cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ትኩረት ለሀገራችን ኢትዮጵያ Tekuret lhagerachin Ethiopia

ይህ ቻናል ኢትዮጵያዊነትን የሚያለመልም እና ስለኢትዮጵያ አንድነት የሚተርክ ነዉ! @tebibussolomon ሀገሬ ኢትዮጵያ ሁሉ ነገር የነበራት፣ ሁሉ ነገር ያላት፣ ሁሉ ነገር የሚኖራት ሀገር ናትና ሁላችንም በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ታሪካዊ ሥራ እየሰራን ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ እድገት እንምራት፡፡

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
176
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🔔🔔ዜና ቤተክርስቲያን🔔🔔 ወቅታዊ መረጃ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ቅዱሳን ማርያም ገዳም
Hammasini ko'rsatish...
video_2021-05-25_09-33-36.mp418.69 MB
እስራኤል ወታደራዊ አመራሮችን መግደሏን ተከትሎ የሀማስ ታጣቂዎች በርካታ ሮኬቶችን ተኮሱ‼️ ከሰሞኑ በእስራኤልና ፍልስጥኤም መካከል ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ ትላንት እስራኤል በከፈተችው የአየር ድብደባ የሃማስ ወታዳራዊ አዛዦችን ገድላለች። በጋዛ የሚገኝ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻን ወደ ፍርስራሽነት ቀይራለች። ለዚህም የአጸፋ እርምጃ ሀማስ በርካታ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወንጭፏል። ቀጣናው የገባበት ቀውስ ወደለየለት ጦርነት እንዳይሸጋገር የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ስጋቱን ገልጾል። ይህ ግጭት በእስራኤል ውስጥ በአይሁዶችና በእስራኤል አረቦች መካከልም የጎዳና ላይ ሁከት እንዲፈጠር ሰበብ ሆኗል። ፖለቲካዊ አመራሮች ውጥረቱን እንዲያረግቡ ተማጽኖ አቅርበዋል። በእስራኤልና ፍልስጥኤም የተነሳው ግጭት ከፍ ወዳለ ጦርነት እንዳያመራ ተፈርቷል። በዚህ ግጭት ምክንያት በጋዛ በትንሹ 67 በእስራኤል ደግሞ 7 ሰዎች ተገድለዋል። ካሳምንታት ውእረት በኃላ ባለፈው ሰኞ በምስራቃዊ እየሩሳሌም ለሙሰሊሞችም ይሁን ለአይሁዶች ቅድስት ተብላ በምትቆጠር ስፍራ መነሻነት ወደ ግጭት ያመራው። ግጭቱ በተጀመረ በሁለተኛ ቀን ደግሞ ክልስ አይሁዶችና አረቦች ተቀላቅለው በሚኖሩበት የእስራኤል አካባቢ በተፈጠረ ሁከት ምክንያት 36 የፖሊስ መኮንኖች መጎዳታቸውን የእስራኤል ፖሊስ ገልጾል ይህንንም ተከትሎ 374 ሰዎች ታስረዋል። ትላንትና ዕረቡ በጋዛ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎች ደግሞ 130 ሚሳኤሎችን መተኮሳቸውን ገልጸዋል። ይህም በጋዛ የሚገኘው አል ሻሩቅ ህንጻ በእስራኤል ለደረሰበት ጥቃት አጸፋ መሆኑንም ተናግረዋል። በእስራኤል የአየር ድብደባ ከጥቅም ውጪ የሆነው አል ሻራርቁ በጋዛ 3ተኛው ረጅም ህንጻ ነበር።
Hammasini ko'rsatish...
እስራኤል ወታደራዊ አመራሮችን መግደሏን ተከትሎ የሀማስ ታጣቂዎች በርካታ ሮኬቶችን ተኮሱ‼️ ከሰሞኑ በእስራኤልና ፍልስጥኤም መካከል ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ ትላንት እስራኤል በከፈተችው የአየር ድብደባ የሃማስ ወታዳራዊ አዛዦችን ገድላለች። በጋዛ የሚገኝ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻን ወደ ፍርስራሽነት ቀይራለች። ለዚህም የአጸፋ እርምጃ ሀማስ በርካታ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወንጭፏል። ቀጣናው የገባበት ቀውስ ወደለየለት ጦርነት እንዳይሸጋገር የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ስጋቱን ገልጾል። ይህ ግጭት በእስራኤል ውስጥ በአይሁዶችና በእስራኤል አረቦች መካከልም የጎዳና ላይ ሁከት እንዲፈጠር ሰበብ ሆኗል። ፖለቲካዊ አመራሮች ውጥረቱን እንዲያረግቡ ተማጽኖ አቅርበዋል። በእስራኤልና ፍልስጥኤም የተነሳው ግጭት ከፍ ወዳለ ጦርነት እንዳያመራ ተፈርቷል። በዚህ ግጭት ምክንያት በጋዛ በትንሹ 67 በእስራኤል ደግሞ 7 ሰዎች ተገድለዋል። ካሳምንታት ውእረት በኃላ ባለፈው ሰኞ በምስራቃዊ እየሩሳሌም ለሙሰሊሞችም ይሁን ለአይሁዶች ቅድስት ተብላ በምትቆጠር ስፍራ መነሻነት ወደ ግጭት ያመራው። ግጭቱ በተጀመረ በሁለተኛ ቀን ደግሞ ክልስ አይሁዶችና አረቦች ተቀላቅለው በሚኖሩበት የእስራኤል አካባቢ በተፈጠረ ሁከት ምክንያት 36 የፖሊስ መኮንኖች መጎዳታቸውን የእስራኤል ፖሊስ ገልጾል ይህንንም ተከትሎ 374 ሰዎች ታስረዋል። ትላንትና ዕረቡ በጋዛ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎች ደግሞ 130 ሚሳኤሎችን መተኮሳቸውን ገልጸዋል። ይህም በጋዛ የሚገኘው አል ሻሩቅ ህንጻ በእስራኤል ለደረሰበት ጥቃት አጸፋ መሆኑንም ተናግረዋል። በእስራኤል የአየር ድብደባ ከጥቅም ውጪ የሆነው አል ሻራርቁ በጋዛ 3ተኛው ረጅም ህንጻ ነበር። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Hammasini ko'rsatish...
#ጾመ_ድጓ፡-ሁለተኛዉ የዜማ መጽሐፍ ሲሆን የሚጠናና ለመምህርነት የሚያበቃ ነዉ፡፡ድጓ ቁጥሩ ከአስተምህሮ ሲሆን በዐቢይ ጾም የሚደርስ ራሱን የቻለ መጽሐፍ ነዉ፡፡ #ዝማሬ፡-ሦስተኛዉ የዜማ መጽሐፍ ነዉ፡፡ ዝማሬ ምስጋና ማለት ነዉ፡፡ ዝማሬ በጸሎተ ቅዳሴ ከድርገት በኋላ በቅዳሴ ማብቂያ አካባቢ የሚዜም የሚዘመር የጸሎተ ቅዳሴዉን ዓላማ ተከትሎ የሚሔድ ማለት ነዉ፡፡ ☸️መጽሐፈ ዝማሬ በይዘቱ አምስት ነገሮች አሉት፡፡እነርሱም ኅብስት፣ ጽዋ፣ መንፈስ፣ አኮቴት እና ምስጢር ናቸዉ፡፡ ☸️መሥዋዕት፡አራተኛዉ የዜማ መጽሐፍ ነዉ፡፡መሥዋዕት የቃሉ ትርጓሜ ሁለት ዓይነት ነዉ፡፡ አንደኛዉ ምልልስ ማለት ነዉ፡፡በግራና በቀኝ እየተመላለሰ ወይም እየተቀባበለ የሚባል ስለሆነ ነዉ፡፡ የመሥዋዕት ሁለተኛዉ ትርጉሙ ደግሞ የነፍስ መመላለስ《መሸጋገሪያ》ማለት ነዉ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀትን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ዕርገቱን የሚያስረዳ ነዉ፡፡ የመሥዋዕት አገልግሎት ለሙታን ጸሎተ ፍትሐት ለማድረስ በበዓላትና በአጽዋማት ደግሞ ስብሐተ ነግሕ ለማድረስ ነዉ፡፡ ☸️ምዕራፍ፡-የቅዱስ ያሬድ አምስተኛዉና የመጨረሻዉ የዜማ መጽሐፍ ነዉ፡፡የምዕራፍ ቀጥተኛ ትርጉሙ ማረፊያ ወይም ማሳረፊያ ማለት ነዉ፡፡ምዕራፍ ከመዝሙረ ዳዊት የተዉጣጣ ድርሰት ሲሆን የዳዊት መዝሙራትን በመስመር《ምዕራፍ》እየከፋፈለ የዜማዉን አይነትና ማሳረፊያ ይገልጻል፡፡ ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር! አሜን::
Hammasini ko'rsatish...
⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️ የሰው ልጅ ሲኾን “ምድራዊ መልአክ” የተባለ - ከምድር ወደሰማይ ተነጥቆ የመላእክትን ቋንቋ የተማረ - በመላእክት ቋንቋ የዘመረ - ከእነርሱም የተማረውን ዜማ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ያበረከተ - የዜማ መጻሕፍትን ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን የሰጠ - ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን አስማምቶ የተረጎመ - የቅኔ ድርሰት ጀማሪ - ርዕሰ ሊቃውንት - የቤተክርስቲያን ብርሃን - የተዋህዶ አበባ ነው - ጻድቁ አባታችን - ቅዱስ ያሬድ! የቅዱስ_ያሬድ_ታሪክ_ባጭሩ ኢትየጵያዊዉ ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ/ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡እናቱ ታዉክሊያ/ክርስቲና/አባቱ ደግሞ ይስሐቅ/አብድዩ/ይባላሉ፡፡ አባቱ የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡ ያሬድ ሰባት ዓመት ሲሆነዉ አባቱ ስለሞቱበት እናቱ ት/ቤት ለማስገባት ወደ አጎቱ መምህር ጌዲዮን ጋር ወሰደችዉ፡፡ አባ ጌድዮንም በአክሱም ቤተ ቀጢን《ቤተ ጉባኤ》መምህር ነበሩ፡፡ ☢️ያሬድ ያኔ!ምን ነበር !? በትምህርቱ የሚያሳየዉ ዉጤት ደካማ ስለነበር ከሌሎች ህጻናት ጋር ሊወዳደር አልቻለም፡፡መምህሩ ጌዴዎን ለተግሣጽ ቢቀጡትም መታገስ ተስኖት ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ እናቱ መንደር መደባይ ወለል ተጓዘ፡፡ ህጻን ያሬድ ከዛፍ ስር ተቀምጦ በምን ምክንያት ገጓደኞቹ በታች እንደሆነ ሲያዝን ሲተክዝ ቆየ፡፡ ታደሰ አለማየሁ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ብርሀን ቅዱስ ያሬድ››በሚለዉ መጽሐፉ‹‹አንድ ትል የዛፉን ፍሬ ለመመገብ ፈልጎ ወደላይ እየወጣና እየወደቀ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በሰባተኛዉ ጊዜ ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከተ፡፡ ☸️ያሬድም የዚህ ትል ተስፋ አለመቁረጥ ትዕግስቱን ጽናቱን ተመልክቶ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 《እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ብዙ ጥረት ካደረኩ እንደዚህ ሊሳካልኝ ይችላል›ብሎ ወደ መምህሩ ለመመለስ ወሰነ ይላል》ያሬድ የ አጎቱ ምክርና ተግሣጽ ለሕይወቱ የሚጠቅም መሆኑን በመረዳቱ ትምህርቱን በትጋት ቢማርና ቢያጠና ያሰበዉ ደረጃ ለመድረስ እንደሚችል በመገንዘብ ወደ መምህሩ ጌዲዮን ጉባኤ ቤት ተመለሰ፡፡ ☢️ መምህሩም ምን አሉት!? እሳቸውም ተቀብለዉ አስተማሩት፡፡ አጭር ጊዜ አልገባ ያለዉ ትምህርት ተገልጾለት ትምህርቱን በሚገባ አጠናቀቀ፡፡ በኋላም የብሉይና የሐዲስ መምህር ሆኖ በመምህሩ በጌዲዮን ወንበር ተተካ፡፡ #የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_እና_ዓይነቶቹ ☢️የቅዱስ ያሬድ ዜማ!? በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጸለት ለመሆኑ መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ቅዱስ ያሬድ ዜማዉን ያዘጋጀዉ በሦስት ዓይነት ድምፅ ማለትም በግእዝ፣በዕዝል፣እና በዓራራይ ዜማ ነዉ፡፡ እነዚህ የዜማ አይነቶች የአንዱ ድምፅ ከሌላኛዉ ድምፅ ያልተደበላለቀ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸዉ፡፡ዜማዎቹንም በስምንት ምልክቶች ቀምሮታል፡፡ የምልክቶች አገልግሎትም በትምህርት ሂደት ጊዜ የጠቋሚነት ሚና በመጫወት ለዜማዉ መጠበቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ናቸዉ፡፡ ☢️ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀል!? ቅዱስ ያሬድ የተነሳዉ ዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ዘመን ነዉ፡፡ በዘጠኙ ቅዱሳን የተተረጎሙት ቅዱሳን መጻሕፍት በቅዱስ ያሬድ የድርሰት ስራ ዉስጥ ጉልህ ድርሻ ነበራቸዉ፡፡ ☸️ቅዱስ ያሬድ ከመጻሕፍቱ ያገኛቸዉን ምስጢራት ቃል በቃል እየጠቀሰ እንዲሁም ሐሳባቸዉን ጨምቆ በመዉሰድ በራሱ ቋንቋ እያራቀቀ ለድርሰቱ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሙራደ ቃል በተባለ ቦታ ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲያዜም ንጉሱ አፄ ገብረ መስቀል ከነሰራዊቶቻቸዉ ንግስቲቱ ከነደንገ ጡሮቿ ፣መሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ሊቃዉንቱና ካህናቱ አየመጡ ያዳምጡ ነበር ይላሉ ርእሰ ደብር ጥዑመ ልሳን ካሣ በመጽሐፋቸዉ፡፡ ☢️ ቅዱስ ያሬድ ድርሰት ማ ፤ ማ ናቸው!? በግእዝ፣በዕዝል በዓራራይ ዜማ ዝማሜ እየደረሰ እያለ ንጉሱ አፄ ገብረ መስቀል ተገኝተዉ ነበር፡፡በዜማዉ ተመስጠዉ አይን አይኑን እያዩ እንደ እርሱ እዘምማለሁ ብለዉ በያዙት የብረት ዘንግ ሳያዉቁት ቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ቸከሉት፡፡ ሁለቱም በተመስጦ ስለነበሩ የሆነዉን ነገር አላስተዋሉትም ነበር፡፡ ዜማዉ አብቅቶ ሁለቱም ከተመስጧቸዉ ሲነቁ የቅዱስ ያሬድ እግር ዘንጋቸዉ ተሰክቶ ብዙ ደም ፈሶት ነበር፡፡ንጉሡም ደንግጠዉ እጅግም አዝነዉ‹‹ደምህን አፍስሻለሁና የምትፈልገዉን ማንኛዉንም ነገር ጠይቀኝ እሰጠሃለሁ››ሲሉ ቃል ገቡለት፡፡ ቅዱስ ያሬድም‹‹ይምለምነዉ አንድ ነገር አለ እርሱን ፈጽምልኝ›› አላቸዉ፡፡ ‹‹የፈለከዉን ጠይቅ ፈቅጄልሃለሁ›› አሉት፡፡ እርሱም‹‹እስካሁን እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መሰረት በዚህ ከተማ ከእርሰዎ ጋር ቆይቻለሁ፡፡ብዙ ደቀ መዛሙርትም ተክቼያለሁ፡፡ከእንግዲህ በኋላ የቀረኝን ዘመን በጸሎትና በብሕትዉና መኖር እንድችል ከከተማዉ ራቅ ወዳለ ቦታ ሔጄ ፈጣሪየን ማገልገል እፈልጋለሁ››ብሎ የንጉሱን ፈቃድ ጠየቀ፡፡ ☸️አፄ ገብረ መስቀልም የቅዱስ ያሬድን ቃል ሰማተዉ በዚያኑም በገቡለት ቃል መሰረት ፈቀዱለት፡፡ከዚያም ጉዞዉን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ሰሜን ተራሮች አደረገ፡፡በዚያም አሁን በስሙ የታነጸዉ ቤተ ክርስቲያን ባለበት ቦታ ላይ በምናኔ ተወስኖ ፈጣሪዉን በብሕትዉና እያገለገለ ኖረ፡፡ምናኔ ደብረ ሐዊ ከተባለዉ ተራራ ላይ ብዙ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በጸለምት ዋሻ በአንዱ ግንቦት 11 ቀን በ571 ዓ/ም ተሰወረ፡፡ #የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች ቅዱስ ያሬድን ብቸኛ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መስራች አድርጎ ለማየት በቂ ምክንያት አለን፡፡ እንዲያዉም የግእዝ ስነ ጽሑፍ መስራች ከማለት ይልቅ የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራች ልንለዉ ይገባል፡፡ 《ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ኃይሌ የቅዱስ ያሬድ ታሪክና የግእዝ ስነ ጽሑፍ፤1999፤ገጽ3》ፕሮፌሰሩ በዚሁ ጥናታቸዉ እንዳብራሩት የግእዝ ስነ ጽሑፍን ለሁለት ልንከፍለዉ እንችላለን ይላሉ፡፡ ☸️ምክንያቱን ሲያብራሩ፡-አንዱ ክፍል ከባህር ማዶ ተጽፈዉ ወደ ግእዝ የተተረጎሙትን መጻሕፍት ይይዛል፡፡ ሁለተኛዉ ክፍል በቀጥታ በግእዝ የተደረሱትን ድርሰቶች ያጠቃልላል፡፡ ☸️ እነዚህም፡-የቅዱስ ያሬድ፣የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣የርቱዐ ሃይማኖት፣የ አፄ ዘርአ ያዕቆብ፣የ ዐርከ ሥሉስ፣የ አባ ባሕርይ ድርሰቶች የሚቀድም በ ግእዝ ቋንቋ የተደረሰ ድርሰት እስከ አሁን አለመገኝቱን ጥናቱ ያሳያል፡፡ 《1999፡3》 ☸️ ቅዱስ ያሬድ ድርሰቶችን ሲያዘጋጅ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ብሉያትን ከሐዲሳት፣ከሊቃዉንት እያጣቀሰ ያለምንም ችግር የድርሰት ሥራዉን ሊያከናዉን ችሏል፡፡ ☸️የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች መንፈሳዊ ይዘት ያላቸዉ ናቸዉ፡፡በድርሰቶቹ የሚታዩት የቃላት አመራረጥ፣የ ዐረፍተ ነገር አወቃቀር፣የሚስጥር፣የዘይቤ አገላለጥ ቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ የስነ-ጽሑፍ ተሰጥኦ እንደነበረዉ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ☸️ በቅዱስ ያሬድ የተደረሱት የዜማ መጻሕፍት አምስት ናቸዉ፡፡እነርሱም ድጓ፣ጾመ ድጓ፣ዝማሬ፣ምሥዋዕትና ምዕራፍ ናቸዉ፡፡ #ድጓ፡-የቅዱስ ያሬድ ትልቁ የዜማ መጻሕፍ ነዉ፡፡ #ድጓ:- ማለት ስብስብ ማለት ነዉ፡፡በዉስጡ የዓመቱን በዓላትና የሳምንታት መዝሙራት ሰብስቦ የያዘ ነዉ፡፡ይህ መጽሐፍ በዐበይት በዓላት በዜማ የሚቀርበዉን ምስጋና ሰብስቦ የያዘ የዜማ መድብል ነዉ፡፡ #ድጓ በአራት ትልልቅ ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ይኸዉም፡-የዮሐንስ ድጓ፣አስተምህሮ ድጓ፣ጾመ ድጓ፣የፋሲካ ድጓ ተብሎ ይታወቃል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
እንኳን ለቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። ግንቦት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን (አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል) 2.ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ (ሰማዕት) 3.አባ ሚካኤል ገዳማዊ 4.አባ ይስሐቅ ግብጻዊ ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ 4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል "ናቡከደነፆርም መልሶ:- መልአኩን የላከ : ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን : የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን : በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::" (ዳን. 3:28) ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Hammasini ko'rsatish...
… እውነት ነው ቤተ ክርስቲያን ስደት ላይ ናት። አሁን ይሄንን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቢቃወሙ፦ • ዶር ዘሪሁን ሙላት ይሰድባቸዋል። ታዬ ደንደአ ይዘረጥጣቸዋል፣ የኢዜማው ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ይቆጧቸዋል። ሱዩም ተሾመ ያዋርዳቸዋል። መናፍቁ፣ ተረኛው፣ አክራሪ ፕሮው ይደነፋባቸዋል። እኛም ዝም ብለን እናያለን። እንመለከታለንም። … በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ያሉ የተዋሕዶ ልጆች ሁለት ምርጫ ነው ያላቸው። በህይወት ለመኖር በግድ መስለም። አልያም መታረድ። ዘመኑ የዐቢይ አሕመድ፣ የጀዋር መሐመድ፣ የሙፈሪያት ካሚል፣ የደመቀ መኮንን ነው። አማራጭ የላቸውም። ማዕተባቸውን በጥሰው፣ መስቀላቸውን ቀምተው በግድ ያሰልሟቸዋል። ይሄ ሙስሊሙ በሚበዛበት ክልልል ነው። አዲስ አበባ ያለው በእነ አቡበከር "ኢስላም ፍቅር ነው" ስብከት ደንዝዞ ይጦዛል። የኔታ እሸቱ፣ ዳንኤል ክብረት፣ ዘሪሁን ሙላት፣ አፈቀላጤዎቻቸው ናቸው። ወለጋ ከሆንክ ደግሞ በአደባባይ ትረሸናል። የወለጋ ጴንጤ ዐማራ የሆነ ሙስሊምም ኦርቶዶክስም ማየት አይፈልግም። ይደፋሃል። … የምእመናኑን ፊት ተመልከቱ እስቲ። አቅም ያጣ ፊት፣ ተስፋ ያጣ ፊት፣ ከምር አንጀት ነው የሚበሉት። ከምናርዳችሁ ፣ በጅምላ ከምንፈጃችሁ ማዕተባችሁን በጥሱ። ፖሊሱም የእኛው ነው። ወታደሩም የእኛው ነው። መከላከያውም የእኛው ነው። ፍርድ ቤቱም የእኛው ነው። ዘመኑ የእኛው ነው። እናም ማዕተባችሁን በጥሱ። እምቢ ካላችሁ አንገታችሁን ነው የምንበጥሰው። … ጴንጤው ይሄን ሲያይ ይስቅብናል። አክራሪ እስላሙ ይፎክርብናል። እነ ኢሳት እሳት ለብሰው፣ እሳት ጎርሰው ያቀረሹብናል። እነሱ ተደራጅተው ሊያጠፉን ተማምለዋል። የእኛ ሚኒስትሮች ሆድ እንጂ ጭንቅላት አልባ ስለሆኑ ምንም አይገዳቸውም።
Hammasini ko'rsatish...
video_2021-05-13_12-37-14.mp41.85 MB
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳውያን ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት የተሰጠ የአቋም መግለጫ👇
Hammasini ko'rsatish...
እንኳን ለቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ። ❖ግንቦት 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1: ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ (የትእግስት አባት) 2: አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ምኔት (የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ-መዝሙርና የአቡነ አረጋዊ ጉዋደኛ) 3: "22" ሰማዕታት (የአባ ኤሲ ማሕበር) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 2፡ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 3፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 4፡ ቅዱስ አቤል ጻድቅ 5፡ አባ ጳውሊ ገዳማዊ 6፡ አባ ሕርያቆስ ዘብሕንሳ "ወንድሞች ሆይ! የመከራና የትዕግስት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ:: እነሆ በትዕግስት የጸኑትን ብጹዓን እንላቸዋለን:: ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታቹሃል:: ጌታም እንደፈጸመለት አይታቹሃል:: ጌታ እጅግ የሚምር: የሚራራም ነውና::" ያዕ. 5:10
Hammasini ko'rsatish...
እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.