የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Kanalga Telegram’da o‘tish
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Ko'proq ko'rsatish4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
4 374
🌾✞ #ቤተ_ክርስቲያን ✞🌾
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ኦሮሞ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #አማራ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ትግራይ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ጉምዝ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #አፋር አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ሱማሌ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ሲዳማ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ጉራጌ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ስልጤ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ወላይታ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ጋንቤላ አይለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ሀድያ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ኮንሶ አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ሀመር አይደለችም፤
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ሰማያዊት ናት እንጅ #ምድራዊት አይደለችም።
⛪️✞ ቤተክርስቲያን #ክርስቶሳዊት ናት።
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #አምላካዊት ናት።
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #ህያዊት ናት።
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #በዘር የተመሰረተች አይደለችም።
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን #በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ናት እንጅ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን #የብሔር_አይደለችም።
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንጂ አምኖ ለመጣው ሁሉ ኦሮሞ አማራ ደቡብ ትግሬ ሳትል ለሁሉ እኩል ታስተምራለች፤ እኩል ሲሞት ትፈታለች፤ እንግዲህ ሰው በዘር ሲተራመስ ቤተ ክርስቲያንን ኢላማ ማድረግ ተገቢ አይደለም።
⛪️✞ ቤተ ክርስቲያን መንግስተ እግዚአብሔር መንግሥተ ሰማያትን እንጅ መንግስተ ምድርን ዘርን አሰብክም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ዓይን ብሌናችን እንጠብቃት መንግሥተ ሰማያትን የምናይባት ናትና።
✍መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
4 374
4ኛ፥ አንዳንድ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የግፉዓን ሰማዕታቱን መጠቃት አላግባብ ለቡድናዊ እና ፖሊቲካዊ ትርፍ በመጠቀም በሐዘናችን ከመሣለቅ እንዲቆጠቡ፣ መንግሥትም ተገቢውን ክትትል በማድረግ እንዲያስታግሥ በቤተ ክርስቲያን አበክራ ታሳስባለች፡፡
•••
5ኛ፥ በ2012 ዓም መባቻ፣ በአንድ ቀን 97 ዜጎች እና ምእመናን ካለቁበት የወርኅ ጥቅምቱ ጥቃት እንዲሁም የወርኅ ጥር የበዓለ ጥምቀት አከባበር ወቅት ከተፈጸሙ ግድያዎችና ዘረፋዎች ጀምሮ በልዩ ልዩ የአገራችን አካባቢዎች በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ እየደረሱ ያሉ ግፎችንና በደሎችን መንግሥት አጣርቶ ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ ውጤቱንም በይፋ ለሕዝብ እንዲገልጽ ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ትጠይቃለች።
•••
7ኛ፥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለአገር ሰላምና ለሕዝብ አንድነት ባበረከተችው አስተዋጽኦ በገነባችው የተቀደሰ በህል እና ባወረሰችው ዘርፈ ብዙ እሴት በኢትዮጵያውያን ኹሉ ልትከበር እና ልትወደድ የሚገባት ናት። ከሞላው ጸጋዋ እና በረከቷ ያልተቋደሰ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ተብሎ የማይገመት በመኾኑ፣ የኹሉ እናት እና ባለውለታ ናት ብለን እናምናለን።
•••
ኾኖም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሱ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች፣ አብዝቶ እንደሚነገረው፣ “በሽግግር ላይ የሚያጋጥሙ” ተብለው ብቻ የሚታለፉ ሳይኾኑ፣ የተሳሳቱ ርእዮተ ዓለማዊ ትርክቶችና ጂኦ ፖለቲካዊ ዳራዎችን መነሻ በማድረግ የተቀነባበረ እና በተደራጀ ስልት የሚፈጸሙ ኦርቶዶክሳውያንን የ“ማጽዳት” እንቅስቃሴዎች እንደኾኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግልጽ እየኾነ መምጣቱን ቤተ ክርስቲያናችን ትገነዘባለች፡፡ በአጭር ጊዜ ሳይታረም በዚሁ ከቀጠለም፣ የከፋ ፍጻሜ ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ ታስገነዝባለች።
•••
ስለዚህም፣ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት፥ በእነዚህ ስሑት አስተሳሰቦች እና ሐሳዊ ትርክቶች ማዕቀፍ፣ ኾነ ተብሎ የሚፈጸም ኦርቶዶክሳውያንን የማሳቀቅ እና የማዳከም ሃይማኖት ተኮር ጥቃትን አስቀድሞ በመከላከል፣ ፍትሕን በማስፈን፣ ተጎጂዎችን በአግባቡ በመካስ እና በማቋቋም፣ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ በአጽንዖት ታሳስባለች፡፡
የተወደዳችኹ ተጎጂ ምእመናንና ምእመናት ልጆቻችን፤
•••
የግፍ ጥቃቱ የደረሰባችኹና በአሁኑ ወቅት በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን አዳራሾች እና በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች ተጠልላችኹ እንደምትገኙ ይታወቃል። ይህ ስለ ቀናች ሃይማኖታችኹ የተቀበላችኹት መከራ በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት መዝገብ በወርቅ ቀለም ተጽፎ የሚኖር ነው፡፡ በግፈኞች ፊት ለማዕተበ ክርስትናችሁ ባሳያችኹት ጽናት እና በከፈላችሁት መሥዋዕት፣ የአገራችሁን ህልውና እና፣አንድነት ታድጋችኋል። የቤተ ክርስቲያናችሁን ልዕልና አስመስክራችኋል። ይኸውም፤ ለትውልድ አብነት ኾኖ በምሳሌነት ሲነገር የሚኖር በመኾኑ እናት ቤተ ክርስቲያናችኹ ኮርታባችኋለች፡፡ ለወደፊትም፣ መላው ኢትዮጵያውያንና ኦርቶዶክሳውያን፣ በሚያስፈልጋችሁ ኹሉ ከጎናችኹ ይቆማሉ። ብቻችሁን እንዳልኾናችኹም ቤተ ክርስቲያን ታረጋግጥላችኋለች። ዛሬ ባገኛችሁ መከራ ግፍ አድራሾቹ ቢደሰቱም፣ በጊዜው ፍትሕን በሕግ ተጎናጽፋችኹ እንባችኹ እንደሚታበስ እና ኃዘናችኹ ወደ ደስታ እንደሚለወጥ ቤተ ክርስቲያናችን ታምናለች።
•••
በአገር ውስጥና በወጭ የምትገኙ የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ልጆቻችን፤ አሠቃቂው ጥቃት ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ፣ በኢትዮጵያዊ ነባር አስተምህሮ እና የአብሮነት ባህል እርስ በርስ በመረዳዳት፣ ዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ያሳደረው ከባድ የኑሮ ጫና ሳይበግራችኹ እና ርቀት ሳይገድባችኹ የጥቃቱን ሰለባዎች ለመታደግ እና መልሶ ለማቋቋም ያደረጋችኹትንና በማድረግ ላይ ያላችኹትን ልዩ ልዩ አስተዋፅኦ ቤተ ክርስቲያናችን በከፍተኛ አንክሮ ትመለከታዋለች፤ የጎሣ እና የእምነት ልዩነት ሳይገድባችኹ ላደረጋችኹት ሰብአዊ እና ኢትዮጵያዊ ርዳታ እና ድጋፍ፣ ልዑል እግዚአብሔር ዋጋችኹን ይከፍላችኹ ዘንድ ዘወትር ትጸልያለች፡፡
•••
በሌላ በኩል በክርስቲያናዊ የትብብር መንፈስ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰው ጉዳት ተሰምቷችኹ ጥቃቱን በማውገዝ አጋርነታችኹን በመግለጫ እና በልዩ ልዩ ድጋፎች ላሳያችኹ የዓለም ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የከበረ ምስጋናዋን ታቀርባለች፡፡
•••
አሁንም፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ተጠናክሮ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት፣ ተጎጂዎችን ለመርዳት እና በዘላቂነት ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፥ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በሞያ እንድትድገፉ፣ እንደ አስፈላጊነቱም በቀጣይነት ለሚያስተላልፈው ጥሪ ንቁ ምላሽ ለመስጠት እንድትዘጋጁ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ በዚኹ አጋጣሚ በአገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ምእመናን ድጋፍና አስተዋፅኦ ማደረረግ ያለባችሁ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው የርዳታ አሰባሳቢ አካል በከፈታቸው የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ብቻ መኾኑን እናስታውቃለን።
•••
ቸሩ እግዚአብሔር ለአገራችንና ለዓለም ሰላምን ለሕዝባችን አንድነትን፣ በግፍ ለተገደሉት ልጆቻችን ዕረፍተ ነፍስንና ለተጎዱት መጽናናትን እንዲሰጥልን እንለምናለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት።
4 374
#ከቅዱስ_ሲኖዶስ_የተሠጠ_መግለጫ
#ETHIOPIA | ~ ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች ይነበብላቸው።
ቀን፡- ነሐሴ 19/2012 ዓ.ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡
•••
የልጃችን የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ እና ግድያውን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች የተጎዱ ኦርቶዶክሳውያንን መርዳትንና መልሶ ማቋቋምን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ።
•••
“ አማን አማን እብለክሙ ከመ ትበክዩ ወትላህዉ አንትሙ፤ ወዓለምሰ ይትፌሣህ፤ ወአንትሙሰ ተኃዝኑ፤ ወኃዘንክሙ ፍሥሐ ይከውነክሙ። እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንት ታለቅሳላችኹ፤ ሙሾም ታወጣላችኹ፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል። እናንተም ታዝናላችኹ፤ ነገር ግን ኃዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። ” (ዮሐ 16፥ 20)
•••
ሃጫሉ ሁንዴሳ ስመ ጥምቀቱ ኃይለ ገብርኤል፣ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት በአዲስ አበባ መገደሉ ይታወሳል። ቤተ ክርስቲያን፥ በዚያ ድንገተኛ የልጇ ግድያ ከባድ ኃዘን ተሰምቷታል፡፡ ኾኖም፣ በግድያው የተሰማትን ኃዘን ለመወጣት ጊዜ ሳይሰጣት፣ ኃዘንተኛነቷ ተረስቶ እና እንደ ጠላት ተቆጥራ፣ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በክርስቲያን ልጆቿ ላይ ዘግናኝ ፍጅት እና መከራ ተፈጸመባቸው።
•••
በኦርቶዶክሳዊነታቸው ብቻ በአሠቃቂ መልኩ በገጀራ ተቀሉ፤ በቆንጨራ ተቆራረጡ፣ በጦር ተወግተው በጩቤ ተዘከዘኩ፣ በሜንጫ ተተለተሉ፣ በዱላ ተቀጥቅጠው እና በደንጊያ ተወግረው ተገደሉ፣ አስከሬናቸውሸበጎዳና እየተጎተተ ሲንገላታ ዋለ፣ ለቀናት በየቦታው ወድቆ የቆየው የሰውነት ክፍላቸው ለከርሰ አራዊት ሲሳይ ኾነ። ሴቶች በልጆቻቸው፣ በአባቶቻቸው እና በባሎቻቸው ፊት ተደፈሩ። ለዘመናት የደከሙበት ቤት ንብረታቸው በጥናትና በጥቆማ እየተለየ ከተዘረፈ በኋላ ቀሪው ጋዝ እየተርከፈከፈበት በእሳት እየጋየ ወደመ። ብዙዎች ከሞቀ ቀዬአቸው ተፈናቅለው የክረምቱን ጨለማ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በሚገኙ መቃብር ቤቶች እና አዳራሾች፣ በልዩ ልዩ መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም በግሰለቦች ቤት ተጠልለው ለማሳለፍ ተገደዱ። በአስከፊ ማኅበራዊ እና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተዳረጉ።
•••
ቤተ ክርስቲያናችን ይህንኑ ጥቃት እንደሰማች፣ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓም የሐዘን መግለጫ አውጥታለች። በአገር ውስጥና በውጭ በኃዘንና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ስታመለክት ከርማለች፤ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም፥ “አጥፊዎችን አንታገሥም፣ ተገቢውን ፍትሕ እንሰጣለን፤ የተጎዱትን እንክሳለን፤” ብለው ቃል የገቡትን ይፈጽሙ እንደ ኾነ በማለት በትዕግሥት ጠብቃ ነበር። ኾኖም ዜጎችን ዜጎችን ከጥቃት አስቀድሞ የመከላከል እና የመጠበቅ ፣ ፍትሕን የማስፈንና ተጎጂዎችን በአግባቡ የመካስ ሓላፊነታቸውን በወቅቱና በብቃት ሲወጡ አላየችም።
•••
በጉዳዩ ላይ የተወያየው ቋሚ ሲኖዶስም፣ በየሥፍራው በአካል ተገኝቶ የደረሰውን ጉዳት የሚያጠና ዐቢይ ኮሚቴ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እንዲቋቋም መመሪያ ሰጥቷል፡፡ በዚኽም መሠረት ዐቢይ ኮሚቴው፣ ተጎጂዎችን በጊዜያዊነት ለመርዳት እና በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉትን ልዩልዩ ንኡሳን ኮሚቴዎችን አደራጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
•••
ዐቢይ ኮሚቴው ባወጣው መርሐ ግብር የሥራ መጀመሪያ ያደረገው፣ ጥቃቱ የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች በዝርዝር በመለየት፣ ተጎጅዎችን የማጽናናት እና መረጃ የማሰባሰብ ጉዞ ማካሔድ ነበር፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የአገር ሽማግሌዎችን፣ መንፈሳውያን ማኅበራትንና በርካታ የብዙኃን መገናኛዎችን ጨምሮ 260 ያኽል ልኡካን የተሳተፉበት ይኸው ጉዞ፣ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች ውስጥ ስድስት አህጉረ ስብከትንና 25 ወረዳዎችን የሸፈነ ነበር፡፡
•••
የዐቢይ ኮሚቴው ልኡካን ተጎጂዎችን በማነጋገር እና ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች በመጎብኘት ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት፣ የልጃችን የኃይለ ገብርኤልን ግድያ ተከትሎ፣ በኦሮሚያበክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ተገን ያደረጉ የእምነትና የብሔር ጽንፈኞች አስቀድመው ከተደራጁ ኀይሎች ጋር በመቀናጀት የፈጸሙት ስልታዊ እና አረመኔያዊ ጥቃት ዋና ዒላማ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን እንደነበሩ ተረጋግጧል፡፡
•••
ከሰኔ 22 ቀን ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በተፈጸመው በዚያ ጥቃት፥ ከ67 በላይ ምእመናን በግፍ እና በአሠቃቂ ኹኔታ ተገድለዋል። 38 ምእመናን ቋሚ ( ከባድ) 29 ምእመናን ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ7ሺ በላይ ምእመናን ከመኖሪያ ቤታቸው ከመፈናቀላቸውም ባሻገር በተለያየ ደረጃ ለሚገለጽ ሥነ ልቡናዊ እና ሥነ አእምሯዊ ቀውስ ተዳርገዋል። ከአምስት ቢልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረታቸውንም በዘረፋ እና በቃጠሎ ማጣታቸውን
የጥቃቱን አስከፊነት በዚኽ መልኩ የተረዳው ከዐቢይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።
•••
የጥቃቱን አስከፊነት በዚህ መልክ የተረዳው ዐቢይ ኮሚቴው ተጎጅዎችን በአፋጣኝ ባሉበት ለመርዳት እና በዘላቂነት ለማቋቋም ይቻል ዘንድ፣ አደረጃጀቱን በዐዲስ መልክ በማጠናከር ተልእኮውን በአጭር ጊዜ ለማከናወን የሚያስችለውን ስልት ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የጉዳቱን መጠን በነፍስ ወከፍ ደረጃ የመለየት ሥራ የተሠራ ሲኾን፣ በዚኽም መነሻነት፣ ርዳታው በቀጥታ ለተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲደርስ ይደረጋል፤ በዘላቂነት ለማቋቋምም ኹኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
•••
ዐቢይ ኮሚቴው፣ በጉዳት ጥናት መረጃው መሠረት፣ ጊዜያዊ ርዳታን ከማድረስ እና ከማቋቋም ባሻገር፣ መንግሥት በአስቸኳይ ሊፈጽማቸው የሚገቡ ተግባራት አሉ ብሎ ያምናል፤ እነዚህም፤
•••
1ኛ፥ ተጎጅዎች በሃይማኖታቸው በደረሰባቸው ስልታዊ እና ዘግናኝ ጥቃት የተነሣ፣ በከፍተኛ የደኅንነት ስጋት ላይ እንደሚገኙ በቀረበው ሪፖርት እና ማስረጃ አረጋግጠናል፡፡ በወቅቱ ያሉበት ኹኔታ፣ ለኮሮና ቫይረስ እና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች የሚያጋልጣቸው እንደሆነ ለመታዘብ ተችሏል። በመኾኑም፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና የፌዴራል መንግሥት፣ የኦርቶዶክሳውያን ኢትዮጵያውያንን በሕይወት የመኖር እና ሀብት የማፍራት ሰብአዊ እና ዜግነታዊ መብቶችን በማስከበር የደኅንነት እና የኑሮ ዋስትና በአፋጣኝ እንዲያረጋግጥላቸው ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ታሳስባለች፡፡
•••
2ኛ፥ መንግሥት፥ ጥቃቱን ያቀዱትን፣ የፈጸሙትንና ያስተባበሩትን ኃይሎች እንዲሁም የተጣለባቸውን ሓላፊነት ወደ ጎን በማለት ጥቃቱን በዝምታ የተመለከቱትን በመዋቅሩ ውስጥ ያሉትን ሹማምንት እና የጸጥታ አካላት የኾኑ አጥፎዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል እና በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ፍትሕ ርትዕ እንዲያሰፍን ታሳስባለች፡፡ በዚኽ ረገድ መንግሥት ፣ ከጥቃቱም በኋላ ቢኾን፣ ሕግን ለማስከበር እያደረገ ያለውን ጥረት ቤተ ክርስቲያን በቅርበት የምትከታተለውና የምታደንቀውም ነው። ለውጤታማነቱም፣ ማንኛውንም የበኩሏን ድጋፍ ለነለማድረግ ዝግጁ መኾኗን ትገልጻለች።
•••
3ኛ፥ በአሳዛኝ ኹኔታ በደል እና ግፍ የተፈጸመባቸው ኾነው እያለ፣ በጥፋቱ ምንም ሱታፌ የሌላቸው ንጹሐን ዜጎች፣ በኦርቶዶክሳዊነታቸው ብቻ ታስረው እየተንገላቱ በመኾኑ ጉዳያቸው በጥንቃቄ ታይቶ ከእስር እንዲፈቱ ታሳስባለች።
•••
4 374
• ✅✅ 📯•
ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች አንድ የ Youtube ቻናል እንጠቁሞት !
በ 100 ሺዎች በላይ ተከታይ ያለው የ youtube ቻናል
---------------------------------------------------------
አዳዲስ እና ቆየት ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች መገኛ የሆነው የ Youtube ቻናል ኦተመ Tube
📌 ልሳነ ግእዝ ቋንቋ ትምህርቶች
📌 ዜና ቤተ - ክርስቲያናትን 📌 መንፈሳዊ ፊልሞች
📌 የአባቶች ምክር 📌 ስነ ፁፎችን ,ግጥሞች
📌 ብሂለ አበው 📌 የዘማሪያን የመድረክ ስራዎች
📌 ስብከቶችች 📌 ወዘተ...
🔔 የመምህር ምህረት አብ አሰፋ ልዩ ጉባዬ የማንቂያ ደውል መላው ዓለም በጉጉትና በናፍቆት የሚጠብቀውን የቀጥታ ስርጭት ጨምሮ የሚተላለፍበት መረሀ ግብር ዝግጅቱን አጠናቆ ሙሉ መሙሉ በአዲስ መልክ መቶልናል አሁኑኑ SUBSCRIBE ያርጉት ! ከታች ያለውን Link ተጭነው !
---------------------------------------------------------
👇👇 👇👇 👇👇 👇👇 👇👇 👇👇👇 👇
https://www.youtube.com/channel/UCptb7G0iVwCCLRRdEzXud1w?sub_confirmation=yes
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 👆👆👆👆👆

🎯 • 📯• 🎯

🌾✞ #ትህትና ✞🌾
💠ትህትና እኔ ከሁሉ ታናሽ ነኝ ማለት ነዉ እንደ #ዮሃንስ፤
💠ትህትናስ እኔ ትል ነኝ ማለት ነዉ እንደ #ዳዊት፤
💠ትህትናስ ኃጢያተኛ ነኝ ማለት ነዉ እንደ #ጴጥሮስ፤
💠ትህትናስ እኔ ጭንጋፍ ነኝ ማለት ነዉ እንደ #ጳውሎስ፤
💠ትህትናስ እኔ አፈርና አመድ ነኝ ማለት ነዉ እንደ #አብርሃም፤
💠ትህትናስ ባሪያ ነኝ ማለት ነዉ እንደ #ያእቆብ
"ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።" ሉቃ፡፲፬፥፲፩
"ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ከፍ ይላል፤ ትህትና ክብርን ትቀድማለች።" ምሳ፡፲፰፥፲፪
✅✞የሚገርመው ግን እራሱን የሚያዋርድ ከፍ ይላል የሚለውን ቃሉን
እግዚአብሔር ለ ቅዱሳኑ ሲፈጽምላቸው በመጸሐፍቅዱስ ውስጥ እናያለን።
✅✞ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ ዘድን የሚገባኝ አይደለሁም ብሎ ራሱን ዝቅ ሲያደርግ።
ኢየሱስ ግን አክብሮት መጥምቀ መለኮት ለመባል አበቃው። ማቴ፡፫፥፲፩ ፣ዮሐ፡፩፥፳፮
✅✞ቅዱስ ጴጥሮስም ራሱን በማዋረዱና ዝቅ ከማድረጉ የተነሳ እንዲህ ብሎአል "ጌታ ሆይ እኔ ኃጢያተኛ ነኝና ከኔ ተለይ" አለው።
ክርስቶስ ግን አክብሮት ጴጥሮስን ሊቀ ሐዋርያት አደረገው። ሉቃ፡፭፥፰ ፣ዮሐ፡፳፩፥፲፯
✅✞ቅዱስ ዳዊትም እራሱን ዝቅ ሲያደግ እንዲህ አለ "እኔ ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም" አለ።
እግዚአብሔር ግን አክብሮት እንዲህ አለው "እንደ ልቤ የሆነ ዳዊት"
ብሎ አከበረው።
https://t.me/EOTC2921
🌾✞ #እንደ_አባቶቻችን ✞🌾
ምግባርን ተላብሰን ሁሉንም እናክብር፣
ያን ያማረ ህይወት ደግሞም እናስተምር፣
በቀጥተኛይቱ በኦርቶዶክስ መንደር፣
ልክ እንዳስተማሩን እውነተኛን ፍቅር፣
የሰማዕታት አንገት በሰይፍ ቢታረድ፣
በቀደመችዋ በተዋህዶ መንገድ፣
እንደ አባቶቻችን በጽናት እንሂድ፣
ዛሬም ብሷልና የዘመኑ ትውልድ።
ሐይማኖትን ይዘን ፍቅርን ተጎናጽፈን፣
ነውር ሳይኖርብን ትህትናንም ወርሰን፣
የቅዱሳን ክብር ለእኛም እንዲተርፈን፣
እንኑር በጥንቱ እንደ አባቶቻችን፡፡
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#በደላችንን_ይቅር_በለን
https://telegram.me/EOTC2921
1. እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን እንደሚወድ
አምላካችን ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ባይወድ ኖሮ ይቅርታን እንድንጠይቅ አይነግረንም ነበር፡፡ አዎ እኛ ከተመለስን ምንም ያህል በደለኛ ብንሆን ይቅር ሊለን፤ ምንም ያህል ብንቆሽሸ ሊያድነን ዝግጁ ነው፡፡ እንዲህ እያለ ይጠራናል፤ «እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ»፡፡ ስለዚህ በዚሀ ጸሎትም ላይ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጠይቀው አስተማረን፤ ይቅር ይለን ዘንድ፡፡
2. ይቅር ለመባል ምን ማድረግ እንዳለብን፤
ይቅር ሊለን ስለወደደም ይቅርታን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በዚሁ ቃል ነግሮናል፤ ማድረግ ያለብን ምንድን ነው?
- ኀጢአታችንን ማወቅ፣ ማመን፣ ማስታወስ
- የበደሉንን ይቅር ማለት
- ይቅርታን መለመን
#ኅጢአታችንን_ማወቅ /ማመን/
ጌታ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጸልይ ሲነግረን በመጀመሪያ ደረጃ በደለኛ እንደሆንን እያስታወስን /እንድናስታውስ እያደረገን/ ነው፡፡
ሁልጊዜም በማሰብ፣ በመናገርና በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የሆነውን ልባችንን /ኅሊናችንን/ እና ሰውነታችንን እናቆሽሻለን፤ መድኃኔዓለም ክርስቶሰ የሞተለትን ማንነታችንን እናጎድፋለን፡፡ ይህም የሰው ልጆች በቅድስና እርሱን መስለን እንድንኖር በኋላም የተዘጋጀልንን የዘለዓለም መንግሥት እንድወርስ ብቻ ፈቃዱ የሆነውን እግዚአብሔርን ያሳዝናል፤ በአርአያውና በአምሳሉ ለክብር የፈጠረው ሰውነታችን መጉደፍ ያስቆጣዋል፤ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ እርሱ ኀጢአት አይስማማውምና፡፡
እንግዲህ ይቅር ለመባል በመጀመሪያ እንዲህ ኀጢአት እየሰራን መሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልገናል፡፡ ወደዚህ ዕውቀት ለመድረስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መማር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ስህተት የሚታወቀው ያለውን ሁኔታ /ድርጊታችንን ንግግራችንን፣ ሀሳባችንን.. / መሆን ከነበረበት /ከትክክለኛው/ ጋር በማነጻጸር በሚዛን ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የማነጻጻሪያ ሚዛኖቻችን ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ሕግጋትና ትዕዛዛት ናቸው፡፡ እነዚህን ስናውቅ ጉድለቶቻችን፣ ድካሞቻችን ፍንተው ብሎ ይታዩናል፡፡ አሊያ ግን እየበደለን ያልበደልን ሊመስለን ይችላል፡፡
https://telegram.me/EOTC2921
#የበደሉንን_ይቅር_ማለት
ጌታ በዚህ ጸሎት ይቅርታ እንድንጠይቀው በማስተማር ይቅር ሊለን እንደሚወድ ዝግጁም እንደሆነ ቢነግረንም ይቅር ለመባል ግን እኛ የበደሉንን ይቅር ማለታችን የግድ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦልናል፤
«በደላችንን ይቅር በለን» ከማለታችን በፊት «እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል» እንድንል ያዘዘን እኛ ይቅርታ የምናገኘው ሌሎችን ይቅር ስንል ብቻ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡
ጌታችን ይህንን ጉዳይ በሌሎች የተለያዩ ቦታዎችም በተደጋጋሚ አስተምሮናል፤ በዚሁ በተራራው ስብከት ይኸው ጉዳይ ሁለት ጊዜ በጌታችን ትምህርት ተሰጥቶበታል፡፡
«እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡ » /ማቴ.7-2/
በሌላ ቦታም እንዲህ ሲል ይህንኑ ጉዳይ በምሳሌ አስተምሯል፤
መንግስተ ሰማያት ባሮቹን ለመቆጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች መቆጣጠርም በጀመረ ጊዜ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ባለ እዳው ሰው የሚከፍለው ስላጣ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ንጉሡ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው፡፡ የዚያም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፡፡ ይህ ባርያ ግን ወጥቶ ከባልጀሮቹ /እንደርሱ ባርያ ከሆኑት/ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው፡፡ ባልንጀራው ባርያም ወድቆ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤ ብሎ ለመነው፡፡ እርሱ ግን ሊተወው አልወደደም፡፡ ዕዳውን እስኪከፍልም በወኀኒ አኖረው፡፡ ይህንን ያዩ ሰዎችም አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ሁሉ ለንጉሡ ተናገሩ፡፡
«ከዚህ ወዲያ ንጉሡ ጠርቶ፣ አንተ ክፉ ባርያ ስለለመንከኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን የሆነውን ባርያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን አለው፡፡ ጌታውም ተቆጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚያሰቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡»
ጌታ ይህንን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ የምሳሌውን ትርጉም እንዲህ ሲል ገልጦታል፤ ብሏል፤ «ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርገባችኋል»/ማቴ.18. 23- 35/
በአጠቃላይ ይቅር ለመባል ይቅር ማለት የግድ ነው፡፡ በእኛ ላይ የሚፈረድብን ፍርድ በእኛው እጅ ላይ ነው፡፡ ጌታችን በእነዚህ ትምህርቶች እንዲህ እያለን ነው «እኔ እናንተ ላይ የምፈርደው እናንተ በራሳችሁ ላይ በፈረዳችሁበት መንገድ /መልኩ ነው/»፡፡
#ይቅርታ_መጠየቅ
ኀጢአታችንን ካወቀንና ካመንን፣ የበደሉንንም ከልብ ይቅር ካልን በኋላ ይቅር እንድንባል መጠየቅ /መለመን/ አለብን ፡፡
«ይቅር በለን» ብላችሁ ጸልዩ ብሎ በማስተማሩ ይህንን እንረዳለን፡፡ ወደ ንስሐ አባት መሄድና ኀጢአትን ተናዞ ቀኖና መቀበለ የሚገባወሙ መጀመሪያ በዚህ መልኩ ስለ ኀጢአት ካለቀሱ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም ቀኖና ተቀብለን ስንፈጽምም ሆነ ከዚያ በኋላ ይኸው ስለ ኀጢአት ይቅርታ መጠየቁ ይቀጥላል፡፡
በእርግጥም ይቅርታ የምንጠይቀው አዳዲስ ስለሰራናቸውና ንስሐ ገና ስላልገባንባቸው ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ስለገባንባቸው ስለ ቀደሙት በደሎቻችንም ጭምር ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ዳዊት «የቀደመ በደላችንን አታስብብን ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን» /መዝ.78-8/ እያልን ሰለ ቀድሙ በደሎቻችንንም እያሰብን በሕይወታችን ዘመን ሁሉ መጠየቅ አለብን፡፡
ይቅርታ የምንጠይቀው ስለምናውቃቸው /ስለምናስተውላቸው/ ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ስለማናስተውላቸውም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ «ይቅር በለን» ስንል እኛ ካስተዋልናቸው መንገዶች ውጪ በብዙ መልኩ እርሱን እንደምንበድል አስበን ተማጽኗችን ስለነዚህም መሆን አለበት፡፡
ስለዚህ ለጸሎት ከመቆማችንና የጌታን ጸሎት ከመጸለያችን በፊት የበደሉንን ይቅር እንዳልን እርግጠኛ መሆን አለብን እኛ የበደሉንን ይቅር እንዳልን ልንል ነውና፡፡
«እኛንም በደላችንን ይቅር በለን» ስንልም ከላይ ያየናቸውን ነገሮች ሁሉ እያሰብን፤ ይቅር ሊለን የወደደ አምላካችንንም እያመሰገንን መሆን አለበት፡፡ በእውነት ይህንን ጸሎት የምንጸልየው በዚህ መልኩ ነውን? ካልሆነ ልምምዱን ዛሬውኑ እንጀምረው ፡፡ ይህንን ማድረግ እንችል ዘንደ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን፡፡
https://telegram.me/EOTC2921
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
4 374
#ገብርኤል_ማን_ነው?
🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾
#ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን
ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን
አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ
ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ”
እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
#ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው
ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ
👉*ገብርኤል ነው፡፡*
የአሸናፊና የኃይል መልአክ
*ገብርኤል ነው፡፡*
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
*ገብርኤል ነው፡፡
🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📙 ቅዱሳት መጻሕፍትን በ PDF እና መንፈሳዊ መተግበሪያዎችን እንዴት ላግኝ ወይስ ከየት ላምጣ ብለው ፈልገው ያውቃሉ 🤔🤔
በ👉 https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw ቻናል አዳዲስና ቆየት ያሉ PDF መጽሐፍቶችን እንዱሁም የብራና መጽፍቶችንና መተግበሪያዎችን ያቀርባል!
ይቀላቀሉ👇👇
👉 https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
▰▰▰
#አገልግሎቱን_ለመደገፍ ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ!! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
👆SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

✅✞ሰላም ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች፤ እነሆ ለእናንተ ይጠቅማል፤ ያስተምራል ያልነውን የመጽሐፍ ትረካ ዛሬም አመጣንላችሁ።
✅✞ደራሲ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ ከዚህ በፊት ያቀረብንላችሁን እመጓ መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ ለማኅበረ ቅዱሳን እንዲውል ማበርከታቸው ይታወቃል። በእውነት ለመምህራችን ከዚህም በላይ የሚያገለግሉበት ጥበብና ማስተዋል ከሙሉ እድሜና ጤና ጋር እግዚአብሔር አምላክ ይስጥልን። አሜን
https://t.me/EOTC2921
#ኢትክሥት_ወይትንግር_ስመ_ዝጎራ_እስመ_አኮ_መካነ_ኁከት_ወነጎርጎር_ዘእንበለ_መካነ_ጸሎት_ወአርምሞ።"
[ይህ ተራራ የጸሎትና የአርምሞ እንጂ የግርግርና የወረት አይደለምና ስሙን አትግለጸው።]
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯