cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የግጥም መድብል

"መፃፍ መፃፍ አለኝ ማቅለም ወረቀት 📃 ብዕሬን ማስቆጣት ቀይ ደም ማስተፋት" ✒️ ግጥም ለመላክ ከስምዎ ጋር Admin @AmNOTmine

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
1 175
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለ2015 አዲስ አመት በዓል በሰላም አደረሳቹ ፣ አዲሱ ዓመት ሰላም ፍቅርና አንድነት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣበት ዓመት ያድርግልን! @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
▪️| ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የተጣላ የሚታረቅበት ዘመድ ከወዳጁ አብሮ የሚበላበት ዘንድሮ በተለየ መልኩ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ የምናደርግበት ነው። በዓሉን ስናከብር ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ፤ ስለፈናቀሉ እና ስለጎዱ ዜጎቻችን ፀሎት በማድረግ ልናስባቸው ይገባል። መልካም በዓል @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
# የተራዘመ_ውልደት ጌታ ሆይ ከአባትህ ቤት ወተህ ፥ ለኛ ስትቀጣ ከሀጢአት ነፃነት ፥ ነፃ ስታወጣ እንደ ድሮ መስሎ ዳግም ለመወለድ ፥ ዘንድሮ ብትመጣ አይ አይ አይ እኚያ በትንፋሽ ፥ የሚያሞቁ ከብቶች ግማሾቹ ታርደው ፥ ግማሾቹ በጥይት ተገለው እስትንፋሳቸው ቆሟል ፥ ከሜዳ ላይ ወድቀው አይ አይ አይ ደሞ አህዮቹን ያሞቁኛል ብለህ ፥ ብታስብ አሁንም ብትፈልግ ብትፈልግ ፥ አይኖሩም ከግርግም ካ..ገ..ኘ..ሃ..ቸ..ው..ም ሲላላኩ ነው ሚውሉ ፥ በጦርነት ግድም አይ አይ አይ ሁሉ..ሁሉ..ሁሉ..ቀርቶ ወገብ ማሳረፊያ ምናል ፥ ቢፈለግ ተገኝቶ ሲታሰስ ሲታሰስ ደጋግሞ ሲታሰስ በእሳት ተበልቷል አለ የተባለበት ፥ ምጣዱ ጋር ሳደርስ ወዲያ ማዶ ከጋራው ላይ አንዲት ጎጆ ዘንበል ያለች እኔን ለመውለድ ከቶ ትበቃለች ብለህ ከቦታው ጋር ስደርስ ፥ ብታገኝም በረት እሱም ተይዞ ፥ ጥይት ሆኗል፥ የሚከማችበት እሱም ተይዞ ፥ ልጃገረድ አዛውንት ፥ ሆኗል የሚደፈርበት ለዛ ለዛ ለዛ ይኼን ሁሉ በደል ይኼን ሁሉ ስቃይ ይኼን ሁሉ ጭካኔ ገና ሳትወለድ ፥ ከባሰ ከዛኔ በቃ እንደውም እንደውም በድሮ ውልደት ፥ እኛ ስንፃናና ጊዜውን አራዝመኸ አንተ አትወለድ ፥ በዘንድሮ ገ'ና ይቅርብህ ይቅርብህ ።።።።።።።።።።።።።።።። ✍ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
አልሆን ያለህ ግዜ መጉላትና መግዘፍ ከትልቆች መሃል አንዱን መርጠህ ዝለፍ ~~~~ @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
ነገ ተፈታኝ ለሆናቹ ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆንላቹ እንመኛለን ። ይቅናቹ 👍 @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
ትዝብት ጀብድ እንደፈፀመ ለሚደሰኩረው፣ ወሬው ከግብሩ ጋር ለማይዛመደው፣ ቁልቁል ሽቅብ ሳያቅ "ታከተኝ" ለወጣው፣ ምክር ቢጤ ጥለህ እንዲሁ ዝለለው። የሚጠላን እንጂ የሚወድ'ን ወ'ዶ፣ አክባሪ አያገኝም ቀ'ሎ 'ሚኖር ከብዶ። ድሮስ! የራስ በሚያዋርቅ እንቶ ፈንቶ ዓለም፣ ነሆለል ሺህ እንጂ ከቶ አንድ አይደለም። ጭንቅላተ ወና የራስ ቅሉ ባዶ፣ መቼም "ላንተ" አይልም "ለኔ" ማለት ለምዶ።                             🖋ዳንኤል ምህረቱ
Hammasini ko'rsatish...
ወዲህም ካየሽ ፈሶ ደም ወዲያም ካየሽ ፈሶ ደም ሌላው ሌላው ቢቀር "እኔን"ንን ለማለት ፤ አፍሽ አይለጉም ።።።።።።።።።።።።።።።፡።።። ✍ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu
Hammasini ko'rsatish...
ሀገሩን በሙሉ ፤ ዳታ ጠፍቶ ሲደብረው፣ "የቴሌ ደንበኛ ነኝ" ያለ ስለ ቴሌ ጥቅል ፤ ጉርሻ ከሚያ'ቆለፓፕሰው፣ እኔ ግን ማደንቀው በችግሬ ጊዜ ቪፒኤን ፤ ሼር ያደረገልኝ ሰው፣😂 ።።።።።።።።።።።።።።።።። መነሻ ሀሳብ #በላይ_በቀለ_ወያ ✍ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
"በትንሳዔ ማግስት ፆም ስግደቱ ሲቆም ጸሎቱም ተረሳ እኛ መሞት ጀመርን አንተ ስትነሳ" ከfacebook መንደር @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
እርሱ ግን፦ "አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።" •••••••••••••••••••••••••••••••• ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! በዓለ ትንሳኤው የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን፡፡ @poetryzz
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.