያታልለው "ደስ የተሰኘህ ሕፃን" ቢለው ቅዱሱ ሕፃን "ትክክል ተናገርክ: ለእኔ በሰማያት ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን እውነተኛው አምላክ ይፈርድብሃል" አለው:: በሦስት ዓመት ሕፃን አንደበት ዘለፋ የገጠመው ከሃዲ ተቆጣ:: እናትና ልጅን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃያቸው:: ሰውነታቸውን ቸነከረ: አካላቸውን ቆራረጠ: ዓይናቸውን አወጣ:: ሌላም ሊናገሩት የሚጨንቅ ስቃይን አሰቃያቸው:: በዚህች ቀን ግን ትልቅ ድስት አሰርቶ ባሩድ: አረር: ስብና የመሳሰሉትን ጨምረውበት በእሳት አፈሉት:: የእሳቱ ወላፈን አካባቢውን በላው:: በድስቱ ውስጥ ያለው ነገር እየፈላ ሲገላበጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ይጮህ ነበር:: የስድስት ሰዓት የእግር መንገድ ድረስም ተሰምቷል:: ቅድስት ኢየሉጣ ይሔኔ ነበር ልቧ ድንግጥ ያለው:: ሕፃኑ ቂርቆስ የእናቱን ፍርሃት ሲመለከት ጸለየ:: "ፈጣሪዬ! ፍሬው ያለ ግንዱ አይቆምምና እኔን እንዳጸናሕ እናቴንም አጽናት" ሲል ለመነ:: "እግዚኦ ትፈቅድኑ ለፍሬሁ ተአልዶ: እንዘ በእሳት ታውኢ ጉንዶ" እንዲል:: በዚያች ሰዓት ቅድስት ኢየሉጣ ዓይኖቿ ተከፍተው ሰማያዊ ክብርን ተመለከቱና ልቧ ወደ ድፍረቱ ተመለሰ:: ልጇንም "አንተ አባቴ ነህ: አንተን የተሸከመች ማኅጸኔ የተባረከች ናት" አለችው:: ከዚያም ሁለቱንም ወደ ፈላው ድስት ውስጥ ቢጨምሯቸው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደላቸው:: በበትረ መስቀሉ ባርኮ የፈላውን አቀዘቀዘው:: የነደደውን ውኃ አደረገው:: ቅዱሳኑ ቂርቆስና ኢየሉጣ ከብዙ መከራ በኋላ በሰማዕትነት አልፈዋል:: ††† ቅዱስ በጥላን ጠቢብ ††† ††† ቅዱሱ ከአሕዛብ ወላጆቹ ተወልዶ: ያደገውም በጣዖት አምልኮ ነው:: በሙያው እጅግ የተመሠከረለት ሐኪም ነበር:: የሃገሩ ሰዎች "ጠቢብ" እያሉም ይጠሩታል:: በጥላን ምንም ጣዖት አምላኪ ቢሆን በተፈጥሮው ተመራማሪና ቅን ነበር:: አንድ ካህንም በጐረቤቱ ነበርና ዘወትር ስለ ሃይማኖት ይከራከሩ ነበር:: ካህኑ ሌሊት ሌሊት ስለ በጥላን ተግቶ ይጸልይ ነበርና ተሳክቶለት አሳመነው:: አንድ ቀን በጥላን መንገድ ሲሔድ እባብ ሰው ነድፎ ለሞት ደርሶ አየውና ጸሎት አድርሶ ስመ ክርስቶስን ቢጠራ የተነደፈው ድኖ እባቡ ሞተ:: በዚህ ተዓምር ደስ ብሎት ወደ ካህኑ ሒዶ ተጠመቀ:: ከዚያም ጾም ጸሎትን ጀመረ:: በየቦታው እየዞረ ሕሙማንን እንደ ቀድሞው በመድኃኒት ሳይሆን በጸሎት ያድናቸው ነበር:: ስላዳናቸውም በርካቶቹ ወደ ክርስትና መጡ:: የአካባቢው ሰው: ወላጆቹን ጨምሮ ክርስቲያኖች ሆኑ:: በመጨረሻም ቅዱስ በጥላን: ቤተሰቦቹ: ካህኑና ከደዌ የዳኑት ወገኖቹ በአካባቢው ጣዖት አምላኪ ንጉሥ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ሰብከው በሰማዕትነት ዐርፈዋል:: ††† ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና ††† ††† እስና ማለት ግብጽ ውስጥ የምትገኝ የቀድሞ አውራጃ ናት:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በከተማዋ በርካታ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የእንዴናው መኮንን መጥቶ "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: ሕዝቡ በአንድ ድምጽ መለሱ:- "ይሕማ ፈጽሞ ሊደረግ አይችልም::" መኮንኑ ተቆጥቶ "ሁሉንም ግደሉ" አለ:: ወታደሮቹ ሰው አልመረጡም:: ከታዘለ ሕፃን አልጋ ላይ እስካለ ሽማግሌ: ከጤነኛ እስከ ሕመምተኛ: ሁሉንም ጨፈጨፏቸው:: ከተማዋ በደም ተነከረች:: ከከተማዋ ክርስቲያኖች ወሬ ለመንገር አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም:: ሁሉም ስለ ክርስትና ደማቸውን አፈሰሱ:: ††† ጌታችን ስለ ሰማዕታቱ ብሎ: ደማቸውንም አስቦ በሃይማኖታችን ያጽናን:: ከመከራም ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያድለን:: ††† ሐምሌ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ኢየሉጣ 3.ቅዱስ በጥላን ጠቢብ ሰማዕት እና ማኅበሩ 4.ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ 3.አቡነ ስነ ኢየሱስ 4.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም ††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ መራቆት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቆጠርን::' ተብሎ እንደተጻፈው ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" ††† (ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፯) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Hammasini ko'rsatish...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ✝️ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ✝️ሐምሌ ፲፪✝️ ❖ ✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ሚካኤል ሊቀ መላእክት" የተአምር በዓልና ለሰማዕቱ "አባ ሖር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" ተአምረ ቅዱስ ሚካኤል "*+ =>ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን በዚህች ዕለት የመላእክት ሁሉ አለቃቸው: የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም በሆነ ተአምር ከከተማው #ኢየሩሳሌም ጋር ታድጐታል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ከመድኃኒታችን #ክርስቶስ ልደት 700 ዓመታት በፊት #ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር:: ደጋጉ #ዳዊትና #ሰሎሞን ካረፉ በሁዋላ የሕዝቅያስን ያክል ቅን እና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ አልነገሰም:: ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጐም ነበር:: +ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት:: ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት:: +"እገብርልሃለሁ:: የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ:: ሃገሬን ግን አታጥፋ:: ኢየሩሳሌምን አታቃጥል:: ሕዝቤንም አትግደል" በሚል ለመነው:: እጅ መንሻ ግብሩንም ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት:: +ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ : ቅዱስ ስሙንም ተገዳደረ:: ለሕዝቅያስም "ከእኔ እጅ የሚያድንህ ማነው? ሕዝቡንም #እግዚአብሔር ያድናል ብለህ አታታልላቸው" ሲል ላከበት:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ:: +መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ #ቅዱስ_ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና በኢሳይያስ አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ #ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ::" +በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ:: በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል:: +በድንጋጤ ወደ #ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች (አድራማሌክና ሳራሳር) ገደሉት:: ትዕቢተኛው ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖ የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: (1ነገ. 18:13, 19:1) +*" ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት "*+ =>ዳግመኛ በዚህ ቀን #አባ_ሖር ሰማዕቱ ይታሠባል:: +ቅዱሱ:- ¤ስርያቆስ በምትባል የግብጽ አውራጃ ተወልዶ ያደገ: ¤ገና በልጅነቱ መንኖ እግዚአብሔርን ያገለገለ: ¤ዘመነ ሰማዕታት በመጣ ጊዜም በመኮንኑ ፊት ቀርቦ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመነ: ¤ከመኮንኑም ብዙ ስቃይ የደረሰበት: ¤ብዙ ተአምራትን በመስራቱ ያሰቃየው የነበረውን መኮንን ወደ ክርስትና መልሶ ለሰማዕትነት ያበቃ አባት ነው:: +እርሱም የሰማዕትነትን ክብር በእጅጉ ሽቷታልና ወደ ሌላ ሃገር ሒዶ በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል:: በሐዋርያዊ አገልግሎቱ ያሳመናቸው 127 ወንዶችና 20 ሴቶችም አብረውት ተሰይፈዋል:: =>እግዚአብሔር በሊቀ መላእክት ክንፍ ሃገራችንን ከአሕዛብ ስውር ጦር ይጠብቅልን:: ከሰማዕቱም በረከት ያሳትፈን:: =>ሐምሌ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ሕዝቅያስ ንጉሥ 2.ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል 3.ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት 4."147" ሰማዕታት (የአባ ሖር ማሕበር) =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ድሜጥሮስ 5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት) 7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ =>+"+ እግዚአብሔር ይላል:- ስለ እኔም ስለ ባሪያየም #ስለ_ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ:: በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ:: ከአሦራውያንም ሠፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ:: ማለዳም በተነሱ ጊዜ እነሆ ሁሉ በድኖች ነበሩ:: +"+ (1ነገ. 19:34) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Hammasini ko'rsatish...
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ስለ_ቤተክርስቲያን "አንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን ከኖኅ መርከብ ትበልጣለች ቢል አልተሳሳተም፡፡ የኖኅ መርከብ እንስሳትን ወደ ውስጥዋ ብታስገባም እንስሳት አድርጋ ጠበቀቻቸው እንጂ አልለወጠቻቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን እንስሳትን ትቀበላለች፤ ትለውጣቸውማለች፡፡ ለምሳሌ ወደ ኖኅ መርከብ ቁራ ገባ፤ የወጣውም ግን ቁራ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ገባ፤ የወጣውም ግን ያው ተኵላ ኾኖ ነው፡፡ እዚህ ቤተ ክርስቲያን ግን አንድ ሰው እንደ ቁራ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ ርግብ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ በግ ኾኖ ነው፡፡ እንደ እባብ ኾኖ ቢመጣ የሚወጣው እንደ ጠቦት በግ ኾኖ ነው፡፡ ተፈጥሮው ወደዚያ ስለሚለወጥ ግን አይደለም፤ ክፋቱ ስለሚርቅለት እንጂ፡፡ ስለ ንስሓ አብዝቼ የማስተምረውም ከዚህ የተነሣ ነው፡፡" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ንስሐና ምጽዋት) ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ "ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ ኃጢአትህንም አርቃት፡፡ በአደባባይ የምትወድቀው ቊጥሩ ከምትነሣው ጋር እኩል ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ በደል ኃጢአት የምትሠራውን ያህልም ፍጹም ተስፋ ሳትቈርጥ ንስሐ ግባ፡፡ ኹለተኛ ብትበድል ኹለተኛ ንስሐ ግባ፡፡ በስንፍና ተይዘህ በፍጹም ምግባር ትሩፋት መሥራት አይቻለኝም አትበል፡፡ በእርግና ዘመን ብትኾንና ብትበድልም እንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሆስፒታል እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡ እዚህ ስትመጣ ካህናት [“እግዚአብሔር ይፍታሕ” ብለው] ከኃጢአት እስራት ፈትተው ይቅርታ ይሰጡሃል እንጂ “ለምን በደልህ?” ብለው አይፈርዱብህምና፡፡ ስለዚህ፡- “አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ ኃጢአትህም ይቀርልሃል (መዝ.50፡4)፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Hammasini ko'rsatish...
"" ስንክሳር - ሐምሌ ፯/7 "" ሐምሌ 6-2015
Hammasini ko'rsatish...
✝እንኳን አደረሳችሁ!✝ ✝አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ማኅቶት፤ ዘባረክዎ ለአብርሃም በዊኦሙ በድርገት፤ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በላዔ መጻሕፍት ወሊቀ ሊቃውንት፤ አግናጥዮስ ሐዋርያ ሊቀ ጳጳሳት ወሰማዕት፤ አርሲመትሪዳ ሲኖዳ በዓለ ሥልጣት ብሑት፤ እህተ ጴጥሮስ ወእንድርያስ ዘአብርሁ በውስተ ጽልመት!
Hammasini ko'rsatish...
የእመብረሃን ወዳጅ አባ ጊዮርጊስ
Hammasini ko'rsatish...