cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አምሳል ኢትዮጵያ

ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
184
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

እንደ መሰንቆ መዝሙር የሚመስጥ በደስታ ማዕድ ዙሪያ እንደሚሰማ ምስጋና ደስ የሚያሰኝ ዝክረ ስምሽ የአማረ ንባብ ቃልሽም የሚጥም የቅድስናና የንጽሕና ደም ግባትን የተመላሽ የእግዚአብሔር ወልድ እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ ሰማይ ስትኾኝ ልጅሽ ክርስቶስ ነው፡፡ አንቺ ገነት ስትኾኝ ልጅሽ ክርስቶስ ማረፊያ ነው ፡፡አንቺ መረከብ ስትኾኝ ልጅሽ ክርስቶስ ምርጥ ሀብት ነው፡፡ አባጊዮርጊስ እንዳመሰገነሽ እኔም ላመስግንሽ፡፡ እንኳን አደረሳቹሁ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
"በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር!" #Ethiopia | "ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው!" የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መግለጫ ሰጡ። ሐዋ. ፳፫፥፭ "በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር" የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻ በማድረግ መግለጫውን የጀመሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ላይ በጥራዝ ነጠቅነት የተሳሳተ መረጃ መስጠት ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ታዝናለች" ብለዋል። በሀገር ውስጥና በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አባትን በዚህ መንገድ መናገር ሉዓላዊ የሆነች የኢ/ኦ/ቤ/ክንን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን መድፈር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ትርፍ ማግኘት አይቻልም ሲሉ አብራርተዋል። ብፁዕነታቸው አክለውም ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን በውጪ ሀገር መትከል ከጀመረች ጀምሮ ጽላት በአሠራሯ መሠረት ትልካለች። የታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እና ልጆቿ በረሃብ እየተገረፉ የጠበቁትን ሁኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ታሸሻለች ብሎ ማሰብ ንስሐ ያስገባል። ይህ የቅዱስነታቸውን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ክብር መንካት ነው ብለዋል። መንግሥት ለምን ብሎ መጠየቅ እና መመርመሩ ተገቢ ነው። ነገር ግን ቅርጽና ቅርስ መለየት ያስፈልጋል። በቀጣይም በጉዳዮ ላይ ግልፅነት ለመፍጠር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በቀጣይ እንወያያለን በማለት በመግለጫቸው ጠቅሰዋል። *** "ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን በውጪ ሀገር መትከል ከጀመረች ጀምሮ ጽላት በአሰራሯ መሰረት ትልካለች። የታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እና ልጆቿ በረሃብ እየተገረፉ የጠበቁትን ሁኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ታሸሻለች ብሎ ማሰብ ንስሐ ያስገባል።"ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምንጭ:-ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
Hammasini ko'rsatish...
በሰማይ የሚኖሩ ሠራዊት አለቃ የሚሆን የቅዱስ ገብርኤል ተአምር በሐምሌ 19 ቀን የሚነገረው ፡ ሕፃኑን ቂርቆስ ና እናቱን ኢየሉጣን ያዳነበት የእግዚአብሄር ሀይል የተገለጠበት እለት ነው ፡፡ እኛንም ከመከራ ስጋ ከመከራ ነብይ ይሰውረን፡፡ እንኳን አደረሳቹሁ፡፡https://t.me/joinchat/UPjbOPzHSKoOM9Tz
Hammasini ko'rsatish...
አምሳል ኢትዮጵያ

ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ

* እውነተኛ ጓደኛ ጻድቅ ነው እውነተኛ ጓደኛ የልብ ንጽሕና እና የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲኖርህ የሚጥርልህና ለዘላለማዊነትህ የሚተጋልህ ሰው ነው ፡፡ ኃጢአትን በመፈጸም ውስጥ ከአንተ ጋር የሚያብረው ግን እውነተኛ ጓደኛ አይደለም ፤ እርሱ ከእግዚአብሔር በራቀ ሕይወት ውስጥ ያለ ወደጅ እንጂ ፡፡ ስለዚህ በጓደኛና በወዳጅ መካከል ልዩነት አለ፡፡ https://t.me/joinchat/UPjbOPzHSKoOM9Tz
Hammasini ko'rsatish...
አምሳል ኢትዮጵያ

ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ

"ከእግዚአብሔር ከሆንክ የመስቀል ምልክትን አሳየኝ " አፎሚያም ጥንተ ጠላታችን ዲቢሎስን እንደዚህ ብላው ጠየቀችው ከእግዚአብሔር ከሆንክ መሀተቡን ወይም የመስቀል ምልክቱን አሳየኝ ፡፡ ለምሳሌ አለችው ምድራዊ ንጉስ እንኳን የሚልከው መልዕክት በመሀተብ ወይም ንጉሱን ሊገልጥ በሚችል ምልክት ነው ብላ በመጠየቋ እውነተኛ የሆነውን የእግዚአብሔር መለአክን ለማወቅ ችላለች፡፡ እኛስ ምልክት እንጠይቅ ይሆን ወይስ የመጣውን ሁሉ መቀበል ነው ልማድ ያረግ ነው ፡፡ ዛሬ ላይ የመጣውን ሁሉ እንደመልካም በመቀበላችን ለተለያዩ ፈተናዎች እየተዳረግ ነው ፡፡ምልክት እንጠይቅ ክፋን እና ደጉን ለመለየት ፡፡ አፎሚያም ምልክት በመጠየቀ ከሞት ተረፈች ለኖህም ቀስተ ደመና ምልክት ተሰጠው ፡ለአብርሃምም ከአህዛብ የሚለይበትን የግዝረት ፣ ለሙሴም ባህረ ኤርትራን የሚከፍልበትን ፣ ረዓብም ቀይ ፈትል ምልክት በመስኮት በማረጓ ከጥፋት እራሷም ቤተሰቦቻንም አተረፈች ፡፡ ለእኛም ዘላለማዊ የሆነች ቅድስት ድንግል ማርያምን ተሰጠችን ፡፡ ምልክታችን አጥብቀን እንያዝ ከዘመኑ መቅሰፍት ለመዳን እንዲሁም የእኛ የሆነውን ለመለየት ፣ ከእግዚአብሔርም እርዳታ እንድናገኝ ፡አጥብቀን እውነተኛ ምልክቶቻችንን መሆናቸውን እንጠይቅ ፡፡ እውነተኛ ምልክቶቻችን ፡- ምልክታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ምልክቶቻችን ቅዱሳን መልአኮችን ምልክቶቻችን ቅዱሳን ነብያትን ምልክታችን ቅዱስ መስቀሉን ምልክቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያትን ምልክቶቻችን ቅዱሳን ሰማዕታትን ምልክቶቻችን ቅዱሳን ፃድቃንን ምልክቶቻችን ቅዱሳን ገዳማትን እንኳን ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል አደረሰን ተድላ ለገሰ 2014 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
ቅዱስ ሚካኤል የመላእክቶች ሀሉ የበላይ አለቃ ነው ፡፡ የይሁዳ መልእክት ም ፡ 1:ቁ 9:: ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ አንድም ዕፁብ ድንቅ መልአክ ኪዳኑ ወምክሩ ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርኀራኄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሥልጣኑን የሚገልጽበትና ኀይሉን የሚያሳይበት እንዲሁም ቸርነቱንና ይቅርታውን የሚያስተላልፍበት ይህ ቅዱስ ሚካኤል ነው ፡፡ቅዱስ ሚካኤል በጸሎቱና በአማላጅነቱ የሚተማመኑትን በጭንቀታቸውና በመከራቸው ሰዓት ሊረዳቸውና ሊያፅናናቸው ፈጥሮ ደራሽ ነው፡፡ እንኳን አደረሳቹሁ አደረሰን ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ቀዳም ስዑር የተሻረ ሰንበት ማለት ነው፡፡ የተሻረ የተባለውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ደቀ መዛሙርቱ ‹‹የጌታችንን ትንሣኤ ሳናይ እህል አንቀምስም›› ብለው በአክፍሎት ስለጾሙበት ነው፡፡ በዚህ ዕለት ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፤ አንቀጸ ገነት፣ ርስት ገነት ተከፈተልን፡፡ አባታችን አዳም ከፈጣሪ ታረቀልን በማለት በመስቀሉ ሰላምን አደልን እያልን የተድላና የደስታ ምልክት ወይም መግለጫ ቄጠማ ይዘን የምሥራች እንባባላለን፡፡ (ግብረ ሕማማት) በቀዳሚ ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል (ቃለ ዓውዲ) እየመቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ አገሀደ ትንሣኤሁ፤ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ፤ በትንሣኤውም ገለጠልን›› የሚለውን ያሬዳዊ ዜማን በመዘመር፣ ጌታችን በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመን ይሰጣሉ፡፡ ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቁ ምእመናን ብሥራት ይሆናሉ፡፡ ምእመናኑም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ (ጾመ ድጓ፤ ቀዳም ስዑር ዜማ)
Hammasini ko'rsatish...