uz
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Kanalga Telegram’da o‘tish

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Ko'proq ko'rsatish
4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
#የልዳው_አንበሳ የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ ሦስት ጊዜ ሞቶ ጊዮርጊስ ተነሳ/2/ #አዝ........ በተጋድሎ ጸና........ቅዱስ ጊዮርጊስ በእውነት መሰከረ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያሉ ጊዮርጊስ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ ተመተረ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ የልዳው አንበሳ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠላት አይገዛህ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይጣንን ተዋጋው..ቅዱስ ጊዮርጊስ ጎልማሳው ሥጋህ...ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዲድያኖስ ተቆጣ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ጽናትህን አይቶ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀጣ ተነሳ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ በትዕቢት ተሞልቶ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ባንተላይ ወገኑ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታት........ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምድረ ገፅ አንተን....ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍፁም ለማጥፋት.....ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ......... በመበለቷ ቤት ..........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተአምር ሰራ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ምሶሶ አለምልሞ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ እውራን አበራ................ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባት አክሊላትን ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተቀበለ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ጌታ ፍቅር ..............ቅዱስ ጊዮርጊስ ባደባባይ ዋለ................ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዝክርህን ዘክሮ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ስምህን የጠራ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በነፍስም በሥጋ....ቅዱስ ጊዮርጊስ የለበት መከራ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ደራጎንን አጥፋ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ አርቅልን ከኛ........ቅዱስ ጊዮርጊስ በዝሙት በኃጢአት....ቅዱስ ጊዮርጊስ ደርሶብናልና..............ቅዱስ ጊዮርጊስ

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ተጋድሎ_በኢትዮጵያ_ሊቃውንት 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ የዚኽም ቅዱስ አባቱ በቀጶዶቅያ መስፍኑ አንስጣስዮስ ሲኾን እናቱ ቴዎብስታ ትባላለች፤ የተወለደውም በልዳ በሶርያ ፍልስጥኤም በ፪፻፹ ዓ.ም. ነው፤ ታናሽ ኾኖ ሳለ አባቱ ዐርፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ፈረስ ግልቢያን ተምሮ ኻያ ዓመት በኾነው ጊዜ ቢሩት ሀገር በመኼድ በዚያ ሀገር ይመለክ የነበረውን መንፈሰ ሰይጣን ያደረበትን የመኰንኑን ልጅ እንዲበላት የተሰጠውን ዘንዶ በክርስቶስ ስም ከገደለው በኋላ እጅ መንሻ ይዞ ወደ ንጉሠ ፋርስ ኼደ፡፡ ❖ በዚያ ሀገር ግን ነገሥታቱ ጣዖታትን በማምለክ ክርስቲያኖችን ሲያሳድዷቸው አይቶ ዐዘነ፤ ልቡም በክርስቶስ ፍቅር ነድዶ ወደ ሀገሬ አልመለስም ስለ ክርስቶስ ስም እሞታለኊ አለና “ክርስቲያናዊ አነ ወአአምን በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” (እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው) በማለት መሰከረ፡፡ ❖ ከዚያም ንጉሡ ልብሱን ገፍፈው በዕንጨት ላይ እንዲሰቅሉት፤ ዳግመኛ የዘንባባ እሾኽ የመሳሰሉ ፸ የብረት ችንካሮች ሠርተው በነዚያ እንዲቸነክሩትና ዐጥንቱን ኹሉ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በትዕግሥት በመኾን “እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል” (ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም) አለ፡፡ ❖ ዳግመኛም በውስጡ ረዣዥም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማን ባጫሙት ጊዜ “ሠጠቅዎ ወመተርዎ ዐሥራዊሁ እስከ ውኅዘ ደሙ ዲበ ምድር ከመ ማይ ወሶበ ስዕነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ” ይላል ችንካሮቹ ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ እስኪፈስስ ድረስ እግሩን ዘልቀው ሥሩን በጣጠሱት፤ መኼድም ባልቻለ ጊዜ አጐንብሶ ኼዷል፤ ከዚያም የፈላ የብረት ጋን ውስጥ ከትተው ሰውነቱ በደም እስኪጥለቀለቅ ድረስ ራሱን በመዶሻ ሲመቱት ወደ ጌታችን ጸለየ፤ ያን ጊዜ “ጊዮርጊስ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝና ጽና” የሚል ቃል ከሰማይ መጣለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ከሕመሙ ፈውሶታል፡፡ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡ ❖ ንጉሡም ይኽነን ባየ ጊዜ እጅግ የሚያስጨንቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀን አሠርቶ ለቅዱስ ጊዮርጊስ “እመሰ ትሠውዕ ለአጵሎን ትነሥእ ጌራ መንግሥት ወእመሰ ኊልቊ አንተ ከመ ትትልዎ ለክርስቶስ ነጽር ዘንተ መንኰራኲረ ዘግበርኩ ለከ ከመ እግድፍ በውስቴታ ታማስን ሥጋከ” (ለአጵሎን ብትሠዋ የመንግሥትን ዘውድ ትቀዳጃለኽ፤ ግን ክርስቶስን ለማገልገል የቈረጥኽ ብትኾን ሥጋኽን ትፈጭ ዘንድ በውስጧ ልትጣልባት ያዘጋጀኋትን መንኰራኲር ተመልከት) አለው፤ ይኽ ሲኾን ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣሪው ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ እነርሱም ወደ መንኰራኲሩ በመወርወር ፵ ሰዎች ያዞሩት ዠመር ከዚያም ሰውነቱ ለዐሥር ክፍል ተከፋፈለ፤ እነርሱም ሥጋውን በጒድጓድ ውስጥ ቀበሩት፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመምጣት እንደገና ከሞት አስነሣውና ባረከው፡፡ ❖ ርሱም ከሞት ተነሥቶ እንደገና ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ እነርሱም እጅግ ለመስማት የሚከብዱ መከራዎችን አደረጉበትና ሰውነቱን ጨምቀው አንጀቱን ዘረገፉት፤ ከዚያም ሥጋውን አቃጥለው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ ይድራስ ወደተባለ ተራራ ወስደው ዐመዱን በትነውት ተመለሱ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመውረድ አራቱን ነፋሳተ ምድር የተበተኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋዎች እንዲሰበስቡ አዝዞ እንደገና ከሞት አስነሥቶታል፤ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በክርስቶስ አምነው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም ብዙ ተጋድሎዎችን ለሰባት ዓመታት ከፈጸመ በኋላ ንጉሡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ በሰይፍ እንዲቈረጥ አዝዞ ወደ መሰየፊያው ቦታ ሲኼድ እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያኖች ጸጥ ይል ዘንድ ጸለየ፤ ወዲያውኑም እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት አቃጥሏቸዋል፤ ከዚያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፤ ከዚያም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ሚያዝያ ፳፫ በሰይፍ ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል፡፡ ❖ ከአገልጋዮቹ የቀሩት ሥጋውን ወስደው በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ወደ ሀገሩ ልዳ በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጡ አኖሩት፤ ከርሱም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገልጠዋል፡፡ ❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌ ድርሰታቸው ላይ፦ “ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ” (የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከኾነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለርሱ ኹሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) ርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል) ይሉታል፨ ❖ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቁ አርከ ሥሉስም የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስን ተጋድሎ፡- “ሰላም ለከ ሰርዌ ሰማዕታት አእላፍ ዘሞገሰ ስምከ በጽሐ መንገለ ኲሉ አጽናፍ በቅድመ ፀሓይ ብሩህ ዘኢየዐርብ ለዘልፍ ሕማምየ ዝሩ ነሢአከ ወጸዊረከ እስትንፋሰ አፍ ጊዮርጊስ ቀሊለ ክንፍ ከራድዮን ዖፍ” (ዘወትር በማይጠልቅ በብሩህ ፀሓይ ፊት በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የስምኽ ባለሟልነት የደረሰ የአእላፍ ሰማዕታት አለቃቸው ሰላምታ ለአንተ ይገባል፤ ክንፈ ፈጣን ከራድዮን ዖፍ የተባልኽ ጊዮርጊስ ሆይ የአፍ እስትንፋስን ተቀብለኽና ተሸክመኽ ሕማሜን በትን) እያለ ተማፅኖታል፡፡ ❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለጊዮርጊስ ሰማዕት ዘፀሓየ ጽድቅ ዘተአምሪሁ ከመ ኆጻ ባሕር ዘኢይትኌለቊ ኮከበ ክብር ዘማእከለ ሰማይ ወምድር ዘአርአየ ኀይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር ብእሲ አዛል ወመስተጋድል ኀያል ዝሕዙሐ ገድል”፡፡ (ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኀያል፤ ተጋዳይ ጐልማሳ (ብርቱ) ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን ላይ ኀይልን ያሳየ፤ በሰማይና በምድር መኻከል ያለ የማይቈጠር የክብር ኮከብ፤ ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሓየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት ለኾነ ለጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፨ ❖ የስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ ደራሲ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ፦ "እምብሩር ወወርቅ ይትበደር ሞገሱ ለጊዮርጊስ ቅዱስ በዲበ ጸዐዳ ፈረሱ ለረዲኦትነ ይምጻእ ወያንሶሱ" (ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም) ይለዋል፨ 👇👇👇👇👇👇👇 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥       #የቅዱስ_ሉቃስ_በዓለ_ዕረፍት      ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ ጥቅምት 22 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✅ ቅዱስ ሉቃስ ቊጥሩ ከ72ቱ አርድእቱ ውስጥ ሲኾን በግሪክ ቋንቋ ሉቃስ ማለት ብርሃን የሚሰጥ ማለት ሲኾን በግብሩ ደግሞ “መበሥር” (አብሣሪ) ተብሏል፤ ምክንያቱም ቅዱስ ገብርኤል ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ተልኮ አምላክን እንደምትፀንስ ያበሠራትን ብሥራት የጻፈ ሲኾን ይኽ ወንጌላዊ በስሙ የተጠራለት ወንጌልንና የሐዋርያት ሥራን ጽፎልናል፤ ይኽ ወንጌላዊ ሐኪም (ዶክተር) ነበር፤ በኋላ ግን የነፍስ ሐኪም እንዲኾን ክርስቶስ መርጦታል፤ ቅዱስ ጳውሎስም ✍“የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል” በማለት መስክሮለታል 📖ቆላ 4፥14 ✅ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታን የስቅለቱን ሥዕል እንደሣለ በተመሳሳይ መልኩ ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ለመዠመሪያ ጊዜ የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል የሣለ ነው የመልክአ ሥዕል ደራሲም ✍“ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱ ሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ” 👉ከወንጌላውያን አንዱ ዐዋቂ ሉቃስ በእጅ ለሣላት ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል ብሏል፤ ይኽቺም የሣላት የእመቤታችን ሥዕል ከላይዋ ላይ ዘይት እየፈሰሰ፤ ወዝ እየወዛ ብዙ ተአምራትን ትሠራ ነበር፤ ዓለም ዐቀፍ ሊቃውንትም ‘Saint Luke painting the Virgin Mary’ በማለት ሲታወቅ፤ በሰማዕታት ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች በመከራው ሰዓት በሚደበቁበት ግበበ ምድር (ካታኮምብ) ዋሻ ግድግዳ ላይ ቅዱስ ሉቃስ እንደሣላት እያስመሰሉ የእመቤታችንን ሥዕሏን ይሥሉ ነበር፡፡ ✅ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ እንደምናነብበው በ460 ዓ.ም. ያረፈው የንጉሥ ቴዎዶስዮስ 2ኛ ሚስት ኢውዶኪያ “መራሔ ፍኖት” ተብላ የምትጠራውን ቅዱስ ሉቃስ የሣላትን ሥዕል ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለንጉሥ አርቃዴዎስ ልጅ ለፑልቼሪያ ልካላት ነበር፤ ቅዱስ ሉቃስ በዘመኑ ሰባት የእመቤታችንን ሥዕል የሣለ ሲኾን የተለያዩ ጥንታውያን ሀገራት ውስጥ ሲገኙ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥንታውያን ገዳማት ውስጥ ቅዱስ ሉቃስ የሣላቸው የእመቤታችን ሥዕላት በተለያየ ጊዜ መጥተዋል (Cormack, Robin (1997) Painting the Soul, Icones, p.46)፡፡ ✅ ይኽ ቅዱስ ሉቃስ ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት በሮሜ ካረፉ በኋላ ርሱ ወደዚኽች ሀገር ገብቶ ወንጌልን ሲሰብክ ጣዖታት ይደቅቁ ነበር፤ ካህናተ ጣዖታቱም አማልክታቸው እየረገፉ መውደቃቸውን ሲመለከቱ በንዴት ልብሳቸውን ቀድደው ጠጒራቸውን ይነጩ ነበር፤ ከዚያም ወደ ንጉሡ ኔሮን ኼደው ነገሩት፤ ርሱም ይኽነን በሰማ ጊዜ ተበሳጭቶ ባስቸኳይ ተይዞ እንዲመጣ አዘዘ፤ ሉቃስም ከዚኽ ዓለም መውጫው እንደ ደረሰ በመንፈስ ቅዱስ ዐውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ በመኼድ ዓሣ ያጠምድ የነበረውን አረጋዊ ጠራው፤ ርሱም በሉቃስ ላይ ያደረውን ጸጋ እግዚአብሔር ባየ ጊዜ በእግሩ ሥር ወድቆ ሰገደ፤ ርሱም ከወደቀበት አንሥቶ መጻሕፍቱን በመስጠት ✍“ዕቀብ እሎንተ መጻሕፍተ እስመ እማንቱ ይበቊዓከ ወያበጽሓከ ውስተ ፍኖተ እግዚአብሔር” 👉ወደ እግዚአብሔር መንገድ መርተው ያደርሱኻልና እሊኽን መጻሕፍት ጠብቃቸው ብሎታል፡፡ ✅ ከዚያም በወታደሮች ተይዞ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቈሞ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ ንጉሡም በብስጭት የቅዱስ ሉቃስ ደም እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲገረፍ አደረገ፤ ከቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በመዠመር ወንጌልን የጻፈውን የቀኝ እጁን እንዲቈረጥ አዘዘ፤ በቈረጡት ጊዜ ✍“ኦ ንጉሥ አእምር ከመ ኢንፈርህ ሞተ ዝንቱ ዓለም ወዘንተ ብሂሎ ነሥኣ ለምትርት እዴሁ ዘየማን በፀጋማይ እዴሁ ወአስተላጸቃ ውስተ መካና ወኮነት ድኅንተ ከመ ቀዳሚ” ይላል 👉ንጉሥ ሆይ እኛ የዚኽን ዓለም ሞት እንደማንፈራ ዕወቅ፤ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኀይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይኻለኊ ካለው በኋላ ብሥራተ ድንግልን የጻፈባት ሥዕሏን የሣለባት የተቈረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቈረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደቀድሞዋ ጤነኛ አድርጓታል፤ ይኽነንም አይተው 477 ሰዎች አምነዋል፤ ከዚያም ንጉሡ ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሳቸው እንዲቈረጥ አዝዞ ጥቅምት 22 የምስክርነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡ ✍ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን በዐርኬው ላይ ሲገልጽ “ሰላም ለሉቃስ እንተ ረትዐ ልሳኑ ወንጌለ መለኮት ይጽሐፍ እምእለ ብዙኃን ወጠኑ ከመ ያርኢ ኀይለ ቅድመ ኔሮን ወተዐይኑ አስተላጸቃ ወሌለያ ለምትርት የማኑ እስመ ላዕሌሁ ተሰውጠ ለክርስቶስ ሥልጣኑ” 👉ብዙዎች ሊጽፉት የዠመሩት ከመኾኑ የተነሣ የመለኮትን ወንጌልን ይጽፍ ዘንድ አንደበቱ ለቀና ለሉቃስ ሰላምታ ይገባል፤ በኔሮንና በሰራዊቱ ፊት ኀይልን ያሳይ ዘንድ የተቈረጠች ቀኝ እጁን ለያት መልሶም አጣበቃት በርሱ ላይ የክርስቶስ ሥልጣን ተጨምሯልና በማለት ጽፎታል 📚ስንክሳር ጥቅምት 22፤ ገጽ 227-229 ✅ቅዱስ ሉቃስ ሆይ ቅዱስ ወንጌልን በጻፈው እና የአምላክን እናት ሥዕሏን በሣለው እጅኽ እንድትባርከን እንለምንኻለን፡፡ 📌 ምንጭ ✍ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ 📚መዐዛ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ

የሚጠብቀኝ አይተኛም.m4a8.93 KB

አድነኝ አምላኬ.m4a8.84 KB

ተስፋዬ ድንግል ናት @EOTC2921 ግጥም.3gp4.68 KB

#አምላክን_በድንግልና_የወለደች_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ተአምራት_አድርጋ_ደቀ_መዝሙር_ማትያስን_ከእሥር_ቤት_ያዳነችበት_ዕለት_ነው፡፡ 📖ጥቅምት 21📖 ✞ ንግሥና ንቀው የመነኑ፣ ታቦተ ጽዮንን 40 ዓመት ያጠኑ፣ አንበሳን 7 ዓመት ውኃ ያስቀዱት፣ 22 ዓመት ተረግዞ ኖሮ በኃላ በጸሎታቸው ኃይል ፂምና ጥርስ ያለው ልጅ እንዲወለድ ያደረጉት ታላቅ ጻድቅ አቡነ አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ + ነቢዩ ቅዱስ ኢዩኤል ዕረፍቱ ነው፡፡ + ጌታችን ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሥጋው ፍልሰት ሆነ፡፡ ✞ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ በተባለው በንጉሣችን በዐፄ ዳዊት ዘመን የነበሩትና ከእርሱም ጋር መልካም ግንኙነት የነበራቸው የኢየሩሳሌሙ አባ ዮሐንስ ዐርፈዋል፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ኢዩኤል፡- ይኸውም ቅዱስ ነቢይ የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር፡፡ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም መኖርና የሕይወትን ትምህርት ማስተማሩን በትንቢት ተናግሯል፡፡ ደግሞም በጌታችን ላይ ይደርበት ዘንድ ስላለው መከራው ትንቢት ተናገረ፡፡ በሐዋርያት፣ በሰባ ሁለቱ አርድእትና በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- ‹‹በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ፤ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ፣ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ፡፡ ያንጊዜም ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል፡፡›› ነቢዩ ኢዩኤል ዳግመኛም ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት ትንቢት ሲናገር ‹‹ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፣ ከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል›› አለ፡፡ ነቢዩ የትንቢቱን ወራት ከፈጸመ በኋላ እግዚአብሔርን አገልግሎ በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፏል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! #የቅዱስ_አልዓዛር_የሥጋው_ፍልሰት፡- ይኸውም ቅዱስ አልዓዛር ከሞተ ከ4 ቀን በኋላ ጌታችን ከሞት ያስነሣውና ተአምሩን ያደረገለት ሲሆን እርሱም ወንጌልን እየሰበከ ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገ ክርስትናን አስፋፍቷል፡፡ በተሾመባት ቆጵሮስ ከተማም የመጀመሪያው ጳጳስ በመሆን እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ መጋቢት 17 ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ቅዱስ አልዓዛር በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ ከክርስቲያን ነገሥታት መካከል አንዱ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቁስጥንጥንያ አፈለሰው፡፡ ሊያፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የድንጋይ ሣጥን ውስጥ ሆኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት፡፡ በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ፡- ‹‹ይህ በመቃብር ውስጥ አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ነው፡፡›› ይህንንም ጽሑፍ ባነበቡ ጊዜ ደስ ተሰኝተው ተሸክመው ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ወሰዱት፡፡ ካህናቱም ሁሉ በዝማሬ በክብር ተቀበሉት፡፡ ባማረ ቦታ አስቀምጠውት በዚህች ዕለት በዓሉን አደረጉለት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! #የኢየሩሳሌሙ_አባ_ዮሐንስ፡- ከደጋግ ክርስቲያን ቤተሰብ ተወልደው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምረው ነው ያደጉት፡፡ በቅስና ማዕረግ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ አባ ዮሐንስ በጾም በጸሎት ምጽዋትም በመሥጠት፣ድኆችን በመርዳትና በስብከታቸው በእጅጉ ይታወቃሉ፡፡ ከብዙ ተጋድሎአቸውም በኋላ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት ሆኑ፡፡ ሰውም ስለ ቅድስናቸው በጣም ይወዳቸው ነበር፡፡ ጻድቁ እግዚአብሔርን በትጋት እያገለገሉ ሳለ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስ አባ ዮሐንስን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ዐፄ ዳዊትን እንዲለምኗቸው ነገሯቸው፡፡ እስላሞች በእስክንድርያ እያመፁ ሲያስቸግሩ የኢትዮጵያው ንጉሥ ዐፄ ዳዊት ሄዶ ፈጅቷቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ዐፄ ዳዊት እስላሞችን እንዳይፈጃቸው መልአክት ይነግሩት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን የምስር አገሩ ንጉሥ ጠየቃቸው፡፡ አባ ማርቆስም ወደ ኢትዮጵያው ንጉሥ ዐፄ ዳዊት የሚላኩ ሰዎችን ከመኳንንቱና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ከሀገር ታላላቅ ሽማግሌዎች ጋር ተማክሮ የኢየሩሳሌምን አባ ዮሐንስንና የምስሩን አገር አባ ሳዊሮስን በአስተዋይነታቸው፣ በዕውቀታቸውና በቅድስናቸው መርጠዋቸው ወደ ኢትዮጵያ ላኳቸው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን ታዛዥ ሆነው ወደ አገራችን መጡ፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት አሽከሮቹን አስከትሎ ወጥቶ ሄዶ አክብሮ ተቀበላቸው፡፡ ከእነርሱም በረከትን ተቀበለ፡፡ እነርሱም የአባ ማርቆስን ደብዳቤ ሰጡት፡፡ ዐፄ ዳዊትም ደብዳቤውን ተቀብሎ አንብቦ ለሊቀ ጳጳሳቱ ቃል ታዛዥ መሆኑን ገለጠላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ዮሐንስና አባ ሳዊሮስን ወደ ሀገረ ስብከታቸውና ሕዝባቸው ተመልሰው ይሄዱ ዘንድ አልተዋቸውም ስለ ቅድስናቸውና ስለ ትምህርታቸው ጣዕም በጣም ወዷቸዋልና በእርሱም ዘንድ እንደ መላእክት ሆነዋልና፡፡ ከጥቂት ወራትም በኋላ አባ ዮሐንስን ከዚህ ዓለም ድካም ያሳርፋቸው ዘንድ እግዚአብሔር ወዷልና ጥቂት ሕማም ካገኛቸው በኋላ ዐርፈዋል፡፡ የአባ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን! #እመቤታችን_ለሐዋርያው_ማትያስ_ያደረገችለት_ተአምር፡- የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡ ሐዋርያው ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ ጌታችንና ወደ እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡ እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ይዘው በአንገታቸው ገመድ አግብተው ለ3 ቀን በሀገራቸው ጎዳናዎች ላይ ሁሉ ጎተቱዋቸው፡፡ ሁለቱም ሐዋርያት በጸሎታቸው ከእሥር ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃ አፈለቁና ውኃው ሀገራቸውን ሁሉ እስኪያጥለቀልቅና ሰዎቹንም እስከ አንገታቸው ድረስ እስከሚደርስ ሞላ፡፡ ሁሉም በተጨነቁ ጊዜ ሁለቱ ሐዋርያት በፊታቸው ተገለጡና ‹‹በጌታችን እመኑ ትድናላችሁ›› በማለት ወንጌልን ሰብከውላቸው አሳመኗቸው፡፡ ምሥጢራትንም ሁሉ ገለጡላቸው፡፡ ደግሞም የአራዊት ጠባይን ከሰዎቹ ያርቅላቸው ዘንድ ወደ ጌታችንና ወደ ተወደደች እናቱ ከጸለዩ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ያ የአውሬነት ጠባያቸውም ጠፍቶላቸው የዋህ፣ ቅንና ሩኅሩኆቸ ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመውላቸው ወደ ሌላ ሀገር ሄዱ፡፡

ባሰማት ጊዜ @EOTC2921.m4a5.64 KB

•••✞ #ባሰማት_ጊዜ_ቃሉን ✞••• •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልካም ዜና እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና /2/ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ ድንግል ቀረበች ወደእርሱ ፍፁም ትህትና ይዛ #አዝ••••••• ትጸንሻለሽ ሲላት መላኩ ፍፁም በልቧ ሳትመካ እንደቃልህ ይሁን አለችሁ በቃሉ ተማርካ/2/ #አዝ••••••• የአለም መድኃኒት ነውና ካንቺ እሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ትሰይሚዋለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ/2/ #አዝ••••••• እፁብ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ለድንግል ማርያም የተሰጣት ክብር የአምላክ እናት ሆና መመረጥ ከሴቶች መካከል /2/ #አዝ••••••• ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ይገባሻል ላንቺ ክብርና ምስጋና የፍጥረታት ጌታ ሁልጊዜ ካንቺ ጋር ነውና /2/ #አዝ•••••••

#ገብርኤል_ማን_ነው? 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 #ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡ #ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ 👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ 👉*ገብርኤል ነው፡፡* የአሸናፊና የኃይል መልአክ *ገብርኤል ነው፡፡* ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ *ገብርኤል ነው፡፡ 🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏 ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ሀለዉ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ወተቀበልዋ ኲሎሙ ነፍሳተ አበው እለ አዕረፉ እምአዳም እስከኔሁ ወሰገዱ ላቲ እንዘ ይብሉ ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘፈጠረ ለነ ኪያኪ ሥጋ እምሥጋነ ወዐፅመ እምዐፅምነ” ይላል መላእክት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉበትን የጻድቃን የማረፊያቸውን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ ወደ ገነት አሳረጓት፤ በዚያም ከአዳም ዠምሮ እስከዚያው ያረፉ ያባቶች ነፍሳት ተቀብለዋት “ከዐፅማችን አንቺን ዐጥንት ከሥጋችን አንቺን ሥጋ ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባው” እያሉ የአክብሮት ስግደት ሰግደውለታል፡፡ ❖ ከዚያም መላእክት የጻድቅ ሰው ነፍስ ከሥጋው ሲለይ ያለውን ፍጹም ክብርና የሚወርሰውን የገነት ርስቱን መላእክት ካሳዩዋት በኋላ፤ ኃጥኣን ነፍሳቸው ከሥጋቸው ሲለይ ያላቸውን ጭንቅ ነፍሳቸው በሲኦል የምትቀበለውን ከፍተኛ መከራ አሳዩዋት፤ “ወሶበ ተስእኖሙ አምስጦ ይቤሉ እንዘ ይኬልሑ ኦ እግዝእትነ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን ንዒ ኀቤነ ከመ ትፍትሕነ እማእሰሪሁ ለሰይጣን ወኢትኅድግነ” ይላል ለማምለጥ ባልተቻላቸውም ጊዜ “የመድኅን እናቱ የብርሃን መገኛ እመቤታችን ሆይ ከዚኽ ከዲያብሎስ ቊራኝነት ታላቅቂን ዘንድ ድረሺልን ቸል አትበዪ” እያሉ ምልጃዋን ሽተው በታላቅ ጩኸት ያለቅሱ ዠመር፡፡ ❖ ያን ጊዜ ርኅርኅት የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ወይ ሎሙ ወአሌ ሎሙ መኑ እምዜነዎሙ ለውሉደ ሰብእ ኢይምጽኡ ዝየ” (ወዮላቸው ወዮታ አለባቸው ወደዚኽ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ኹሉ ማን በነገራቸው) እያለች ስታለቅስ፤ መላእክትም ለርሷ “ኢትፍርሂ ኦ ማርያም እስመ እግዚአብሔር ምስሌኪ ወምስለ እለ የአምኑ ብኪ” (እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ስለኾነና ባንቺ አማላጅነት ከአመኑት ኹሉ ጋር ስለ አለ አይዞሽ) በማለት ነገሯት፡፡ ❖ ርሷም “እስእለከ እግዚኦ ወአስተበቊዐከ በእንተ ኲሉ ዘየአምን ብየ ረስዮ እግዚኦ ግዑዘ እምሲኦል ተዘኪረከ ረኃበ ወጽምዐ ወኲሎ መከራ ዘረከበኒ ኀቤከ ወምስሌከ” (አቤቱ በኔ ቃል ኪዳን ስላመነ ኹሉ እማልድኻለኊ እለምንኻለኊ፤ መራቤን መጠማቴንም ካንተ ጋር በምድረ ግብጽ ያገኘኝን ረኃብና ጥም ኹሉ አስበኽ አቤቱ ወደ ሲኦል ከመውረድ ነጻ አድርገው) በማለት ወደ ልጇ ፍጹም ልመናን አቀረበች። ❖ ጌታችን ተገልጾላት “ይኩን በከመ ትቤሊ እፌጽም ለኪ ኲሎ መፍቅደኪ አኮኑ ተሰባእኩ በእንተ ዝንቱ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ከመ ኢይሔሱ ኪዳንየ” (የለመሺዉን ኹሉ ይደረግልሽ፤ የምትፈቅጂውን ኹሉ እፈጽምልሻለኊ የለመንሺዉን ኹሉ ላደርግልሽ ሰው ኹኜአለኹና፤ መሐላዬን እንዳላፈርስ አማንየ በርእስየ ብዬ በራሴ ማልኹልሽ) ሲል ለእናቱ የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳንን ገብቶ ገብቶላታልና በዓሉ “ኪዳነ ምሕረት” በመባል ይታሰባል:: ❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በዝማሬው ላይ ጌታ ለእናቱ ስለገባላት ቃል ኪዳን፡- ✍ “ይቤላ ለእ ማርያም እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተካየድኩ ምስሌኪ ኪዳነ ምሕረት ከመ አድኅን ዘተአመነኪ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ዘመሐልኩ አነ ለኖኅ ገብርየ ወለአብርሃም ፍቁርየ፤ ዘመሐልኩ አነ ለዳዊት ኅሩይየ ብእሲ ምእመን ዘከመ ልብየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ በቅዱስ ሥጋየ ወበክቡር ደምየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ከመ ኢይሔሱ ማእኰትየ” ✍(ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያምን እንዲኽ አላት በምልጃሽ ያመነብሽን አድን ዘንድ ካንቺ ጋራ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተጋባኊ፤ ለአገልጋዬ ለኖኅና ለወዳጄ ለአብርሃም ቃል የገባኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ እንደ ልቤ ለምለው ለታመነው ለዳዊት የማልኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ በቅዱስ ሥጋዬና በክቡር ደሜ የማልኊ እኔ ምዬ እንደማልከዳ ማልኹልሽ) በማለት ጽፎታል፡፡ [በቀራንዮ ከፈጣሪያችን የተቀበልንሽ ስጦታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን] ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ኪዳነ ምሕረት ✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ቃል ኪዳን” የሚለው ቃል 257 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፤ ኪዳን ማለት ቃል “ተካየደ” ከሚለው ከግእዝ ቃል የወጣ ሲኾን “ተዋዋለ፣ ተስማማ፣ ተማማለ” ማለትን ሲያሳይ እግዚአብሔር ሰውን ከማፍቀሩ የተነሣ ለሰው ልጅ እንደ ባልንጀራ አድርጎ መሐላን ይምላል፣ ቃል ኪዳንም ይገባል፡፡ ❖ ክቡር ዳዊት በመዝ 88፡2-3 ላይ “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” እንዳለ ከኹሉም ቅዱሳን በላይ ኾና ሰማይ ምድር የማይወስኑትን አምላክ በማሕፀኗ ለመሸከም፣ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚሸከሙትን ሰማያዊ መለኮትን በዠርባዋ ለማዘል፣ በክንዷ ለመታቀፍ፣ ሰማይ ምድር ከፊቱ የሚሸሹትን የባሕርይ አምላክን በከናፍሮቿ ለመሳም፣ ፍጥረታትን ኹሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሓይ አብስሎ የሚመግበውን፤ ለቅዱሳን መላእክት ርሱ የገለጸላቸው ምስጋና ምግብ ኹኗቸው እንዲኖሩ ያደረገውን ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለውን እግዚአብሔር ወልድን የድንግልና ጡቶቿን ለማጥባት ከተመረጠች ከእናቱ ጋር የገባው ጽኑዕ የምሕረት ቃል ኪዳን እጅግ ልዩ እና ለኃጥኣን ኹሉ ተስፋ የሚኾን ነው፡፡ ❖ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልም በአምላክ እናት ፊት ቆሞ “ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻልና አትፍሪ” በማለት ከፍጡራን ወገን ማንም ሊያገኘው የማይችለውን ይኸውም በልዑል እግዚአብሔር ዘንድ መወደድን በማግኘት ከባለሟልነት ኹሉ የላቀ ባለሟልነት ይኸውም የአምላክ እናት የመኾንን የማማለድ ልዩ ጸጋና ክብር እንደተሰጣት ነግሯታል፡፡ ❖ መልአኩ በዚኽ ምስጋናው ላይ “ሞገስን አግኝተሻልና” አለ እንጂ “ወደ ፊት ታገኛለሽ” አለማለቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንቱኑ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተጠበቀችና በልዑል የተመረጠች መኾኗን የሚያረጋግጥም ነበር፡፡ ከዚኽ ከተሰጣት ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ልጇን በማሳሳብ ውሃው ወደ ወይን እንዲለወጥ አስደርጋለች (ዮሐ 2፡1-10)፡፡ ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እንደምናነብበው በአምላካቸው ፊት ባለሟልነትን ያገኙ ብዙዎች ቅዱሳን ቢኖሩም ቅሉ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ግን ለነዚኽ ኹሉ ቅዱሳን ሰማያዊ ክብርን ቃል ኪዳንን የሰጠውን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና በመውለዷ “ወላዲተ አምላክ” የመባል ታላቅና ልዩ ባለሟልነት ተሰጥቷታልና የርሷ ክብር ከማንም ቅዱሳን ክብር ጋር ፈጽሞ የማይነጻጸር ነው፡፡ ❖ ከ 432-447 ዓ.ም ሴሌኡሲያ ላይ ጳጳስ የነበረው ሊቁ ባስልዮስም እግዚአብሔር ለእናቱ የሰጣት ልዩ ባለሟልነትን ከቅዱሳን ጋር በማነጻጸር ሲጽፍ “What encomiums can we offer her as she deserves, when everything of this world is beneath her merits?...” (የሚመጥናትን ምን ዐይነት ልዩ ምስጋና እናቅርብላት? የዚኽ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር “ዓለም አልተገባቸውም” (ዕብ ፲፩፥፴፰) ካላቸው፤ ለአምላክ እናትማ ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሓይ ለኾነችው ለርሷ ምን ልንል እንችል ይኾን? (ራእ ፲፪፥፩)... ምን ምስጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናንና አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነ አስተውል፤ ታዲያ የአምላክን እናት ታላቅነት ኹሉም ሰው እንደምን አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ላገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ (የሐዋ ፭፥፲፭)፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ ፲፱፥፲፩)፤ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? ✔ ለቅዱሳኑ ይኽነን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሰደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይኾን? በምን ዐይነትስ ስጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ “ክርስቶስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ” ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቊልፍ ከተሰጠው (ማቴ ፲፮፥፲፮-፲፱)፤ ርሷ ከኹሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትኾን? (ሉቃ ፩፥፵፭)፤ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ “ምርጥ ዕቃ” ከተባለ (የሐዋ ፱፥፲፭)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች ርሷ ምን ዐይነት ልዩ ዕቃው ትኾን? ✔ ነገር ግን ስለርሷ ብዙ እናገራለኊ ብዬ ስለክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኊ ስለዚኽ ካኹን ወዲኽ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጬአለኊ) በማለት በእግዚአብሔር ፊት የተሰጣት ባለሟልነት ፍጹም እንደኾነና ከቃላት በላይ እንደኾነ አስተምሯል፡፡ ❖ ዳግመኛም ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን ካገኙት ሞገስ የተነሣ ወደ ፈጣሪያቸው እንዲያማልዱን ስንማጸናቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ግን የአምላክ እናት ናትና ካገኘችው ከዚኽ ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ወደተወደደው ልጇ እንድታማልደን እንማጸናታለን፤ ከዚኽም የተነሣ ነው ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬምም በእሑድ ውዳሴ ማርያም ላይ፦ ✍ “ለኪ ይደሉ ዘእምኲሎሙ ቅዱሳን ትሰአሊ ለነ ኦ ምልእተ ጸጋ…” (ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ኹሉ ይልቅ ትለምኚልን ዘንድ ላንቺ ይገባል፤ አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጪያለሽ፤ ከነቢያትም ከመምህራንም ትከብሪያለሽ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ፤ በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ) በማለት ያመሰገናት፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ካገኘችው ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ፭ሺሕከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ያለ ዘርዐ ብእሲ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና የፀነሰች፤ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በኅቱም ድንግልና የወለደች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በጀርባዋ ያዘለች ርሷ ብቻ ናትና፤ በርሷ አማላጅነት የምናቀርበው ጸሎት ምን ያኽል ታላቅ እንደኾነ በሰዓታት መጽሐፉ ላይ፡- ✍“ወፈድፋደሰ በእንተ ማርያም እምከ እንተ ይእቲ ትምክህተ ዘመድነ …” (ይልቁንም የባሕርያችን መመኪያ ስለምትኾን ስለ እናትኽ ስለ ማርያም አንተን በመፅነስና አንተን በመውለድ ዕድፍ ጒድፍ ስላላገኘው ስለ አልተለወጠ ድንግልናዋና ስለ ተሸከመኽ ማሕፀኗ፤ ስለ ታቀፉኽ ስለ ክንዶቿና፣ ስለ ዳሰሱኽ ስለ እጆቿ፤ ስለ ሳሙኽ ስለ ከንፈሮቿ ስለ አሳደጉኽ ስለ ጡቶቿ፤ ከአንተ ጋር ስለ ተመላለሱ ስለ እግሮቿና፤ ስለ ዐዘለኽ ስለ ጀርባዋ፤ ብሩሃት ስለሚኾኑ ስለ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ስላላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች ስለሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ስለ ተበሠሩ (ብሥራትን ስለ ሰሙ) ስለ ጆሮቿ፤ ከርሷ ስለነሣኸው ሥሮችና ጸጒር፣ ደምና፣ ዐፅም ስለ ነፍስና ሥጋ፤ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮትነትኽ ጋራ አንድ ያደረግኸው) በማለት እንዳስተማረ፤ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ባለሟልነት እንዳገኘች በብርሃናዊዉ መልአክ የተመሰከረላት የአምላካችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ታማልደን ዘንድ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያልን እንማጸናታለን፡፡ ❖ ይኸውም ታላቁ የነገረ ማርያም መጽሐፍ እንደሚያስረዳን ጌታችን ካረገ በኋላ እመቤታችን ጌታችን ወደ ተቀበረበት ጎልጎታ እየኼደች ትጸልይ ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸው በየካቲት ፲፮ ዕለት ስትጸልይ “አዕረግዋ ውስተ ሰማይ ከመ ያርእይዋ መካነ ዕረፍቶሙ ለጻድቃን ኀበ

#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር ••••• #የመጨረሻው_ክፍል •••• #የባልንጀራህን_ሚስት_ንብረት_አትመኝ አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ ፣በሐሰት አትመስክር በማለት ክፉ አድራጎትን ወይም የጥፋት ሥራዎችን የሐሰት ንግግሮችን ይከለክላል። #አትመኝ በማለቱ ደግሞ ክፉ ምኞትንና መጥፎ ሐሳብን ይከለክላል። በውጭ በተግባር የሚደረጉት ከውስጥ በልቡናችን ከሚፈፀሙት ጋር ማለት ከምኞትና ከሐሳብ ጋር እንደሚታየው እንደ ግንዱ የተያያዙ ናቸው። ሥሩ ደኀና ከሆነ ግንዱም ደኀና ይሆናል። አንድ ነገር በድርጊት ከመፈፀሙ በፊት ነገሩ የሚጠነሰሰውና የሚጀመረው በምኞትና በሐሳብ ውስጥ ውስጡን ነው። ክፉ ሰው ከልቡ ክፋ ነገርን ያወጣል ፤ ደግ ሰው ግን ከልቡ ደጋግ ነገሮችን ያወጣል። #መመኘት ማለት የሌላውን ሰው ሚስት /ባልና ሀብት ለራስ እንዲሆን መፈለግና ማሰብ ስለሆነ አንድ ነገርን የተመኘ ሰው ጊዜና ቦታ ባይገድበውና ሁኔታዎች ቢመቻቹለት በልቡ የፈለገውን በሐሳብ ያቀደውን፣ በስሜቱ የፈቀደውን ከማድረግ አይመለስም። ስለዚህ የኀጢአት ምንጩ የወንጀል አባቱ በልቡና የሚገኘው ክፉ #ምኞት ነው። ስለዚህ የሰውን ንብረት ከመመኘት መታቀብ አለብን። ይህንንም ለማጥፋት እና ኀሊናን ለማፅዳት መትጋት አለብን። የሕግ ሁሉ ፍፃሜና ማጠቃለያ #ፍቅር ነው። ሁሉም ትዕዛዞች በፍቅር ይጠቃለላሉ። ባልንጀራውንም አምላኩንም የሚወድ ህግን ይጠብቃል። ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞

#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር ••••• #ክፍል_9 ••••• #በሐሰት_አትመስክር ምስክርነት ምን ማለት ነው? በሐሰት መመስከርስ እንዴት ነው? #ምስክርነት ማለት በዳኛ ፊት ወይም በባለሥልጣን ፊት ወይም በአስታራቂ ሽማግሌዎች ወይም ስለ ሥነ ስርዓት ጉዳይ በተሰየመ ጉባኤ ፊት የቀረበውን ሙግትና ክርክር በትክክል ለመፍረድና ለመወሰን የሚረዳ የቃል ማረጋገጫና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያመለክት ነው ። በእውነት የሚቀርበው ምስክርነት በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ያስመሰግናል። ነገር ግን ሰዎች በልዩ ልዩ ጥቅም ተገዝተው ወይም ባልንጀራን አለአግባብ ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲባል እውነቱን ነገር በመሸሸግ ሐሰት ነገር በመፍጠር ያልተነገረውን ተነገረ ያልተደረገውን ተደረገ በማለት በመሐላም ሆነ ያለ መሐላ የሚቀርበው የውሸት ማስረጃ ሁሉ የሐሰት ምስክርነት ይባላል። በኀብረተሰቡ ውስጥ እውነትና ሐቅ ጠፍቶ ፍርድ ጎድሎ ድሀ ተበድሎ ሰዎች ሁሉ ጊዜያቸውንና ኃይላቸውን ገንዘባቸውንም በክርክርና በጠብ እንዳያጠፋና ሰላማቸውን እንዳያጡ በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ በማሰብ እግዚአብሔር "በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር" የሚለውን ትእዛዝ እንድንጠብቀው ሰጥቶናል። ይህን ትዕዛዝ መተላለፍ ትልቅ በደል ነው። #በመጀመሪያ መስካሪው እውነት እመሰክራለው ብሎ የገባውን ቃል ኪዳን ወይም መሐላ አፍርሶ ውሸት በመናገሩ፣ #2ኛ ዳኛውን በማሳሳት የሐሰት ፍርድ በማስፈረዱ፣ #3ኛ የተፈረደበትን ሰው ሳያጠፋ በማስቀጣቱ በደሉ ብዙ ነው። ይህ ትዕዛዝ ቀጥታ ምስክሮችን ብቻ የሚመለከት አይደለም። ልዩ ልዩ የሐሰት መረጃዎችን በማዘጋጀት ሰነዶችንና መዝገቦችን በማጭበርበርና በማዘዋወር አስመስሎ በመፈረምና በተሰረቁ ማኀተሞች በመጠቀም እንደዚሁም ሌሎች ይኽን የመሰሉ በተንኮል የተቀናበሩትን ሁኔታዎች በማመቻቸት የሚያስፈርዱትንና የሚፈርዱትንም ሁሉ ይመለከታል። ስለዚህ ምስክርነታችን ሁሉ #በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ። •••••••✞ #ይቀጥላል ✞•••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር •••••• #ክፍል_8 ••••• #አትስረቅ፦ መስረቅ ማለት የሌላውን ገንዘብና ንብረት መውሰድ ሲሆን አወሳሰዱም ባለቤቱ ሳያውቅ ወይም በማታለል ወይም በኀይል ይፈፀማል። #ጉቦኝነትም ሰዎች በሥልጣናቸው አማካኝነት የሌላውን ገንዘብ የሚወስዱበት ወይም ጥቅም የሚያገኙበት መንገድ እስከሆነ ድረስ ስውር ስርቆት ነው ማለት ይቻላል። አባይ ሚዛንም ስርቆት ነው። "ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው ፡ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም " ተብሎ ተፅፏል። (ምሳ 20:23) የሰውን ገንዘብ ከመውሰድ የከፋ ነገር ቢኖር የቤተክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት መስረቅ ነው። ምክንያቱም ይህንን ያደረገው ሰው ከስርቆት ወንጀል ሌላ የእግዚአብሔርን ስም አቃሏል፤ ሃይማኖቱንም ክዷል ማለት ይቻላል። ስለዚህ አድራጎቱ የበደል በደል ነው። እንደዚህ አይነት ሰው ባልንጀራውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው የበደለው። ሌሎችም እንደስርቆት የሚቆጠሩ ነገሮች አሉ። በምቀኝነትም ይሁን በተንኮል ወይም በግፍ የሰውን ገንዘብና ንብረት ማስቀረት ወይም መቀነስ ወይም ማቆየት ነው። የሰራተኞችን ደመወዝ ማስቀረት ወይም አለአግባብ ደመወዛቸውን መቁረጥ አሰሪዎችን በደለኞች ያደርጋቸዋል። ቅዱስ ያዕቆብ "እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮሀል፡፡ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባኦት ጆሮ ገብቷል ። " (ያዕ5:4) ሌላው የአደራ ገንዘብን መብላትና የተዋሱትን የተበደሩትን ገንዘብ አለመመለስም እንደ ስርቆት ይቆጠራል። የተሳሉትን ስዕለት፣ የገቡትን ብፅዓት አለመፈፀም እግዚአብሔርን መበደል ነው። ልንፈፅመው የማንችለውን ነገር ቃል አለመግባት ይሻላል። አስራት በኩራትን ማስቀረት እግዚአብሔርን መስረቅ ነው። ሰዎች ሁሉ እንኳን የሌላውን ገንዘብ መስረቅ ቀርቶ የራሳቸውንም እንዲያካፍሉ ታዘዋል። ስለዚህ የቀማን መልሰን የበደልን ክሰን ያለንን አካፍልን ከስርቆት ተቆጥበን ልንኖር ይገባል። •••••••✞ #ይቀጥላል ✞•••••••

#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_ዓርማ https://telegram.me/EOTC2921 1, #የዓርማው_ቅርጽና_ይዘት ፩. መደቡ ነጭ ፪. ዙሪያው የስንዴ ዛላና የወይን ዘለላ ፫. ከላይ ከአናቱ አክሊል፤ ከታች ከግርጌው መሐል ለመሐል ወጥቶ አናቱ ከአክሊሉ ሥር የደረሰና መስቀል ያለበት አርዌ ብርት ፬. በግራ ኹኖ በቀኝ እጁ አርዌ ብርት፤ በግራ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ፤ በቀኝ ኹኖ በግራ እጁ አርዌ ብርት በቀኝ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ ፭. ከአርዌ ብርቱ ሥር “ነዋ ወንጌለ መንግሥት” ተብሎ የተጻፈበት ቅዱስ መጽሐፍ ፮. ከቅዱስ መጽሐፍ ሥር መስቀለኛ የ”ጸ” ፊደል ቅርፅን የሚመስል፤ ኹለቱ ጫፎቹ ከመደቡ ወደ ውጭ የወጣ ሰበን፤ ፯. የስንዴ ዛላና የወይን ዘለላ በተገናኙበት የዓለም ምስል፤ ያለበት ይኾናል፡፡ 2, #የዓርማው_ትርጉም ሀ/ #መደቡ_ነጭ_መኾኑ ዘመነ ሥጋዌ የምሕረት የደስታና የነፃነት ዘመን መኾኑን ያመለክታል። (ዮሐ.፳፥፲፪፤ የሐዋ. ሥራ ፩፥፲) ለ/ #የዓርማው_ዙሪያ_በወይን_ዛላና #በስንዴ_ዘለላ_የተከበበ_መኾኑ ምዕመናን በቅዱስ ቊርባን አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን፣ ስርየተ ኃጢአትን፣ የዘለዓለም ሕይወትን የሚያገኙ መኾናቸውን ይገልጻል። (ዮሐ. ፮፥ ፶፫-፶፰፤ ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ መዝ. ፬፥፯) ሐ/ #በዓርማው_መሐል_ቀጥ_ብሎ #የቆመ_የዓርዌ_ብርት_ምስል_በበላዩ_ላይ #መስቀል_ከዚያም_ከፍ_ብሎ_አክሊለ #ክህነት_አለው_የዚኽ ትርጉም ሕዝበ እስራኤል ዓርዌ ብርቱን ባዩ ጊዜ ከእባብ መርዝ እንደ ዳኑ ኹሉ መስቀል ላይ በተሰቀለ በጌታችን በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ኹሉ በዲያቢሎስ ምክንያት ከመጣባቸው ፍዳ ኃጢአት የሚድኑ መኾናቸውን መስቀሉ የቤተ ክርስቲያንc የድኅነት ዓርማ መኾኑን። (ዘኍ. ፳፩፥፰፤ ዮሐ. ፫፥፲፬) መ/ #አክሊል ቅዱሳን በሰማያዊ መንግሥት የሚቀዳጁትን አክሊለ ክብር እና ማኅተመ ጽድቅን ያመለከታል። (ዘጸ. ፴፱፥፴፤ ፩ተሰ. ፪፥፲፱፤ ፪ጢሞ. ፬፥፰፤ ፩ጴጥ. ፭፥፲፬፤ ራእይ ፪፥፲፤ ፬፥፲፬) ሠ/ #ኹለት_መላእክት_የዘንባባ #ዝንጣፊና_ዓርዌ_ብርቱን_ይዘው #ይታያሉ_ይህም_ዘንባባ። በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ መንፈሳዊ ደስታንና ድኅነተ ነፍስን ያመለክታል ቅዱሳን መላእክት የቤተ ክርስቲያን ጠባቂዎችና የመልካም ዜና አብሣሪዎች መኾናቸውን ያሳያል ዓርዌ ብርቱን ይዘው መቆማቸው ነገረ መስቀሉን አምኖና ሃይማኖቱን አጽንቶ ይዞ የሚኖር የዘለዓለም ድኅነትን የሚያገኝ መኾኑን ያመለክታል። (መዝ. ፺፥፲፩፤ ሉቃ. ፲፫፥፮-፱፤ ዕብ. ፩፥፲፬) ረ/ #የዓርማው_መሀል_ቅዱስ_መጽሐፍ ሆኖ፥ “ #ነዋ_ወንጌለ_መንግሥት ” #የሚል_ጽሑፍ_በበላዩ_አለበት_የዚኽ_ትርጉም። የቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖት ቀኖና እና ትውፊት በቅዱስ መጽሐፍ ትምህርት ላይ የተመሠረተ መኾኑን ያመለክታል፡፡ (ማቴ. ፳፬፥፲፬) ሰ/ #የወይኑ #የስንዴው_ዛላና_ዘለላ_በተገናኙበት ላይ የሚታየው ክብ ነገር፥ ዓለምን (የሚወክል: ኾኖ ዓለም በክርስቶስ መዳኑን ያመለክታል፡፡ (ዮሐ. ፫፥፲፯) 3. #የዓርማው_ክብር ሀ/ #ዓርማው የቤተክርስቲያኒቱ ሉዓላዊ ክብር መገለጫ ስለኾነ በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ ሀገር የሚገኙ ቤተክርስቲያን መዋቅር /ቤቶች ከዚኽ ዓርማ በቀር ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡ ለ/ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ደብዳቤ ኾኖ ይህ ዓርማ የሌለበት ማኅተምና የማዘዣ የሚጠቀም ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጽ/ቤት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞

#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር ••••• #ክፍል_7 •••• #አታመንዝር አቅመ አዳምና አቅመ ሔዋን የደረሱት ወንድና ሴት ከጋብቻ በፊትም ሆነ በኀላ ሕግ ከሚፈቅድላቸው የጋብቻ ግንኙነት ውጭ የሚፈፅሙት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሁሉ #አመንዝራነት ወይም #ዝሙት ይባላል። ይህም አድራጎት በ7ኛው ትዕዛዝ የተከለከለ ነው። አመንዝራነት በገነነበት ሀገር ሕጋዊ ጋብቻ ይናቃል። #ጋብቻ ከሌለ ጤናማ ቤተሰብ አይኖርም። ጤናማ ቤተሰብ ከሌለ ደግሞ ጠንካራ ኀብረተሰብና ጥሩ ዜጎችን ማግኘት አይቻልም። እንዲያውም ከሐዲና ዘማዊ ትውልድ ይፈጠራል። ይህም የሀገርን ውድቀት ያስከትላል። የእግዚአብሔርን እርግማን ያመጣል። ስለዚህ በልዩ ልዩ በደልና ክፋት የተያዙትን በተለይም በዓመፅ ስራና በዝሙት ኀጢአት ብዛት ከገፀ ምድር የጠፋትን የኖኀ ዘመን ሰዎችን (ሰብአ ትካትን ) በአብርሃም ዘመን የነበሩትን ሰዶምና ገሞራን እያሰብን ከዝሙት ራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል። ቤተክርስቲያን በዝሙት እንዳንወድቅ የምትሰጠው መፍትሄ አለ። ይኸውም፦ ራሳችንን በከፍተኛ ደረጃ በመቆጣጠር፣ በተዓቅቦ መኖር፡ አንድ ወንድ በአንዲት ሴት፡ አንዲት ሴት በአንድ ወንድ መፅናት እንዲሁም መንፈሳዊ ተጋድሎ ማድረግ ነው። የዝሙት የርኩሰት ሥራ ሁሉ እንስሳዊ ባህርያችንን ስለሚያጎላም በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረችውን ነፍሳችንን በጣም ይጎዳታል። የዝሙት ኀጢአት በድርጊት ብቻ የሚፈፀም ሳይሆን (በሀልዩ) በሐሳብ፣ በምኞት ጭምር የሚፈፀም ነው። ጌታችን በወንጌል "አታመንዝር እንደተባለ ሰምታቹሀል። እኔ ግን እላቹሀለሁ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሯል። /ማቴ5:27/ እንግዲህ ይህ ድርጊት አልባ የሆነው የዝሙት ምኞትና ሐሳብ ቆይቶ ወደ ድርጊት ስለሚያመራ በቅድሚያ እሱን መቆጣጠር የመጀመሪያው ሥራችን መሆን ይገባዋል። የዝሙትና የሐጢአት ሁሉ መነሻቸውና ምንጫቸው ምኞት መሆኑን ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ነግሮናል። "እየያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። ከዚህ ቡሃላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ፣ ኃጢአትም ካደገች ቡሃላ ሞትን ትወልዳለች " (ያዕ1:14) በርግጥ በአሁን ሰአት ወጣቶችን የሚያማልል የዝሙትን ነገር የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ፊልሞች ይታያሉ። እንደዚህ ዓይነቱ የዝሙት ሐሳብን የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ሥዕሎች፣ ልብ ወለድ ድርሰቶችና የመሳሰሉት በየሱቁና በየቦታው ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝነው በመገናኛ ብዙሀንም ይኽን የመሰለ ነገር በየጊዜው በመታየቱ ነው። ጤናማውን የሞራል የቤተሰብንና የማኀበራዊ ኑሮን የሚመርዙት ፊልሞችና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች ቀርተው በምትኩ የትምህርትና የሥራ ጉዳዮች፣ የልማትና የምርት ስራዎች፣ የጤናና የማህበራዊ ኑሮን የመሳሰሉት ፕሮግራሞች ሰፋ ያለ ጊዜ ተሰጥቷቸው በመገናኛ ብዙሀን ቢታዩና ቢሰሙ ለሀገርና ለወገን ይጠቅማል። መዝናኛም ከተፈለገ የሀገሩን ባሕል፣ የሕዝቡን ሃይማኖትና ሞራል በመጠበቅ በወጉና በአግባቡ ሊደረግ ይችላል። ራስን በመግዛት በንፅህና በመመላለስ ከዝሙት መራቅ ይገባናል። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር •••• #ክፍል_6 •••• #አትግደል ሕይወት በአጋጣሚ ፣ በልማድና በእንዝሕላልነት የምትገኝ አይደለችም። ሕይወት ለራሱ ምክንያትና አስገኝ ከሌለው እግዚአብሔር የተገኘች ገንዘብ ነች። ሕይወትን ማንም ሊያዝባት እንደፈለገው ሊያደርጋት አይችልም። ለምን ? የእርሱ አይደለችምና ለዚህ ነው #አትግደል የተባለው። #መግደል ማለት በተለያዩ መንገዶች ተጠቅሞ የሰው ሕይወት እንዲሞት ማድረግ ነው። #መግደል ከውስጥ ከሰው የሚወጡ ሰውንም የሚያረክሱ ብሎ ጌታችን ከዘረዘራቸው ክፋ ሥራዎች አንዱ ነው ። ማቴ 15:19 ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ ላይ ከዘረዘራቸው 16 የስጋ ስራዎች አንዱ መግደል ነው። #በሕይወት ላይ ስልጣን ያለው #እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰውን ቢያድንም ቢገድልም ስልጣኑ የእርሱ ብቻ ነው። #መግደል ሲባል ፊት ለፊት ሄዶ የሰውን ሕይወት ማጥፋት ብቻ ሳይሆን ሰውን ለሞት የሚያበቁትን ነገሮች ሁሉ ነው ። ይኸውም #ሀ በተለያዩ ሁኔታ (በቃላትና በመጠቆም) አጥፊውን መርዳት #ለ የሰው ሕይወት ሊድን የሚችልበትን መረጃ በመከልከል #ሐ በሽታና ድካምን ሌላም ችግርን እያዩ ለሞት የሚያደርስ ስራ ማሰራት #መ ለሞት የሚያደርስ ረሀብና ጥም አይተን አለመርዳት #ሠ ሰውን በስጋ ብቻ ሳይሆን በነፍሱ መከራ የሚያመጣበትን መንገድ መፍጠር መግደል ነው። #ረ ዓለማውያንን በመንፈስ ባዶ ቀፎ ሆነው የተበላሹትን ወደ እናት ቤተክርስቲያን አለማምጣት ነፍስን መግደል ነው። ወደ መግደል የሚያደርሱ ብዙ ነገሮች አሉ እነሱም ቅንዓት፣ ምቀኝነት፣ ስድብ፣ ጥላቻ፣ ቁጣ ጥቂቶቹ ናቸው። እራሳችንን በመግዛት እና ወንድማችንን በመውደድ ከዚ ድርጊት ልንቆጠብ ይገባናል። መሞት እንደማንፈልገው ሁሉ የሰው ነፍስ ማጥፋት የለብንም። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር ••••• #ክፍል_5 ••••• #አባትህንና_እናትህን_አክብር ይህ ትዕዛዝ የፍቅረ ቢፅ መጀመሪያ ነው። አባትና እናት ሲል የወለዱንን ብቻ ሳይሆን በአርአያ #ሥላሴ የተፈጠረ ሁሉ እንድናከብር ነው። እነዚህም የሥጋ አባቶችና የመንፈስ አባት በማለት ለሁለት ይከፈላሉ። #የስጋ አባት የምንላቸው፦ ወላጆቻችን፣ የቀለም አባቶች፣ የሀገር መሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ የጡት አባት፣ የእንጀራ አባት ... #የመንፈስ_አባትና_እናት፦ የንስሀ አባት ፣ ካህናት ፣ ሰባኪ ወንጌሎች፣ የክርስትና እናትና አባት፣ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ናቸው። #አክብር ማለት መውደድ፣ መታዘዝ፣ መርዳት፣ አለማቃለል ማለት ነው። በሁሉ ለወላጆቻችሁ ሲል በሁሉ የሚለው ቃል ብዙ ነገሮችን ያመለክታል። ይኸውም #ሀ ምክራቸውን በመስማት #ለ በተቸገሩ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን በመስጠት #ሐ በሌላቸው ጊዜ የሚረዱበትን መንገድ ማዘጋጀት #መ በጠቅላላው ለወላጆች ብድራትን መመለስ። ወላጆቻችንም ሆኑ ሌሎችን የሥጋና የመንፈስ አባቶችን ሲኖራቸውም ፣ሲያጡም፣ ጤና ቢሆኑ፣ ቢታመሙም ፣ባረጁ ጊዜ ልንረዳቸውና ልናከብራቸው ይገባል። ይሁንና ወላጆችም ሆኑ ሌሎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣላና የሚያጋጭ ትዕዛዝ ቢያዙን ግን እንቢ ልንላቸው ይገባል። ••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••