cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ከፍልስፍናው መንደር።

ስለ ፍልስፍና ብቻ ይመቻቹ ሁሌም ይለቀቃል።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
241
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🌿ወጣትነት ማለት... ____
ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም! 
.
.
ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!
.
.
ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም... 
.
.
ወጣትነት ባህር ነው። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው።
.
.
ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው። ወጣትነት ብርሃን ነው። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው። ወጣትነት እሳት ነው። ወጣትነት ቤንዚል ነው። ወጣትነት ቅጠል ነው። ወጣትነት ጤዛ ነው። ወጣትነት ታክሲ ነው። ወጣትነት ምርጫ ነው። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ...።
.
. ምንጭ ፦ "ኤጭ...!" መጽሐፍ -- ከገጽ 170-172 የተቀነጨበ -- • ◉ Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🎖 @cekuaa🎖
Hammasini ko'rsatish...
"የማይጠቅመንን በምንሰማበት ሰአት የሚጠቅመንን እናድርግበት! ሶቅራጥስ አንድ ጓደኛ ነበረው አሉ፡፡ አንድ ቀን ይኼ ጓደኛው መጣና «ሶቅራጥስ እገሌ ስለሚባል አንድ ወዳጅህ የሰማሁትን ነገር ታውቃለህ?» አለው፡፡ ሶቅራጥስም ዝም ብሎ ተወው፡፡ ሰውዬው ግን በሰማው ነገር ሳይደነቅ አልቀረምና እየደጋገመ«በጣም የሚገርምኮ ነው፡፡ እንዲህ ይሆናል ብዬ የማልገምተው ነገር ነው» ይለው ነበር፡፡ በነገሩ የተሰላቸው ሶቅራጥስም «በጣም ጥሩ፡፡ የሰማኸውን ነገር ትነግረኛለህ፡፡ መጀመርያ ግን ሦስት ጥያቄዎችን መመለስ አለብህ፡፡ የምትነግረኝ ነገር የእነዚህን የሦስት ጥያቄዎች መልሶች የሚያሟላ ከሆነ ብቻ እሰማሃለሁ» አለው፡፡ ሰውዬውም በዚያው ሃሳብ ተስማማ፡፡ «የመጀመርያው ጥያቄዬ የእውነታ ጥያቄ ነው» አለው፡፡«ቀጥል» አለ ሰውዬው «ለመሆኑ አሁን ለእኔ የምትነግረኝ ነገር መቶ በመቶ እውነት መሆኑን ርግጠኛ ነህ?» አለው፡፡ ሰውዬው ጥቂት አሰበና «መቶ በመቶ እውነት መሆኑን አላረጋገጥኩም፡፡ ነገር ግን የሰማሁት ነገር» ብሎ ሊቀጥል ሲል ሶቅራጥስ አቋረጠውና «ስለዚህ ያነሣኸው ነገር እውነት ይሁን ውሸ ትእርግጠኛ አይደለህም ማለት ነው፡፡ መልካም አሁን ወደ ሁለተኛው ጥያቄ እንለፍ፡፡ ሁለተኛው ጥያቄ የመልካምነት ጥያቄ ነው፡፡ ለመሆኑ ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የተዘጋጀኸው ነገር መልካም ነገር ነው?» አለው፡፡ሰውዬውም «መልካምማ አይደለም፤ እንዲያውም በተቃራኒውነው» ሲል መለሰለት፡፡ ሶቅራጥስም «ስለ ወዳጄ የምትነግረኝ ነገር እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፣ ደግሞም መልካም ያልሆነ ነገር ነው፡፡ ይገርማል፡፡ አሁን ሦስተኛው ጥያቄ ይቀርሃል፡፡ ሦስተኛው ጥያቄ የጠቀሜታ ጥያቄ ነው፡፡ ለመሆኑ ስለ ወዳጄ የምትነግረኝ ነገር ለእኔ ምን የሚጠቅም ነገር አለው?» አለና ጠየቀው፡፡ ሰውዬውም «ላንተ የሚጠቅምህ ነገር የለውም፡፡ግን ብትሰማው መልካም ነው ብዬ ነው» አለው፡፡«በጣም ጥሩ» አለ ሶቅራጥስ፡፡ «አሁን ስለ ወዳጄ የምትነግረኝ ነገር እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፣ መልካም ያልሆነና ለእኔም ምንም የማይጠቅመኝ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ ታድያ ለምን ይህንን ነገር እሰማሃለሁ?» አለና መለሰለት፡ 🌾 ለመልካም ነው! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🌼@cekuaa🌼
Hammasini ko'rsatish...
ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል

🖇"የፍልስፍና ስራው ጥያቄ መፍጠር ነው ! ✨የፍልስፍና አስኳሉ ነፍሱ ህይወቱ "ለምን" ነው። "ለምን" ባይኖር ኖሮ ሶቅራጦስ የለ ፑሉቶ ✨የእምነት(ሀይማኖት) ስራ ደግሞ ጥያቄ እንዳይፈጠር ብቻ ሳይሆን ለጥያቄው መልስ መሆን ነው ስራው። "ሀይማኖት መርቀቂያ እንጂ መራቀቂያ አይደለም"👨🏼‍🎓 "እምነት መመራመሪያ ሳይሆን መመርመሪያ ነው!👨🏼‍🔬 💦ሀዲስ እሸቱ 🌾 ለመልካም ነው! 🌾 🌼@cekuaa🌼
Hammasini ko'rsatish...
🌿"ዓላማ መር ሕይወት"🌿 [ By Rick Warren ] ቀን-14፡ እግዚአብሔር የራቀ ሲመስል፡ "ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፤ እርሱንም ተስፋ አደርገዋለሁ።"ኢሳ. 8፥7 √ ምንም ይሰማህ ምን እግዚአብሔር እውን ነው። ነገሮች በመልካም ክንውን ላይ ባሉ ጊዜ ማለት እግዚአብሔር ምግብ፣ ጓደኞች፣ ቤተሰብ፣ ጤና እና ደስ የሚሉ ሁኔታዎችን ሲሰጥህ እርሱን ማምለክ ቀላል ነው። ነገር ግን ሁኔታዎች ሁልጊዜ ደስ የሚሉ አይደለም። እንዲህ ባለው ጊዜ እግዚአብሔርን የምታመልከው እንዴት ነው? አንድ ሚሊዮን ኪሎ ሜትር የራቀ ሲመስልህ ምን ታደርጋለህ? √ የአምልኮ ጥልቀት መለኪያዎች በህመም ጊዜ እግዚአብሔርን ማክበር፣ በመከራ ጊዜ ማመስገን፣ በፈተና ወቅት በእርሱ መታመን፣ በስቃይ ጊዜ ራስን ለእርሱ ማስረከብ እና የራቀ በሚመስልበት ጊዜ እርሱኑ መውደድ ናቸው። √ ወዳጅነት ብዙ ጊዜ በመለየትና በዝምታ ይፈተናል። ሰው በአካል በመራራቅ ወይም ለመነጋገር ባለመቻል ይለያያል። ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖርህ ወዳጅነት አብዛኛውን ጊዜ ወደ እርሱ የቀረብህ መስሎ አይሰማህም። <<በማንኛውም ግንኙነት የመቀራረብና የመራራቅ ጊዜ አለ፤ ከእግዚአብሔር ጋር በሚደረግ ግንኙነትም የቱንም ያህል ቁርኝት ቢኖር መቀራረብና መራራቁ ይፈራረቃል።>> ፊሊፕ ያንሲ(ታዋቂ የሥነ-መለኮት ፀሐፊ) ብለዋል። አምልኮ አስቸጋሪ የሚሆነው እንዲህ ባለ ጊዜ ነው። √ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማሳደግ ሲል የተወህና የረሳህ በሚመስል ሁኔታና ጊዜ አማካይነት ወዳጅነታችሁን ይፈትነዋል። አንድ ሚሊዮን ኪሎ ሜትር የራቀህ ይመስልሃል። ጆን ኦፍ ዘ ክሮስ የተባለው ሰው መንፈሳዊ ድርቀት፣ የጥርጣሬ እና የመራራቅ ስሜት የሚፈጠርባቸውን እነዚህን ቀናት "ጨለማዎቹ የነፍስ ሌሊቶች" ብሏቸዋል። ሄነሪ ኖውን የተባለ ሰው ደግሞ "ያለመገኘት አገልግሎት"፤ ኤ. ደብልዩ. ቶዘር የተባሉት፦"የሌሊት አገልግሎት" ሌሎች ደግሞ "የልብ ክረምት" ብለውታል። √ እግዚአብሔር "እንደ ልቤ የሆነ ሰው"(1ሳሙ. 13፥14፤ ሐዋ. 13፥22) ያለውና የእግዚአብሔር የቅርብ ወዳጅ የሆነ ዳዊት እግዚአብሔር ጎኑ ያልተገኘ በሚመስለው ጊዜ ሁሉ እንዲህ በማለት በተደጋጋሚ ቅሬታውን ገልጧል፦ "እግዚአብሔር ሆይ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ?"መዝ. 10፥1፤ "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ? እኔን ለማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ።"መዝ. 22፥1፤ "ለምን ተውከኝ?" መዝ. 43፥2 እግዚአብሔር ዳዊትን አልተወውም፤ አንተንም አይተውህም። እግዚአብሔር እንዲህ በማለት በተደጋጋሚ ተስፋ ሰጥቶሃል፦ "አልለህም አልተውህም" ዘዳ. 31፥8። በተጨማሪም መዝ. 36፥28፤ ዮሐ. 14፥16-18፤ ዕብ. 13፥5። ነገር ግን፦ "ሁልጊዜ ህልውናዬ ይሰማሃል" በማለት እግዚአብሔር ቃል አልገባም። እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ፊቱን ከእኛ የሚሰውር መሆኑን ያምናል(ኢሳ. 45፥15)። በሕይወትህ የሚያከናውነውን ሥራ አቋርጦ በድንገት የሚጠፋ የሚመስልባቸው ጊዜዎች አሉ። √ ፍሎይድ ማክለንግ የተባለ ሰው እንዲህ ያለውን ጊዜ ሲገልጠው፦ <<አንድ ቀን ማለዳ ከእንቅልፍህ በምትነቃበት ጊዜ መንፈሳዊ ስሜቶችህ ሁሉ ትተውህ እንደጠፉ ትረዳለህ። ትፀልያለህ፣ ምንም አይሆንም። ዲያብሎስን ትገስፃለህ፣ ድርጊትህ የሚያመጣው ለውጥ የለም። ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ነገሮችን ታከናውናለህ...ትዝ የሚሉህን ኃጢአቶች ሁሉ ትናዘዛለህ፤ የምታውቃቸውን ሰዎች ሁሉ እየዞርክ ይቅርታ ትጠይቃቸዋለህ። ትፆማለህ፣ አሁንም ምንም የሚሆን ነገር አይኖርም። ይህ መንፈሳዊ ጭጋግ እስከ መቼ ነው የሚቆየው? የሚለው ነገር ያሳስብሃል። ለቀናት? ለሳምንት? ለወራት?...ያልፍ ይሆን? ጸሎትህ ከጣራ ጋር እየተላተመ የሚመለስ መስሎ ይሰማሃል። ምን ነካኝ? እያልክ በተስፋ መቁረጥ ታለቅሳለህ።>> √ እውነቱን ለመናገር አንተ ምንም አላጠፋህም!!! ይህ ሁኔታ የተለመደና ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ወዳጅነት መፈተሻና ማሳደጊያ ሂደት ነው። ማንኛውም ክርስቲያን ቢያንስ አንዴ፣ አብዛኛውን ጊዜ ግን በተደጋጋሚ እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ያልፋል። ሁኔታው አስቸጋሪና ግራ የሚያጋባ ቢሆንም ለእምነትህ ማደግ ፍጹም አስፈላጊ ነው። በሕይወቱ የእግዚአብሔር ህልውና የሌለው መሆኑ በተሰማው ጊዜ ይህን ማወቁ ለኢዮብ ተስፋ ሆኖለታል። ይህንኑ እንዲህ በማለት ገለጠው፦ "ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ በዚያ የለም፤ ወደ ምዕራብም ብሄድ እርሱን አላገኘውም፤ በሰሜን እየሰራ ሳለ አላየውም፤ ወደ ደቡብ በምዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም"(ኢዮ. 23፥8-10)። √ እግዚአብሔር የራቀ በሚመስልህ ጊዜ በአንተ የተቆጣ ወይም በኃጢአት ምክንያት የሚቀጣህ መስሎ ይሰማህ ይሆናል። እርግጥ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የቅርብ ግንኙነት ያቋርጠዋል። ባለመታዘዝ፣ ከሌሎች ጋር በምናደርገው ግጭት ወይም ፀብ፣ በሥራ ምክንያት፣ ከዓለም በመወዳጀትና በሌሎች ምክንያቶች የእግዚአብሔርን መንፈስ እናሳዝንና ከእርሱ ጋር ያለንን አንድነት እናጠፋው ይሆናል(መዝ. 51፤ ኤፌ. 4፥29-21፤ 1ተሰ. 5፥19፤ ኤር. 2፥32፤ 1ቆሮ. 8፥12፤ ያዕ. 4፥4)። √ ይሁን እንጂ ይህ በእግዚአብሔር የተተውን ወይም ከእርሱ የራቅን ሆኖ የመሰማት ጉዳይ ከኃጢአት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ሁላችንም የምንጋፈጠው የእምነት መፈተኛ ነው። የእግዚአብሔር ህልውና በማይሰማህና በሕይወትህ በመሥራት ላይ የመሆኑ ግልጥ ማረጋገጫ በማይኖርህ ጊዜ እግዚአብሔርን መውደድህን፣ ማመንህን፣ መታዘዝህንና ማምለክህን ትቀጥላለህ? √ ክርስቲያኖች ዛሬ በአምልኮ ውስጥ የሚፈጽሙት በጣም የተለመደ ስህተት ከእግዚአብሔር ይልቅ አንድ ዓይነት ልምምድ መፈለጋቸው ነው። አንድ ዓይነት ስሜት ይፈልጋሉ፤ ከሆነላቸው፣ ስለ ማምለካቸው እርግጠኞች ይሆናሉ። ይህ ስህተት ነው!! ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር በእነርሱ እንዳንደገፍ ስሜቶቻችንን ያስወግዳቸዋል። ስሜትን መሻት፣ ከክርስቶስ ጋር የመቀራረብ ስሜት ቢሆንም እንኳን አምልኮ አይደለም። √ አዲስ ክርስቲያን በሆንክ ጊዜ እግዚአብሔር ብዙ የማረጋገጫ ስሜቶችን ይሰጥሃል፤ በጣም ጨቅላና ግለ ተኮር ጸሎቶችህንም ይመልሳል። ይህን የሚያደርገው ሕያውነቱን ታውቅ ዘንድ ነው። በእምነት እያደግክ ስትሄድ ግን እነዚህን ጥገኝነቶች ያቋርጣቸዋል። √ የእግዚአብሔር በሁሉም ሥፍራ መገኘትና የህልውናው መገለጥ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አንደኛው የተረጋገጠ እውነት ሲሆን ሌላው ብዙ ጊዜ ስሜት ነው። መገኘቱ ደግሞ በስሜት ሊገለጥ የማይቻልና እጅግ ታላቅ ነው። √ አዎ፣ መገኘቱ እንዲሰማህ ይፈልጋል፤ ነገር ግን በስሜት ከምታውቀው ይልቅ በእርሱ ማመንህን ነው ይበልጥ የሚሻው። እግዚአብሔርን የሚያስደስተው የስሜቶች ጉዳይ ሳይሆን እምነትህ ነው። √ እምነትህን በጣም እንዲያድግ የሚያደርጉት ሁኔታዎች ሕይወትህ ሲመሰቃቀልና እግዚአብሔርን ፍጹም ልታገኘው በማትችልበት ወቅት ውስጥ ያለህ በሚመስልህ ጊዜ ያሉት ናቸው። ኢዮብ ይህን የመሰለ ሁኔታ ደርሶበታል። ቤተሰቡን፣ ሥራውን፣ ጤናውንና ያለውን ነገር ሁሉ አንድ ቀን ውስጥ አጣ። ከሁሉ ተስፋ የሚያስቆርጠው ነገር ደግሞ ሰላሳ ሰባት ምዕራፎች ሙሉ እግዚአብሔር ዝም ማለቱ ነው!!! 🌾 ለመልካም ነው! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🌼@cekuaa🌼
Hammasini ko'rsatish...
ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል

🌿"ዓላማ መር ሕይወት"🌿 [ By Rick Warren ] ቀን-13፡ እግዚአብሔርን የሚያስደስት አምልኮ: ••• እግዚአብሔር ሁሉንተናህን ይፈልጋል። እግዚአብሔር የሚፈልገው የአንተነትህን አንድ ክፍል ብቻ አይደለም። ልብህን በሙሉ፣ ነፍስህን በሙሉ፣ አዕምሮህን በሙሉ እና ኃይልህን በሙሉ ይፈልጋል። እግዚአብሔር ግማሽ ልብ የሆነ መሰጠትህን፣ ከፊል ታዛዥነትህንና ትርፍ ጊዜህን እንዲሁም ገንዘብህን አይደለም የሚፈልገው። ሙሉ ፍቅርህንና ታዛዥነትህን እንጂ የሕይወትህን ትንሽ ክፍል አይደለም የሚፈልገው። ••• የምታመልክበት ሥፍራ ከምታመልክበት ምክንያቶችና በአምልኮም ጊዜ ለእግዚአብሔር ካለህ መሰጠት ጋር እኩል ጠቃሚነት ያለው ጉዳይ አይደለም። ትክክል የሆነና ያልሆነ የአምልኮ ሁኔታ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦"ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።"(ዕብ.12፥28-29) ••• እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አምልኮ አራት ባሕርያት አሉት፦ 1.አምልኳችን ትክክለኛ ሲሆን እግዚአብሔር ደስ ይለዋል። ሰዎች ብዙ ጊዜ፦ <<እግዚአብሔር እንደ......ነው ብዬ ለማሰብ እፈልጋለሁ>>ይላሉ። ከዚያም ሊያመልኩት ስለሚፈልጉት የእግዚአብሔር ዓይነት ይናገራሉ። ነገር ግን የራሳችን የሆነና ለእኛ የሚስማማ ወይም በሁሉም ተቀባይነት ያለው የእግዚአብሔር ምስል ፈጥረን ልናመልክ አንችልም። እንዲህ ያለው ድርጊት ጣኦት አምልኮ ነው። ••• አምልኮ ስለ እግዚአብሔር በሚኖረን አስተሳሰብ ላይ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ መምሥረት አለበት። ኢየሱስ ለሳምራዊቷ ሴት እንዲህ አላት፦"ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።"(ዮሐ.4፥23-24) ••• በ"እውነት ማምለክ(መስገድ)" ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለጠው እውነት መሠረት እግዚአብሔርን ማምለክ ማለት ነው። 2. በእውነት ስናመልከው እግዚአብሔር ደስ ይለዋል። ••• ኢየሱስ "በመንፈስ ማምለክ" አለባችሁ ሲል ስለመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን ስለአንተ መንፈስ መናገሩ ነበር። በእግዚአብሔር አምሳል የተሠራህና በአካሉ ውስጥ በመንፈስ የምትኖር ነህ። ከእርሱ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ትችል ዘንድ እግዚአብሔር መንፈስህን ቀረፀው። አምልኮ መንፈስህ ለእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጥበት ሁኔታ ነው። ••• ኢየሱስ፦"እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና ነፍስህ ውደድ" ሲል አምልኮ እውነተኛና ከልብ መሆን አለበት ማለቱ ነው። ትክክለኛ ቃላትን የመናገር ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ከልብህ የምትናገር መሆንም አለብህ። ከልብ ያልሆነ ምስጋና ምስጋና አይደለም፤ ዋጋ የሌለውና እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። ••• በምናመልክበት ጊዜ እግዚአብሔር ከቃላቶቻችን ባሻገር የልባችንን ዝንባሌ ነው የሚመለከተው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ሰው ፊትን(የውጪውን ገፅታ) ያያል፣ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው"(1ሳሙ. 16፥7) አምልኮ በእግዚአብሔር ደስ የመሰኘት ነገር ስለሆነ ስሜቶችህንም ይጨምራል። እግዚአብሔር ስሜቶችን የሰጠህ በጥልቅ ስሜት እንድታመልከው ነው። በስሜቶችህ የምትገልጣቸው ነገሮች ግን እውነተኞች እንጂ ማስመሰል መሆን የለባቸውም። እግዚአብሔር ግብዝነትን ይጠላል። በአምልኮ ወቅት አስመሳይነትን ወይም ውሸትን አይፈልግም። ታማኝና እውነተኛ ፍቅርህን እግዚአብሔር ይፈልገዋል። ፍጹም ባልሆነ ሁኔታ እግዚአብሔር ልናመልከው ብንችልም ከልብ ባልሆነ ወይም ቅንነት በሌለበት ሁኔታ ግን አንችልም። ••• እርግጥ ቅንነት ብቻውን በቂ አይደለም፤ ቅን ሆነህ ትሳሳት ይሆናል። ለዚህ ነው መንፈስና እውነት ያስፈለጉት። አምልኮ ትክክልም እውነተኛም መሆን አለበት። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው አምልኮ በጥልቅ ስሜትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ላክ የተመሠረተ ነው። በምናመልክበት ጊዜ ልብና አዕምሯችንን እንገለገልባቸዋለን። ••• ዛሬ ብዙ ሰዎች በሙዚቃ የሚደረግን የስሜት መነሳሳት ይቆጥረታል።ሁለቱ የሚመሳሰሉ ነገሮች አይደሉም። እውነተኛ አምልኮ በሙዚቃ ቃና የሚነሳሳ ሳይሆን መንፈስህ ለእግዚአብሔር መንፈስ መልስ በሚሰጥበት ጊዜ የሚከናወን ነው። እንደውም አንዳንድ ስሜትን የሚኮረኩሩና በራስ አሳብ ላይ ያተኮሩ ዜማዎች ትኩረታችንን ከእግዚአብሔር ላይ በማንሣት ስሜታችን ላይ እንድናነጣጥር ስለሚያደርጉን አምልኮን ያደናቅፋሉ። አምልኮህን ከሚያውኩ ነገሮች ዋነኛው አንተው ራስህ ነህ። ፍላጎትህና ሰዎች ስለእኔ ምን ያስባሉ የሚለው ጭንቀትህ አምልኮን ያውካሉ። ••• መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ የአምልኮ ዓይነቶች ተገልጠዋል። ከእነርሱም ንስሃ፣ ዝማሬ፣ ጩኸት፣ በአክብሮት መቆም፣ መንበረከክ፣ ጭፈራ፣ የደስታ ድምፅ ማሰማት፣ መመስከር፣ የሙዚቃ መሣሪያ መጫወትና እጃችንን ማንሳት፣ ወላጆች የሌላቸው ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፣ በዓለም ከሚገኝ እድፍ የራስ ማንነትን መጠበቅ(ያዕ. 1፥26-27፤ መዝ. 7፥17፤ ዕዝ. 3፥11፤ መዝ. 149፥3፤ 150፥3) ይገኙባቸዋል። ከሁሉ የሚበልጠው አምልኮ እግዚአብሔር በሰጠህ ልምድና ግለ-ባሕርይ ላይ ተመሥርተህ ለእርሱ ያለህን ፍቅር በእውነት የምትገልጥበት ነው። <<ብዙ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ሕያው ወዳጅነት ከመመሥረት ይልቅ በማያረካና አሰልቺ በሆነ የአምልኮ ሁኔታ ውስጥ ተዘፍቀዋል። ይህ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር እነርሱን በልዩ አካኋን ላዘጋጀበት ሁኔታ በማይስማማ ፅሞና ወይም አምልኮ ሁኔታ ውስጥ ለመግባት ራሳቸውን ስለሚያስገድዱት ነው። እግዚአብሔርን ሆን ብሎ የተለያየን አድርጎ ከፈጠረን ለምንድነው ሰዎች ሁሉ በተመሳሳይ ሁኔታ እግዚአብሔርን እንዲወዱት የሚጠበቅባቸው?>> ጌሪ ቶማስ(የሪክ ዋረን የሥራ ባልደረባ) ••• ጌሪ ቶማስ 'ቅዱስ መንገዶች በሚለው መጽሐፉ ውስጥ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ከሚቀርቡባቸው መንገዶች ዘጠኙን ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ገልጿቸዋል። 1. የተፈጥሮ አድናቂዎች፡ ከቤት ውጪ ሆነው ተፈጥሮን በሚያደንቁበት ጊዜ እግዚአብሔርን ለመውደድ መንፈሳቸው ይበልጥ ይነሳሳል። 2.ስሜቶኞች፡ እግዚአብሔርን በስሜታቸው ስለሚወዱት ጆሯቸውን ብቻ ሳይሆን ማየትን፣ ማጣጣምን፣ ማሽተትንና መዳሰስን የሚያካትቱ አምልኮዎችን ይወዷቸዋል። 3. ባሕል አጥባቂዎች፡ በሃይማኖታዊ ሥርዓቶች፣ አምልኮዎች፣ ስዕሎች(ምልክቶች) እና በማይለወጡ አደረጃጀቶች አማካይነት ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር ይቀርባሉ። 4. ባህታዊያን፡ በብቸኝነት ሕይወትና አኗኗር ፍቅራቸውን ለእግዚአብሔር ቢገልጡለት ይመርጣሉ። 5. ለውጥ ፈላጊዎች፡ ክፉ ሁኔታዎችንና ድርጊቶችን በመጋፈጥ፣ ከፍትህ አዛቢዎች ጋር መታገልና ዓለምን ምቹ የመኖሪያ ሥፍራ ለማድረግ በመሥራት አማካይነት ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ይገልጣሉ። 6. በጎ አድራጊዎች፡ ሌሎችን በመውደድና የሚያስፈልጋቸውን በማድረግ ሥራቸው አማካይነት እግዚአብሔርን ይወዱታል። 7. በስሜት ተደሳቾች፡ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር የሚገልጡት በመፈንጠዝ ነው። 8. የጽሞና ሰዎች፡ በማምለክ እግዚአብሔርን ያከብሩታል። 9. ምሁራን፡ በአዕምሯቸው በማጥናት እግዚአብሔርን ይወዱታል።
Hammasini ko'rsatish...
🌿"ዓላማ መር ሕይወት"🌿 [ By Rick Warren ] ቀን-12፡ ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነትህን ማሳደግ ••• ወደ እግዚአብሔር ያለህ ቀረቤታ ልትቀርበው በመረጥከው ልክ ነው። እንደ ማንኛውም ወዳጅነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማሳደግ መጣር አለብህ። በአጋጣሚ የሚሆን ነገር የለም። ፍላጎት፣ ጊዜና ብርታትን ይጠይቃል። ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅና የቀረበ ግንኙነት እንዲኖርህ ከፈለክ ስሜትህን ለእርሱ በታማኝነት ማካፈልን ልመድ፣ አንድ ነገር ሲያዝህ በእምነት አድርገው፣ እርሱ የሚወደውን መውደድን ተማር፣ ከሁሉም ይልቅ የእርሱን ወዳጅነት ፈልግ። 3. ለእግዚአብሔር እውነተኛ መሆንን መምረጥ አለብኝ። ••• ከእግዚአብሔር ጋር ለሚኖር ጥልቅ ወዳጅነት የመጀመሪያው የማዕዘን ድንጋይ ስለድካሞችህና ስሜቶችህ ፍጹም እውነተኛና ግልፅ መሆን ነው። ፍጹምነትን እግዚአብሔር ከአንተ አይጠብቅም፤ እውነተኛና ግልፅ መሆንህን ግን በጥብቅ ይፈልገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት የእግዚአብሔር ወዳጆች አንዳቸውም እንኳን ፍጹም አልነበሩም። የእግዚአብሔር ወዳጅ የመሆኛው መስፈርት ፍጹምነት ቢሆን ኖሮ ወዳጆቹ ለመሆን በፍጹም አንችልም ነበር። መልካሙ ነገር ከእግዚአብሔር ፀጋ የተነሣ ኢየሱስ አሁንም "የኃጢያተኞች ወዳጅ"(ማቴ. 11፥19) መሆኑ ነው። ••• መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት የእግዚአብሔር ወዳጆች ስሜታቸውን በመግለጥ፣ ቅሬታቸውን ለፈጣሪያቸው በማሳወቅ፣ ውሳኔዎችን በመንቀፍና በመከራከር የሚሰማቸውን በእውነተኛነት የሚገልጡ ነበሩ። በዚህ ግልጥነታቸው እግዚአብሔር የተቸገረ አይመስልም፤ እንደውም ድርጊታቸውን አበረታታ። አብርሃም የሰዶም ከተማ ጥፋትን በተመለከተ ጥያቄ እንዲያነሣና እንዲደራደር እግዚአብሔር ፈቅዷል። ዳዊት "ረሳኸኝ"፣ "ጣልከኝ"፣ "ተውከኝ" በማለት ያቀረባቸውን አቤቱታዎች እግዚአብሔር በትዕግስት አድምጧል። ኤርሚያስ እግዚአብሔር እንዳታለለው በተናገረ ጊዜ አልቀሰፈውም። ኢዮብ በሰቆቃው ጊዜ ምሬቱን እንዲናገር ተፈቅዶለት ነበር። በመጨረሻ ግን እውነተኛና ግልፅ በመሆኑ እግዚአብሔር ተሟግቶለታል። ጓደኞቹን ግን እውነተኞች ባለመሆናቸው ገስጿቸዋል። ••• እውነተኛ ወዳጅነት በግልጥነት ላይ ነው የሚመሰረተው። ድፍረት የሚመስል ነገር እግዚአብሔር እንደ እውነተኛነት ያየዋል። በጥልቅ ስሜት የሚገለጡትን የወዳጆቹን ቃላት ያደምጣል። አታካች ሃይማኖታዊ ድግግሞሾች ግን ያሰለቹታል። ወዳጁ ለመሆን ትችል ዘንድ ሊሰማህ ወይም ልትናገረው ስለሚገባህ ነገር ሳይሆን እውነተኛ ስሜትህን በማካፈል ግልፅ ልትሆንለት ይገባል። ••• በሕይወትህ አንዳንድ ሁኔታዎች የተታለልክ መስሎህ ወይም ቅር የተሰኘህበት ነገር እንዳለ ተሰምቶህ በእግዚአብሔር ላይ በድብቅ ተቆጥተህ እንዲሁም ተበሳጭተህ ከሆነ ንስሃ መግባት ያስፈልግሃል። በሕይወታችን ላይ የሚደርስን ማንኛውንም ነገር እግዚአብሔር ለበጎ የሚጠቀምበት መሆኑን ወደ መረዳት ደረጃ እስክናድግ ድረስ መልካችንን፣ ያለፈ ሕይወታችንን፣ መልስ ያላገኙ ፀሎቶቻችንን፣ ያለፈ ጉዳቶቻችንና እኛ እግዚአብሔር ብንሆን ኑሮ እንለውጣቸው የነበሩ ሌሎች ነገሮችን እናስብና በእግዚአብሔር ላይ ቅር እንሰኛለን። ሰዎች ብዙ ጊዜ ከሌሎች ለሚደርስባቸው ጉዳት እግዚአብሔርን ይወቅሳሉ። እንዲህ ያለው ነገር ዊሊያም ባክስ(ስመ-ጥር ፀሐፊ) እንዳለው፦ <<ከእግዚአብሔር ጋር ባለህ ግንኙነት መካከል ስውር ሸለቆን>> ይፈጥራል። መራራነት ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነት እንዳይመሠረት የሚያግድ ትልቅ እንቅፋት ነው። ••• እግዚአብሔር ቅንነትንና እውነተኛነትን ሊያስተምረን መዝሙረ ዳዊትን ሰጠን። መዝሙረ ዳዊት እሮሮን፣ አድናቆትን፣ ጥርጣሬን፣ ፍርሃትን፣ ቅሬታን ከምስጋና ጋር የተጣመረ ጥልቅ ስሜትን፣ ውዳሴን እና የእምነት መግለጫዎችን የያዘ የአምልኮ መመሪያ ነው። አሉ የምንላቸው ስሜቶች ሁሉ መዝሙረ ዳዊት ውስጥ ተመዝግበዋል። የዳዊትንና የሌሎቹን በጥልቅ ስሜት የታጀበ ንስሃ በምታነብበት ጊዜ እግዚአብሔር የሚፈልገው ምንም ሳትሸሸግ በዚህ እንድታመልከው መሆኑን ተገንዘብ። እንደ ዳዊት "ብሶቴን በፊቱ አፈሳለሁ፤ ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ"(መዝ.።142፥2)በማለት ልትፀልይ ትችላለህ። ••• የእግዚአብሔር የቅርብ ወዳጆች ሁሉ ሙሴ፣ ዳዊት፣ አብርሃም፣ ኢዮብና ሌሎቹም ከጥርጣሬ ጋር ትግል የነበረባቸው መሆኑን ማወቁ ያበረታታል። ጥርጣሬን መግለጥ አንዳንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ወዳጅነት ወደ ሁለተኛው ደረጃ የመሸጋገሪያ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። 4. እግዚአብሔርን በእምነት መታዘዝን መምረጥ አለብኝ። ••• የእግዚአብሔርን ጥበብ ባመንክና ትዕዛዙ የማይገባህ ቢሆን እንኳን በፈፀምከው ጊዜ ሁሉ ከእርሱ ጋር ያለህን ወዳጅነት ታሳድገዋለህ። ታዛዥነት ከእግዚአብሔር ጋር ለመወዳጀት ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ኢየሱስ እንዲህ በማለት በግልጥ አስገንዝቧል፦ "ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ።"(ዮሐ. 14፤15) ኢየሱስ "ወዳጆቼ" ብሎ ሲጠራን የተጠቀመበት ቃል ንጉሳዊ ቤተ መንግስት ውስጥ <<የንጉሥ ወዳጆች>> የሆኑ ሰዎችን የሚያመለክት ሊሆን እንደሚችል ባለፈው ምዕራፍ ላይ ገልጫለሁ። የንጉሡ ወዳጆች የተለየ ዕድል ቢኖራቸውም ለእርሱ መገዛትና ትዕዛዛቱንም መፈፀም ነበረባቸው። የእግዚአብሔር ወዳጆች እንጂ አቻዎቹ አይደለንም። አፍቃሪ ገዢያችን ስለሆነ እንከተለዋለን። ••• እግዚአብሔርን የምንታዘዘው ከኃላፊነት፣ ከፍርሃት ወይም ከመገደድ የተነሣ ሳይሆን ስለምንወደውና ለእኛ የሚጠቅመንን ያውቃል ብለን ስለምናምን ነው። ይቅር በመባለችንና ነፃ በመውጣታችን ከፍቅር የተነሣ እንታዘዛለን፤ ያዛዥነታችንም ታላቅ ደስታን ያመጣልናል።(ዮሐ. 15፥9-11) ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ያለው ግንኙነት እኛ ከእርሱ ጋር ለሚኖረን ወዳጅነት ምሳሌ ነው። ኢየሱስ ከፍቅር የተነሣ አብ የጠየቀውን ሁሉ አደረገ። ••• እውነተኛ ወዳጅነት በተግባር ይገለጣል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን እንድንወድ፣ ችግረኞችን እንድንረዳ፣ ያለንን እንድናካፍል፣ ሕይወታችንን በንፅህና እንድንጠብቅ፣ ይቅርታ እንድናደርግና ሌሎችን ወደ እርሱ እንድናመጣ ሲጠይቀን በፍጥነት እንድንታዘዘው ፍቅር ያነሳሳናል። ••• ለእግዚአብሔር <<ታላቅ ነገር>> እንድናደርግ በተለምዶ ሲነገረን ሁልጊዜ እንሰማለን። በመሠረቱ እግዚአብሔር ይበልጥ ደስ የሚለው በፍቅር በመታዘዝ ትናንሽ ነገሮችን ስናደርግለት ነው። ሥራዎቻችን በሌሎች ሰዎች አይታወቁ ይሆናል። እግዚአብሔር ግን ያያቸዋል፤ እንደ አምልኮም ይቀበላቸዋል። ••• ታላላቅ ዕድሎች ወደ እኛ የሚመጡት በሕይወት ዘመናችን አንድ ጊዜ ብቻ ሊሆን ይችላል። ትንንሾቹ ዕድሎች ግን ሁልጊዜ በዙሪያችን ናቸው። እውነት በመናገር፣ በደግነት፣ ሌሎችን በማጽናናትና በመሳሰሉ ትንንሽ ድርጊቶቻችን እንኳን እግዚአብሔርን ፈገግ እንዲል እናሰኘዋለን። ••• ከጸሎት፣ ከምስጋና ወይም ከስጦታችን ይልቅ ለትንንሽ የመታዘዝ ድርጊቶቻችን ከፍ ያለ ዋጋ ይሰጣቸዋል። "ሳሙኤልም፦ 'በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።'" (1ሳሙ. 15፥22
Hammasini ko'rsatish...
ድፋዉ! ብርጭቆህን ባዶ አድርግ! ***
ብዙዎች ዉስጣቸው ያበጠ ነዉ። ሁሌም ልክ ናቸዉ። ቆንጆዎች ናቸው። አዋቂዎች ናቸዉ። ተጫዋቾች ናቸዉ። የተከበሩና የተወደዱ ናቸዉ። ሁሉም የሞላላቸዉ ናቸዉ። ከማንም ምንም አይፈልጉም። ማንንም አይለምኑም። ለምንም አይደክሙም። ደጃቸው የሞላ ነዉ። ጤነኞች ናቸዉ። ሰላምና ደስታ አላቸዉ። ሁሌም ልክ ናቸዉ። የጎደለ ነገር ነገር የላቸዉም...

...ይህ ሁሉ ግን በራሳቸው አይን ነዉ። 

በተመልካች አይን የእነዚህ ሰዎች እዉነት ሌላ ነዉ። ጉረኞች ናቸዉ። ትእቢተኞች ናቸዉ። ሁሉ አይለፈኝ ናቸዉ። አስመሳዮች ናቸዉ። ጤና የራቃቸዉ ናቸው። ስዶች ናቸዉ። ባለጌዎች ናቸዉ። ተሳዳቢዎች ናቸው። የሚናገሩትን አያዉቁም። የሚያደርጉትን አያስተዉልም። በደመ ነፍስ ነዉ የሚራመዱት። ይሉኝታ የላቸዉም። ራሳቸዉን ይዋሻሉ። ሌሎችን በከንቱ ያስቀናሉ። ህሊና ቢሶች ናቸዉ። አላማ የላቸዉም። ብልህነት ይጎድላቸዋል...

...እኛ ራሳችንን የምናይበትና ሰዎች እኛን የሚያዩበት አይን ሁሌም አንድ አይደለም። እኛ ፍፁም መልካም ሰዎች እንደሆን ስናስብ አብሮን የሚውለዉ የቅርብ ወዳጅ ግን ስለክፋታችን በምሬት የሚናገር ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ፅዋችን እስከአፉ ሞልቶ እያየን ትንሽም ቢሆን ለማጉደል አንሞክርም። ይህ ፅዋችንን የሞላዉ የሁሉም አይነት ዉድቀት መነሻ ትእቢት ይባላል። 

ትእቢት ዉስጣችንን ከሞላዉና ለማጉደል ዝግጁዎች ካልሆንን የትም አንደርስም። ብዙ ለዉጦች ከትንሽ ነዉ የሚጀምሩት። ለማጅ መባል አለብህ። ተማሪ መሆን አለብህ። ስህተት መስራት አለብህ። እነዚህ ሁሉ ደግሞ ከትእቢትና "ከኢጎ" ጋር አብረዉ አይሄዱም። ለዉጥን ስትፈልግ ትእቢትክን ከራስህ ማራቅ አለብህ። 

ብርጭቆህን ባዶ አድርግ። ሌላ መጠጣት የምትፈልግ ከሆነ። አዲሱንና ለየት ያለዉን ነገር መቅመስ የፈለገ ሁሉ ይህንን ማድረግ አለበት። ይህ ማለት የግድ ክብርህን መጣል አለብህ ማለት አይደለም። ትእቢተኛ ሰውና ክብሩን የሚጠብቅ ሰዉ የተለያዩ ናቸዉ። አንዱ በራሱ አለም አድጎ እንደጨረሰና ከማንም ምንም እንደማይፈልግ ያስባል። ሁለተኛዉ ደግሞ እድገቱንና ለዉጡን ከባህልና ከወጉ፣ ከእምነቱና ከስብእናዉ ጋር ያለምንም ተቃርኖ እንዲሄዱና ከዚህ የዘለሉትን መስመር እንዲይዙ በግልፅ እየታገለ ይጓዛል። ሁለት የተለያዩ ምርጫዎች።

ትእቢት ካለብህ ራስህን አንቀህ እየገደልክ ነው። የለዉጥና የእድገት ድልድይህን አፍርሰሃል። ትእቢት ማለት ስንፍና ስለሆነ። የሚነገረዉን አለመስማት ስለሆነ። ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ ብሎ ማሰብና ሌሎችን ማንቋሸሽ ስለሆነ። ትእቢተኛ ሰዉ ሁለት ሰዉ ነዉ። ከእሱ በታች ካሉ ሰዎች ጋር ሲገናኝ የምናየዉ ባህሪዉ አለ። ከእሱ የተሻለ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎችን የሚያስተናግድበት ባህሪዉ አለ። ትእቢተኞች በዚህ ይለያሉ። ብርጭቆህ የያዘዉ ይህንን ነው። በሰማይም በምድርም በርህን የመዝጋት ጉልበት ያለዉ አንድ ነገር ይህ ትእቢት የሚሉት በሽታ ብቻ ነው። ይህንን ድፋና ህይወትህን ካቆምክበት ቀጥል! በትእቢት ዉስጥ ከነበርክ የእስከዛሬዉ ኑሮ አልነበረም!

ላ/ማርያም 🌾 ለመልካም ነው! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🌼@cekuaa🌼
Hammasini ko'rsatish...
ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል