Lidu ⓅⓄⓔⓜ
ይሄንን ለምታነቡ በሙሉ 1፡ለፍቅረኛችሁ💑 2፡ለናታችሁ👪 3፡ለጓደኛችሁእንዲሁም👭👫 መልእክት መላክ ለምትፈልጉት በሙሉ በግጥም መልክ አንዲተላለፍላችሁ @liduu11 በዚህ ያናግሩን። #የይቅርታ_ግጥም📝 #የፍቅር_ግጥም📝 #የመልካም_እድል_ግጥም📝 #የሀዘን_ግጥም 📝 #የልደት_ግጥም📝 #እንዲሁም በተለያዩ ርዕሶች ላይ በፈለጋችሁት መልኩ አግጥሞችን እንገጥማለን።😍
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
272
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar
- Kanalning o'sishi
- Post qamrovi
- ER - jalb qilish nisbati
Ma'lumot yuklanmoqda...
Obunachilar o'sish tezligi
Ma'lumot yuklanmoqda...
የሚመካ!
አንዳች ሳይታበይ
ሰው በሰውነቱ
በዕብሪት ሳይታጎል
ሳይከዳው ጉልበቱ
የመልካም ስራና
የመልካም ምኞቱ
ፍሬው እንዲባረክ
እንዲሰምር ህይወቱ
ኑሮው እንዲቀደስ
ጥረቱ እንዲሳካ
ከቶ የሚመካ!
በእግዚአብሔር ይመካ!!!!!
@lidupoemm
@lidupoemm
👍 9
የመኖር ትርጉሙ
የመኖር ትርጉሙ
የምባ ቅብብል ነው
በትውልድ ማህል
አባትህ ያነባው
ላንተም ይደርስሀል
ሰው የሆንሁ ለታ
ደርሶኛል ይህ እጣ
አልቅሼ እንደገባሁ
አስለቅሸ ልወጣ
@lidupoemm
👍 4
@lidupoemm
አንቺ ሴት ውድ ነሽ
ውስጥሽ ቆሽሾ ላይሽ ያላማረ
ግን የውስጥሽ ውበት በገላሽ ላይ ያለ
ላይሽ ብቻ አይደለም ውስጥሽ የተኳለ
ጣፋጭ ቃል በልብሽ በአንደበትሽ ያለ
ክብርሽን ጠብቀሽ ባለሽ ነገር ኮርተሽ
እራስሺን ሳትክቢ እራስሽን ሆነሽ
በራስ መተማመን በእውቀት የተካንሽ
ሰው ሁሉ ሚሰማሽ ስትመክሪ ሚያምርብሽ
አሉ ባልታን ሳይሆን ፈጣሪሽን ፈርተሽ
በቃሉ ተሰርተሽ እንደ ቃሉ የኖርሽ
ልባሟን ሴት ሆነሽ ጌታሽን ያከበርሽ
- ሂወትሽ ቢሸተት ልዩ መአዛ ያለሽ
በእውነት ልንገርሽ
አንቺ ሴት ውድ ነሽ
በ:ሊድ(ዞዊ)
@NebseLemelemechh
👇👇👇👇👇
👉@lidupoemm
👉@lidupoemm
👍 6
🌼እግዚአብሔር ያለፈውን አመት አሻግሮ ለዚህኛው አመት በሰላም ያሸጋገራችሁ በምክንያት ነው፡፡በእናንተ ያልጨረሰው ጉዳይ ስላለው እንደሆነ ማወቅ አለባችሁ፡፡ድሮም ቢሆን የተፈጠራችሁት በእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ዓላማ ነው፡፡በሕይወት ያቆያችሁ በምክንያት ነው፡፡እኔ ከሞት አፈፍ የተመለስኩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፤ እነዚህ ክስተቶች ግን እግዚአብሔር እንደማይፈልገኝ ሳይሆን ያሳዩኝ፣ እርሱ ገና በእኔ ያልጨረሰው ሥራ እንዳለ ነው፡፡ሳዖል ዳዊትን ለመግደል ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፡፡ነገር ግን እግዚአብሔር በዳዊት ላይ ዓላማ ስለነበረው፥ ለጠላቶቹ አሳልፎ አልሰጣቸውም፡፡ለእናንተ የመኖር ትርጉም ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ሕይወት ትርጉም የምታጣው ያለ ክርስቶስ ስትሆኑ ነው፡፡እርሱ ከእናንተ ጋር ሁኖ ሳለ ሕይወት ሙሉ ነች፡፡እራስን ማጥፋት የሚባለው የሰይጣን ሐሳብ ይከሽፋል፡፡የምትኖሩት ለእግዚአብሔር ነው፡፡ብዙ ሰዎች ለራሳቸው ብቻ የሚኖሩ ለሌላው የማይጠቅሙ ለእግዚአብሔር የማያስፈልጉ እየመሰላቸው የሕይወት ትርጉም ይጠፋባችዋል፡፡እናንተ የራሳችሁ እንዳልሆናችሁ፤ የእግዚአብሔር እንደሆናችሁ ስታውቁ የምትኖሩት ለራሳችሁ ሳይሆን ለእርሱ እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ይሄ አመት እግዚአብሔር በእናንተ ለትውልድ፣ ለሀገር፣ ብሎም ለአለም ያየላችሁን ራዕይ እናንተ የምታዩበት አካል የሚለብስበት አመት እንዲሆንላችሁ እጸልያለሁ፡፡አመቱን ዋጁት፡፡ከአሁኑ የሚመጡ ቀናት ውስጥ ቃል ዙሩባቸው፣ በሂደት የዘራችሁት ቃል መብቀሉ የማይቀር ነው፣ እናንተም በመጨረሻው አመት የዘራችሁት ዘር የምታጭዱበት ጊዜ ይሆናል፡፡መልካም አዲስ አመት እንዲሁንላችሁ፤ መልካሙን ነገር ዝሩ፡፡ተባረኩ!በጌታ ፍቅር እወዳችዋለሁ፡፡
🌼🌼 @Yezelalemhiywet 🌼
🌼🌼 @Yezelalemhiywet 🌼
🌼🌼 @Yezelalemhiywet 🌼
Hammasini ko'rsatish...