የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Kanalga Telegram’da o‘tish
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Ko'proq ko'rsatish4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
4 374
🌿🌿#በእፀ_መስቀል_ላይ#🌿🌿
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
💟💟💟💟💟💟💟💟💟💟
በእጸ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ /፪/
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ
#አዝ
መስቀል አስይዘው ኪራያላይሶን
ወደ ጎልጎታ >>
ሲገራፉ ሲዳፉ >>
ስትንገላታ >>
#አዝ
ያንን አቀበት ኪርያላይሶን
ያንን ዳገት >>
ጀርባህ ተገርፎ >>
ስትቃትት >>
#አዝ
አንተን እያዩ ኪርያላይሶን
ሴቶች ሲያለቅሱ >>
እናቶች ቀርበው >>
ላብህን ዳበሱ >>
#አዝ
መስቀል አስይዘው ኪያላይሶን
እንዲያ ሲያዳፉህ >>
የቀሬናው ሰው >>
ስምኦን አገዘው >>
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
4 374
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክEOTC2921:
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
💐🌍ስርዓተ በዓል ወጾም ዘኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን🌍💐
🌹 @EOTC2921 @EOTC2921🌹
❀☞ ዓመተ ምህረት🌾🌾🌾🌾፪ሺ፲፩
❀☞ ወንጌላዊ🌾🌾🌾🌾🌾ሉቃስ
❀☞ የዘመን መለወጫ ቀን🌾ማክሰኞ
❀☞ አበቅቴ🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾፳፭
❀☞ መጥቅዕ🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾፭
❀☞ ጾመ ነነዌ🌾🌾🌾🌾የካቲት ፲፩
❀☞ ዐብይ ጾም🌾🌾🌾የካቲት ፳፭
❀☞ ደብረዘይት🌾🌾🌾መጋቢት ፳፪
❀☞ ሆሳዕና🌾🌾🌾🌾ሚያዝያ ፲፫
❀☞ ስቅለት🌾🌾🌾🌾ሚያዝያ ፲፰
❀☞ ትንሣኤ🌾🌾🌾🌾🌾ሚያዝያ ፳
❀☞ ርክበ ካህናት🌾🌾🌾ግንቦት ፲፬
❀☞ ዕርገት🌾🌾🌾🌾🌾ግንቦት ፳፱
❀☞ ጰራቅሊጦስ🌾🌾🌾🌾ሰኔ ፱
❀☞ ጾመ ሐዋርያት🌾🌾🌾🌾ሰኔ ፲
❀☞ ጾመ ድኅነት🌾🌾🌾🌾ሰኔ ፲፪
👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇#Join #Join #Join👇
👇👇👇👇👇👇👇👇
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌼 @EOTC2921 🌼🌻🌻
🌻🌻🌼 @EOTC2921 🌼🌻🌻
🌻🌻🌼 @EOTC2921 🌼🌻🌻
4 374
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
❖ የ 2011 ዓ.ም አጽዋማትና በዓላት ❖
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ(ፍዳ)
= 2011 + 5500 =7511
❖ ወንጌላዊ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡
= ዓመተ ዓለም ÷ 4
= 7511 ÷ 4 = 1877
1877 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል
7511- 4×1877 = 3
ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 4 ' ወይም ' 0 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል። ስለዚህ ቀሪው ' 3'
ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ሉቃስ ስሆን ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ይባላል።
❖ መባቻ፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው።
መባቻ = ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት ÷7
= 7511 + 1877 ÷ 7
= 9388 ÷ 7 = 1341 ቀሪ 1
ቀሪው ' 0 ' ከሆነ ሰኞ
ቀሪው ' 1' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው ' 4 ' ከሆነ ዓርብ
ቀሪው ' 5 ' ከሆነ ቅዳሜበመግደፍ
ቀሪው ' 6 ' ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ቀሪው ' 1 ' ስለሆነ ዘንድሮ
መባቻ ማክሰኞ ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
❖ መደብ = ዓመተ ዓለምን በ19 እናገኛለን።
= 7511 ÷ 19 = 395 ደርሶ 6 ይቀራል። ስለዚህ መደብ 6 ይሆናል
❖ ወንበር = ከመደብ አንድን ለዘመን በመተው ወንበርን እናገኛለን።
ወንበር = 6 - 1= 5 ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
❖ አበቅቴ ፦ አበቅቴን ወንበርን በጥንተ አበቅቴ አባዝተን በ30 ገድፈን
እናገኛለን።
አበቅቴ = 5 ×11= 55
= 55 ÷ 30, ' 1' ደርሶ ቀሪው '25' ስሆን ዘንድሮ አበቅቴ ' 25 ' ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
❖ መጥቅዕ ፦ ወንበርን በጥንተ መጥቅዕ አባዝተን ለ 30 አካፍለን እናገኛለን።
መጥቅዕ = 5×19 = 95,
= 95 ÷ 30 ቀሪው ' 5 ' ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ ' 5 ' ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረው ውጤቱ ከ30 መብለጥና ማነስ የለበትም
ሁሌ 30 ይሆናል በዚህ የሥራችን ትክክለኛነትንበመስከረም
እናረጋግጣለን።በጥቅምት
ለምሳሌ የዘንድሮው 25+5 =30
መጥቅዕ 5 ስሆን ከ 14 ያንሳል ስለዚህ በጥቅምት ይውላል። በመሆኑም
ዘንድሮ ጾሜ ነኔዌ በየካቲት ይብታል።
✿መጥቅዕ፦ ከ14 በላይ ከሆነ ፤ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይውላል፡፡
በመስከረም ቢውል በጥር ፤ ቢውል በየካቲት ጾም ነኔዌ ይብታል(ይገባል)።
❖ ፆሜ ነኔዌ = ፆሜ ነኔዌን መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ በመደመር እናገኛለን፡፡
ዘንድሮ መጥቅዕ በጥቅምት ስውል ጥቅምት 5 በሰኞ ይውላል። ጋር
የሰኞ ተውሳክ 6 ነው። ስለሆነም ፆሜ ነኔዌ 6 + 5 = 11 ስሆን ከ30
ስለምያንስ ' 11' ን እንጠቀማለን። ስለዚህ ዘንድሮ በየካቲት ' 11 ' ሰኞ ፆሜ
ነኔዌ ይገባል።
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
✿ ሌሎችን አጽዋማት ተውሳኩን ከነኔዌ ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን
እናገኛለን።
➊ ከነነዌ ጾም እስከ ዐቢይ ጾም 14 ቀኖች አሉ ስለዚህ የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14
ይሆናል፡፡
➋ ከነነዌ እስከ ደብረዘይት 41 ቀኖች አሉ፡፡ 41 ÷ 30 = 1 ደርሶ ቀሪው 11
የደብረዘይት ተውሳክ ይሆናል፡፡
➌ ከነነዌ እስከ ሆሣዕና 62 ቀኖች አሉ፡፡ 62 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 2 የሆሣዕና
ተውሳክ ይሆናል፡፡
➍ ከነነዌ እስከ እስከ ስቅለት 67 ቀኖች አሉ፡፡ 67 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 7
የስቅለት ተውሳክ ይሆናል፡፡
➎ ከነነዌ እስከ ትንሣኤ 69 ቀኖች አሉ፡፡ 69 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 9 የትንሣኤ
ተውሳክ ይሆናል፡፡
➏ ከነነዌ እስከ ርክበ ካህናት 93 ቀኖች አሉ፡፡ 93 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀሪው 3
የርክበ ካህናት ተውሳክ ይሆናል፡፡የጾመ
➐ ከነነዌ እስከ ዕርገት 108 ቀኖች አሉ፡፡ 108 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀሪው 18
የዕርገት ተውሳክ ይሆናል፡፡
➑ ከነነዌ እስከ ጰራቅሊጦስ 118 ቀኖች አሉ፡፡ 118 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀርው 28
የጰራቅሊጦስ ተውሳክ ይሆናል፡፡
➒ ከነነዌ እስከ ጾመ ሐዋርያት 119 ቀኖች አሉ፡፡ 119 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀሪው
19 ሐዋርያት ተውሳክ ነው፡፡
➓ ከነነዌ እስከ ጾመ ድኅነት 121 ቀኖች አሉ፡፡ 121 ÷ 30 = 4 ደርሶ ቀርው 1
ስሆንሰኞ የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ይሆናል፡፡ ከዚህ ተነስተን አጽዋማትንና
በዓላትን ተውሳኮቻቸውን ከነነዌ ጋር እየደመርን እናገኛለን፡፡
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
❖ ዓብይ ፆም = ተውሳኩ 14 ነው
= 14 + 11= 25, ስሆን ስለዚህ ዘንድሮ በዘመነ ሉቃስ ዓብይ ጾም በየካቲት 25
ይገባል ማለት ነው፡፡
❖ ደብረ ዘይት = ተውሳኩ 11 ነው
= 11+ 11 = 22, ይሆናል፡፡ 22 ከ 30 ስለሚያንስና በየካቲት ስላለፍን ቀጣዩን
በመጋቢት እናገኛለን። ስለዚህ በመጋቢት 22 እሁድ ደብረዘይት ይሆናል።
❖ ሆሣዕና = ተውሳኩ 2 ነው
= 2+11 = 13, ስሆን ከ30 ስለሚያንስና በመጋቢት ስላለፍን ቀጣዩን
በሚያዝያእሁድ እናገኛለን ስለዚህ በሚያዝያ 13 እሁድ በዓለ ሆሣዕና ይውላል።
❖ ስቅለት = ተውሳኩ 7
=7 + 11= 18,ስሆን ዘንድሮ በሚያዝያ 18 ዓርብ ስቅለት ይሆናል፡፡
❖ ትንሣኤ = ተውሳኩ 9 ነው
= 9 + 11 = 20, ስሆን ሚያዝያ 20 በዓለ ትንሣኤ ይውላል።
❖ ርክበ ካህናት = ተውሳኩ 3 ነው
= 3 +11 = 14 , ስሆን 14 ን በሚያዝያ ስላለፍን በግንቦት 14 ረቡዕ ርክበ
ካህናት ይሆናል።
❖ ዕርገት = ተውሳኩ 18 ነው
= 18 + 11 = 29, ስሆን ዘንድሮ ግንቦት 29 ሐሙስ በዓለ ዕርገት
ይሆናል።ረቡዕ
❖ጰራቅሊጦስ = ተውሳኩ 28 ነው
= 28 + 11 = 39
39ን ለ30 ስናካፍል ቀሪው 9 ነው። ስለዚህ ሰኔ 9 እሁድ በዓለ ጰራቅሊጦስ
ይውላል።
❖ ፆመ ሐዋርያት = ተውሳኩ 29 ነው
= 29 + 11 = 40 ,
40 ን በ30 ገድፍን ቀሪው 10 ስሆን ሰኔ 10 ሰኞ የሐዋርያት ፆም ይገባል።
❖ ፆመ ድህነት = ተውሳኩ 1 ነው
= 1 + 11 = 12, በመሆኑም ጾመ ድህነት(የረቡዕና ዓርብ ፆም) ሰኔ 12
ይገባል።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ትኩረት
☞ ፆሜ ነኔዌ፣ አቢይ ፆም፣ፆሜ ሐዋርያት ከሰኞ አይወጡም።
☞ በዓለ ደብረዘይት፣ሆሣዕና፣ትንሣኤ፣ጰራቅሊጦስ ከእሁድ አይወጡም
☞ ዕርገት ከሐሙስ ስቅለት ከዓርብ አይወጣም።
☞ ርክበ ካህናትና ፆሜ ድህነት ከረቡዕ አይወጡም፡
#JOIN #JOIN #JOIN
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
4 374
ዓለመ፡፡
✍ቸር እረኛ እስራኤልን የሚጠብቃቸው
ታዛዥ የሆነ ክርስቶስ ለአሕዛብ የመጣ፡፡ እሺ ብሎ ታዛዥ ሆኖ ዓለምን ይቤዥና ያድን ዘንድ ከሰማይ ወረደ፤
መጣ፡፡›› (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ገጽ)፡፡ በማለት ሁሉን
የሚገዛ አምላክ ዓለሙን ሊቤዥና ሊያድን እሺ ብሎ በፈቃዱ መምጣቱን መሰከረ፡፡
ሁሉን የሚመግብ፣ የሕይወት እንጀራንና የሕይወት መጠጥን የሚሰጥ ጌታ ወደ ሰርግ ተጠራ፡፡ ለፍጥረቱ ማዕድን የሚያዘጋጅ ጌታ በፈሪሳዊው ስምዖን ቤት
ለግብዣ ተጠራ፡፡ ዮሐ 2፤2፣ ሉቃ ፤36-37፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በፈሪሳዊው ማዕድ ላይ የቀረበው የጌታ ማዕድ በሚለው ስብከቱ ‹‹ ንስሓ ስለምትገባው ስለዚያች ኃጢአተኛ ሴት ሲል ከግብዣው ቤት ተገኘ፤ ጌታ ርሀቡ ሥጋዊው ምግብ ሳይሆን የዚያች ኃጢአተኛ እንባ እንጂ… ወደ ፈሪሳዊው ስምዖን ቤት የሄደው በምግብና በመጠጥ ለመዝናናት አልነበረም ሕይወት መድኃኒት የሆነውን ትምህርቱን በማዕዱ ለማቅረብ በመሻቱ ነበር እንጂ፡፡ … ክፉ የተባለው ሰይጣን በመብል ምክንያት አዳምና ሔዋንን ሞትን የሚያመጣ ምክርን እንደመከራቸው እንዲሁ ቸሩ ጌታችን ደግሞ በማዕድ ቦታ ተገኝቶ ሕይወት ሰጪ የሆነ ትምህርቱን ለአዳም ልጆች በማዕዱ አቀረበ፡፡ እርሱ ጌታችን የጠፉትን ነፍሳት ለማጥመድ አሳ አስጋሪ ነበር፡፡ ቀራጮችና አመንዝሮች ወደ ስካርና ሥርዐት አልበኝነት ሲፋጠኑ ተመለከታቸው፤ ሥጋንም ከሚያወፍር የማዕድ ቦታ እነርሱን በማስገር ነፍስን ወደሚያወፍር ጾም ሊያሻግራቸው የቃሉን መረብ በማዕዱ ውቅያኖስ ላይ ጣለው፡፡››በማለት ገለጸው፡፡"ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም"
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#JOIN #JOIN #JOIN #JOIN
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
4 374
✍☞⛪️ ነገረ ክርስቶስ ⛪️☜✍
🌼💓 @EOTC2921 💓🌼
✍ብርህት፣ ንጽህት፣ ጽድልት፣ የሆነች ቤተክርስቲያናችን
ከምታስተምራቸው ትምህርቶች አንዱና ዋነኛው ነገረ
ክርስቶስ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ትምህርት ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል ወልድ ሲሆን
ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ ሲሆን በኋላኛ
ዘመን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን
ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆነ፡፡
እንዲህ እናምናለን፤ እንዲህም እናስተምራለን፡፡(ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ)፡፡
✍ነገረ ክርስቶስ ማለት ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የምናምነውን እምነት የምናስተምረውን
ትምህርት የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህ ክፍለ ትምህርት
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ስለ ጌታችን
መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የሚታመነው፣ የሚነገረው፣ የምንመራበት ምንድነው
የሚለውን በሚገባ ለመረዳት በቅዱሳት መጻሕፍት፣
በሊቃውንት፣ በትውፊት የተላለፈውን አስተምህሮ
የምናቀርብበት ነው፡፡
አግዚአብሔር አምላካችን የሚታየውን ዓለም
ከማስገኘቱ በፊት እስከ ዘላለም ድረስ በአንድነቱና
በሦስትነቱ፣ በመለኮቱ፣ በመንግሥቱ አለ፡፡ ከጎሕና
ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት
ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር አለ፡፡ ሰማያት ሳይዘረጉ፣
የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ
እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከሚንቀሳቀስ እንስሳ
በፊት ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት፣ እግዚአብሔር በመንግስቱ ነበረ፡፡ አዳምን በእርሱ
አምሳልና አርአያ ሳይፈጥረው፣ ትእዛዙንም ሳያፈርስ
እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ
ማርያም ሥግው ከአምላክ የተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን
የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ የተገኘ ባሕርይ፣ ከሕይወት
የተገኘ አዳኝ ከመድኃኒት የተገኘ መድኅን፣ ከገዥ የተገኘ
ገዢ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ህላዌ እንደሆነ
እናምናለን (መዝገበ ሃይማኖት)፡፡
ከአብ መወለዱም በዚህ ዘመን፣ በዚህ ወቅት፣ በዚህ
ሰዓት ተብሎ ዘመን አይቆጠርለትም፤ በሰውና በመላእክት
አእምሮም ሊመረመር አይችልም፡፡ ሰውንም ስለማዳን
በአባቱ ፈቃድ በእርሱም ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ
ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር በድንግልና
ተወለደ፡፡ ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ
አልተለወጠም፡፡ በሚያስደንቅ ትሕትና ሰው ሆነ፤
በሚያስደንቅ ዙፋኑ ለደቀመዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት
ጊዜ አገልጋዮች መላእክት ደነገጡ፡፡ ትሕትና ወዳለበት
ፍቅር የአሕዛብን እግረ ልቡና ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት
በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ መላእክት ደነገጡ
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘስሩግ)፡፡ ፍጥረቱን ሁሉ
ሰብስቦ የያዘና ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግብ ጌታቸው
በብብቷ (በክንዷ) ተቀምጦ ጡቷን ሲጠባ ባዩ ጊዜ
በአርያም ፈለጉና በዚህ ዓለም እንደ ቀድሞው ከአባቱና
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አገኙት፡፡ የጌታን ትሕትና ባዩ ጊዜም
ዓይኖቻቸውን ወደ ላይ ወደ አርያም ከፍ ከፍ አደረጉ
ክንፋቸውንም ዘርግተው ለሁሉ ጌታ ለአንተ ምስጋና
ይገባሃል እያሉ ጌታቸውን አመሰገኑ፡፡ (አንቀጸ ብርሃን)
አዳምን ካልታረሰች መሬት የፈጠረው ሔዋንንም ከአዳም
ያለእናት የፈጠራት እርሱ ከንጽሕት ድንግል ያለ ወንድ
ዘር ተወለደ፡፡ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና ስለዚህ
የአዳምን ብድራት ትከፍለው ዘንድ አዳም ያለ እናት
ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት
ክርስቶስን ወለደች ይህም ድንቅ በሚሆን አንድነት
የፍጥረት ሁሉ እኩልነት ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ (ሃይማኖተ
አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡
ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ከአዳም አጥንት
ጎድን ሲነሳ ምንም አካል እንዳልጎደለው እንዲሁ
ከድንግል የምትናገር ነፍስን ሲነሳ ማኅተመ ድንግልናዋ
አልተለወጠም፡፡ አዳም የጎድን አጥንት ከእርሱ ከተነሳ
በኋላ አካል ሳይጎድለው ፍጹም ሆኖ እንደኖረ እንዲሁ
ድንግልም ሕጻን ክርስቶስ ከእርሷ ከተወለደ በኋላ
በድንግልና ጸንታ ኖረች›› አለ፡፡ ሕዝ 44፤1-3፣ መኃ 4፤12
ነቢያት ስለእርሱ ሰው መሆን ተነበዩ፡፡ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም
አማኑኤል ይሉታል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር
ሆነ ማለት ነው›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም
በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና
በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ
የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።›› በማለት ትንቢት ተናገረ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃኑ አባቱንና
እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን
ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ›› አለ፡፡ (ኢሳ
14 ፣ 9፤6፣ 8፤4)፡፡ ጌታችን በመወለዱ በዲያብሎስ የተያዙትን ማርኳል፣ ሲኦልን በዝብዟልና ስሙ ‹‹ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ›› ተብሎ ተጠራ፡፡
የማይደፈር ግሩም ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን ትሑት ነው፡፡ የማይደረስበት ልዑል ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን የባርያውን
መልክ ነሳ፡፡ የማይዳሰስ እሳት ነው፡፡ እኛ ግን አየነው፣ ዳሰስነው፣ ከእርሱም ጋር በላን ጠጣንም (ቅዳሴ
ማርያም)፡፡ ሁሉ በእርሱ የተፈጠረና ሁሉን ሚመግብ
ሁሉ በእጁ የተያዘ መላእክት የሚታዘዙለትና የሚያገለግሉት፣ እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል
ነኝ አለ (ሉቃ 22፤27)፡፡
በአዳም ምክንያት የጨለመውን ልቡናችንን ለማብራትና በእርሱ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኖ የመጣ (ዮሐ 12፤16)፡፡ ጨለማን ያስወገደ ብርሃን
የሃይማኖትና የጽድቅ ጣሪያዋ (ጠፈሯ)፣ ሃይማኖትም ወንጌልም፣ በብዙ ድካም እርሱን ደስ ያሰኙት የሚወርሱት፣ የሃይማኖት ገንዘብን ይዘው በሠርክ
የሚገቡበት መንግስተ ሰማያት እርሱ ነው (ሉቃ 17፤21፣ መልክአ ኢየሱስ)፡፡
ክብርና ምስጋና ይግባውና የእኛን ሞት ሞቶ የእርሱን ሕይወት የሰጠን፡፡ ድዳ ለነበሩት ቃል፣ ለተሰበሩት ምርጉዝ፣ ለዕውራን ብርሃን፣ለሐንካሶች መሄጃ፣
ለለምጻሞች የሚያነጻቸው ሆነ፡፡ በዴዌ የተያዙትን አዳነ፣ ደንቆሮዎችን ፈወሰ፣ ሞትን ዘለፈው ጨለማንም
አሰቃየው፡፡ ብርሃን ኅልፈት የሌለበት፣ ፀሐይ፣ የማይጠፋ
ፋኖስ፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ፣ በተወሰነ በቁርጥ ፈቃድ ለዓለም ጌጥ ሁሉን የፈጠረ፣ ሰውን
ለማዳን ለሁሉ የተገለጠ፣ ነፍሳችንን የመለሳት እርሱ ነው
(ኪዳን ዘነግህ)፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ምንስ እላለሁ ምንስ እናገራለሁ ከዘመን በፊት የነበረ እርሱ ትንሽ ሕጻን ሆኗልና ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ
የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ›› በማለት የጌታን ትሕትና አደነቀ፡፡ ነፋሳት
የሚታዘዙለት፣ መላእክት የሚላላኩት እርሱ ለእናቱና ለዘመዶቹ እየታዘዘ አደገ፡፡ ሁሉን አዋቂ ሲሆን አልአዓዛርን የት ቀበራችሁት ብሎ ጠየቀ፤ እርሱ የሕይወት ውሃ ሲሆን ከሳምራዊት ሴት ውሃ ለመነ፡፡ ምራቅ ከጭቃ ጋር ለውሶ እውር ያበራ እርሱን አይሁድ ምራቅ ተፉበት፡፡ ጠባቂ አጥተው ለባዘኑት መልካም እረኛ ሆኖ መጣ ስለበጎቹም ነፍሱን ሰጠ፡፡ (ዮሐ 1፤11) ቅዱስ ያሬድ ‹‹ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለእስራኤል ዘመጽአ ውስተ ዓለም ተአዛዚ ከዊኖ ክርስቶስ ለአሕዛብ፡፡ ኦሆ ብሂሎ ተአዛዚ ከዊኖ ወረደ ወመጽአ ለአድኅኖ… ከመ ይቤዙ ወያድኅን
4 374
4 374
ውድ የተዋህዶ ልጆች ይህ የምትመለከቱት ፓስተር "ጌታ ያድነኛል ጌታ ፍሉን ውሃ ያቀዘቅዝልኛል...." እያለ ነበር ነገር ግን የትኛው ፅድቁ ሊያድነው...????
✍ @EOTC2921 ✍
