የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Kanalga Telegram’da o‘tish
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Ko'proq ko'rsatish4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
4 374
#ስምህ_በሁሉ_ተመሰገነ
ስምህ በሁሉ ተመሰገነ፣
ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ፣
አንተን ማወደስ ያስደስተናል፣
ስምህን ማክበር ግብራችን ሆኗል።
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
አምላክ ተመስገን በሰማያት፣
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት፣
ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ፣
አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ፡፡ /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
በምግብ እጦት ብንሰቃይም፣
ማኅሌትህን አናቋርጥም፣
የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም፣
እንዘምራለን ለአምላኝችን ስም። /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
ሰማዩ ዝናብ ደመና ሲያጣ፣
ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም፣
ቸርነትህን እንጠብቃለን፣
ከአንተ ደጅ አምላክ የት እንሄዳለን፣
ቸርነትህን እንጠብቃለን፣
ከአንተ ደጅ ጌታ የት እንሄዳለን። /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
አምላክ ተመስገን በሰማያት፣
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት፣
ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ፣
አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ፡፡ /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
4 374
🌾🕊✞ #እውነተኛው_ሰላም ✞🕊🌾
እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው(2)
አርዳኝ አልናወፅ እለምንሃለሁ(2)
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
ሀጢያቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል፣
ካንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል፣
ወዳንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለሁ፣
እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ለቅዳሴው ጸሎት ዘውትር እንዳልተጋሁ፣
ባደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ፣
ተሰነካክዬ ወድቄያለሁና፣
እርዳኝ አማኑኤል በሐይማኖት ልፅና።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
አይኔ እንባን ያፍስ ላልቅስ ስለሀጥያቴ፣
የንስሃ ትሁን ቁሪዋ ህይወቴ፣
በመዳኔ ሰዓት በዛሬዋ ዕለት፣
ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ካንተ ፊት።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ጌታ ሆይ ፀፀቴን እንባዬን ተቀበል፣
አባትሽ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል፣
ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መተህብኝ፣
በርህን በመዝጋት ከደጅ አታስቀረኝ።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
4 374
#ዝሙት_የስጋና_የነፍስ_በሽታ_ነው!!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
☞አሁን ባለንበት ዘመን በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙት ነው። የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱም ሴት ልጅ የሚፈልግበት የተፈጥሮ ስጦታ አለው ። ቅዱስ ጳውሎስ" ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን" ( 1ኛ ቆሮ 14፥40) እንዳለው ማንኛው ሰው ተፈጥራዊ ስሜት ይንሮው እንጂ እንደ እንስሳ ሳይሆን በስርዓት መሄድ ይኖርበታል ። አንድ ሰው በሂወቱ
ሃላፊነት ካልወሰደ በስተቀር ማንም ሃላፊነት ሊወስድለት አይችልም።
ወንዱ ይሁን ሴቷ የእግዚአብሔር ሕግ ከማስቀደም ይልቅ ፋሽን እየተባለ ወንዱ
በየቀኑ ሴቶችን እንደ ልብስ እየቀያየረ ፣ ሴቷም በየቀኑ ወንዶች እንደ ልብስ
እየቀያየረች ወደ ሞት ይነዳሉ። ይህ የዝሙት መንፈስ የተጠናወተበት ሰው
በስጋው ይሁን በነፍሱ የረከሰና የድያብሎስ መኖርያ ይሆናል።
አላስተዋልም እንጂ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ሥጋውን ቆርሶ ደሙን
አፍስሶ በዋጋ የገዛን በመሆናችን በራሳችን ላይ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ የማድረግ ስልጣን የለንም። ሰለዚህ እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፡፡(1ቆሮ 3፥16)
☞ታድያ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናችሁ ከተባልን የእግዚአብሔር መንፈስ
መኖርያ እንሆን ዘንድ ከዝሙት መራቅ አለብን። አለበለዚያ ንስሐ ሳንገባ
በዝሙት ተጠምደን የምንኖር ከሆንን ግን ነፍሳችን ከእግዚአብሔር ፀጋ ተራቁታ ወደ ሲኦል ትገባለች። ዝሙት የነፍስና የስጋ በሽታ መሆኑን የአምላክ ቃል እንዲህ ብሎ ያስተምረናል፦
☞ " ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን
ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ፡፡ ( 1ኛ ቆሮ 3:17)
#መፅሐፍ_ቅዱስ_ስለ_ዝሙት_እንዲ_ይለናል፦
☞ " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል "( ማቴ 5፥32)።
☞ " ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት
መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና" ( ማቴ 15፥19)።
☞ " ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ
ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ
ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና
ይስጣችሁ "( ሐዋ.ሥራ 15፥28-29)።
☞ " በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥
በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን ( ሮሜ 13፥13)።
☞ " በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት
ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና (1ኛ ቆሮ 5፥1)።
☞ " መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው " ( 1ኛ ቆሮ 6:13)።
☞ " ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤
ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል" ( 1ኛ ቆሮ 6:18)።
#ታድያ_ምን_እናድርግ????
" እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ " (ራእ.ዮሐ 2፥10)። ይህ የህይወት አክሊል የሚገኘው በፆም ፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ ንስሐ ገብተን በቅዱስ ቁርባን መኖር፣ አስራት በኩራት በማውጣት ስንኖር ነው። ቅዱስ አምላካችን በማቴ 6፥33 ላይ " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" እንዳለው በምግባር በሃይማኖት ፀንተን ስንኖር የፈለግነው እንደሚሰጠን በተስፋው ቃል እንኖራለን።
☞እህቴ ሆይ ከላይ በማቴ 6:33 የተጻፈውን ስትፈፅሚ አምላካችን ሌላው
ይጨመርላችኋል እንዳለን ከዝሙት ለመራቅ፣ ለመተጋገዝና ለመረዳዳት፣ ዘር
ለመተካት በአጠቃላይ ለትዳር የሚሆንሽ ወንድ ልጅ ላንቺ ይሰጥሻል።
☞ወንድሜ ሆይ ከላይ በማቴ 6፥33 ላይ የተጻፈውን ስተፈፅም አምላካችን ሌላው
ይጨመርላችኋል እንዳለን ከዝሙት እንድትርቅ፣ የምትረዳህና ዘር ለመተካት
በአጠቃላይ ለትዳር የምትሆንህ ሴት ልጅ ላንተ ይሰጠሃል።
🙏ንስሐ ገብተን የአምላካችን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን እንቀበል ዘንድ
አምላካችን ይፍቀድልን🙏(ዮሐ 6፥53-56)!!!
•✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዘላለሙ አሜን ✞•
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #ፍቅር_እስከ_መቃብር
ክፍል_፴፭_35
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #ጎሐ_ጽዮን
ክፍል_፴፬_34
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #ይሁንና_በዛብሽ
ክፍል_፴፫_33
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #አባ_አለም_ለምኔ
ክፍል_፴፩_31
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #የበዛብህ_ደብዳቤ
ክፍል_፴_30
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #የንጉስ_ግብር
ክፍል_፳፰_28
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #አዲስ_አበባ
ክፍል_፳፯_27
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #የሰብለ_መታሰር
ክፍል_፳፮_26
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #ስለ_ሰብለ_መታጨት
ክፍል_፳፭_25
t.me/EOTC2921
