cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Reyan Records

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
296
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-1130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
04:24
Video unavailableShow in Telegram
174.99 MB
ማስ ||| ይህን ዙረት ይህን ኑረት ከመተንፈስ ውጪ ምን አተረፍኩበት? ቂም አርግዘው በወፈሩ ስም በርዘው በሚዞሩ እኔ ያሉት በከዳቸው ክብር ያልኩት ተሰዋቸው ይህ እስትንፋስ ከየት መጣ ምን ሊፈይድ ሳቄን ቀጣ ለማን ተረፍኩ በመኖሬ ምን አተረፍኩ በመዞሬ ምንስ ሆንኩኝ ታካች እንጂ ምን አገኘሁ ከ'ኡፍፍፍ' ውጪ? ቀኔን ሳድል ለወደድኩት ማባበያ ስሜት ሳብል መከፋትን ማስኮብለያ ቅጥሬን ሳጥር ለዕኩይ ጎኔ መታነቂያ መልኬ ሆነ መሳለቂያ መና መቅረት ላስፈራቸው መናኝ ልቤ ቃል ሰጣቸው መናኛ እኔ ቢበልጣቸው ሳይሰለፍ ቢቀድማቸው ተወዳድረው ተወራርደው እኔ ላሉት እኛን አድረው እኔ ላሉት እኛን አርደው መና ይኸው ወና ይኸው ውርርድ ያጸቀው ውድ-ዕድር ያነቀው. . . ይህን ዑደት ይህን ሕይወት ከመተንፈስ ውጪ ምን አተረፍኩበት? እውነት ውጦ መጨናነቅ ሀቅን ይዞ መሸማቀቅ ልክነት ላይ ሃሳብ ማጨቅ ከራስ ጋራ መጨቃጨቅ ከሰው፣ ለሰው፣ በሰው፣ ማዘን 'አይ ሰው' ብሎ ማለዛዘን. . . ታትሮ መታከት ታክቶ ለመታተር ወጥኖ ለማጠር ጥሮ ለመታጠር ሰክኖ ለመጣደፍ ተጣድፎ ለመስከን ከብሮ ለመራከስ ተራክሶ ለመክበር ለመፈለግ ሰበብ በሰብ ለማሳበብ በመክሰም ለማበብ በመግደል ለማከም በምታደክም ዓለም ተንቃ ልክነት ተልቃ ጥምነት ምን ትርፍ አለኝ ከ'ውነት? ይህን ስካር ይህን ዙረት ይህን ውብ ጣር ይህን ኑረት ይህን ጭናቅ ይህን ዑደት ይህን ጭራቅ ይህን ሕይወት ከመተንፈስ ውጪ ምን አተረፍኩበት? ልክ አለመሆንን ከተቀባች ቀኔ ስማኝ እኔ ጎኔ ማስ ለራስህ ዛሬ ማሳ አይደለም ጢሻ ማስ አይሆን ንክሻ ማስነጠስህ ላይቀር 'ይማርህ' ባዮቹን 'ኑሩ' ብለህ እደር ስማኝ እኔ ጎኔ ምን አገኘህበት ከትንፋሽህ ለኔ?
Hammasini ko'rsatish...
1
የአሳ ፍቅር አንድ ወጣት የሰራውን አሳ በችኮላና በጉጉት እያጣጣመ ሲበላ አንድ አዛውንት፣ “ለምንድን ነው ይህንን አሳ እንደዚህ በጉጉት የምትበላው?” አሉት፡፡ ወጣቱም በመመለስ ፣ “አሳ በጣም ስለምወድ ነዋ” አለ፡፡ አዛውንቱም፣ “ኦ አሳ ትወዳለህ? ለዚህ ነው ከሚኖርበት ከውኃው ውስጥ አጥምደህ፣ አውጥተህና ትንፋሽ አሳጥተህ እንዲሞት በመተው የቀቀልከውና የበላኸው? እባክህን፣ አሳ እንደምትወድ አትንገረኝ፡፡ የምትወደው ራስህን ነው፡፡ አሳው ስለሚጥምህ፣ ስለሚያረካህና ስለሚጠቅምህ ከውኃ ውስጥ አውጥተህ ቀቀልከውና በላኸው፡፡ የወደድከውና የጠቀምከው ራስህን እንጂ አሳውን አይደለም”፡፡ እኝህ አዛውንት በዚህ ገጠመኛቸው ላይ በመመርኮዝ ትምህርት ሲሰጡ እንዲህ ይላሉ፣ “አብዛኛው ፍቅር ብለን የምንጠራው ነገር በሌላ መጠሪያው “የአሳ ፍቅር” ነው ሊባል የሚገባው፡፡ እውነተኛ ፍቅር የሚለካው በምንቀበለው ነገርና በምናገኘው ጥቅም ሳይሆን በምንሰጠውና ሌላውን በምንጠቅመው ነገር ነው፡፡ የምንወደውን ሰው እንሰጠዋለን፡፡ ስንሰጠው ደግሞ የመነሻ ሃሳባችን ወሳኝ ነው፡፡ በሁለት ንጽጽራዊ ምሳሌዎች እናብራራው፡፡ እቤታችን ያለውን በግ እንወደዋለን ስለዚህም ምግብ እንሰጠዋለን፡፡ ይህ በግ በሰጠነውና ባበላነው ቁጥር የማይደልብ ቢሆንና እንዲያው በሆነ ምክንያት ለምግብነት አይሆንም ብንባል ግን ለበጉ ምግብ መስጠታችንንና መቀለባችንን እናቆማለን ወይም እንቀንሳለን፡፡ ለምን? ፍቅራችን “የአሳ ፍቅር”፣ ፍቅራችን እኛ ከምናገኘው ጥቅም አንጻር ስለሆነ፡፡ በተቃናኒው እቤታች ያለውን ልጃችንን እንወደዋለን ስለዚህም ምግብ እንሰጠዋለን፡፡ ይህ ልጃችን ባበላነው ቁጥር ቢከሳና ህመምተኛ  ቢሆን መመገብን አናቆምም፡፡ እንዲያውም ለእሱ ያለን ኃዘንና ፍቅር ይብስበታል፡፡ ለምን? የፍቅራችን መነሻ ልክ እንደ አሳው ፍቅር ከእኛ ጥቅም ሳይሆን ከእሱ ጥቅም ስለሆነ ነው፡፡ ማንኛውንም የቀላል ጓደኝነት፣ የፍቅር፣ የትዳርም ሆነ የስራ ቅርበታቸሁንና “ፍቅራችሁን” ተመልከቱት፡፡ እነዚያ ሰዎች እናንተን እስከጠቀሙ ድረስ የምትወዷቸው፣ የማይጠቅሙበት ሁኔታ ሲከሰት ወይም የነበራቸው ሁኔታ ሲቃወስባቸው ዘወር የምትሉ ከሆነ ፍቅራችሁ “የአሳ ፍቅር” ይባላል፡፡ አንድ ሰው ስለሚጠቅመንና ስለሚያግዘን መውደዳችንና መንከባከባችን በራሱ ችግር ባይኖረውም ይህንን ሰው ከጥቅማችን አንጻር ብቻ መውደዳችንና የማይጠቅመን እንደመሰለን ስንጥለው ግን የወረደው የፍቅር ደረጃ ላይ ይመድበናል፡፡    ✍✍✍ታዚ
Hammasini ko'rsatish...
1
Photo unavailableShow in Telegram
እረፉ? እረፉ ምትይን እረፍትን በቁና ይመስል ያደልሽን ሌት እየቀሰቀስሽ ቀን እያባነንሽን ማረፍ ደግ ነበር ሰላም ደግ ነበር በጥባጩ ባይበዛ ሰው እንዴት አርጎ ነው በራሱ ለራሱ ጠላቱን 'ሚገዛ ያ ልጅሽ ያንቺው ጉድ ለእኔም ያልሽው ወንድም ወድቄ ቢያገኘኝ እንደው ባንዱ ግድም ተጎዳሁ እያልኩት ቁስሌ አጥንቴን ዘልቆ ውስጤን እያመመኝ ማዳን ያልቻለበት አይዞህ ያሸከመኝ ያ ልጅሽ ያንቺው ጉድ... ሲርቀኝ እፎይ አልኩ ሲቀርበኝ ፈራሁት ሲያቅፈኝ አሳቀቀኝ ሲስመኝ ጠላሁት ይሄንን አመሌን ከየት አመጣሁት? ደሞ ያባብለኛል ራሱ አስለቅሶ? ደሞ 'እኔን' ይለኛል እሱው ሆድ አስብሶ? ለምን ይመስልሻል አጥብቀሽ የያዝሽው የሚበጠስብሽ? አስበሽ የሳልሽው የሚንጋደድብሽ? ፈገግታ ነስተሽው ያሳደግሽው ልጅሽ ምን አውቆ ያስቅሽ? ማቀፍ ያላወቀ የተገፋ ትውልድ እንዴት ይደግፍሽ? ትይናለሽ አሉ ህልም አልባ ነው ሁሉም እብደት የወረሰው ግን አትሳሳቺ ከኛ አስቀድሞ ነው ዘመንሽ የቃዠው ለጤና ነው ብለሽ ያዋጥሽን መድሀኒት አርጎን በሽተኛ የት ምድር ላይ እንቁም የት ሀገር እንተኛ? (እረፉ አትበይን ማረፍ አናውቅ እኛ!) በአቤኒ የተጻፈ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
Hammasini ko'rsatish...
"ቆንጆ ነኝ" ባይ ማነሽ? በውበትሽ ማርከሽ ንጉስን ከዙፋን ፥ ማውረድ ሳትችዪ ማነሽ "ቆንጆ" ሲሉሽ ፥ አቤት የምትዪ? ድሮ ድሮ እኮ የሴት ልጅ ውበቷ ፥ ዙፋንን ያስረሳል ያንዲት ሴት ቁንጅና ፥ ካንድ ጦር ይብሳል። ድሮኮ ድሮኮ መንግስት ህዝብ ላይ ፥ በስልጣን ሲለግም ከዙፋን ለማውረድ አንዲት ቆንጆ እንጂ ፥ ትግል አያስፈልግም። ድሮኮ ድሮኮ ፈጣሪ የሾመው ፥ ጥበብን አድሎት ዙፋኑን እንዳይለቅ "ቆንጆ አታሳየኝ" ነው ፥ ያንድ ጠቢብ ፀሎት። ንጉስን ለማውረድ ፥ህዝብ ሲያጣ አቅም እኛው ከኛው ጦር ጋር ፥"ልቀቅ አንለቅም" እየተባባልን ፥እርስ በርስ ብናልቅም ቆንጆ ስንል አቤት ፥ ያለንን አናውቅም። 🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
Hammasini ko'rsatish...
እንዴት አላችሁ ክቡራትና ክቡራን የ 'ለሩህ ቅመም' ቤተሰቦች..እንዴትም ሁኑ አላህ ሰላም ያድርጋችሁ🤍 ከሰሞኑ ከልቤ ላይ አንድ ሀሳብ ውል አለብኝና ቀድሜ ሀሳቤን ለአንድ ወዳጄ ብቻ ሹክ  ብዬው ብዙ ካሰብኩበት በኋላ ወደናንተው ይዤው መጣሁ። ሁላችንም እንደምናውቀው እኛ ማለት የአንብብ ትውልዶች ነን..ሪሳላቸውን በአንብብ የጀመሩ የኚያ ታላቅ ነብይ ህዝቦች ነን። ቁም ነገሩ ግን የአንብብ ትውልድ መሆናችንን በምን አይነት መልኩ ነው እየተጠቀምንበት ያለነው? ብዙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፀሀፊያን ሳሉን ሙስሊሙ ህብረተሰብ አጥጋቢ  አንባቢ ያልሆነበት ምክንያት ምንድነው?   አላህ በረሱላችን ላይ በመጀመሪያ ያወረደው አንቀፅ አንብብ የሚል ነበር። አንብብ! ይህም የስኬቶች ሁሉ ጅማሮ ከዚህ መሆኑን ለማመልከት ይመስላል። ካለንበት condition አንፃር ግን እውነት እኛ የአንብብ ትውልድን መስለን ተገኝተናል? (መልሱን ለራሳችን ተውኩ) ነገር ግን እኛ ከዚህ ጎራ ባንገኝ እንኳ፣የስም የአንብብ ትውልድ ብንሆንም ካስተዋልን ግን አንባቢ ትውልድን መፍጠር እንዲሁም አንባቢ ማህበረሰብን መገንባት የምንችልበት ብዙ way አለ። በርግጥ ከስር መሰረቱ ያላደበርነው ጉዳይ ኋላ ላይ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። አስቸጋሪ ቢሆንም ይህንን መቅረፍ የማንችልበትና ማዕረጋችንን የማንመስልበት ምንም ምክንያት ግን አይኖርም። ወደጉዳዬ ስገባ ኢንሻ አላህ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በግሌ ባነበብኳቸው መፅሀፍቶች መሰረት የመፅሐፍ ጥቆማ (book suggestion) በሚል ርዕስ የተለያዩ መፅሀፍቶችን የምንቃኝ እንዲሁም ይዘታቸውን የምንዳስስ ይሆናል። በዚህ ሳያበቃ በእናንተም በኩል በተለያየ ይዘት ያነበባችኋቸውን መፅሀፎች በማጋራትና ይዘታቸውን በማብራራት በዛ ዙሪያ የምንወያይበትን የጋራ መድረክ እንከፍታለን። ይህም ቢያንስ መፅሀፍ ለመግዛትም ሆነ ለማንበብ ስናስብ መፅሀፉ ምን ላይ focus እንደሚያደርግ confused ሳንሆን may be መፅሀፉ እዚሁ ያወራንበት ከሆነ በተጠቋቆምነው መሰረት መፅሀፉ ስለምን ሊያወራ እንደሚችል ቀድመን የምናውቅበት እድል እንፈጥራለን ማለት ነው። ለማንኛውም በዚህ ሀሳብ ዙሪያ ሀሳብ ካላችሁ ሼር በማድረግ እንጀምር...በዚሁ አሁን ባነሳነው ሀሳብም ላይ ከዚሁ በተሻለ መርሀ ግብርና በአዲስ ይዘት እመጣለሁ። እስከዛው ግን ስራችንን እስክንጀምር ቻናሉን ለአንባቢያን ሼር እያደረጋችሁና ወደቻናሉ እየጋበዛችሁ ይህን ሀሳብ በጋራ እንድንካፈል እፈልጋለሁ። . . . (መፅሀፍ አንብቤ ስጨርስ አንድ የግል ልምድ አለኝ.. የመፅሀፉ የመጨረሻው ገፅ ላይ ቀለሜን ሳኖር <እኛም የአንብብ ትውልድ ኸበሮች ነን> የሚልን አረፍተ ነገር አኖራለሁ። ራሴን motivate የማደርግበት መንገድ ቢሆንም እውነታው ግን ሌላውም በዚህ ማዕረግ መጠቀምም መነሳትም እንዳለበት  ለማመልከትና ምናልባት inspire ማድረግ ከቻለ በሚለው ነው። እያጋራችሁ ቆዩኝ! @z_spicesoul @z_spicesoul (አብድልቃድር ኑር)
Hammasini ko'rsatish...
....<<የእናንተ ዘመን ተፈኩር መጀመሪያውም መጨረሻውም ሴት ላይ ነው። ሲበዛ ለስሜታችሁ ቅርብ ናችሁ። እንጂ ለማማሩም ሆነ ለማስተንተኑ ከሰማይና ከከዋክብት፤ከጨረቃና ከደመና በላይ ውብ አለ? የለም።ግን እንደዚህ አታስቡም።አለም የእነዚህን ታላላቅ ፍጥረታት ውበት ያደንቅ ስለነበር የሚወደውን ፍጡር እንኳን...እንደ ጨረቃ ታበራለህ እያለ ያሞግስ ነበር። ቀስ በቀስ በስሜት እየታወረና የፈጣሪን ተዓምር ማስተንተን የማይችል ትውልድ እየፈራ ሲመጣ.... ይኸው ልትተኙት የምትመኙትን ነገር ብቻ የምታሞግሱ ጉዶች ተፈጠራችሁ።የታላላቆቹ ፍጡሮች ውበት ከቶም አይታያችሁም።>>..... 👉ከኢፋዳ መፅሀፍ የተወሰደ🥰
Hammasini ko'rsatish...
ከወሎ የመጡ ትልቅ ሰው ናቸው የነገሩኝ አንድ ሸኽ እሳቸው ዘንድ ለሐደሩት ቁርአን ይፈስራሉ አላህ በአያቱ እንዲህ ብሏል … እዛ ውስጥ ያለ አላስችል ያለው ደጋግሞ እያቋርጣቸው የኔም አያትኮ እንደዚህ ብሏል😁 …ያው አያቱን ከፍ ሊያደርግ ዘሩንም ሊያስጠራ መሆኑ ነው ሸኽየው << ዛሬ ደሞ አላህ በአያቱ እንዲ ብሏል ስል አያቴም እንዲ ብሏል ሚል ይምራብኝ >> 😂😂 የገጠመን …🤦🙇
Hammasini ko'rsatish...
😁 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.