cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ማኅበረ ቅዱሳን በአውስትራሊያ

Mahibere Kidusan Australia

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
240
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሠላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሠላም:: በልዕል እግዚአብሔር ሰላምታ እንደምን ቆያችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች ሁሌም እንደተለመደው ዛሬ ማታ ጸሎት እና ተከታታይ ትምህርት ይኖረናል ላልስሙት ለውንድም እህቶቻችን መልክቱን እንዲደርሳቸው በማድረግ እኛም በሳዓቱ በመገኝት ትምህርቱን እንድንከታተል እናሳስባለን።    ትምህርት ክፍል  ዘወትር ዓርብ 9pm ሜልበርን እና ፐርዝ 7pm በተለመደው ዙም ጆይን እናድርግ https://us04web.zoom.us/j/3382355051
Hammasini ko'rsatish...
Join our Cloud HD Video Meeting

Zoom is the leader in modern enterprise video communications, with an easy, reliable cloud platform for video and audio conferencing, chat, and webinars across mobile, desktop, and room systems. Zoom Rooms is the original software-based conference room solution used around the world in board, conference, huddle, and training rooms, as well as executive offices and classrooms. Founded in 2011, Zoom helps businesses and organizations bring their teams together in a frictionless environment to get more done. Zoom is a publicly traded company headquartered in San Jose, CA.

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዙ። * ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣ቅዳሴ ቤቱን ለማክበርና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለመባረክ እንዲሁም ምዕመናንን ለማስተማር ዛሬ ማለዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዙ። ቅዱስነታቸው ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑካንን በመምራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና ከቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል። በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራው የልዑካን ቡድን ደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ኦሊቨር ታምቦ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚደርሱበት ጊዜ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የከምባታና ሀላባ፣ ሀዲያና ስልጤ ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ካህናትና ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ያሚያደርጉላቸው ይሆናል። ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Hammasini ko'rsatish...
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሠላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሠላም:: በልዕል እግዚአብሔር ሰላምታ እንደምን ቆያችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች ሁሌም እንደተለመደው ዛሬ ማታ ጸሎት እና ተከታታይ ትምህርት ይኖረናል ላልስሙት ለውንድም እህቶቻችን መልክቱን እንዲደርሳቸው በማድረግ እኛም በሳዓቱ በመገኝት ትምህርቱን እንድንከታተል እናሳስባለን። ትምህርት ክፍል ዘወትር ዓርብ 9pm ሜልበርን እና ፐርዝ 7pm በተለመደው ዙም ጆይን እናድርግ https://us04web.zoom.us/j/3382355051
Hammasini ko'rsatish...
Join our Cloud HD Video Meeting

Zoom is the leader in modern enterprise video communications, with an easy, reliable cloud platform for video and audio conferencing, chat, and webinars across mobile, desktop, and room systems. Zoom Rooms is the original software-based conference room solution used around the world in board, conference, huddle, and training rooms, as well as executive offices and classrooms. Founded in 2011, Zoom helps businesses and organizations bring their teams together in a frictionless environment to get more done. Zoom is a publicly traded company headquartered in San Jose, CA.

በልዑል እግዚአብሔር ሰላምታ እንደምን ቆያችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች። ዛሬ ነገረ ሃይማኖት ትምህርት በሜልበርን 8:30pm ፐርዝ 6:30 የሚቀጥል ሲሆን በሰዓቱ እንድንገኝ እና መልእክቱን ለሌሎች እንድናስተላልፍ አደራ እንላለን። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Hammasini ko'rsatish...
ኀሙስ ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች (ሉቃ. ፳፬፥፳፭-፵፱)፡፡ ዐርብ የትንሣኤ እሑድ ስድስተኛዋ ዐርብ ደግሞ በክርስቶስ ደም ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቤተ ክርስቲያን› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ ሐዋ. ፳፥፳፰)፡፡ ቀዳሚት ሰንበት በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበያይባት ‹የቁራ ገበያ፣ የገበያ ጥፊያ› ተብላ ትጠራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጕልበታቸው ላገለገሉት፤ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት፤ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት፤ በትንሣኤውም ጌታችንን ከዅሉ ቀድሞ ለማየት ለበቁት ሴቶች መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቅዱሳት አንስት› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፭፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፫፥፳፯-፴፫፤ ፳፬፥፩-፲)፡፡ እሑድ ሰንበት በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤ ሰኞ የትንሣኤው ማግሥት ዕለተ ሰኞ ‹ፀአተ ሲኦል› ወይም ‹ማዕዶት› ትባላለች፡፡ ይህቺውም ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ናት (ዮሐ. ፲፱፥፲፰፤ ሮሜ. ፭፥፲-፲፯)፡፡ ማክሰኞ ይህቺ ዕለት፣ ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቶማስ› ተብላ ትጠራለች፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ በመጣ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት ‹‹ሳላይ አላምንም›› ብሎ ነበር፡፡ በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን በድጋሜ ለሐዋርያት ተገለጸ፡፡ ስለዚህም ይህቺ ዕለት በሐዋርያው ቶማስ ስም ተሰይማለች (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ረቡዕ ጌታችን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላስነሣው ለአልዓዛር መታሰቢያ ናት፡፡ በክርስቶስ ሥልጣን የአልዓዛርን ከሞት መነሣት አይተው ብዙ ሕዝብ በጌታችን ስለ አመኑ ዕለቲቱ (ረቡዕ) ‹አልዓዛር› ተብላ ትታሰባለች (ዮሐ. ፲፩፥፴፰-፵፮)፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
"እናመስግን አማኑኤልን"ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

"እናመስግን አማኑኤልን"ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video) #MKZwT#ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን#Mahiberekidusan Subscribe:

https://www.youtube.com/channel/UC2U27bED0bj7ONXPNmBEKmA

Telegram:

https://t.me/+5e0PniMWKnsyMWFh

Hammasini ko'rsatish...
"ሞታችንን ሻረ" ZwT || ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

"ሞታችንን ሻረ" ZwT || ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video) #MKZwT#ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን#Mahiberekidusan Subscribe:

https://www.youtube.com/channel/UC2U2...

Telegram:

https://t.me/+5e0PniMWKnsyMWFh

Hammasini ko'rsatish...
"ስለ ሥነ-ስቅለት" ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

Hammasini ko'rsatish...
"ኣሪፍ ኣይቸኩልም"ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

"ኣሪፍ ኣይቸኩልም"ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video) #MKZwT#ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን#Mahiberekidusan Subscribe:

https://www.youtube.com/channel/UC2U27bED0bj7ONXPNmBEKmA

Telegram:

https://t.me/+5e0PniMWKnsyMWFh