የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Kanalga Telegram’da o‘tish
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Ko'proq ko'rsatish4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
4 374
❤️ አዳም ማለት ያማረ፣ የሰመረ፣ የተዋበ፤ እንደ ረዓይት /እጅግ በጣም ረዥም የነበሩ/ ሳይረዝም፤ እንደ ድንክ ሳያጥር የተፈጠረ፤ ይህ ቀረህ የማይባል እጅግ መልከ መልካም ማለት ነው። አንድም ዘተሰገወ እምድር - ከመሬት የተገኘ /ሰው የሆነ/ ማለት ነው። አንድም “ሰብእ - ሰው” ይባላል። ሰብእ - ሰብአ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ሰባት ማለት ነው። ከሰባት ባሕርያት የተገኘ ስለሆነ ሰብእ ወይም ሰው ተብሏል። ሰባቱ አዳም የተፈጠረባቸው ባሕርያት ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ማለትም ሌሎች ፍጥረታት የተፈጠሩባቸው እሳት፣ ውሃ፣ ነፋስና መሬት ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ ባሕርያተ ነፍስ /ከሌሎች ፍጥረታት በተለይም ከእንስሳት የሚለዩት/ ለባዊነት /አስተዋይነት/፣ ነባቢነት /ተናጋሪነት/ እና ሕያውነት /ዘላለማዊነት/ ናቸው።
💚 እንዲሁም እጓለ እመሕያው ይባላል። እጓል ማለት ልጅ፣ እመ /እም/ ማለት እናት ማለት ነው። ልጅ የተባለ እራሱ አዳም፣ እናት የተባለ የአዳም አስገኚ እግዚአብሔር “አንተ አቡነ ወአንተ እምነ አንተ አባታችን አንተ እናታችን ነህ” /እንዳለ ቅዱስ ያሬድ/ እናት ሁሉን እንደምታስገኝ ሁሉ እግዚአብሔርም የሁሉ መገኛ ነው። ስለዚህ እጓለ እመሕያው ማለት ከእግዚአብሔር የተገኘ ልጅ ማለት ነው። አንድም ሕያው የተባለ መልአክ ነው መላእክትን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር የተገኘ ልጅ ሲለው፤ አንድም እጓል ልጅ፣ እመ /እም/ የተባለች ምድር፤ እናት ሁሉን እንደምታስገኝ ሁሉ ምድርም ሁሉን ታስገኛለች “ምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ - ምድር ፋሬዋን ትሰጣለች” እንዲል፤ ሕያው የተባለ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እጓለ እመሕያው ማለት ሕያው እግዚአብሔር ከፈጠራት ምድር የተገኘ ልጅ ማለት ነው።
💛 እግዚአብሔር አምላክ “ንግበር ሰብአ” ባለ ጊዜ ነፍስና ሥጋው በአንድ ጊዜ ተዋሕደው ተፈጥረዋል። “ወገብሮ እግዚአብሔር ለሰብእ እመሬተ ምድር ወነፍሐ ውስተ ገጹ መንፈሰ ሕይወት ወኮነ እጓለ እመሕያው - እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፣ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት።”
❤️ ሃያ አንዱን ፍጥረታት ከፈጠረ በኋላ እርሱን ሃያ ሁለተኛ አድርጎ በመጨረሻ ለምን ፈጠረው? የሚል ጥያቄ ብንጠይቅ የዚህ ምክንያቱ አንድ ሰው እቤቱ እንግዳ ሲጋብዝ አስቀድሞ የሚበላውን፣ የሚጠጣውን አዘጋጅቶ ነው እንጂ እንግዳው ከገባ በኋላ አይደለም ማዘጋጀት የሚጀምረው። እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔርም ለአዳም የሚያያስፈልገውን የሚበላውን፣ የሚጠጣውን፣ የሚገዛው፣ የሚነዳውን ሁሉ ካዘጋጀ በኋላ ፈጠረው።
💟 ሌሎችን እንስሳት ስንመለከት ሁሉም ጎንበስ ብለው የተፈጠሩ መሆናቸውን እናስተውላለን፤ ነገር ግን አዳምን ቀና አድርጎ ከሌሎቹ ለይቶ ፈጥሮታል። ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን፦
➣፩. አዳምን ገዢ፣ ሌሎችን ተገዢ ናችሁ ሲላቸው፤ አንድም አዳም ሞቶ፣ ፈርሶ፣ በስብሶ አይቀርም ከሞት በኋላ ትንሳኤ አለው፤ ሌሎችን ግን ፈርሳችሁ፣ በስብሳችሁ ትቀራላችሁ ሲላቸው እርሱን ቀጥ አድርጎ፣ እንስሳትን አጎንብሰው እንዲሄዱ አድርጓቸዋል። አዳም ቀና ማለት ብቻ ሳይሆን የሚቆምም የሚቀመጥም፤ የሚተኛ የሚነሳ አድርጎ ነው የፈጠረው። መቆሙ ሰማያዊ ነህ ሲለው፤ መቀመጡ ምድራዊ ነህ ሲለው ነው። በመተኛቱ በዚህ ዓለም መዋቲ መሆኑን፣ በመነሳቱ በወዲያኛው ዓለም የመነሳቱ ምልክት ነው።
➣፪. ደግ አባት የወለደው ልጁን ኩሎ ከመዳሩ በፊት ለኑሮ የሚያስፈልገውን ሁሉ እንዲያሟላለት እግዚአብሔርም አስቀድሞ የሚኖርበትን ዓላማ የሚበላውን የሚጠጣውን የሚገዛውን የሚነዳውን ሁሉ ፈጥሮ አዳምን አስገኘ።
➣፫. 10ቱ ቃላተ ኦሪት፣6ቱ ቃላተ ወንጌል፣ 5ቱ አዕማደ ምሥጢር (21) ይሆናሉ። እነዚህን የሚፈጽሙ ጻድቃን ሲበዙ፣ሲመሉ ዳግማዊ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ሊፈርድ የመምጣቱ ምሳሌ ነው።
➣አንድም፦ አዳም ፊደላቱ ሲቆጠሩ 144 ሲሆን ዳግማዊ አዳም ኢየሱስ የሚለው ፊደላቱ ሲቆጠሩ 144 ይሆናል።
#የሔዋን_ተፈጥሮ🙎♀
💚አዳም በተፈጠረ በስምንተኛው ቀን፣ በሶስት ሰዓት ሔዋን ተፈጠረች። “ወይቤ እግዚአብሔር ኢኮነ ሠናየ ለእጓለ እመሕያው ይንበር ባሕቲቶ አላንግበር ሎቱ ቢጸ ዘትረድኦ - አዳምን ብቻውን ይኖር ዘንድ አይገባውም ረዳትን እንፍጠርለት” ዘፍ. 2፥18 ዘይረድኦ- የሚረዳው ማለቱ ስለምን ነው? ቢሉ ልጅ በመውለድ፣ በአቅልሎ ክበደ ዋዕይ /በሀዘን ጊዜ በማጽናናት/ እንዲሁም እርሱ በሜዳ፣ እርሷ በጓዳ፤ እርሱ የአፍአውን /የውጪውን/፣ እርሷ የውስጡን በማከናወን ይረዳዳሉ።
💙 እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ተናግሮ ባልፈጸመው ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያሉ በየወገኑ ቢቆጥሩ ከእሑድ እስከ ዐርብ ያዘጋጀው ፍጥረት ፳፪ ይሆናል።
◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶
ይ🀄️ጥላል
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖
💚💛❤️️ ክፍል ፯ 💚💛❤️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞
🤵🦖🦉🦆🦓🐆🦒🐫
#የዕለተ_ዐርብ_ፍጥረታት
🐄🐑🐐🐂🐕🐈🐂🦋
https://t.me/EOTC2921
🍎 ዓርብ ዐረበ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ተካተተ ማለት ነው። ስለዚህ ዓርብ ማለት መካተቻ መደምደሚያ ማለት ነው። ምዕራብ ስንል መግቢያ፣ መጥለቂያ /ለምሳሌ የፀሐይ መግቢያን ምዕራብ የምንለው ለዚህ ነው/ ማለት ሲሆን ዐርብ ሲባልም ተመሳሳይ ነው። ከኢየሩሳሌም ምዕራባዊ አቅጣጫ ያሉ ሀገራት የዐረብ ምድር ይባላሉ። ዐርብ የተባለበት ምክንያት በዕለተ እሑድ መፈጠር የጀመሩት ፍጥረታት ተፈጥረው ያበቁበት /የተካተቱበት/ ቀን ስለሆነ ዐርብ ወይም መካተቻ ተብሏል። ዕለተ ዓርብ ለሥነ ፍጥረት ስድስተኛ፣ ለጥንተ ቀመር አምስተኛ፣ ለጥንተ ዮን አራተኛ ቀን ነው።
💚 በዚህ ቀን እግዚአብሔር “ወይቤ እግዚአብሔር ለታውፅዕ ምድር ዘመደ እንስሳ ወዘይትሐወስ ወአራዊተ ምድር በበዘመዶሙ - እግዚአብሔር አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥራታትን እንደ ወገኑ እንስሳትን ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ።” ዘፍ.1፥24 በዚህን ጊዜ ሶስት ፍጥረታት በየወገናቸው ተፈጥረዋል። እነዚህም ልክ እንደ ሐሙስ ፍጥረታት በእግር የሚሽከረከሩ፣ በልብ የሚሳቡ እና በክንፍ የሚበሩ ናቸው። ከዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት የሚለዩት የሐሙስ ፍጥረታት ከባሕር የተገኙ ሲሆን የዓርብ ፍጥረታት ደግሞ ከየብስ ወይም ከመሬት የተፈጠሩ ናቸው። የሐሙስና የዓርብ መሆናቸውን የምንለየውም በአኗኗራቸው ሲሆን የሐሙስ ፍጥረታት በባሕር /aquatic animals/፤ የዓርብ ፍጥረታትም በየብስ / terrestrial animals / ይኖራሉ። ስለምን በባሕርና በየብስ አድርጎ ፈጠራቸው? ቢሉ አምላከ ባሕር ወየብስ ነኝ ሲል ነው። በዚህ ቀን በአራተኛ አዳምን ፈጥሯል። ይህንን በኋላ እንመለስበታለን።
#ከዐርብ_ፍጥረታት_ምን_እንማራለን?
↪️በዕለተ ሐሙስ ምስጢረ ጥምቀትን እንደተማርን ሁሉ ከዕለተ ዓርብ ፍጥረታት ደግሞ ምስጢረ ትንሳኤ ሙታንን ተምረናል። ሰው ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ መልካም የሰሩ በመላእክተ ብርሃናት አማካኝነት በገነት፣ ክፉ የሰሩ ደግሞ በመላእክተ ጽልመት አማካኝነት ወደ ሲዖል ተወስደው በእነዚህ ዓለማተ መሬት ይቆያሉ። በዕለተ ምጽዓት ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ መለኮት በክበበ ትስብዕት ሲመጣና “ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም - ሙታን ተነሱ!” ባለ ጊዜ ፍጥረታት መነሳት ይጀምራሉ። የዕለተ ዓርብ ከየብስ በተፈጠሩት ፍጥረታት ልክ ሶስት ጊዜ ንፍሐተ ቀርን ይደረጋል።
💛 በልብ መሳብ የመጀመሪያ ንፍሐተ ቀርን “በቀዳሚ ንፍሐተ ቀርን ይትጋባእ ጸበለ ሥጋ ዘተዘርወ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም - በመጀመሪያ አዋጅ በዓለም ዙሪያ የተበተነ የሥጋ ዘር ይሰበሰባል።”፤ በእግር መሽከርከር የሁለተኛ ንፋተ ቀርን “ወበዳግም ንፍሐተ ቀርን ይሰፈያ አዕፅምት ምስለ ሥጋ ወይከውን በድነ ፍጹመ ዘእንበለ አንሳሕስሖ ወኢተሐውሶ እስከ ጊዜሁ - በሁለተኛ አዋጅ ሙታን ወደ ቀደመ መገናኛው ይመለሳል /ሥጋ ከአጥንት ጋር ይገናኛል/ ያለመንቀሳቀስ ያለመለወጥ ፍጹም በድን ይሆናል።”፣ በክንፍ መብረር የሶስተኛ ንፋተ ቀርን ምሳሌ ነው። “ወበሳልስ ንፍሐተ ቀርን ይትነስኡ ሙታን ከመ ቅጽበተ ዓይን ጻድቃን ወኃጥአን እንዘ ይጸውሩ ምግባራቲሆሙ እምዲበ ምድር ዘተለዎሙ እመሂ እኩየ ወእመሂ ሠናየ - በሶስተኛው አዋጅ ሙታን እንደ ዓይን ጥቅሻ ይነሳሉ። /ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ/ ስለዚህ በልብ መሳብ የመሰብሰብ፣ በእግር መሽከርከር የፍጹም በድን መሆን፣ በክንፍ መብረር የትንሳኤ ምሳሌ ነው።
➣ አንድም በልብ መሳብ የፍጹም በድን የመሆን ምሳሌ፣ በእግር መሽከርከር የትንሳኤ /የመነሳት/ ምሳሌ፣ “ወበደሃሪ ንፍሐተ ቀርን ይትነስኡ ሙታን እንዘ ይትከነዩ - የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን” 1ኛ ቆሮ. 15፥52 በክንፍ መብረር የተመስጦ “ከዚህ በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፣ ጌታን በአየር ሆነን ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤” 1ኛ ተሰ. 4፥17
❤️ ንፋተ ቀርን ማለት እንደ አባቶቻችን ትርገሜ መለከት ተይዞ እንደ ጥሩንባ ይነፋል ማለት አይደለም። ይህ ማለት አንድም አዋጅ ሲታወጅ ማለትም እግዚአብሔር “ንቃህ መዋቲ ዘትነውም!” ብሎ ሲናገር ማለት ነው። አንድም እግዚአብሔር “ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም!” ሲል መላእክት በመጀመሪያ አዋጅ “ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለሙታን” ብለው በታላቅ ድምጽ ያሰማሉ፣ በሁለተኛ አዋጅ “ቅዱስ ኃያል ዘያነቅሖሙ ለሙታን” ፣ በሶስተኛው አዋጅ “ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘያነቅሖሙ ለሙታን” ብለው ስለሚያሰሙ ነው። ቅዱስ ጳውሎስም የእግዚአብሔር አዋጅ በመላእክት ቃል እንደሚታጀብ ሲናገር “እስመ ይኤዝዝ እግዚእነ ምስለ ቃለ ሊቀ መላእክት ወንፍሐተ ቀርን ዘእግዚአብሔር -ጌታ እራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳል” ይላል። 1ኛ ተሰ.4፥16
💟 በባሕር የተፈጠሩት ደግመው በየብስ መፈጠራቸው በጥምቀት የወለድኳቸውን በትንሳኤ እወልዳችኋለው ሲል ነው። ይህም ማለት ዳግም ሲመጣ በትንሳኤ ዘለክብር አስነሳቸዋለሁ ሲል ነው። “ወዘንተ ባሕቱ አእምሩ ኩልክሙ ከመእለ ተጠመቅነ በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ውስተ ሞቱ ተጠመቅነ ወተቀበርነ ምስሌሁ ውስተ ጥምቀት - በሞቱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከትንሳኤው ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?” ሮሜ. 6፥6
#የሰው_ልጅ_ተፈጥሮ 👴
💚ሥላሴ በዕለተ ዓርብ በነግህ “ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ - ሰውን በመልካችንና በምሳሌያችን እንፍጠር” በማለት አራቱን ባሕርያተ ሥጋና ሶስቱን ባሕርያተ ነፍስ አዋሕደው አዳምን በማዕከለ ምድር በቀራንዮ /ኤልዳ/ ፈጠሩት። አዳም ሲፈጠር የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ነበር። ለምን በማዕከለ ምድር በኤልዳ ፈጠሩት? ቢሉ የአዳም ባሕርይ ከሌሎች ልዩ ሲሆን ይኸውም ባሕርየ መልአክ - የመልአክ ባሕርይ እና ባሕርየ እንስሳ - የእንስሳ ባሕርይ ስላለው ማዕከላዊ ነህ ሲለው ነው። አዳም እንስሳዊ ባሕርያት አሉት ማለት መብላት፣ መጠጣት፣ መተኛት፣ መሞት …ወዘተ አሉት ማለት ሲሆን መልአካዊ ባሕርያት ደግሞ ማስተዋል፣ መናገር፣ ዘላለማዊነት /ሞቶ አለመቅረት/ ባሕርያት አሉት ማለት ነው።
💛በመልካችንና በአምሳላችን እንፍጠር ማለታቸው ለሥላሴ እንደ ሰው ግዙፍ የሆነ አካል ባይኖራቸውም ረቂቅ በሆነው አካላቸው ላይ በሰው ላይ ያለው መልክ አላቸውና ነው። አንድም ሥላሴ ዘላለማውያን ስለሆኑ አዳምም የማትሞት ሕያዊት የሆነች ነፍስ ስላለው ነው። አንድም በአንድነትና በሶስትነት ይመስላቸዋልና ነው። ሥላሴ ለባውያን፣ ነባብያን፣ ሕያዋን እንደሆኑ ሁሉ አዳምም ነባቢት፣ ለባዊት፣ ሕያዊት ነፍስ አለው። ሥላሴ ለባውያን፣ ነባብያን፣ ሕያዋን ቢሆኑም ሶስት አማልክት አይባሉም። እንደዚሁ ሁሉ አዳምም ለባዊ፣ ነባቢ፣ ሕያዊ ስለሆነ ሶስት ሰው አይባልም። አንድ ሰው ይባላል እንጂ።
ይ🀄️ጥላል
4 374
❤️ የዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት ብዛታቸው ሶስት ሲሆን በሶስት ወገን ሆነው መፈጠራቸው የሶስቱ ዐበይተ ነገድ /ታላላቅ ነገዶች/ ምሳሌ ሲሆኑ እነዚህ ሶስቱ ነገድ የሚባሉት ነገደ ሴም፣ ነገደ ያፌት፣ ነገደ ካም ናቸው። ነገደ ሴም የነገስታት ወገን፣ ነገደ ያፌት የካህናት ወገን፣ ነገደ ካም የምዕመናን ወገን ናቸው። ሶስቱንም ፍጥረታት ከባሕር እንደፈጠራቸው ሁሉ ጥምቀት ለሶስቱም ነገድ በእኩል የተሰጠች የመሆኗ ምሳሌ ነው። አንድም ጥምቀተ ክርስትና በሶስቱ የስላሴ ስሞች የመፈጸሙ ምሳሌ ነው። “ወከመ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ - በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው።” ማቴ. 28፥19
እግዚአብሔር አምላክ የፈጠራቸውን ፍጥረታት ዘርዝሮ መናገር አይቻልም።
"እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት። ሥራህ ግሩም ነው።" መዝ. 65፥3 እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ከመገረም ውጭ ማንስ ተመራምሮ ሊያስበው ይችላል❓
💟 በዕለተ ሐሙስ ከተፈጠሩት ፍጥረታት መካከል በግዝፈታቸው ከሚታወቁትና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሦስት ቦታ ላይ ብቻ ስማቸው የተጠቀሱትን ብሔሞትና ሌዋታንን መጥቀስ ይቻላል። እነዚህን ፍጥረታት ሳይንስ እስካሁን ያላወቃቸውና እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከመታየት በጥበቡ የሰወራቸው ፍጥረታት ናቸው።
💙 እነዚህን ግዙፍ ፍጥረታትን ለማየት የበቁና ጥርሳቸውንም የቆጠሩ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ አባት አቡነ ዘርዐብሩክ ዘጎጃም ናቸው።
🍎ሰለ ብሔሞትና ሌዋታን የተወሰነ መረጃ የሚገኘው፤(በገድለ አቡነ ዘርዐ ብሩክ ዘጎጃም፣ በመጽሐፈ አክሲማሮስ ዘኤጲፋንዮስ ዘኀሙስ፣ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ)
💙 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስማቸው ተጠቅሷል። (ዕዝ.ሱቱኤል 4÷49-51፣ ሄኖክ 16፥12፣ ኢሳ.27፥1) ይመልከቱ።
💟ሌላው በዕለተ ሐሙስ ከተፈጠሩ ፍጥረታት በእግር ከሚሽከረከሩት በክንፍ ከሚበሩት አዕዋፍ መካከል #ከርከቤደል የምትባል ወፍ አለች። ይህቺም ወፍ በቀኝ ማኅጸኗ ዕንቁ በግራ ማኅጸኗ አዕዋፍን ያለ ወንድ ዘር ታስገኛለች። ይህቺም ንጽሒት እም አዕዋፍ ተብላ የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት።
➣የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ የሆኑት ሁለቱ አዕዋፍ
፩. #ከራድዮን:- ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በዐርብ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
፪. #ፊንክስ አምስት መቶ ዓመት የሚኖር፦ መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘኤጲፋኒዮስ ዘሐሙስና ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ተመልከቱ እርሱ ግን የቅዱስ ኤጲፋኒዮስን ከርከቤዴል ዖፈ ብርጋና ብሏታል። በተጨማሪም ኪዳነ ወልድ ክፍሌን ይመልከቱ።
◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶
ይ🀄️ጥላል
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖
💚💛❤️ ክፍል ፮ 💚💛❤️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞
🐠🐬🐳🐋🦈🐊🦏🦛🐸
#የዕለተ_ኀሙስ_ፍጥረታት
🦜🦃🦢🦕🦆🐗🐍🐡🐠
https://t.me/EOTC2921
💚 ሐሙስ የሚለው ሐመሰ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን አምስት አደረገ ማለት ነው። ለሥነ ፍጥረት አምስተኛ ቀን ስለሆነ ሐሙስ ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንደተመለከትነው ረቡዕ ለሥነ ፍጥረት አራተኛ፣ ለቀመር ሁለተኛ፣ ለጸሐይ /ለጥንተ ዮን/ አንደኛ ቀን ነው ብለናል። በዚሁ መሰረት ሐሙስ ለሥነ ፍጥረት /ለጥንተ ዕለት/ አምስተኛ፣ ለቀመር ሶስተኛ፣ ለፀሐይ /ለጥንተ ዮን/ ሁለተኛ ቀን ነው። በዚህ ቀን እግዚአብሔር “ለታውጽዕ ማይ ዘይተሐወስ ዘቦ መንፈሰ ሕይወት ወአዕዋፍ ዘይሰርሩ መልዕልተ ምድር ወመትሕይተ ሰማይ ወኮነ ከማሁ - እግዚአብሔር አለ፦ ውሃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾችን ታስገኝ፣ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ይብረሩ።” ዘፍ. 1፥20
💛 “ወአመ አዘዛ እግዚአብሔር ለባሕር አውጽአት ኩሉ ዘመደ እንስሳ ወአራዊተ ወአዕዋፈ አበይተ ወደቃቀ ዘአልቦ ሁልቊ - እግዚአብሔርም ታላላቅ አንበሪዎችን ውሃይቱ እንደወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ እንደወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ።” ዘፍ. 1፥21 በዚህን ጊዜ፦
↪️በእግር የሚሽከረከሩ፣
↪️በልባቸው የሚሳቡ፣
↪️በክንፋቸው የሚበሩ በየወገኑ በየወገኑ አድርጎ ሶስት ፍጥረታትን በደመ ነፍስ ሕያዋን የሆኑ ከባሕር ፈጠራቸው። ❤️ እነዚህ ፍጥረታት ከተፈጠሩ በኋላ ሁሉም በባሕር ውስጥ አይውሉም። በባሕር ፀንተው የሚኖሩ አሉ፤ ከባሕር ወጥተው በየብስ ውለው በባሕር ተመልሰው የሚያድሩ አሉ፤ ከተፈጠሩም በኋላ በርረው በየብስ የቀሩ አሉ። እንዲሁም በእግር የሚሽከረከሩ፣ በልብ የሚሳቡ፣ በክንፍ የሚበሩ አሉ።
➣እነዚህ አምሳልና መርገፍ ናቸው፤ ማለትም ምሳሌ አላቸው። ምሳሌነታቸውም፦
፩. #በባሕር_ውስጥ_ጸንተው_የሚኖሩት
➣በእምነታቸው ጸንተው፣ እግዚአብሔርን አምነው የሚኖሩ ምሳሌ፣
➣አንድም በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው በትዳር ተወስነው በሀብት በንብረታቸው መልካም ስራ እየሰሩ ማለትም ለቤተ እግዚአብሔር አንጽፈው፣ መስዋዕት አቅርበው፣አስራታቸውን /ከደሞዛቸው ከአስር አንድ / በኩራታቸውን /ከሰውና ከእንስሳ በመጀመሪያ የተገኘውን ለቤተ እግዚእብሔር ለግሰው/ ቀዳማያት/ከሰብላቸው፣ ከአዝርዕታቸው ቀዳሚውን ሰጥተው/ የሚኖሩ በሕግ ጋብቻ ተወስነውና ጸንተው ሚኖሩ ሰዎች ምሳሌ፣
➣አንድም ክፉ ግብራችንን አንተውም ብለው በመስረቅ፣ በመቀማት፣ ቋንጃ በመቁረጥ፣ ነፍስ በማጥፋት፣ በመዘሞት ጸንተው የሚኖሩ የኃጥአን ምሳሌ ናቸው።
፪. #ከባሕር_ወጥተው_የቀሩት፦
➣ወምንት ይበቁኦ ለሰብእ ለእመ ኩሉ ዓለመ ረብኀ ወነፍሶ ሐጒለ - ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?”
በሚለው ቃል ተማርከው ይህን ዓለም በመናቅ ከዘመድ ባዳ፣ ከሀገር ምድረ በዳ ከሕገ ሰብእ ሕገ መላዕክት፤ ከተግባረ ስጋ ተግባረ ነፍስ ይሻለናል ብለው ይህን ዓለም ንቀው በገዳማት በአድባራት ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ የሌሊት ቁሩን የቀን ሐሩር፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን ታግሰው ዳባ ለብሰው፣ ዳዋ ጥሰው፣ ከገደል ወድቀው፣ ከዛፍ ስር ተጠግተው የሚኖሩ የመናንያን መነኮሳት ምሳሌ ነው። ዕብ. 11፥35
፫. #በባሕርና_በየብስ_ወጣ_ገባ_የሚሉ
➣አንድ ጊዜ ወደ ገዳም፣ ዕጸበ ገዳም ሲያስቸግራቸው እንድ ጊዜ ወደ ዓለም ወጣ ገባ እያሉ የሚኖሩ የመነኮሳት ምሳሌ፣
➣አንድ ጊዜ ወደ ሃይማኖት አንድ ጊዜ ወደ ክህደት የሚሄዱ የምዕመናን ምሳሌ፣ (አስሩ ማዕረጋት /አስሩ ማዕረጋት የሚባሉት ጽማዌ፣ ልባዌ፣ ጣዕመ ዝማሬ፣ ሑሰት፣ ፍቅር፣ አንብዕ፣ ንጻሬ መላዕክት፣ ተሰጥሞ፣ ከዊነ እሳት፣ ነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ/ ደርሰው ተመልሰው አቡነ ዘበሰማያት ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ - አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር …በደላችንን ይቅር በለን/ ብለው የሚለምኑ ሰዎች ምሳሌ ነው።
↪️እንዲሁም ከእነዚህ ፍጥረታት ውስጥ በእግር የሚሽከረከሩ፣ በልብ የሚሳቡ እና በክንፍ የሚበሩ አሉ። ይኸውም፦
➛በእግር መሽከርከር የመንግስት ምሳሌ፣
➛በልብ መሳብ የክህነት ምሳሌ፣
(ክህነት የዐቢ እመንግስት - ክህነት ከመስፍንነት ይበልጣል ምሳሌ 26፥7
➛በክንፍ መብረር የጥምቀት ምሳሌ ነው። አንድም
➛በእግር የሚሽከረከሩ የመነኮሳት፣
➛በልብ የሚሳቡ የሕጋውያን /በቅዱስ ጋብቻ የሚኖሩ/ የሰብኣ ዓለም ምሳሌ፣
➛በክንፍ የሚበሩ የሰማዕታት ምሳሌ ናቸው።
#ከዕለተ_ሐሙስ_ፍጥረታት_ምን_እንማራለን?
💚በአጠቃላይ ከእለተ እሑድ ፍጥረታት ምስጢረ ስላሴን፣ ከእለተ ሰኑይ ፍጥረታት ምስጢረ ሥጋዌን፣ ከዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት ሃይማኖትንና ስነ ምግባርን፣ ከዕለተ ረቡዕ ፍጥረታት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደተማርን ሁል ከዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት ምስጢረ ጥምቀትን እንማራለን።
💛ከላይ እንደጀመርነው የዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት ከባሕር ቢፈጠሩም ሁሉም በባሕር ውስጥ ጸንተው አይኖሩም። የተወሰኑት በባሕር ጸንተው የሚኖሩ አሉ። ከባህር ከወጡ መኖር የማይችሉ ለምሳሌ የዓሳ ዘር በሙሉ፤ ከባሕር ወጥተው በዛው የቀሩ አሉ፤ አንድ ጊዜ ባሕር አንድ ጊዜ የብስ እያሉ የሚኖሩ አሉ።
#በባሕር_ጸንተው_የሚኖሩ፦ በጥምቀተ ክርስትና አምነው ተጠምቀው የሚኖሩ ምሳሌ ናቸው። “ዘኢተጠምቀ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ ኢይክል ርዕዮታ ለመንግስተ እግዚአብሔር - ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያያት አይችልም።’’ ዮሐ፤ 3፣5 “ዘአምነ ወዘተጠምቀ ይድኅን ዘኢአምነ ወዘኢተጠምቀ ይደየን - ያመነ የተጠመቀ ይድናል፣ ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል።” ማር. 16፥16
#ከባሕር_ወጥተው_የቀሩት፦ በጥምቀተ ክርስትና አምነው ተጠምቀው ሲያበቁ በተለያየ ምክንያት ማለትም በፈተና፣ በምንፍቅና፣ በክህደት፣ ለዚህ ዓለም ባለጸግነት ብለው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ያገኙትን የእግዚአብሔር ልጅነታቸውን፣ የተዋሕዶ ሃይማኖታቸውን የሚያጡ ሰዎች ምሳሌ ናቸው።
#አንድ_ጊዜ_ከባሕር_አንድ_ጊዜ_በየብስ_የሚኖሩ፦ በጥምቀት ያገኙትን የእግዚአብሔር ልጅነት በደንብ ተረድተው ያልያዙ፤ ሲላቸው በሃይማኖት ሲያሻቸው በክህደት የሚኖሩ፤ ባካና ልቡና ይዘው እንደ ሁኔታው የሚቀያየሩ፤ በደግ ጊዜ በሃይማኖት የሚኖሩ፣ ፈተና ሲመጣ ፈተናውን ለማለፍ በሚል ሰበብ የሚክዱ ሰዎች ምሳሌ ናቸው።
ይ🀄️ጥላል
4 374
️🌟✨️ #መገብተ_ከዋክብት ✨️🌟
➣ከከዋክብት መካከል ዕለትን፣ ወርኅን እና ወቅትን የሚመግቡ፣ የሚመሩ ከዋክብት ተሹመዋል። የእነዚህን ከዋክብት ስማቸውን ከዚህ ቀጥሎ እንመለለከታቸዋለን።
፩. #መገብተ_ዕለት፦ መገብተ ዕለት የሚባሉት ከዋክብት ብዛታቸው በሳምንቱ ዕለታት ልክ ሰባት ናቸው። እነዚህም ሸምሽ፣ ቀመር፣ መሪህ፣ መስተሪህ፣ ዙሀል፣ አጣርድ እና ናርድ ይባላሉ። እያንዳንዳቸው እንደ ቅደም ተከተላቸው ከሰኞ እስከ ዐርብ ያሉትን ቀናት ይመግባሉ። ለምሳሌ ሸምሽ ሰኞን፣ ቀመር ማክሰኞን …ናርድ አርብን ይመግባሉ።
፪. #መገብተ_አውራኅ፦ እነዚህም በአስራ ሁለቱ ወራት ልክ አስራ ሁለት ናቸው። እነርሱም አልሐመል፣ አልሰውር፣ አልጃሙዛ፣ አልሸርጣን፣ አልሰአድ፣ አልሰንቡላህ፣ አልሚዛን፣ አልአቅረብ፣ አልቀውስ፣ አልዛዲፍ፣ አልደለው፣ አልሃት ይባላሉ። እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ ያሉትን ወራትን ይመግባሉ። ለምሳሌ አልሐመል መስከረምን፣ አልሰውር ጥቅምትን፣ … አልሃት ነሐሴን ይመግባሉ ማለት ነው።
፫. #መገብተ_ወቅት፦ እነዚህም ታላላቅ ከዋክብት ሲሆኑ በዚህም የተነሳ ሊቃነ ከዋክብት /የከዋክብት አለቆች/ ይባላሉ። የእነዚህ ቁጥርም በዓመቱ ውስጥ ባሉ ወቅቶች ልክ አራት ናቸው። በዓመት ውስጥ ያሉት አራቱ ወቅቶች የሚባሉት ክረምት፣ መፀው /መኸር ወይም መከር/፣ ሐጋይ /በጋ/ እና ፀደይ /በልግ/ ናቸው። አራቱ ሊቃነ ከዋክብት የሚባሉት ናርኤል፣ ብርክኤል፣ ምልኤል እና ኅልመልሜሌክ ናቸው።፡እነዚህም እያንዳንዳቸው አራቱን ወቅቶች በየተራ ይመግባሉ። መጽሐፈ ሄኖክ 28፥19 ይመልከቱ፤
➣እነዚህ ከዋክብት ማለትም መገብተ ዕለት ከዋክብት በየሳምንቱ፣ መገብተ ወርኅ ከዋክብት በየዓመቱ፣ መገብተ ወቅት ከዋክብት በየሶስት ወራቱ የሚመላለሱበትን ኆኅት /መስኮት/ አላቸው። እነዚህም መስኮቶች በምስራቅ በኩል ስድስት፣ በምዕራብ በኩል ስድስት ናቸው። ሄኖክ. 24፥8
#ከዕለተ_ረቡዕ_ፍትረታት_ምን_እንማራለን?
💚 በዕለተ ረቡዕ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንማራለን። ቤተክርስቲያን ስንል ሶስት ዓይነት ትርጉም ያለው ሲሆን እነዚህም የክርስቲያኖች መሰብሰቢያ የሆነው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ፣ የምእመናን አንድነቱ ወይም ስብስቡ /ማኅበረ ምዕመናኑ/ እና የእያንዳንዱ ምእመን ልቡና ቤተ ክርስቲያን ይባላል። “ወተሰምዩ አርድዕት ክርስቲያነ በአንጾኪያ ቀዲሙ - አርድት በመጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ” የሐዋ ሥራ 11፥27 ከሚለው ቃል የምዕመናን ስብስብ /ማኅበረ ምዕመናን/ ቤተ ክርስቲያን እንደሚባሉ ያሳየናል። “አንትሙሰ ኢታይምሩኑ ከመ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር - እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅድስ እንደሁናችሁ አታውቁምን?” 1ኛ ቆሮ. 3፥10 ከሚለው የእያንዳንዱ ምዕመን ልቡና ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ክርስቲያን እንደሚባል እንመለከታለን።
💛 ስለዚህ በዚህ ቀን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንማራለን ስንል በምእመናኑም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ሥርዓት እንማራለን ማለታችን ነው።
➣ፀሐይ ሁልጊዜ ሙሉ ስለሆነች የጻድቃን ምሳሌ ናት። ጻድቃን በምግባር በሃይማኖት ዘወትር ምሉዕ /ሙሉ/ ናቸው።
➣ጨረቃ አንድ ጊዜ ስለምትሞላ አንድ ጊዜ ስለምትጎድል የኃጥአን ምሳሌ ናት። ኃጥአን በምግባርና በሃይማኖት እንድ ጊዜ ሲሞሉ አንድ ጊዜ ሲጎድሉ ይኖራሉ። “ልቡ ለአብድ የሐፅፅ ከመ እንተ ወርኅ - የሃጢአተኛ ልብ እንደ ጨረቃ ሲጎድል ያድራል” እንዲል ሲራክ 43፥7
➣አንድም ፀሐይ የኃጥአን ምሳሌ፣ ጨረቃ የጻድቃን ምሳሌ፤ ጸሐይ ሁልጊዜ ምሉዕ እንደ ሆነች ሁሉ ኃጥአንም በክፉ ስራቸው፣ በክፉ ምግባራቸው፣ በክህደታቸው ምሉዓን ናቸው።
➣ጨረቃ አንድ ጊዜ ስትሞላ አንድ ጊዜ እንደምትጎድለው ሁሉ ጻድቃንም በኃጢአት አንድ ጊዜ ሲወድቁ ሌላ ጊዜ በንስሐ ሲነሱ ይኖራሉ። “ጻድቅሰ ስብዐ ይወድቅ ስብዐ ይትነሳእ - ጻድቅ ሰው ሰባት ጊዜ ይወድቃል ሰባት ጊዜ ይነሳል:፡” ምሳሌ. 24፥6
❤️ በዕለተ እሑድ ከፈጠረው ብርሃን ወስዶ ለሰባት ከፍሎ የቀባቸው የሰባቱ ማዕርጋተ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው።
➣እነዚህም ማዕርጋተ ቤተ ክርስቲያን የሚባሉት፦ አናጉንስጢስ /አንባቢ/፣ ዲያቆን፣ ቄስ፣ ቆሞስ፣ ኤጲስ ቆጶስ፣ ሊቀ ጳጳስ እና ፓትርያርክ ናቸው።
➣ሶስቱም ብርሃናት ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሲወጡ ሲገቡ ፊታቸውን ወደ ምስራቅ አድርጎ ፈጥሯቸዋል። እንደዚሁም ሁሉ ምዕመናን ፊታቸውን ወደ ምስራቅ አዙረው ለመጸለያቸው ምሳሌ ነው።
➣ጨረቃ ሠርቅ ካደረገች በኋላ ለአስራ አራት ቀናት መጋቤ ወርኅ መልአክ ብርሃን እያወጣ እንደሚስልባት ሁሉ ምዕመናን ከመምህራን አስሩ ቃላተ ኦሪትን፣ ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን፣ ዶግማ /ትምህርተ ሃይማኖትን …ወዘተ ሲማሩ ለመኖራቸው ምሳሌ ነው። በመጨረሻም በሃያ ዘጠነኛ ቀን መጥፋቷ መምህራን ከሞቱ በኋላ ሥልጣናቸው በእግዚአብሔር እጅ የመያዙ ምሳሌ ነው።
➣ለከዋክብት መመላለሻ በምስራቅ ስድስት፣ በምዕራብ ስድስት መስኮት እንዳላቸው ሁሉ ምዕመናን በስድስቱ ቃላተ ወንጌል /የሐዲስ ኪዳን/ ሕግ ፀንተው ለመመላለሳቸው፣ ለሞታቸው እና ለመነሳታቸው ምሳሌ ነው።
◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶
ይ🀄️ጥላል
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖
💚💛❤️ ክፍል ፭ 💚💛❤️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞
🌕🌞🌤💥💫☀️✨🌙🌟🌕
🌟 #የዕለተ_ረቡዕ_ፍጥረታት 🌟
☀️💫⭐️🌟🌙✨💥🌤🌞🌕
https://t.me/EOTC2921
💚 ረቡዕ ረብዓ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አራት አደረገ ማለት ነው። ሥነ ፍጥረት መፈጠር ከጀመረ አራተኛ ቀን ስለሆነ ረቡዕ ተብሏል። ይህ ቀን ለሥነ ፍጥረት አራተኛ ቀን፣ ለቀመር ደግሞ ሁለተኛ ቀን ነው። የዕለተ ሠሉስ ፍጥረት ላይ እንደተመለከትነው ሠሉስ /ማክሰኞ/ ለቀመር የመጀመሪያ ቀን ነው። ረቡዕ ደግሞ ሁለተኛ ቀን ይሆናል ማለት ነው። በዚህ ቀን እግዚአብሔር ሶስት ፍጥረታትን የፈጠረ ሲሆን “ለይኩን ብርሃን ውስተ ጠፈረ ሰማይ - በጠፈር ላይ ብርሃን ይሁን” ዘፍ. 1፥12 ብሎ ሲያዝ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ተፈጥረዋል። በመጀመሪያ ሰዓተ ሌሊት “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እሳተ ወነፋሰ በበንስቲት ወገብረ ሰሌዳ ፀሐይ - እሳትን ከኮሬብ፣ ነፋስን ከአዜብ አምጥቶ የፀሐይን ሰሌዳ ፈጥሯል።”
💛 ፀሐይ ከእሳትና ከነፋስ የተፈጠረች ሲሆን ከእነዚህ ፍጥረታት መፈጠሯ በምን ይታወቃል? ቢሉ ከእሳት ለመፈጠሯ ታተኩሳለች /ታቃጥላለች/ ከነፋስ ለመፈጠሯ ትሔዳለች። “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር ነፋሰ ወማየ በበንስቲት ወገብረ ሰሌዳ ወርኅ - በመቀጠል ውሃን ከናጌብ ነፋስን ከአዜብ አምጥቶ የጨረቃንና የከዋክብትን ሰሌዳ ፈጥሯል። ሄኖ.21፥4 ይህስ በምን ይታወቃል? ቢሉ በነፋስነታቸው ይሄዳሉ፣ በውሃነታቸው ይቀዘቅዛሉ።
❤️ ዕለተ እሑድ ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩበት ቀን ስለሆነ ጥንተ ዕለት፣ ዕለተ ሠሉስ በዓለም ውስት የሚኖሩ ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩበት ቀን ስለሆነ ጥንተ ቀመር እንደተባሉት ሁሉ በዕለተ ረቡዕ ብርሃናት የተፈጠሩበት ቀን ስለሆነ ጥንተ ዮን ይባላል። #ዮን ማለት ብርሃን፣ ፀሐይ ማለት ነው። “ዮን ይእቲ ስማ ለፀሐይ ሀገረ ፀሐይ ዮን ይእቲ -ዮን ማለት የፀሐይ ስም፣ የጸሐይ ሀገር ማለት ነው።” እንዲል አረጋዊ መንፈሳዊ፤ ሶስቱ ጥንታት የሚባሉት እነዚህ ናቸው።
💙 የፀሐይ የጨረቃና የከዋክብት ብርሃንስ ከየት የተገኘ ነው? ብለን ብንጠይቅ በዕለተ እሑድ ለይኩን ብርሃን ብሎ እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ከፈጠረው ብርሃን የስንዴ ቅንጣት ታክል ወስዶ ለሰባት በመክፈል ሶስቱን እጅ ለፀሐይ፣ ሁለቱን እጅ ለጨረቃ፣ አንዱን እጅ ለከዋክብት፣ የቀረውን አንድ እጅ ደግሞ ለማያት /ለውሆች/ እና ለደመናት ቀብቷቸዋል።
💜 ከዋክብትን ሲቀባቸው ሁሉንም እኩል አድርጎ አልቀባቸውም፤ እንደ ክብራቸው አበላልጦ ቀብቷቸዋል። የአንዱ ኮከብ ብርሃን ከሌላው ይበልጣል። “አሐዱ ኮከብ እምአሐዱ ኮከብ ይሄይስ በክብር - የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይበልጣል።” እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 15፥39
💟“ወአመ ተፈጥሩ ከዋክብት ሰብሑኒ ኵሎሙ መላእክትየ በዐቢይ ቃል - ቅዱሳን መላእክትም የፀሐይን ሙቀት፣ የጨረቃን ድምቀት፣ የከዋክብትን መበላለጥ አይተው ይህን ላደረገ አምላክ እልል ብለው አመስግነዋል።” ኢዮ. 38፥7 እንኳንስ መላእክት እግዚአብሐርም በፈጠረው ፍጥረት ደስ ብሎታል። “ወርእየ እግዚአብሔር ከመ ሰናይ እግዚአብሔርም ያም መልካም እንደሆነ አየ” እንዲል ሙሴ ዘፍ፤ 1፥12 ቅዱስ ዳዊትም “ይትፌሳሕ እግዚአብሔር በተግባሩ - እግዚአብሔር በስራው ደስ ይለዋል” ብሏል። መዝ.103፥33
💚 እነዚህ ብርሃናት የተፈጠሩበት ዋናው ዓላማ “ወሴሞሙ እግዚአብሔር ለፀሐይ ወለወርህ ወለከዋክብት ከመይፍልጡ ሌሊተ እማዕከለ መዓልት ወሰዓተ እማዕከለ ዕለት ወዓመተ እማዕከለ ዘመን- መዓልቱን ከሌት፣ ሰዓቱን ከዕለት፣ ዓመቱን ከዘመን ለመለየት ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ሹሟቸዋል።” እንዲል ኩፋሌ 2፥13
🌤 #በእንተ_ፀሐይ ☀️
➣ፀሐይን ሶስት ማዕረግ ሶስት ኬክሮስ ዝቅ አድርጎ ፈጥሯታል። ይህም ማለት በምስራቅ በኩል ፀሐይ ሶስት ኬክሮስ አብርታ በምዕራብ በኩል ትጠልቃለች። “ፀሐይኒ አዕመረት ምዕራቢሁ - ፀሐይ ምዕራቧን /መግቢያዋን/ አወቀች” እንዲል ቅዱስ ዳዊት መዝ 103፥19 ፤ ሄኖ. 27፥4 የፀሐይ ብርሃን እንደ ጨረቃ ሕፀጽ ወይም መጉደል የለባትም። ፀሐይ በቀን ብቻ ትሰለጥናለች። “ለፀሐይ ዘአኮነኖ መዓልተ - ለፀሐይ ቀንን ያስገዛ” መዝ. 135፥8 ምነው ፀሐይን ቀኑን ብቻ አብርታ ሌሊቱን ሳታበራ ቀረች? ቢሉ ፀሐይ ቀኑንም ሌሊቱንም ብታበራ ኖሮ ከዋዕዩ ብዛት፣ ከሐሩሩ ጽናት የተነሳ ፍጥረቱ ሁሉ ባለቀ ነበር። ፀሐይ አውደ ዐመቱን የምታሳውቀን ሲሆን አንድ አውደ ዓመት የሚባለው በፀሐይ 365 ቀን ከአስራ አምስት ኬክሮስ ወይም ከስድስት ሰዓት ነው።
🌖 #በእንተ_ወርኅ( #ጨረቃ) 🌙🌕
➣ጨረቃ እንደ ፀሐይ ሶስት ኬክሮስ አብርታ ከምስራቅ አንስታ በምዕራብ ትገባለች። ወይትናፀሩ በገሃህ - ገጽ ለገጽ ይተያያሉ። ሁለቱ በአንድ ኆኅት /መስኮት/ ቢፈጠሩም ነገር ግን ጨረቃ ስለምታፅፅ ማለትም ስለምትሞላ ስለምትጎድል ዓመታዊ ዑደታቸው /ዙረታቸው/ እኩል አይደለም።
➣ጨረቃ ለአስራ አራት ቀን መጋቤ ብርሃን መልአክ አላት። ይህም መልአክ ብርሃን እያወጣ ይስልባታል። ከአስራ አምስተኛ ቀን ጀምሮ ብርሃን እየተከፈለ ማለትም አንድ እጅ ብርሃን እየቀነሰ በሃያ ዘጠነኛ ቀኗ ጨርሳ ትጠፋለች። በዚህም ዕለት ከፀሐይ ጋር ተራክቦ ታደርጋለች። በሠላሳኛው ቀን ማጭድ መስላ በስተምስራቅ ትወጣለች። ሄኖ. 22፥14
➣ጨረቃ በአንደኛው ወር ሃያ ዘጠኝ ቀን፣ በሁለተኛው ወር ሙሉ ሠላሳ ቀን ስለምትዞር ማለትም ስድስት ወር ሃያ ዘጠኝ ቀን፣ ስድቱን ወር ደግሞ ሠላሳ ቀን ስለምትዞር ይህ በዓመት ሶስት መቶ ሃምሳ አራት ቀን ይሆናል። እነዚህ የጨረቃ ዓመታዊ ዑደት እንደ ፀሐይ ሶስት መቶ ስልሳ አምስት ቀን ሳይሆን ሶስት መቶ ሃምሳ አራት ቀን ብቻ ነው።
⭐️ #️በእንተ_ከዋከክብት ✨️🌟💥
➣ከዋክብት ከላይ እንደተመለከትነው እንደ ክብራቸው የብርሃናቸው መጠን ይለያያሉ። ከዋክብት ከጨረቃ ጋር አብረው በሌሊት በመሰልጠን ለሌሊቱ ድምቀትን፣ ግርማ ሞገስን ያጎናጽፋሉ። ከዋክብት ብዙ ዓይነት ስለሆኑ ከዚህ ቀጥሎ ለባሕረ ሐሳብ ትምህርታችን የሚጠቅሙንን መገብተ ከዋክብት የሚባሉትን ብቻ እንመለከታለን።
ይ🀄️ጥላል
4 374
🌾✞ #ይበራል_በክንፉ ✞🌾
ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው
የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው
ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው /፪/
ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ
እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ
ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ
ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ
#አዝ----▶✞◀---▶✞◀---
በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ
አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ
የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከርሱ ጋራ
ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ
#አዝ----▶✞◀---▶✞◀---
በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን
ፅድቅ እየመገበ ኣሳደገኝ ልጁን
የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ
እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ
#አዝ----▶✞◀---▶✞◀---
ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር
ይስማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር
ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ
ታላቁት በረከት በውስጤ አፈሰሰ
#አዝ----▶✞◀---▶✞◀---
ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ
መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ
የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ
በፀጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ
4 374
🌾✞ #ኦ_ሚካኤል ✞🌾
ኦ ሚካኤል /፪/ ሊቀ መላዕክት
በኃጢያት እንዳንወድቅ እንዳንሞት
ፈጥነህ ተራዳን አፅናን በእምነት
ለያዕቆብ ነገድ ለእሥራኤል
ጠባቂያቸው ነህ መልአከ ሃይል
ፍቅርን አድለን ምህረት
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት/፪/
#አዝ----▶✞◀---▶✞◀---
ነፀብራቃዊ ተክህኖ ልብስህ
ሐመልማለ ወርቅ ዐይኑ ዘርግብ
ፍቅርን አድለን ምህረት
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/
#አዝ----▶✞◀---▶✞◀---
በስእልህ ፊት እሰግዳለሁኝ
ፈጥነህ አረጋጋኝ አለሁ በለኝ
ፍቅርን አድለን ምህረት
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት/2/
#አዝ----▶✞◀---▶✞◀---
4 374
💚በዕለተ ሠሉስም እግዚአብሔር አምላክ ሶስት ፍጥረታትን ፈጥሯል። “ወይቤ እግዚአብሔር ለታብቁል ምድር ሐመልማለ ዘርዕ ዘይዘራዕ በበዘርዑ ወበበዘመዱ- ምድር ዘርን የሚሰጥ ሳርን ቡቃያን በምድር ላይ እንደወገኑ እንደወገኑ ዘር ያለበትን፣ ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል ብሎ እግዚአብሔር አዘዘ እንዲህም ሆነ” ዘፍ. 1፥12 በዚህ ትዕዛዝ ሶስት ፍጥረታት ተፈጥረዋል። እነሱም፦
↪️በምሳር /በመጥረቢያ/ የሚቆረጡ ዕጽዋትን፣
↪️በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕትን፣
↪️በእጅ /በጣት/ የሚለቀሙ አታክልትን ከአራቱ ባሕርያት ፈጥሯል።
#ከአራቱ_ባሕርያት_መፈጠራቸው_በምን_ይታወቃል_ቢሉ?
➣ከእሳት ለመፈጠራቸው እርስ በራሳቸው ቢያጋጯቸው እሳት ይፈጠራል፣ ምሳሌ:- አስታና ዶግ
➣ከውሃ መሆኑን ሲቆርጧቸው እንደ ወተት፣ ውሃ ያለ ነገር ይወጣቸዋል፣ ምሳሌ፦ ቁልቋል፣ ቅንጭብ
➣ከነፋስ ለመፈጠራቸው በነፋስ ያድጋሉ፣
➣ከአፈር ለመሆኑ ቆርጠው ቢጥለቸው ፈርሰው በስብሰው አፈር ይሆናሉ።
↪️ሳይንሱም ቢሆን የሚስማማበት በዝናብ /በውሃ/ ይበቅላሉ፣ በነፋስ ያድጋሉ፣ በፀሐይ /እሳታዊ ናት/ ይበቅላሉ፣ ከመሬት ምግባቸውን ይወስዳሉ ይላል። ይህም አባባል እነዚህ ፍጥረታት ከአራቱ ባሕርያት መፈጠራቸውን ያረጋግጣል።
💚“ወተከለ እግዚአብሔር ገነተ መንገለ ምስራቅ እመልዕልተ ምድር ወታህተ ሰማይ- እግዚአብሔር አምላክ በምስራቅ በኤደን ገነትን ተከለ፤ ከምድር ከፍ ብላ ከሰማይ ዝቅ ብላ በመካከል ገነት ተተከለች።” ዘፍ.2፥8-9 ከዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት መካከል የሆኑትን ዕፀ ሕይወትን፣ ዕፀ በለስን፣ ሌሎች መልካም የሆኑ ዕጽዋት ተፈጥረዋል። ዘፍ.2፥9 ፣ሕዝ. 46፥13 ፣ራዕ.22፥2 በተጨማሪም “ወተከለ እግዚአብሔር አርባዕተ ዐበይተ ዕጽዋተ በዐርባዕቱ ማዕዘኒሃ ለዕፀ ሕይወት- ከዕፀ ሕይወት በአራቱ ማዕዘንዋ አራት ታላላቅ ዕጽዋትን ተከለ” ከእነዚህም ታላላቅ ዛፎች ስር አራቱ ታላላቅ ወንዞችን አወጣ። ዘፍ.2፥10 የእነዚህ አራቱ ወንዞች ስማቸው ግዮን፣ ኤፍራጥስ፣ ኤፌሶን/ፊሶን/ እና ጤግሮስ ይባላሉ። እነዚህ አፍላጋት በገነት እያሉ ወተት፣ ዘይት፣ ወይንና ማር ሆነው ይወጣሉ። ወደዚህ ዓለም ሲመጡ ግን ንጹሕ ውሃ ሆነው ይወርዳሉ። “ሰው መልካም ምግብ በልቶ፣ ጥሩ ውሃ ጠጥቶ፣ ወደ እዳሪ ሲወጣ ተለውጦ እንዲወጣ ሁሉ እነዚህም ተለውጠው ይወጣሉ።”
💛ግዮን ፈለገ ሀሊብ/ወተት/ ነው፤ በኢትዮጵያ ይዞራል። ኤፍራጥስ ፈለገ ዘይት ነው፤ በሮምያ ይዞራል። አፌሶን ፈለገ ወይን ነው፤ በአንጾኪያ ይዞራል። ጤግሮስ ፈለገ መዓር /ማር/ ነው፤ በቁስጥንጥንያ ይዞራል። ዘፍ.2፥11 በገነት ሌሎች ታላላቅና ታናናሽ ዕጽዋት ተፈጥረዋል። ፍሬያቸውም የሚምር ጣዕማቸውም ልዩ የሆኑ ናቸው። እነዚህን ዕጽዋት፤ አታክልትን ማን ይመገባቸዋል? ቢሉ በብሄረ ብጹዓን ያሉ ቅዱሳን፣ በገነት ያሉ አዕዋፍ ይመገቡታል።
️#ከዕለተ_ሠሉስ_ፍጥረታት_ምን_እንማራለን?
💟ከዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት በርካታ ነገሮችን የምንማር ሲሆን በምሳሌ እንመለከተዋለን፦
↪️እነዚህ ፍጥረታት በስራቸው የሚያፈሩ፣ በጎናቸው የሚያፈሩ፣ በጫፋቸው የሚያፈሩ አሉ። በሚስቶቻቸው/በባሎች/ በልጆቻቸው የሚጠቀሙ፤ በጌታ ትምህርት አምነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖሩ ሰዎች ምሳሌ ነው።
💚 #በጎናቸው_የሚያፈሩ፦ በሰራተኞቻቸው፣ በጎረቤቶቻቸው የሚያምኑ፣ በሐዋርያት ስብከት ያመኑ፣ በጥምቀት የዳኑ ሰዎች ናቸው።
💛 #በጫፋቸው_የሚያፈሩት፦ እነዚህ ደግሞ በራሳቸው ጥረው ግረው ራሳቸውን የሚረዱ፣ የሚያድኑ፣ እንዲሁም በሌሎች መምህራን ትምህርት ያመኑ የክርስቶስን ሞቱን፣ ትንሳኤውን አምነው በመስቀሉ የዳኑ ሰዎች ምሳሌ ነው።
🔑 ሚስጥሩ ደግሞ በስራቸው የሚያፈሩ ባለ ሰላሳ፣ በጎናቸው የሚያፈሩ ባለስልሳ፣ በጫፋቸው የሚያፈሩት ባለመቶ ፍሬ የሚያፈሩ ሰዎች ምሳሌ ናቸው። ማቴ.13፥1
❤️ #ፍሬያቸውን_በስራቸው፣ በጎናቸው በጫፋቸው የሚይዙ /የሚያፍኑ/ አሉ። በስራቸውና በጎናቸው በመሸፈን ከወፍ ከጠላት የሚከላከሉ፤ መልካም ትሩፋትን ሰርተው ነገር ግን እኛ አላደረግንም የሚሉ ቅዱሳን ምሳሌ ናቸው።
💚 #ፍሬያቸውን_በጫፋቸው በመያዝ ወፍ የሚበላባቸው፣ ጠላት የሚያጠፋባቸው ደግሞ የሰሩትን በጎ ስራና ትሩፋት እንዲያዩላቸው በመፈለግ፤ ይወቁልን፣ ይስሙልን የሚሉ ሰዎች ምሳሌ ናቸው። ማቴ.6፥1
💛 በአንድ መሬት ላይ በቅለው ግማሹ ጣፋጭ ፍሬ ያላቸው፣ ግማሹ መራራ ፍሬ ያላቸው አሉ። ይኸውም በአንዲት ምድር ላይ የተፈጠሩ የሰው ልጆች ግማሹ መልካም ስራ በመስራት ፈጣሪያቸውን የሚያስደስቱ፣ ሌላው ደግሞ በመጥፎ ስራቸው በመኖር እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ ሰዎች ምሳሌ ነው።
🌻 ዕጽዋት፣ አዝርዕት፣ አታክልት፦ አበባ የሌላቸው ፍሬ ያላቸው አሉ፣ አበባ ያላቸው ፍሬ የሌላቸው አሉ፣ አበባም ፍሬ የሌላቸው፣ አበባና ፍሬ ያላቸው አሉ።
🌾 አበባ የሌላቸው ፍሬ ያላቸው፦ ሃይማኖት ሳይኖራቸው ምግባር ያላቸው ምሳሌ ናቸው።
🌷 አበባ ያላቸው ፍሬ የሌላቸው፦ ሃይማኖት ያላቸው ምግባር የሌላቸው ምሳሌ፤
🌱 አበባም ፍሬ የሌላቸው፦ ምግባርም ሃይማኖትም የሌላቸው ምሳሌ፤
🌹 አበባና ፍሬ ያላቸው ደግሞ ምግባርም ሃይማኖትም አስተባብረው የያዙ ሰዎች ምሳሌ ናቸው።
🌽 በሰኔ ተዘርተው የክረምቱን ዝናብ ተቋቁመው ለፍሬ የሚደርሱ አሉ፤ ይኸውም ብዙ መከራና ስቃይ ተቋቁመው ለክብር የሚበቁ ቅዱሳን ምሳሌ ናቸው። እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉ። “ንሕነሰ በብዙህ መከራ ከለወነ ከመ ንባዕ ውስተ መንግስተ እግዚአብሔር- እኛስ በብዙ መከራ የእግዚአብሐርን መንግስት እንወርሳለን” ሐዋ.14፥21
🥭 በክረምት መውጫ ተዘርተው በጥቂት ዝናብ በቅለው ለፍሬ የሚበቁ አሉ። ይኸውም በጥቂት ምግባርና ትሩፋት የሚጠቀሙ፣ እንዲሁም አንድ ቀን መከራን በመቀበል የእግዚአብሔርን መንግስት የሚወርሱ ሰዎች ምሳሌ ናቸው።
🌻 በክረምት ለምልመው በበጋ የሚደርቁ፤ በዚህ ዓለም ሳሉ በልተው፣ ጠጥተው፣ ለብሰው፣ ደምቀው አምሮባቸው የሚኖሩ ነገር በሚመጣው ዓለም ተስፋ ነፍስ የሌላቸው ምሳሌ ናቸው። እንደነማን? ያሉ ቢሉ እንደ ነዌ፣ እንደ ኪራ ያሉ። “ይበቁዓከ ዘከመ ፈጋዕከ በሕይወትከ- በሕይወት ሳለህ በተድላ በደስታ መኖርህን አስብ” ሉቃ.16፥20
🍂በክረምት ደርቀው በበጋ የሚለመልሙት፤ በዚህ ዓለም ተርበው፣ ተጠምተው፣ ታርዘው፣ አከው የሚኖሩ በወዲያኛው ዓለም ግን ተስፋ ነፍስ ያላቸው ናቸው። እንደነማን? ቢሉ እንደ አልዓዛር ያሉ ናቸው።
🌵ክረምትም በጋም የማያፈሩ፣ የማይለመልሙ አሉ፤ እነዚህ በዚህ ዓለም ሳሉ ተቸግረው፣ አዝነው፣ ተክዘው፣ ጎስቁለው አከው የሚኖሩ ነገር ግን የደረሰባቸውን በአኮቴት የማይቀበሉ ነገር ሀጢአት በመስራት በመስረቅ፣ በመቀማት ኖረው በወዲያኛውም ዓለም ሳይጠቀሙ የዲያብሎስ ባሪያ ሆነው የሚቀሩ ሰዎች ምሳሌ ናቸው። “ድሃውን ስለድህነቱ አይምረውም እርሱን ደስ ካላሰኘው” እንዳለ ቅዳሴ አትናቴዎስ፤ ሮሜ. 9፥13
🍇🍋በክረምትም በበጋም አፍርተው፣ ለምልመው የሚኖሩ አሉ። እነዚህም በዚህ ዓለም በተድላ በደስታ ኑረው በሃብታቸው ተግባረ ጽድቅ ሰርተውበት በወዲያኛው ዓለም የሚጠቀሙ ሰዎች ምሳሌ ነው። እነዚህ እንደ አብርሃም፣ እንደ ይስሐቅ፣ እንደ ያዕቆብ ያሉ ናቸው።
◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶
ይ🀄️ጥላል
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
4 374
📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖
💚💛❤️ ክፍል ፬ 💚💛❤️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞
🎋🌲🌳🍀🍀🌳🌻🌺🌳🌴🍀🌳
#የዕለተ_ሠሉስ( #የማክሰኞ_ፍጥረታት
🌳🌿🍀💐🌹🌾🌱🌿🌾🌱🌿🌴
https://t.me/EOTC2921
💚ሠሉስ ማለት ሶስት ማለት ነው ይህ ቀን ፍጥረታት መፈጠር ከተጀመሩ ሶስተኛ ቀን ሆኗልና ሰሉስ /ሶስተኛ/ ተብሏል። ይህ ቀን ጥንተ ቀመር ይባላል። ቀመር - ቀመረ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ቆጠረ ማለት ነው። ቁጥር መቁጠር የተጀመረው በዚህ ቀን ነው። ጠቢባን ስላሴ ከዕለታት መርጠው ዓለምን የፈጠሩት በዕለተ እሑድ እና ሰኞ ሲሆን ‘ዕለተ ጠቢባን’ ይባላሉ። ዓለማት ተፈጥረው ያለቁት በእነዚህ ሁለት ቀናት ነው። ዓለማት በቁጥር ሃያ ሲሆኑ ሃያውም ዓለማት የተፈጠሩት በእነዚህ ቀናት ናቸው። በዕለተ ሠሉስ ደግሞ በሃያው ዓለማት ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩበት ዕለት ስለሆነ ጥንተ ቀመር ተብሏል።
🌐🌍 #ሃያው_ዓለማት 🌍🌐
✅✞ በዕለተ እሑድ ተፈጥረው በዕለተ ማክሰኞ በየቦታቸው የተከናወኑት ሃያው ዓለማት የሚባሉትም።
💠 #ዓለማተ_እሳት፦ ስንት ናቸው ቢሉ ዘጠኝ ናቸው።
➛ሦስቱ ዓለማተ መላእክት ኢዮር፣ ራማ፣ ኤረር፤
➛አራተኛው ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፤
➛አምስተኛ ሰማይ ውዱድ፤
➛ስድስተኛ መንበረ ስብሐት፤
➛ሰባተኛ ጽርሐ አርያም፤
➛ስምንተኛ ምጽንዓተ ሰማይ ባሕረ እሳት፤
➛ዘጠነኛ ገሃነመ እሳት ናቸው። የጋራ ስማቸውም #ኮሬብ ይባላል።
💠 #ዓለማተ_ነፋስ፦ ስንት ናቸው ቢሉ ሁለት ናቸው፤
➛አንደኛው ነፋስ ባቢል የሚባል ከላይ የረጋ ሲሆን ሐኖስን ተሸክሞ የሚኖር ነው፤
➛ሁለተኛው ነፋስ በርባሮስ ሲሆን ይህችን ዓለም ከበርባሮስ ጀምሮ ተሸክሞ የሚኖር ታላቁ ነፋስ የሚገኘው በዚሁ በርባሮስ ነው። የጋራ ስማቸውም #አዜብ ይባላል።
❤️ #በርባሮስ፦ ወደ ታች የመጨረሻው ጥልቁ ቦታ ሲሆን በጨለማ የተከበበ ነው፤ እልፍ አእላፋት ፀሐይ ቢገባበት ጨለማዋ የማይገፋ ነው። በብረት እንደማይወቀር ድንጋይ አድርጎ አፀናት። ምድርን የተሸከመው ታላቁ ነፋስም በዚኹ ይገኛል።
💠 #ዓለማተ_ማያት፦ ስንት ናቸው ቢሉ አራት ናቸው፤
➛አንደኛው ከላይ ሐኖስ፤
➛ሁለተኛው ጠፈር፤
➛ሦስተኛው ውቅያኖስ፤
➛አራተኛው ከታች የምድር ምንጣፍ የሆነችው ውኃ ናት። የጋራ ስማቸውም #ናጌብ ይባላል።
💠 #ዓለማተ_መሬት፦ ስንት ናቸው ቢሉ አምስት ናቸው።
➛አንደኛው ከታች ወደ በርባሮስ የሚቀርበው ሲዖል፤
➛ሁለተኛ ይህች ዓለም፤
➛ሦስተኛ ብሔረ ብፁዓን፤
➛አራተኛ ብሔረ ሕያዋን፤
➛አምስተኛ ገነት ናቸው። የጋራ ስማቸውም #ዱዳሌብ ይባላል።
✅✞ በመጀመሪያ ሃያ ዓለማት የሚባሉ አየን። እነሱም በክፍል አራት ናቸው። ከአራቱ ውስጥ አንዱ ዓለማተ መሬት የሚባለው እንመለከታለን። ዓለማተ መሬት በውስጡ አምስት ቦታዎችን ይይዛል። እነርሱም፦
፩ ገነት
፪ ብሔረ ሕያዋን
፫ ብሔረ ብጹአን
፬ ይህች ዓለምና
፭ ሲዖል (ለበርባሮስ ቅርቧ) ናቸው።
ከሃያው ዓለማት ውስጥ በአምስቱ ዓለማተ መሬት ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ናቸው።
1⃣ #ገነት፦ ገነት ከዚህች ምድር በስተ ምሥራቅ ስትገኝ ከዓለማተ መሬት ሁሉ ከፍ ብላ የምትገኝ ናት። በገነት ውስጥ የሚኖሩት በአካለ ነፍስ ብቻ የሄዱ ናቸው፤ መልካሚቱን ሐይማኖትን ከምግባርና ከስራ ጋር አዋህደው ሙሉ ዘመናቸውን በቅን የኖሩ፤ ለእግዚአብሔር የታዘዙና በቅን ያገለገሉ፤ እንደ እግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት የኖሩ፤ አስራት በኩራትና ቀዳሚያትን ሣይሰሥቱ ለእግዚአብሔር የሠጡ፤ የተራበን ያበሉ የተጠማን ያጠጡ በአጠቃላይ መልካም ተጋድሎን ያደረጉ እነዚህ ሁሉ ደስ እያላቸው በገነት ይኖራሉ። ይህ ሲባል ገነት ለአካለ ነፍስ እንጂ ለአካለ ስጋ አይደለችምና እስከ ዕለተ ትንሣኤ ድረስ የጻድቃን ነፍስ ማረፊያ ቦታ ነች።
2⃣ #ብሔረ_ሕያዋን፦ ብሔረ ሕያዋን ከዚህች ምድር በስተ ሰሜን የምትገኝ ሲሆን ከገነት ዝቅ ከብሔረ ብጹአን ከፍ ብላ የምትገኝ ናት። በአካለ ስጋ የሄዱ አባቶች ያሉባት ስትሆን በውስጣ የሚኖሩ ሰዎችም በንጽህና በቅድስና የሚኖሩ ናቸው። እነዚህም ቅዱሳን ከመልካም ሥራቸው በተጨማሪ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከነ ስጋቸው ተነጥቀው የተወሰዱ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ ቅዱስ ኤርሚያስ፣ ቅዱስ ሄኖክ፣ አቡነ አረጋዊ፣ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሃንስ፣ ቅዱስ ያሬድ ይገኙበታል። በብሔረ ሕያዋን የሚኖሩት ቅዱሳን ሁሉ አይወልዱም አይዋለዱም፣ አያገቡም አይጋቡም፣ አይበሉም አይጠጡም፤ በአሉበት ጸንተው እግዚአብሄርን እንደ መላእክት ያመሰግናሉ እንጂ።
3⃣ #ብሔረ_ብጹአን፦ ብሔረ ብጹአን ከዚህች ምድር ከፍ ከብሔረ ሕያዋን ዝቅ ብላ በስተ ደቡብ ትገኛለች። ይህች ቦታ ለየት ያለች ናት፤ ሰው አይቷት የማያውቅ ነገር ግን እግዚአብሔር ለመረጣቸው ቅዱሳን ብቻ መኖሪያ የሆነች ናት፤ በዚህም ቦታ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ይኖራሉ። በብሔረ ብጹአን የሚኖሩ ሰዎች ልብስ የላቸውም ክርስቶስ ያለበሳቸውን የብርሃን ልብስ ለብሰው ይኖራሉ እንጂ፤ በዚህ የሚኖሩትም ቅዱሳን ስማቸው ብጹአን ይባላል። በብሔረ ብጹአን የሔዱት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ፤ እነርሱም፦ ቅዱስ ዞሲማስ ዘሀገረ ፊሊስጤም እና ወጌላዊው ቅዱስ ማቲዮስ ናቸው።
4⃣ #ይህች_ምድር፦ እኛ የምንኖርበት ምድር ሦስት ስሞች ያሏት ሲሆን ከውሃ ሳትለይ ፀብር /ጭቃ/፣ ከውሃ ከተለየች በኋላ ምድር /ማኅደር ወይም መኖሪያ/ ከደረቀች በኋላ መሬት ትባላለች። በዚህች ምድር ላይ የተለያዩ አይነት ሰዎች ይኖራሉ። ጻድቃንና ሃጥኣን፤ የሚበድሉ የሚበደሉ፣ የሚገሉም የሚያስገድሉም፣ ይኖራሉ ሁሉም ግን ገነትም ፣ብሄረ ሄዋንም፣ ብሄረ ብፁአንም ወደ ሲኦልም የሄዱት ከዚህ ምድር ላይ ነው ከሌላ ቦታ የመጡ አደሉም።
5⃣ #ሲዖል፦ ሲዖል ከዚህች ምድር ዝቅ ብላ የምትገኝ ስትሆን በውስጧም የሚኖሩ ሐይማኖትና ምግባር የሌላቸው፤ በስመ ሥላሴ ያልተጠመቁ፤ ክፉ ስራን የሰሩ፤ ቅዱሳንን የጠሉና አማላጅነታቸውን የማይቀበሉ፤ ክርስቶስን ፈራጅ ሳይሆን አማላጅ የሚሉ፤ እጃቸውን በደም የታጠቡ፤ በእግዚአብሔር ሕግና ትዕዛዝ ያልተጓዙ፤ ለሰይጣን ተገዢ ሆነው ክብራቸውን ያዋረዱ፤ በአጠቃላይ እግዚአብሔርን ያሳዘኑ ሲሆኑ በምድር ላይ የኀጢአት ተድላና ደስታን የወደዱ ነገር ግን ነፍሳቸውን ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ ምግብና መጠጥ ያራቁ ሁሉ እስከ ዕለተ ምጽአት ነፍሳቸው ወደ በርባሮስ ወርዳ በሲዖል ትሰቃያለች። በመጨረሻም ከትንሣኤ በኃላ እጅግ በጣም ከአዕምሮ በላይ አስፈሪ ወደሆነው ወደ ገሃነመ እሳት የሚገቡ ናቸው።
✅✞ ከበርባሮስ ይህች ዓለም ብርህት ናት፤ ከዚህች ዓለም ብሔረ ብፁዓን ብርህት ናት፤ ከብሔረ ብፁዓን ብሔረ ሕያዋን ብርህት ናት፤ ከብሔረ ህያዋን ገነት ብርህት ናት።
✅✞ የዓለማተ መሬት አፈጣጠር እንደምነው ቢሉ ከሁሉ በታች ድቅድቋ ጨለማ በርባሮስ ናት፤ ከበርባሮስ በላይ ይህች ዓለም ናት፤ ከዚህች ዓለም በላይ በደቡብ ብሔረ ብፁዓን ናት፤ በሰሜን ብሔረ ሕያዋን ናት፤ በምሥራቅ ገነት ናት፤ በምዕራብ ወደ በርባሮስ ዝቅ ያለችው ሲዖል ናት።
✅✞ እግዚአብሔር ይህን ዓለም ሲፈጥር አንድ ዓለም ብቻ አይደለም የፈጠረው፤ ሃያ ዓለማትን ሃያ ዓየራትን ፈጥሯል እንጂ። በነዚህም በሀያው ዓለማትና በሀያው ዓየራት በውስጣቸው ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከሥላሴ በቀር የሚያውቀው የለም።
✍በገብረ ሥላሴ መንግሥቴ
#ምንጭ፦
መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ
ይ🀄️ጥላል
4 374
✝✞ #የመስቀል_መዝሙሮች ✞✝
https://t.me/EOTC2921
🌾✞ #በእንተ_መስቀሉ ✞🌾
🌾✞ #ለእግዚነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ✞🌾
1. ወሪዶ
2. ዮምሰ ለእሊአለ
3. ጥልን በመስቀሉ
4. መድኀኒተ
5. ከመትባርከነ
6. ዘዕጣን አንጸረ
7. እሌኒ ንግሥት
8. ጸጋ ነሳይነ
9. መስቀል ኃይልነ
10. ይቤልሙ ኢየሱስ
11. ቀበርነው ብለው
12. በወንጌሉ ያመናችሁ
13. መስቀልከ
14. ወአንቲኒ
15. ዘዕጣን አንጸረ
16. መርሕ ለፍኖት
17. መስቀል ብርሃን
18. ይትቀደስ ስምከ
19. በመስቀሉ ወበቃሉ
20. ኃይልነ ወጸወንነነ
21. በመስቀሉ ቤዘወነ
22. በመስቀልከ
23. መስቀልከ
24. መስቀሉሰ
25. ቤተ ክርስቲያን ርእየቶ
26. ዝንቱ መስቀል
27. እንተ ተሐንፀት በስሙ
28. ኧኸ በመስቀልከ
29. መስቀል ቤዛ ብዙኃን
30. ዮም በዓለ መስቀሉ
31. ለዕፀ መስቀል
32. ርእዩ ዕበዮ
33. ዮም መስቀል
34. ወበእንተዝ
35. ትቤሎ እሌኒ
36. ሀብሩ ቃለ
37. ዝንቱ መስቀል
38. ብከ ንወግዖሙ
39. መስቀል አብርሃ
40. መፅናኛ መመኪያ
41. ደስ ይበለን
42. መስቀል አበባ
43. ብርሃን ወጣ
44. ኀበ ቀራንዮ
45. ግማደ መስቀሉ
46. እዮሃ አበባዬ
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
1⃣ኛ. በሰማየ ኢዮር ካሉት መላእክት ከነገደ ኪሩቤል ገጸ - ሰብዕና ገጸ - አንበሳን፣ ከነገደ ሱራፌል ገጸ-ላሕምና ገጸ-ንስር መርጦ በሰማየ ውዱድ አኖራቸው። እነዚህም ፊት ለፊት አይተያዩም “አይትናጸሩ ገጽ በገጽ - ፊት ለፊት አይተያዩም” እንዲል። ራዕ. 4፥7
➣ #ገጸ_ሰብእ አቋቋሙ በምስራቅ ሆኖ ወደ ምዕራብ ያያል፤
➣ #ገጸ_አንበሳ አቋቋሙ በምዕራብ ሆኖ ወደ ምስራቅ ያያል፤
➣ #ገጸ_ላሕም አቋቋሙ በሰሜን ሆኖ ወደ ደቡብ ያያል፤
➣ #ገጸ_ንስር አቋቋሙ በደቡብ ሆኖ ወደ ሰሜን ያያል ሕዝ. 1፥10
↪️ነገደ ሱራፌል ባለስድስት ክንፍ ሲሆኑ ነገደ ኪሩቤል ባለ ብዙ ዓይኖች ናቸው። “ወኪሩቤል እለ ብዙኀት አዕይንቲሆሙ ወሱራፌል እለ ስድስቱ ክነፊሆሙ” እንዲል ራዕ. 4፥6-8 ኢሳ.6፥3 አንቀጸ ብርሃን ዘያሬድ። ሁለቱን ክንፋቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ፊታቸውን ይሸፍናሉ፣ ሁለቱን ወደታች ዘርግተው እግራቸውን ይሸፍናሉ፣ ሁለቱን ደግሞ ግራና ቀኝ በትዕምርተ መስቀል ይዘረጉታል። ወደላይ መዘርጋታቸው ቢወጡ፣ ቢወጡ አትገኝም ሲሉ፤ አንድም የተመስጦ ምልክት ነው። ወደታች መዘርጋታቸው ቢወርዱ፣ ቢወርዱ አትገኝም ሲሉ፤ አንድም የትህትና ምልክት ነው። ግራና ቀኝ መዘርጋታቸው ጽንፍ እስከ ጽንፍ ቢሄዱ ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ፤ አንድም የተልዕኮ ምሳሌ ነው። አንድም የጌታ ስቅለቱ ምሳሌ ነው። ሕዝ. 1፥50፤ራዕ. 4፥6
2⃣ኛ. በሰማየ ራማ ካሉት መላዕክት ሃያ አራት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ መንግስት ዙሪያ ክንፍ ለክንፍ አያይዞ አቆማቸው። የብርሃን ዘውድ ደፍተው፣ የብርሃን መስቀል ይዘው፣ የብርሃን ማዕጠንተ ወርቅ ጨብጠው የሚያመሰግኑ እና መንበሩን የሚያጥኑ አድርጓቸዋል። ራዕ. 4፥4 እነዚህ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚባሉት ሲሆን በቀንናበሌሊት ሳያቋርጡ ስብሐት ወክብር ለስሉስ ቅዱስ ይደሉ እያሉ ያመሰግኑታል። በእኛም ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ምድራውያን ካህናት በሰማውያን ካህናት ምሳሌ “ስብሐት ወክብር ለስሉስ ቅዱስ ይደሉ …” እያሉ ያመሰግኑታል። ይህንንም በኪዳን፣ በወንጌል በቅዳሴ ጊዜ ጥምጥማቸውን አውልቀው የሚያመሰግኑት በራዕይ 4፥10 በተጻፈው ምሳሌ ነው።
3⃣ኛ. በኤረር ካሉት መላዕክት ሃያ አራት ሺህ መርጦ ለሰማይ አስራ ሁለት ሺህ ኆኅት /መስኮት/ አበጅቶ በእያንዳንዱ መስኮት ሁለት ሁለት መላዕክትን አስፍሯቸዋል። እነዚህ መላእክት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በመብረር ዓለምን በሙሉ ይቆጣጠራሉ።
#ከሰኞ_ፍጥረታት_ምን_እንማራለን?
በእለተ እሑድ በፈጠረው ፍጥረት ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጸ ሁሉ በዕለተ ሰኑይ ፍጥረት ምስጢረ ሥጋዌ ተገልጿል። ይህም ከምድር እስከ ብሩህ ሰማይ ኤረር ድረስ የሞላው ውሃ ከሶስት ከፍሎ ሁለት እጁን ማለትም ጠፈርንና ሐኖስን ከላይ ማስፈሩ፤ ሥጋ ለብሰው አልታዩምና የአብና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው። አንዱ እጅ ወደ መሬት መውረዱ ከሶስቱ አካል አንዱ አካል ወልድ በተለየ አካሉ ከሰማየ ሰማያት ወደ ምድር ወርዶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በተዋሕዶ ከብሮ የመወለዱ ምሳሌ ነው። “ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል አስተርአየ - በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ” መዝ. 79፥1 የሚለው የቅዱስ ዳዊት ትንቢትና ልመና በወልደ እግዚአብሔር በምድር ላይ መገለጥ ተፈጽሟል።
◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶
ይ🀄️ጥላል
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖
💚💛❤️ ክፍል ፫ 💚💛❤️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞
☁️☁️☁️☁️☁️☁️⛅️⛅️⛅️⛅️
#የዕለተ_ሰኑይ( #የሰኞ_ፍጥረታት
☁️️⛅️☁️⛅️☁️⛅️☁️⛅️☁️⛅️
https://t.me/EOTC2921
💚 ሰኑይ ማለት ሁለተኛ ወይም ሁለት አደረገ ማለት ነው። ይህ ቀን ለሥነ ፍጥረት ሁለተኛ ቀን ስለሆነ ሁለተኛ ተብሏል።
💙 አንድም ሰኑይ የሚለው ቃል ‘ሠነየ’ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ሲሆን ይኸውም መልካም ሆነ ማለት ነው። “ወርዕየ እግዚአብሔር ኩሎ ዘገብረ ከመ ሠናይ ጥቀ - እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት መልካም እንደሆነ አየ” ዘፍ. 1፥12 በዚህ ቀን የተፈጠረው አንድ ፍጥረት ሲሆን ይኸውም ጠፈር ነው። በዕለተ እሑድ የተፈጠረው ውሃ ከእሑድ እስከ ሰኞ ድረስ ከምድር እስከ ብሩህ ሰማይ ኤረር ድረስ ሞልቶ ነበርና “ለይትጋባዕ ማይ ውስተ ምዕላዲሁ - ውሃ ወደ መከማቻው ይሰብሰብ” ዘፍ. 1፥6 በማለት እግዚአብሔር አምላክ ሲያዘው ለሶስት ተከፍሏል። አንዱን እጅ “ለይኩን ጠፈር በማዕከለ ማያት - በውሆች መካከል ጠፈር ይሁን” ዘፍ. 1፥9 ብሎ ውሃን እንደ ብረት አጠንክሮና አጽንቶ ጠፈርን ፈጥሮታል። አንዱን እጅ የውሃው ባሕርይ ሳይለወጥ ከጠፈር በላይ ሰቅሎ አስፍሮታል። ይኽም ሐኖስ ሲለው፤ አንዱን እጅ ደግሞ በምድር አስቀርቶታል።
↪️በምድር የቀረውን ውሃ እንዲሁ ለሶስት የተከፈለ ሲሆን አንዱ እጅ ከምድር በታች የሰፈረው ባሕር ነው። ምድር የጸናቸው በዚህ ውሃ ነው። ቅዱስ ዳዊት “ዘአጽንአ ለምድር ዲበ ማይ - ምድርን በውሃ ላይ ያጸናህ” መዝ. 135፥6 እንዳለው። ሁለተኛው ምድርን እንደመቀነት የከበባት ውቅያኖስ ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ የሰው ልጅና እንስሳት የሚጠቀሙበት በየተራራው፣ በየሸንተረሩ የሚገኘው ውሃ ነው። ይህም ቀላያት፣ አፍላጋት የሚባሉት ናቸው። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የውሃ መከማቻውን ባሕር፣ የብሱን ምድር ብሎ ጠራው። ኢዮ.38፥8 ፣መዝ. 11፥35
↪️የዕለተ ሰኑይን ፍጥረት ስንመለከት ሶስት ስሞችን በዋናነት አይተናል። እነዚህም ጠፈር፣ ሐኖስ እና ውቂያኖስን ተመልክተናል። ነገር ግን የዚህ ቀን ፍጥረት አንድ ብቻ ነው እንላለን። ለምን ሶስት ፍጥረት አንልም የሚል ጥያቄ በሕሊናችን ልናነሳ እንችላለን። አዲስ ፍጥረት ተፈጠረ የሚባለው አንድ ነገር ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ ነገር ሲቀየር ወይም ሲለወጥ /Changed/ ነው። ይህም ለውጥ አካላዊና መሰረታዊ የባሕርይ ለውጥ /physical and chemical change/ መሆን አለበት። አሁን ከሶስቱ እንዲህ ዓይነቱን ለውጥ የምንመለከተው በጠፈር ላይ ብቻ ነው። ምክንያቱም ጠፈር ሙሉ በሙሉ ውሃዊ ባሕርይውን ትቶ በቅርጽም፣ በመልክም ተቀይሮ፤ ፈሳሽ/liquid/ የነበረው የረጋ /solid/ ፣ እርጥብ የነበረው ይቡስ ወይም ደረቅ ፤ መልክ አልባ የነበረው መልክ ያለው ሆኗል:፡ ሌሎቹን ስንመለከት ግን እንዲህ ዓይነት ለውጥ ሳይሆን የተደረገላቸው የቦታና የአቀማመጥ ብቻ ነው። ውሃዊ ባሕርያቸው አልተለወጠም። ውሃ ደግሞ የእሑድ ፍጥረት ሆኖ ስለተቆጠረ እዚህ ጋር እንደአዲስ አንቆጥረውም። ሐኖስ ማለት ብጽብጽ ወይም ያልረጋ ውሃ ማለት ነው። ውሃው እራሱ ባህርይውን ሳይለቅ ከጠፈር በላይ አስፍሮታለ። ውቂያኖስም ሆነ ባህር በተመሳሳይ ሁኔታ የቦታ ለውጥ እንጂ የባሕርይ ለውጥ ስላልተደረገላቸው እንደ አዲስ ፍጥረታት አይቆጠሩም።
↪️ጠፈርን ከላይ እንዳየነው መልክ ያለው ሲሆን መልኩ ሰማያዊ ነው። የዚህ ምክንያቱ በርካታ ሲሆን ለአብንት ለመጥቀስ ያህል፦
፩ኛ. የሰውልጅ ሰማይ ሰማዩን እያየ ሰማያዊቷን ኢየሩሳሌምን እንዲያስታውስና በሰማይ ሰማያዊ ርስት እንዳለው ተስፋ እንዲያደርግ፤
፪ኛ. የጠፈር መልኩ ነጭ ቢሆን ኑሮ የፀሐይ ብርሃን እያንጸባረቀ የሰዎች አይን ይጎዳ ነበር፤ መልኩ ደግሞ ጥቁር ቢሆን ዓይናችንን ይከብደንና ድንግዝዝ ይልብን ነበር ነገር ግን መልኩን ሰማያዊ አድርጎ ከነዚህ ችግሮች አድኖናል።
💚 በተጨማሪም ጠፈር ሌሎች ጥቅምች አሉት። ጠፈርን ስንመለከተው ቅርጹ ልክ እንደ በሬ ሻኛ ጎበብ ያለ ነው። እንደዚህ አድርጎ የፈጠረው የፀሐይን ብርሃን ሳይነዛ ሰብስቦ እንዲይዝ ለማድረግ ነው። ነገር ግን ጠፈር ዝርግ ሆኖ ቢፈጠር ኖሮ ብርሃኑ ተነዝቶ ወደ ምድር ሳይመጣ በዛው ይቀር ነበር።
💛 ሌላው ጠፈር ባይኖር ኖሮ የፀሐይ ብርሃን በቀጥታ በመምጣት በሰው አናት ላይ ሙሉ በሙሉ ይወድቅ ነበር። በዚህም የሰው ናላ ይዞራል፣ ሀሞት ይበተናል፣ የሰው ልጅም ሆነ ሌሎች ፍጥረታት ይጎዱ ነበር። ነገር ግን ጠፈር ቀዝቃዛ በመሆኑ የፀሐዩን ሐይል በማቀዝቀዝ ለሰው ልጅ እንዲስማማ ያደርገዋል። እንዲሁም በዕለተ ረቡዕ ብርሃናት ማለትም ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ይፈጠራሉና ለእነርሱ ማኅደር /ማደሪያ/፣ መመላለሻ ይሆን ዘንድ ጠፈር ተፈጥሯል።
❤️ በዚህ ቀን በመጀመሪያ ሰዓተ ሌሊት ጠፈር የተፈጠረ ሲሆን ጠፈር ከተፈጠረ በኋላ የቀረውን ሃያ ሶስቱን ሰዓት ምን ሰርቶበታል ቢሉ መላእክትን ቦታ ቦታ ሰጥቶ ለአገልግሎት አሰማርቷቸዋል። ሁሉን መዘርዘር ባይቻልም የተወሰነውን ለመግለጽ ያህል፦
ይ🀄️ጥላል
4 374
💚ከዘጠነኛው ሰዓተ ሌሊት ጀምሮ ለፍጥረት ሰባተኛ የሆኑት መላዕክት ተፈጥረዋል። እግዚአብሔር መላዕክትን ከፈጠረ በኋላ በሶስቱ ሰማያት ውስጥ በመቶ ነገድ፣ በአስር ከተሞች አስፍሯቸዋል። በአስሩ ከተሞች ውስጥ አስር የነገድ አለቆች ተሹመዋል። በዝርዘር ስናያቸው፦
↪️በዘጠነኛው ሰዓተ ሌሊት ነገደ ሳጥናኤልን /አጋዕዝትን/፣ በአስረኛው ሰዓተ ሌሊት ነገደ ኪሩቤልና ነገደ ሱራፌልን፤ በአስራ አንደኛው ሰዓተ ሌሊት ነገደ ኃይላትን፣ በአስራ ሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ነገደ አርባብን፣ ነገደ መና ብርትንና ነገደ ሥልጣናትን፤ በአስራ ሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ነገደ መኳንንትን፣ ነገደ ሊቃናትንና ነገደ መላዕክትን ፈጥሯል።
↪️መላዕክት ከሰፈሩበት ቦታ አይወጡም፣ አይናወጡም። ነገር ግን ለተልዕኮ ከላይ ከጽርሐ ዓርያም እስከ ታችኛው በርባሮስ ድረስ ይወጣሉ፣ ይወርዳሉ፣ ይላላካሉ። እግዚአብሔር መላእክትን ሲፈጥራቸው ጥበበኛና አስተዋይ አድርጎ ስለሆነ ፈጣሪያቸውን ተመራምረው ያግኙ! በማለት ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወረ። በዚህን ጊዜ ሳጥናኤል ‘’እኔ አምላካችሁ ነኝ!’’በማለቱ ከስልጣኑ ወረደ። ሄኖ.12፥3 የእርሱን ፈጣሪነት አምነው የተቀበሉት አብረው ሲወርዱ፤ በማመንና ባለማመን መካከል በመሆን የተጠራጠሩት ደግሞ በአየር ላይ የአየር አጋንንት ሆነው ቀርተዋል። በተቃራኒው የእርሱን አምላክነት ባለመቀበል በተሰጣቸው ጥበብ አማካኝነት አምላቸውን እሰኪያገኙ ድረስ በጽናት የታገሱት መላእክት ስለ እምነታቸው ጽናት፣ ስለትዕግስታቸው ብዛት ሹመትና ማዕረግ አግኝተዋል።
↪️የዕለተ እሑድ የመጨረሻውና ስምንተኛው ፍጥረት ብርሃን ነው። “ለይኩን ብርሃን በማዕከለ ጽልመት- ብርሃን ይሁን አለ ብርሃንም ሆነ።” ብርሃንን በመጀመሪያው ሰዓተ መዓልት ወይም ከጠዋቱ በአንድ ሰዓት ፈጥሮታል። ይህ ብርሃን እውነተኛውን አምላካቸውን በትዕገስት በጠበቁ ቅዱሳን መላእክት ላይ ባበራ ጊዜ ብርሃኑ ዕውቀት ሆኗቸው እግዚአብሔርን ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ብለው አመስግነውታል። ኢሳ.6፥1
↪️በሁለተኛው ሰዓተ መዓልት መንፈስ ቅዱስ ክንፉን ዘርግቶ “የአብና የወልድ
ሕይወታቸው እኔ ነኝ!” ብሎ ኅቡዕ ስሙ የተፃፈበት ሰሌዳ ሰጣቸው። እነርሱም
ይህን ተቀብለው ስብሐት ለአብ፣ ስብሐት ለወልድ፣ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው በማመስገን ሚስጥረ ሥላሌን መስክረዋል። ስለሃይማኖታቸው ጽናት፣ ስለትዕግስታቸው ብዛት አምላካቸው ሹሟቸዋል። ሹሞም የብርሃን ዘውድ አቀዳጃቸው፣ የብርሃን ዘንግ አስያዛቸው፣ የብርሃን አስኬማ ቀረጸባቸው። በዚህም መሰረት ከሶስተኛው ሰዓተ መዓልት እስከ አስራ ሁለተኛው ሰዓተ መዓልት ድረስ በአስሩ ከተሞች ውስጥ ያሉትን መላእክት በመሾም የየነገዱን አለቃ ሰይሞላቸዋል።
↪️የመላዕክት ከተሞች፣ ነገዳቸውና አለቆቻቸው፦
1⃣ #ሰማየ_ኢዮር፦
➣በአጋዕዝት ከተማ የነገድ አለቃ ሳጥናኤል ነበር፤ ወደ ጥልቁ ከተጣለ በኃላ ለቅዱስ ሚካኤል ተደርቦለታል። የተሾመ በ3ኛው ሰዓተ መዓልት
➣በኪሩቤል ከተማ የነገድ አለቃ ኪሩብ፣ የተሾመ በ4ኛው ሰዓተ መዓልት
➣በሱራፌል ከተማ የነገድ አለቃ ሱራፊ፣ የተሾመ በ5ኛው ሰዓተ መዓልት
➣በኃይላት ከተማ የነገድ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፣ የተሾመ በ6ኛው ሰዓተ መዓልት
2⃣ #ሰማየ_ራማ
➣በአርባብ ከተማ የነገድ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል፣ የተሾመ በ7ኛው ሰዓተ መዓልት
➣በመናብርት ከተማ የነገድ አለቃ ሩፋኤል፣ የተሾመ በ8ኛው ሰዓተ መዓልት
➣በሥልጣናት ከተማ የነገድ አለቃ ሱርያል፣ የተሾመ በ9ኛው ሰዓተ መዓልት
3⃣ #ሰማየ_ኤረር
➣በመኳንንት ከተማ የነገድ አለቃ ሰዳካኤል፣ የተሾመ በ10ኛው ሰዓተ መዓልት
➣በሊቃናት ከተማ የነገድ አለቃ ሰላታኤል፣ የተሾመ በ11ኛው ሰዓተ መዓልትና
➣በመላእክት ከተማ የነገድ አለቃ አናንኤል፣ የተሾመ በ12ኛው ሰዓተ መዓልት
↪️እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ እንደዚህ አድርጎ ሃያ አራቱን ሰዓት ስራ ሰርቶበታል። ይህም የሚያሳየው ሃያ አራት ሰዓት ስራ መስራት ተገቢ መሆኑንና የእርሱም ፈቃድ መሆኑን፤ አንድም በኋላ የሚነሱ ቅዱሳን አባቶች ሃያ አራት ሰዓት እርሱን ለማመስገናቸው ምሳሌ ነው። “እባርኮ ለእግዚአብሔር በኩሉ ጊዜ ወዘልፈ ስብሐቲሁ ውስተ አፉየ- እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ
ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው። መዝ.33፥1
#የጨለማና_የብርሃን_ምሳሌ፦🌑🌕
1⃣ኛ. ካልፈለጋችሁኝ አታገኙኝም ሲል ጨለማን ፈጠረ። ብትሹኝ፣ ብትመረመሩኝ እገኛለሁ ሲል ብርሃንን ፈጠረ። ጨለማን በአርምሞ መፍጠሩ ሰሚ አካል /መላዕክት/ አልነበሩም። ብርሃንን በነቢብ /በመናገር/ ። “ለይኩን ብርሃን በማዕከለ ጽልመት - በጨለማ መካከል ብርሃን ይሁን” ማለቱ ሰማዕያን የሆኑ መላዕክት ስለተፈጠሩ ነው። “ብርሃኑን ቀን፣ ጨለማውን ሌሊት ብሎ ጠራው” ዘፍ.1፥3 ሁለቱን አንድ አድርጎ ሃያ አራቱን ሰዓት አንድ ዕለት ብሎታል። ዘፍ.1፥5ና 13
2⃣ኛ. ጨለማ የኦሪት፣ ብርሃን የወንጌል ምሳሌ ነው። “ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ብርሃን ዐቢይ ሠረቀ ላዕሌሆሙ- በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው” ኢሳ.9፥2 ሮሜ.13፥12 በጨለማ ውስጥ ምንም አንደማይታይ ሁሉ በኦሪትም የሰው ልጅ ልጅነቱን ተገፎ በቀቢጸ ተስፋ ይኖር ነበር። በሐዲስ ኪዳን ጌታ ተወልዶ፣ ተጠምቆ፣ ሞቶ፣ ልጅነቱ ተመልሶ ብርሃን ሆኖለታል።
3⃣ኛ. ብርሃንና ጨለማውን /ቀንና ሌሊቱን/ አንድ አድርጎ አንድ ቀን ማለቱ ኦሪትና ወንጌል ሕግ በመባል አንድ ለመሆናቸው ምሳሌ ነው። አንድም ጨለማ የትብስእት /የሥጋ/ ብርሃን የመለኮት ምሳሌ ነው። ሁለቱን አንድ አድርጎ አንድ ቀን ማድረጉ ሥጋና መለኮት በተዋሕዶ አንድ የመሆናቸው ምሳሌ ነው። ዮሐ.1፥1
◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶
ይ🀄️ጥላል
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ 📚📖
💚💛❤️ ክፍል ፪ 💚💛❤️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞
🌍🌎🌘🌗🌖🌕🌔🌓🌒🌑🌏🌍
#የዕለተ_ሰንበት( #የእሑድ_ፍጥረታት )
🌍🌎🌘🌗🌖🌕🌔🌓🌒🌑🌏🌍
https://t.me/EOTC2921
💚እሑድ የሚለው አሐደ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አንድ አደረገ ወይም የመጀመሪያ ማለት ነው። “ወበቀዳሚ እግዚአብሔር ገብረ ሰማየ ወምድረ -በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ።” ዘፍ.1፣1 በዚህ ቀን እግዚአብሔር ስምንት ፍጥረታትን ፈጥሯል። በመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት /ከምሽቱ አንድ ሰዓት/ አምስት ፍጥረታትን የፈጠረ ሲሆን እነሱም፦ እሳት፣ ውሃ፣ ነፋስ፣ መሬትና ጨለማ ናቸው።
💛እሳት፣ ውሃ፣ ነፋስና መሬት አራቱ ባሕርያት የሚባሉ ሲሆን በዓለም ውስጥ ያሉ ሁሉም ፍጥረታት መገኛቸው እነዚህ ፍጥረታት ናቸው። አራቱ ባሕርያት እርስ በራሳቸው የማይስማሙ፤ አንዱ አንዱን የሚያጠፋ ሲሆን ነገር ግን እግዚአብሔር በረቂቅ ጥበቡ አስማምቷቸው ዓለምን ፈጥሮባቸዋል። እንዲሁም የአንዱ ፍጥረት ባሕርይ /ጠባይ/ በሌላው ውስጥ ስለሚገኝ ባሕርያቸው እርስ በራስ ይወራረሳል። ባሕርያቸው እንዴት እንደሚወራረስ ከዚህ ቀጥሎ እንመለከተዋለን።
1ኛ. #እሳት፦ እሳት ሶስት ባሕርያት /ጠባያት/ አሉት እነሱም
☑️ውዑይነት /ሙቀትነት፣ የሚያቃጥል/
☑️ብሩሕነት /ብርሃንነት/
☑️ይቡስነት /ደረቃማነት/ ናቸው።
እነዚህን ጠባያት ከሌሎች ባሕርያት የነሳው ሲሆን ይኸውም፦
↪️ውዑይነትን /ሙቀትነትን/ …ከነፋስ
↪️ብሩሕነትን /ብርሃንነትን/ ...ከውሃ
↪️ይቡስነትን /ደረቃማነትን/ ...ከመሬት ነው።
2ኛ. #ውሃ፦ ውሃም ሶስት ባሕርያት አሉት። እነዚህም፦
☑️ብሩሕነት /ብርሃንነት/
☑️ርጡብነት /እርጥብነት/
☑️ቆሪርነት /ቀዝቃዛነት/ ናቸው።
እነዚህን ባሕርያት ያገኘው ከሌሎቹ ሶስት ፍጥረታት ነው።
↪️ብሩሕነትን …ከእሳት
↪️ርጡብነትን …ከነፋስ
↪️ቆሪርነትን …ከመሬት ነው።
3ኛ. #ነፋስም በተመሳሳይ ሶስት ባሕርያት አሉት እነርሱም፦
☑️ርጡብነት …እርጥብነት
☑️ውዑይነት …ሞቃታነት
☑️ጽሉምነት …ጨለማነት ናቸው።
እነዚህን ጠባያት የነሳው ወይም ያገኘው
↪️ርጡብነትን …ከውሃ
↪️ውዑይነትን …ከእሳት
↪️ጽሉምነትን …ከመሬት ነው።
4ኛ. #መሬት፦ መሬትም እንዲሁ ሶስት ጠባያት ሲኖሩት እነርሱም፦
☑️ይቡስነት …ደረቃማነት
☑️ጽሉምነት …ጨለማነት
☑️ቆሪርነት …ቀዝቃዛነት ናቸው።
እነዚህን ጠባያት የነሳው፦
↪️ይቡስበትን …ከእሳት
↪️ጽሉምነትን …ከነፋስ
↪️ቆሪርነትን …ከውሃ ነው።
እነዚህ ፍጥረታት ከላይ እንደተገለጸው አንዱ ከአንዱ ጋር አይስማሙም፣ ይጣላሉ። ነገር ግን አንዱ ሌላውን እያስታረቀ በእግዚአብሔር ቸርነት ይኖራሉ።
❤️ለምሳሌ እንደሚታወቀው እሳትና ውሃ አይስማሙም፤ ውሃ አሳትን ያጠፋዋል።
ነገር ግን ነፋስ ገብቶ ያስታርቃቸዋል። ነፋስና መሬት ጠበኞች ናቸው፤ ነፋስ
መሬትን ይጠርገዋል፣ እንዲሁም ይሰነጥቀዋል። ነገር ግን ውሃ ገብቶ
ያስታርቃቸዋል።
#አራቱን_ባሕርያት_ለምን_በመጀመሪያ_ፈጠራቸው?
አራቱ ባሕርያት ቀድመው የተፈጠሩት አንድም ዓለም በሙሉ የሚፈጠረው ማለትም እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ /ካለምንም/ ከተፈጠሩት ውጪ ያሉት የሚፈጠሩት በእነዚህ ፍጥረታት ስለሆነ ከሌሎቹ ቀድመው ተፈጥረዋል።
አንድም የእነዚህ ፍጥረታት እና የሌሎችም ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር አምላክ በባሕርይው አራት ነገሮች እንዳሉት ለማጠየቅ ነው። እነዚህም ባዕልነት /ባለጸጋነት/፣ ርኅሩኅነት /ቸርነት/ ፣ ከሀሊነት /ሁሉን ቻይነት/፣
ፈታሒነት /ፈራጅነት/ ናቸው።
1ኛ. #ባዕልነት_በመሬት_ይመሰላል፦
ባዕልነት ማለት ባለጸጋነት ሲሆን ባለጸጋ ሁሉን ያስገኛል። እግዚአብሔር የሁሉ
መገኛ እንደሆነ ሁሉ መሬትም የሚበላውን ፣ የሚጠጣውን …ወዘተ የምታፈራ፣ የምታስገኝ ናት። መዝ. 84 “እግዚአብሔር የሁሉ መገኛ ነው።’’ ይላል።
2ኛ. #ርኅራኄውና_ቸርነቱ_በውሃ_ይመሰላል፦
ውሃ ያደፈውን ያጠራል፣ የቆሸሸውን ያጸራል፤ ጌታም ኃጢአት ሰርተው ቢተዳደፉ ይቅር በለኝ ብለው በንስሃ ቢመለሱ ኃጢአትን ይቅር ይላል። ዮሐ. 6፥37
3ኛ. #ከሃሊነቱ_በእሳት_ይመሰላል፦
እሳት ገደል፣ ባሕር፣ እውቂያኖስ ካልከለው በስተቀር ደረቁን፣ እርጥቡን ሁሉ ሳይለይ ያቃጥላል። እግዚአብሔርም ቸርነቱና ርኅራኄው ካልከለው በስተቀር ሁሉን ማጥፋት ይችላል። ዘፍ.19፥1 ዘፍ.7፥21 ማቴ.19፥26 ሉቃ.1፥37
4ኛ. #ፈታሒነቱ_በነፋስ_ይመሰላል፦
ነፋስ ፍሬን ከገለባ፣ ገለባን ከፍሬ እንደሚለይ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክም ኃጥኡን ከጻድቁ፣ ምዕመኑን ከመናፍቁ ይለያል። ዘፍ.7፥2 ማቴ.3፥12 ማቴ.25፥32
በዚሁ ሰዓት ማለትም በመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት አምስተኛውን ፍጥረት ጨለማን ፈጥሯል። “ምድር ባዶ ነበረች አንዳች አልነበረባትም ጨለማም በጥልቁ ነበረ።” ዘፍ.1፥2
💚ከሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ ስምንተኛው ሰዓተ ሌሊት እግዚአብሔር ለፍጥረት ስድስተኛ የሆኑትን ሰባቱን ሰማያት ፈጥሯል። ሰማያት የተፈጠሩት ከእሳት ሲሆን ከእሳት ብርሃኑን ነስቶ /ወስዶ/ ሙቀቱን ትቶ ፈጥሯቸዋል። ሰባቱ
ሰማያት የሚባሉትም፦
1ኛ. #መንበረ_መንግስት፦ ይህ ሰማይ በሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት የተፈጠረ ሲሆን በዚህ ቦታ እግዚአብሔር እንደወደደ ለቅዱሳኑ የሚታይበት ነው። ለምሳሌ ለያዕቆብ ዘፍ.28፥12፤ ለነቢዩ ኢሳይያስ ኢሳ.6፥1፤ ለነቢዩ ሕዝቅኤል
ሕዝ.1፥26፤ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ራዕ.4፥2
2ኛ. #ጽርሐ_አርአም፦ ይህ ሰማይ በሶስተኛው ሰዓተ ሌሊት የተፈጠረ ሲሆን በመንበረ መንግስት ላይ ተዘርግቶ እንደ ጠፈር የሚጋርድ ነው። ሥላሴ በመንበራቸው ላይ ሆነው የሚሰለሱት፣ የሚቀደሱት በዚህ ሰማይ ነው። ሰባት የእሳት መጋረጃ ተጋርዶበታል ፣ሰባት የእሳት ቅጥር ተቀጥሮበታል። “ዘሰባቱ መንጦላዕት ዘእሳት አይቴ ተደለወ ወአይቴ ተተክለ - ሰባቱ የእሳት መጋረጃ በየት ተዘጋጀ? በየትስ ተተከለ?’’ ቅዳሴ ማርያም
3ኛ. #ሰማየ_ውዱድ፦ በአራተኛው ሰዓተ ሌሊት የተፈጠረ ሲሆን ይህ ሰማይ የሥላሴን ዙፋን የተሸከሙት አራቱ እንስሳት /ገጸ ሰብዕ ወይም የሰው መልክ ያለው፣ ገጸ አንበሳ፣ ገጸ ንስር ወይም ወፍ፣ ገጸ ላህም ወይም የላም መልክ ያላቸው/ ከነገደ ኪሩቤልና ከነገደ ሱራፌል የተወጣጡ መላእክት በእንስሳት መልክ ሆነው ዙፋኑን በጀርባቸው ተሸክመው የሚገኙበት ሰማይ ነው። ሕዝ.1፥22ና 26
4ኛ. #ኢየሩሳሌም_ሰማያዊት፦ በአምስተኛው ሰዓተ ሌሊት የተፈጠረች ሰማይ ስትሆን ሳጥናኤል የተፈጠረው በዚህ ቦታ ነው። እርሱ ከወደቀ በኋላ ለሰው ልጆች ዘላለማዊ መኖሪያ እንድትሆን ተዘግታ የምትገኝ ናት። መንግስተ ሰማያት የምትባለው ይህቺው ሰማይ ናት። ዮሐ.14፥1 የእመቤታችን ምሳሌ የሆነችው ታቦት ዘዶር የምትገኘው በዚህ ሰማይ ነው። ራዕ.11፥19 ቅዳሴ ማርያም
5ኛ. #ሰማየ_ኢዮር፦ በስድስተኛው ሰዓተ ሌሊት፣
6ኛ. #ሰማየ_ራማ፦ በሰባተኛው ሰዓተ ሌሊት፣
7ኛ. #ሰማየ_ኤረር፦ በስምንተኛው ሰዓተ ሌሊት ተፈጥረዋል። እነዚህ ሶስቱ ሰማያት ዓለመ መላዕክት ይባላሉ።
ይ️🀄️ጥላል
4 374
#የሃያ_ሁለቱ_ሥነ_ፍጥረት_መገኛ
💜 ፍጥረታት የተፈጠሩት በሁለት መንገድ ሲሆን እነሱም፦
✍️ #እምኀበ_አልቦ_ኀበ_ቦ ፡- ከምንም ምን ወይም በባዶ፦ ካለምንም የተፈጠሩ ሰባት ፍጥረት ሲሆኑ እነሱም እሳት፣ ውሃ፣ ነፋስ፣ መሬት፣ ጨለማ፣ ሰባቱ ሰማያት እና መላዕክት ናቸው።
✍️ #ግብር_እምግብር፡- ወይም ፍጥረት እምፍጥረት፦ እነዚህ ከአንድና ከዚያ በላይ ከሆኑ ፍጥረታት የተፈጠሩ ሲሆኑ ከላይ ከተጠቀሱት ሰባቱ ፍጥረታት ውጪ ሌላው አስራ አምስቱ በዚህ መልክ የተፈጠሩ ናቸው። መገኛቸውም ከአራቱ ባሕርያት /ከእሳት፣ ከውሃ፣ ከነፋስና ከመሬት/ የተፈጠሩ ናቸው።
💚 ፍጥረታት ሲፈጠሩ በሶስት ዓይነት ሁኔታ ነው:-
፩. #በአርምሞ፦ በዝምታ ወይም ባለመናገር ሲሆን በአርምሞ የተፈጠሩ ሰባት ፍጥረታት ናቸው። እነሱም፦ አራቱ ባሕርያት፣ ጨለማ፣ ሰማያትና መላዕክት ናቸው።
፪. #በነቢብ /በመናገር/፦ በመናገር የተፈጠሩ አስራ አራት ፍጥረታት ሲሆኑ እነሱም ከብርሃን ጀምሮ ያሉ አስራ አራቱ ፍጥረታት ናቸው።
፫. #በገቢር / በመስራት/፦ በገቢር የተፈጠረው ሃያ ሁለተኛው ፍጥረት አዳም ብቻ ሲሆን ከምድር አፈር አበጃጅቶ በሰባት ባሕርያት አጽንቶ ፈጥሮታል። ዘፍ. 2÷7 እነዚህ ሰባት ባሕርያት የሚባሉት አራቱ ባሕርያተ ሥጋ እሳት፣ ውሃ ፣ ነፋስና አፈር እንዲሁም ሶስቱ ባሕርያተ ነፍስ የሚባሉት ሕያውነት/ዘላለማዊነት/፣ ነባቢነት/ተናጋሪነት/ እና ለባዊነት/አስተዋይነት/ ናቸው።
◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶
ይ🀄️ጥላል
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ 📚📖
💚💛❤️ ክፍል ፩ 💚💛❤️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞
💠 ዘልማዱ ኂሩት (ምሕረት ይቅርታ ልማዱ) የሆነ እግዚአብሔር ቅድመ ዓለም እንደ ዛሬ በአንድነት በሦስትነት ሳለ ክብሩ በባሕርዩ ብቻ እንደቀረ አይቶ ዓለምን ልፍጠር ብሎ አሰበ አስቦም አልቀረ 22ቱን ሥነ-ፍጥረታት ፈጠረ። ኩፋ.፫፥፱ ሲፈጥርም ሰውና መላዕክትን ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመልበስ መንግስቱን ለመውረስ ሰማይና ምድርን ለፍጥረታት መኖሪያ አራቱ ባሕርያተ ሥጋን ለፍጥረታት ማስገኛ ሌላውን ግን ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ ለአንክሮ ለተዘክሮ ፈጠረ፡፡
💙 የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚጀምረው ከሥነ ፍጥረት መፈጠር ነው።
#ሥነ_ፍጥረት_ምን_ማለት_ነው?
🔵 ሥነ ፍጥረት ከሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን ሥን ማለት ያማረ፣ የሰመረ ማለት ሲሆን ፍጥረት ደግሞ የተፈጠረ ወይም የተገኘ ማለት ነው። ሥነ ፍጥረት ያማረ፣ የሰመረ የተዋበ ፍጥረት ማለት ነው።” ወርእየ እግዚአብሔር ኩሉ ዘገብረ ከመ ሠናይ ጥቀ - እግዚአብሔር ፍጥረታቱ ሁሉ መልካም እንደሆነ አየ’’ ዘፍ፤ 1፥21 ይላል።
💚 አንድም ሥነ ፍጥረት የፍጥረት መበጀት ወይም መሰራት ማለት ነው። የበጀ ማለት ደግም መልካም ማለት ነው።
💚 አንድም የፍጥረት መስማማት ማለት ነው። የማይስማሙና ጠበኞች የሆኑ አራቱ ባሕርያት በእግዚአብሔር ኃይል ተስማምተው ስለሚኖሩ የፍጥረት መስማማት እንለዋለን።
#የሥነ_ፍጥረት_አስገኚ_ማን_ነው?
🔵በዚህ ዓለም ላይ ላሉ ነገሮች ሁሉ አስገኚ አላቸው። ለምሳሌ ሸክላ ያለሰሪ፣ ልብስ ያለ ሰፊ፣ ዕፅዋት፣ አታክልትና አዝርዕት ያለ መሬት፣ ሰው ያለእናት አባት እንደማይገኙ ሁሉ በዓለም ውስጥ ያሉ ፍጥረታት ሁሉ ያለፈጣሪ ሊገኙ አይችሉም። የሰማይ መዘርጋት፣ የምድር መርጋት፣ የቀንና የሌሊት፣ የበጋና የክረምት መፈራረቅ፤ እንዲሁም ነፋሳት፣ ደመናት፣ መባርቅት፣ ብርሃናት፣ ውሆች ሁሉ አዛዥና ገዥ፣ ፈጣሪ፣ አስገኚ እንዳላቸው ያሳያሉ።
↪️ሥነ ፍጥረት ስንል አሁን እየተፈጠረ ያለ አዲስ ነገር አይደለም። ይልቁንም ከጥንት ጀምሮ በአባቶች ሲነገር የነበረ ነው። በአንዳንድ ሳይንቲስቶች አመለካከት በአሁን ሰዓት ሰው እያገኛቸው ያሉ ግኝቶችን ልክ አሁን እንደተገኙ ከዚህ ቀደም እንዳልነበሩ ተደርጎ ይነገራሉ። ነገር ግን ሁሉም ከጥንት ጀምሮ በአባቶቻችን በቃል ሲነገር፣ በጽሑፍ ሲሰፍር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የኖረ ነው። በአሁን ሰዓት የሰው ልጅ ጥቂቶቹን ተመራምሮ የደረሰባቸውን በማስተዋወቅ፣ በማስረዳት በስራ ላይ እንዲውሉ፣ ለአገልግሎት እንዲበቁ አድርጓል። ይህ ማለት ግን ያልነበረውን አዲስ ፍጥረት ፈጥሯል ማለት አይደለም። ሥነ ፍጥረት አንድ ጊዜ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ “ሁሉም በእርሱ ሆነ/ተፈጠረ/፣ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም” ዮሐ.1፥3 እንዳለው።
↪️እንደውም ለፈጣሪ መኖር ዋነኛው አስረጂዎች እነዚሁ ፍጥረታት ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ “ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደተዘጋጁ ስለዚህ የሚታየው ነገር ከሚታየው እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።” ዕብ. 11፥3 ይላል። እንዲሁም የማይታየውና ጥንት የማይታወቀው አምላክ በእነዚሁ በፍጥረታት አማካኝነት እንደተገኙም “ወዘኢያስተርኢ እግዚአብሔር እምፍጥረተ ዓለም ተዐውቀ በፍጥረቱ በሀልዮ ወበአዕምሮ - የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሰሩት ታውቆ ግልጽ ሆነ።”
ሮሜ. 1፥20 በማለት የማይታየው ፣የማይጨበጠው አምላክ መኖሩ የታወቀው በፈጠረው ፍጥረት ነው። ማር ይስሐቅም “ወለእመ ፈቀድከ ታእምር ዘንተ ብከ ሰማዕት ወመምህር እምአፍአ ዘይመርኀከ ኀበ አእምሮተ እግዚአብሔር የእግዚአብሔርን መኖር /ሕልውና/ ለማወቅ ከወደድክ መምህር ምስክር ሆኖ እግዚአብሐርን ወደማወቅ የሚመራህ ሥነ ፍጥረት አለልህ” /ማር ይስሐቅ እመጽሐፈ መነኮሳት ምዕ. 1 አንቀጽ 2/ ይላል። በእርግጥም አባቶቻን እግዚአብሔርን ፈልገው ያገኙት በፈጠረው ፍጥረት አማካኝነት ነው። ስርወ ሃይማኖት፣ አርከ እግዚአብሔር የተባለው አብርሃም በእግረ ልቡና፣ በፍኖተ አእምሮ ተጉዞ ከአምላኩ ጋር ያገናኙት እነዚሁ ፍጥረታት ናቸው። እኛ የምንኖርበትን ትንሽ ጎጆን ብንመለከት የቤቱን ጣራ ባለበት ቦታ ለማቆም ስንት ነገር ማለትም በዙሪያው የቆመው ግድግዳ፣ እርሱም ካልበቃው ቁጥራቸው እንደ ቤቱ ስፋት በሚወሰኑ ቋሚዎች /collens/ አማካኝነት ካልሆነ የቤቱ ጣራ ሊቆም አይችልም። ነገር ገን እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰማይ ብንመለከት ይህን ያህል ከአድማስ እስከ አድማስ ሲዘረጋ መደገፊያ ግድግዳ ወይም ቋሚዎች አላስፈለጉትም። ቅዱስ ዳዊት “ሰማያት የእርሱን ጽድቅ /መኖር/ ይናገራሉ።” እንዳለው መዝ. 18፥1 ፤ መዝ. 96፥6
#እግዚአብሔር_ሥነ_ፍጥረትን_ለምን_ፈጠረ?
💚ከዓለማት አስቀድሞ እግዚአብሔር በአንድነት በሶስትነት /አንድነቱ ሶስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሶስትነቱ ደግሞ አንድነቱን ሳይከፋፍለው/ ሲቀደስ፣ ሲሰለስ ይኖር ነበር። ባሕርይው ባሕርይውን እያመሰገነ በክብሩ በጌትነቱ ይኖር ነበረ። ዮሐ 17፥5
#በዓለም_ውስጥ_ያሉ_ፍጥረታት_ስንት_ናቸው?
💚እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት እያንዳንዱ ቢቆጠር ፍጡር ተናግሮ ባልጨረሰው ነበር። ይህን ያህላል ተብሎም በሰዎች አዕምሮም ሊወሰን አይችልም። ነገር ግን በየወገኑ፣ በየወገኑ፤ ብዙውን አንድ፣ ብዙውን አንድ አድርገን ስንቆጥር ሃያ ሁለት ናቸው። “እስከ ሰባተኛይቱ ቀን ድረስ ሃያ ሁለት ፍጥረታትን ፈጠረ።” መ.ኩፋሌ 3፥9 ይላል። ሊቀ ነቢያት ሙሴ የሥነ ፍጥረቱን ቁጥር የሃያ ሁለቱ አርእስተ አበው ምሳሌ አድርጎ ተናገሯል። እነዚህ አርዕስተ አበው ከአዳም ጀምሮ እስከ ያዕቆብ ድረስ ያሉ ናቸው። “ከአዳም ጀምሮ እስከ ያዕቆብ ድረስ ያሉ አበው ሃያ ሁለት ናቸው።”
↪️እንዲሁም አዳም በገነት እያለ ይጸልይባቸው የነበሩ በኋላም ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳቸው ስመ አምላክ /የአምላክ ስሞች ሃያ ሁለት ናቸው። እነዚህም “አሌፍ፣ ቤት፣ ጋሜል፣ ዳሌጥ፣ ዋው፣ ዛይ፣ ሔት፣ ጤት፣ … ታው” መዝ፤ 118፥1 ሰቆ.ኤር. ከምዕ.1-ምዕ.4 ያሉት ናቸው። ስለዚህ የሃያ ሁለቱ ፍጥረታት ቁጥር ከእነዚህ ጋር የተያያዘ ነው።
ይ️🀄️ጥላል
4 374
🌾✞✞✞ #ቅድስት_ሥላሴ ✞✞✞🌾
#ሥላሴን_ቅድስት_ሥላሴ_እያልን_የመጥራታችን_ምስጢር_ምንድን_ነው❓❔❓
💠 አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም።
💠 አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ።
💠 አንድም ሴት አዛኝ ናት፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፥ ይራራሉ፥ ምህረት ይሰጣሉ።
👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል። ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ በማለት ያመሰጥራል። ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፥ ርህራሄያቸውና፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን።
💠 አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም፥ አይፈቅዱም በመሆኑም ቅድስት ይባላሉ።
💠 አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም። ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተዉ ለንስሐ ያደርሱታል።
💠 ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት እንላቸዋለን።
💠 አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው። በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ ቅድስት ይባላሉ።
የእግዚአብሔር አብ በረከት፣
የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣
የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ✞
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
ሴጋ (Masterbation)
ሴጋ (Masterbation) የፈጸመ ሰው ተክሊል ይገባዋል❓
➾ በእምነት ላይ
➾ በትዳር ላይ
➾ በወጣትነት
➾ አጠቃላይ በወደፊት እጣ ፋንታችን ላይ ሚያመጣው ችግር ምንድነው??
➾ ሱሱን እንዴት ልንተው እንችላለን? ምንድነው እንዲህ ሴጋ ልንተው ብለን እንዳንተው ሚያረገን?
➾ ከግብረ አውናን (Masterbation) እንዴት መላቀቅ ይቻላል ?
👆👆በዚህ ዙሪያ ማወቅ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ ቻናላችንን ይቀላቀላሉ👇👇
👉 https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
▰▰▰
በዩቲዩብ ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ!! 👇
👉 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
👉 https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
▰▰▰▰▰
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇
4 374
ሴጋ (Masterbation)
ሴጋ (Masterbation) የፈጸመ ሰው ተክሊል ይገባዋል❓
➾ በእምነት ላይ
➾ በትዳር ላይ
➾ በወጣትነት
➾ አጠቃላይ በወደፊት እጣ ፋንታችን ላይ ሚያመጣው ችግር ምንድነው??
➾ ሱሱን እንዴት ልንተው እንችላለን? ምንድነው እንዲህ ሴጋ ልንተው ብለን እንዳንተው ሚያረገን?
➾ ከግብረ አውናን (Masterbation) እንዴት መላቀቅ ይቻላል ?
👆👆በዚህ ዙሪያ ማወቅ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ ቻናላችንን ይቀላቀላሉ👇👇
👉 https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
▰▰▰
በዩቲዩብ ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ!! 👇
👉 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
👉 https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
▰▰▰▰▰
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇
