ቲቪ ጥገና Tv maintenance , ቲቪ ቴክኒሻን ,Tv repair 🖥
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ ቻናል በመቀላቀሎ የሚያገኝዋቸው ጥቅሞች ፩የኤሌክትሮኒክስ እውቀቶን ያዳብራሉ። ፪ቲቪ ፣ ሳተላይት ሪሲቨር ፣ ሞባይል ፣ ኮምፕዩተር ፣ ፍሪጅ እና የልብስ ማሺን ወዘተ ባለሙያዎችን የትም መሄድ ሳያስፈልጎ እዚህ ያገኛሉ። @Yilymj @newgroupmaintenance ለቲቪ መለዋወጫ Website : ysak-electronics.netlify.app
Ko'proq ko'rsatish2 915
Obunachilar
-224 soatlar
-47 kunlar
-430 kunlar
Postlar arxiv
"የመጀመሪያው የኢትየዮጵያ ሳተላይት በያዝነው ዓመት በታህሳስ ወር በቻይና ከሚገኝ የማምጠቂያ ማዕከል ወደ ጠፈር የሚላክ ሲሆን ይህ ሳተላይት ለግብርና፣ ለደን ልማት እና ለአካባቢ ጥበቃ አገልግሎት የሚያስፈልጉትን የሳተላይት መረጃዎች ለመቀበል ይውላል፡፡
ቴክኖሎጂ ነክ ነገሮችን
ያው ያወቅነውን እናሳውቃለን
https://t.me/joinchat/AAAAAFEzzpz4Tn1x8Ns3ZA
በችግሮችህ ላይ ያለህ እይታ ምን ይመስላል?
“ጉዞው ሲበረታ፣ ብረቱዎች ጉዟቸውን ይቀጥላሉ”
በአሁን ሰዓት እኔና አንተ የምንጋራቸውን ነገሮች እንዘርዝር ብንል ብዙ ሁኔታዎችን እናገኛለን፡፡ ከእነዚህ ሁኔታዎች አንዱ “ችግር” የሚባለው ጉዳይ ነው፡፡ ሁላችንም ብንሆን በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ችግሮችን እንጋፈጣለን፡፡ ችግርን በመጋፈጥ ደረጃ አንድ ስንሆን፣ የምንለያየው በችግራችን ላይ ባለን አመለካከት ነው፡፡
ችግሮችህ ከአቅምህ ቢበልጡ ኖሮ ባለፉት ሁኔታዎችህ ተውጠህ በቀረህ ነበር፡፡ አንተ ማንኛውም ሰው ካሉበት ችግር አልፎ የመሄድ ብቃት እንዳለው ከሚያመላክቱ ዋነኛ ምልክቶች አንዱ ነህ፡፡ አንድናድ ጊዜ ግን ችግሮችህ ያየሉና ከአቅምህ በላይ እንደሆኑ ልታስብ ትችላለህ፡፡ ይህ የመሸነፍ ስሜት ከተለያዩ ተጽእኖዎች ሊመጣ ይችላል፡፡
ከሚከተሉት አጉል ተጽእኖዎች ነጻነትህን አውጅ፡-
1. የሌሎች ልምምድና ሁኔታ ተጽእኖ
አሁን በሕይወትህ የሚጋፋህ ችግሮች ከዚህ በፊት በሌሎች ሰዎች ላይ ያስከተሉትን አስከፊ ሁኔታዎች ስታስብ የፍርሃት ስሜት ሊያጠቃህ ይችላል፡፡ አንድ ችግር ሌላውን ሰው አሸነፈው ማለት ግን አንተን ያሸንፍሃል ማለት አይደለም፡፡
2. የግልህ ልምምድና ሁኔታ ተጽእኖ
አሁን የተጋፈጥከው ችግር ከዚህ በፊት ጎድቶህ ካለፈ አሁንም ያው ሁኔታ የሚደገም ስለሚመስልህ ፍርሃት ሊጫጫንህ ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ከመፍራት ይልቅ ሁኔታው ከዚህ በፊት ሳያሸንፍህ እዚህ መድረስህ ላይ ማተኮርን ምረጥ፡፡
3. የመሰረተ-ቢስ ፍርሃት ተጽእኖ
አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ራሱ ያስፈራናል፡፡ በውስጥህ የሚሰማህን ፍረሃት ምንጭ ለማወቅ ብትሞክር እንኳ ላታገኘው ትችላለህ፡፡ ይህ አይነቱ ፍርሃት እንዲያደክምህ ግን መፍቀድ የለብህም፡፡ መፍራትህን በመፍራት አትንበርከክ፡፡ አደጋው ያለው ፍርሃት ላይ ሳይሆን ለፍርሃት የምትሰጠው ምለሽ ላይ ነው፡፡
በቅንነት ሼር ያድርጉ 👇
