uz
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Kanalga Telegram’da o‘tish

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Ko'proq ko'rsatish
4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር ••••• #የመጨረሻው_ክፍል •••• #የባልንጀራህን_ሚስት_ንብረት_አትመኝ አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ ፣በሐሰት አትመስክር በማለት ክፉ አድራጎትን ወይም የጥፋት ሥራዎችን የሐሰት ንግግሮችን ይከለክላል። #አትመኝ በማለቱ ደግሞ ክፉ ምኞትንና መጥፎ ሐሳብን ይከለክላል። በውጭ በተግባር የሚደረጉት ከውስጥ በልቡናችን ከሚፈፀሙት ጋር ማለት ከምኞትና ከሐሳብ ጋር እንደሚታየው እንደ ግንዱ የተያያዙ ናቸው። ሥሩ ደኀና ከሆነ ግንዱም ደኀና ይሆናል። አንድ ነገር በድርጊት ከመፈፀሙ በፊት ነገሩ የሚጠነሰሰውና የሚጀመረው በምኞትና በሐሳብ ውስጥ ውስጡን ነው። ክፉ ሰው ከልቡ ክፋ ነገርን ያወጣል ፤ ደግ ሰው ግን ከልቡ ደጋግ ነገሮችን ያወጣል። #መመኘት ማለት የሌላውን ሰው ሚስት /ባልና ሀብት ለራስ እንዲሆን መፈለግና ማሰብ ስለሆነ አንድ ነገርን የተመኘ ሰው ጊዜና ቦታ ባይገድበውና ሁኔታዎች ቢመቻቹለት በልቡ የፈለገውን በሐሳብ ያቀደውን፣ በስሜቱ የፈቀደውን ከማድረግ አይመለስም። ስለዚህ የኀጢአት ምንጩ የወንጀል አባቱ በልቡና የሚገኘው ክፉ #ምኞት ነው። ስለዚህ የሰውን ንብረት ከመመኘት መታቀብ አለብን። ይህንንም ለማጥፋት እና ኀሊናን ለማፅዳት መትጋት አለብን። የሕግ ሁሉ ፍፃሜና ማጠቃለያ #ፍቅር ነው። ሁሉም ትዕዛዞች በፍቅር ይጠቃለላሉ። ባልንጀራውንም አምላኩንም የሚወድ ህግን ይጠብቃል። ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞

#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር ••••• #ክፍል_9 ••••• #በሐሰት_አትመስክር ምስክርነት ምን ማለት ነው? በሐሰት መመስከርስ እንዴት ነው? #ምስክርነት ማለት በዳኛ ፊት ወይም በባለሥልጣን ፊት ወይም በአስታራቂ ሽማግሌዎች ወይም ስለ ሥነ ስርዓት ጉዳይ በተሰየመ ጉባኤ ፊት የቀረበውን ሙግትና ክርክር በትክክል ለመፍረድና ለመወሰን የሚረዳ የቃል ማረጋገጫና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያመለክት ነው ። በእውነት የሚቀርበው ምስክርነት በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ያስመሰግናል። ነገር ግን ሰዎች በልዩ ልዩ ጥቅም ተገዝተው ወይም ባልንጀራን አለአግባብ ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲባል እውነቱን ነገር በመሸሸግ ሐሰት ነገር በመፍጠር ያልተነገረውን ተነገረ ያልተደረገውን ተደረገ በማለት በመሐላም ሆነ ያለ መሐላ የሚቀርበው የውሸት ማስረጃ ሁሉ የሐሰት ምስክርነት ይባላል። በኀብረተሰቡ ውስጥ እውነትና ሐቅ ጠፍቶ ፍርድ ጎድሎ ድሀ ተበድሎ ሰዎች ሁሉ ጊዜያቸውንና ኃይላቸውን ገንዘባቸውንም በክርክርና በጠብ እንዳያጠፋና ሰላማቸውን እንዳያጡ በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ በማሰብ እግዚአብሔር "በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር" የሚለውን ትእዛዝ እንድንጠብቀው ሰጥቶናል። ይህን ትዕዛዝ መተላለፍ ትልቅ በደል ነው። #በመጀመሪያ መስካሪው እውነት እመሰክራለው ብሎ የገባውን ቃል ኪዳን ወይም መሐላ አፍርሶ ውሸት በመናገሩ፣ #2ኛ ዳኛውን በማሳሳት የሐሰት ፍርድ በማስፈረዱ፣ #3ኛ የተፈረደበትን ሰው ሳያጠፋ በማስቀጣቱ በደሉ ብዙ ነው። ይህ ትዕዛዝ ቀጥታ ምስክሮችን ብቻ የሚመለከት አይደለም። ልዩ ልዩ የሐሰት መረጃዎችን በማዘጋጀት ሰነዶችንና መዝገቦችን በማጭበርበርና በማዘዋወር አስመስሎ በመፈረምና በተሰረቁ ማኀተሞች በመጠቀም እንደዚሁም ሌሎች ይኽን የመሰሉ በተንኮል የተቀናበሩትን ሁኔታዎች በማመቻቸት የሚያስፈርዱትንና የሚፈርዱትንም ሁሉ ይመለከታል። ስለዚህ ምስክርነታችን ሁሉ #በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ። •••••••✞ #ይቀጥላል ✞•••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር •••••• #ክፍል_8 ••••• #አትስረቅ፦ መስረቅ ማለት የሌላውን ገንዘብና ንብረት መውሰድ ሲሆን አወሳሰዱም ባለቤቱ ሳያውቅ ወይም በማታለል ወይም በኀይል ይፈፀማል። #ጉቦኝነትም ሰዎች በሥልጣናቸው አማካኝነት የሌላውን ገንዘብ የሚወስዱበት ወይም ጥቅም የሚያገኙበት መንገድ እስከሆነ ድረስ ስውር ስርቆት ነው ማለት ይቻላል። አባይ ሚዛንም ስርቆት ነው። "ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው ፡ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም " ተብሎ ተፅፏል። (ምሳ 20:23) የሰውን ገንዘብ ከመውሰድ የከፋ ነገር ቢኖር የቤተክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት መስረቅ ነው። ምክንያቱም ይህንን ያደረገው ሰው ከስርቆት ወንጀል ሌላ የእግዚአብሔርን ስም አቃሏል፤ ሃይማኖቱንም ክዷል ማለት ይቻላል። ስለዚህ አድራጎቱ የበደል በደል ነው። እንደዚህ አይነት ሰው ባልንጀራውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው የበደለው። ሌሎችም እንደስርቆት የሚቆጠሩ ነገሮች አሉ። በምቀኝነትም ይሁን በተንኮል ወይም በግፍ የሰውን ገንዘብና ንብረት ማስቀረት ወይም መቀነስ ወይም ማቆየት ነው። የሰራተኞችን ደመወዝ ማስቀረት ወይም አለአግባብ ደመወዛቸውን መቁረጥ አሰሪዎችን በደለኞች ያደርጋቸዋል። ቅዱስ ያዕቆብ "እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮሀል፡፡ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባኦት ጆሮ ገብቷል ። " (ያዕ5:4) ሌላው የአደራ ገንዘብን መብላትና የተዋሱትን የተበደሩትን ገንዘብ አለመመለስም እንደ ስርቆት ይቆጠራል። የተሳሉትን ስዕለት፣ የገቡትን ብፅዓት አለመፈፀም እግዚአብሔርን መበደል ነው። ልንፈፅመው የማንችለውን ነገር ቃል አለመግባት ይሻላል። አስራት በኩራትን ማስቀረት እግዚአብሔርን መስረቅ ነው። ሰዎች ሁሉ እንኳን የሌላውን ገንዘብ መስረቅ ቀርቶ የራሳቸውንም እንዲያካፍሉ ታዘዋል። ስለዚህ የቀማን መልሰን የበደልን ክሰን ያለንን አካፍልን ከስርቆት ተቆጥበን ልንኖር ይገባል። •••••••✞ #ይቀጥላል ✞•••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር ••••• #ክፍል_7 •••• #አታመንዝር አቅመ አዳምና አቅመ ሔዋን የደረሱት ወንድና ሴት ከጋብቻ በፊትም ሆነ በኀላ ሕግ ከሚፈቅድላቸው የጋብቻ ግንኙነት ውጭ የሚፈፅሙት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሁሉ #አመንዝራነት ወይም #ዝሙት ይባላል። ይህም አድራጎት በ7ኛው ትዕዛዝ የተከለከለ ነው። አመንዝራነት በገነነበት ሀገር ሕጋዊ ጋብቻ ይናቃል። #ጋብቻ ከሌለ ጤናማ ቤተሰብ አይኖርም። ጤናማ ቤተሰብ ከሌለ ደግሞ ጠንካራ ኀብረተሰብና ጥሩ ዜጎችን ማግኘት አይቻልም። እንዲያውም ከሐዲና ዘማዊ ትውልድ ይፈጠራል። ይህም የሀገርን ውድቀት ያስከትላል። የእግዚአብሔርን እርግማን ያመጣል። ስለዚህ በልዩ ልዩ በደልና ክፋት የተያዙትን በተለይም በዓመፅ ስራና በዝሙት ኀጢአት ብዛት ከገፀ ምድር የጠፋትን የኖኀ ዘመን ሰዎችን (ሰብአ ትካትን ) በአብርሃም ዘመን የነበሩትን ሰዶምና ገሞራን እያሰብን ከዝሙት ራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል። ቤተክርስቲያን በዝሙት እንዳንወድቅ የምትሰጠው መፍትሄ አለ። ይኸውም፦ ራሳችንን በከፍተኛ ደረጃ በመቆጣጠር፣ በተዓቅቦ መኖር፡ አንድ ወንድ በአንዲት ሴት፡ አንዲት ሴት በአንድ ወንድ መፅናት እንዲሁም መንፈሳዊ ተጋድሎ ማድረግ ነው። የዝሙት የርኩሰት ሥራ ሁሉ እንስሳዊ ባህርያችንን ስለሚያጎላም በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረችውን ነፍሳችንን በጣም ይጎዳታል። የዝሙት ኀጢአት በድርጊት ብቻ የሚፈፀም ሳይሆን (በሀልዩ) በሐሳብ፣ በምኞት ጭምር የሚፈፀም ነው። ጌታችን በወንጌል "አታመንዝር እንደተባለ ሰምታቹሀል። እኔ ግን እላቹሀለሁ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሯል። /ማቴ5:27/ እንግዲህ ይህ ድርጊት አልባ የሆነው የዝሙት ምኞትና ሐሳብ ቆይቶ ወደ ድርጊት ስለሚያመራ በቅድሚያ እሱን መቆጣጠር የመጀመሪያው ሥራችን መሆን ይገባዋል። የዝሙትና የሐጢአት ሁሉ መነሻቸውና ምንጫቸው ምኞት መሆኑን ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ነግሮናል። "እየያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። ከዚህ ቡሃላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ፣ ኃጢአትም ካደገች ቡሃላ ሞትን ትወልዳለች " (ያዕ1:14) በርግጥ በአሁን ሰአት ወጣቶችን የሚያማልል የዝሙትን ነገር የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ፊልሞች ይታያሉ። እንደዚህ ዓይነቱ የዝሙት ሐሳብን የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ሥዕሎች፣ ልብ ወለድ ድርሰቶችና የመሳሰሉት በየሱቁና በየቦታው ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝነው በመገናኛ ብዙሀንም ይኽን የመሰለ ነገር በየጊዜው በመታየቱ ነው። ጤናማውን የሞራል የቤተሰብንና የማኀበራዊ ኑሮን የሚመርዙት ፊልሞችና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች ቀርተው በምትኩ የትምህርትና የሥራ ጉዳዮች፣ የልማትና የምርት ስራዎች፣ የጤናና የማህበራዊ ኑሮን የመሳሰሉት ፕሮግራሞች ሰፋ ያለ ጊዜ ተሰጥቷቸው በመገናኛ ብዙሀን ቢታዩና ቢሰሙ ለሀገርና ለወገን ይጠቅማል። መዝናኛም ከተፈለገ የሀገሩን ባሕል፣ የሕዝቡን ሃይማኖትና ሞራል በመጠበቅ በወጉና በአግባቡ ሊደረግ ይችላል። ራስን በመግዛት በንፅህና በመመላለስ ከዝሙት መራቅ ይገባናል። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር •••• #ክፍል_6 •••• #አትግደል ሕይወት በአጋጣሚ ፣ በልማድና በእንዝሕላልነት የምትገኝ አይደለችም። ሕይወት ለራሱ ምክንያትና አስገኝ ከሌለው እግዚአብሔር የተገኘች ገንዘብ ነች። ሕይወትን ማንም ሊያዝባት እንደፈለገው ሊያደርጋት አይችልም። ለምን ? የእርሱ አይደለችምና ለዚህ ነው #አትግደል የተባለው። #መግደል ማለት በተለያዩ መንገዶች ተጠቅሞ የሰው ሕይወት እንዲሞት ማድረግ ነው። #መግደል ከውስጥ ከሰው የሚወጡ ሰውንም የሚያረክሱ ብሎ ጌታችን ከዘረዘራቸው ክፋ ሥራዎች አንዱ ነው ። ማቴ 15:19 ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ ላይ ከዘረዘራቸው 16 የስጋ ስራዎች አንዱ መግደል ነው። #በሕይወት ላይ ስልጣን ያለው #እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰውን ቢያድንም ቢገድልም ስልጣኑ የእርሱ ብቻ ነው። #መግደል ሲባል ፊት ለፊት ሄዶ የሰውን ሕይወት ማጥፋት ብቻ ሳይሆን ሰውን ለሞት የሚያበቁትን ነገሮች ሁሉ ነው ። ይኸውም #ሀ በተለያዩ ሁኔታ (በቃላትና በመጠቆም) አጥፊውን መርዳት #ለ የሰው ሕይወት ሊድን የሚችልበትን መረጃ በመከልከል #ሐ በሽታና ድካምን ሌላም ችግርን እያዩ ለሞት የሚያደርስ ስራ ማሰራት #መ ለሞት የሚያደርስ ረሀብና ጥም አይተን አለመርዳት #ሠ ሰውን በስጋ ብቻ ሳይሆን በነፍሱ መከራ የሚያመጣበትን መንገድ መፍጠር መግደል ነው። #ረ ዓለማውያንን በመንፈስ ባዶ ቀፎ ሆነው የተበላሹትን ወደ እናት ቤተክርስቲያን አለማምጣት ነፍስን መግደል ነው። ወደ መግደል የሚያደርሱ ብዙ ነገሮች አሉ እነሱም ቅንዓት፣ ምቀኝነት፣ ስድብ፣ ጥላቻ፣ ቁጣ ጥቂቶቹ ናቸው። እራሳችንን በመግዛት እና ወንድማችንን በመውደድ ከዚ ድርጊት ልንቆጠብ ይገባናል። መሞት እንደማንፈልገው ሁሉ የሰው ነፍስ ማጥፋት የለብንም። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር ••••• #ክፍል_5 ••••• #አባትህንና_እናትህን_አክብር ይህ ትዕዛዝ የፍቅረ ቢፅ መጀመሪያ ነው። አባትና እናት ሲል የወለዱንን ብቻ ሳይሆን በአርአያ #ሥላሴ የተፈጠረ ሁሉ እንድናከብር ነው። እነዚህም የሥጋ አባቶችና የመንፈስ አባት በማለት ለሁለት ይከፈላሉ። #የስጋ አባት የምንላቸው፦ ወላጆቻችን፣ የቀለም አባቶች፣ የሀገር መሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ የጡት አባት፣ የእንጀራ አባት ... #የመንፈስ_አባትና_እናት፦ የንስሀ አባት ፣ ካህናት ፣ ሰባኪ ወንጌሎች፣ የክርስትና እናትና አባት፣ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ናቸው። #አክብር ማለት መውደድ፣ መታዘዝ፣ መርዳት፣ አለማቃለል ማለት ነው። በሁሉ ለወላጆቻችሁ ሲል በሁሉ የሚለው ቃል ብዙ ነገሮችን ያመለክታል። ይኸውም #ሀ ምክራቸውን በመስማት #ለ በተቸገሩ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን በመስጠት #ሐ በሌላቸው ጊዜ የሚረዱበትን መንገድ ማዘጋጀት #መ በጠቅላላው ለወላጆች ብድራትን መመለስ። ወላጆቻችንም ሆኑ ሌሎችን የሥጋና የመንፈስ አባቶችን ሲኖራቸውም ፣ሲያጡም፣ ጤና ቢሆኑ፣ ቢታመሙም ፣ባረጁ ጊዜ ልንረዳቸውና ልናከብራቸው ይገባል። ይሁንና ወላጆችም ሆኑ ሌሎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣላና የሚያጋጭ ትዕዛዝ ቢያዙን ግን እንቢ ልንላቸው ይገባል። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር •••• #ክፍል_4 •••• #የሰንበትን_ቀን_ትቀድሰው_ዘንድ_አስብ ፦ የቃሉ ትርጉም አቆመ አረፈ ማለት ነው። ይህ ማለት የሰው ልጅ ከጌታ ጋር የሚቀራረብበት መገናኛ መንገድ ነው። ከማንኛውም ስጋዊ ተግባር የምናርፍበት ፣ ትርጓሜው የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናስታውስ የሚያደርግበት ቀን ነው። #ሰንበት የመንግስተ ሰማይ ምሳሌ ነች። የሰው ልጅ በዓለም ሠርቶ ወርዶ በመልካም ሥራው የሚያርፍበት ቦታ ናት። ሰው ዕረፍት ያስፈልገዋል የሰንበት ቀን የተፈጠረውም ለዚህ ነው። የሰንበት ቀን የዕረፍት ቀን ስለሆነ የሚከተሉትን ሁለት ነገሮች ያሳስበናል። #1ኛ ሰው በኀጢአት ከመውደቁ በፊት ከአምላኩ ጋር ያለውን ግንኙነት የነበረውን ዕረፍት #2ኛ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን ዘላለማዊ የነፍስ እረፍት። በሐዲስ ኪዳን ሰንበት ሁለት ናቸው #ቅዳሜና_እሁድ። #ቅዳሜ ማለት የበፊቷ የቀደመችው ማለት ነው። #እሑድ ማለት ደግሞ መጀመሪያ ስለሆነ ከዚህ ጀምረን ስንቆጥር ቅዳሜ ሰባተኛ ቀን ይሆናል። በ3ኛው ትዕዛዝ እንዲከበር የታዘዘው ይህ ቀን ነው። ፈሪሳውያን በሰንበት ቀን እግር ከዘረጉ አያጥፋም ፣ ከአጠፋም አይዘረጉም መልካምም ሥራ ቢሆን አይሰሩም። #እሑድ ሥነፍጥረት የጀመረበት ፣ ኀላም ጌታ የተነሳበት፣ መንፈስቅዱስ የወረደበት እንዲሁም ጌታ የሚመጣበት ዕለት ነው። ስለዚህ እናከብረዋለን። በቤተክርስቲያን ታሪክ ደግሞ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ቀን ስለሆነች ሥራ እንዳይሰራ በሕገመንግስቱ አፅድቆ እንዳወጀና እንደወሰነ ይነገራል። ስለዚህ ሰንበት የእረፍት ቀን ነው ስለተባለ ሥራ ፈተን መዋል የለብንም። በእግዚአብሔር ቤት በመገኘት ማስቀደስ ፣ ቃሉን መማር ፣ መዘመርና ማመስገን አለብን። ከዚህም ሌላ ጌታ በሰንበት መልካም ሥራ ማድረግ ተፈቅዷል ስላለ የታመመና የታሰረ መጠየቅ ፣ የተጣላ ማስታረቅ ፣ ያዘነ ማፅናናት ፣ ለተቸገረ ደግሞ ምፅዋት መመፅወት አለብን። እንግዲህ በክርስትና ሰንበት የሚከበረው እንዲህ ነው። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር ••• #ክፍል_3 ••• #የእግዚአብሔር_የአምላክህን_ስም_በከንቱ_አትጥራ ስም ሲባል አንድ ነገር ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት መጠሪያ ነው። ስም ጠባይን ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ ሆኖ ሊሰየም ይችላል። እግዚአብሔርም ባሕርዩን ሕልውናውን ግብሩን የገለፁ ብዙ ስም አለው። በሐዲስ ኪዳንም እግዚአብሔር ወልድ በስጋ ሲገለጥ #አማኑኤል #ኢየሱስ #ክርስቶስ በሚባሉ ስሞች ተጠርቷል። የእግዚአብሔር ስም ባዶ ቃል አይደለም። ኃይሉን ግርማውን ይዞ ይገኛል። የማይታየው እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በስሙ አማካኝነት ነው። በተለይም ክርስቶስ በስጋ በተገለጠ ጊዜ ስሙን ለዓለም አስታውቋል። /ዮሐ 17:26/ ስሙም ከሁሉ በላይ ነው። /ፊል 2:9/ ስሙ #ቅዱስ ነውና አክብረን ልንይዘውና ልንቀድሰው ይገባል እንጂ በከንቱ ልንጠራው አይገባም። መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሚያመሰግኑት አምላክ መሆኑን አውቀን ስሙን በከንቱ መጥራት ግብሩን ማርከስ ነው። በማህበር ስንኖር ከሳሽ ተከሳሽ ስለሚኖር የክርክሩ መፈፀሚያ የእውነት ማረጋገጫ መሐላ ስለሆነ ዳኛው እንዲምል ካስገደደው መማል ይፈቀዳል። /ዘፀ 22:11 ዕብ 6:13/ ከዚህ ሌላ ቃል ለመግባት አንድ ነገርን ለመስራት መሐላ መማል ቃል መስጠት የእግዚአብሔር ስም መጥራት የሚያስፈልግባቸው ጊዜ አለ። እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማገልገል ሲሉ ብፅዓት የሚያደርግ አለ ይኸውም በቤተክርስቲያን ስርዓት የተፈቀደ ነው። ለምሳሌ በድንግልና ለመኖር ። #በከንቱ_አትጥራ ከንቱ ማለት በእግዚአብሔር የተናቀ የማይገባ ነገር ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ስም በእንዲህ አይነት ሁኔታ መጥራት እንደማይገባ ይህ ትዕዛዝ ያስተምረናል። እነሱም፦ 1.ስጋዊ ፍቃድ 2.ጣኦትን ማምለክ 3.ሐሰተኛ ትንቢት 4.በእግዚአብሔር ስም መማል 5.በእግዚአብሔር ስም መራገም 6.በእግዚአብሔር ስም መጠንቆል ... በነዚህ ሁሉ ስሙን መጥራት በከንቱ መጥራት ነውና በማስተዋል ልንጠብቀው ይገባል። #የእግዚአብሔርን_ስም_የምንጠቀመው_ምን_ጊዜ_ነው ? 1.በፀሎት ጊዜ 2.በሰላምታ ጊዜ 3.በአምልኮ ጊዜ 4.በቡራኬ ጊዜ ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር ••• #ክፍል_2 ••• #አታምልክ ማምለክ ሲባል እምነትን ተስፋን ፍቅርን በአምላክ ላይ መጣል ነው። አንድ ሰው እምነቱን ተስፋውን ፍቅሩን ከእግዚአብሔር ላይ አንስቶ በሌሎች አማልክት ላይ ሲጥል ነው ሌላ አምላክ አመለከ የሚባለው። #አምልኮት በተግባር የሚውለው በሚከተሉት ነገሮች ነው። #1በስግደት #2ጸሎት #3መስዋዕት #4ውዳሴ #5መገዛት #6ፍርሃት ወዘተ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ ነገር ብንሰጣቸው ሌላ አመለክን ማለት ነው። ይህን ህግ የሚያፈርሱ ሰዎች ብዙ ዓይነት በደል ይበድላሉ። ይኸውም #1የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የተባለውን ትዕዛዝ ይለውጣሉ። #2ከቤተክርስቲያን አንድነት ውጭ ይሆናሉ #3ተስፋ ቢስ ሁሉ የጨለመባቸው ሆነው ይገኛሉ። #ሌሎች_አማልክት_የተባሉት፦ ሰው እንደ እግዚአብሔር የሚያያቸውና ብቸኛውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ የሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ አምላክ ሊሆኑበት ይችላሉ። እነሱም፦ #1 ገንዘብ ማቴ 6:24 #2የሰው ሃይል ኤር 17:5 #3የሰው ጥበብ እውቀት ኤር 9:23 #4ሆድ ራስ ወዳድነት #5 የምንታመንባቸው ሰዎች (ባለ ሃብት ባለ ስልጣን ) #6አባትና እናት #7ተድላ ደስታ #8የተቀረፀ ምስል ዘፀ 20:4 አምልኮ ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም አይሰጥም። አክብሮትና የጸጋ ስግደት ግን ለቅዱሳን መላዕክት እና ለቅዱሳን ሁሉ ልናደርግ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳንን #አማልክት ይላቸዋል። ለምሳሌ ሙሴን ለፈርኦን አምላክ አድርጌሃለው በማለት እግዚአብሔር ነግሮታል። በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳንን እናከብራለን ይህ ከትዕዛዙ ወይም ከህጉ ጋር አይጋጭም የእግዚአብሔርን አምልኮትና አክብሮት ለቅዱሳን አንሰጥምና። እንዲያውም ለእነርሱ የምንሰጠው ክብር እግዚአብሔርን ማክበር ስለሆነ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር እናቀርባለን። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር ••• #ክፍል_1 ••• #10ቱ_ትዕዛዛት (ኦሪ ዘፀ 20) #1.እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ ነኝ ከኔ በቀር ሌሎቹ አማልክት አይሁኑልህ፡፡ #2.የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አታንሳ፡፡ #3.የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡ #4.እናትና አባትህን አክብር #5.አትግደል #6.አታመንዝር #7.አትስረቅ #8.በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር #9.የባልንጀራህን ቤት አትመኝ #10.ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ። የክርስትና ህግ የፍቅር ህግ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈፅሞታል ካለ ቡሃላ ከ10ቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ #ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ መሆኑን በግልፅ ይናገራል። /ሮሜ 13:8/ ጌታችን እንዳስተማረን ፍቅር #በ2 ይከፈላል። #1ኛ_ፍቅረ_እግዚአብሔር #2ኛ_ፍቅረ_ቢፅ። በሌላ በኩል ደግሞ ከአዎንታዊና አሉታ ከመነገራቸው አንፃር #በ2 ይከፈላሉ። #1ኛ_ሕግ_በአሉታ_የተነገሩ /አታድርግ/ #2ኛ_ትዕዛዝ_በአዎንታ_የተነገሩ /አድርግ/ ይባላሉ። ከዚህም ሌላ ከአፈፃፀማቸው አንፃር ሲታዩ #በ3 ይከፈላሉ። #1ኛ_በሐልዩ /በማሰብ/ የሚፈፀሙ ህግ1,3,4 እና 9 #2ኛ_በነቢብ /በመናገር/ የሚፈፀሙ ህግ 2,8 #3ኛ_በገቢር /በማድረግ/ ህግ 5,6,7,10 ናቸው። #10ቱ ትዕዛዛት ለሙሴ በተሰጡ ጊዜ በሁለት የድንጋይ ፅላቶች ላይ ተፅፈው ነበር። እንዲሁም ሁሉ በተለይም እስራኤል ዘነፍስ የምንባለው ለእኛ ለክርስቲያኖች ከልባችን ፅላት ላይ በመንፈስ ልንፅፈው ይገባል። በቤተክርስቲያናችን በፅላቶቻችን ላይ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይገኛል። ጌታችን ደግሞ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለው ካለ ቡሃላ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ብሎ አስተምሯል። እንዲህ ከሆነ የሚያስፈልገንን ነገር ለመለመን የጌታችን ስሙ ስለተፃፈበት በዙሪያው ተሰብስበን መለመን ያስፈልጋል። ህጉ ከልባችን ስለማይጠፋ ሕጉን መጠበቅና መፈፀም ይገባናል። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_የሥነ_ምግባር_ትምህርት #መግቢያ "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያመሰግኑት ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ " ማቴ 5:16 ክርስቲያን የክርስቶስ ወገን ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ማለት የክርስቶስ ወገን የሆነ ሁሉ ሊሰራው የሚገባ ያማረ ትክክለኛነትና አርአያነት ያለው ስራ ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ስነምግባር መገለጫው የተለያየ መልክ ሲኖረው ከስፋቱና ከአይነቱ አንፃር በ2 ከፍለን እንመልከተው ። እነሱም ግላዊ ስነምግባር እና ማህበራዊ ስነምግባር ናቸው ። #1ኛ_ግላዊ_ሥነ_ምግባር ፦ መንፈሳዊ ሰው በመጽሐፍትና በመምህራን የተላለፋለትን አምላካዊ ቃል በህሊናው ጽፎ በልቦናው ቀርፆ ከሰውነቱ ጋር አዋህዶ ሁልጊዜም ደግና መልካም የሆነውን ነገር እየፈፀመ ክፉ ከሆነው ነገር ደግሞ ተቆጥቦ እና ሸሽቶ በእለት ተእለት ህይወቱ የሚከተለው ( የሚተገብረው ) የሥነ ምግባር አይነት ነው። ግላዊ ሥነምግባር ገላጭ ባህርያት ከሆኑት በጥቂቱ፦ ➊ በትህትና እና እራስን ዝቅ በማድረግ መኖር ➋ ቃሉን በመጠበቅ በትክክለኛው መንገድ በመራመድ ➌ እግዚአብሔርን ከመበደል በመጠበቅ ➍ ራስን መግዛት ➎ ፈቃደ ሥጋን ለፍቃደ ነፍስ ማስገዛት እና ወዘተ... #2ኛ_ማህበራዊ_ሥነ_ምግባር፦ አንድ ክርስቲያን በዕለት ተዕለት ሥራውና በማህበራዊ ኑሮ ግንኙነቱ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ሲኖር መተሳሰብን ፍቅርን አንድነትን የሚገልጥበት ፣ ሰዎችን አለአግባብ መቃወምን ግለሰቦችን መናቅን ቁጣን እና ራስ ወዳድነትን የሚያስወግድበት በአጠቃላይ ከሰዎች ጋር ተስማምቶ እና ተፋቅሮ የሚኖርበት የሥነ ምግባር አይነት ነው ። ከመገለጫዎቹ በጥቂቱ፦ ➊ተግሳፅን መቀበል ➋ሌሎች ሰዎች ከእኔ የተሻሉ ናቸው ብሎ ማሰብ ➌ሰብአዊ ርህራሄ ➍ከግል ጥቅም ይልቅ ማህበራዊ ጥቅምን ማስቀደም ➎ይቅር ማለት እና ወዘተ... በአጠቃላይ ለክርስቲያናዊ ስነምግባር መሠረቱ ሕገ-እግዚአብሔር ቃለ-እግዚአብሔር ሲሆን ህጉን ለመጠበቅ እና እንደ ቃሉ ለመኖር ትልቁ ኃይል ፈሪሃ-እግዚአብሔር ነው ። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

🌾✞ #መዝሙረ_ዳዊት_ዘቀዳሚት ✞🌾 ☑️✞ ሁለተኛው ንጉስ {፻፵፩-፻፶} ☑️✞ #ቃልዬ_ኀበ_እግዚአብሔር 📖መምህር ሥነፀሐይ ቦጋለ ምሥራቀ ፀሐይ አዲሱ ቅዱስ ሚካኤል #ባሕርዳር ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 t.me/Geez_Abinet ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

መዝሙር ፻፵፱ (149) @EOTC2921.aac1.73 MB

መዝሙር ፻፵፰ (148) @EOTC2921.aac1.62 MB

መዝሙር ፻፵፯ (147) @EOTC2921.aac1.32 MB

መዝሙር ፻፵፮ (146) @EOTC2921.aac1.52 MB

መዝሙር ፻፵፭ (145) @EOTC2921.aac1.42 MB

መዝሙር ፻፵፬ (144) @EOTC2921.aac2.51 MB

መዝሙር ፻፵፫ (143) @EOTC2921.aac3.32 MB