የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Kanalga Telegram’da o‘tish
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Ko'proq ko'rsatish4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
4 374
✞✞✞ #ጥንተ_ስቅለት ✞✞✞
መጋቢት 27 የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው፡ ‹‹ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ›› (ማቴዎስ 27፡45) ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች፡፡ እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት፡፡ ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ፤ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች፤ በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር፡፡ እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋር አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡ (1 ጴጥሮስ 3፡18-19) እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ፣ ለእርሱም
ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሡን ሰውቶ ያዳነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል፡፡ የተወደዳችሁ ሆይ፡ የመጋቢት 27 ቀን ክብረ በዓል በሕማማት ቀን ውሎ ስለ ነበር አባቶቻችን ወደዚህ የሚያዝያ ወር በማሸጋገር በዚህ ዕለት እንዲከበር ወስነዋል፡፡ በዓሉም በየ አብያተ ክርስቲያኑ በደመቀ አከባበር አልፏል፡፡
ለዘለዓለሙ የመስቀሉም በረከት በላያችን ይደር፤ አሜን፡፡
(የመጋቢት 27 ቀን ስንክሳር )
4 374
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
ምዕራፍ፡13፤
1፤በሰዎችና፡በመላእክት፡ልሳን፡ብናገር፡ፍቅር፡ግን፡ከሌለኝ፡እንደሚጮኽ፡ናስ፡ወይም፡እንደሚንሿሿ፡ጸናጽል፡ኾኛለኹ።
2፤ትንቢትም፡ቢኖረኝ፡ምስጢርንም፡ዅሉና፡ዕውቀትን፡ዅሉ፡ባውቅ፥ተራራዎችንም፡እስካፈልስ፡ድረስ፡እምነት፡ዅሉ፡ቢኖረኝ፡ፍቅር፡ግን፡ከሌለኝ፡ከንቱ፡ነኝ።
3፤ድኻዎችንም፡ልመግብ፡ያለኝን፡ዅሉ፡ባካፍል፥ሥጋዬንም፡ለእሳት፡መቃጠል፡አሳልፌ፡ብሰጥ፥ፍቅር፡ግን፡ከሌለኝ፡ምንም፡አይጠቅመኝም።
4፤ፍቅር፡ይታገሣል፥ቸርነትን፡ያደርጋል፤ፍቅር፡አይቀናም፤ፍቅር፡አይመካም፥አይታበይም፤
5፤የማይገ፟ባ፟ውን፡አያደርግም፥የራሱንም፡አይፈልግም፥አይበሳጭም፥በደልን፡አይቈጥርም፤
6፤ከእውነት፡ጋራ፡ደስ፡ይለዋል፡እንጂ፡ስለ፡ዐመፃ፡ደስ፡አይለውም፤
7፤ዅሉን፡ይታገሣል፥ዅሉን፡ያምናል፥ዅሉን፡ተስፋ፡ያደርጋል፥በዅሉ፡ይጸናል።
8፤ፍቅር፡ለዘወትር፡አይወድቅም፤ትንቢት፡ቢኾን፡ግን፡ይሻራል፤ልሳኖች፡ቢኾኑ፡ይቀራሉ፤ዕውቀትም፡ቢኾን፡ይሻራል።
9፤ከዕውቀት፡ከፍለን፡እናውቃለንና፥ከትንቢትም፡ከፍለን፡እንናገራለንና፤
10፤ፍጹም፡የኾነ፡ሲመጣ፡ግን፡ተከፍሎ፡የነበረው፡ይሻራል።
11፤ልጅ፡ሳለኹ፡እንደ፡ልጅ፡እናገር፡ነበር፥እንደ፡ልጅም፡ዐስብ፡ነበር፥እንደ፡ልጅም፡እቈጥር፡
ነበር፤ጕልማሳ፡ኾኜ፡ግን፡የልጅነትን፡ጠባይ፡ሽሬያለኹ።
12፤ዛሬስ፡በመስተዋት፡በድንግዝግዝ፡እንደምናይ፡ነን፡በዚያን፡ጊዜ፡ግን፡ፊት፡ለፊት፡እናያለን፤ዛሬስ፡
ከዕውቀት፡ከፍዬ፡ዐውቃለኹ፡በዚያን፡ጊዜ፡ግን፡እኔ፡ደግሞ፡እንደ፡ታወቅኹ፡ዐውቃለኹ።
13፤እንዲህም፡ከኾነ፥እምነት፡ተስፋ፡ፍቅር፡እነዚህ፡ሦስቱ፡ጸንተው፡ይኖራሉ፤ከነዚህም፡የሚበልጠው፡ፍቅር፡ነው።
4 374
•••✞✞✞ #ደብረ_ዘይት ✞✞✞•••
•✞ የዓብይ ጾም ፭ኛ ሳምንት ✞•
☞✞ በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን የክርስቶስ ዳግመኛ ወደ ምድር መምጣትና የዓለም መጨረሻ (ዳግም ምፅአቱ) ይታሰባል፡፡ #ደብረዘይት የቃሉ ትርጉም #የዘይት_ተራራ ማለት ሲሆን በወይራ ዛፍ የተሸፈነ በመሆኑ የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡ ደብረዘይት ይህንኑ እውነታ ጌታ ለሐዋርያት ያስታወቀበት ተራራ ነው፡፡ ዳግመኛም መምጣቱ በዚሁ ተራራ እንደሆነ ይታመናል፡፡ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል።
☞✞ ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸው ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል። ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
#ምስባኩም፦ መዝ.፵፱፥፫ ነው። ትርጉም፦መዝ.49፥3 እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽዕ እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል
ወአምላክነሂ ኢያረምም አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ እሳት በፊቱ ይቃጠላል
☞✞ ይህ ሀይለ ቃል ለቀዳማዊውም ለዳግም ምፅዓቱም ይነገራል:: በቀዳማዊ ምፅዓቱ ግልጥ ሆኖ ይመጣል ሲል፤ በባህርዩ የማይታይ የማይዳሰስ ሲሆን ከእመቤታችን በነሣው ሥጋ የሚታይ የሚዳሰስ ሆኖ ምጣቱን ሲያጠይቅ ነው፡፡ እሳት ይነዳል ማለቱ አልመለስ ካሉ ፈርዶ የሚያጠፋበት ሥልጣኑ የባህርዩ መሆኑን ያሳያል፡፡ ማቴ ፳፫
☞✞ ለዳግም ምፅዓቱ ግልጥ ሆኖ ይመጣል ሲል፤ በክበበ ትስብዕት በግርማ መለኮት የሚመጣ መሆኑን ነው፡፡ ሲመጣም ሁሉ ተካክሎ ያየዋል፡፡ ላንዱ ቅርብ ላንዱ ሩቅ አይሆንም፡፡ አንዱ ከፊት ሌላው ከኋላ አንዱ ከቀኝ ሌላው ከግራ በኩል ሆኜ አየሁት አይልም ሁሉ በእኩል ርቀት ለሁሉ በፊታቸው ይታያቸዋል፡፡ ይህም ግርማ መለኮትን ወይም ምሉዕነቱን ያሳያል፡፡ ሲመጣም ጻድቃን ኃጥአን ፣ያመኑ ያላመኑ ሁለ ያዩታል፡፡ ዝምም አይልም ማለቱ ጻድቃንን ንዐ ኀቤየ(ወደኔ ኑ) ይጠራል፡፡ ኃጥአንን (ሑሩ እምኔን) ከእኔ ሂዱ ብሎ ሲያሰናብት ይሰማልና ነው፡፡ እሳት በፊቱ ይቀጣጠላል የተባለ ፍርዱ ነው፡፡
☞✞ ወንጌሉም ማቴ.፳፬፥፩-፴፮ ነው።
ሐዋርያት በደብረዘይት ሁለት ዓበይት ጥያቄዎች ጠይቀውታል፡፡
#፩. ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ አይቀርም ብሎቸው ነበርና በዚያ አስደናቂ ቤተመቅደስ ላይ ይህ መቼ እንደሚፈፀም ማወቅ ፈልገው ነበር፡፡ ይህም በ፸ ዓ.ም በጥጦስ ዘመን ሆኗል፡፡ ጌታ በቤተመቅደሱ ላይ የተናገረው ፈጥኖ መድረሱ ላላውም በጊዜው ጊዜ መፈፀሙ የማይቀር መሆኑን ያስረግጣል፡፡
#፪. ዳግመኛ መምጣቱ መቼ እንደሚሆን፡- ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? ሐዋርያት በተለያየ ጊዜ ግለሰባዊ ጥያቄዎች እየጠየቁ ከጌታችን ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘታቸው በአሁኑ አጠያየቃቸው ላይ ጥንቃቄ ወስደዋል፡፡ አሁንም ግን “መቼ” የምትልውን ጥያቄ ጌታችን በተለመደው የማይመረመር ጥበቡ አልፏታል፡፡ ቀኑን ቆጥሮ ጊዜውን ሠፍሮ መናገሩ ፍጡራኑን ለሁከት ለጭንቀት ቢዳርግ እንጂ አይጠቅምምና ፤አንድም እውነተኛ ወዳጅ ከአስመሳዩ (ከግብዙ) ይለይበታልና፤አንድም ሰው ከዕለተ ሞቱ ይልቅ ለዳግም ምፅዓቱ ትኩረት በመስጠት ከዕለቲቱ በብዙ ዘመናት የሚርቁት በኃጢአት ተዘፍቀው በበደል ተገርኝተው በሞቱ ነበር፡፡ በዳግም ምፅዓት ይዘን የምንቀርበው በሞታችን ጊዜ የነበረንን ነውና እንዳይጎዱ ቀኒቱን ሠወራት፡፡ ከሞት በኋላ ክፉም ሆነ በጎ ለመሥራት ፤ጻድቅም ሆነ ኃጥዕ ለመሆን፤ለማመንም ሆነ ለመካድ አይቻልምና፡፡ማቴ 24፥36
☞✞ ከዚያ ይልቅ ጌታችን የወደደው ምልክቶቹን መንገር ነው፡፡ ምልክቶቹ በጥቅል ሲታዩ በሁለት መክፈል ይቻላል፡፡
#ሥጋዊ_መከራዎች፡ረሃብ፣ቸነፈር፣ጦርነት፣የተፈጥሮ አደጋዎች፣መንግስት በመንግስት ሕዝብም በሕዝብ ላይ መነሣት ወዘተ…በሥጋ ላይ የሚመጡ መከራዎች ነገር ግን መንፈሳዊነትም ጭምር የሚፈተንባቸው ናቸው፡፡ የሆነው ሁሉ ሊሆን ግድ ነውና ከመማረር ይልቅ ቀናቱ እንዲያጥሩ መፀለይ፡፡ ሌሎች በመከራው ተማረው ከሃይማኖት እንዳይወጡ በክፉ ምግባር እንዳይለወጡ መምከር ማስተማር የመንፈሳዊነት መገለጫ ነው፡፡ በጦርነት ውስጥ ምህረት፣በረሃብ ወቅት ተካፍሎ መብላት ፤በቸነፈር የሞት ጥላ ውስጥ መራራት በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ የታየና የሚጠበቅም ነው፡፡
#መንፈሳዊ_ውጊያዎችን ይህም ዲያቢሎስ የክርስቶስ የሆኑትን ርትዕት ከሆነችው መንገድ ለማውጣት የሚከፍተው ነው፡፡ በዋናነት ከተጠቀሱት “እኔ ክርስቶስ ነኝ” እያለ በስሙ የሚመጡ እንዳሉና ሀሰተኞችም ነቢያትና መምህራንም እንደሚነሱ የተናገረው ነው፡፡ ይህም በየዘመናቱ ተፈፅሟል፡፡ ዛሬም አለ ነገ ይብስ ይመጣል፡፡ የዛሬ መልካምነቱ ከነገ የተሻለ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ የሚብስውን መጠበቅ ማስተዋል ነው፡፡ መፅሐፍ ቢቻላቸው “የተመረጡትን እስኪያስቱ ድረስ” ማለቱ ስህተቱ ምን ያህል በከፋ ደረጃ እንደሚመጣ ያሳያል፡፡ነገር ከመራን ዘንድ ዛሬም በአዲስ አበባ ሀሰተኞች መምህራን ነቢዩ ኤልያስ መጥቷል እያሉ ህዝቡን ማደናገራቸው የዚሁ እውነታ አንዱ መገለጫ ነው፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ብቻውን ሳይ ሆን ከነቢዩ ሄኖክ ጋር እንደሚመጣ በኢየሩሳሌም አንደሚገለጡ ከሐሳዊው መሲህም ጋር ብርቱ ትግል አድርገውና ሀሰተኛነቱን ገልጠው ሕዝበ እግዚአብሔርን ካፅናኑ በኋላ በሰማዕትነት እንደሚሞቱ እናምናለን፡፡ ራዕይ 11፥1-13
☞✞ በቅዳሴ የሚነበቡት ጥቅሶችም፦
፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫-ፍጻሜው
፪ኛ ጴጥ ፫፥፯-፲፭፤
ሐዋ ፳፬፥፩-፳፪ ።
•✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞•
4 374
✞ #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ✞
•••✞✞✞••ማርያም••ማለት••✞✞✞•••
#ማ__ማኅደረ_መለኮት ማለት ነው።
#ር__ርግብየ_ይቤላ ማለት ነው።
#ያ__ያንቀዓዱ_ኀቤኪ_ኲሉ_ፍጥረት ማለት ነው።
#ም__ምስአል_ወምስጋድ_ወምስትስራየ_ኃጢአት ማለት ነው።
#ደግመኛም_ማርያም_ማለት፦ ተፈስሒ ቤተ ይሁዳ ወተሐሰዪ ቤተ እስራኤል ማለት ነው።
#እንድም_ማርያም_ማለት፦ ልዩ ከጣኦት ክብርት እምፍጥረታት ንጽህት እምኃጢአት መልአክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው።
#አንድም_ማርያም_ማለት፦ መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው። ይህስ እንዴት ነው ቢሉ እንሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሷም በፍቅሯ ፤ በጣዕመ ፍቅሯ የሰውን ሁሉ ኃጢአት ክፋት ፍቃ ከልጅዋ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታገባ ስለሆነች ስለዚህ መርህ ለመንግስተ ሰማያት አላት።
#አንድም_ማርያም_ማለት፦ ሰረገላ ፀሐይ ማለት ነው። ይህስ እንዴት ነው ቢሉ እንሆ ዛሬ በዚህ አለም ፀሀይ በሰለገላ ወጥቶ የረጠበውን ያደርቃል፤የበረደውን ያሞቃል ፤የጨለመውን ያስለቅቃል ፤ የተሰወረውን ሁለ ይገልጣል እንደዚህም ሁሉ ጌታችን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ በስጋወ በደሙ ከአብ ከባህርይ አባቱ ከመንፈስ ቅዱስ ከባህርይ ህይወቱ አስታርቆ ከገሃነመ እሳት አውትቶ መንግስተ ሰማያት የሚያገባ ስለሆነ ስለዚህ ሰረገላ ፀሀይ አላት።
#አንድም_ማርያም_ማለት ፦ተላኪተ እግዚአብሔር ወስብእ ማለት ነው። ይኸስ እንዴት ነው ቢሉ መለኮት ከትስብእት ትስብእት ከመለኮት ተዋህዶ በእመቤታችን በእግዝእትነ ማርያም ማኅፀን አድሮ ነበርና ስለዚህ ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ አላት። አንድም የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔር የእግዚአብሔርን ይቅርታ ወደ ሰው እያመላለሰች በፍቅሯ በጣዕመ ፍቅሯ ከልጅዋ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ተላኪተ እግዚአብሔር ወስብእ አላት።
#አንድም_ማርያም_ማለት ፦ውህብት (ስጥውት) ማለት ነው። ይህስ እንዴት ነው ቢሉ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም የተወለደች እለት በአባት ተገኝታለች በኋላ የዓለሙ ሁሉ አማለጅ ሁና ሞታለች ስለዚህ ውህብት (ስጥውት) አላት።
ከዚህም በኋላ እርሱም ፀሀየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በጊዜ ሞቷ ከመከራ ወደ እረፍት፤ ከኀዘን ወደ ትፍስሕት ትሄጅ ዘንድ ሙቺ አላት እርሷም እግዝእትነ ማርያም ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ አንተን ወልጄ ያንተ እናት ሆኜ እኔ እንዴት ልሙት ብትለው እርሱም ፀሀየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በፈቃዷ እንዳልሞተችለት አውቆ ፱፼ ከ፱ሺሀ ከ፱፻ ከ፺፱ ነፍሳት በአንድ ቀን ተኮንነው ገሃነመ ሲወርዱ አሳያት። እነዚህም ነፍሳት እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ባዩ ጊዜ እናታችን እመቤታችን ሆይ ለዘመዱ የሚያዝን አንጀት ራሱን የማይሸከም አንገት አንጀቱም አንጀት አንገቱም አንገት አይደለም ከልጅሽ አስታርቂን ከገሃነም እሳት አውጭን መንግስተ ሰማያት አግቢን ብለው ቢያለቅሱባት እርሷም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ልጄ ሆይ ወጃጄ ሆይ እባክህ ማርልኝ አለችው። እርሱም ጸሀየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ደቂቀ አዳምን ከገሃነመ እሳት አውጥቼ መንግስተ ሰማያት ያገባሁ ተገፍቼ፤ ተገርፌ ፤ተሰቅዬ ፤ተቸንክሬ ፤ሞቼ፤ ተነስቼ አይደለምን? አንቺ ለእነዚህ ነፍሳት በኃጢአታቸው ካልሞትሽላቸው ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ይቀራሉ አላት። እርሷም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እነዚህ ነፍሳት ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ሲቀሩስ ስንኳን አንድ ጊዜ ፯ ጊዜ ልሙት ብላ ሙታለች ኋላም ለፍጥረቱ ሁሉ መጽደቂያ ሁና ተገኝታለችና ስለዚህ ውኅብት (ስጥውት) አላት።
#ደግመኛም_ማሪሃም_ይላታል፦ ለአብርሃም ማለት አበ ብዘኃን ማለት እንደሆነ ስለምን የሁሉ እናት አላት ያለ እግዚአብሔር ያለ ክርስቶስ ልጅ አላትን ቢሉ ያንድ የእግዚአብሔር እናት ነኝና ብላ ትንሽ ትልቁ፤ ክፉ በጎው ቢለምናት ልመናህን አልሰማህም አትለውም አትፀየፈውም የሰውን ሁሉ ኃጢአት ክፋት ፍቃ ከልጅዋ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት እምታገባ ስለሆነች ስለዚህ የሁሉ እናት አላት።
•••✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክበቡር ✞✞✞•••
4 374
#ድንግል_ሆይ_ስላንቺ
•••✞•••✞•••✞•••
ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሀሪ
አማልጅኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ
ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ
ፊቱንም እንዳላይ ስራዬ አስቸገረኝ
#አዝ•••••••
ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ
ትዛዙን እንደሻርሁ ህጉን እንደጣስኩኝ
#አዝ•••••••
በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ
እለምንሃለሁ ከአሁኑ ይቅርታ
#አዝ•••••••
አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሳሪ
አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ
#አዝ•••••••
ፃድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ
#አዝ•••••••
4 374
•✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞•
መጋቢት ፲፱
•••✞ #ቅዱስ_አስከናፍር ✞•••
☞✞ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አስከናፍር የሚባል ደግ ክርስቲያን ማርታ የምትባል በሃይማኖትና ምግባር የምትመስለውን ሴት አግብቶ ይኖር ነበር። እንደ ሕጉና ሥርዓቱ በሥጋ ወደሙ ተወሥነው እንግዳ ቢቀበሉ፥ ነዳያንን ቢያበሉ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ አርቃድዮስና ዮሐንስ የሚባሉ ልጆችን ሰጣቸው።
☞✞ አስከናፍርና ማርታ ልጆቻቸውን ጥበብ መንፈሳዊን (ቃለ እግዚአብሔርን) አስቀድመው አስተምረው ሥጋዊ ጥበብን እዲማሩላቸው ቢልኩዋቸው መንገድ ላይ መርከብ ተሰብሮባቸው ብዙዎቹ ሲሞቱ ወንድማማቾች ግን የመርከብ ስባሪ ወደተለያየ ቦታ አድርሷቸዋል።
☞✞ አርቃድዮስና ዮሐንስ "ወደ ዓለም አንመለስም" ብለው መነኑ። ወላጆቻቸው የሆነውን ሰምተው በጭንቅ ሃዘንና ለቅሶ ለብዙ ጊዜ ኑረዋል። ከዘመናት በሁዋላ ግን የልጆቻቸውን መኖር በራዕይ የተረዱት አስከናፍርና ማርታ ሃብት ንብረታቸውን ለነዳያን አካፍለው ወደ በርሃ መንነው ሔደዋል።
☞✞ ጥበበኛ እግዚአብሔር አራቱንም አገናኝቷቸው ለብዙ ዓመታት በአንድ ገዳም ውስጥ ተጋድለዋል። በዚሕች ዕለትም አራቱም ወደ ሰማያዊው ሠርግ ተጠርተዋል። ••••✞✞✞•••
☞✞ መጋቢት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
➊ ቅዱስ አስከናፍር : ሚስቱ ማርታ : ልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ
➋ ቅዱስ አርስጥቦሎስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር)
➌ ሰባቱ ቅዱሳን ሰማዕታት (ከተለያየ ቦታ ተሰብስበው በክርስቶስ ስም የሞቱ)
☞✞ ወርሐዊ በዓላት
➊ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
➋ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
➌ አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
➍ አቡነ ስነ ኢየሱስ
➎ አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
"እንግዲህ ወንዶች በሥፍራ ሁሉ አለ ቁጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ:: እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ:: እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ: ወይም በዕንቁ: ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።" 1ኛጢሞ 2፥8
•••✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞•••
4 374
•••✞ #ባሰማት_ጊዜ_ቃሉን ✞•••
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልካም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና /2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ
ድንግል ቀረበች ወደእርሱ ፍፁም ትህትና ይዛ
#አዝ•••••••
ትጸንሻለሽ ሲላት መላኩ ፍፁም በልቧ ሳትመካ
እንደቃልህ ይሁን አለችሁ በቃሉ ተማርካ/2/
#አዝ•••••••
የአለም መድኃኒት ነውና ካንቺ እሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ/2/
#አዝ•••••••
እፁብ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ለድንግል ማርያም የተሰጣት ክብር
የአምላክ እናት ሆና መመረጥ ከሴቶች መካከል /2/
#አዝ•••••••
ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ይገባሻል ላንቺ ክብርና ምስጋና
የፍጥረታት ጌታ ሁልጊዜ ካንቺ ጋር ነውና /2/
#አዝ•••••••
4 374
ግሎ በደከመ ጊዜም ሕዝቡ በአልጋ ላይ አስቀምጠው ተሸክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ያደርሱትና ያስተምራቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ በተወለደ በ115 ዓመቱ ጥቅምት 12 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፏል፡፡
🙏የቅዱስ ድሜጥሮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!🙏
4 374
#መጋቢት_፲፪_ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል_ወደ_ጠንቋዩ_በለዓም_ተልኮ_አህያዋን_በሰው_አንደበት_አናግሮ_የእስራኤልን_እርግማን_ወደ_በረከት_የመለሰበት_ዕለት_ነው፡፡
☞✞ ከመላእክት ጋር በማዕድ አብረው ይቀመጡ የነበሩትና የዠማን ወንዝ በሐምሌ ወር አቁመው የተሻሩት፣ ሙታንን በጸሎታቸው ያስነሡ የሸዋው አቡነ አቡነ ተስፋ ጽዮን ዕረፍታቸው ነው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ዳዊት ልጅና የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ወንድም ናቸው፡፡
☞✞ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ለቅዱስ ዲሜጥሮስ ንጽሕናውን
ድንግልናውን ለሕዝቡ እንዲገልጽ የነገረበት ዕለት ነው፡፡ የቅዱስ ዲሜጥሮስም ልደቱ በዚሁ ዕለት ነው፡፡
☞✞ ከፍልስጤም አገር የተገኘው ሰማዕቱ ቅዱስ መላዚ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡
#አቡነ_ተስፋ_ጽዮን፡- ጻድቁ ሀገራቸው ሸዋ ሲሆን የንጉሡ የዐፄ ዳዊት ልጅና የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ወንድም ናቸው፡፡ ስንክሳሩ ‹‹መናኔ መንግሥት ወብእስት›› በማለት ይጠራቸዋል፡፡ አቡነ ተስፋ ጽዮን በመጀመሪያ ‹‹በዓለም ነግሦ መኖርን
አልፈልግም›› በማለት የዓለምን ጣዕም ንቀው በመተው ገዳም ገብተዋል፡፡
በታላቅ ተጋድሎ እየኖሩ አጠቃላይ የመርሐ ቤቴ ገዳማትን ሲመሩና
ሲያስተዳድሩ ነበር፡፡ ጻድቁ በመስቀላቸው በመባረክ በሐምሌ ወር የዠማን ወንዝ አቆመው የተሻገሩ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ብዙ ሙታንን በማስነሣትና ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ነው ወንጌልን ሲሰብኩ የነበረው፡፡ አበታችን ከመላእክት ጋር በማዕድ አብረው ይቀመጡ የነበሩ ናቸው፡፡ በተለያየ ሀገር የሚኖሩ ቢሆኑም ከወለቃው አቡነ ዘአማኑኤል ጋር በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እየተገናኙ ስለ ገዳማት ይወያዩ ነበር፡፡ አቡነ ተስፋ ጽዮን በትግራይ ትልቅ ገዳም ያላቸው ሲሆን በደብረ በግዕና በዜና ማርቆስ ገዳም ደግሞ ቅዱስ ገድላቸው ይገኛል፡፡ ጻድቁ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ጌታችን ተገልጦላቸው ታላቅ ቃልኪዳን ሰጥቷቸው በዛሬዋ ዕለት መጋቢት 12 በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
#ቅዱስ_ድሜጥሮስ_ተካሌ_ወይን፡- ዲሜጥሮስ ማለት ‹‹መስተዋት›› ማለት ነው፡፡ ይህም ታላቅ ጻድቅ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 12ኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ነው፡፡ ከአባቱ ከአርማስቆስና ከእናቱ ኢላርያ መጋቢት 12 ቀን ተወለደ፡፡
አስቀድሞ መጻሕፍትን ያልተማረ ሕዝባዊ ገበሬ ስለነበር በወላጆቹም የወይን
አትክልት ቦታዎች ይሠራ ነበር፡፡
በትንሽ ዕድሜውም ልዕልተ ወይን የምትባል ሚስት አጋቡት፡፡ እርሷም የአጎቱ ልጅ ነበረች፡፡ ባልና ሚስት ሆነው በአንድ አልጋ አብረው እየተኙ ነገር ግን በግብር ሳይተዋቁ መልአክ እየጋረዳቸውና እየጠበቃቸው ለ48 ዓመታት አብረው ኖሩ፡፡ ድንግልናቸውን ንጽሕናቸውን እየጠበቁ ሲኖሩ ይህንን ምሥጢራቸውን ከእግዚአብሔር በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፡፡ ከሐዋርያው ማርቆስ ቀጥሎ በእርሱ መንበር 11ኛው ሊቀ ጳጳሳት የነበረው አቡነ ዮልዮስ ዕረፍቱ በደረሰ ጊዜ መልአክ ተገልጦለት ‹‹ነገ የወይን ዘለላ ይዞ ወደ አንተ የሚገባ ሰው አለ፣ ከአንተ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት የሚሆነው እርሱ ነውና ያዘው›› አለው፡፡ በዚያችም ቀን ድሜጥሮስ ወደ አትክልቱ ቦታ ገብቶ ሳለ ያለጊዜዋ ያፈራች የወይን ዘለላ አገኘ፡፡ እርሱም ‹‹ይህችንስ የወይን ዘለላ ለሊቀ ጳጳሳቱ ሰጥቻቸው በረከት
እቀበልባታለሁ›› ብሎ አሰበና ወደ አባ ዮልዮስ ዘንድ ይዞ ሄደ፡፡ በመንገድም ሳለ
ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ዮልዮስ ዐርፈው ጳጳሳቱና ሕዝቡ ሊቀብሯቸው ሲወስዷቸው
አገኛቸው፡፡ እርሳቸውም ከማረፋቸው በፊት ከእርሳቸው በኋላ ማን እንደሚሾም
ለሕዝቡ ምልክት ነግረዋቸው ነበር፡፡ ይኸውም ‹‹ያለጊዜዋ ያፈራች የወይን ዘለላ ይዞ የሚመጣውን ሰው በእኔ ቦታ እንድትሾሙት የእግዚአብሔር መልአክ
አዞኛል›› ብለው ነግረዋቸው ስለነበር ሊቀብሩ ሲወስዷቸው ድምጥሮስን
ያለጊዜዋ ያፈራች የወይን ዘለላ ይዞ ሲመጣ አገኙትና ከቀብራቸው በኋላ ወስደው በሐዋርያው በቅዱስ ማርቆስ መንበር 12ኛው ሊቀ ጳጳሳት አድርገው
በተወለደበት ዕለት መጋቢት 12 ቀን ሾሙት፡፡ ከሹመቱ በኋላ ቅዱስ ድምጥሮስ በቍርባን ጊዜ ጌታችንን በግልጽ ያየው ነበር፡፡ የሰዎቹም ሁሉ ድብቅ ኃጢአት በግልጽ ይታየው ስለነበር የበቃውንና ያልበቃውን እለየለ ንስሓ ይሰጣቸው ነበር እንጂ በኃጢአት ውስጥ እንዳሉ እንዲሁ በድፍረት ወደ ሥጋወደሙ አያቀርባቸውም ነበር፡፡ በዚህም ብዙዎቹን በቅድስና ጠበቃቸው
ነገር ግን ሰይጣን ያደረባቸው ክፉዎች ሰዎች ቀንተውበት ‹‹እራሱ ሚስት አግብቶ ጋለሞታ ይዞ ሳለ ድንግል ሳይሆንና ሳይገባው በወንጌላዊው ማርቆስ መንበር እየኖረ…›› ብለው አሙት፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦለት ‹‹በአንተና በሚስትህ መካከል ያለውን ቅድስና ለሕዝቡ ግለጥላቸው›› አለው፡፡
ድሜጥሮስም ከቅዳሴ በኋላ ሰው እንደተሰበሰበ ደመራ አስደምሮ ልብሰ
ተክህኖውን እንደለበሰ በሚነደው እሳት ውስጥ ገብቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ በእሳት
ውስጥ እንዳለ ከእሳቱ ፍም አንስቶ በሚከናነብበት ቀጸላ አደረገ፡፡ ሚስቱንም
ጠርቶ መጎናጸፊያሽን ዘርጊ አላትና በመጎናጸፊያዋ የእሳቱን ፍም ጨመረ፡፡ ነገር ግን የእርሱን ቀጸላና የሚስቱን መጎናጸፊያ ምንም እሳት አልነካውም ነበር፡፡ በእሳቱም መካከል በአንድነት እየጸለዩ በቆሙ ጊዜ ሕዝቡ ይህን ተመልክቶ እጅግ አደነቀ፡፡ እርሱም የእሳቱን ፍሕም እያነሳ ቢረጨው ሐሜተኞችን ብቻ እየመረጠ አቃጠላቸው፡፡ ሕዝቡም ቅድስናውንና ንጽሕናውን አይተው በመጸጸት ‹‹ይቅር በለን›› ብለው ይቅር ብሏቸው ስለ ኃጢአታቸው ጸልዮላቸዋል፡፡ ቅዱስ ዲሜጥሮስንም የተአምራቱን ምሥጢር በጠየቁት ጊዜ እንዲህ አላቸው፡-
☞✞‹‹ይህን ሥራ የሠራሁት ከንቱ ውዳሴ ሽቼ አይደለም፣ እንናተ እኔን አምታችሁ እንዳትጎዱ ከዚህችም ሴት ጋር በመካከላችን ተሰውሮ ያለውን ምሥጢር እገልጥላችሁ ዘንድ የእግዚአብሔር መልአክ ስላዘዘኝ ነው እንጂ፡፡ እርሷ የአባቴ የወንድሙ ልጅ ናት፡፡ በሕፃንነቷም አባቷ ስለሞተ በአባቴ ቤት ከእኔ ጋር አደገች፡፡ አካለ መጠንም በደረስን ጊዜ አባቴ እርሷን አጋባኝ፡፡ ወደ ጫጉላ ቤትም በገባን ጊዜ ‹እኔ እኅትህ ስሆን ለአንተ እንዴት አጋቡኝ› አለችኝ፡፡ እኔም የምትፈቅጂ ከሆነ ድንግልናችንን ጠብቀን በአንድነት እንኑር ይህንንም በመካከላችን ያለውን ምሥጢር የሚያውቅ ማንም አይኑር አልኳት፡፡ በዚህም ተስማምተን በአንድ ቤት
ውስጥ በአንድ አልጋ እየተኛን አንድ መጎናጸፊያም እየተጎናጸፍን 48 ዓመት ያህል ኖርን፡፡ ይህንንም ሥራችንን ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ እኔም እርሷ ሴት እንደሆነች አላወቅኋትም እርሷም እኔን ወንድ እንደሆንኩ አታውቅም፡፡ በየሌሊቱም ሁሉ በንስር አምሳል ወደ መኝታ ቤታችን እየገባ ክንፎቹን አልብሶን ያድራል ሲነጋም ከእኛ ይሠወራል›› አላቸው፡፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ መንፈስ ቅዱስ አድሮባልና የብሉይና የሐዲሳትን መጻሕፍት ሁሉ አንብቦ ተረጎማቸው፣ ምሥጢራትም ተገለጡለት፡፡ ባሕረ ሀሳብ የተባለውንም ድንቅ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ሠርቶ ያዘጋጀው ይህ ቅዱስ ድሜጥሮስ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህ ጻድቅ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የቀመረውን ይህን የድሜጥሮስን ቀመር በሚገባ እየተጠቀመችበት ነው፡፡ በዚህ የቀን አቆጣጠር ቀመር መሠረት የደብረ ዘይት፣ የሆሳዕና፣ የትንሣኤና የጰራቅሊጦስ በዓላት ሁልጊዜ በየዓመቱ ከእሁድ አይወጡም፡፡ ስቅለትም ሁልጊዜ ከአርብ አይወጣም፡፡ የጌታችን የዕርገቱም በዓል ከሐሙስ አይወጣም፡፡ ቀመሩንም አዘጋጅቶ ሲጨርስ ለኢየሩሳሌም፣ ለሮሜ፣ ለኤፌሶንና ለአንጾኪያ አገሮች ላከላቸው፡፡ ጻድቁ አርጅቶና ሸም
4 374
#6_ቅትለተ_ዘካርያስ፦
~~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የካህኑ ዘካርያስ መሞት ፣ መገደል ማለት ነው። የእግዚአብሔር
ካህን የነበረው ዘካርያስ የተገደለው በተልዕኮ ላይ እያለ በቤተመቅደስ ውስጥ በመሠዊያው አጠገብ ነበር። እርሱም የሞተው ጥፋት ኖሮበት ሳይሆን በግፍ ነው። እንደዚሁም ሁሉ የእግዚአብሔር ዓይኖች (አዕይንተ እግዚአብሔር) የተባሉ
እውነተኞች ካህናት በሐሳዊ መሲሕ ጊዜ አገልግሎታቸው ለእውነተኛው አምላክ
ለኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ መከራ ይደርስባቸዋል ፣ በአገልግሎትም ላይ እያሉ ይገደላሉ። ስለዚህ ይህ የሚያመለክተው የቅዱሳን ካህናትን መከራ መቀበልና በሰማዕትነት ማለፍ ሲሆን እነ ሄኖክና ኤልያስ ሌሎችም የተሰወሩ ቅዱሳን አባቶቻችን ሞት በሰው ልጆች ትክሻ ላይ የተሰየመ ነውና ወደዚህ ዓለም መጥተው በዚህ አውሬ (ሐሳዊ መሲሕ) ዘመን በሰማዕትነት ያርፋሉ የሞትንም ጽዋ ይቀምሳሉ። ሚል 4፥5 ፣ ማቴ 23፥25-36 ፣ ራዕይ 11፥3-13
--------------------//----------------
#7_ሞተ_ወልደ_እግዚአብሔር፦
~~~~~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት ንፁህና ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ስለሰው ልጆች ፍቅር እና ሕይወት እንጂ
አንዳች በደል ኖሮበት ወይም ተገኝቶበት አይደለም። ንፁሐ ባህርይ አምላክ ሆኖ
ሳለ እውነተኛ ፍርድ ስለጠፋ ነው በቅንዓተ አይሁድ የሞተው ፤ እንደዚሁም በዚህ ሐሳዊ መሲሕ ዘመን እውነተኛ ፍርድ ትጠፋለች ፣ ፍትህ ትጓደላለች ፣
ክርስቲያኖች ያለ አግባብ ይታሰራሉ ፣ ይሰቃያሉ ፣ ይገደሉማል። ዮሐ 15፥18-20
፣ ማቴ 10፥16-20
---------------------//----------------
ከዚህ በኋላ ደግሞ ፦ "ዘንዶው ኃይሉንና ዙፋኑንም ትልቅም ሥልጣን ሰጠው"
ይላል ራዕ 13፥2
#ዘንዶ_የተባለው_ማነው?
~~~~~~~~~~~~~~
የዘንዶውን ማንነት ለማወቅና ለመረዳት ደግሞ ወደ ራዕይ 12፥3 ፣7፣ 9
እንመለሳለን። በዚህ በራዕይ 12፥3 "ታላቅ ቀይ ዘንዶ" ማለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ስለዘንዶው ማንነት ይናገራል። ይህም ዘንዶ የተባለው አባታችንን አዳምና እናታችን ሔዋንን ያሳተው ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ ነው። ዘፍ 3፥1 ^ታላቅ^ መባሉ የቀድሞውን ተፈጥሮውንና ክብሩን ለመግለፅ ነው፣ የመላዕክት
አለቃ ነበርና! "ቀይ" መባሉ ደግሞ ተፈጥሮው እንደ ሌሎቹ ብርሃናዊያን
እሳታዊያን ቅዱሳን መላዕክት ከእሳትና ከነፋስ ስለሆነ ነው። መዝ 103፥4 ፣ ዕብ
1፥7 ፣ ሕዝ 28፥14 ፣ ኢሳ 14፥12 ።
#ምድር_ሁሉ_አውሬውን_ይከተላል ራዕ 13፥4 መላው ዓለም በአውሬው የተመሰለው ይህ ሐሳዊ መሲሕ በሚያደርገው ምትሐታዊ ተአምር ይሳባል ፣ ይደነቃል "እውነተኛ አምላክ ነው" እያለም ይከተለዋል ማለት ነው። በምትሀታዊ ተአምራቱም ሕዝቡን ሁሉ ያስገርም ዘንድ ሥልጣን ለሰጠው ለዘንዶውም ይሰግዱለታል ፣ ይገዙለታል። አውሬውን "ማን
ይመስለዋል? ማንስ ይስተካከለዋል? ብቸኛ ገናና አምላክ ነው" ብለው
ያመልኩታል ማለት ነው። ዘዳ 13፥1-8 ፣ ማቴ 12፥38-39
#አውሬው_ተሳዳቢ_ነው (ራዕ 13:5-7)
አውሬውም ታላቅንም ነገርንና ስድብ የሚናገርበት አፍ ተሰጠው ፣ አርባ ሁለት
ወርም እንዲሰራ ሥልጣን ተሰጠው" ይላል ራዕይ 13:5
ይህ አውሬ (ሐሳዊ መሲሕ) በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ይሰድባል። "እግዚአብሔር ማን ነው? የትስ አለ? እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አምላክ እኔ ነኝ።"
ይላል። እውነተኛውን አምላክ ሰዎች እንዳይረዱና እንዳያመልኩት ርኩስ መንፈስ በልባቸው ያሳድርባቸዋል ፤ ደግሞም ያስታቸዋል። ዛሬም ቢሆን ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ "ፍጡር ፣ አማላጅ" የሚሉ አሉ። እነዚህ ለአውሬው ጥርጊያ መንገድ የሚያዘጋጁ ናቸው። ምክንያቱም በዮሐ 1፥1 ላይ መጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ቃልም ሥጋ ሆነ" ተብሎ የተነገረለትን እግዚአብሔር ወልድን ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አሳንሶ "ፍጡር አማላጅ" ነው ማለት እግዚአብሔር መሳደብ ነው። እግዚአብሔርም ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለምና ፣ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለምና።
አውሬው (ሐሳዊ መሲሕ) ስድቡን በዚህ አያበቃም አርባ ሁለት ወር (ሶስት
አመት ከስድስት ወር) ሙሉ የወደደውን ምትሐታዊ ተአምር እየሰራ ራሱን ብቻ
ከፍ በማድረግ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ይሳደባል። ይላል ሐዋርያው ቅዱስ
ዮሐንስ በራዕይ 13፥6!
#የእግዚአብሔር_ማደሪያ_ማን_ናት?!
የእግዚአብሔር ማደርያ የተባለችው ጌታን ያየንባት በሁለት ወገን ድንግል
የምትሆን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው እመቤታችን ወላዲተ አምላክ
ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።
እንግዲህ ድንግልን ነው ዘንዶውና ተከታዮቹ ማርያም አታማልድም፣ ሞታለች፣ ሌላም ሌላም እያሉ የሚሰናከሉባት። እንግዲህ ትንቢት ነውና ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ! ይማረክም ዘንድ እጁን አይስጥ!!
🙏አቤቱ ወደውና ፈቅደው ከሚጠፋት ጋር አታጥፋን!!🙏
✞ #አሜን_አሜን_አሜን ✞
------------------//----------------
4 374
#7ቱ_ሀገሮች_እና_7ቱ_የኃጢአት_ራሶች
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
➊ ፋርስ
➋ ባቢሎን
➌ ግሪክ
➍ ሜዶን
➎ ግብፅ
➏ ሮም
➐ ኢየሩሳሌም
በመጨረሻው ዘመን እነዚህ ሰባቱ ሀገሮች በሐሳዊው መሲሕ ወይም
በውሸተኛው ክርስቶስ ቁጥጥር ሥር የሚውሉ መላውን ዓለም በክህደት
ትምህርትና በታላላቅ ምትሐታዊ ተአምራት የሚያስቱና የሚያናውጡ ናቸው።
_____________\\____________
#ሰባት_ራሶች፦ የተባሉት በመጨረሻው በሐሳዊ መሲህ ዘመን የሚፈጸሙ
ሰባቱ ዋና ዋና ኃጢያቶች ናቸው። እነዚህም 7ቱ አርዕስተ ኃጣውዕ ወይም 7ቱ የኃጢአት ራሶች ይባላሉ!
እነርሱም፦
➊ ኃጢያተ አዳም (ወይም የአዳም ኃጢያት
➋ ቅትለተ አቤል (የአቤል መገደል)
➌ ጥቅመ ሰናዖር (የሰናዖር ህንፃ)
➍ ኃጢያተ ሰዶም (የሰዶምና ጎሞራ ሰዎች ኃጢያት)
➎ ኃጢያተ እስራኤል (የእስራኤላዊያን ኃጢያት)
➏ ቅትለተ ዘካርያስ ካህን (የዘካርያስ ካህን መገደል)
➐ ሞተ ወልደ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ወልድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት)
ናቸው።
-------------------//--------------
#1_ኃጢያተ_አዳም፦
~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የአዳም ኃጢያት ማለት ነው። የመጀመሪያው ሰው አዳም
አምላክነትንና ፈጣሪነትን ስለሻተና ስለተመኘ አትብላ የተባለውን "ዕጸ በለስን" በላ። በዚህም ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከክብር ቦታ ከገነት ተባርሮ ወጣ። አሁንም በዚህ በመጨረሻ ዘመን የሚነሳው ይህ ሐሳዊ መሲሕ "እኔ አምላክ ነኝ፤ እኔ ፈጣሪ ነኝ፤ ለእኔ ስገዱ" እያለ የሚመጣ ሰው ነው። በሞተ-ወልደ
እግዚአብሔር ተደምስሳ የነበረችውም የአዳም ኃጢያት (አምላክነትን መሻት)
በዚህ በሐሳዊው መሲሕ ዘመን ለመጨረሻ ጊዜ አይላ ትፈፀማለች ማለት ነው። ዘፍ 3:1
በምንም የሚያስታችሁ አይኑር ፤ ክህደት ሳይመጣና የአመፅ ሰው እርሱም
የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያቺ ቀን አትመጣምና። ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ለሁሉም እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ የሚል በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የሚቀመጥ ራሱንም እንደ እግዚአብሔር የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው።" 2ኛ ተሰ 2፥3-5
-------------------//----------------
#2_ቅትለተ_አቤል፦
~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የአቤል መገደል፤ መሞት ማለት ነው። አቤልና ቃየል የአዳምና
የሔዋን ልጆች ናቸው። ዘፍ 4:1-12 ቃየን የገዛ ወንድሙን በግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ገድሎታል። አሁንም በዚህ የአውሬው (የሐሳዊው መሲሕ)
ዘመን መገዳደል እጅግ ይበዛል ፤ ርህራሄ ከሰው ልጆች ዘንድ ትርቃለች።
ወንድም ወንድሙን ይገድላል። እህት እህቷን ትገድላለች ማለት ነው።
ማቴ 10:21-36 "ወንድምም ወንድሙን ፣ አባት ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል።
ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሳሉ ፤ ይገድሉዋቸዋልም።"
-------------------//----------------
#3_ጥቅመ_ሰናዖር፦
~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የሰናዖር ሕንፃ (ግንብ) ማለት ነው። ባቢሎናዊያን በቀድሞ ወቅት
ሰይጣን በልባቸው አድሮ፣ ልባቸው በትዕቢት ተወጥሮ፣ የማይታየውን ረቂቅ
አምላክ እናየዋለን ፣ የማይዳሰሰውን አምላክ እንዳስሰዋለን ፣ በጦርም ወግተን ከዙፋኑ እናወርደዋለን፣ በማለት በእግዚአብሔር ላይ በትዕቢት ተነሳስተው ግንብ መገንባት ጀመሩ። የግንቡም ርዝመት 5532 ክንድ ነበር። በዚህን ጊዜ ጌታ እግዚአብሔር ሦስትነቱን ገልጦ እንዲህ አለ፦ ንዑ ንረድ ወንከአው ነገሮሙ ለከለዳውያን። ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ
እንደባልቀው" ዘፍ 11:7 ወዲያውኑ ቋንቋቸው ተደበላለቀባቸው። ድንጋይ
አቀብለኝ ሲለው ውኃ ፣ ውኃ አቅብለኝ ሲለው ደግሞ እንጨት ያቀብለው ጀመር
፤ በዚህም ዓይነት ቋንቋቸው ተደበላለቀ። እግዚአብሔርም በትዕቢታቸው ምክንያት በተናቸው። (መዝ 2:5) ዛሬም በእኛ ዘመን የሚያጣላን የዘረኝነት ጉዳይ ነው። አስተውለን ካየነው የቋንቋችን ብዛትና ልዩነት በኃጢአታችን ብዛት እንዳንደማመጥና እንዳንስማማ
የተደበላለቀብን እንጂ የጽድቃችን ምልክት አይደለም። አሁንም በዚህ ሐሳዊ መሲሑ ዘመን ከዚህ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ቴክኖሎጂው ይራቀቃል፣ ይሰለጥናል። ሰዎችም እጅግ ኮምፒዩተራይዝድ በሆኑ መሳሪያዎች
እግዚአብሔር ያለበትን ቦታ ለማግኘት ከጨረቃ አልፈው ይመጥቃሉ ፣
እግዚአብሔርን ግን አያገኙትም ፤ አያዩትም። መዝ 2፥4-5 እንዲህ ይላል፦
"በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቅባቸዋል። እግዚአብሔርም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቁጣው ይናገራቸዋል ፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።"
ትንቢተ አብድዩ 1፥1-4 "ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ
መስማትን ሰማሁ ፤ ከባቢን ወደ አሕዛብ ልኮ ፥'ተነሱ ፤ በላይዋም እንነሳና
እንውጋት። እነሆ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ። አንተ እጅግ ተንቀሃል።
በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ እንደሚኖር ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ ፤
በልቡም ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል ፥ በልብህ ትዕቢት እጅግ
አኩርቶሃል። እንደንስር መጥቀህ ብትወጣ ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያም አወርድሃለሁ' ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በዚህም ጊዜ ሐሳዊው መሲሕ እግዚአብሔር የት አለ? አምላክ ፣ ፈጣሪ እኔ ነኝ" ይላል። ለዚህም ሙት ያስነሳል። እሳት ከሰማይ ያወርዳል ፣ ታላላቅ ተዓምራትን ያሳያል። በዚህም እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እያስነገረ በቤተ መቅደስ ይቀመጣል። በዚህን ጊዜ መላው ዓለም አውሬውን ማን ያህለዋል? ማንስ ይመስለዋል? እያለ ይከተዋል፤ ይሰግዱለታልም። ማቴ 24፥23-27 ፣ 2ኛ ተሰ 2፥4 ፣ ራዕ 13፥4
-------------------//----------------
#4_ኃጢአተ_ሰዶም፦
~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት ኃጢያተ ሰዶም ተብሎ የሚጠራው በሎጥ ዘመን በሰዶምና በገሞራ የተፈፀመው የኃጢያት ስራ ነው። ሰዶምና ጎሞራ በአንድ ወቅት ትዕዛዘ-እግዚአብሔርን አፍርሰው ሕጉንም ተላልፈው ለባሕርያቸው የማይስማማውን የማይገባውን እንስሳዊ ግብር በመፈፀማቸው እግዚአብሔር ተቆጥቶ ከሰማይ እሳት (ዲን) አዝንቦባቸዋል። ዘፍ 19፥24 ፣ መዝ 48፥12 ፣ ሉቃ 17፥18-30 ፣ 2ኛ
ጴጥ 2፥6-8 ፣ ሮሜ 1፥22-32
ይህ ግብረ ሰዶም በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ላይ እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው። በተለይም በሰለጠነው ዓለም ይህ ግብረ ሰዶም ሕጋዊ እንዲሆን ተደርገዋል። በብዙዎችም ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷል። ይህ የሚያስረዳን የጊዜው መቃረብና ከዛሬ ሦስት ሺህ ዓመተ በፊት የነበረው ኃጢአት በዚህ ሐሳዊ መሲህ ዘመን እንደ አዲስ መምጣቱንና የግብረሰዶም ኃጢያት በገሀድ እንዲፈጸም መደረጉን ያሳያል። ማቴ 24፥15
------------------//----------------
#5_ኃጢያተ_እስራኤል፦
~~~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት ሀገረ እግዚአብሔር ፣ ህዝቡም "ሕዝበ እግዚአብሔር" ይባሉ
እንደነበር በመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ ሁላችንም የምናውቀው ነው። እስራኤላዊያን ግን በዚያን ጊዜ የአባቶቻቸውን አምላክ የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሔርን ትተውና ረስተው ሕጉንም ተላልፈው በአሕዛብ ጣዖታት ያመልኩና ለጣኦታቱም ይሰግዱ ነበር። እንደዚሁም ሁሉ በዚህ በሐሳዊ መሲሕ ዘመን ብዙ ሰዎች ከአምልኮተ እግዚአብሔር ወጥተውና ተለይተው ወደ ተለያየ አምልኮተ ጣዖት ይገባሉ። የአውሬው (የሐሳዊው መሲሑ) ስምና መንፈስ ፣ መለያ ቁጥሩ ለሆነው 666 ላለበት ጣዖት ይገዛሉ። ራዕይ 13፥15
------------------//----------------------
