cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል

ይኽ የፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ቻናል ነው። በዚኽ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 016
Obunachilar
-124 soatlar
+17 kunlar
+430 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
Photo
1300Loading...
02
+<< #ወይን_ለማይጠጣ_ሕይወቱ_ምንድን_ነው? >>+ "ምንትኑ ሕይወቱ ለዘኢይሰቲ ወይነ" (ሲራክ. 34:26) =>#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን ወይንን (ጠላ: ቢራ . . .) ¤"አትጠጡ" ብላ አትከለክልም:: ¤ግን ደግሞ "ጠጡ" ብላም አታበረታታም:: ¤አልኮል መጠጦችን መጠቀም "ኃጢአት ነው" አትልም:: ¤ግን ደግሞ " . . . ካያያዝ ይቀደዳል" እንዲሉ አጠቃቀማችን ወደ ኃጢአት ሊወስደን ስለሚችል "ጥንቃቄን አድርጉ" ትለናለች:: +በዘመናችን ከመጠጥ ጋር በተያያዘ (በተለይ ለክርስቲያኖች) 2 ፈተናዎች ይታያሉ:: 1.አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመን (በተለይ ወጣቱና ጐልማሳው) አነሰም በዛም ጠጪ እየሆነ ነው:: (ልብ በሉልን "ይሰክራል" አላልኩም) 2.እጅግ በሚያስቀይም መንገድ ለመጠጣት ጥቅሶች ከቅዱስ መጽሐፍ ሲጠቀሱ እየሰማን ነው:: +በተለይ "#ወይን_ያስተፌስሕ_ልበ_ሰብእ" (መዝ. 103:15) ከእኛው አልፎ በዘፈንና በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያዎች ላይ ሲጠቀስ ስንሰማ አንጀታችን ካላረረ የቁም ሙት ሆነናል ማለት ነው:: +አሕዛብ ከመጽሐፋቸው አንዲት ዘለላ ብትነካ ሃገሪቱን በተቃውሞ እንደሚንጧት እናውቃለን:: ¤እኛ ግን #የሊቀ_ሰማዕታት ስም የቢራ ማሻሻጫ ሲሆን: #ቅዱስ_ቃሉ ለአልኮል መጠጥ ሲጠቀስ: #በአባቶቻችን_ካህናትና_ጻድቃን ላይ በፌዘኞች (ኮሜዲያን ነን ባዮች) ሲቀለድ: ማንም ባለጌ በተቀደሰች ሃይማኖታችን ላይ አፉን ሲከፍት ምንም አይመስለንም:: (አንቀላፍተናላ!!!) =>ወደ ጉዳዬ ልመለስና የወይንን ነገር እንጨዋወት:: "የትውልዱ ክፋቱ ኃጢአት መሥራቱ አይደለም:: ይልቁኑ ኃጢአቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስመሰሉ እንጂ" ብለውኛል የኔታ ክንፈ ገብርኤል:: (በቀኝ ያቁማቸውና!!!) +ዛሬ በሃገሪቱ የሚገኘውን ጠጪ (ካልጠጣ የሚሞት የሚመስለው) በመቶኛ/በ% ቢሰላ አብዛኛው (ምናልባት እስከ 90 % ) ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ባይ ነው:: +ታዲያ ይህ ጥራዝ ነጣቂ ትውልድ ለምን ስትሉት "ዳዊት እንዲህ አለ: ሐዋርያው ቅ/ዻውሎስ እንዲህ አከለ . . ." ይላል:: << ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ስለ ወይን መጠጣት የሚናገሩ ቃላት ትርጉም እንደሚባለው ነው?? #ለመሆኑ_ቅዱስ_መጽሐፍ_ጠጪነትን_ያበረታታል?? አምላካችን እግዚአብሔርስ ወደዚህች ምድር ያመጣን ለዚሁ ግብር ነው?? (ሎቱ ስብሐት!!!) >> +ቅዱስ ቃሉን ለገዛ ፈቃድ መተርጐም ፍጹም ኃጢአት ነው:: (2ዼጥ. 1:20) ስለዚህም "ወይን" የሚሉ ቃላት ምንድን ናቸው? ወደሚለው እንመለስ:: +በመጀመሪያ ግን #ብርሃነ_ዓለም: #ዓዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ) #ቅዱስ_ዻውሎስ ለደቀ መዝሙሩ #ቅ/ጢሞቴዎስ ስለ ምን "ውሃ ብቻ አትጠጣ:: ጥቂት ወይን ጨምር" አለው ቢሉ:- 1.ወይን በዘመኑ ለሆድ በሽተኞች ፍቱን መድኃኒት ስለ ነበር ነው:: (ቃሉም የሚለው ስለ ሆድህ ህመም ነው(1ጢሞ. 5:23)) ቅዱሱ ከገድል የተነሳ ሆዱ ፍጹም ሕመምተኛ ነበርና:: 2.ወይን መጠጣት በልኩ (ጥቂት) የሆነ እንደሆን አካልን ያለመልማል:: ልቡናን ያረጋጋል:: ግን በጊዜው: በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ነው:: +#ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ ግን "ወይን" ተደጋግሞ የተጠቀሰባቸው በርካታ መንፈሳዊ ምስጢራት አሉ:: እነዚህን መነሻ ርዕስ ባደረግነው: በቃለ ሲራክ ተመርኩዘን እንመልከታቸው:: =>ነቢዩ "#ወይን_ለማይጠጣ_ምን_ሕይወት_አለው?" ይላል:: 1.ወይን=(#ምስጢረ_ሥላሴ) ¤"ምስጢረ ሥላሴን ላላመነ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ይለናል:: የእግዚአብሔርን አንድነት: ሦስትነት ሳያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወት የለምና:: (ዮሐ. 1:12, 3:17, ማቴ. 28:19) +ምስጢረ ሥላሴ በወይን መመሰሉን #አባ_ሕርያቆስ በቅዳሴው "አብ ጉንደ ወይን: ወልድ ጉንደ ወይን ወመንፈስ ቅዱስ ጉንደ ወይን . . ." ሲል ነግሮናል:: 2.ወይን=#ክርስቶስ (#ምሥጢረ ሥጋዌ) ¤በወልድ (ክርስቶስ) ያላመነ የዘለዓለም ሕይወት የለውም:: (ዮሐ. 3:36) ስለዚህ ነገር ጌታችን ራሱን የወይን ግንድ: አባቱን ተካይ አድርጐ ሲጠራ እንሰማዋለን:: "#አነ_ውእቱ_ጉንደ_ወይን=እኔ የወይን ግንድ ነኝ" እንዲል:: (ዮሐ. 15:1) +መዳን የሚቻለውም መድኅን ክርስቶስን "#አምላክ_ወልደ_አምላክ: #ወልደ_አብ_ወልደ_ማርያም: #ሥግው_ቃል" ብሎ ማመን ሲቻል ነው:: 3.ወይን=#ድንግል_ማርያም (#ነገረ_ማርያም) ¤ጌታን ወይን ካልን ድንግል ማርያምን #ሐረገ_ወይን: #አጸደ_ወይን ልንላት ግድ ይለናል:: (እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘመነ ጽጌ) +መዳንን የሚሻ ሁሉ እመቤታችን ማርያምን #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን: #ዘለዓለማዊ_ድንግልናዋን: ፍጹም ሞገስ ያላት #አማላጅ መሆኗን: #ቅድስናዋንና #ክብሯን ሊያምን ግድ ይለዋል:: (መዝ. 44:9, 86:5, ኢሳ. 1:9, 7:14, ሕዝ. 44:1) 4.ወይን=#ቅዱሳን (#ነገረ_ቅዱሳን) ¤መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን የወይን ግንድ ብሎ አልቀረም:: ወዳጆቹን #ወአንትሙሂ_አዕጹቂሁ=እናንተ የወይኑ ቅርንጫፎች ናችሁ" ይላቸዋል:: (ዮሐ. 15:5) +ስለዚህም በቅዱሳን #ክብር: #አማላጅነት: #ፈራጅነትና #የጸጋ_አማልክትነት ልናምን ግድ ይለናል:: (ዘጸ. 7:1, መዝ. 81:1, ማቴ19:28) 5.ወይን=#ሥጋ_ወደሙ (#ምስጢረ_ቁርባን) ¤#እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ቸር ልጇን የጠየቀችው ስለጊዜአዊው መጠጥ ቢመስልም ምስጢሩ ግን ለዘለዓለማዊው መጠጥ (ክቡር ደሙ) ነው:: (ዮሐ. 2:1) +ለዚያም "#ወይንኬ_አልቦሙ=ወይንኮ የላቸውም" ስትለው: "ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ=እናቴ ሆይ! በቀራንዮ አንባ ሥጋና ደሜን የምሰጥበት ጊዜየ ገና ነው" ሲል የመለሰላት:: +ወንጌል ደግሞ እንዲህ ይላል:: "የክርስቶስን ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም::" (ዮሐ. 6:53) ¤የወይን ትርጉም ይቀጥላል . . . ለእኛ ግን እዚህ ላይ ይብቃን:: +ቅዱሱ #ነቢይ_ሲራክ "ወይን ለማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ሲል በአንክሮ የጠየቀው ስለዚህ ነው:: ¤በወይን በተመሰሉ #በሥላሴ: #በምስጢረ_ሥጋዌ: #በነገረ_ማርያምና #ነገረ_ቅዱሳን ሳያምኑ: ከወይኑ ግንድ ክርስቶስ ጐን በፈሰሰ #ማየ_ገቦ ሳይጠመቁና #ከቁርባኑ ሳይሳተፉ ሕይወት የለምና:: =>ቸር አምላከ ቅዱሳን የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን:: << ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
1192Loading...
03
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ††† ††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው : በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው:: ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር:: አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት : ገና በ3 ዓመቱ : እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ:: ††† ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:- 1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ:: 2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ:: 3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው:: ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን:: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው:: "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን : ዕጸበ ገዳምን : ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል:: ††† በዘመኑም:- 1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል:: 2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል:: 3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል:: 4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን:: ††† ሰኔ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ 2.ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው) 3."16,000" ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ) 4.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) ††† "ይሕንን እዘዝና አስተምር :: በቃልና በኑሮ : በፍቅርም : በእምነትም : በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው:: እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር : ለማስተማርም ተጠንቀቅ::" ††† (1ጢሞ. 4:11) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
1390Loading...
04
ዕርገት ‹ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡ በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪-፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡ በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡- ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡- ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡ በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩-፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ ‹አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው›፤›› በማለት ቅዱስ ወንጌልን መሠረት ባደረገ ኃይለ ቃል ጌታችን ወደ ሰማይ ስለ ማረጉና ለሐዋርያት አምላካዊ ትእዛዝ ስለ መስጠቱ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡ ይቆየን
1230Loading...
05
https://m.payquiz.icu/75237184342481291/
980Loading...
06
††† ✝እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አቡነ ተጠምቀ መድኅን ††† ††† ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው #ወልደ_ክርስቶስና #ወለተ_ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ #ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ #ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ:: ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት:- 1.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል 2.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል 3.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) 4."7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: ††† ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ #ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ #በጋሾላ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: ††† ቅድስት ማርታ ††† ††† እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች:: መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን (በበዓለ ልደት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት:: ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት:: ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ25 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች:: ††† የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: ††† ††† ሰኔ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ማርታ ተሐራሚት 2.አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 3.ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት 4.ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት †††ወርኀዊ በዓላት 1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን) 4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5.አቡነ ዜና ማርቆስ 6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል ††† "አልሞትም: በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ::" †††  (መዝ. 117:17-22) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
2330Loading...
07
††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ††† †††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:- ¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ ¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ ¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ ¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ ¤ጌታውን ያጠመቀና ¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:- ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች:: ††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ††† ††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:- ¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ ¤መናኔ ጥሪት የተባለ ¤በድንግልና ሕይወት የኖረ ¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት ¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ ¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል:: ቅዱስ ዮሐንስ ¤ቁመቱ ልከኛ ¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ ¤የራሱ ጸጉር በወገቡ ¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ ¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር:: ቅዱስ ኤልሳዕ ¤በጣም ረዥም ¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ) ¤ቀጠን ያለ ¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር:: በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት:: ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል:: በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል:: ††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን:: †††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ) 3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ †††ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ 4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ †††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" ††† (ማቴ. 11:7-15) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
1900Loading...
08
Photo
1673Loading...
09
"የጥበብ  መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው" ምሳሌ ፩÷፯ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የተወደዳችሁ የሰንበት ት/ቤታችን አባላትና የመፅሐፍ ቅዱስ ንባብ ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ ፥ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረስ። 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 ከሰኔ 03/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከጥበብና የመዝሙር መፃሕፍት ውስጥ የሚመደበውን መፅሐፈ ምሳሌ ማንበብ እንደምንጀምር እናበስራለን። መጽሐፈ ምሳሌ 24 ምዕራፎች ሲኖሩት ሰዎች በተለይም በወጣትነት ዘመናቸው በአኗኗራቸው ጥበበኞች እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል መጽሐፍ ነው። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 የመጽሐፈ ምሳሌ ዋነኛ ትኩረት – ሰው ጥበብ ፥ ማስተዋልና እውቀት እንዲያገኝ – ሰው ትክክለኛ፥ ፍትሐዊና፥ መልካም ነገርን እንዲያደርግ፥  – ሰው የተለያዩ ምሳሌዎችን፥ ምሳሌያዊ አነጋገሮችንና እንቆቅልሾችን እንዲረዳ፥  – ጥበበኞች በጥበባቸው ላይ ተጨማሪ ጥበብ እንዲያገኙ ለመርዳት፥  – ሰው ሥርዓት በተሞላበት ሕይወት እንዲኖር ለማስቻል፥  – ሰው የጥበብ መጀመሪያ የሆነውን «እግዚአብሔርን መፍራት» እንዲማር ለመርዳት የሚያችሉ ሀሳቦችን በውስጡ ይዟል። 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ይህንን የጥበብ መፅሐፍ አንብበን ከጥበብ ገበታ ለመሳተፍ እየተዘጋጀን እንቆይ። ከ ሰኔ 03/2016 ጀምሮ  ⏳⏳⏳
2063Loading...
10
👍
10Loading...
11
Photo
2170Loading...
12
፨፨፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚችም ዕለት የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም አመታዊ የበዓሏ መታሰቢያ ነው፨፨፨ ✝✞✝ ቅድስት ዜና ማርያም ✝✞✝ ፨ በ11መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት ግንቦት 30 ቀን በጎጃም ክፍለ ሀገር ተወለደች። የአባቷ ስም ገብረ ክርስቶስ የእናቷ ስም አመተ ማርያም ይባላሉ። እጅግ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፡ ቅዲስ ጋብቻቸውን በንጽሕና የሚጠብቁ፡ ለሰው የሚራሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ። እንዲህ ባለ መልካም ግብር ከኖሩ በኀላ በፈቃደ እግዚአብሔር 3 ወንዶች ልጆች እናት አንዲት ሴት ልጅ ወለዱ። ይህችም ሴት ልጅ ተወዳጇ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ናት። ፨ ቅድስት ዜና ማርያም እናት እና አባቷን እያገለገለች፡ ፈርሐ እግዚአብሔን፡ በጎ ምግባርን ከወለጆቿ እየተማረች አደገች። ለአቅመ ሔዋንም በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ ወጣት አጯት። ታላቅ ግብዣ ተደረጎ በተክሊል ተዳረች። በዚያው ወራት ግን የዜና ማርያም እናት አመተ ማርያም አምስተኛ ልጅ ወልዳ ተኝታ ሳለች በአካባቢው ሕማመ ብድብድ (ተላላፊ በሽታ) በመነሳቱ የዜና ማርያም እናት ታማ ነበር፡ በመጨረሻም ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈች። ፨ ከዚህ በኋላ የታመመውን ወንድሟንና ሌሎቹንም በመያዝ ከተላላፊው በሽታ ለመትረፍ ሲሉ አካባቢውን ለቀው ወደ በረሃ ወጡ። በዚያም ሌሊት የዱር አራዊት መጥተው ከበቧቸው ሁሉንም ሊበሏቸው ሞከሩ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ስመ እግዚአብሔርን ስትጠራ አራዊቱ ወደኋላ በመሸሽ ከአካባቢው ራቁ። እርሷም ከክፉ ሁሉ የጠበቃቸውን፡ ከአራዊት መበላት የሰወራቸውን እግዚአብሔርን አመሰገነች። በነጋም ጊዜ የታመመውን ወንድሟን እና ሌሎችን በመያዝ መንገድን ቀጠሉ አንዲት ባዶ ቤት አግኝተው ከእርሷ ተጠጉ። በፀሐዩ ንዳድና ታናሽ ወንድሟን በማዘል እጅግ ስለደከመች ከባድ እንቅልፍ ጣላት። ጠዋት ስትነሳ ግን የታመመው ወንድሟ ከአጠገቧ አላገኘችውም ሌሊት የዱር አራዊት በልተውታልና። አጅም አዘነች የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብላ አራሷን አፅናናች የወንድሟን ተረፈ ሥጋ አጠራቅሟ ቀበረች። በመቀጠልም በአካባቢው ካለ ገዳም ሔዳ ምንኩስናን ተቀበለች። ፨ ከዚህ በኋላ ባሏ አባቷን ሚስቴን አምጣ እያለ ስለጨቀጨቀው ከብዙ ልፋት እና ድካም ፈልጎ አገኛት ወደ ሀገሯም ወሰዳት። በዚያም ወደ ጉባኤ ቀርባ ለምን ወደ ገዳመ እንደሄደች እና ባሏን አንደከዳች ተጠየቀች። እርሷም እግዚአብሔር ከብዙ መከራ አድኖኛል እና እራሴን ለእግዚአብሔር ሰጥቻለሁ አለች። የጉባኤው ተሰብሳቢ በሏ ሀብቷን ወርሶ እንዲያሰናብታት ፈረዱ። እርሷም በዚህ ነገር በመስማማት የነበራትን ላም እና በሮች አስረከበች። ፨ ከዚህ በኋላ በአባቷ ቤት ለአንድ ዓመት ያህል በመቀመጥ የእናቷን ተዝካር አውጥታ ወደ ገዳሙ ተመለሰች በዛም ለጥቂት አመታት የተለያዩ ገድላትን ስትፈጽም ከቆየች በኋሏ ከነፍስ አባቷ ባሕታዊ አባ ገብረ መስቀል ጋር ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ እንፍራንዝ (ጣራ ገዳም) አካባቢ ዋሻ እንድርያስ በተባለው ለ25 ዓመት በብሕትውና ኖረች። አሁንም ድረስ በዚያ ዋሻ እናታችን ዜና ማርያም በፀሎት ጊዜዋ እንቅልፍ እንዳይጥላት ስትጠቀምበት የነበረ ዘንግ ፣ የምተቆምበት ዙሪያውን በገመድ የታሰረ የተቦረቦረ ግንድ አሁንም ድረስ ተአምር እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚህም በመቀጠል ዛሬ ዜና ማርያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ዋሻ ሔደች በዚያም በጾምና በጸሎት በልዩ ልዩ ተጋድሎ እስከ እለተ እረፍቷ ድረስ በዚያ ኖራለች። +++ የገድል ዓይነቶች +++ ፨ በየሰዓቱ ከ 100-300 ትሰግድ ነበር ፨ ሁለት ቀን እየፆመች በሶስተኛ ቀን ጥቂት ጥሬ ቀምሳ ሳምንቱን ታሳልፈው ነበር ፨ 150ን መዝሙረ ዳዊት እና ወንጌል በየቀኑ ትጸልይ ነበር ፨ በብሕትውና ወራት ማር፣ ቅቤን፣ ወተትን ፈጽሞ አትቀምስም ነበር ፨ የጌታችን መከራ መስቀል እና ስትየ ሐሞት በማሰብ በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ኮሶ የሚባል ቅጠል እየበጠበጠች ከቅል ውስጥ ከሚገኘው መራራ ፍሬ ጋር በማዋሐድ ትጠጣ ነበር ፨ ከጸሎት እና ከስግደት በምታርፍበት ጊዜ አትክልት በመትከል እና በመኮትኮት ጊዜዋን ታሳልፍ ነበር ፨ የጌታችንን ግርፋቱን በማሰብ 100 ጊዜ ጀርባዋን ስለምትገረፍ እና ደም ስለሚፈሳት ጀርባዋ ይቆስል እና ይተላ ነበር። +++ተአምራት+++ ፨ ዓይናቸውን በተለያየ በሽታ የታመሙ ሰውዎች ሁሉ ከህመማቸው ተፈውሰዋል ፨ የራስ በሽታ ( የራስ ፍልጠት፣ ጭንቀት፣ ማዞር) የታመሙ ጸበሉን በመቀባት ድነዋል፡፡ ፨ ጸበሉን በመጠመቅ፤ የጻድቋን ተአምር በማዘል፤ ስዕለት በመሳል መካኖች ወላድ ሆነዋል። ሌሎች በየቀኑ ብዙ ተአምራትን እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ታደርጋለች። +++ቃል ኪዳን+++ ቅድስት ዜና ማርያም ከዚህ ዓለም የምታርፍበት ጊዜ እንደደረሰ በመንፈስ ቅዱስ በአወቀች ጊዜ ከታላቅ ዛፍ ወጥታ ስትፀልይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ጋር፣ ከነቢያት፣ ከሐዋርያት፣ ከሰማዕታት፣ ከጻድቃን፣ ከደናግል መነኮሳት ጋር በመሆን ተገልጾ ከአረጋጋት በኋላ ቃል ኪዳንን ሰጧታል። ፨ በፀሎትሽ ያመነውን ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ ፨ በስምሽ የተራበውን ያበላ በመንግስተ ሰማያት ኅብስተ ሕይወት አበላዋለሁ፤ የተጠማውን ያጠጣ ጽዋዓ ሕይወትን አጠጣዋለሁ ፨ መጽሐፈ ገድልሽን የጻፈውን፡ ያጻፈውን፡ የሰማውን፡ ያሰማውን ስሙን በዓምደ ወርቅ እጽፈዋለሁ ፨ ከሕፃንነትሽ እስከ አሁን ድረስ ስለ እኔ ብለሽ ብዙ መከራ ተቀብለሻል፦ ደጅሽን የረገጠ የሦስት ጭነት ጤፍ ያህል ነፍሳትን እንደሚምርላት፡ እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት ጌታችን በማይታበል ቃሉ ቃልኪዳን ገብቶላታል። እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት፡፡ +++ ገዳሟ እና መገኛው+++ ፨ የቅድስት ዜና ማርያም መካነ መቃብሯ ( ጸበሏ) በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ከም ከም ወረዳ ይገኛል ቦታውም አዲስ ዘመን ከተማ 20 ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከከተማው በስተሰሜን በኩል "ደሪጣ" ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ይገኛል። "ደሪጣ" ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜው ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ (ገዳም) ተብሎ እስከ አሁን ድረስ እየተጠራ ይገኛል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም በቅድስት ዜና ማርያም ገድል ውስጥ " ወትሰቲ ሲካር (ኮሶ) ደሪፃ" የሚል ቃል ይገኛል። ይህም ማለት ኮሶ የተባለውን እንጨት (ቅጠል) ቀጥቅጣ (አልማ) ከቅል ውስጥ ከሚገኘው ፍሬ ጋር በማደባለቅ ትጠጣለች ማለት ነው። ስለዚህ ቦታው "ደሪፃ" ተብሎ ተሰየመ በማለት በአካባቢው የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ። በመጨረሻም ተጋድሎዋን በመፈጸም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን ከዚህ አለም ድካም ዐርፋለች። የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም በረከቷ ቸርነቷ ይደርብን። አሜንን!! +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎታ፡፡ ወበረከታ ለቅድስት ዜና ማርያም የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን!!! +++ https://t.me/zikirekdusn
1791Loading...
13
<<+>>✝✝   #የሰኔ_መዓልት <<+>>✝✝ =>ቀደምት #ኢትዮዽያውያን ሰው ወሬ ሲያበዛባቸው "#ምነው_የሰኔ_መዓልትን_ሆንክብኝ!" ሲሉ ይተርቡ ነበር:: "አሳጥርልኝ! ወሬህ ረዘመብኝ!" ለማለት ነው:: +ለዚህ መነሻ የሆነው ደግሞ ከ13ቱ ወራት መዓልቱ (ቀኑ) ቶሎ የማይመሽበት ወር ሰኔ መሆኑ ነው:: በእርግጥ ንግግራችን አጭርና ግልጽ ቢሆን ሁሌም መልካም ነው:: ሰው እስኪሰለቸን ድረስ ማውራቱ የሚገባ: የሚመችም አይደለምና:: +"ሺ ዓመት አላወራ! በናትህ (ሽ) ትንሽ ላውራ?" እያሉ መንዛዛቱም ቢሆን አይመከርም:: << እኔም ወደ ጉዳዬ ልግባ >> +ከዓመቱ 13 ወራት የሰኔ መዓልቱ ለምን ረዘመ ብንል:- መልሱ አጭር ነው:: "#ይህ_የእግዚአብሔር_ጥበብና_ሥራ_ነው::" ሳይንሱ ሺህ መንስኤን ሊደረድር ይችላል:: ለእኛ ግን አበው እንዳስተማሩን ሰኔ #የሥራና_የጾም ወር ነው:: +ትጋትን የሚወድ አምላክ ይህንን ወቅት ለጾም ለሥራና: ለበጐ ተግባር አርዝሞልናል:: በእርግጥ ጥቂት ሠርተን ብዙ ለምንተኛ ለዚህ ዘመን ሰዎች ይህ ሊጸንብን ይችል ይሆናል:: ግን ምንም እንኩዋ ሁሉ ወራት ለሥራ ቢሠሩም ወርሃ ሰኔ #ለገበሬና #ለክርስቲያን ትልቁን ሥራ የሚጀምሩበት ወቅት ነው:: +በሰኔ ያልተጋ #ገበሬ ዓመቱን ሙሉ መከረኛ ነው:: ከነ ተረቱም "#ሰነፍ_ገበሬ_ይሞታል_በሰኔ" ይባላል:: +#ክርስቲያንም ከበዓለ ሃምሳ ማግስት #በዓለ ዸራቅሊጦስን ተደግፎ ሰኔን ሊተጋባት ግድ ይላል:: በመከራ ዘመን የሚመሰል #ክረምት ሳይመጣ በወርሃ ሰኔ ሊተጋ ግድ ይለዋል:: ሽሽቱ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆንም ይጸልያል:: (ማቴ.24:20) +#እግዚአብሔር ሁሉን በሁሉ የሠራ: ያዘጋጀና የፈጸመ ጌታ ነው:: ምንም እንዳይጐድልብንም አድርጐናል:: በተለይ #የኢ/ኦ/ተ_ቤተ_ክርረስቲያን ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነው:: ለሁም ነገር ትርጉምና ሸጋ የሆኑ ሐተታዎች አሏት:: +ስለዚህም የዘመን ቀመሯን መሠረት አድርጋ #ወርሃ_ሰኔ መዓልቱ 15: ሌሊቱ 9 ነው ትላለች:: ብርሃኑ ሲበዛም እንዲህ ትለናለች:: ¤ብርሃን #ጌታ_ነው:: (ዮሐ. 9:5) ¤ብርሃን #ድንግል_ማርያም_ናት:: (ራዕይ. 12:1) ¤ብርሃን #ቅዱሳን_ናቸው:: (ማቴ. 5:14) +ቀጥሎም መጽሐፍ እንዲህ ይለናል:- "#አምጣነ_ብክሙ_ብርሃን: #እመኑ_በብርሃን: #ከመ_ትኩኑ_ዉሉደ_ብርሃን: #ዘእንበለ_ይርከብክሙ_ጽልመት" (ጨለማ ሳያገኛችሁ: ብርሃንም ሳለላችሁ: የብርሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ: በብርሃን እመኑ) (ዮሐ. 12:36) =>አምላከ ብርሃን: ወላዴ ሕይወት አምላካችን: ቸር ብርሃኑን ይላክልን:: ተረፈ ዘመኑንም የሰላምና የበረከት ያድርግልን:: << ወስብሐት ለእግዚአብሔር >> " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ (re)  Dn  Yordanos Abebe 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
2442Loading...
14
Photo
3121Loading...
15
✝✝✝ በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: ✝✝✝ "✝" ግንቦት 26 "✝" +*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+ =>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው:: +እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ:: +አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል:: +ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ:: +አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ:: +አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ:: +በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው:: +በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ:: +ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- +ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ:: +በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው:: +ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ:: +ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል:: +እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም:: "እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ:: መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል:: +ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::} << ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! >> =>+"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: +"+ (1ዼጥ. 5:3)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
2731Loading...
16
Media files
2971Loading...
17
አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡"
3090Loading...
18
Media files
10Loading...
19
†✝️†🌷 እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †✝️†🌷 †✝️†🌷 ደብረ ምጥማቅ 🌷†✝️† =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: +ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: +በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: +እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: +የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: +እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ††† 🌷አባ መርትያኖስ 🌷††† =>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር:: +አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው:: ††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: ††† =>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ) 2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት) 3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ 4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ =>ወርኀዊ በዓላት 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ =>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17) ✝️✝️✝️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝️✝️✝️
3170Loading...
20
በፎቶው ላይ የምታዩት አፄ ቅዱስ ካሌብ የመነነበት : አክሱም አካባቢ የሚገኝ የአባ ጰንጠሌዎን ገዳም ነው) የቅዱሱ ንጉሥ በረከቱ ይደርብን:: https://t.me/zikirekdusnt
3110Loading...
21
የወርሐ ግንቦት ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት መጽሔትን ያውርዱት ..........ያንብቡት..........ያጋሩት የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የመካነ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
3 1707Loading...
22
"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡ እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡" (ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)
3382Loading...
23
Media files
3000Loading...
24
†✝† እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †✝† †✝† በዓለ ዸራቅሊጦስ †✝† ✝✞✝ ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,978 ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን:: ††† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል *ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ: *በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ: *በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: *ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ: *በ30 ዘመኑ ተጠምቆ: *ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ: *በፈቃዱ ሙቶ: *በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ: *በአርባኛው ቀን ያርጋል:: +ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው:: +እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው:: +ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ:: +ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል:: "ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ: ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ: ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ:: +በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:- 1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-" *እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና:: 2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-" *አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች:: ††† አባ ገዐርጊ ††† =>በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር። ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ።እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ። በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት። ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ። ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች። እሊህ ቅድሳንም ለመነኰሰኘሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኃላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ።ከእርሱ በኃላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን። =>በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። =>አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን:: =>ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት 2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ:: ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
2580Loading...
25
Photo
2460Loading...
26
📝ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው። 📝ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት። 📝እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው፦ 1. ወንጌላዊ 2. ሐዋርያ 3. ሰማዕት ዘእንበለ ደም 4. አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ) 5. ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት) 6. ወልደ ነጐድጓድ 7. ደቀ መለኮት ወምሥጢር 8. ፍቁረ እግዚእ 9. ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ) 10. ቁጹረ ገጽ 11. ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ) 12. ንስር ሠራሪ 13. ልዑለ ስብከት 14. ምድራዊው መልዐክ 15. ዓምደ ብርሃን 16. ሐዋርያ ትንቢት 17. ቀርነ ቤተ ክርስቲያን 18. ኮከበ ከዋክብት 🤲 በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር። ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን። 🤲 🗓 ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ) 3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት) 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ   (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም) 4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 7.አባ ዳንኤል ጻድቅ 📖"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፡ የእናቱም እህት፡ የቀለዮዻም ሚስት ማርያም፡ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን፡ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት። ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።" (ዮሐ. 19:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨ 🔗https://t.me/zikirekdusn
2730Loading...
27
✝ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ 🗓 ግንቦት 16 የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 🌕 ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ 📝 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ፡ በገሊላ አካባቢ አድጐ፡ ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል። 💡ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል። 📝 ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ። ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው። 📝 ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል። ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው። ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል። 📝3 መልዕክታት፡ ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል። ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል። ከእሳት እስከ ስለት፡ እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል። እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል።      ቅዱሱ በኤፌሶን 📝ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል። ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ። 📝ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ። ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው። በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች። ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ። ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ። 💡ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ። እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም። በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው። 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ። እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ። 📝አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ። 1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው። 2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው። ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች። 📝ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ። እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ። ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው። ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ። 📝የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ። ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው። 📝ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ። ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው። መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ። በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ። ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው። 💡በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ። እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን፡ ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው። በስመ ሥላሴ አጥምቆ፡ ካህናትን ሹሞ፡ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል። በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል። ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች። 📝ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው። በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች። አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት። 📝ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል። ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው። በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት፡ በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል። ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል። የፍቅር ሐዋርያ 📝ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች። ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል።  በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር። 💡በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል፦ "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል:: ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ፦ "ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፡ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ) 📝ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው፡ እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር። እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና። 📝ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል። ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል። 📝ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው። ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው፡ ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ፦ "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ፡ ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት።
2242Loading...
28
በቅርብ ቀን ...
2420Loading...
29
ስለ ሥራው ሁሉ እግዚአብሔርን አመሥግኑ ፩ኛ ተሰሎንቄ ፭፥፲፰ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በቅድሚያ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያቀረብን በሰንበት ትምህርት ቤታችን ዘውትር ሐሙስ እንዲሁም በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች ወደ አምላካችን የምንጸልያቸውን የጸሎት ክፍሎች በአንድ ላይ ያካተተ የጸሎት ጥራዝ በህትመት ላይ ይገኛል። ☘☘☘☘☘☘☘ በዚህ የበረከት ሥራ ውስጥ ለመሳተፋ የምትፈልጉ እንዲሁም ቃል የገባችሁ አባላትና የገብረ መንፈስ ቅዱስ ወዳጆች ......... አንድ ጥራዝ በግላችሁ በማሳተም ከጸሎት በረከት ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ✨✨✨✨✨✨✨ በዚህ ሥራ ውስጥ የሚሳተፉ አባላት ሥመ ክርስትና ዘወትር በሰንበት ት/ቤቱ የጸሎት መርሐ ግብር ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ +251940252987                                       +251973406517 ሥነ-ሥርዓትና ግንኙነት ክፍል
2720Loading...
30
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊 (ማቴ ፫:፫) ✨በአማን ተንሥአ መድኃኒነ!✨ 🌿ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም። ⚜ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ። 🌿ወልደ እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ዕቀብ  ሕይወተነ እም ገሀነመ እሳት ወእምኵሉ መንሱት በእንተ ቅዱስ ስምከ ወበእንተ ማርያም እምከ ወበእንተ ቅዱስ መስቀል ወበእንተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሀባ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተክርስቲያን። ⚜ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በዛቲ ዕለት መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት። ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኩሉ ሰዓት እንበለ ንስሐ ኪያነ ኢይንሣእ ሞት። 🌿አንቅሐኒ በጽባሕ ክሥተኒ ዕዝንየ በዘአጸምእ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ" ⚜ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፤ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፤ ገዳማውያን ወሊቃውንት፤ ሰአሉ ለነ ኲልክሙ፥ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት። 🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን። ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር) 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🔰🛑ግእዝ ለመማር  https://t.me/lisanegeez5
2060Loading...
31
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡ በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
3091Loading...
32
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +°✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ✝°+ =>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:: << ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? >> +ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: +ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: +ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: +ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: +ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል " አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: +በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: +አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ (ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: +ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: +በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: +"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: +"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: +'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: +አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: +ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: +ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል:: ✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- *ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ *አፈ በረከት *አፈ መዐር (ማር) *አፈ ሶከር (ስኳር) *አፈ አፈው (ሽቱ) *ልሳነ ወርቅ *የዓለም ሁሉ መምሕር *ርዕሰ ሊቃውንት *ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) *ሐዲስ ዳንኤል *ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) *መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ *ጥዑመ ቃል - - - +እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ ይክፈለን:: +ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56 ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል:: +እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: ❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር ያድለን::
2852Loading...
33
ያሬድ ነጎድጓድን ..ከደመናት ተውሶ ዜማን ....ከመላዕክቱ ማዕድ ቆርሶ ብስራትን ...ከገብርኤል ቀንሶ የሚካኤልን ሰይፍ... ተንተርሶ ያሬድ በልሳኑ እያዜመ ...በልቡ እየተቀኘ የድጓውን ባህር ቀዝፎ...በቅኔው ማዕበል እየዋኘ ከላይ....ከመላዕክቱ ነጥቆ ምድርን ..በዜማ ሰንጥቆ በመወድሱ ጎርፍ ...አጥለቅልቆ በዝማሬው ሰረገላ ...አምጥቆ መሬት ላይ አንስቶ...ከሰማይ ያደረሰን ከመላዕክቱ ጋር አቁሙ...ግዕዝና ዕዝል ያዘመረን አራራይ ብሎ በርህራሔ...በዝማሬ ሲቃ ያስለቀሰን ያሬድ ዋይ ዜማ እያለ....ዋይታን አጥፍቶ ዋይታ ልቅሶአችን ቀይሮ...ዋይ ዜማ ዝማሬን ተክቶ እንደ መላእክቱ አርቅቆ እንደ ሰውም አድምቆ ሰማይና መሬት አስተባብሮ ከመላእክቱ ጋር ደምሮ "ሃሌ ሉያ" ብሎ አዘምሮ በዜማ ቁልፉ ከፍቶ...በቅኔው በትር ገልጦ አሳየን ከላይ እግዜርን...ከዜማ ወንበር ላይ አስቀምጦ ያሬድ ኢትዮጵያ ላይ... የቆመ የዜማ ብርሃን ሻማ ጥበብን ያገኘንበት ...የመስፈሪያው አውድማ ይህ ነው ብርሃን የአለሙ...ኢትዮጵያዊ ነው ቀለሙ ከያሬድ በተጨማሪ..."ምድራዊ መልአክ" ነው ስሙ Moges Hunyalew
2623Loading...
+<< #ወይን_ለማይጠጣ_ሕይወቱ_ምንድን_ነው? >>+ "ምንትኑ ሕይወቱ ለዘኢይሰቲ ወይነ" (ሲራክ. 34:26) =>#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን ወይንን (ጠላ: ቢራ . . .) ¤"አትጠጡ" ብላ አትከለክልም:: ¤ግን ደግሞ "ጠጡ" ብላም አታበረታታም:: ¤አልኮል መጠጦችን መጠቀም "ኃጢአት ነው" አትልም:: ¤ግን ደግሞ " . . . ካያያዝ ይቀደዳል" እንዲሉ አጠቃቀማችን ወደ ኃጢአት ሊወስደን ስለሚችል "ጥንቃቄን አድርጉ" ትለናለች:: +በዘመናችን ከመጠጥ ጋር በተያያዘ (በተለይ ለክርስቲያኖች) 2 ፈተናዎች ይታያሉ:: 1.አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመን (በተለይ ወጣቱና ጐልማሳው) አነሰም በዛም ጠጪ እየሆነ ነው:: (ልብ በሉልን "ይሰክራል" አላልኩም) 2.እጅግ በሚያስቀይም መንገድ ለመጠጣት ጥቅሶች ከቅዱስ መጽሐፍ ሲጠቀሱ እየሰማን ነው:: +በተለይ "#ወይን_ያስተፌስሕ_ልበ_ሰብእ" (መዝ. 103:15) ከእኛው አልፎ በዘፈንና በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያዎች ላይ ሲጠቀስ ስንሰማ አንጀታችን ካላረረ የቁም ሙት ሆነናል ማለት ነው:: +አሕዛብ ከመጽሐፋቸው አንዲት ዘለላ ብትነካ ሃገሪቱን በተቃውሞ እንደሚንጧት እናውቃለን:: ¤እኛ ግን #የሊቀ_ሰማዕታት ስም የቢራ ማሻሻጫ ሲሆን: #ቅዱስ_ቃሉ ለአልኮል መጠጥ ሲጠቀስ: #በአባቶቻችን_ካህናትና_ጻድቃን ላይ በፌዘኞች (ኮሜዲያን ነን ባዮች) ሲቀለድ: ማንም ባለጌ በተቀደሰች ሃይማኖታችን ላይ አፉን ሲከፍት ምንም አይመስለንም:: (አንቀላፍተናላ!!!) =>ወደ ጉዳዬ ልመለስና የወይንን ነገር እንጨዋወት:: "የትውልዱ ክፋቱ ኃጢአት መሥራቱ አይደለም:: ይልቁኑ ኃጢአቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስመሰሉ እንጂ" ብለውኛል የኔታ ክንፈ ገብርኤል:: (በቀኝ ያቁማቸውና!!!) +ዛሬ በሃገሪቱ የሚገኘውን ጠጪ (ካልጠጣ የሚሞት የሚመስለው) በመቶኛ/በ% ቢሰላ አብዛኛው (ምናልባት እስከ 90 % ) ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ባይ ነው:: +ታዲያ ይህ ጥራዝ ነጣቂ ትውልድ ለምን ስትሉት "ዳዊት እንዲህ አለ: ሐዋርያው ቅ/ዻውሎስ እንዲህ አከለ . . ." ይላል:: << ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ስለ ወይን መጠጣት የሚናገሩ ቃላት ትርጉም እንደሚባለው ነው?? #ለመሆኑ_ቅዱስ_መጽሐፍ_ጠጪነትን_ያበረታታል?? አምላካችን እግዚአብሔርስ ወደዚህች ምድር ያመጣን ለዚሁ ግብር ነው?? (ሎቱ ስብሐት!!!) >> +ቅዱስ ቃሉን ለገዛ ፈቃድ መተርጐም ፍጹም ኃጢአት ነው:: (2ዼጥ. 1:20) ስለዚህም "ወይን" የሚሉ ቃላት ምንድን ናቸው? ወደሚለው እንመለስ:: +በመጀመሪያ ግን #ብርሃነ_ዓለም: #ዓዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ) #ቅዱስ_ዻውሎስ ለደቀ መዝሙሩ #ቅ/ጢሞቴዎስ ስለ ምን "ውሃ ብቻ አትጠጣ:: ጥቂት ወይን ጨምር" አለው ቢሉ:- 1.ወይን በዘመኑ ለሆድ በሽተኞች ፍቱን መድኃኒት ስለ ነበር ነው:: (ቃሉም የሚለው ስለ ሆድህ ህመም ነው(1ጢሞ. 5:23)) ቅዱሱ ከገድል የተነሳ ሆዱ ፍጹም ሕመምተኛ ነበርና:: 2.ወይን መጠጣት በልኩ (ጥቂት) የሆነ እንደሆን አካልን ያለመልማል:: ልቡናን ያረጋጋል:: ግን በጊዜው: በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ነው:: +#ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ ግን "ወይን" ተደጋግሞ የተጠቀሰባቸው በርካታ መንፈሳዊ ምስጢራት አሉ:: እነዚህን መነሻ ርዕስ ባደረግነው: በቃለ ሲራክ ተመርኩዘን እንመልከታቸው:: =>ነቢዩ "#ወይን_ለማይጠጣ_ምን_ሕይወት_አለው?" ይላል:: 1.ወይን=(#ምስጢረ_ሥላሴ) ¤"ምስጢረ ሥላሴን ላላመነ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ይለናል:: የእግዚአብሔርን አንድነት: ሦስትነት ሳያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወት የለምና:: (ዮሐ. 1:12, 3:17, ማቴ. 28:19) +ምስጢረ ሥላሴ በወይን መመሰሉን #አባ_ሕርያቆስ በቅዳሴው "አብ ጉንደ ወይን: ወልድ ጉንደ ወይን ወመንፈስ ቅዱስ ጉንደ ወይን . . ." ሲል ነግሮናል:: 2.ወይን=#ክርስቶስ (#ምሥጢረ ሥጋዌ) ¤በወልድ (ክርስቶስ) ያላመነ የዘለዓለም ሕይወት የለውም:: (ዮሐ. 3:36) ስለዚህ ነገር ጌታችን ራሱን የወይን ግንድ: አባቱን ተካይ አድርጐ ሲጠራ እንሰማዋለን:: "#አነ_ውእቱ_ጉንደ_ወይን=እኔ የወይን ግንድ ነኝ" እንዲል:: (ዮሐ. 15:1) +መዳን የሚቻለውም መድኅን ክርስቶስን "#አምላክ_ወልደ_አምላክ: #ወልደ_አብ_ወልደ_ማርያም: #ሥግው_ቃል" ብሎ ማመን ሲቻል ነው:: 3.ወይን=#ድንግል_ማርያም (#ነገረ_ማርያም) ¤ጌታን ወይን ካልን ድንግል ማርያምን #ሐረገ_ወይን: #አጸደ_ወይን ልንላት ግድ ይለናል:: (እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘመነ ጽጌ) +መዳንን የሚሻ ሁሉ እመቤታችን ማርያምን #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን: #ዘለዓለማዊ_ድንግልናዋን: ፍጹም ሞገስ ያላት #አማላጅ መሆኗን: #ቅድስናዋንና #ክብሯን ሊያምን ግድ ይለዋል:: (መዝ. 44:9, 86:5, ኢሳ. 1:9, 7:14, ሕዝ. 44:1) 4.ወይን=#ቅዱሳን (#ነገረ_ቅዱሳን) ¤መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን የወይን ግንድ ብሎ አልቀረም:: ወዳጆቹን #ወአንትሙሂ_አዕጹቂሁ=እናንተ የወይኑ ቅርንጫፎች ናችሁ" ይላቸዋል:: (ዮሐ. 15:5) +ስለዚህም በቅዱሳን #ክብር: #አማላጅነት: #ፈራጅነትና #የጸጋ_አማልክትነት ልናምን ግድ ይለናል:: (ዘጸ. 7:1, መዝ. 81:1, ማቴ19:28) 5.ወይን=#ሥጋ_ወደሙ (#ምስጢረ_ቁርባን) ¤#እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ቸር ልጇን የጠየቀችው ስለጊዜአዊው መጠጥ ቢመስልም ምስጢሩ ግን ለዘለዓለማዊው መጠጥ (ክቡር ደሙ) ነው:: (ዮሐ. 2:1) +ለዚያም "#ወይንኬ_አልቦሙ=ወይንኮ የላቸውም" ስትለው: "ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ=እናቴ ሆይ! በቀራንዮ አንባ ሥጋና ደሜን የምሰጥበት ጊዜየ ገና ነው" ሲል የመለሰላት:: +ወንጌል ደግሞ እንዲህ ይላል:: "የክርስቶስን ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም::" (ዮሐ. 6:53) ¤የወይን ትርጉም ይቀጥላል . . . ለእኛ ግን እዚህ ላይ ይብቃን:: +ቅዱሱ #ነቢይ_ሲራክ "ወይን ለማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ሲል በአንክሮ የጠየቀው ስለዚህ ነው:: ¤በወይን በተመሰሉ #በሥላሴ: #በምስጢረ_ሥጋዌ: #በነገረ_ማርያምና #ነገረ_ቅዱሳን ሳያምኑ: ከወይኑ ግንድ ክርስቶስ ጐን በፈሰሰ #ማየ_ገቦ ሳይጠመቁና #ከቁርባኑ ሳይሳተፉ ሕይወት የለምና:: =>ቸር አምላከ ቅዱሳን የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን:: << ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
Hammasini ko'rsatish...
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ††† ††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው : በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው:: ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር:: አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት : ገና በ3 ዓመቱ : እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ:: ††† ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:- 1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ:: 2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ:: 3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው:: ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን:: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው:: "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን : ዕጸበ ገዳምን : ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል:: ††† በዘመኑም:- 1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል:: 2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል:: 3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል:: 4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን:: ††† ሰኔ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ 2.ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው) 3."16,000" ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ) 4.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) ††† "ይሕንን እዘዝና አስተምር :: በቃልና በኑሮ : በፍቅርም : በእምነትም : በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው:: እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር : ለማስተማርም ተጠንቀቅ::" ††† (1ጢሞ. 4:11) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Hammasini ko'rsatish...
ዕርገት ‹ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡ በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪-፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡ በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡- ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡- ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡ በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩-፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ ‹አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው›፤›› በማለት ቅዱስ ወንጌልን መሠረት ባደረገ ኃይለ ቃል ጌታችን ወደ ሰማይ ስለ ማረጉና ለሐዋርያት አምላካዊ ትእዛዝ ስለ መስጠቱ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡ ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...
††† ✝እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አቡነ ተጠምቀ መድኅን ††† ††† ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው #ወልደ_ክርስቶስና #ወለተ_ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ #ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ #ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ:: ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት:- 1.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል 2.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል 3.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) 4."7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: ††† ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ #ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ #በጋሾላ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: ††† ቅድስት ማርታ ††† ††† እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች:: መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን (በበዓለ ልደት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት:: ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት:: ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ25 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች:: ††† የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: ††† ††† ሰኔ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ማርታ ተሐራሚት 2.አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 3.ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት 4.ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት †††ወርኀዊ በዓላት 1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን) 4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5.አቡነ ዜና ማርቆስ 6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል ††† "አልሞትም: በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ::" †††  (መዝ. 117:17-22) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Hammasini ko'rsatish...
††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ††† †††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:- ¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ ¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ ¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ ¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ ¤ጌታውን ያጠመቀና ¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:- ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች:: ††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ††† ††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:- ¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ ¤መናኔ ጥሪት የተባለ ¤በድንግልና ሕይወት የኖረ ¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት ¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ ¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል:: ቅዱስ ዮሐንስ ¤ቁመቱ ልከኛ ¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ ¤የራሱ ጸጉር በወገቡ ¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ ¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር:: ቅዱስ ኤልሳዕ ¤በጣም ረዥም ¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ) ¤ቀጠን ያለ ¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር:: በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት:: ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል:: በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል:: ††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን:: †††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ) 3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ †††ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ 4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ †††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" ††† (ማቴ. 11:7-15) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Hammasini ko'rsatish...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/