cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 075
Obunachilar
+124 soatlar
-47 kunlar
+1830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

•••✿ ❒ የነቢዩሏህ_እስሃቅ_ና_የአቆብ_ዐለይሂሰላም_ታረክ ❒ ✿••• #ክፍል 2 አሁን ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን አስቆጥሯል። ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል። አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው። ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ። ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ። ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው። አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው። ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ። በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት አራራቃቸው። ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ ተዘጋጀ። አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት ሆኗል። ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች። ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት። ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ ትሄዳለህ!!! ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው። ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም። ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል አልነሳም አለች። ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው ተመለሰ። ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር። አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን በቀል ፈርቷል። እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ ለወንድሙ ላከለት። በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400 እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን በኩል ለያዕቁብ መጣችለት። ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ። ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ። ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት... 200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች 200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች 30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች 20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ። የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል.... እንዲ እንዲ እያለ አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው። ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው። ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ። አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት። እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ እየነዱ አስረከቡት። ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ ወንድሙ ጉዞ ጀመረ። (በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።) ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ። ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ ነበር። በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን" ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም ሁሉ ኬት አምጥተህ ነው?" አለው። ያዕቁብም፦"እነዚህ አላህ የሰጠኝ ስጦታዎቼ ናቸው" አለው። ይህን ግዜ የያዕቁብ ልጆች እና ሚስቶች ተራ በተራ እየመጡ ዒስን ከዘየሩ በኋላ ያዕቁብ በአገልጋዮቹ አማካኝነት ለዒስ የላከውን ስጦታ ዒስ መቀበል እንቢ አለ። ያዕቁብም ለምኖት እንዲቀበል አደረገው'ና አብረው በረሀውን እያቆራረጡ አባታቸው ወደሚገኝበት የፊለስጢን ምድር መትመም ጀመሩ። በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ያኔ....ያዕቁብ አጎቱ ጋ ሲሄድ ተኝቶ ህልም ያየበትን ቦታ ደረሱና እዛ ቦታ ያዕቁብ በ200 በግ ያንን ቦታ ከአንድ ገበሬ ገዛው'ና አንድ ትልቅ የአምልኮ ቦታ ሰራ(ቁድስ) ከዚያ በኋላ ነው በሱለይማን ዘመን ሱለይማን ያደሰው። በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ነበር አንድ ደስታ እና ትልቅ ሀዘን በያዕቁብ ቤተሰብ የተከሰተው። ነፍሰ ጡር የነበረችው ትንሿ ራሂል ምጥ አስቸገራት...ብዙ ከተጨነቀች በኋላ ቢንያሚን የተባለ ልጅ ተገላግላ ለራሷም ዱንያን ተገላገለቻት። ያዕቁብም ባለቤቱን መንገድ ላይ ቀብሮ ሀዘኑን ታቅፎ ወደ አባቱ ጉዞ ቀጠለ። ከአባቱም ተገናኝቶ በከንዓን ምድር ሀብሩን በምትባል(ኢብራሂም ይኖር በነበረበት) አካባቢ መኖር ጀመረ። ኢስሀቅም እርጅና ተጫጭኖትም ስለነበር ጌታው የፃፈለትን 180 አመት ካጠናቀቀ በኋላ ነፍሱን ለጌታው አስረከበ። የነበቢዩሏህ የኢስሃቅ ዐለይሂሰላም ታረክ አዚህ ላይ ተፈፀመ። የነቢዩሏህ የአቆብ ዐለይሂሰላም ታሪክ የቀረውን የነቢዩሏህ ዩሱፍ ታረክ ውስጥ እናየወለንን!!       •••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿••• በቀጣይ #የነብዩሏህ_ዩሱፍ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰 #share https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

👍 2
' •••✿ ❒ የነቢዩሏህ_እስሃቅ_ና_የአቆብ_ዐለይሂሰላም_ታረክ ❒ ✿••• #ክፍል 1 ለኢስሀቅ አባቱ ኢብራሂም (ዐሰ) በህይወት ሳለ በ40 አመቱ ነበር ረፍቃ ቢንት በትዋዪል ከተባለች እንስት ትዳር ያስያዘው። ምንም እንኳን ረፍቃ መውለድ የማትችል መሃን ብትሆንም በባለቤቷ ያላሰለሰ ዱዓ ሁለት መንታ ልጆችን ለመታደል በቅታለች። አንደኛው፦ዒስ ሲሆን ሁለተኛው፦ያዕቁብ (ዐሰ) ይባላል። ዒስ የሮም ህዝቦች ቅድመ አያት ሲሆን፤ ያዕቁብ ደሞ የእስራኢላውያን ቅድመ አያት ነው። የሁለቱም አባት ሁለቱንም ልጆቹን በጣም ቢወዳቸውም ከያዕቁብ ይልቅ ለዒሱ ግን ለየት ያለ ቦታ ነበረው። እናታቸው ረፍቃ ግን ያዕቁብ ታናሽ ስለሆነ ይበልጥ እሱን ነበር የምትወደው። ኢስሀቅ ከእርጅና የተነሳ አይናቸው ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል። ከእለታት አንድ ቀን ኢስሀቅ (ዐሰ) ስጋ ያምራቸውና የሚወዱትን ልጃቸውን ዒስን አደን አድኖ ስጋ እንዲያመጣለቸው እናም ከባድ ዱዓም እንደሚያደርጉለት ነግረውት እሱም ለአደን ሄደ። ይህን በድብቅ ስትሰማ የነበረችውም የልጆቹ እናት ረፍቃ ለያዕቁብ ነግራው ከፍየሎቹ ወፍራሙን ሙኩት እንዲያርድ ካደረገች በኋላ የወንድሙን ዒስን ልብስ አልብሳው እራሱን(ዒስን) አስመስላ የሰራውን ስጋ ለአባቱ እንዲያቀርብ አደረገች። ያዕቁብም ያዘጋጀውን ምግብ ይዞ አባቱ ዘንድ ሲያቀርብ አባቱ፦"ማን ነህ አንተ?" አሉት። ያዕቁብም፦"ልጅዎት ነኝ"አለ። አባቱም(ኢስሀቅ)፦"ድምፅህ የያዕቁብ ነው፤ልብስህ ግን የዒስ ነው" በማለት የቀረበላቸውን ምግብ በሉት። ምግቡን በልተው እንደጠገቡም ምግቡን ላቀረበው አላህ ክብሩን ከፍ እንዲያደግለት፣ የበላይ ዘርም እንዲያደርገው፣ልጆቹንም ሪዝቁንም አላህ እንዲያበረክትለት ዱዓ አደረጉ። ልክ ዱዓውን እንዳጠናቀቁ ያዕቁብ አሚን ብሎ የአባቱን ክፍል ለቆ ወጣ።ያዕቁብም ሲወጣ ዒስ በታዘዘው መልኩ ያደነውን ስጋ ጠባብሶ ለአባቶ አመጣ'ና አቀረበ። አባቱ ግን ቅድሙኑ ጠግበዋል። ዒስ ምግቡን ሲያቀርብላቸው፦"ልጄ ይህ ምንድነው?" አሉት። ዒስ'ም፦"አምጣልኝ ያሉት ስጋ ነዋ" አላቸው። አባትየውም፦"አሁን አምጥተህልኝ በልቼ ዱዓ አላደረግኩልም እንዴ!!!"ሲሉት ወንድሙ ያዕቁብ እንደቀደመው እና ዱዓውንም ሸውዶ እንደተቀበለ በመረዳት ሀይለኛ እልህ ያዘው። ዒስ አባታቸው ኢስሀቅ ከሞተ ያዕቁብን እንደሚገድለውም ይዝትበት ጀመር።ያን ግዜ አባት ለልጃቸው ዒስ ማስተዛዘኛ ይሆም ዘንድ፦"አላህ ዝርያዎችህን ጠንካሮች ያድርጋቸው፣ፍራፍሬዎችን እና ሪዝቆቹንም አላህ ሰፋ አድርጎ ይስጥህ" በማለት ዱዓ አደረጉለት። ነገር ግን እናት ልጇ ያዕቁብ ላይ ሚዛተው ዛቻ እረፍት ነስቷት ስለነበር የዒስ ቁጣ እስኪበርድለት ድረስ ያዕቁብን ሀራን በሚባል አካባቢ ወደሚገኘው ወንድሟ (ላባን) ላከችው። ያዕቁብም ስንቁን ይዞ ወደ አጎቱ ላባን እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ መሸበት እና አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ፏ ያለ እንቅልፍ ተኛ። እዛው በተኛበትም በህልሙ ወደ ሰማይ መወጣጫ ይመለከታል።በዚያ መወጣጫ መላዕክት ይወጣሉ...ይወርዳሉ።በዚያ መሀከል አላህም፦"እኔ አንተን እባርክሀለሁ።ዝሪያዎችህንም አበዛልሀለሁ...ምድርንም ላንተ እና ለዝርያዎችህ አደርጋታለሁ" አለው። በህልሙ ማለት ነው.... ልክ ይሄን እንዳየ ከእንቅልፉ ነቃ። ባየው ነገርም በጣሙን ተደሰተ'ና፦"ጌታዬ አሁን ከምሄድበት በሰላም ከመለስከኝ እዚህ ቦታ ላይ ላንተ አምልኮ እሚሆን ቤት እገነባለሁ።ከሚኖረኝም ሀብት አንድ አስረኛውን ባንተ መንገድ አውላለሁ" በማለት እዛ ቦታ ላይ የሆነ ምልክት አድርጎ ስለት ገብቶ ጎዞውን ቀጠለ። ብዙ ተጉዞ የሀራንን ምድር ደረሰ'ና ከአጎቱም ተገናኘ።ለአጎቱ ሁለት ሴት ልጆች ነበሩት አንዷ (ለያ) ስትባል ታናሿ ደሞ (ራሂል) ትባላለች። ምነው ለያ ራሂል...ስል የዩሱፍ ፊልም ትዝ አላችሁ ሀ....!!! ቆይ ዩሱፍንም ደርሰነዋል ትንሽ ነው የቀረን። ትንሸኛዋ ራሂል ቆንጅዬ ነገር ስትሆም ትልቋ ግን እስከዚህም ነገር ነበረ።ከዚያም ያዕቁብ ትንሸኛዋ ራሂል በልቡ መግባቷን ሲያውቅ አጎቱን ላባንን እንዲድረው ጠየቀው። አጎቱም፦"7 አመት በጎችን ካገድክልኝ እድርሀለሁ" በማለት ቃል ገባለት'ና ያዕቁብም ቆንጂዬዋን ራሂልን ለማግኘት ለ7 ተከታታይ አመታት እረኛ ሆኖ አሳለፈ። የማይደርስ የለም'ና ሰባቱ አመት ተጠናቅቆ የቀጠሮው ቀን ብቅ አለ።ላባንም ድል ያለ ድግስ ደግሶ ዘመድ አዝማድ ከጠራ በኋላ ኒክህ እስሮ ሙሽሪትንም ለያዕቁብ አስረከበው። በማግስቱ ጠዋት ላይ ጨለማው በብርሀን መገፈፍ ሲጀምር ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት። ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት። ያዕቁብ በጣም ተናደደ.... ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት። ያዕቁብ በጣም ተናደደ በጠዋት አጎቱ ጋ በመሄድ፦"አንተ ቃል ኪዳንን አፍርሰሀል።እኔ የተዋዋልኩት ልጅህን ራሂልን ሀኖ ሳለ እንዴት ለያን ትሞሽርልኛለህ" በማለት ወቀሰው። የያዕቁብ አጎትም ላባን ብልጣ ብልጥ ነገር ነበር'ና፦"ይህማ በኛ ባህል ነውር ነው...እንዴት ታላቅ እያለች ታናሽ ትዳራለች!!! በል ራሂልን ምትፈልግ እንደሆን ለ7 አመት በጎችን አግድልኝ" አለው። ያዕቁብም ራሂልን በጣም ወዷት ስለነበር 7 አመታትን ለመጠበቅ ተገደደ።የማይደርስ የለም'ና ይህም ቀን ደረሰ።ያዕቁብም ለ14 አመት የጠበቃትን ራሂልን በእጁ አስገባት። (በነገራችን ላይ ሁለት እህትማማቾችን በአንድ ግዜ ማግባት በነሱ ህግ/ሸሪዓ ክልክል አልነበረም።ከዚያ በኋላ ነው ተውራት ሲወርድ ይህ ህግ የተሻረው።) ከዚያ ያዕቁብ ሁለት እህትማማቾችን አግብቶ ሳለ አጎቱ ላባን ለሁለት ለልጆቹ ሁለት አገልጋዮችን በስጦታ መልኩ ጀባ አላቸው። ለያ ለምትባለዋ፦ዘልፋ የምትባል አገልጋይ ሲሰጣት ራሂል ለምትባለዋም፦በልሃ የምትባል አገልጋይ ሰጣት። አላህም ለያ የምትባለዋን(ፉንጋዋን) 4 ወንድ ልጆችን በመስጠት ካሳት።ልጆቿም 1፦ረውቢል 2፦ሸምዑን 3፦ላዊ 4፦የሁዳ...ናቸው። ትንሿ ረሂል ምንም እንኳም ቆንጅዬ ብትሆንም ልጅ መውለድ ግን አትችልም። በታላቅ እህቷ መውለድ በጣም ቅናት ይይዛት'ና እራሷ ዘንድ የምትገኘውን በልሀ የተባለችውን አገልጋይ ለገዛ ባለቤቷ ዳረችው'ና አገልጋይዋም ከያዕቁብ 5፦ዳን 6፦ኒፍታሊ...የተባሉ ልጆችን ወለደች። ያን ግዜ ለያ ከእህቷ ረሂል እልህ ተያያዘች'ና እሷም ዘልፋ የምትባል አገልጋይዋን ለያዕቁብ ዳረችለት'ና ያዕቁብም ከዘልፋ 7፦ጃድ 8፦ዐሺር...የተባሉ ልጆችን ወለደችለት። ኧረ የሌላ ይደላል ያዕቁብ ዐ ሰ በመሀል ተመቻቸው እኮ...ሱብሀን አላህ የአላህ ተርቲብ ከዚያም ለያ(ታላቋ) አምስተኛ አረገዘች'ና 9፦ያሳካር...የተባለ ልጅ ወልዳ ብዙም ሳትቆይ 10፦ዛብሎን... የተባለ ልጅ ደገመች። አሁንም አላረፈችም 11፦ዲና... የምትባል ሴት ልጅ ለያዕቁብ አሳቀፈችው።ያ ማለት ለያ ከያዕቁብ 7 ልጆችን ወለደች ማለት ነው። ይህን ስታይ መቋቋም ያቃታት ራሂል አላህን ልጅ እንዲሰጣት መማፀን ጀመረች። አላህም በሩን ያንኳኳውን በከንቱ ማይመልስ ጌታ ነው'ና ዱዓዋን ተቀብሎ 12፦ዩሱፍ (ዐሰ) የሚባል ውብ እና ገራሚ የሆነ ልጅ ጀባ አላት። ይህ ሁሉ የሚሆነው በአጎቱ ሀገር በሀራን ምድር ላይ ነው። ክፍል 2 ይቀጥላል... #share https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿••• #ክፍል 5 አባቴ ሆይ ይህንን ድንጋይ ምን ነው ይዞልህ የመጣው ሲል ጠየቀው ፣ ያ መተረሰት የመይፈለገው እንዲሁም የማይደክመው አካል ጅብሪል ነው ያመጣልኝ አለው። እናም አል ሀጀሩል አስወድ ከጀነት ነው። ይህን ትልቅ ቤትም ገንብተው ካጠናቀቁ በኋላ አላህም ኢብራሂምን፦"ሰዎች ከየሀገሩ በመምጣት ቤቴን ይጎብኙ ዘንድ ተጣራ" አለው። ኢብራሂምም፦"ጌታዬ እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ ድምፄ እኮ አይደርስም"አለው። አላህም፦"አንተ ተጣራ ማድረስ የኔ ስራ ነው" አለው። ኢብራሂምም ትልቅ ተራራ ላይ በመውጣት ተጣራ።ያን ግዜ ከየሀገሩ ያሉ ህዝቦች ጥሪውን በመቀበል መካ መጥተው ሞሉ። ኢብራሂምም የሀጅን ስነስርዐት ለሁሉም አስተማራቸው። ከዚያ በኋላ የኢብራሂም ሚስት ሳራ በከንዐን ምድር ሀብሩን በምትባል ቦታ በ127 አመቷ ዱንያን ተሰናበተች። ከዚያ በኋላ ኢብራሂም ለሳራ ልጅ ኢስሀቅ ሪፍቃ ቢንት በቱኢል የተባለችን እንስት አጭቶለት አጋባው። ኢብራሂም እደሚያቸው 175 ሲሆን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። እስማኢል ና እስሃቅቀበሯቸው። ኢብራሂም የተቀበሩት #በሀብሩንነው።የቺ አከባቢ በሁን ሰዐት ከሊል በመባል ትተወቃለች። አይሁዶች ና እንግሊዛዊያን ሄብሮን በማለት ይጠሯታል።እብራሂም ዐ ሰ የነቢያት አባት ነቸው። ከኢብራሂም ዐ ሰ ብሇላ ከሰቸው ዘር ካልሆነ በስተቀር አንደም ነቢይ አልተላከም።   •••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿••• በቀጣይ #የነብዩሏህ_ኢስሃቅ_ና_የያእቁብ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰 #share https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

3
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿••• #ክፍል 4 ከዚያ አባት ኢብረሂም በሆዱ አስተኝቶ ፊቱን ወደ መሬት በመድፋት የጌታውን ትዕዛዝ ተፈፃሚ ሊያደርግ ቢለዋውን በልጁ ኢስማዒል አንገት ላይ ሲያሳርፍ ከዚያም ቢለዋውን በንገቱ ለይ ማንቀሳቀስ ጀመረ ፣ ገዘገዘው ገዘገዘው ግን ቢለዋ መቁረጥ አልቻለችም ኢብራሂም እሳት ማቀጠል እንዳልቻለቺው ሁሉ ቢለዋም እስማኢለን መቁረጥ አልቻለችም። በአሏህ ፉቃድ ቢሆን እንጂ ቢለዋ የመቁረጥ ችሎታ የላትም፡፡ እሳትም በአሏህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ የማቃጠል ችሎታ የላትም፡፡ በጊዜው አሏህ ሱ ወ እንዲህ ያለውን ችሎታ ነጥቋወት ነበረ ኢብረሂም ዐ ሰ ቢለዎውን ጫን እያለ የገዘገዝ ጀመረ እስማኢለም ደግሞ አባቴ ጫን በል የለዋል ጫን ብሎ ይገዘግዛል፥ ግን ቢለዋ አልቻለችም አልቆረጥ አለች አሏህ ሱ ወ ይሂነን ቲረት አስመልክቶ ሲናገር ሁለቱም ተዛዙን በተቀበሉና በግንባሩ ግን ላይ በጣለው ግዜ የሆነው ሆነ ይላል። አስለማ ይላል እጅ ሰጡ ትዛዙን ለመፈፀም ሆኑ። ፈተናው አዚህ ቦታ ላይ ተጠናቀቀ። ከላይ በኩል፦"ኢብራሂም ሆይ !!! ህልሙን እውን አድርገሀል እኛም እንደዚህ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን" የሚል ድምፅ መጣ። ኢብራሂምም ቀና ሲል ከሰማይ አንድ መልዐክ ለኢስማዒል ቤዛ ይሆን ዘንድ፡ከጀነት የሆነን በግ ይዞ መጣ'ና፦"ኢስማዒልን ፈትተህ ይሄን እረድ" አለው። ከዚያም ኢብራሂም ደስታው ወደር አጣ...እየተቻኮለ የልጁን...የአብራኩን ክፋይ እጆች መፍታት ጀመረ። ከዚያም ከሰማይ የመጣለትን በግ አረደው።ያን ቀን በማስመልከት ነው እንግዲህ በየዐረፋ በአሉ የእርድ ስነስርዐት ሙስሊሞች የምንፈፅመው። የእስሃቅን ብስራት በተመለከተ፣ በስራቱ የተፈጠመው እብራሂም ዐ ሰ በመካ ልጁን የመሰዋት ፈተና ከለፈና ወደ ፊሊስጢን መደር ከተመለሰ ብሇላ ነው፡፡ አሏህ ሱ ወ እሱን እና በለቤቱን ሰራን ማክበር ፈለገ ፤ በዚያን ግዜ የእብራሂም ዐ ሰ እድሜ 120 ነበር፤ የሳረ እድሜ ደግሞ 90 አመት ነበር። እነርሱን ሊያበስራቸው 3 መላዕከን ከሰማይ አወረደ፦ ጂብሪል ፣ ሚካኢል ና መለከል ሞት ነቸ የወረዱት። አመጣጠቸውም አሏህ ሱ ወ የሉጥ ህዝቦችን እንዲያጠፉ አዙያቸው ነበር። ወደዚያ እየሄዱ ሳለ እግር መንገዳቸውን ወደ እብራሂም ዐ ሰ እና ወደ ባለቤቱ ሳረ ወረዱ ሲወርዱ የሰው ልጅን መልክ የዘው ነበር የወረዱት። እብራሂ ዐለይሂሰላም እንግጆችን ይወድ ሰለነበር፣እንግዶቹ ወደሱ ሲመጡ ተመለከተ ሰላም አሉት እናም እሱም በመገረም ሰላም አለቸው፡፡ ለምን ተገረመ ? እነዚህ ሰወች በአከባቢው የሚታወቁ ሰወች አልነበሩም ፣ የመንገጀኛ ምለክትም አልነበረቸውም፤ የሚታወቅ  የጉዞ መለያ ፤ መጓጓዣ አንሰሳም አልነበራቸውም፡፡ ወደ ቤት አስገባቸው ና ወሬ ሳያበዛ ጥጃን አረደላቸው የተጠበሰ የጥጃ ስጋ አቀረበላቸው። አቦ ወላሂ ይመቸው እንግዳን በወሬ ከማድረቅ በፊት ምግብ ሲቀርብ ነው ሙድ ያለው...ጥጃ ማረደም አያስፈልገም ነበር ግን የእብራሂም ቸረነት እስከዚህ ነበር ፡፡ ቸረነት የነቢያት ና የመልክተኞች መለያ ነት፡፡ ኢብራሂም ምግቡን ካቀረበ በኋላ እጃቸውን ቢያይ ቢያይ ምንም ወደ ምግቡ አይዘረጉም። ይህን ግዜ ኢብራሂም በልቡ ፍራቻ አደረ። ሊዘርፉኝ የመጡ ሌቦች ናቸው!!!? ወይስ ሊገድሉኝ..!!? ወይስ ሚስቴን ሊተናኩሉ ነው..!!? እያለ ይጨነቅ ጀመር። አላተዕ ኩሉን(አትበሉም እንዴ ሲላቸው) አዎ ስጦታን አነቀበለም ገዝተን ካልሆነበቀር አንበላም አሉት የባላል፣ ዋጋዉን ክፈሉና ብሉ አለቸው፡፡ መላእክትም ዋጋው ስንት ነው ብለው ሲጠየቁት፣ ዋጋው መብላት ከመጀመራቹህ በፊት ብስሚላህ ማለታቹህ እና ስታጠናቅቁ ደግሞ አልሀምዱሊላህ መለታቹህ ነው አላቸው። በዚህም ግዜ ከሊሉረህማን የአረህማን ወዳጅ ብሎ ላንተ ስያሜ መሰጠቱ ተገቢነው አሉት። ኢብራሂምም፦"ምን ፈልጋችሁ ነው እነ ማን ናችሁ?" ብሎ ጠየቃቸው። ወጣቶቹም፦ አትፉራ "እኛ ከሰማይ የመጣን መላዕክቶች ስንሆን ላንተ ልጅ እንደምትወልድ ልናበስርህ እና የሉጥን ህዝቦች ልናጠፋ ነው የመጣነው" አሉት! ይሁን ሁሉ ንግግራቸውን ስትሰማ የነበረችው ሳራ ቁማ ነበር እና ከት ብላ ሳቀችም። ለምን ነበር የሳቀቺው? ገና በልጅ ዜና ሰትበሰር በፊት ነበር። ኡለማ እንደተናገሩት የሰቀችበት ምክኒያት የሉጥ ህዝቦች እንደሚያጠፉ በመስማቱዋ ነው ብለዋል።ያም እነሱ ምደረን በጥፋት መድረስ በመሆነቸው ሳቢያ ነው። እንደ ሚጠፉ ስሰማ ነው የሳቄቸው ብለዋል። ኢብራሂም ሚያላግጡበት መስሎት በመገረም፦"ይህ እንዴት ይሆናል? እኔ እኮ የጃጀው ሽማግሌ ነኝ" አላቸው። እነሱም፦"ይህ የጌታህ ትዕዛዝ ነው እሱ ባሻው ነገር ላይ ቻይ ነው" ብለው መለሱለት። መላዕቱም ወደ ሳራ ዞሩ'ና፦"አንችም ኢስሀቅ የተባለን ነቢይ ትወልጃለሽ" አሏት። ሳራም በጣም በመገረም አፏን ይዛ፦"ይህ ግን እንዴት ይታሰባል ኢብራሂም እኮ የጃጀ ሽማግሌ ሲሆን እኔም መሀን ነኝ" ስትላቸው። መላዕክቱም ምንም እንኳን ሳራ መሀን ብትሆን እና ኢብራሂምም ሽማግሌ ቢሆንም አላህ ልጅ በቅርቡ እንደሚሰጣቻው እና ያ ልጅም ወደፊት ነቢይ እንደሚሆንም አክለው አረጋገጡላቸው። እና መላዕክቱም ጉዞ ወደ ሰዶማውያን ጀመሩ።(በነገራችን ላይ ሉጥ ከኢብራሂም ከተለያየ በኋላ ሰዶም ወደተባለ ሀገር በመሄድ ዳዕዋ ማድረግ ጀምሯል።ይህን ደሞ ነገ ምንዳስሰው ይሆናል። ብዙም ሳይቆይ ወደመካ በተጎዘበት ግዜ ዳግም ሌላ ትዕዛዝ ከጌታው በኩል መጣለት፦"ከልጅህ ጋር በመሆን ልጅህ በሚገኝባት ከተማ እኔ ምመለክበትን ቤት(ካዕባ) ስራ" የሚል ነበር ትዕዛዙ። ኢብራሂምም ለጌታው ታዛዥ በመሆን ልጁን ሲያማክረው ልጁም መርሀባ ይለውና ማቴርያል አሰባስበው ግንባታ ጀመሩ። ኢብራሂም እላይ ሲክብ ኢስማዒል ደሞ ከታች ድንጋይ ያቀብለው ነበር። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ፦"ጌታችን ሆይ! የምንሰራውን ተቀበለን አንተ ሰሚም አዋቂም ነህ" በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር። አሁን የታዘዙትን ቤት ሰርተው አጠናቀዋል ኢብራሂምም ከቤቱ ጎን በመቆም፦" ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን። ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና...ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ። ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለምእመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማር" በማለት ዱዐ አደረገ። በግን ባታው ላይ እያሉ ወደ መዐዘኑ ሲደርሱ እበራሂም ዐለይሂሰላም የህ መዐዘን ከሌለ የተለየ እንዲሆነና የተቀረው ግንባታ ከርሱ እንዲቀጥል ፈለገ ከዚያም እስማኢልን ከዛ መዐዘን የሚገጥም ደንጋይ እንዲፈለግ አዘዘው፡፡ እስማኢለም አባቴ ሆይ ደክሞኛል አለው ተነስ አለው ምንም እንኳ የደከመ ቢሆነም አባቱ በዘዘው ግዜ ቆመና ድንጋይ ሊፈለግ ጀመረ ፈለገ ፣ ፈለገ፣ ፈለገ ግን ለዚያ መዐዘን የሚሆን ዲንጋይ ሊገኝ አልቻለም። ተመለሰ ከዚያን አንደ እጅግ ነጭ የሆነ ድንጋይ በመዐዘኑ ላይ ተቀምጦ አየ፣ እብራሂም ዐለይሂሰላም ግንባተውን እያገባደደ ተመለከተ፣ ክፍል 5 ይቀጥላል.. #share https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

👍 3
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿••• #ክፍል 3 አሁን የሳራ እንግልት ከወደ ውስጥ በኩል ጀምሯል....ንጉሱ ሊተናኮላት ሲሞክርም፦"ጌታዬ እኔ ባንተ ያመንኩ ስሆን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ። ይህንንም ንጉስ እኔ ላይ ስልጣን አትስጠው" እያለች አላህን ተማፀነችው። ንጉሱም እጁን ወደ ሳራ ሲዘረጋ እዛው በዘረጋበት እጁ ደርቆ ቀረ።ያን ግዜ ንጉሱ በከፍተኛ ሁኔታ መጮህ ሲጀምር ሳራም ይህ ንጉስ ከሞተ ወታደሮቹ እሷንም እንዷይገድላት ሰግታ አላህን ለመነችው። አላህም የንጉሱን እጅ ሲለቅለት ንጉሱ ከመጀመሪያው ፀያፍ ተግባር አልተማረም ነበር።ዳግም እጁን ወደ ሳራ ላከ....ሳራም እንደመጀመሪያው ጌታዋን ተማፀነች።የንጉሱ እጅም በቦታው ደረቀ። ያን ግዜ ንጉሱ በከፍተኛ ሁኔታ መጮህ ሲጀምር አሁንም ሳራም ይህ ንጉስ ከሞተ ወታደሮቹ እሷንም እንዳይገድላት ሰግታ አላህን ለመነችው። አላህም የንጉሱን እጅ ሲለቅለት ንጉሱ ከመጀመሪያው ውዳቂ ተግባር አልተማረም ነበር።ዳግም እጁን ወደ ሳራ ላከ....ይህን ግዜ አላህ የንጉሱን መላ ሰውነት ፓራላይዝድ አደረገው።ንጉሱም ዳግም ላይተናኮላት ቃል ገብቶላት አላህም ለቀቀው። ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ሰው ናት ብላችሁ ሸይጣን ታመጡልኛላችሁ እንዴ!!! በሉ አንድ አገልጋይ ስጧት'ና ከዚህ አስወጡልኝ" አላቸው። አሁን እነኢብራሂም ሁለት ሆነው የገቧትን ከተማ ከአገልጋይቱ ሶስት ሆነው ወጡ። በነገራችን ላይ ሳራ ምንም እንኳን ቆንጂት ብትሆንም መውለድ ማትችል(መሀን) ነበረች። ኢብራሂምም እድሜውን ዳዕዋ ላይ ብቻ በማሳለፍ እድሜውን ፈጅቶ ሸምገልገል ብሏል።ሳራ አንድ ቀን ኢብራሂምን፦"አንተ እድሜህ ገፍቷል እኔም እንደምታየው መውለድ አልቻልኩም።ስለዚህ ይህችን አገልጋያችንን አግባት'ና ልጅ ውለድ" አለችው። ኢብራሂምም፦"ተይ ተይ...ሳራ እኔ እሷን ባገባ ትንሽ ቅናት ቢጤ ሊያገኝሽ ይችላል።በተለይ ደሞ ልጅ ስንወልድ...እኔ ደሞ አንችን ምንም እንዲከፋሽ አልፈልግም" ብሎ መለሰ ጁምሁሮች እዛ በመካ ሸለቆ ሰፈሩና ሃጀር የመኖሪያ ሁኔታ እንደዚህ ሆነ፡፡ ዘምዘምን ለእነዛ ሰወች እያከራየች በምታገኘው መተዳደር ጀመረች፡፡ እስማኢል በጁሩሁም ጎሳወች መሀከል አደገ፤ ከነሱም የነጠቀ አረበኛ ቋንቋ ተማረ፡ እንደውም ከሁለቸውም የበለጠ አንደበሩትዕ እስኪሆን ደረሰ፡፡እስሚኢለም ቆይቶ ከጁሩሁም ጎሳ የሆነችን ሴት ነው የገባው፡፡ አልዐዕአረቡ ሙስተዕሪባ ወደ አረብነት የተለወጡ በመባል የተሰየሙት የአረብ ትውልዶች ከኢስማኢል ትውልዶች ነቸው፡፡ ነቢዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከነዚህ ዚረያች መሃከል ነቸው፡፡ይህ የሆነው አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ የአብራሂምን ዐለይሂሰላም ጥረ (ዱዓ) በመቀበሉ ነበር፡፡ እብራሂም አለይሂሰለም በተጎዘና ሃጀር ከጠገቡ በተመለሰች ግዜ በቁረዐን የተጠቀሰውን ዱዓ ዐደረገ። ያጥሪ መልስ አገኜ ፦ ጌታችን ሆይ በተከበረው ቤትህ፡አጠገብ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ ከዝሪያወቼ አስፉረያለሁ አለ፡፡ የተከበረው ቤት በዘን ሰዐት ነበር እንዴ? እብራሂም ሃጀረን እዛ በስቀመጠበት ግዜ የተገነባ ቤት ነበረዴ ? አልነበረም ከዚያ በፊት ተገንብቶ የነበረ ነው ወይነስ ቦታው ብቻ ነበር የሚታወቀው፤ በዘመህ ዙሪያ ሁለት ዘገባወች አሉ፣ እንዴኛው ቦታው ብቻ ነው የሚታወቀው ሌሌኛው ደግሞ ከዚያ በፊት የአደም alehesalam ልጅ ሺስ ገብቶት ነበረና ከግዜ ረዝመት እና ቆይታ ቡሇላ ነው የፈራረሰው የሚል ነው ሁለተኛው፡፡ አለህ ሱበሃነሁ ወተዓላ የተባረከ ሲሆን ሰወች የመልኩበት ዘንድ የሰወች መጀመሪያ የተቀመጠላቸው ቤት በመካ የለው ነው ሰለሚል ሺስ ገንብቶት መሰረቱ ነበር የሚለውን ዘገባ ጠንካራ ነው፡፡ እብሪሂሚም ከጥሎ ዱዓውን ጌታዬ ሆይ ሶላትነም እንዲያቋቅሙ ከሰወች ወደ እነርሱ የሚያዘነብሉ ልቦችን አድረግ ሊያመሰግኑህም ዘንድ ከፈራፈሬወችም መግባቸው ብለው ዱዓ አደረጉ። በተግባረም ተለውጦ የጁሩሁም ጎሳወች ሃጀር አከባቢ ሰፈሩ። ቀናት አመታት አልፎ እስማኢል በጁሩሁም ውስጥ ወጣት ሆነ። ከረጅም ግዜ በኋላም ኢብራሂም ልጁን ኢስማዒልን እና ሚስቱን ሀጀርን ከምን እንደደረሱ ለማጣራት ያስቀመጣቸው ቦታ ሲመጣ ቦታውን ሊያውቅ አልቻለም። ምክንያቱም ያኔ ሲመጣ አከባቢው ምንም አይነት ነፍስ ያለው ነገር የማይኖርበት ምድረ በዳ ነበር። አሁን ግን ቤቶች ተገንብተዋል...የብዙ ተጓዥ ነጋዴዎችም ማረፊያ ከተማ ሆኗል። ይህን ሲያይ መንገድ ተሳስቼ ይሁን እያለ ያሰላስል ጀመር።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ የአከባቢውን ሰው ሀጀር ስለምትባል ሴት ሲጠይቁት ከነ ቤቷ ጠቆሙት። ኢብራሂምም ቤቷ ሲሄድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ከልጇ ጋር ተመለከታት...እንባ ተናነቀው...ሁለቱንም ለረጅም ሰዐት አቀፏቸው ያለቅስም ጀመር። ከዚያ በዚህ ሁኔታ ከተገናኙ በኋላ ኢብራሂም ወደ መጣበት ተመለሰ። ምንም እንኳን የልጁ ኢስማዒል እና የሚስቱ ፍቅር እንደ አዲስ በውስጡ ማንሰራራት ቢጀምርም በመሀከላቸው ካለው ርቀት አንፃር በፈለገ ሰዐት እየመጣ ሊዘይራቸው ምቹ አልነበረም'ና ሁሌ በአመት አመት ሊያያቸው መምጣት ጀምሯል። ኢብራሂም ዐለይሂሰለም ሰላም፡በዐማት አንድ ግዜ ከሃጅር ጋ በመካ የለውን እስማኢልን ይጠይቅ ነበር፤ አንድ ታላቅ ክስተት እስከመጣበት ግዜ ደረስ በዚህ ሁኔታ ላይ ዘወተረ፡፡ ኢብራሂም አለይሂሰላም መካን በጎበኘበት በአንደኛው ጉብኝት አስማኢል ሊጎበኝ በመጣበት፡በመካ ተኝቶ ሳለ በእንቅለፉ ውስጥ ህልም(ራኢይ ተየው) "ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅን ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ ሰማ'ና ደንግጦ ተነሳ። ከዚያም፦"ጌታዬ ኢስማዒልን እንዳርደው ምትፈልግ እንደሆን ታዛዥህ ነኝ" ብሎ ተመልሶ ተኛ። አሁንም እንቅልፍ ትንሽ ሸለብ እንዳደረገው፦"ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅህ ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ በህልሙ ተሰማው። አሁንም ደንግጦ ተነሳ'ና ረክዐተይን ሰግዶ አላህ ትዕዛዙን ግልፅ እንዲያደርግለት ዱዓ አድርጎ ተመልሶ ተኛ። አሁንም ልክ እንደተኛ ለሶተኛ ግዜ፦" ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅህ ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ ሲሰማ ኢብራሂም የነቢያት ህልም ውሸት እንደል ሆነ ስለሚያቅ ቅዠት የማታዝል እና ሸይጣነም ተመስሎ እነደማይቀርበበት በረግጥ ያውቅ ነበር እናም የጌታው ትዕዛዝ ምንም እንኳን ለህሊና ሚከብድ ቢሆንም ኢብራሂም ሊፈፅም ወሰነ። ኢስማዒልን ብቻውን ሊያናግረው ወጣ አድርጎ፦"ልጄ አንተን እንዳርድህ ጌታዬ በህልሜ አዞኛል ምን ትላለህ!?" አለው። ኢስማዒል፦"ዞር በል ከዚህ. ስንት አመት ጥለኸኝ የትም የትም ብዬ ካደግኩ በኋላ አባትህ ነኝ ብለህ ስትመጣ መቀበሌ አንሶህ ልረድህ ትለኛለህ እንዴ!!!" አላለውም ነበር። ነገር ግን በእናቱ መልካም ተርቢያ ያደግው የመልካም ስነምግባር ባለቤት የሆነው ኢስማዒል፦"አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ፈፅም አሏህ ካለ እኔንም ከተጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ" ነበር መልሱ።አሁን ኢብራሂም ልጁን ሊያርድ ዝግጅቱን ጀምሯል። ኢስማዒለም አበቴ ሆይ ልታርደኝ ከፈለክ ግንባሬን መሬት ላይ ድፋው የሂን ያልኩበት ምክኒያት ፊቴን አይተሄው ረህራሄ እንዳይዝህ ብዬ ነው አለው፡፡ ተመልከት ጭንቀቱን ሊያቀልለትና ነገረን ሊያገራለት ሲፈልግ ነው፡፡ ክፍል 4 ይቀጥላል.. #share https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

👍 2
' •••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿••• #ክፍል 2 ከዚያም ህዝቡ ሙሉ ለሙሉ መሰብሰቢያው ቦታ ሲሆድ እሱን ለምን እንደማይሄድ ሲጠይቁት፦"አሞኛል" ይል ነበር። በመጨረሸም ሰዉ ሁሉ ከተማይቷን ለቅቆ ወደመሰብሰቢያው ሄደ'ና ኢብራሂም ብቻውን በከተማይቱ ቀረ። አሁን ልበ ሙሉው ኢብራሂም ሀሳቡን ሊያሳካ ጉዞ ወደ ቤተ አምልኮ ጀምሯል...ልክ ጣኦታቱ ያሉበትን በር ሲከፍተው ቤተ አምልኮው ከተለያዩ እንጨቶች እና ድንጋዮች በተሰሩ ጣኦታት ተሞልቷል። ኢብራሂም ምንም አልፈራም ዘልቆ ወደ ውስጥ ገባ።ከዚያም በጣኦታቱ አጠገብ በቁርባን መልኩ የተደረደረውን የምግብ መዐት ተመለከተ'ና ጠኦቶቹን፦"አትበሉም እንዴ!!!" አላቸው እየፎገረ... አሁንም በመሀከላቸው ትንሽ ተዟዟረና፦…………… "ምንድነው...!! !መልሱልኛ ማውራትም አትችሉም እንዴ!!" አላቸው። ምንም ሚመልሱት ነገር የለም። በእጁ በያዘው ፋስ እያንዳንዱን የድንጋይ እና የእንጨት ቅርፃ ቅርፅ ብትንትኑን አውጥቶ አንድ ትልቁን ጣኦት ብቻ ተወው'ና ሌሎች ጣኦታትን የቆረጠበትን ፋስ በትልቀኛው ላይ አሸክሞ ሰዉ ከተሰበሰበበት ሳይመጣ ኢብራሂም ቤተ አምልኮውን ትቶ ወጣ። ህዝቡ ገና ከተማ ከመግባቱ አማልክቱ ጋር ሊሳለም ሲገባ ሁሉም አይናቸውን ማመን እስኪያቅታቸው ድረስ ያዩት ነገር አስደነገጣቸው። ህዝቡ ባጠቃላይ ክፉኛ ተቆጣ...ይህን ተግባር የተገበረውንም ሰው አይቀጡ ቅጣትንም ለመቅጣት መዛት ጀመሩ። ግን ነገሩን በጥልቀት ሲመረምሩት ከኢብራሂም ሌላ ማንም እንዲህ ሊያደርግ እንደማይችል በመገመት ኢብራሂምን ለፍርድ ለማቅረብ ፍለጋ ተጀመረ..... ብዙም ሳይፈልጉት ነበር ኢብራሂምን አግኝተው ለፍርድ ያቆሙት። ዳኛውም፦"ይህን አሳፋሪ ተግባር በአማልክቱ የፈፀምከው አንተ ነህ እንዴ?" ኢብራሂም፦"አረ እኔ አይደለሁም ይሄ ትልቀኛው ነው እሱም ጠይቁት እንጂ...በዛ ላይ ፋስ ተሸክሟል እራሱ ነው የፈጃቸው። ከፈለጋችሁ ጠይቁት"አላቸው። ህዝቡ፦"እንዴት መናግር እና መስማት የማይችልን ጣኦት ጠይቁት ትላለህ!!!" ኢብራሂም፦"አያችሁ መናገር እና መስማትን የማይችሉ ጣኦታትን ነው እያመለካችሁ ያላችሁት።ግን ትንሽ አታስተነትኑም!!!" ኢብራሂም እችን ሲናገር ሁሉም ጥፋት ላይ መሆኑን ተረድቶ ቀዘቀዘ። ነገር ግን ሸይጣን አስውቦ ገለፀላቸውና ወደ ጥመታቸው በመመለስ ኢብራሂምን ለሰራው ቅጣት ይሆን ዘንድ በእሳት ለማቃጠል ትዕዛዝ አስተላለፉ። አሁን ኢብራሂምን ለማቃጠል ማገዶ ለቀማ ተጀምሯል...እያንዳንዱ ነገድ በርካታ ማገዶ እንጨቶችን ሰብስቦ መከመርም ጀምሯል። በመጨረሻም ኢብራሂምን ለማቃጠል የተከመረው የእንጨት ብዛት ትልቅ ተራራን አከለ። ከተለያዩ አጎራባች ሀገራት የኢብራሂምን አስከፊ እና ዘግናኝ ቅጣት ለመመልከት ወደ ባቢሎን ከተማ ሰዉ መጥቷል። እሳቱ መቀጣጠል ሲጀምር የእሳቱ ነበልባል በሰማይ በራሪ አዕዋፋትን እየጠበሰ ይጥላቸው ነበር።እንግዲ በዚህ ውስጥ አሁን ኢብራሂም ሊገባ ነው። እሳቱ በጣም ከተፋፋመ በኋላ አይደለም ኢብራሂምን ለማስገባት ይቅርና ራቅ ብሎ እንኳን ወደ እሳቱ ድንጋይ ለመወርወር ነበልባሉ አይሰጥም ነበር። ይህን ግዜ ሸይጣን በሰው ተመስሎ መጣ'ና አንድ መፍትሄ ሹክ አላቸው።እሱም መስፈንጥር በመጠቀም ኢብራሂምን ወደ እሳቱ ማስፈንጠር እንዳለባቸው ነገራቸው። ከዚያም ያ የተባለው መስፈንጥር ተዘጋጀ'ና ኢብራሂምን ወደ እሳቱ ለመወርወር ማስፈንጠሪያው ላይ አስቀመጡት። ልክ ኢብራሂም እዛ ላይ ቁጭ ብሎ ሳለ ጂብሪል መጣ'ና፦"ምትፈልገው ነገር ካለ እኔ ልርዳህ...ከፈለግክም እሳቱን ላጥፋልህ" አለው። ኢብራሂምም፦"አይ ዛሬ እርዳታን ከአላህ ብቻ ነው ምፈልገው" ብለው መለሱለት። በመስፈንጥሩ ኢብራሂም ወደ እሳት ሲወረወር እዛ የተሰበሰበው ህዝብ ሁላ፦'እሳት ትገባላችሁ እያለ ይዝትብን የነበረው ሰውዬ ቀድሞ እራሱ ገባ አይደል!!" እያለ ማላገጥ ጀመረ። ነገር ግን በአላህ ልዕልና እና በሁሉ ነገር ቻይነቱ እሳትን፦"አንች እሳት ሆይ!!! ኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ እና ሰላም ሁኚለት" በማለት ትዕዛዙን አስተላለፈ። ከረጅም ርቀት በማስፈንጠሪያ ወደ እሳቱ የተወረወረው ኢብራሂምም ልክ እሳቱ ውስጥ ሲገባ ከላይ እሳት ሆኖ የታየው ውስጡን እንደ ጀነት ሆኖ አገኘው። እሳቱ ተፋፍሟል ህዝቡ በደስታ እራሱን አያውቅም።በመጨረሻም እብራሂም ሞቷል ብለው ሁሉም ተበታተኑ እሱቱ ግን ይባስ እየተፋፋመ ነው። የኢብራሂም እናት ቁጭ ብላ የልጇን መጨረሻ በመጠባበቅ ላይ ሳለች ድንገት ከነበልባሉ ውስጥ ልጇን ኢብራሂምም ተመለከተች። ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦"ኢብራሂም....እኔ ወደንተ ልመጣ እፈልጋለሁ ጌታህን ለምንልኝ'ና አንድ ግዜ ልምጣ" አለችው። ኢብራሂምም መንገድ እየጠቆማት፦"ነይ በዚህች በኩል" አላት። እሷም እየፈራች ትንሿን መንገድ ይዛ ወደ ልጇ ገሰገሰች።መሀል ከደረሰች በኋላም እሳቱ ሲንቀለቀል ስታይ፦"ኢብራሂም ፈርቻለሁ"አለችው።  (ወይ እናት!!!) ኢብራሂምም፦"እናቴ እሳቱ እኮ አያቃጥልም ዝም ብለሽ ነይ" ሲላት እሳቱ መሀል ደረሰች'ና ያብራኳን ክፋይ በእቅፏ አስገባችው። በሁለት እጆቿ አቅፋው እየሳመችው ፊቱን ትጠራርግ'ና ዳግም ወደ እቅፏ ታስገባዋለች።ለተወሰኑ ሰዐታት አብራው ካሳለፈች በኋላ ኢብራሂምም ወደ ህዝቧ እንድትመለስ ያዝዛትና ለመመለስ ስትሞክር እሳቱን ይበልጥ ተፋፍሞ አገኘችው። ወደ ልጇ ዞራም፦"ልጄ በጌታህ ይሁንብህ ጌታህን ለምንልኝ'ና አሳልፈኝ"አለችው።ኢብራሁምም ዱዓ አደረገና እናቱን እንድትሻገር አደረገ።እናትየውም ልክ የእሳቱን መውጫ ጫፍ ላይ ስትደርስ፦"ልጄ ሰላም ሁን" ብላው ወጣች። በነጋታው የከተማይቱ ነዋሪ እሳቱ ጋር መጥተው ሲያጣሩ እሳቱ እንደነበር ነው ምንም አልቀነሰም።በዚህ ሁኔታ ኢብራሂም ለ40 ቀናት እሳት ውስጥ አሳለፉ። በመጨረሻም እሳቱ ሲጠፋ ህዝቡ ግር ብሎ መጣ።በዚህ አጋጣሚ ነበር ኢብራሂም ከመጀመሪያ ውበቱ 70 እጥፍ ጨምሮ ከእሳቱ ሲወጣ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ሸይጣን መስሎት ኡኡኡ....ያለው። ኢብራሂም ሲከተላቸው እነሱ ሲሸሹ ሩቅ ከተጓዙ በኋላ አላህ እሱን አድኖት እነሱን አጠፋቸው።የኢብራሂም በእሳት 40 ቀን ቆይቶ በሰላም የመውጣቱ ነገር በተለያዩ ሀገራት ለአመታት የሰው ልጆች መነጋገሪያ ሆኖ ከረመ። ኢብራሂም ምንም እንኳን የዳዕዋ ጥሪያቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም ሳራ እና ሉጥ ከተባሉ ሁለት ሰዎች በላይ ተከያይ ሊያፈሩ አልቻሉም ነበር። ኢብራሂምም ሚስቱ ሳራን እና ሉጥን ይዞ ወደ ሌላ ሀገር ለመሰደድ ወሰነ።ከባቢሎን ምድር ብዙ ተጉዘው ፊለስጢን ደረሱ። በዚያ ዘመን ፊለስጢንን የሚያስተዳድረው የግብፅ ንጉስ ነበርና ሳራ የምትባል በጣም ቆንጅዬ ሴት በግዛቱ ውስጥ እንደምትገኝ በወሬ ደርሶት ወታደሮቹ እሷንም አብሯት ያለውንም ሰው እንዲያቀርቡለት አዘዘ። ሁለቱም በወታደሮች ተከበው ወደ ቤተ መንግስት በመሄድ ላይ ሳሉ አንድ ነገር ተመካከሩ።ኢብራሂም ባሏ ነኝ ብሎ ከተናገር ስለሚገድሉት ወንድሟ ነኝ ሊል ወሰኑ። ሌላው የአላህ ስራ ነው ብለው ኢብራሂምን ወደ እንግዳ ማረፊያ አስገብተው ሳራን ለንጉሱ አሳልፈው ሰጡ። ኢብራሂምም ምኗ ነህ ተብሎ ሲጠየቅ ወንድሟ ብሎ በመመለሱ ከሞት ተርፏል።አሁን የሳራ እንግልት ከወደ ውስጥ በኩል ጀምሯል....ንጉሱ ሊተናኮላት ሲሞክርም፦"ጌታዬ እኔ ባንተ ያመንኩ ስሆን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ። ክፍል 3 ይቀጥላል.. #share https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

👍 1
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿••• #ክፍል 1 #ኢብራሂም #(ኡሉል-ዐዝም)ከተባሉት ከአምስቱ ከበርት ነቢያቶች አንዱ ናቸው።      ኢብራሂም ከጣኦት አምላኪያን ቤተሰቦች ነው የተወለዱት።አንዱ ድንጋይ ጠርቦ ያመልካል፣ከፊሉ ፀሀይን እና ኮከብን ያመልካል፣ሌላው ደሞ ንጉሶች ያመልካል። በዚህ የድንቁርና ዘመን ኢብራሂም ገና በልጅነታቸው ነበር የሰዉ ጅልነት ሚያስገርማቸው።ከምንም በላይ እሚገርመው የኢ ብየ አባት ነበር ለከተማይቱ ህዝብ የተለያዩ ጣኦታትን እየሰራ የሚሸጥላቸው። በዚህም የተነሳ የነኢብራሂም ቤተሰብ እጅጉን የተከበሩ ነበሩ። በዚህች ድንቁርና በተጠናወታት ባቢሎን በምትባል ከተማ ኢብራሂም ከጣኦታት ሁሉ ታቅበው አደጉ።አሁን አሁን ኢብራሂም በጣም ማሰላሰል ጀምረዋል። ኢብራሂም ብቻውን ቁጭ ብሎ፦"እንዴት አባቴ ከእንጨት እና ከድንጋይ እየጠረበ የሚሽጠውን ግኡዝ ነገር ሰዉ ያመልከዋል !!! ሰዉ ጤና የለውም እንዴ !!! አይ... ! አይ... ! ነገሩ እንኳን እንዲህ አይሆንም። በእርግጠኝነት ጌታ ማለት ፍጥረታትን ይፈጥራል እንጂ ፍጥረታት እሱን አይፈጥሩትም።  እሺ እነዚህ አማልክት ምንም አይጠቅሙም አይጎዱም ካልኩ ታዲያ ፈጣሪ የታለ !!! እራሱስ ማን ነው?" በማለት ያሰላስላል ከእለታት አንድ ቀን ኢብራሂም ዐ ሰ እንደተለምዶዋቸው ቢቻቸውን ቁጭ ብለው ስለ ፈጣሪ ማንነት እና ምንነት እያሰላሰሉ ስለ ድንገት አይናቸው ጨለማ ውስጥ በሚምዘገዘግ ኮከብ ላይ አረፈ ኢብራሂምም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦"ይሄው ጌታዬን አገኘሁ። አዎ ጌታዬ በሰው እጅ አይፈጠርም እንደ ጣኦታትም ወድቆ አይሰበርም" አሉ።          በጣም ተደሰተ ከደስታው ብዛት ለዚያ ኮኮብ ሌሊቱን ሙሉ ሲሰግድ አደረ።በዚያ ሌሊት ትክክለኛውን ጌታ እንዳገኘ ለህዝቡ ሁሉ ተናገረ።ሌሊቱን ሲሰግድ ካነጋ በኋላ ድንግት ጠዋት ላይ ቀና ሲል ያ ጌታ የመሰለው ኮከብ በብርሀን ተሸፈኖ ጠለቀ። አሀ...አሁን ማታውን ሙሉ ሲሰግድ ያሳለፈው ለትክክለኛ ጌታ እንዳልሆነ ተገነዘበ።ከዚያም፦"እኔ ጠላቂዎችን አልወድም" አለ። ኢብራሂም አሁንም ግን ተስፋ አልቆረጠም።ጌታውን ፍለጋ ዳግም አጠናክሮ ቀጥሏል።በሁለተኛውም ቀን ኢብራሂም በማታ ብቻውን ቁጭ ብሎ ስለ ጌታው እያሰላሰለ ሳለ ወደ ላይ ቀና ሲል የሰማዩን ፅልመት በብርሀኑ የገፈፈ ውብ ጨረቃ ተመለከተ። አሁን ትንሽ ከመጀመርያው ረጋ አለ'ና፦"ትክክለኛ ጌታዬማ ይህ ነው እንዴት ግን እስካሁን አላየሁትም!!!" ሲል ከራሱ አወራ። የዛሬዋን ግን እንደትናንቱ እየሰገደ አላደረም ትንሽ ቆይቶ ተኛ።ጠዋት ላይ ጌታዬን ልየው ብሎ ሲያንጋጥጥ ጨረቃው ተሰውሯል። ኢብራሂምም እጅጉን አዘነ እዛው ባለበት ሆኖም፦"ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ እራሱ ካልመራኝ ከተሳሳቾች እሆናለሁ" አለ።       ተስፋ ቆርጦ በባይተዋርነት ውጭ ላይ ቁጭ ብሎ ሳለ ፀሀይን ተመለከተ።በጣም ግዙፍ ናት፣ከጨረቃ እና ከኮከብ ስትነፃፀር በጣም ጎልታ ታየችው። ኢብራሂምም ፦"ጌታዬን አገኘሁ ይህ ትክክለኛው ጌታዬ ነው በዛ ላይ ከሁሉም ይገዝፋል" ብሎ ቀኑን በደስታ አሳለፈ። በመጨረሻም ፀሀይ ወደ ጀምበሯ ስትቃረብ ዘውታሪ አለመሆኗን ተረዳ።ጌታ ሁሌም ያልለ መሆኑን ተገነዘበ እንዲህም አለ፦"ወገኖቼ ሆይ !! እናንተ ከምታጋሩት ነገር እኔ ነፃ ነኝ" አሁን ኢብራሂም ሁሉ ነገር እየተገለፀለት መጥቷል..ጨረቃም፣ፀሀይም ፣ኮከብም አንድ አስተናባሪ ጌታ እንዳላቸው እና እነሱም ጌታ እንዳልሆኑ ተረዳ። ያ ጌታ ደሞ በአይን ሊታይ እንደማይችልም ተገንዝቦ በዛ የፍጥረተ አለሙ ጌታ በሆነው አላህ አመነበት።      አሁን ኢብራሂም ከድንቁርና ወጥቷል...ቀጣይ እቅዱ ህዝቡን ከድንቁርና ለማውጣት ቢሆንም ቅድሚያ ለአባቱ መስጠት እንዳለበት ተገንዝቧል። አባቱ ዘንድም ሄደ'ና፦"አባቴ ሆይ! ለምንድነው እነዚህን የማይጠቅሙ አማልክትን ጌታ አድርገህ የምትገዛው? እስቲ አባቴ ተመልከት እነኚህ አማልክት... ምንም አያዩም አይሰሙም እንዴት በነዚህ ታምናለህ። አባቴ ሆይ!! ፈጣሪያችን አላህ ነው። ልናየው አይቻለንም እሱን ብቻ ነው ልንገዛ የሚገባን።ይህም ብቻ ነው ቀጥተኛው መንገድ" በማለት አባቱን ጥሪ አደረገለት። ያን ግዜ አባቱ ቁጣው ገነፈለ..."ይህ ብላቴና እንዴት እድሜ ልኬን ካመለክኩት ጣኦት ተው ይለኛል" ብሎ በጣም ተናደደ።      ኢብራሂምም፦"አባቴ ! ላንተም ለወገኖችህም ሸይጣን ነው ይህንን መንገድ አስውቦ ሚያሳያችሁ። በምትፈፅሙት ሺርክ ከዝወተራችሁ መመለሻችሁ ወደ እሳት ይሆናል" እያለ በመለማመጥ ወደ አላህ ይጠራቸው ጀመር። ከዚያም አባትየው በጣም በመቆጣት ካሁን በኋላ ግን ሊመታው፣ሊገድለው፣በድንጋይም ሊወግረው እንደሚችል አስጠንቅቆ ኢብራሂምን ከቤት አባረረው።       ኢብራሂም አባትየውን መምከር ምንም ጥቅም እንደሌለው በተረዳ ግዜ፦……… "ሰላም ሆንልኝ።ጌታዬንም ላንተ ምህረት እንዲያደርግልህ እለምነዋለሁ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነው'ና" ብሎት ቤቱን ትቶ ተሰናበተው። በቃ አሁን የዳዕዋው ጥሪ ከቤት ወጣ ለመላው ህዝብ ይሰራጭም ጀመር። ኢብራሂምም ከአላህ ሌላ ምንም አምላክ እንደሌለ እና ሌላ አማልክትም ምንም እንደማይፈይዱ በየሄደበት ማውራት ጀመረ። ይህ የኢብራሂም ጉዳይ ቀስ በቀስ የከተማዋ ወሬ ሆነ።በዘመኑ ሀገሪቷን ይመራ ለነበረው እና ከአማልክቱ አንዱ አካል ለሆነውም ኑምሩድ ይህ ወሬ ደረሰው። ኢብራሂምንም እንዲያቀርቡለት ወታደሮቹን አዘዘ። ኢብራሂምም ከንጉሱ ፊት ቆመ። በሀገሪቱም ሆነ በመላ አለም የሚመለኩ አማልክት ሁላ እንደማይጠቅሙ እና እንደማይጎዱ በድፍረት አስረዳው።አላህ ህያው የሚያደርግ እና የሚገድል ጌታ መሆኑንም አክሎ ነገረው። ንጉሱም፦"እኔ መግደልም ህያው ማድረግም እችላለሁ" አለው። ኢብራሂምም፦"እንዴት?" አለው። ያን ግዜ ንጉሱ ሁለት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን እስረኞች እንዲቀርቡ ካደረገ በኋላ አንዱን በመግደል አንዱን በመተው፦"ይኸው እገድላለሁም ህያውም አደርጋለሁ" ብሎ ተመፃደቀበት። ኢብራሂምም፦"አላህ ፀሀይን ከምስራቅ አስወጥቶ በምዕራብ ያስገባታል።እስቲ አንተ ጌታ ከሆንክ ከ ምዕራብ እስወጣት"ሲለው ንጉሱም በሀፍረት አንገት ደፋ። ነምሩድ ስለተባለው ንጉስ ወደፊት እናያለን ኢንሻ አላህ የኢብራሂምን ጥሪ ለማሰናከል ሲሞክር አላህ እሱንም ወታደሮቹንም በትንኝ አጠፋቸው።ከእለታት አንድ ቀን የሀገሪቱ ህዝብ ለአመታዊ በአል በጠዋት ወደ መሰብሰቢያ ቦታ መትመም ጀመሩ። ኢብራሂምም በዚህ አጋጣሚ አንድ ምርጥ ሀሳብ መጣላቸው'ና ለመፈፀምም ወሰኑ። ክፍል 2 ይቀጥላል.... #share https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

👍 2
...ላ አባትህ ነኝ ብለህ ስትመጣ መቀበሌ አንሶህ ልረድህ ትለኛለህ እንዴ!!!" አላለውም ነበር። ነገር ግን በእናቱ መልካም ተርቢያ ያደግው የመልካም ስነምግ ባር ባለቤት የሆነው ኢስማዒል፦"አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ፈፅም እኔንም ታጋሽ ሆኜ ታገኘኛለህ" ነበር መልሱ። አሁን ኢብራሂም ልጁን ሊያርድ ዝግጅቱን ጀምሯል።የኢስማዒልን እጅ ወደኋላ አድርጎ ካሰረ በኋላ በጀርባው ካስተኛው አይኑን ሲያይ ሆዱ አይችልም'ና በሆዱ አስተኝቶ ፊቱን ወደ መሬት በመድፋት የጌታውን ትዕዛዝ ተፈፃሚ ሊያደርግ ቢለዋውን በልጁ ኢስማዒል አንገት ላይ ሲያሳርፍ ከወደ ላይ በኩል፦"ኢብራሂም ሆይ !!! ህልሙን እውን አድርገሀል እኛም እንደዚህ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን" የሚል ድምፅ መጣ። ኢብራሂምም ቀና ሲል ከሰማይ አንድ መልዐክ ለኢስማዒል ቤዛ ይሆን ዘንድ ሙኩት ይዞ መጣ'ና፦"ኢስማዒልን ፈትተህ ይሄን እረድ" አለው። ከዚያም ኢብራሂም ደስታው ወደር አጣ...እየተቻኮለ የልጁን...የአብራኩን ክፋይ እጆች መፍታት ጀመረ።ከዚያም ከሰማይ የመጣለትን ሙኩት አረደው።ያን ቀን በማስመልከት ነው እንግዲህ በየዐረፋ በአሉ የእርድ ስነስርዐት ሙስሊሞች የምንፈፅመው። ኢብራሂምም ወደ ሀገሩ ተመልሶ ብዙም ሳይቆይ ዳግም ሌላ ትዕዛዝ ከጌታው በኩል መጣለት፦"ከልጅህ ጋር በመሆን ልጅህ በሚገኝባት ከተማ እኔ ምመለክበትን ቤት(ካዕባ) ስራ" የሚል ነበር ትዕዛዙ። ኢብራሂምም ለጌታው ታዛዥ በመሆን ወደ ልጁ ሄዶ ሲያማክረው ልጁም መርሀባ ይለውና ማቴርያል አሰባስበው ግንባታ ጀመሩ። ኢብራሂም እላይ ሆኖ ሲመርግ ኢስማዒል ደሞ ከታች ድንጋይ ያቀብለው ነበር።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ፦"ጌታችን ሆይ! የምንሰራውን ተቀበለን አንተ ሰሚም አዋቂም ነህ" በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር። አሁን የታዘዙትን ቤት ሰርተው አጠናቀዋል ኢብራሂምም ከቤቱ ጎን በመቆም፦" ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን። ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና... ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ። ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለምእመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማር" በማለት ዱዐ አደረገ። ይህን ትልቅ ቤትም ገንብተው ካጠናቀቁ በኋላ አላህም ኢብራሂምን፦"ሰዎች ከየሀገሩ በመምጣት ቤቴን ይጎብኙ ዘንድ ተጣራ" አለው። ኢብራሂምም፦"ጌታዬ እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ ድምፄ እኮ አይደርስም"አለው። አላህም፦"አንተ ተጣራ ማድረስ የኔ ስራ ነው" አለው። ኢብራሂምም ትልቅ ተራራ ላይ በመውጣት ተጣራ።ያን ግዜ ከየሀገሩ ያሉ ህዝቦች ጥሪውን በመቀበል መካ መጥተው ሞሉ። ኢብራሂምም የሀጅን ስነስርዐት ለሁሉም አስተማራቸው። ከዚያ በኋላ የኢብራሂም ሚስት ሳራ በከንዐን ምድር ሀብሩን በምትባል ቦታ በ127 አመቷ ዱንያን ተሰናበተች። ከዚያ በኋላ ኢብራሂም ለሳራ ልጅ ኢስሀቅ ሪፍቃ ቢንት በቱኢል የተባለችን እንስት አጭቶለት አጋባው። ከዚያም ኢብራሂምም ለራሱ ቀንጡራ የተባለችን ሴት በማግባት 1፦ዙምራን 2፦የቅሻን 3፦ማዳን 4፦መድየን 5፦ሺያቅ 6፦ሸውህ...የተባሉ ልጆችን ወለዱ። በመጨረሻም በ200 አመቱ #ኢብራሂም ዱንያን ተሰናበት....ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም _____ የኢብራሂምን ዐ ሰ ትረካ ስንዳስስ የኢስማዒልን እና የኢስሀቅን (ዐሰ) ትንሽ ነካ ነካ ማድረጋችን ይታወሳል። ስለዚህ በቀጣይ በአላህ ፍቃድ የሁለቱንም ትረካዎች በማያያዝ የምናቀርብላችሁ ይሆናል። ምንጮቻችን፦ ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ / ﺻﺤﻴﺢ ﻣﺴﻠﻢ ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ነብዩሏህ #ኢስማኢል እና #ኢስሀቅ ታሪክ ኢንሽአላህ ይ......ቀ.....ጥ.....ላ......ል፡፡ ሌሎች የነብያት፣ ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

....ምር ያዕቁብ ሙሽሪት ን ተመለከታት።ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት። ያዕቁብ በጣም ተናደደ.......          #የነብዩሏህ_ያዕቁብ_ታሪክ   ኢንሻአላህ https://t.me/Umete_Resul
Hammasini ko'rsatish...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

#ኢብራሂም ነብዩሏህ_ዒስማኢል እና #ነብዩሏህ_ዒስሃቅ አሁን ዒስማኢል (ዐሰ) ጎርምሷል፣ለሁሉ ነገር ብቁ የሆነ ወጣትም ሆኗል።ውሀ ፍለጋ መጥተው እዛው ኑሮዋቸውን ያደረጉት የጁርሀም ብሄረሰቦችም ኢስማዒልን እጅጉን ይወዱታልም። ቋንቋቸውንም አስለምደውት ባህላቸውንም አላብሰውታል።ለአቅመ አዳም መድረሱን በተመለከቱም ግዜ ከራሳቸው ዘር የሆነችን እንስትም ዳሩለት። ኢስማዒል (ዐ ሰ) ትዳር እንደያዘ እናትየው ሀጀር ብዙም ሳትቆይ ነበር ለፈጣሪዋ ነፍሷን ያስረከበችው።ኢስማዒልም ያለ አባት ያሳደገችው እናቱ ስትለየው እጅጉን ቢያዝንም ምላሹ ግን ዱዓ ብቻ ነበር። ምንም እንኳን የኢስማዒል አባት ኢብራሂም (ዐ ሰ) በዛ ግዜ ትልቅ ሽማግሌ ቢሆኑም የአብራካቸውን ክፋይ ለመጎብኘት ከፊለስጢን ምድር መካ ድረስ በየግዜው ይመላለሱ ነበር።ነገር ግን አሁን ትንሽ ሰንበትበት ብለዋል መካ ከመጡ... ልክ መካ እንደደረሱ ልጃቸው ቤት ሲገቡ የልጃቸውን ሚስት ያገኟታል።ኢስማዒል የት እንዳለም ሲጠይቋት ለአደን ከከተማ እንደራቀ ነገረቻቸው። እሳቸውም ቀጠል አድርገው ፦"ልጄ ኑሯቸሁ እንዴት ነው?" ብለው ሲጠይቋት እሷም፦"ኑሮዋችን በጣም ዝቅተኛ ነው..."በማለት ብዙ ስሞታ አቀረበች። እሳቸውም፦"በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ እንዲቀይርም ንገሪው" ብለዋት ትተው ሄዱ። ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ እንድትቀይር አዞሀል" ስትለው አባቱ መሆኑን አውቆ የበር መዝጊያ ደሞ ሚስቱን እንደሆነ በመረዳት ሚስቱን ፈታት። ኢስማዒልም ሌላ አዲስ ሚስት አገባ።ከእለታት አንድ ቀንም የልጃቸው ናፍቆት አላስቀምጥ ያላቸው ኢብራሂም ከ ፊለስጢን ምድር ልጃቸውን ሊያዩ ሲከንፉ መጡ። ቤት ሲደርሱ ሌላ ሴት ተመለከቱ'ና፦"ልጄ ኢስማዒል የት ነው" ብለው ሲጠይቋት እሷም፦"ለአደን ራቅ ወዳለ ቦያ ሄዷል ኑ ግቡ"አለቻቸው። እሳቸውም፦" ኑሮዋችሁስ እንዴት ነው?" ሲሏት እሷም፦"በጣም ጥሩ ነው ሁሌ ድሎት ሁሌ ምቾት ነው" ብላ መለሰችላቸው። እሳቸውም፦" በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ ጠበቅ አድርጎ እንዲይዝ ንገሪልኝ" ብለዋት ሄዱ። ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ ጠበቅ አድርገህ እንድትይዝ አዞሀል" አለችው። ኢስማዒልም አባቱ ይህችኛዋን ሚስቱን እንደወደዱለት ተረድቶ ይልቅ ያከብራትም ጀመር። ለዚያ አካባቢ እና በዙሪያዋ ላሉ ነገዶች፣ለአማሊቃዎች፣ለጁርሀሞች እና ለየመኖች በነቢይነት ሲያገለግል የነበረው ኢስማዒል (ዐ ሰ) ቀደምት አባቶቹ የቀመሱትን የሞት ፅዋ መቅመሻው ግዜ ሲደርስ ነስማ የተባለችውን ሴት ልጁን የወንድሙ የኢስሀቅ ልጅ የሆነው ዒስ እንዲያገባት ተናዝዞ በተወለደ በ173 አመቱ የሙታንን መንደር ተቀላቀለ።...{ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም} አሁን እግረ መንገዳችን የኢስሀቅን ህይወት ጎራ ብለን እንመልከት... ለኢስሀቅ አባቱ ኢብራሂም (ዐሰ) በህይወት ሳለ በ40 አመቱ ነበር ረፍቃ ቢንት በትዋዪል ከተባለች እንስት ትዳር ያስያዘው። ምንም እንኳን ረፍቃ መውለድ የማትችል መሃን ብትሆንም በባለቤቷ ያላሰለሰ ዱዓ ሁለት መንታ ልጆችን ለመታደል በቅታለች። አንደኛው፦ዒስ ሲሆን ሁለተኛው፦ያዕቁብ (ዐሰ) ይባላል። ዒስ የሮም ህዝቦች ቅድመ አያት ሲሆን፤ ያዕቁብ ደሞ የእስራኢላውያን ቅድመ አያት ነው። የሁለቱም አባት ሁለቱንም ልጆቹን በጣም ቢወዳቸውም ከያዕቁብ ይልቅ ለዒሱ ግን ለየት ያለ ቦታ ነበረው። እናታቸው ረፍቃ ግን ያዕቁብ ታናሽ ስለሆነ ይበልጥ እሱን ነበር የምትወደው። ኢስሀቅ ከእርጅና የተነሳ አይናቸው ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል። ከእለታት አንድ ቀን ኢስሀቅ (ዐሰ) ስጋ ያምራቸውና የሚወዱትን ልጃቸውን ዒስን አደን አድኖ ስጋ እንዲያመጣለቸው እናም ከባድ ዱዓም እንደሚያደርጉለት ነግረውት እሱም ለአደን ሄደ። ይህን በድብቅ ስትሰማ የነበረችውም የልጆቹ እናት ረፍቃ ለያዕቁብ ነግራው ከፍየሎቹ ወፍራሙን ሙኩት እንዲያርድ ካደረገች በኋላ የወንድሙን ዒስን ልብስ አልብሳው እራሱን(ዒስን) አስመስላ የሰራውን ስጋ ለአባቱ እንዲያቀርብ አደረገች። ያዕቁብም ያዘጋጀውን ምግብ ይዞ አባቱ ዘንድ ሲያቀርብ አባቱ፦"ማን ነህ አንተ?" አሉት። ያዕቁብም፦"ልጅዎት ነኝ"አለ። አባቱም(ኢስሀቅ)፦"ድምፅህ የያዕቁብ ነው፤ልብስህ ግን የዒስ ነው" በማለት የቀረበላቸውን ምግብ በሉት። ምግቡን በልተው እንደጠገቡም ምግቡን ላቀረበው አላህ ክብሩን ከፍ እንዲያደግለት፣ የበላይ ዘርም እንዲያደርገው፣ልጆቹንም ሪዝቁንም አላህ እንዲያበረክትለት ዱዓ አደረጉ። ልክ ዱዓውን እንዳጠናቀቁ ያዕቁብ አሚን ብሎ የአባቱን ክፍል ለቆ ወጣ።ያዕቁብም ሲወጣ ዒስ በታዘዘው መልኩ ያደነውን ስጋ ጠባብሶ ለአባቶ አመጣ'ና አቀረበ። አባቱ ግን ቅድሙኑ ጠግበዋል። ዒስ ምግቡን ሲያቀርብላቸው፦"ልጄ ይህ ምንድነው?" አሉት። ዒስ'ም፦"አምጣልኝ ያሉት ስጋ ነዋ" አላቸው። አባትየውም፦"አሁን አምጥተህልኝ በልቼ ዱዓ አላደረግኩልም እንዴ!!!"ሲሉት ወንድሙ ያዕቁብ እንደቀደመው እና ዱዓውንም ሸውዶ እንደተቀበለ በመረዳት ሀይለኛ እልህ ያዘው። ዒስ አባታቸው ኢስሀቅ ከሞተ ያዕቁብን እንደሚገድለውም ይዝትበት ጀመር።ያን ግዜ አባት ለልጃቸው ዒስ ማስተዛዘኛ ይሆም ዘንድ፦"አላህ ዝርያዎችህን ጠንካሮች ያድርጋቸው፣ፍራፍሬዎችን እና ሪዝቆቹንም አላህ ሰፋ አድርጎ ይስጥህ" በማለት ዱዓ አደረጉለት። ነገር ግን እናት ልጇ ያዕቁብ ላይ ሚዛተው ዛቻ እረፍት ነስቷት ስለነበር የዒስ ቁጣ እስኪበርድለት ድረስ ያዕቁብን ሀራን በሚባል አካባቢ ወደሚገኘው ወንድሟ (ላባን) ላከችው። ያዕቁብም ስንቁን ይዞ ወደ አጎቱ ላባን እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ መሸበት እና አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ፏ ያለ እንቅልፍ ተኛ። እዛው በተኛበትም በህልሙ ወደ ሰማይ መወጣጫ ይመለከታል።በዚያ መወጣጫ መላዕክት ይወጣሉ...ይወርዳሉ።በዚያ መሀከል አላህም፦"እኔ አንተን እባርክሀለሁ።ዝሪያዎችህንም አበዛልሀለሁ...ምድርንም ላንተ እና ለዝርያዎችህ አደርጋታለሁ" አለው። በህልሙ ማለት ነው.... ልክ ይሄን እንዳየ ከእንቅልፉ ነቃ። ባየው ነገርም በጣሙን ተደሰተ'ና፦"ጌታዬ አሁን ከምሄድበት በሰላም ከመለስከኝ እዚህ ቦታ ላይ ላንተ አምልኮ እሚሆን ቤት እገነባለሁ።ከሚኖረኝም ሀብት አንድ አስረኛውን ባንተ መንገድ አውላለሁ" በማለት እዛ ቦታ ላይ የሆነ ምልክት አድርጎ ስለት ገብቶ ጎዞውን ቀጠለ። ብዙ ተጉዞ የሀራንን ምድር ደረሰ'ና ከአጎቱም ተገናኘ።ለአጎቱ ሁለት ሴት ልጆች ነበሩት አንዷ (ለያ) ስትባል ታናሿ ደሞ (ራሂል) ትባላለች። ምነው ለያ ራሂል...ስል የዩሱፍ ፊልም ትዝ አላችሁ ሀ....!!! ቆይ ዩሱፍንም ደርሰነዋል ትንሽ ነው የቀረን። ትንሸኛዋ ራሂል ቆንጅዬ ነገር ስትሆም ትልቋ ግን እስከዚህም ነገር ነበረ።ከዚያም ያዕቁብ ትንሸኛዋ ራሂል በልቡ መግባቷን ሲያውቅ አጎቱን ላባንን እንዲድረው ጠየቀው። አጎቱም፦"7 አመት በጎችን ካገድክልኝ እድርሀለሁ" በማለት ቃል ገባለት'ና ያዕቁብም ቆንጂዬዋን ራሂልን ለማግኘት ለ7 ተከታታይ አመታት እረኛ ሆኖ አሳለፈ። የማይደርስ የለም'ና ሰባቱ አመት ተጠናቅቆ የቀጠሮው ቀን ብቅ አለ።ላባንም ድል ያለ ድግስ ደግሶ ዘመድ አዝማድ ከጠራ በኋላ ኒክህ እስሮ ሙሽሪትንም ለያዕቁብ አስረከበው። በማግስቱ ጠዋት ላይ ጨለማው በብርሀን መገፈፍ ሲጀ..
Hammasini ko'rsatish...