የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Kanalga Telegram’da o‘tish
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Ko'proq ko'rsatish4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
4 374
🌾✞ #በእምነታቸው_ዳኑ ✞🌾
https://t.me/EOTC2921
በእምነታቸው ዳኑ ከዚያ ነበልባል /፪/
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /፪/
ናቡከደነፆር ጨካኙ ንጉስ
በባቢሎን ሀገር ጣዖት የሚያነግስ
እያለ ስገዱ አማኙን ሲያምስ
ወጣቶች ተነሱ በቅናት መንፈስ
#አዝ
ለሰራኸው ጣዖት አንሰግድም እያሉ
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልባቸውን ሞሉ
የፈጠረን አምላክ ያድነናል ሲሉ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /፪/
#አዝ
ነበልባል ነዲዱ እንዲያቃጥላቸው
በጭካኔ መንፈስ አስወረወራቸው
ገብተው ሲጸልዩ እቶን ሳይነካቸው
መልአኩን ልኮ አበረደላቸው
ገብርኤል /፪/ በመስቀሉ
#አዝ
እንደ ሦስቱ ህፃናት በእምነት ለሚቆው
መልአኩን ይልካል እግዚአብሔር ሲረዳው
እሳቱም ይበርዳል መልአኩ ሲነካው
ገብርኤል /፪/ በመስቀል
#አዝ
🎤ሊቀ መዘምራን ዓባይ አጥሌ
4 374
#እንደ_አናንያ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
•••
✔ለምሳሌ አንድ አሣ አስጋሪ ሰው መርምህናም ( ማር ምህናም፤ ቅዱስ ምህናም ማለት ነው) እርዳኝ እያለ ሲጠራ ‹‹ወበጊዜሃ መጽአ ኅቡረ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወቅዱስ መርምሕናም ተፅኢኖሙ ዲበ አፍራሲሆሙ...›› ተብሎ እንደተገለጸው ቅዱስ ጊዮርጊስም አብሮ ተገልጾ እንደረዱት የሚነግር ተአምር በገድለ ጊዮርጊስ ተአምሩ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ግን በዋናነት ሊገለጽ የሚችለው በገድለ መርምሕናም እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ በቅዱሳን ዘንድ አንዱ ብቻ ነው እንጂ ሌሎቹ የሉም የሚያስብል ታሪክም ድርጊትም የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ ልዩነት ያለ የሚመስለን መገለጦችን የምንረዳበት ሒደት አነስተኛ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
✔ይህ ከሆነ ታዲያ በሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ገብርኤል ጎልቶ ለምን ይወጣል? በዓል ሆኖ የሚከበረው ለቅዱስ ገብርኤል፤ በሥዕልም ላይ አራተኛው ተብሎ በናቡከደነጾር የተገለጸው ሰው የቅዱስ ገብርኤል ሥዕል ሆኖ የሚሣለው ለምንድን ነው?
✔ይህም የሆነበት ምክንያት ዝም ብሎ ወይም በአጋጣሚ አይደለም፡፡
እግዚአብሔር ሥጋዌውን አስቀድሞ የገለጸው መላእክትንም በሰው አምሳል እንዲገለጹ በማድረግም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ለሙሴ መጀመሪያ የተገለጠለት በዚሁ መንገድ ነበረ፡፡ ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ›› / ዘጸ 3፤2/ ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ይህም ግን ነገረ ተዋሕዶን የሚስረዳ
የምስጢረ ሥጋዌ መገለጥ ነው፡፡
እግዚአብሔር ራሱን በመላእክት አምሳል ሲገልጥ ደግሞ ቅድሚያውን ስፍራ የሚይዘው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ምክንያቱም ገብርኤል ማለት
ቃለ እግዚአብሔር እንዲሁም ሰውና አምላክ ማለት ስለሆነ ነው፡፡ እመቤታችንን ሊያበስር የተላከውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
✔ስለዚህ እግዚአብሔር ለናቡከደነጾር ሥጋዌውን ‹‹ አራተኛ ሰው አያለሁ››
እስኪል ድረስ ሰውነቱን በመገለጥ ያሳየው ከሦስቱ ሊቃነ መላእክት
ይህን ምስጢር በስሙም በተልእኮም ቅዱስ ገብርኤል የተሸከመው በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ሦስቱም ሊቃነ መላእክት በጠባቂ መላእክትነታቸውና ረቂቃን ኃይላት በመሆናቸው ቢኖሩም እግዚአብሔር ሊገልጠው ለፈለገው ታላቅ ምስጢር ተስማሚ የሆነውን (ራሱ ገብርኤል መሆኑ ትርጉምና መልእክት ያለው ነውና) መልአክ በአምሳ ወሬዛ ኀየል ወይም የነገሥታትን ልጅ በሚመስል መንገድ የንጉሠ ሰማይ ወምድር የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ምሳሌ ሆኖ እንዲገለጽለት አደረገ፡፡
በዓሉ ለእርሱ የተሠጠውና ሥዕሉ የእርሱ የሆነበት ምክንያትም ይኸው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ቅድሰት ተዋሕዶ ይህን ሁሉ ምስጢር እንዲህ ባለ ታላቅ ሥርዓተ በዓል እንዲከበር በሥዕልም እንዲታይ በማደረግ ነገረ ሠጋዌውንም የሕጻናቱን ተጋድሎም የመላእክቱንም ጠባቂነት ስትገልጽበትና ስታስረዳበት ትኖራለች፡፡
✔መጽሐፍ ቅዱስን በምልዓት መረዳት ያለው በእውነተኛው የሐዋርያትና የሊቃውንት ትምህርት ትውፊትና ሥርዓተ አምልኮ ጸንታ በምትኖረው ቅድስት ተዋሕዶ ነው፡፡
የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል፡የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና ልመና ረድኤትና በረከት አይለየን።
••• ተፈፀመ •••
4 374
••• በእያንዳንዱ ነገራችንና ፈተናችን ላይ ወደ እግዚአብሔር እያመለከቱ የሚጠብቁን የሚያድኑን የሚያስፈርዱልን ወይም የሚያስፈርዱብንም እነርሱ ናቸውና፡፡
✔እንደናቡከደነጾር ያለውን አስፈርደውበት አውሬ አድርገው ሣር
ያስግጡታል፤ እርሱም ራሱ አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ብሎ አሁንም አረጋግጧል /ዳን 4 ፤13/፡፡ እንደ ሔሮድስ ያለውን ደግሞ ‹‹ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ›› /ሐዋ 12 ፤23/ ተብሎ እንደተጻፈው አስፈርደው ይቀስፉታል፡፡ እንደ ዳንኤል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ዮሴፍ፣
ሠለስቱ ደቂቅ ያሉትን ደግሞ ያድኗቸዋል፡፡ ‹‹... እርሱ ከአዳኝ
ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥
በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዓይኖችህ ብቻ
ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ
እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። ... ›› /መዝ 90 / ተብሎ ተጽፏልና፡፡
✔ጠባቂ መላእክቶቻቸው የሚያድኗቸው ቢሆንም በራእዩ የታየው አንድ ሆኖ ሳለ ሦስቱ ተደርገው በሦስት ድርሳናት ለምን ተገለጸ የሚል ጥያቄም ልናነሣ እንችላለን፡፡ እንዲህ ያሉትን ምስጢራት መረዳት የምንችለው በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ተመሳሳይ ታሪኮችና ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ስናውቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የጌታችንን ትንሣኤ አስመልክቶ አራቱም ወንጌላውያን
መዝግበውልናል፡፡ አራቱም የመዘገቡበት መንገድ ግን ተቃርኖ ባይኖረውም ልዩነት አለው፡፡ አበይት ልዩነቶቹ ሦስት ነገሮች ላይ ናቸው፡፡ የተገለጹት መላእክት ቁጥር ላይ፤ የመጡት ሴቶች ማንነትና ሴቶቹ የመጡበትን ሰዓት በተመለከተ የአዘጋገብ ልዩነት አለ፡፡ ለዛሬው
ለጉዳያችን ቅርበት ያለው የመላእክቱ ብዛት ላይ እናተኩር፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ‹‹እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ
አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ፈጥናችሁም ሂዱና። ከሙታን ተነሣ፥ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው /ማቴ 28 ፤2-7/ ሲል ይገልጻል፡፡
✔ማርቆስ ደግሞ ‹‹ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ፤ ...›› /ማር 16 ፤5/ ይላል፡፡
✔ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ‹‹እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ ›› /ሉቃ 24 ፤4/ ይለናል፡፡
✔ቅዱስ ዮሐንስም ብዙ ነገር ስለ ትንሣኤው ካተተ በኋላ ‹‹ ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም
በእግርጌ ተቀምጠው አየች /ዮሐ 20 ፤ 11-12/ ሲል መዝግቦልናል፡፡
✔እነዚህን አገላለጾች ስናያቸው የአዘጋገብ ልዩነት ቢታይባቸውም ቅራኔና የእውነታ ልዩነት ግን የላቸውም፡፡ ማቴዎስና ማርቆስ ስለ አንድ መልአክ
ማነጋገር ቢገልጹም ሌላ መልአክ እንዳልነበረ ግን አላመለከቱም፡፡ እንዲያውም ማቴዎስና ማርቆስ የመዘገቡልን ስለ አንድ መልአክ ይሁን
እንጂ ሁለቱም የመዘገቡት ግን ስለተለያዩ መላእክት ነው፡፡ ማቴዎስ ከመቃብሩ ወጭ ድንጋዩን አንከባሎ ስለተቀመጠው ዘግቦ ከመቃብሩ ውስጥ በቀኝ በኩል (በራስጌ ወይም በግርጌ) ስላለው አልመዘገበም፡፡ ማርቆስ ደግሞ ውስጥ ከገቡ በኋላ ስላለው መዝግቦ በውጭ በኩል ስላለው ወይም የመቃብሩ ድንጋይ ላይ ስላለው አልመዘገበም፡፡ ሁለቱም ግን ሌላውን መልአክ አልነበረም አላሉም፤ ‹‹የለም›› በሚያሰኝ መንገድም አልገለጹም፡፡ ሉቃስና ዮሐንስ ደግሞ ሁለቱንም መኖራቸውንና በግርጌና በራስጌ መሆናቸውን ገለጹልን፡፡ ስለዚህ
ሁሉም ትክክል ናቸው፡፡ የተለያዩና የማይቃረኑ የተባለው ለዚህ ነው፡፡
ይህም ቢሆን በተዘገበው መንገድ ስለተገለጹት መላእክት ይናገራል
እንጂ በትንሣኤው ዕለት ስለነበሩት መላእክት አጠቃልሎና ዘግቶ
አይናገርም፡፡ የነበሩትን መላእክትም ሁለት ብቻ ነበሩ ማለት ፍጹም
ስሕተት ላይ ይጥላል፡፡
✔ወንጌላውያኑ በዚህ በመላእክቱም ቁጥር ሆነ በሌሎቹ ጉዳዮች
የተለያዩትስ ለምንድን ነው ስንል ደግሞ አንድ መሠረታዊ መልእክት እናገኛለን፡፡ ይኸውም ስለመላእክቱ የተለያየ ዓይነት መገለጥ የገለጹት ለተለያዩ ሰዎች በትንንሽ የጊዜ ልዩነት የታየውን መገለጥና ለአንዳንዶችም በተቀራራቢ ግን በተለያየ ጊዜ የተገለጠውን
ስለመዘገቡ ነው፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ መቅደላዊት ማርያም መመላለሷ ከማሳየቱም በላይ ለእርሷ የተደረገውን የአንድ ጊዜ መገለጥ ብቻ ነው የነገረን፡፡
ሉቃስ ደግሞ ለሌሎች ሴቶች የተደረገውን (ምክንያቱም ተመላልሰው
ያዩም አንድ ጊዜም ያዩ አሉ፤ ብዙ ታሪኮች በውስጡ አሉና) እያሉ ከነጊዜው ስለመዘገቡ እንጂ አንዱን ነጠላ ድርጊት ለያይተውና አሳሰተው መዝግበው አይደለም፡፡ በዚህ መሠረት ቀስ ብሎና በዚህ ጽሑፍ መጀመሪያ ክፍል ላይ እንዳየነው ከመንፈስ ቅዱስ መገለጥ
ተሰጥቷቸውና በጊዜው የነበረውን እውነተኛውን ትውፊት ከሐዋርያትና
ከነበሩት ሰምተው ከተረጎሙት ሳይረዳ ልክ እንደዚያ ርኩሳን እንደተባሉት እንስሳት ሳያመሰኳ ወይም እውነታውን ሳይቆነጥጥ ወይም እንደ አሳዎቹ ሐዋርያት የእምነት መከላከያ ጋሸ (ቅርፊት) እና ምስጢራትን የሚረዳበት ክንፈ ጸጋ ሳይኖረው በአመክንዮ (ሎጂክ) ብቻ እረዳለሁም አስረዳለሁም ቢል ይሳሳታል፡፡
✔ስለዚህ የሠለስቱ ደቂቅ ድኅነትን በተመለከተ በድርሳነ ገብርኤል ላይ
ገብርኤል ተብሎ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ተብሎና በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ከላይ በወንጌል እንዳየነው ያለ ትውፊቱን ለያይቶ መዘገብ እንጂ ተቃራኒ ነገር አይደለም፡፡በዚሁ መሠረት ሦስቱን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልንም ያዳኗቸው ጠባቂ
መላአክቶቻቸው ናቸው፡፡ እነዚህም ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ናቸው፡፡ ልክ ሥላሴ ለአብርሃም በተገለጹለት መንገድ ሦስት ሆነው ከሦስቱ ጀርባ ቆመው መታየት ነበረባቸው ካላልን በቀር ከጥንት ጀምሮ በተላለፈው ትውፊት ሦስቱ መላእክት የሦስቱ ሕጻናት ጠባቂ መላእክት ነበሩ፡፡ እንኳን ሰዎቹ ሦስት ሆነው ይቅርና አንድም ሰው ቢሆን ሦስትና ከዚያ በላይ መላእክት ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ዮናታን ወልደ ሳዖል ‹‹በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና›› /1ኛ ሳሙ 14 ፤ 6/ እንዳለው በአንድም በብዙ ማዳንም የእግዚአብሔር ፈቃድና ምስጢር እንጂ የማነስና የመብዛት
ጉዳይ አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው ነገር እንኳን በመላእክት ቃል ኪዳን ተቀብለው በሚያማልዱና በሚያድኑ ሰማዕታትና ቅዱሳንም ታሪክ ላይ በተደጋጋሚ የተገለጸ መሆኑን ከተለያዩ ገድላት መረዳት ይቻላል፡፡
••• #ይቀጥላል •••
4 374
#ሠለቱ_ደቂቅን_ያዳናቸው_ማን_ነው?
❖በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል ተብሎ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ተብሎና በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ምሥጢሩ ምን ይሆን?
“ታዲያ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣቸው ማን ነው?” ለሚለው የተሐድሶዎች ጥያቄ በመ/ር ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የተሰጠ መልስ፦
✔መጀመሪውንም መጽሐፍ ቅዱሱ ገብርኤል ነው አይልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚለው የሚከተለውን ነው፤
‹‹የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም፤ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ›› /ዳን 3 ፤ 24 -25/ ፡፡
✔በዚህ ገለጻ መሠረት አራተኛውን ያየው ንጉሡ ናቡከደነጾር ነው፡፡
እርሱም አየሁ ያለው አራተኛ ሰው ነው፡፡ የጨመረበት ቢኖር አራተኛው የአማልክትን ልጅ ይመስላል የሚለውን ነው፡፡ ለመሆኑ አራተኛውን ሰው እርሱ ብቻ ለምን አየ? ሌሎቹ ለምን አላዩም? አንደኛው የጥያቄው ቁልፍ ምስጢር ያለው እዚህ ላይ ነው።
✔እውነቱን ለመናገር ይህ ሰው ጥንቱንም ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እሣት
የጣለው ራሱን ምስል አቁሞ ለምስሉ ሕዝቡን በማሰገድ ራሱን አምላክ አድርጎ ሊያስመልክ ነበር፡፡ ታዲያ ራሱንና እርሱን የመሰሉትን አምላክ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ የሚያየውን አራተኛውን ሰው ‹‹የእኛን ልጅ ይመስላል ወይም እኛን ይመስላል›› ለምን አላለም? ከዚያ ይልቅ አርቆ ሌሎች አማልክትን የሚያመልክ አስመስሎ ‹‹የአማልክትን ልጅ›› ይመስላል ያለበት ምስጢር ምንድን ነው? ይህን ያለበት ምክንያቱ ያየው ነገር አራተኛው አካል ከህልውና ያለው በዘር በሩካቤ የተወለደ ሰው እነርሱ ሳያዩት እሳቱ ውስጥ ገብቶ ሳይሆን ነገሩ መገለጥ ስለሆነ ነው፡፡
✔በብሉይ ኪዳን ከተገለጹት ታላላቅ ሦስት የእግዚአብሔር መገለጦች
ውስጥ አንዱ ይህ የሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ነው፡፡ ➊አንደኛው በመምሬ የአድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል የተገለጠው መገለጥ ነው / ዘፍ 18/፡፡ ➋ሁለተኛው ደግሞ አሁንም እግዚአብሔር ለአባታችን ለያዕቆብ
በጎልማሳ አምሳል ተገልጾ ሲታገለው ያደረበት ታሪክና ያዕቆብንም መጀመሪያ ‹‹ካልባረከኝ አልለቅህም›› ከተባረከ በኋላም ‹‹እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው›› /ዘፍ 32 ፤ 25 - 32/ ያሰኘው መገለጥ ነው፡፡ ➌ሦስተኛው ይህ ለባቢሎኑ አላዊ ንጉሥ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት በጣለበት ወቅት ያደረገው መገለጥ ነው፡፡
✔ሦስቱም መገለጦች የሚያመሳስሏቸው ሁለት ጠባያት አሏቸው፡፡ የመጀመሪያው በሦስቱም ጊዜ እግዚአብሔር በሰው መልክና አምሳል መገለጡ ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ ቃለ እግዚአብሔር በሥጋዌ (ሰው በመሆን) ተገልጦ ለሰው ፍጹም ድኅነት የሚሰጥ መሆኑን አስቀድሞ በምሳሌ መግለጽ ነው፡፡ መሠረታዊ መልእክቱ ደግሞ አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ የሚያድነው የተስፋውን ዘር እሥራኤልን ብቻ ሳይሆን አሕዛብንም ጭምር መሆኑን ለማሳየትና አሕዛብም የሥጋዌው ነገር ቀድሞ የተገለጸው ለእሥራኤል ብቻ ስለሆነ እኛ ልናምንበት
አይገባም እንዳይሉ ለዚህ ደንዳናና ጫካኝ ናቡከደነጾርም ጭምር ገለጸለት፡፡ የእነ ነነዌ ታሪክም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሆኖ የተቀመጠውና
እግዚአብሔር ለአሕዛብም ድኅነት ይፈጽም እንደነበር የተዘገበው
እግዚአብሔር የእሥራኤል ብቻ ሳይሆን የሁሉም አምላክ የነበረ መሆኑን ራሱ ብሉይ ኪዳንም ምስክር እንዲሆን ነው፡፡ እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ታሪኮችና ምሳሌዎችም በብዛት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፡፡ ስለዚህ የዚህ በሠለስቱ ደቂቅ ድኅነት ውስጥ የታየው መገለጥ ዋናው ምስጢሩና መልእክቱም የአካላዊ ቃልን ሰው ሆኖ መገለጥና አዳኝ
መሆኑንን በሐዲስ ኪዳንም እንደ ሠለስቱ ደቂቅ እሳትና ስለት፣ ሰይፍና ጎራዴ፤ እስራትና ግርፋት የሚቀበሉትን ሰማዕታት ሁሉ የሚያድናቸው እርሱ መሆኑን መግለጽ ነው፡፡
✔ታዲያ ዋናው መልእክቱና ምስጢሩ ይህ ከሆነ ገብርኤልም ሆነ ሌሎቹ
መላእክት ለምን አዳኑ ይባላሉ? በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት
መሠረት ለሰዎች ከጊዜያዊና ምድራዊ አደጋና ሰዎች ከሚያመጡባቸው መከራ ድኅነት ሲደረግላቸው ድኅነታቸውን
የሚፈጽሙላቸው ቅዱሳን መላእክት ማለትም ጠባቂ መላእክቶቻቸው
ናቸው፡፡ ምንም አንኳ ይህ መሆኑን አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ
ጊዜ ደግሞ በምስጢር ቢገለጽም የእግዚአብሔር መላእክት
ከሚጠብቋቸው ሰዎች ተለይተው አያውቁም፡፡ ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ያዕቆብን ያስገደለው ሔሮድስ ቅዱስ ጴጥሮስንም ለመግደል ባሰረው ጊዜ በዚያ ወቅት ሊሞት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ መልአኩ እንዲያድነው አድርጓል፡፡ ‹‹እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው።
ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም።
የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ። ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ /ሐዋ 12፤ 7 -11/ ተብሎ እንደተጻፈ ሙት ላነሣውና ስንት ተአምራት ላደረገው ቅዱስ ጴጥሮስ አሁን ግን ይህን ሁሉ የሚያደርግለት መልአኩ ነው፡፡ ይህ መልአክ የቅዱስ ጴጥሮስ ጠባቂ መልአክ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት በትርጓሜያቸው አስተምረዋል፡፡
✔በዚሁ ታሪክ ላይ ‹‹ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። እነርሱም፦ አብደሻል አሉኣት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ›› / 13-15 / ተብሎ እንደተጻፈው ውስጥ የነበሩት ጴጥሮስ አይሆንም ‹‹መልአኩ›› ነው ያሏት እርሱን ሊመስልሽ የሚችለው ጠባቂ መልአኩ ነው ለማለት ነበር፡፡ ይህም የሆነው በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ የጠባቂ መላእክት ጥበቃና መገለጥ በሰፊው ይታወቅ ስለነበረ ነው፡፡
✔በመጽሐፈ ጦቢትም ላይ ቅዱስ ሩፋኤል ሰው መስሎ ለጦብያና
ለቤተሰበው እንዲሁም ለራጉኤልና ለቤተሰቡ ቀድሞ ጸሎታቸውን
በማሳረግ በኋላም ከፈተናቸው በማዳንና ሕይወታቸውን በመባረክ ተገልጾ አይተነዋል፡፡
✔እነዚህ ሁለት ታሪኮች የሚያሰረዱን ጠባቂ መላእክት በድሕነታችን ውስጥ ትልቅ ስፋራ የሚሰጣቸውና በርግጥም እነርሱ የሌሉበት ድኅነት የሌለ መሆኑን ነው፤ ልዩነቱ በአንዳንዶቹ ታሪኮች ላይ መገለጣቸው በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ተገልጠው ለሰው አለመታየታቸው ብቻ ነው፡፡
✔ጌታችንም በወንጌል ‹‹ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና›› /ማቴ 18 ፤10/ ያለው ስለ ጠባቂ መላዕክቶቻችን ነው፡፡
••• #ይቀጥላል•••
4 374
❖ አንድም ገብርኤል ማለት ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው (ገብርኤል ብሂል ብእሴ ወአምላክ) እንዲል። የዚህ መልአክ ስም አስቀድሞ የአምላክን ሰው መሆን ይናገራል። ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን “እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የሀገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡ (እሳቱ የሲኦል ሠለስቱ ደቂቅ ደግሞ የቅዱሳን አበው ምሳሌ ናቸው። ይህም በብሉይ ኪዳን ዘመን ምንም እንኳን አበው ፅድቅ ማድረግ ቢችሉም ድኅነት ያልነበረበት ዘመን ስለነበረ ሁሉም መኖሪያቸው በሲኦል ውስጥ ነበረ።
❖ "ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል" ኢሳ.64፥6 እንዲል። ነገር ግን የእግዚኣብሔር ቸርነት ጠብቋቸው የሲኦል እሳት ግን አያቃጥላቸውም ነበር። ናቡከደነፆር የዲያብሎስ ምሳሌ ነው። ምስሉን አሰርቶ ሲያሰግዳቸው እንደኖረ ዲያቢሎስም ህዝበ እስራኤልን 5500 ዘመን ሙሉ ጣኦት ሲያስመልካቸው ኖሯል። በኃላ ግን ናቡከደነጾር ሰለስቱ ደቂቅ እንዳልተቃጠሉ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር አዳኝነትና አምላክነቱን በመመስከር ከእሳቱ እንዲወጡ እንዳዘዘ ሁሉ ዲያቢሎስም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ሩቅ ብእሲ መስሎት ነፍሱን በሲኦል ስጋውን በመቃብር ለመቆራኘት በመጣ ጊዜ በእሳት አለንጋ አስሮ በገረፈው ጊዜ የእግዚአብሔርን አምላክነት መስክሮ ላጠፋው ጥፋቱ ካሳ እንዲሆን በሲኦል ያሉ ነፍሳትን በሙሉ እንዲወስድ ፈቅዶለታል። "መኑ ዝንቱ ዉዕቱ ስጋ ለቢሶ ዘሞዓኒ" እንዳለ። በዚህ መሰረት ሠለስቱ ደቂቅ በዚህ እሳት ሳይቃጠሉ በናቡከደነፃር ትዕዛዝ እንደወጡ ሁሉ በሲኦል ያሉ ነፍሳትም ራሱ ዲያቢሎስ ፈቅዶ እንደወጡ ያሳያል። በጣም የሚገርመው ናቡከደነፆር የእግዚአብሔርን አምላክነት እንዲህ ብሎ መሰከረ። "መንግስቱ ዘለዓለም ወምኩናኑከኒ ለትውልደ ትውልድ" አለ ይህም መንግስቱ ለዘለዓለም አገዛዙም ለትውልድና ትውልድ ነው" ማለት ነው። ዲያቢሎስም በእለተ አርብ ጌታ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት የእግዚአብሔርን አምላክነት በሚገባ መስክሯል በራሱም ፈቃድ ግዛቱን ሁሉና 5500 ዘመን ሲፈፀም በሶኦል የነበሩ ነፍሳትን አስረክቧል።
❖ ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ፤ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ። የእግዚኣብሔርም ስም በአህዛብ ሁሉ ተመሰገነ (ዳን.3)። ይህም ቅዱስ ማቴዎስ ከተናገረው ጋር ይዛመዳል እንዲህ ብሏል። "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" ማቴ 5፥16 የሰለስቱ ደቂቅ መልካም ስራ በአህዛብ ሁሉ ፊት ብርሃን ሆነ።
❖ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መንጎቿ የእምነትን ፍሬ ከእነዚህ ብላቴኖች ተምረው እግዚአብሔርን በማምለክ እንዲጸኑና የመልአኩን የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት እንዲረዱ ታህሳስ 19 ቀን ይህን ዕለት ትዘክራለች። በታላቅ ድምቀትም ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እምነት በድርጊት ሊታይ የሚገባው ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ የሚል ሁሉ ካመነበት ጊዜ አንስቶ ክርስቶስን መስሎ ለመኖር ሊተጋና መስሎ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡ በሠልስቱ ደቂቅ የታየው እምነት በአንድ ጀምበር የተገነባ እምነት ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ በአንድ እግዚአብሔር ታምነው በቅድስና ሕይወት በመመላለስ የመጣ እምነት ነው፡፡ እነዚህ ብላቴኖች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኙትን የድል አክሊል ተስፋ አድርገዋልና አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል የነደደውን የእሳት እቶን አላስፈራቸውም፤ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው ጽኑ እምነት በእሳት ተቃጥለው ለመሞት እንኳ አስጨከናቸው። እንዲህም ሆነው በመገኘታቸው በእምነታቸው እግዚአብሔርን ደስ አሰኙት፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ባለሟሉን ቅዱስ ገብርኤልን በመላክ ከእሳቱ እቶን ታደጋቸው፡፡
❖ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው የድኅነት መንገድ የተጀመረው በቅዱስ ገብርኤል ምስራች አብሳሪነት ነው። "በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት"ሉቃ.1፥26 ይላል። ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል እሳቱን ያጠፋላቸው ዘንድ እንደተላከላቸው ሁሉ በሐዲስ ኪዳንም የውርስ ኃጢአት በክርስቶስ መወለድ ሊጠፋ እንዳለው ዜና ይዞ ተላከ።
❖ ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ታህሳስ 19 ከቅዱስ ገብርኤል በዓል ጋር እንዲከበር ያደረገው ቅዱስ ደቅስዮስ ነው። ይህም የጌታ ስጋዌ መጋቢት 29 ስለሚከበር ይህ ወቅት ደግሞ ፆም በመሆኑ በፆም ወቅት የስጋዌውን በዓል ማክበር ተገቢ ስላልሆነ ከላይ በተመለከትነው መሰረት በዚህ ቀን ቤተ ክርስቲያን ስጋዌውን ታከብራለች።
🙏 የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን። 🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾✞ #ቅዱስ_ገብርኤል ✞🌾
⛪️ ታኅሣሥ 19
❖ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ.33፥7፤ ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡ የመላእክት አንዱ ተግባር መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን ሰዎች መጠበቅ መሆኑ ተጽፏል፡፡
❖ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ.1፥14፤ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱን ሁሉ ሲያስገዛለት በትዕቢት ተሞልቶ “በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም የሚቃወመኝም የለም፡፡” ኢሳ.10፥13-14 ብሎ በመታበይ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ ዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ አቆመው፡፡ በግዛቱ በልዩ ልዩ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉትን ሹማምንቱንና ገዢዎችን ሰበሰባቸው፤ “የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናና የዋሽንትን የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ወድቃችሁ ንጉሥ ናብከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል ስገዱ፡፡ ወድቆም ለማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣል” ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህን አዋጅ የሰሙ የንጉሥ ሹማምንት ሁሉ የመለከቱና የእንቢልታው እንዲህም የዘፈን ድምፅ በተሰማ ጊዜ ተደፍተው ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡
❖ በባቢሎን አውራጃዎች ላይ የተሾሙ አዛርያ(ሲድራቅ)፣ አናንያና(ሚሳቅ) ሚሳኤል(አብደናጎ) ግን ንጉሥ ላቆመው ምስል አልሰገዱም፡፡ ነገር ሠሪዎችም ይህንን ወሬ ለንጉሥ ነገሩት፤ ንጉሥም እጅግ ተቆጥቶ ወደ እርሱ አስጠራቸው፡፡ እርሱ ላቆመው ለወርቅ ምስል ያልሰገዱ እንደሆነ እጅና እግራቸውን ታስረው ወደ እቶን እሳቱ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን “ናብከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አንፈልግም፡፡ ንጉሥ ሆይ! እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፣ ከሚነደውም ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፤ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ፣ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” ብለው መለሱለት፡፡
❖ የንጉሥ ናብከደነፆር ቁጣ ከፊት ይልቅ እጅግ ነደደ እሳቱንም ሰባት እጥፍ እንዲያቀጣጥሉና እነዚህን ሦስት ብላቴኖች እጅና እግራቸውን አስረው ከእነ ማዕረገ ልብሳቸው ከእቶን እሳት ውስጥ እንዲጨምሩአቸው ትእዛዝን አስተላለፈ። ትእዛዙ አስቸኳይ ነበርና ወደ እሳት ጣሏቸው። ወደ እሳቱ የጣሏቸውም ኃያላን በእሳቱ ወላፈን ተገርፈው ሞቱ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሳለ ግን ሠልስቱ ደቂቅ ወደ አምላካቸው “በፍጹም ልባችን እናምንሃለን፣ እንፈራሃለን፣ አታሳፍረን እንጂ ገጸ ረድኤትህንም እንፈልጋለን፡፡” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ነቢያትም በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበረባቸው መከራና ስቃይ ያድናቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጮሁ ይለምኑ ነበርና። "አንስእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ አምላክ ኃያላን ሚጠነ" እያሉ ለምነዋል።
❖ በብዙ ትንቢትና ኅብረ አምሳል የእግዚኣብሔርን መምጣት በትንቢት ተናግረዋል። እግዚአብሔር አምላክ ጸሎታቸውን ተቀበለ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንም ከመጣባቸው መከራ ይታደጋቸው ዘንድ ላከው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም እስራታቸውን ፈታ፤ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዘቀዘው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅም መልአኩን ልኮ ከዚህ እቶን እሳት ያዳናቸውን አምላክ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር፤ ስምህም ለዘለዓለም የተመሰገነና የከበረ ነው” በማለት አመሰገኑት፡፡ ምስጋናውም የቀረበው ቅዱሳን መላዕክት ከሠለስቱ ደቂቅና ቅዱስ ገብርኤል ጋር በእሳቱ ውስጥ እየተመላለሱ አመስግነዋል። ሠለስቱ ደቂቅም ከእስራታቸው ተፈተዋል። ይህም በሐዲስ ኪዳን ያሉ ምዕመናን ከኃጢአት እስራት በተፈቱ ጊዜ በጌታ የልደት ወቅት ከመላዕክት ያመሰገኑት ምስጋና ምሳሌ ነው።
❖ "በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ። እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ"ሉቃ.2፥6 ይላል። ይህ የሚያስረዳን ሠለስቱ ደቂቅ የእግዚአብሔር ልጅ በአምሳለ ገብርኤል በተገለጠላቸውና ባዳናቸው ጊዜ ከመላዕክት ጋር እንዳመሰገኑ ሁሉ በጌታ ልደት ጊዜም እረኞችና መላዕክት በሰው ልጅ ድኅነት ደስ ተሰኝተው "ስብሐት ለእግዚኣብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ" ብለው አመስግነዋል።
❖ የንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር አራተኛውንም ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ “ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን” ዮሐ.11፥49 ብሎ እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም “እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ ምንም የነካቸው የለም፤ የአራተኛውም መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል” ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው፤ በኋላም መልአክ ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ ምስጢሩ ግን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በኃለኛው ዘመን ሰው ሆኖ እንዲወለድና የአዳም ልጆችን ሁሉ ሲያቃጥል ከነበረው የኃጢአት እሳት እንደሚያድን ለናቡከደነፆር ሲገልጥለት ነው። ❝እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?❞ አላቸው፤ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ" ማቴ 16፥16 እንዲል። እንግዲህ ይህን ለቅዱስ ጴጥሮስ የገለጠለትን ምስጢር እግዚኣብሔር በቸርነቱ ለናቡከደነፆር ገልጦለት እንደነበር ማስተዋል ያስፈልጋል።
❖ እግዚአብሔር ለሰዎች በተለያየ መልክ ይገለጥላቸዋል። በዚህ ታሪክ ላይ እንደምናየው የእግዚአብሔር ልጅ በአምሳለ ገብርኤል እንደተገለጠላቸው ያሳያል። ለዚህ ማረጋገጫ መልክዐ ማርያም በሚባለው የጸሎት መጽሐፍ ላይ እንዲህ ይላል። "እግዚአብሔር ኀቤኪ ፈነዎ ቃሎ ገብርኤልሃ አስተማሲሎ። ማርያም አምላከ ዘወለድኪ በተደንግሎ። ..." ይላል። ይህም ማለት እግዚአብሔር አብ ቃል የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስን በገብርኤል አምሳል ወደ አንች ላከው አንችም ማርያም ሆይ አምላክን በድንግልና ወለድሽው ማለት ነው።
#ይቀጥል ---፪
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
4 374
መልካም ዜና!
እነሆ አዲስ መንፈሳዊ መተግበሪያ!
📌መተግበሪያው በውስጡ
👉የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን ያገኙበታል።
መተግበሪያውን ከታች ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል‼️
👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
