uz
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Kanalga Telegram’da o‘tish

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Ko'proq ko'rsatish
4 374
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
#ሰማዕታተ_አክሚም ☞✞በቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከተካሔደባቸው አካባቢዎች አንዷ ሃገረ አክሚም ናት:: አክሚም ማለት የቀድሞ የግብጽ አውራጃ ናት:: በተለይ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በርካታ ክርስቲያኖች በፍቅር ይኖሩባት ነበር:: በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ጥቡዓን: ታማኞች:ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉና ዘወትር ቅዱስ ቃሉን ለመስማት የሚተጉ ነበሩ:: ለዚህም ደግሞ ከሊቀ ዻዻሱ አባ ብኑድያስ ጀምሮ ካህናቱ: ዲያቆናቱ: ንፍቅ ዲያቆናቱ: መጋቢዎቹ: አናጉንስጢሶቹ (አንባቢዎቹ): መምሕራኑ: መሣፍንቱም ሳይቀር ለክርስቶስ ፍቅር የተጉ መሆናቸው አስተዋጽኦ ነበረው:: በተለይ ግን 2 ወንድማማቾች የነበራቸው ቅድስና ብዙዎችን ስቧል:: እኒህ ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ ይባላሉ:: ከባለ ጸጋና ባለ ስልጣን ቤተሰብ ቢወለዱም ክርስትናቸው አልቀዘቀዘም:: የወጣትነት ስሜት ሳያሸንፋቸውም ወደ በርሃ ተጓዙ:: ☞✞በዚያም በቅድስና ኑረው ለክህነት ማዕረግ በቅተዋል:: ቅዱሳኑ በገዳም ሳሉም መድኃኒታችን ክርስቶስ ተገልጦ "ወደ ትውልድ ሃገራችሁ አክሚም ተመለሱ:: ክብረ ሰማዕታት ይጠብቃቹሃል" አላቸው:: እነርሱም ደስ እያላቸው በፍጥነት ወደ አክሚም ወጡ::በዚያ ሰሞን የጌና ጾም ተፈጽሞ የአክሚም ክርስቲያኖች ለበዓለ ልደት ዝግጅት ሲያደርጉ በጠላት ሠራዊት ተከበቡ:: ይህ ሠራዊት የተላከው ከርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ሲሆን መሪው ደግሞ አርያኖስ ነው:: ዋናው ተልዕኮው ክርስቲያኖችን ለጣዖት ማሰገድ: እንቢ ካሉ ደግሞ መግደል ነው:: ክርስቲያኖቹ መከበባቸውን እያወቁ አልፈሩም:: ታኅሳስ 29 ቀንም ሁሉም የከተማዋ ክርስቲያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰበሰቡ::በዚያም ሊቀ ዻዻሱ ሥርዓተ ቅዳሴን አደረሱ: : ሁሉም በተመስጦ ይጸልዩ ነበርና የክብር ባለቤት ክርስቶስ በገሃድ ተገለጠላቸው:: በዓይናቸው እያዩም ሥጋ ወደሙን አቀበላቸው:: ቅዳሴው ሲጠናቀቅ ግን አርያኖስና ሠራዊቱ ደርሰው ሁሉንም ክርስቲያኖች ያዛቸው:: ☞✞ክርስቶስን ክደው ከመገደል እንዲድኑ ተጠየቁ:: እነርሱ ግን በአንድ ድምጽ "አይሆንም" አሉ:: በዚያን ጊዜ ወታደሮቹ በክርስቲያኖች አንገት ላይ በሰይፍ ይጫወቱ ያዙ::በተራ አሰልፈው ዻዻሱን: ካህናቱን: ዲያቆናቱን: አንባቢዎችን:መሣፍንቱን ሳይጨምር ከ16,000 በላይ ክርስቲያኖች ደማቸው ፈሰሰ:: የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ሞልቶ ደም ወደ ውጭ 20 ክንድ ያህል ፈሰሰ:: በክርስቲያኖች ላይ ግፍ ተፈፀመ። አካባቢውም ያለወሬ ነጋሪ ቀረ:: ግድያው ለ3 ቀናት ቀጥሎ ጥር 1 አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ ሲገደሉ ተጠናቀቀ:: ....☞✞🙏አምላከ ሰማዕታት ፍቅረ ሃይማኖታቸውን ያሳድርብን፤ ከበረከታቸውም ይክፈለን🙏✞☜....

#የሊቀ_ዲያቆናት_የቅዱስ_እስጢፋኖስና_የአክሚም_ሰማዕታት_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_እንኳን_በሰላም_አደረሳችሁ!!! 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 #ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ሊቀ_ዲያቆናት_ወቀዳሜ_ሰማዕት ☞✞በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው። ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ ☞✞የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋ፡5፥33 ላይ ተጠቅሷል::✞በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን : ዻውሎስን : ናትናኤልን : ኒቆዲሞስን....) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል:: ☞✞ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር:: ☞✞በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ:: ☞✞ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው:: "ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: (ሉቃ. 10፥17) ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኳል:: በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት:ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ:: በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7 ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል:: 8ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር' ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5) አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም:: ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማኅበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ' አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት:: ☞✞እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት:: ☞ #ፍልሠት፦✞ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመታት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም ሉክያኖስ ይባል ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም ደስ ብሎት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል (የመምሕሩ ርስት ነው) ሔደ:: ☞✞ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ:: መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ መላእክትም ተሰማ:: ሕዝቡና ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ ጽዮን (በተቀደሰችው ቤት) አኖሩት:: እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ ክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ5 ዓመታት በኋላም እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን ስለ ፍቅሩ አኖሩት::ሚስቱ ወደ ሃገሯ ቁስጥንጥንያ ስትመለስ የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው:: መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ አላት: አምላክ ለዚህ አድሏታልና:: እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም ታላቅ ሐሴት ተደረገ::ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች:: በዚያም ላይ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ #ሞቱ ጥቅምት 17: #ዕረፍቱ ጥር 1 #ፍልሠቱ ደግሞ መስከረም 15 ቀን ነው:: ......✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞......

👉“የእግዚአብሔርን ኃይል አታዉቁም እና ትስታለችሁ” ማቴ 22፥22 ➎✝#አምላክ ➏✝#የዘላለም_አባት ➐✝#የሰላም_አለቃ { ትንቢተ ኢሳያስ (ምዕራፍ 9፥6:7) } 👉"ሕፃን ተወልዷልና ወንድ ልጅም ተሰቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ሀያል አምላክ፡ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፡ ለአለቆች ሰላምን ለዕርሱም ህይወትን አመጣለሁና፡ ከዛሬ ጀሞሮ እስከ ዘልአለም ድረስ በፍርድና በፅድቅ ያፀናውና ይደግፈው ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፡ በዳዊት ዙፋን መንግስቱም ትፀናለች ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንነት ይህንን ያደርጋል።" 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 ውድ የተዋህዶ ቤተሰቦች የሆናችሁ የእናቱ የእናታችን የቅድስት ቅዱሳን የንፅሕይት ንፁሐን የድንግል ማርያም ያአስራት ልጆች የሆናችሁ እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ/ሰን በአሉ የሰላም~የደስታ~የፍቅር~የጤና~የመተሳሰብ የመተዛዘን~የበረከት~የእረድኤት~የስኬት~የቅንነት ይሆንልን ዘንድ የፈጣሪ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን!!!!

✞#ሕፃን_ተወልዶልናልና✞ 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 በስመ አብ ወወለወድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 👉ልደታትን ስንመለከት ብዙ አሉ፦ ልደተ አዳም ከምድር፣ ልደተ ሔዋን ከአዳም ፣ልደተ ሙታን ከመቃብር፣ ልደተ ሕፃናት ከእናታቸው ማህፀን የሚጠቀሱት ናቸው፡፡የእነዚህ ሁሉ ልደት ለራሳቸው እንጂ ለእኛ አይደሉም። 👉#ህፃን_ተወለልዶልናልና የሚለው ግን ለእኛ ነው፡፡ የአምላክን መወለድ ብዙ ነቢያት በብዙ ሕብረ ትንቢት ተናግረዋል በብዙ ሕብረ አምሳል መስለዋል፡፡ 👉ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ አይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ዳግምም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን።ዕብ፡1፥1 በብዙ ሕበረ አምሳል በብዙ ሕብረ ትንቢት እግዚአብሔር ከተናገረባቸው ነቢያት አንዱ ኢሳይያስ ነው። ኢሳይያስ ከነቢያት ወንድሞች በተለየ መልኩ የአምላክን ሰው መሆን የተናገረ ነቢይ ነው። መወለዱን፣ስሙን፣ከማን እነደሚወለድ ፣ለሰው ልጆች ያደረገውን የቤዛነት ስራ መከራ መቀበሉን ፣በጎል መወለዱን በግልፅ ከተናገሩ የተነሳ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ወንጌላዊ ነቢይ የሚል ቀጽል ሰጥተው ይጠሩታል፡፡የትንቢት መጽሐፉንም ደረቅ ሐዲስ በማለት ሰይመውታል፡፡ይህም ማለት ስለክርስቶስ መወለድ በምሰሌ ያይደለ በቀጥታ የተናገረ በመሆኑ ነው ለምሳሌ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡ 👉"ጌታ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"ኢሳ፡7፥14 ከላይ ባጭሩ እንዳየነው ከማን እንደምትወልድ ስሙን ማን አንደሆነ በግልጽ እስቀምጧል፡፡ 👉"በስድስተኛው ወር ገብርኤል መላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ ከዳዊት ወገን የሆነ ስሙ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ከታጨች ከድንግል ዘንድ የዚህች ድንግል ስሟ ማርያም ነው"ሉቃ፡1፥26 በማለት ወንጌለዊው ገልጧል። 👉"በነቢይ ከጌታ ዘንድ እነሆ ድንገል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለውን ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ማቴ፡1፥22 ኢሳይያስ "ሕፃን ተወልዶልናል" ብሎ ለእኛ መዳን የተወለደው ነገረን ቀጥሎም ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል።" ይላል። ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን መድኃኒት ለሆነን እንደመጣ ሊያሳይ፡፡ ከዚህ በመቀጠል እርሱን ለመግለጥ የተጠቀማቸው ቃላት በጣም የሚደንቁ ናቸው፡፡ #ስሙ_ድንቅ_መካር_ኃያል_አምላክ_የዘላዓለምአባት_የሰላምአለቃ በሚሉ #ሰባት ቃላት ገልጾታል ቁጥሩ በእብራዊያን ዘንድ ፍጹም ነው። ከላይ ኢሳይያስ የተጠቀማቸው ሰባት ቃላት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን የሚያስረዱ ናቸው፡፡ ሕፃን ብሎት ነበር ሕፃን የሚለው ስም ታህታዊ ማንም በሥጋ የወለደ ሰው ሲወለድ የሚጠራበር ነው ፡፡ ሰው መሆኑን ለመግለጥ ሕጻን አለው አምላክነቱን ለማስረዳት ስሙም ብሎ ጀምሮ በሰባት ቃለት አስረድቶናል፡፡ ➊✝#ስሙ ስለ ስሙ ቅዱሳት መጻፍት ሲናገሩ ኢየሱስ ፣አማኑኤል፣ ክርስቶስ ፣መድኃኔዓለም የሚባሉት ስመ ስጋዌ ናቸው። ሰው በመሆኑ የተጠራባቸው ኢየሱስ፦ማለት መድሐኒት ማለት ነው፡፡ አማኑኤል፦ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ከእኛ ጋር፦ ሲባል ከስጋችን ሥጋ ከደማችን ደምን ነስቶ ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው። ክርስቶስ፦ማለት መሲህ ፣ሹም፣ንጉሥ ፣አለቃ ማለት ነው፡፡ መድኃኔዓለም፦ማለት የአለም መድኃኒት የዓለም ቤዛ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ በደሙ ዓለምን የዋጀ ማለት ነው፡፡ 👉"ልጅም ትወልዳለች እርሱም ሕዝቡን ከኃጢያታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለች" ማቴ፡1፥21 👉"ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ እርሱ በመጣ ጊዜ ሁሉን ይነግረናል አለችዉ ኢየሱስም የምትናገሪዉ እርሱ እኔ ነኝ አላት።"ዮሐ፡1፥42 👉"እኛ ራሳችን ሰምተነዋል አርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን።"ዮሐ፡4፥42 ከላይ የተመለከትናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስሙንና ግብሩን የሚገልጡ ናቸው፡፡ ትርጉሙ ከተግባር ጋር የተያያዘ ነውና ይህንን ነው ኢሳይያሰ “ሕፃን ተወለደልን” በማለት የተነገረለት ኢሳይያስም ሕጻን ብሎ የጠራዉ ሰዉ ሲሆን አምላክነቱ አልተለወጠምና አምላክነቱን መግለጥ የሚችሉ ቃላት ከስሙ ጀምሮ ተጠቅሟል ስሙ አዳኝ ነው። 👉"አቤቱ በስምህ አድነኝ።"መዝ፡53፥1 👉ስሙ ቅዱስ ነው፤ እርሱ ለእኔ ታላቅ ስራ አድርጎል እና ስሙም ቅዱስ ነው።"ሉቃ 1፥50 👉ስሙ፦ አጋንንትን ይገዛል "አጋንንት በስምህ ተገዙልን።"ሉቃ 10፥17 👉ያመኑትን እነዚህን ምልክቶች ይከተሏቸዋል በስሜ አጋንትን ያወጣሉ እባቦችን ይይዛሉ የሚያሰክር መርዝ ቢጠጡ አይገድላቸውም።ማር 16፥17 👉ስሙ፦ ስግደት የሚገባው ነው ?"እግዚአብሔር/እግዚአብሔርነቱ/ ያለልክ ከፍ ከፍ አድርገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለዉን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከኩ ዘንድ።" ቆላ 2፥9-11 👉ስሙ፦ ምስጋና ይገባዋል 👉"በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ.."ማቴ 6፥9 ➋✝#ድንቅ ድንቅ፦ማለት ቃል እነደሚገባው አድርጎ የማይገልጠዉ ቃላት ላጣንለት ነገር የምንጠቀመዉ ነዉ በህቱም ድንግልና ተጸንሶ በህቱም ድንግልና መወለዱን ሲደንቅ የሚኖር ነውና በኪሩቤል ላይ የሚገለጥ ስጋን ለብሶ መወለዱን የማይወስነዉ መወሰኑ የማይዳሰሰው መዳሰሱ የማይታየው መታየቱ የማይጨበጠው እሳተመለኮት በጨርቅ መጠቅለሉ በጎል መጣሉ የሚደንቀን ነው እነኳን ለኢሳይያስ ለመላእክትም ድነቅ ነው። ሰማይ ዙፋኑ የሆነ አምላክ በትህትና መገለጡ ድሆች እንኳ ባልተወለዱበት የከብቶቸች በረት መወለዱ ድንቅ ነው፡፡ 👉"በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ"(እግዚአብሔርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት) መዝ፡65፥3 ሕፃናትን በእናታቸው ማህጸን የሚጠብቃቸው ሕጻን ሆነ ይህ እንዴት አይደንቅ 👉"ስራህ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታዉቀዋለች።"መዝ 138፥12 በላይ በሰማይ በኪቤል ጀርባ በምድር በእናቱ እቅፍ መታየቱ ድንቅ ነው? "ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ ለዓይናችን ድንቅ ነው።"መዝ 117፥22 ማቴ 22፥42 ➌✝#መካር ሰው ለመሆን መወሰኑን በልብ የመከረውን በነብያት ያናገረውን ያን የፈጸመ ምክረ ከይሲን በምክሩ የሻረ ዲያብሎስን ያሣፈረ በልቡ ጥበብ ከሰው ልጆች በተለየች ምክሩ አዳምን ነጻ ያወጣ መካር ነው፡፡👉"ግሩም ምክሩ እምጎለመኸያው (ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ልዩ ነው)"መዝ 65፥5 በዚህ በልዩ ምክሩ ዲያብሎስ የመከራቸውን የነፍስና የስጋ ተዋህዶ በሥጋ ተወለደ ይህ የዲያብሎስን ስራ ያፈርስ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ ተሰ 3፥7👉"ውዕቱ ጥበቡ ወምክሩ ያድኅነነ መጸአ (እርሱ የአብ ጥበቡና ምክሩ ሊያድነን መጣ)" ይለዋል ቅዱስ ያሬድ ➍✝#ኃያል ኃያልነት የበሕርይ ገንዘቡ ነው "ኀይሉ ለአብ ወጸጋ ለአህዛብ…”የአብ ኃሉ እርሱ ነው ለአህዛብም ጸጋን የሚሰጥ “ እነዳለ መጽሐፈ ኪዳን፡፡ መንግሥትህ ያንተ ናትና ኃይል ምስጋና ክብር ለዘላለሙ” ማቴ 6፥13 በኃይሉ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃዉን ሊነጥቀዉ እንዴት ይቻላል።ማቴ 12፥29👉“ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም /ደካማ/አይደለም ነገር ግን በእናንተ ኃለኛ ነው በድካም ተሰቅሏልና ነገር ግን በእግዚአበሔር /በእግዚአብሔር/ኃይል በሕይወት ይኖራል 1ኛ ቆሮ 13፥3-5 👉“የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው” 1ቆሮ 1፣24-26 ሰዎች ይህንን የእግዚአብሔር ኃይል አላወቁም ነበር።

#ጌታችን_ስለተወለደባት_ምሽት_ሶርያዊው_ቅዱስ_ኤፍሬም_አንዲህ_አለ፦ 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 👉‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ! 👉ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! 👉ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት! ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ 👉ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ! የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!›› #የገና_አባት (ቅዱስ ኒቆላዎስ) ለድኆች ሥጦታ ይለግስ የነበረ ቅዱስ አባት ነው። ታሪኩም በስንክሳር ታኅሣሥ 10 ላይ ተጽፎአል። "የገና ዛፍ ባሕላችን አይደለም እነርሱ ክረምታቸውን የሚያስታውሱበት ነው ከእኛ ጋር አይገጥምም" "የተወለደውን ክርስቶስ የበዓሉ ማዕከል እንዳናደርግ ያደርገናል" ማለት ትክክለኛ ነገር ነው። Pagan Origin (የባዕድ አምልኮ መነሻ) አለው ብሎ ጣዖት አምልኮ ነው ማለት ግን ከገደብ ያለፈ ድምዳሜ ነው። በከዋክብት ያመልኩ የነበሩት የጥበብ ሰዎች በሚያመልኩት ነገር ወደ ክርስቶስ ተጠርተዋል ፣ የዙሐል ጣዖት ይከበርበት የነበረውን ዕለት ከክርስትና በኋላ በእስክንድርያ የቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን ሆኗል። 👉የራሳችንን የገና ባሕላዊ አከባበሮች የገና ጨዋታን ፣ ቀጤማ መጎዝጎዝ የመሳሰሉትን ማክበር ይገባናል። ከዚያ ውጪ በክርስትና መንፈስ እስከተቃኘና የጌታን በበረት መወለድ ፣ የሰብአ ሰገልን ጉዞ ፣ ከዋክብቱን ፣ የመላእክትን ዝማሬ ፣ የእረኞችን ደስታ ፣ የሰብአ ሰገልን እጅ መንሻ የሚያሳይ እስከሆነ ድረስ የኛ ባሕል ያልሆነውን ሁሉ ጣዖት ነው ብሎ ማንቋሸሽ ፣ የሚያምር ነገርን ሁሉ ማውገዝ ያስመስላል። ቅዱስ ኒቆላስም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትዘክረው ቅዱስ ስለሆነ አጋጣሚውን ጻድቁን ለማስተዋወቅም ልንጠቀምበት ይገባል። ሥጦታም የምንሠጣጠው የሰብአ ሰገልን ሥጦታ መነሻ አድርገን ሲሆን ልግስናውን ለነዳያን ብናደርገው የበለጠ በረከት እንቀበልበታለን።"በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ"

ባሰማት ጊዜ @EOTC2921.m4a5.64 KB

#ባሰማት_ጊዜ ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልካም ዜና እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና/2/ ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ ድንግል ቀረበች ወደ እርሱ ፍጹም ትኅትናን ይዛ ትፀንሻለሽ ሲላት መልአኩ ፍጹም በልቧ ሳትመካ እንደ ቃልህ ይሁን አለችው በቃሉ ተማርካ /2/ #አዝ የዓለም መድኀኒት ነውና ከአንቺ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ትሰይሚዋለሽ ስሙንም ብለሽ ኢየሱስ /2/ #አዝ ዕፁብ ድንቅ ነው ለሁልጊዜ ለ ድንግል ማርያም የተሰጣት እድል የአምላክ እናት ሆኖ መመረጥ ከሴቶች መካከል /2/ #አዝ ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ይገባሻል ለአንቺ ክብርና ምስጋና የክብር ባለቤት ሁል ጊዜም ከአንቺ ጋር ነውና /2/

#ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘልደት "ታኅሣሥ ፳፱" 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል። #መልክአ_ሥላሴ ሰላም ለአጻብኢክሙ እለ እምአጽፋር ኢይትሌለዩ፤ ለቤትክሙ ሥላሴ ዘኢየኃልቅ ንዋዩ፤ አመ አብዓልክሙ ሰብአ ድኅረ አንደዩ ጌጋዩ፤ ዘኢርእዩ እምቅድመ ዮም መላእክተ ሰማይ ርእዩ፤ ወአግብርተ ሰብእ መላእክት ተሰምዩ። #ዚቅ ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት፤ ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ። #ወረብ 'ርእይዎ ኖሎት'/፪/ አእኮትዎ መላእክት/፪/ ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል/፪/ #ነግሥ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። #ዚቅ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ። #ነግሥ ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤ ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤ እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤ ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል። #ዚቅ በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ፤ እፎ ተሴሰየ ሀሊበ ከመ ሕፃናት። #ወረብ በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ኃደረ ማኅጸነ ድንግል/፪/ እፎ 'ተሴሰየ'/፪/ ሀሊበ ከመ ሕፃናት ተሴሰየ/፪/ #መልክአ_ኢየሱስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤ አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ። #ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ንሰብከ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፤ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፣ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፤ ትጉኃን የአምኑ ልደቶ፤ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፤ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም የሀበነ ሰላመ፤ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ። #ወረብ 'ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ'/፪/ ሥጋ ኮነ/፪/ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ ሥጋ ሰብእ በሥጋ ሰብእ/፪/ #መልክአ_ኢየሱስ ሰላም ለአጽፋረ እዴከ ዘኅበሪሆን ፀዓዳ፤ በምገባር ወግእዝ እለ ይትዋሐዳ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስፍና አባሉ ለይሁዳ፤ ለመንግሥትከ ሰፋኒት እንዘ ይትመሐለሉ ዓውዳ፤ ሰብአ ሰገል አወፈዩ ጋዳ። #ዚቅ አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል፤ አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ፤ ረኪቦሙ ሕፃነ ዘተወልደ ለነ። #ወረብ አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል/፬/ አምኃሁ አምጽኡ መድምመ/፪/ #መልክአ_ኢየሱስ እምኲሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ፤ ወበወላዲትከ ተማኅፅኖ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እምቤተ መንግሥት ወተክህኖ፤ ተሰብኦትከ እመቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ፤ ያንኮርኲር ታሕት ደይን ግዱፈ ከዊኖ። #ዚቅ ወካዕበ ተማኅፀነ በማርያም እምከ፤ እንተ ይእቲ እግዝእትነ፤ ወትምክሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ። #ወረብ 'ትምክሕተ ዘመድነ'/፪/ በወሊዶተ ዚአከ/፪/ ይእቲ 'እግዝእትነ'/፪/ ማርያም ድንግል/፪/ #ማኅሌተ ጽጌ ኦ ዝ መንክር በዘዚአኪ አምሳል፤ ኮከበ ትንቢት ዘቦቱ መልክአ ሕፃን ሥዑል፤ ሠረቀ ያርኢ ተአምረኪ ድንግል፤ ወመርሖሙ ለሰብአ ሰገል እምርሑቅ ደወል፤ ጽጌኪ ኀበ ሀሎ ይሰክብ በጎል። #ዚቅ ወኖሎት በቤተ ልሔም፤ አንከሩ እምዘርእዩ ወሰምዑ፤ ሰብአ ሰገል ርእዮሙ ኮከበ፤ መጽኡ እምርኁቅ ብሔር፤ ከመ ይስግዱ ለወልድኪ ወይግነዩ ለኪ። #ወረብ በኮከብ መጽኡ ሰብአ ሰገል/፪/ ይስግዱ ለአማኑኤል ይስግዱ/፪/ #አንገርጋሪ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ እምቅድስት ድንግል፤ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ልደቱ። #አመላለስ 'አማን በአማን'/፪/ መንክር 'አማን በአማን'/፪//፩/ መንክር ስብሐተ ልደቱ/፬/ #ወረብ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ/፪/ እምቅድስት 'ድንግል'/፪/ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ/፪/ #እስመ ለዓለም ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ፤ አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤ ሰብአ ሰገል አምጽኡ ሎቱ ጋዳ፤ ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ። #አመላለስ ተወልደ ኢየሱስ 'በቤተ ልሔም'/፪/ ዘይሁዳ በቤተ ልሔም/፪/ አዋልደ ጢሮስ 'አሜሃ ይሰግዳ'/፪/ በቤተ ልሔም/፪/ #ዕዝል በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ፤ ዮም ተወልደ፤ እግዚእ ወመድኅን፤ ቤዛ ኲሉ ዓለም። #አመላለስ ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ/፪/ 'ቤዛ ኲሉ ዓለም'/፪/ ዮም ተወልደ/፬/ #ሰላም ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ንሰብክ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፤ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፤ ትጉሃን የአምኑ ልደቶ፤ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፤ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም የሀበነ ሰላመ፤ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ። 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 🔆 መልካም በዓል 🔆

#ሥርዓተ_ዋዜማ_ዘልደት "ታኅሣሥ ፳፰" #ዋዜማ 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 #ሃሌ_ሉያ እምርኁቅ ብሔር አምጽኡ ሎቱ አምኃሁ፤ ወርቀ ከርቤ ወስኂነ፤ አስከበቶ እሙ ውስተ ጎለ እብን፤ ከደነቶ እሙ ቌጽለ በለሶን፤ ወትቤሎ እሙ መድኃኔዓለም፤ ዮም ተወልደ፤ ከሣቴ ብርሃን። #ምልጣን አስከበቶ እሙ ውስተ ጎለ ዕብን፣ ከደነቶ እሙ ቌጽለ በለሶን፤ ወትቤሎ እሙ፤ ዮም ተወልደ መድኃኔዓለም፤ ዮም ተወልደ ከሣቴ ብርሃን። በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ መዝ: ፳፫ ተወልደ በተድላ መለኮት፤ ብሑተ ልደት እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ተወልደ በተድላ መለኮት። እግዚአብሔር ነግሠ መዝ: ፺፪ ተወልደ መድኅን ክብረ ቅዱሳን፤ እማርያም ድንግል፤ አስከበቶ እሙ ውስተ ጎለ ዕብን፤ ወትቤ መድኅኑ ለዓለም። #ይትባረክ ጸሎተ ፫ቱ ደቂቅ: ፱ ኮከብ መርሖሙ ወአብጽሖሙ እስከ ቤተ ልሔም፤ ወአምጽኡ ሎቱ አምኃሁ ወርቀ ከርቤ ወስኂነ። #ሰላም ይእዜኒ ንትልዋ ለሰላም፤ እስመ ተወልደ ክርስቶስ፤ ዮም በዛቲ እለት ፍሥሃ ንዜኑ ለዘየአምን ዜና ሠናየ፤ ዘውእቱ ሕፃን ሃይሎሙ ወጽንዖሙ ለ፳ኤል። #ምልጣን ይእዜኒ ለሰላም ንትልዋ፤ መድኃኒነ ተወልደ ነዋ፤ ይእዜኒ ለሰላም ንትልዋ። #አመላለስ መድኃኒነ ተወልደ ነዋ/፪/ ይእዜኒ ለሰላም ንትልዋ/፬/

ግሞ ቅዱስ ማርቆስን አስከትሎ ብዙ አሕጉራትን አስተምሯል:: ቆዽሮስም ሃገረ ስብከቱ ናት:: +ቅዱሱ ከብዙ ትጋት በሁዋላ በዚህች ቀን አረማውያንና አይሁድ ገድለውታል:: ቅዱስ ማርቆስም ገንዞ ቀብሮታል:: << ስለርሱ መጽሐፍ "ደግ: መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ነው" ይላልና ክብር ይገባዋል !! >> (ሐዋ. 11:24) +"+ አባ ይስሐቅ ጻድቅ +"+ =>ይህ ቅዱስ በመካከለኛው ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ ገዳማዊ ነው:: መንኖ ለብዙ ዘመናት በገዳም ሲኖር ምኞቱ አንዲት ብቻ ነበረች:: እመቤታችንን በአካል መመልከትን ይፈልግ ነበር:: +የገዳሙ ጠባቂ በመሆኑ መነኮሳት ሲተኙ መቅደሱን ከፍቶ በድንግል ማርያም ስዕል ፊት ይጸልይ: ይሰግድ: ያነባ ነበር:: እንዲህ ለ7 ዓመታት ስለ ተጋ ድንግል እመ ብርሃን ልመናውን ሰማች:: +በዚህ ዕለትም ከፀሐይ 7 እጅ ደምቃ ወደ እርሱ መጣች:: ደንግጦ ሲወድቅ አነሳችው:: "ከ3 ቀናት በሁዋላ እመለሳለሁ" ብላም ተሠወረችው:: በ23ም ዐረፈ:: "በዛቲ ዕለት ሶበ ጸለየ ጥቡዐ:: ለይስሐቅ አስተርዓየቶ እም አይቆናሃ ወጺአ:: እምጸዳለ መብረቅ ጥቀ እንዘ ትጸድል ስብአ::" እንዳለ ደራሲ:: (አርኬ) =>የእሥራኤል እረኛ ሥጋችንን ከመቅሰፍት: ነፍሳችንን ከገሃነመ እሳት ይጠብቅልን:: ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን:: =>ታሕሳስ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ኖላዊ ሔር 2.ቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ 3.አባ ይስሐቅ <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Dn Yordanos Abebe <<< እንኩዋን "ለኖላዊ ሔር ክርስቶስ" : ለቅዱሳን "በርናባስ ሐዋርያ" እና "አባ ይስሐቅ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ >>> +*" ኖላዊ ሔር "*+ =>እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ:: በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ: በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ: በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት:: በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው:: +ከዚህ በሁዋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር:: ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር: ሱባኤ ይቆጠር: ምሳሌም ይመሰል ገባ:: +ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ:: ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት / ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል:: +ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል:: እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል:: =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህችን ዕለት "ኖላዊ ሔር" ብላ ታከብራለች:: ይሕንንም ለሳምንት ያህል ታዘክራለች:: መሠረታዊ መነሻዋም (ዮሐ. 10:1) ነው:: "ኖላዊ" ማለት በቁሙ "እረኛ" ማለት ሲሆን "ሔር" ደግሞ "ቸር-ርሕሩሕ-አዛኝ" እንደ ማለት ነው:: +ገጥመን ብንተረጉመው ደግሞ "ቸር እረኛ" የሚል ትርጉምን ይሰጠናል:: ከአባታችን አዳም ስህተት በሁዋላ ተፈጥረው ከነበሩ ችግሮች አንዱ ቸር እረኛ ማጣት ነው:: እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ: ቸር እረኛ ሆኖ በገነት አሰማርቶት ነበር:: +ኤዶም ገነት የለመለመች: ፈሳሾች የሞሉባት መልካም መስክ ናትና:: አባታችን ቅዱስ አዳም ደግሞ እንደ አቅሙ የጸጋ እረኝነት ተሰጥቶት ነበር:: ድቀት ካገኘው በሁዋላ ግን ከነፍስ እረኛው ጋር ተጣልቶ ከመልካሟ መስክ ገነት ወጣ:: +እርሷንና የነፍሱን እረኛ ሲሻም አለቀሰ:: ተስፋ ድኅነት ሲሰጠውም ለልጆቹ ነገራቸው:: ከዚያም በመንጋው ላይ በአዳም ሴት ተተካ:: ከሴት ኄኖስ: ከኄኖስ: ቃይናን . . . እያለ ከኖኅ ደረሰ:: +ከኖኅም በሴም ከአብርሃም: ከአብርሃምም በይስሐቅና በያዕቆብ ወርዶ ከሙሴ ደረሰ:: ከሙሴም በኢያሱ አልፎ ከነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደረሰ:: እነዚህ ሁሉ እረኞች ምንም እንኩዋ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በትጋት ቢሠሩም ሕዝቡን ከሲዖል ማዳን አልቻሉም:: +ከሲዖል የሚያድን የነፍስ እረኛ ነውና ያን ጊዜ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የራሱን: የአባቶቹንና የልጆቹን ጩኸት ባንድ አድርጐ ጮኸላቸው:: "ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ - የእሥራኤል እረኛ ሆይ ስማን!" አለ:: (መዝ. 79:1) +ጩኸቱም ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ይህንን የሰማ ጌታም በጊዜው ከድንግል ማርያም ተወለደ:: በየጥቂቱ አድጐ ቸር እረኝነቱን ገለጠ:: መድኃኒታችን እንዳስተማረን እርሱ ቸር እረኛ ነው:: +ከእርሱ በፊት የተነሱት ቴዎዳስ ዘግብጽና ይሁዳ ዘገሊላ (ሐዋ. 5:36, ዮሐ. 10:8) ሐሰተኛ እረኞች ነበሩ:: እርሱ ግን እውነተኛው የበጐች በር ነውና (ዮሐ. 10:7) በእርሱ የሚገቡ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛሉ:: +እርሱ እውነተኛ እረኛ ነውና (ዮሐ. 10:11) ለመንጋው ራሱን አሳልፎ ይሰጣል:: በእሥራኤል ባሕል እረኞች ከፊት: መንጋው (በጐቹ) ከሁዋላ ሆነው ይሔዳሉና ገዳይ ቢመጣ መጀመሪያ የሚገድለው እረኛውን ነው:: +መድኃኒታችን ክርስቶስ በሞቱ ሕይወትን: በመራቆቱ የጸጋ ልብስን: በውርደቱ ክብርን: በድካሙ ኃይልን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ:: የማይሞት ንጉሥ ስለ መንጋው ሞተ:: ሰማይን ከነግሡ ምድርንም ከነልብሱ የፈጠረ ጌታ (ዘፍ. 1:1, ዮሐ. 1:2) ስለ በጐቹ ይህንን ሁሉ ታግሦ ከሲዖል አዳነን:: +በሚያርግ ጊዜም በእርሱ ፈንታ ባለ ሙሉ ስልጣን እረኞችን: ሐዋርያትን (ዮሐ. 21:15) ሊቃነ ዻዻሳትን (ሐዋ. 20:28) ካህናትን (ማቴ. 18:18) ሾመልን:: እነርሱን እረኞች አሰኝቶ እርሱ "ሊቀ ኖሎት-የእረኞች አለቃ" ተባለ:: እነርሱም እስከ ዓለም ፍጻም የክርስቶስን መንጋ ሊጠብቁ ስልጣኑም: ኃላፊነቱም አለባቸው:: (ማቴ. 28:19) +*" ቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ "*+ =>ቅዱሱ ሐዋርያ ስሙ ሲጠራ ሞገስ አለው:: የቅዱሱ ሰው የመጀመሪያ ስሙ ዮሴፍ ሲሆን በርናባስ ያለው መድኃኒታችን ክርስቶስ ነው:: ትርጉሙም "ወልደ ኑዛዜ-የመጽናናት ልጅ" እንደ ማለት ነው:: +በምሥጢሩ ግን "ማሕደረ መንፈስ ቅዱስ-የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ" እንደ ማለት ያስተረጉማል:: ቅዱስ በርናባስ ምንም በትውልዱ እሥራኤላዊ ቢሆን ተወልዶ ያደገው በቆዽሮስ ነው:: እስከ ወጣትነት ጊዜውም የቆየው እዚያው ነው:: +የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የመሆኑ ዜና ሲሰማ ግን ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ መድኅን ክርስቶስን ተመለከተ:: ጌታውንም ሊከተል በልቡ ቆረጠ:: የፈጠረን ክርስቶስም እንዲረባ (እንዲጠቅም) አውቆ: ስሙን ቀይሮ አስከተለው:: ከ72ቱ አርድእትም ደመረው:: +ቅዱስ በርናባስ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ለ3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ቁጭ ብሎ ተማረ:: ተአምራቱንም ሁሉ ተመለከተ:: ከጌታ ዕርገት በሁዋላ 120ው ቤተሰብ በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩም አብሮ ይተጋ ነበር:: +በጊዜውም አበው ሐዋርያት በይሁዳ ፈንታ ከ12ቱ የሚቆጠረውን ሰው ለመምረጥ 2 ሰዎችን አቅርበው ነበርና አንዱ ይኸው ቅዱስ ነው:: እዚያውም ላይ ጌታችንን ከመጀመሪያው ጀምሮ ማገልገሉ ተመስክሮለታል:: (ሐዋ. 1:22) +ስሙንም ኢዮስጦስ ብለውታል:: ባለ 3 ስም ነበርና:: በወቅቱም ዕጣ በቅዱስ ማትያስ ላይ ስለ ወደቀ በርናባስ ከ72ቱ አርድእት: ማትያስ ከ12ቱ ሐዋርያት ሆነው ቀጠሉ:: +ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ በርናባስ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በኃይል ያገለግል ጀመር:: የሐዋርያትን ዜና በሚናገር መጽሐፍ ላይ የተጻፉና ስለ ቅዱሱ ማንነት የሚናገሩ ክፍሎችን እንመልከት:: 1.ቅዱሳን ሐዋርያት የእኔ የሚሉት ንብረት ሳይኖራቸው: ያላቸውን በጋራ እየተጠቀሙ በፍቅር ይኖሩ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ ነበር:: ያለውን ሁሉ ሸጦ በሐዋርያት እግር ላይ በማኖር ደግሞ ቀዳሚውን ሥፍራ ቅዱስ በርናባስ ይይዛል:: (ሐዋ. 4:36) በዚህም የዘመነ ሐዋርያት የመጀመሪያው መናኝ ተብሏል:: 2.ልሳነ እፍረት (ብርሃነ ዓለም) ቅዱስ ዻውሎስ ባመነ ጊዜ ሐዋርያት ለማመን ተቸግረው ነበር:: የሆነውን ሁሉ አስረድቶ ቅዱስ ዻውሎስን ከሐዋርያት ጋር የቀላቀለው ይህ ቅዱስ ነው:: (ሐዋ. 9:26) 3.አንድ ቀን መንፈስ ቅዱስ "ፍልጥዎሙ ሊተ ለሳውል ወለበርናባስ - በርናባስና ሳውልን (ዻውሎስን) ለዩልኝ" በማለቱ ሐዋርያት ጾመው: ጸልየው: እጃቸው ከጫኑባቸው በሁዋላ ላአኩአቸው:: (ሐዋ. 13:1) +እነርሱም ወንጌልን እየሰበኩ በየሃገሩ ዞሩ:: በሃገረ ልስጥራን መጻጉዕን ስለ ፈወሱ ሕዝቡ "እናምልካችሁ" ብለው የአማልክትን ስም አወጡላቸው:: 2ቱ ቅዱሳን ግን ይህንን ሲሰሙ ልብሳቸውን ቀደው በጭንቅ አስተዋቸው:: መመለክ የብቻው የፈጣሪ ገንዘብ ነውና:: (ሐዋ. 14:8-18, ዘጸ. 20:1) 4.በአንጾኪያ የነበሩ አሕዛብ ክርስትናን በተቀበሉ ጊዜ ከሐዋርያት ተልኮ ሒዶ በጐ ጐዳናን መራቸው:: (ሐዋ. 11:22) +ቅዱስ በርናባስ በአገልግሎት ዘመኑ መጀመሪያ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር: ቀጥሎ ደ

መመኪያዬ_እርስቴ_የሆነች.m4a9.71 KB

ሰባቱ መብራቶች.m4a1.06 MB

ሰላም ለኪ እንዘንሰግድ.m4a9.29 KB

#ገብርኤል_ማን_ነው? 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 #ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡ #ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ 👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ 👉*ገብርኤል ነው፡፡* የአሸናፊና የኃይል መልአክ *ገብርኤል ነው፡፡* ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ *ገብርኤል ነው፡፡ 🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏 ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ገብርኤል ከሰማይ.m4a1.03 MB

ገብርኤል ስለው.m4a8.76 KB

ገብርኤል መጣ.aac9.77 KB

ገብርኤል ሃያል.m4a1.04 MB

sticker.webp0.72 KB