cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

የጥበብ አፍቃሪ ኖት እንግዲያውስ ትክክለኛውን ቻናል አግኝተዋል። በቻናላችን 👉 በኔና በሌሎች የተፃፉ 👉ግጥሞች🌸 🌹ወጎች 🌸 🌹ልቦለዶች 🌸 አዝናኝ አስተማሪ ታሪኮችና ሌሎች ፅሁፎችን ያገኛሉ... ━━━━━━━━ ✦ ለማንኛውም አስተያየት @itsmetsita Paid Promotion @Tsiyon_awit ይጠቀሙ። Join us @itsmetsiyearsemalj

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
7 901
Obunachilar
+124 soatlar
+297 kunlar
+14730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Hammasini ko'rsatish...
NEAR Wallet

Next-generation telegram wallet built over NEAR blockchain. Build in HOT mining

Hammasini ko'rsatish...
NEAR Wallet

Next-generation telegram wallet built over NEAR blockchain. Build in HOT mining

It's real you won't be disappointed by joining it
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
📣📣📣በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እኛን መከተልዎን አይርሱ የዋን ራይድ ቤተሰብ ይቀላቀሉ!!! የማኅበራዊ ትስስር ድኅረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ Facebook: https://www.facebook.com/rideinone Instagram: https://www.instagram.com/rideinone Telegram Group: http://t.me/rideinone9744 TikTok: https://www.tiktok.com/@rideinone መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ! 𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩: https://shorturl.at/bdyFO 𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩: https://shorturl.at/lJLZ6
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
Call 📞
መተግበርያችንን ያዉርዱ
Join Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
በነፃ ዱባይ ሄደው መዝናናት ይፈልጋሉ? 😎 ቀላል ነው! እስከ ሰኔ 21 የYangoን መተግበሪያ ከAppstroe ወይም Playstore አውርደው፣ የመጀመሪያ ጉዞዎን ያድርጉ። 🚗 አሸናፊው በዕጣ ይመረጣል፤ ውድድሩ እንደተጠናቀቀ አሸናፊውን እናሳውቃለን። መልካም ዕድል!
Hammasini ko'rsatish...
😁 4 2👍 1
Call 📞
መተግበርያዉን ያዉርዱ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
“ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ" ሮሜ12፥9 አስቸኳይ የአርዳታ ጥሪ ፎቶውን የምትመለከቱት ታዳጊ ሙልጌታ ብርሃኑ የ12 ክፍል ተማሪ ባጋጠመው የሰውነት ደም አሰማምረት (aplastic anmeia)ህመም ምክጓት ሀገር ውስጥ ህክምናውን ሲከታተል የቆየ ቢሆጓም ከህመሙ ሲያገግም ባለመቻሱ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የዶክተሮች ቦርድ በህጓድ ሀገር ህክምናውን አንዲከታተል ውስኗል ሆኖም ግን ለህክምና የተጠየቀው ብር ከ4.2 ማለዪጓ ብር በላይ ነው ይህጓጓም ገጓዘብ ለመክፈል ከአቅም በላይ ስለሆነ በፈጣሪ ስም የተቻላችሁጓ አጓድታደርጉ አጓጥይቃለን። 1000402392607 ዘካርያስ ብርሃኑ
Hammasini ko'rsatish...
3.13 MB
👍 15 3
https://t.me/hAmster_kombat_bot/start?startapp=kentId603572874 Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop! 💸 2k Coins as a first-time gift 🔥 25k Coins if you have Telegram Premium
Hammasini ko'rsatish...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

👎 1
Hammasini ko'rsatish...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

1
‹‹እኔ ላቋቁመው ያሰብኩት ፋውንዴሽንና ያንቺን ፋውንዴሽን አሰብሽው….?በጥምረት እኮ በጣም ሰፊ ስራ መስራት ይችላል፡፡የእኔ ፋውንዴሽን ጥሩ የሚባል የገናዘብ አቅም  አለው…አንቺና  እናትሽ  ደግሞ  ኦረዲ  የተጀመረ ስራ፤ ጥልቅ የሆነ መነሻ ምክንያትና አላማ ያለው ነው፡፡እና…›› ፊቷ በደስታ በራ‹‹እና ምን…?›› ‹‹አብረን ልንሰራ እንችላለና…..የሁለቱ ፋውንዴሽን መጣመር እግረመንገዱን የእኔ እና  የአንቺን  መጣመር  ያፈጥነው  ይሆናል…አሰላ  እስክትወስጂኝና  ከብልኋ እናትሽ ጋር እስክታስተዋውቂኝ ቸኮልኩ›› ‹‹በጣም ነው ደስ ያለኝ…››አለች ሳባ፡፡ ቀናውም ‹‹እኔም ደስ ብሎኛል..ደስ ስላለኝ ደግሞ ሞቀኝ እና ሰውነቴን ልለቃለቅ…››ብሎ ከጎኗ ተነሳና ወደሻወር ቤት ገባ፡፡ የሻወር ቤቱን በራፍ ሳይዘጋ ልብሱን አወለቀና  የሻወሩን ውሀ ከፍተ.. ሰውነቱን በውሀ ያስመታ ጀመር… ሳባ ድንገት ስሜቷ ገፋትና  ከተኛበት  አልጋ  ተነሳ  ስሊፐር  በማጥለቅ  ወደሻወር ቤት ተራመደች፡፡ቀናው ፊቱን በተቃራኒው አቅጣጫ አዙሮ ጀርባዋን ለበራፉ በመስጠት ተገትሮ ቆሟል… ከላይ ከቧንቧው እየተስፈነጠረ ከግንባሩ ላይ በመላተም ወደ ጠቅላላ ሰውነቱ እየተንቆረቆረ በሚወርደው ውሃ ሰውነቱን እያቀዘቀዘው ነው፡፡ሳባ በአንድ ሜትር ርቀት ቆማ እርቃን ሰውነቱን በፍዘት እና በተመስጦ እያስተዋለች ነው፡፡ ይህ ፊት ለፊቷ ያለው ወንድ ከምታውቃቸው ከአብዛኞቹ የኢትዮጵያ  ወንዶች  ይለይበታል፡፡  ብዙዎቹ  በተለይ  ደህና  ህይወት ላይ ያሉ በማሳጅ  ቤት  ህይወቷ  የምታውቃቸው  ወንዶች….  ከመቀመጫቸው ሰፋ፤ ከሆዳቸው ገፋ ያሉ ወጣ ገባ የሰውነት ቅርጽ  ያላቸው  ናቸው፡፡ሸንቃጣ መስለው የሚታዩ ወንዶች እንኳን ልብሳቸውን አውልቀው እርቃን ሲቆሙ የላላና የተንዘለዘለ ነገር አያጣቸውም፡፡ ቀናው ግን የሰውነቱ ቅርጽ የአትሌቶችን አይነት ነው፤ ቁመናው የተስተካለ ፤ጡንቻው የፈረጠመ፡፡ይህን ቅርጹን ደግሞ ከልብስ ውጭ እንዲህ እርቃኑን ሆኖ ለዛውም  እንዲህ  እንደሳባ  በፍቅር  አይን ከተመለከቱት የሚያደነዝዝ መሆኑ ብዙም አያስገርምም፡፡ ከተገተረችበት እንደመባን አለችና ተንቀሳቀሰች፡፡ከሳሙና  ማስቀመጫው ሳሙናውን  አነሳችና  ከኃላ  ተጠጋችው  …ሳሙና  የያዘ  እጇን  ጀርባው  ላይ አሳርፋ አካባቢውን ማዳረስ ጀመረች፡፡ቀናው በመመሰጥ ውስጥ ካለበት ስሜት ወጣና ፊቱን አዙሮ በትኩረት ተመለከታ…ገረመው፤ በዝምታ ለምታደርገው ነገር ተባባሪ ነበር፤የአምስት አመት ህጻን የልጇን ሰውነት እንደምታጥብ እንስፍስፍ እናት ከፀጉሩ አንስታ እስከ እግር ጥፍሮቹ ድረስ እሽት አድርጋ አጠበችው፡፡እሱ እንዳደረገችው ነው የሆነላት… ሰውነቱንም መንፈሱም በከፍተኛ ደረጃ ተነቃቃ ፡፡ ሳባ ከእዚህ ሁሉ ማጥና ደባቴ ወጥታ ይሄንን   የመሰለ ዕድል በማግኘቷ ተደሰተች፡፡ የምትወደውን ሰው እያንዳንዱን የሰውነት ክፍሉን መዳሰስ ስለቻለች እሱን ማገዝ..እሱን መንከባከብ ስለቻለች …ከእሱ ጋር  ፍቅር  የመስራን  ያህል ስሜት ሰጥቷታል፡፡ግን ከዚህ አልፋ መሄድ አልሞከረችም፤ለዛሬ ይሄ ይበቃታል ..ምክንያቱም ያንን ማድረግ እንደምትችል እርግጠኛ  አይደለችም..ለዛ  ገና  ቡዙ ቡዙ ማገገም አለባት፡፡ ነገ ተነገ ወዲያ  ደግሞ  ሌሎች  ከእሱ  ጋር  የሚያቆራኟትን  አጋጣሚዎች እየጠነከሩና እየፋፉ ሲሄዱ ምን አልባት ያኔ በቀላሉ ማድረግ ትችል ይሆናል፡፡መታጠቡን ጨርሶ ፎጣ አገልድሞ በግማሽ እርቃን አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ… ከጎኑ በተቀመጠችበት አትኩራ አየችው…፡፡ ‹‹ምነው ጮኸሽ አየሺኝ?›› ‹‹እኔ እንጃ… ማሳጅ ላድርግህ እንዴ?››ከአፏ አመለጣት፡፡ ‹‹እንዴ ተገኝቶ ነው…..በአንድ አፍ…›› ‹‹ምን ነካኝ..አሁን ማሳጅ ብዬ ስሜቴን ተቆጣጥሬ ማሳጅ አድርጌ ብቻ ተወዋለሁ?››ስትል በውስጧ አሰበችናኝ በራሷ ተበሳጨች፡፡ አንዴ ከአፏ ስለወጣ ከተቀመጠችበት ተነሳች…የተወሰኑ የማሳጅ መሳሪያዎችን ለማግኘት ለወራቶች በተለይ ፋሲል ከሞተ በኃላ ዞር ብላ አይታ የማታውቀውን የቁም ሳጥኑን የታችኛውን መሳቢያ ከፈተች….ፍዝዝና ቅዝዝ ብላ እዛው ቀረች፡፡ስትቆይበት ግራ ገባው‹‹ምነው ቆየሽ? ካልተመቸሽ ተይው….ሌላ ቀን እናደረርገዋለን፡፡›› ምንም ሳትናገር አንድ አነስተኛ ጥቁር የቆዳ ቦርሳ አነሳችና ወደእሱ መጣች…አልጋው ላይ አሰቀመጠቸና ከፈተችው፤ውስጡ ያለውን ብረታ ብረቶች ላስቲኮች፤ ሰንሰለቶች፤ ካቴናዎች….ዘረገፈች ግራ ገባው…‹‹.ሳቢ ምንድነው?›› ‹‹ማወቅ አለብህ ..ይሄ የበሽታዬ እንዱ ክፍል ነው..እኔ በኖርማል ወሲብ አይደለም የምረካው.. አንተ አሜሪካ ስለኖርክ በተወሰነ መንገድ ልትረዳኝ ትችላለህ… ወደኖርማል ግንኙነት ለመግባት ምን አልባት አመታት ሊወስድብኝ ይችላል…›› የዘረገፈችውን እቃዎች አንድ በአንድ ወደ ቦርሳው ከተተችና መልሳ ዚፕን በመዝገት‹‹..ከዛሬ ወዲህ እንዚህን ነገሮች ስለማያስፈልጉኝ ነገ የሆነ ቦታ ውሰድና ቅበራቸው ወይም ጣልልኝ፡፡››አለችው ይሄ ሰው ከዶክተሯ በተሻለ ሀኪሞ እየሆነ  እንደሆነ  ከገባት  ቆይቷል፡፡በእሱ መታከም ማለት ግን አእምሮውን ገልብጦ ለእሱ ማስፈተሸ ነው፡፡መላ ታሪክን መዘክዘክና ሀጥያትንም ሆነ የነፍስ መቆሸስን መናዘዝ ነው፡፡ያ ደግሞ በጣም ለሚያፈቅሩት ሰው ሲሆን በጣም ከባድ ነው፡፡ለሚወዱት ሰው የአካል እርቃንን ማሳየት የአእምሮን እርቃን ከማሳየት በጣም  ከባድ  ነው፡፡ይህንን  እውነት የደረሰበት ነው የሚያውቀው፡፡እሷ ግን ቀስ በቀስ ..እለት በእለት ሳትወድ በግዷ እያደረገችው ነው፡፡ ወደራሱ ጎተተና  ተጠመጠመባት…ጭምቅ  አድርጎ  አቀፋት…ግማሽ  እርቃን ሰውነቱ ላይ ተለጠፈች…ግንባሯና አይኖቾን ሳመና‹‹ሳቢ አይዞሽ …ጊዜ ሁሉንም ቁስሎቻችንን ይፈውሳል …ለጊዜ እድሉን ስጪው››አላት፡፡ እሷም እንባዋን ጀርባው ላይ እያንጠባጠበች…‹‹እኔ ተስፋዬን በጊዜ ላይ አይደለም የምጥለው…ቁስሌን ያክምልኝና ያድነኛል ብዬ ተስፋዬን የጣልኩት በአንተ ላይ ነው…በል አሁን ቃል እንደገባሁልህ ማሳጅ ላድርግህ፡፡›› ‹‹እሺ ከዛ በፊት ግን አለና ከእቅፉ አወጣትና ትኩር ብሎ  አያት…  አይኖቾ ተርገበገቡ.. ወደእሷ ከንፈሩን አሞጥሙጦ ተጠጋት..ከፋታ ጠበቀችው.. ጎረሳት….ከእግር ጥፍሯ አንስቶ ወደላይ የሚነጉድ ንዝረት በሰውነቷ ተቀጣጠለ፡፡ ተፈፀመ ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇 @itsmetsiyearsemalj @itsmetsiyearsemalj @itsmetsiyearsemalj @itsmetsiyearsemalj ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
Hammasini ko'rsatish...
👍 66 20😁 7👎 4
ቤርሙዳ ዘ-ካሳንቺስ ምዕራፍ-37 ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ለ15 ቀን ያህል በሶስት ቀን አንዴ እየተመላለሰች ህክምናዋን መከታተልና የታዘዘላትን መድሀኒት በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ከጀመረች በኃላ... ቀናውና ሳባ እሷ መኝታ ቤት አንድ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተው እያወሩ ነው። ‹‹እንግዲህ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነሽ ...ቀጣይ  እቅድሽ ምንድነው?›› "ቀጣይ እቅዴ አንተን ማግባት"አለችው ፍርጥ ብላ "እውነቴን እኮ ነው" ""ወደአሰላ እመለሳለሁ...እዛ የእንጀራ እናቴ የጀመረችልኝ በጣም እስፔሻል የሆነ ስራ አለ …እሱን በሰፊው መስራት ነው የምፈልገው።›› "ምንድነው ስራው?" "ልነግርህ አልችልም...የዛሬ ሳምንት አብረን እንሄዳለን ..የምወዳት እናቴን አስተዋውቅሀለው..ትንሹ      ወንድሜም      እርግጠኛ      ነኝ      ይወድሀል... እናም የምወዳትን እትብቴ የተቀበረባትን ከተማዬን አስጎበኝሀለው...ከዛም የምሰራውን ስራ አሳይሀለው።›› "በጣም ደስ ይለኝ ነበር...ግን እኮ የዛሬ ሳምንት የምበርበት ቀን ነው፡፡" "ምን?"ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቁጭ አለች። ጭራሽ ትዝ ብሏት አስባበት የማታውቀው ነገር ነው፡፡ ቅዝዝ እና ክፍት ብሏት፡፡"የእውነት ጥለኸኝ ልትሄድ ነው...?."ስትል ጠየቀችው፡፡ ‹‹ምን ማድረግ እችላለሁ...?እሺ ብትይኝማ ወደአሜሪካ ብወስድሽ ደስ ይለኛል  " ‹‹እንደዛማ ማድረግ አልችልም...ለስንድ ቃል ገብቼላታለሁ....አባቴን የሚያስደስት ስራ መስራት ነው የምፈልገው፡፡ሀገሬን ለቆ የመሄድ እቅድ የለኝም" "ይገባኛል....ግን የእኛ ነገርስ?" "እኳ አትሂድ ምልህ እኮ ለእኛ ብዬ ነው።...አሜሪካ ምን አለህ ?ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ። እዚህ ለዛውም አሰላ ለመኖር ያንተ ብር አያስፈልገንም።እኔ ሁሉንም ነገር አስተካክላዎለው።ይሄንን ቤት እንሸጥና ጥሩ  ብር  እናገኛለን፡፡  ከዛ   አሪፍ የሆነ ገቢ ሚያስገባ ድርጅት እናቋቁማለን..፡፡›› "መሄድ እኳ የምፈልገው ለገንዘብ አይደለም...የካትሪንና የሱዛና ስም ከስሞ እንዲጠፋ ስለማልፈልግ ነው።በካምፓኒው አመታዊ ትርፍ የሚንቀሳቀስ ካትሪን ኤንድ ሱዛና ፋውንዴሽን የሚባል የእርዳታ ድርጅት ለማቋቋም አስቤ ነበር። "የሚገርምና ደስ የሚል ሀሳብ ነው።.....ግን ፍውንዴሽኑ ምን ላይ ነው የሚሰራው..?ሀሳብህ እንዴት ነው?።›› "እሱን  ገና  አልወሰንኩም...ይሄን  አይነት  ሀሳብ   እራሱ   ወደ   አእምሮዬ የመጣው እኮ አሁን በቅርብ እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ነው።" "አትለኝም...እየቀለድክ መሆን አለበት?" "የእውነቴን ነው፡፡ ወደ ኢትዬጰያ ስመጣ የምኖርበት   የህይወት   አላማ   የሚኖር ከሆነ በስክነትና በመረጋጋት ውስጥ ሆኜ ለመፈለግ ነበረ...እና የዛሬ ወር አካባቢ እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ሳውጠነጥን ነው ሀሳብ የመጣልኝ። ስለዚህ ዝርዝሩን ገና አሜሪካ ከሄድኩ በኃላ ነው የተወሰኑ ጥናቶችን በማድረግ የምወስነው።" ‹‹እሺ ገባኝ ..ግን ለእኔ ስትል አንድ ነገር አድርግ...›› ‹‹ጠይቂኝ". ‹‹ ..ወደአሜሪካ የመሄድ ቀንህን በአንድ ወር አራዝመው..." የተወሰነ እንደማሰብ አለና‹‹ጥሩ እሺ አራዝመዋለሁ...እና ለአንድ ወር እንዴት አድርገሽ ልትንከባከቢኝ ነው ያሰብሽው?›› ‹‹እርግጠኛ ሁን …አሪፍ የሚባል ጊዜ እንድታሳልፍ አደርጋለሁ…›› ‹‹እኮ እንዴት እንዴት አድርገሽ..?›› ‹‹በመጀመሪያ አሰላ ወስድሀለሁ...ከምወዳት እንጀራ እናቴና ከወንድሜ ጋር አስተዋውቅሀለው...ቀጥሎ ደሴ እንሄዳለን?" የደሴን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ "ምን  ..?ደሴ? ምን ለመስራት?" "ቤተሠቦችህን ሳታይ በምንም አይነት  መንገድ  መሄድ  የለብህም..እነሱ  በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የቀሩህ የቅርብህ  የሆኑ  ሰዎች  ናቸው።እንዳልከው  እነሱን ማግኘት የማትፈልገው የሚጠይቁህን ጥያቄ መመለስ ፈርተህ  ብቻ አይመስለኝም?" በገረሜታ አፍጥጦ እያያት ‹‹›.እና ለምን ይመስልሻል?" "ዳግመኛ የእኔ የምትላቸውን ሰዎች ስትነጠቅ ላለማየት ከለህ ፍራቻ ነው። ጨለማውን እየሸሸህ ነው።በጭለማው ሰንጥቀህ ካላለፍክ ደግሞ ብርሀን የሚባል ነገር አታይም…" "ዋው...የስነ-ልቦና ባለሞያዎችን ታስንቂ የለ እንዴ?" "አዎ... በበሽታዬ የተነሳ ከእነሡ ጋር አመታትን አሳለፍኩ እኮ ..አሁን  አሁን እንደእነሡ ማሰብ ጀምሬለሁ።" ‹‹..እሱን በደንብ እያየሁ ነው…ግን ነገሩ እንዳልሽው ቀላል አይደለም.." ‹‹ይሄውልህ ቀናው እኔ ካንተ አላውቅም… አንድ ጓደኛዬ ‹ሁሉም ድርጊቶች የአምላክን ፍቃድ ያገኙ  ናቸው::››የሚል እምነት ነበረወ…  ይሄ  ጓደኛዬ  ሀይማኖተኛ አይደለም…ማለቴ ማንኛውንም ሀይማኖት አይከተልም….ግን በእግዚያብሄር ያምናል..መንፈሳዊ ሰው እንደሆነም ይናገራል፡፡እና እሱ እኛ የሰው ልጆች የእግዚያብሄር ህልውና አንድ  ቅንጣት  ሴሎች  ነን፡፡ከመወለዳችን  በፊት  የእግሩ ሴል ከሆንን ከተወለድን በኃላ ምን አልባት የእጆቹ ሴል ሆነን ሊሆን  ይችላል.. ከሞትን በኃላ ደግሞ የጭንቅላቱ ወይም የፀጉሩ አንድ ቅንጣት ሴል ነው የምንሆነው…ስለዚህ ለእግዚያብሄር ከመወለዳችን በፊትም በተወለድን ጊዜም ሆነ ከሞታችን በኃላም ተመሳሳይ ዋጋ  ነው  ያለን…  ቦታችን  እንቅስቃሴ  ላይ መሆናቸን ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚቀየር ነገር የለም…›› ‹‹ይመስለኛል ጓደኛሽ ለማለት የፈለገው…ሞት   በእግዚያብሄር   ዘንድ   ያለው ትርጉም እኛ እንደምናስበው አይደለም ለማለት መሰለኝ›› ‹‹በትክክል….በቃ አሁን እንተኛ" ‹‹እሺ… ከመተኛታችን በፊት ግን አንድ ጥያቄ መልሺልኝ?›› "ምንድነው?" "እናትሽ..ማለቴ እንጀራ እናትሽ ላንቺ ብላ የጀመረችውን ስራ ምንድነው?እስቲ ንገሪኝ" "ምነው ሄደህ እስክታየው መጠበቅ አቃተህ..?እኔስ እንደሰርፕራይዝ እንዲታይልኝ ፈልጌ ነበር...ያው ከዚህ በፊት ታሪኬን ስተርክልህ ስለአባቴ አደጋ ነግሬህ ነበረ.. በመኪና አደጋ ሁለቱም እጀግሮቹን አጥቶ በዊልቸር ለአመታት ሲገፍ ኖሮ እንደሞተ...እና ድንቋ እናቴ ስንድ በተለያየ ምክንያት  አደጋ  ደርሷባቸው  አካል ጉዳት ላይ የወደቁ ግን ደግሞ ለመታከምና ለማገገም የፋይናንስ አቅም የሌላቸውን ጉዳተኞች እቤት በመከራየት ተንከባካቢ ቀጥራ ሀኪም ቤት እያመላለሰች ትንከባከባቸዋለች ፡፡ሙሉ በሙሉ ድነው ህክምና የማይፈልጉበት  ደረጃ  ላይ ሲደርሱ የተሻለ ነገር ካገኙ መርቀዋትና  ተሰናብተዋት  ይሄዳሉ። እርግጥ  ካላት አቅም አንፃር ለጊዜው አስር  የሚሆኑ  ሰዎችን  ነው  የያዘችው..እኔ  አቅሜን አጠናክሬ ስሄድ እስከመቶ ሰው መቀበልና መንከባከብ ምችል ይመስለኛል..በሂደት ደግሞ ፈንድ በማፈላለግ…እያስፋፋሁት ሄዳለሁ…..ያን በማድረጌ ምን አልባት ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የሰራዋቸውን ቆሻሻ ስራዎች  እግዚያብሄር  ይቅር ይለኝ ይሆናል፡፡በዛ ላይ ደግሞ ከአባቴ የሙት መንፈስ ጋር ያለኝን ቀረቤታ አጠብቅበታለሁ…እያንዳንዱን አካል ጉዳተኛ ስንከባከብ አባቴን እንደተንከባከቡኩ ነው ሚሰማኝ..እሱም ባለበት ሰማይ ቤት ሆኖ ይደሰትብኝ ይሆናል፡፡›› ‹‹የሚገርም ነው..ምን አልባት እኔና አንቺ  መገናኘታችን  እንዲሁ  በዘፈቀደ  የሆነ ነገር አይመስለኝም…የሆነ ታላቅ ህይወት ምስጢራዊ ተልዕኮ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡›› ‹‹አልገባኝም››
Hammasini ko'rsatish...
👍 24 4
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.