uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Agizachew Tefera

Agizachew Tefera

Kanalga Telegram’da o‘tish

"አምላኬ ሆይ፥ በፊትህ የምንለምን ስለ ብዙ ምሕረትህ ነው እንጂ ስለ ጽድቃችን አይደለምና ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዐይንህን ገልጠህ ጥፋታችን... ተመልከት።" (ዳን. 9፥18)

Ko'proq ko'rsatish
1 245
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+67 kun
+830 kun
Postlar arxiv
በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከታዩት ችግሮች መካከል አንዱ በምእመናን መካከል የነበረው መከፋፈል ነው። መከፋፈሉ የመጣውም፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፤ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤ እኔስ የክርስቶስ ነኝ” በሚል ክርክር እንደ ኾነ መጽሐፉ ይነግረናል (1ቆሮ. 1፥11-12)። በዚህ ጕዳይ ክርክር ገጥሞ መለያየት ሥጋዊነት መኾኑን ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ያስረዳል፦ “…ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችኹ ሥጋውያን መኾናችኹ አይደላችኹምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? አንዱ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ኹለተኛውም፦ እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መኾናችኹ አይደለምን? አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው? ጳውሎስስ ምንድር ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችኹ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ። እኔ ተከልኹ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢኾን ወይም የሚያጠጣ ቢኾን አንዳች አይደለም። የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፥ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል። የእግዚአብሔር ዕርሻ ናችኹ፤ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችኹ፤ ከርሱ ጋራ ዐብረን የምንሠራ ነንና።” (1ቆሮ. 3፥4-9)። ዛሬም ከዚህ ባለመማር ክርስቲያን ነን በሚሉ መካከል፥ በሕይወተ ሥጋ ባሉ መሪዎቻቸው፣ አስተማሪዎቻቸው፣ መጋቢዎቻቸው፣ ዘማሪዎቻቸው፣ ወዘተ. ጀርባ ተሰልፈው እኔ የእገሌ ነኝ፤ እኔ የእገሊት ነኝ የሚሉ አይጠፉም፤ አሉ። እነርሱ እንደ ሰው ልማድ የሚመላለሱ ሥጋውያን ናቸው። ካንቀላፉ ቅዱሳን ጀርባም ተሰልፈው፥ “እኔ የእገሌ ነኝ፤ እኔ የእገሊት ነኝ” ከማለት ዐልፈው፥ “እገሊት የእኛ ናት፤ እገሌም የእኛ ነው” የሚሉም ሞልተዋል። በዚህ ረገድ፥ የጌታችንን እናት ቅድስት ማርያምን “የእኛ ናት” ብለው ርሷን የእነርሱ ብቻ አድርገው የሚመለከቱና የሌላው አማኝ ወገን እንዳልኾነች የሚቈጥሩ እጅግ ብዙ ናቸው። እንዲህ የሚያስቡ ሐዋርያው እንዳለው፥ እነርሱ እንደ ሰው ልማድ የሚመላለሱ ሥጋውያን ናቸው። የጌታችንን እናት ጨምሮ በክርስቶስ ያመኑ ኹሉ በክርስቶስ አንድ አካል ናቸው። "እናንተም የክርስቶስ አካል ናችኹ እያንዳንዳችኹም ብልቶች ናችኹ።" (1ቆሮ. 12፥27)። ቅድስት ማርያም፥ “ዕንኾኝ የጌታ ባሪያ” (ሉቃ. 1፥38) በማለት፥ የጌታችን፣ የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት በመኾን ያገለገለች ብፅዕት እናት ናት። የኹላችንን አዳኝ በሥጋ በመውለዷ፥ በርሱ የምናምን የኹላችንም ናት። የኹላችንም ስለ ኾነች ግን፥ እግዚአብሔር በርሷ ያደረገውን ታላቅ ሥራ፥ ወልድ እኛን ለማዳን ከርሷ ሰው ኾኖ መወለዱን እንናገራለን። ከዚህ ዐልፈን ግን ለርሷ ወይም በስሟ የምናደርገው አንዳች ነገር ግን የለም፤ ምክንያቱም ማርያም የጌታችን እናት በመኾኗ የእኛ ብትኾንም፥ እኛ ግን የርሷ ሳንኾን የክርስቶስ ነን። ቃሉም ይህን ያረጋግጣል፦ “ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ ጳውሎስ ቢኾን፥ አጵሎስም ቢኾን፥ ኬፋም ቢኾን፥ ዓለምም ቢኾን፥ ሕይወትም ቢኾን፥ ሞትም ቢኾን፥ ያለውም ቢኾን፥ የሚመጣውም ቢኾን፥ ኹሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችኹ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።” (ቍ. 21-23)። ይህ ቃል በሥጋዊነት የሚያስቡትን አያፈናፍንም፤ እግዚአብሔር ኹሉን የሰጠን፥ የኹሉ እንድንኾን ሳይኾን፥ የክርስቶስ ስለ ኾነን ነው። ስለዚህ በዋጋ ተገዝታችኋልና የሌላው መኾን ቀርቶ የራሳችኹም አይደላችኹም (1ቆሮ. 6፥20)፤ እንዲሁም፥ " በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትኹኑ።" (1ቆሮ. 7፥23) ይላቸዋል። ቃሉ ሕያው ነው፤ ዛሬም ለእኛ ይሠራል። በሥጋዊነት ተይዘን ራሳችንን፥ ላልገዛን አካል ባሮች አድርገን ካቀረብን በክቡር ደሙ የዋጀንን ጌታ እናሳዝናለን። "የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፥ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል።" (1ቆሮ. 3፥8) እንደ ተባለ፥ የጌታችንን እናት ቅድስት ማርያምን ጨምሮ፥ እግዚአብሔርን ያገለገሉ ኹሉ በጎ ብድራታቸውን ይቀበላሉ። ስለዚህ የራሳችንም ኾነ የሌሎች፥ የማርያምም ጭምር አይደለንም፤ እኛ በውድ ልጁ የዋጀን የእግዚአብሔር ብቻ ነን። ክብር ለርሱ ብቻ ይኹን።

ቅዱሳት መጻሕፍት በሚመሰክሩት ምስክርነት፣ በመንፈስ ቅዱስም አብርሆት የተሰቀለውን ያወቀ ሰው የተሰቀለበትን አይሻም። ለተሰቀለበት ይህን ያኽል ቦታ የሚሰጥ ደግሞ የተሰቀለውን እንዳላወቀና ለተሰቀለው ምንም ቦታ እንደሌለው ግልጽ ነው። የተሰቀለበት ወይም ትእምርቱ (ምልክቱ) የተሰቀለውን ካላመለከትና ራሱን ብቻ ካሳየ፥ ምልክትነቱ ቀርቷልና ጣ*ዖ*ት ከመባል አያመልጥም። ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ አኮ ዘተሰቅለ ቦቱ።

ኤችአይቪ ኤድስ 🎗️ የኅብረተ ሰባችን ውስብስብ ችግርና ትልቅ አጀንዳ በነበረባቸው ዓመታት፥ ቫይረሱን ለመከላከልና ከቫይረሱ ጋራ የሚኖሩትን ለመከባከብ፥ ብሎም በሽታውን ለመቈጣጠር፥ የሚመጣ የርዳታ ገንዘብ ነበር። በዚህም ላይ ተመሥርተው፥ የሚንቀሳቀሱ ነበሩ። የሚመጣው የርዳታ ገንዘብ በአብዛኛው የሚውለው በዐውደ ጥናቶችና በስብሰባዎች፥ በየድርጅቱም ለተቀጠሩ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ስለ ነበረና ከቫይረሱ ጋራ የሚኖሩ ሰዎች በስማቸው ከሚመጣው የርዳታ ገንዘብ ብዙም ተጠቃሚዎች ስላልነበሩ፥ ከተጠቃሚነት አንጻር፥ "ከቫይረሱ ጋራ የሚኖሩ" እና "በቫይረሱ የሚኖሩ" የሚል ሐሳብ ይሸራሸር ነበር። እንደ እነዚህ እንደ ኹለቱም ያሉ ሰዎች በኹሉም መስክ አሉ። ለተሰማሩበት ሙያ፣ ሥራ፣ አገልግሎት ራሳቸውን ሰጥተው ከልባቸው የሚኖሩ፥ ከዚህ በተቃራኒው ሙያቸውን፣ ሥራቸውን፣ አገልግሎታቸውን መኖሪያቸው ብቻ የሚያደርጉ ምንደኞች። በወንጌል አገልግሎትም እንኳ፥ የራሳችንን ረብ ፈልገንና ወንጌልን ማትረፊያ አድርገን የምናገለግል ወይም በወንጌል የምንኖር እንዳለን ኹሉ፥ በተቻለና በገባን መጠን ራሳችንን ሰጥተን ለወንጌል የምንኖርም አለን። "ኹሉ #የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም። ነገር ግን (ጢሞቴዎስ) ልጅ ለአባቱ እንደ ሚያገለግል ከእኔ ጋራ ሆኖ #ለወንጌል እንደ አገለገለ መፈተኑን ታውቃላችኹ።" እንዳለ ሐዋርያው (ፊል. 2፥21-22)። ከተሐድሶ አገልግሎት ጋራ በተያያዘም፥ "በተሐድሶ የሚኖሩ" እና "ለተሐድሶ የሚኖሩ" ተብለን ከኹለት ተከፍለን መታየት ያለብን ሰዎችና ተቋማት አለን። በተሐድሶ ከሚኖሩ መካከል አንዱ "ማኅበረ ቅዱሳን" እና ተከታዮቹ ናቸው። ማኅበሩ ከአነሣሡ ጀምሮ እስካኹን ባለው ጕዞ እዚህ የደረሰው፥ በአንድ በኩልና በዋናነት ስለ ተሐድሶ እያወራና እየጻፈ፥ "ተሐድሶ" ያላቸውንም ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን እያባረረና እያስባረረ ነው። እንዲህ ማድረግ ትልቅ "አገልግሎቱ" ነው። በዚሁ አገልግሎት የተጠመዱ ሰዎቹ፥ ዛሬም እንኳ ስለ ተሐድሶ መናገራቸውን አላቋረጡም። https://www.facebook.com/share/p/1CAWMPz968/ በተሐድሶ አገልግሎት ውስጥ ካለን ሰዎች መካከልም "በተሐድሶ የምንኖር" እና "ለተሐድሶ የምንኖር" እንዳለን ግልጽ ነው። በተሐድሶ የምንኖር፥ ልክ በቫይረሱ መኖር በሚገኘው ርዳታ ይኖሩ እንደ ነበሩ ሰዎች፥ ስለ ተሐድሶ እየለፈፍንና ከእኛ በቀር ተሐድሶ የለም እያልን፥ አገልግሎቱን የገንዘብ ማግኛ ምንጭ አድርገን እንደ ቀጠልን፣ በሥራው ላይ ግን ብዙም እንደሌለን፥ ይህም ሳያንስ አገልግሎቱን ወዳልተነሣበት አግጣጫ ለመሳብ እየታተርን እንዳለ የአንዳንዶች አካኼድ ይናገራል። በዚህ መንገድ ከቆምነው ከእኛ የተነሣም፥ የተሐድሶ አገልግሎት እየተነቀፈ ይገኛል። ለተሐድሶ የምንኖርና ለኢኦተቤ መታደስ ብዙ ዋጋ ከፍለን እያገለገልን የምንገኝ ወገኖችም፥ አገልግሎታችንን ሰዎች ላያዩት፣ ላያውቁት ይችላሉ። እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሸክም ግን ብዙ እየተባልንና ብዙ ዋጋ እየከፈልን በማገልገል ላይ እንገኛለን። በተሐድሶ የምንኖር ደግሞ የተሐድሶ አገልጋይ መስለን በተሐድሶ እንነግዳለን። ለተሐድሶ ስኬት ሳይኾን፥ ለራሳችን የግል ጥቅምና ዝና ስንል፥ ጥቅም እስከ ተገኘበት ድረስ፥ ከማይመስሉን ጋራ በመወዳጀት ጭምር የእነርሱ አጀንዳ አስፈጻሚ እስከ መኾን መድረሳችን እየታየ ነው። በአገልግሎቱ ውስጥ ሳንኖር፥ ያለን አስመስለን ብዙዎችን እያደናገርን እንገኛለን። በዚህም እግዚአብሔር ያዝናል። ለተሐድሶ ሸክም ያላቸው ወገኖችም፥ ለተሐድሶ የምንሠራ መስለን፥ ኪሳቸውን በአገልግሎት ስም በማራቈታችን ተስፋ ይቈርጣሉ። በእኛ ሰበብ ለአገልግሎቱ ያላቸው ልብ ይወድቃል። እነርሱም ነገሩን ሲረዱት የተሐድሶን አገልግሎት በእኛ ልክ እየመዘኑ አገልግሎቱን በጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስገባሉ። ስለዚህ ራሳችንን እንመርምርና በተሐድሶ ከመኖር ለተሐድሶ ወደ መኖር እንምጣ። እኛ እግዚአብሔር እንደ ጠራን ለተሐድሶ ስናገለግል፥ እግዚአብሔር ደግሞ የእኛን ሕይወት፣ የእኛን ሥራ፣ የእኛን ኑሮ ይባርካል። አቢግያ ዳዊትን፦ "የእግዚአብሔርን ጦርነት ስለምትዋጋ እግዚአብሔር በእውነት ለጌታዬ የታመነ ቤት ይሠራልና" እንዳለችው (1ሳሙ. 25፥28)። እግዚአብሔርን መምሰልን ማትረፊያ ከምናደርግም፥ ኑሮዬ ይበቃኛል በሚለው መንፈሳዊ ስሌት ሕይወታችንን ብንመራ አንዳች አይጎድልብንም። "ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤" ይላልና (1ጢሞ. 6፥2) ለተሐድሶ እንጂ በተሐድሶ መኖር ያብቃ!

"የተቀበረ መክሊት፦ ለመድሎተ ጽድቅ ከተሰጠ ምላሽ ጋራ"፥ "ዝተቐበረ መክሊት፦ ምስ ንመድሎተ ፅድቂ ዝተውሃበ ግብረ መልሲ" በሚል ርእስ፥ ወደ ትግርኛ ተመልሷል (እግዚአብሔር ሲፈቅድ ይታተማል)። መላ
"የተቀበረ መክሊት፦ ለመድሎተ ጽድቅ ከተሰጠ ምላሽ ጋራ"፥ "ዝተቐበረ መክሊት፦ ምስ ንመድሎተ ፅድቂ ዝተውሃበ ግብረ መልሲ" በሚል ርእስ፥ ወደ ትግርኛ ተመልሷል (እግዚአብሔር ሲፈቅድ ይታተማል)። መላሹ ወንድም ኀይሉ ጫቕሉ ሲኾን፥ "ሓጢኣተኛ ዘፅድቕ ፀጋ እግዚኣብሄር፦ ቅኑዕ ትምህርቲ ድሕነት" የተሠኘውንና "ኀጢአተኛውን የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ" በሚል ርእስ ወደ ዐማርኛ የመለሰውን መጽሐፍ፥ ጳጕሜን 1/2018 ዓ.ም. ለንባብ ያበቃል። ኹላችኹም በዕለቱ ተገኝታችኹ መጽሐፉን እንድትመርቁ ተጋብዛችኋል። አድራሻ፦ ሣር ቤት፣ አዳምስ ፓቪሊዮን (Adams Pavilion) — ዐዲስ ሕይወት አደራሽ ሰዓት፦ የኅብረቱ ፕሮግራም ሙሉ ቀን ሲኾን፥ የምረቃው መርሐ ግብር ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይኾናል፤ መጽሐፉን በቀኑ ከጧቱ ጀምረው ማግኘት ይችላሉ። "በአንድ ድንጋይ ኹለት ወፍ" ይሏል ይህ ነው።

ዛሬ ከጧቱ 4:06 ሰዓት ላይ አንዱ በስልክ ቍጥር +251722233639 ደውሎ "ጥቅል ፓኬጅ ስሞላ በስሕተት ወደ አንተ ተላከ፤ ስለዚህ መልስልኝ" ብሎ አለኝ። ዕሺ አልኹና ለማረጋገጥ ስገባ የገባ ፓ
+1
ዛሬ ከጧቱ 4:06 ሰዓት ላይ አንዱ በስልክ ቍጥር +251722233639 ደውሎ "ጥቅል ፓኬጅ ስሞላ በስሕተት ወደ አንተ ተላከ፤ ስለዚህ መልስልኝ" ብሎ አለኝ።  ዕሺ አልኹና ለማረጋገጥ ስገባ የገባ ፓኬጅ የለም። ከዚያ ከደወለበት ስልክ የጽሑፍ መልእክት ደረሰኝ። በቍጥሬ የገባ የጽሑፍ መልእክት እንጂ የገባ ጥቅል መልእክት የለም። ወጣቱ 4:13 ላይ መልሶ ደወለና "አልመለስኽልኝም እኮ" አለኝ። እኔም ስምኽ ማነው? አልኹት። ተሳደበና ስልኩን ዘጋው። ወዲያው ትሩኮለር ላይ ገብቼ የተመዘገበበትን ስም ስመለከት አጭበርባሪ ይላል። መልሼ ብደውል ስልኩ ተዘግቷል። ወይ አጭበርባሪ!😉

https://www.facebook.com/reel/1024927656808740/ መጽሐፍ ቅዱስ፥ “ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኀጥኣን ምሕረት ግን ጨካኝ ነው።” ይላል (ምሳሌ 12፥10)። አራዊት ግን እንዲህ ዐይነት ዕውቀት ማስተዋል ስለ ሌላቸው፥ አንዱ አውሬ ሌላውን የዱር እንስሳ እየበላ መኖሩ ሕገ ተፈጥሮ ነው። ሰው ደግሞ በሰው ላይ ልዩ ልዩ የጭካኔ ተግባራትን ሲፈጽም ከጥንት እስከ ዘመናችን አይተናል። ልጆች እያለቀሱ ወላጆችን በልጆቻቸው ፊት የቀጠፉ ወይም ለልጆቻቸው ሳያስቡና ሳይራሩ ወላጆችን በልጆቻቸው ፊት ያጠፉ ሰዎች የጭካኔ ድርጊት፥ ለሚሰማውና ለሚያየው ሰው ሰቅጣጭ ነው። ከዚህ አንጻር ከታየ፥ ይህ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲመላለስ አግኝቼ፥ ከታች የለጠፍኹት የቪዲዮ ትዕይንት፥ አውሬ ከሰው ተሽሎ የተገኘበት ነው ማለት ይቻላል። እግዚአብሔር በዐውሎ ነፋስ ኾኖ ኢዮብን፥ “እንግዲህ እንደ ሰው ወገብኽን ታጠቅ እጠይቅኻለኹ፥ አንተም ተናገረኝ።” (ኢዮ. 38፥3) ብሎ ከዘረዘራቸው የፍጥረት ጕዳዮች አንዱ፥ አንስት አንበሳን ያጣቅሳል፤ “በዋሾቻቸው ውስጥ ተጋድመው፥ በጫካም ውስጥ አድብተው ሳሉ፥ ለአንበሳይቱ ዐደን ታድናለኽን? የልጆችዋንስ ነፍስ ታጠግብ ዘንድ ትችላለኽን?” (ኢዮ. 38፥39-40) የሚለው ይገኝበታል። አንበሳይቱ የያዘቻትን የዱር እንስሳ እናትና በርሷው ቍጥጥር ሥር ያለችውን ግልገሏን እንደ ለመደችው ተራ በተራ መዘነጣጠልና መብላት ትችላለች። ነገር ግን የከለከላት ምን ይኾን? ሮጣ ለማምለጥ ዐቅም የሌላት ግልገሊቱ፥ እናቷን ከአንበሳይቱ አፍ ለማስጣል ያደረገችው የመውጋት ሙከራ፣ የአንበሳይቱን ፊት አንዳች ያልጐዳው ቢኾንም፥ በድርጊቷ ግን ልቧ በጣም እንደ ተነካና ርኅራኄ እንደ ተሰማት እንመለከታለን። ምናልባት አንበሳይቱ እንስት ስለ ኾነችም አንዳች የእናትነት ስሜት ተሰምቷት ይኾናል። ስለዚህ ባልተጠበቀና የሚመለከታትን ሰው አጀብ በሚያሠኝ አኳኋን፣ ከአፏ የገባውን የእናቲቱን ዐንገት ለቅቃ ኹለቱንም ትታቸው ኼደች። እንዲህ ያለ የርኅራኄ ልብ ያጣ ሰው፥ ከዚህ የአውሬ ርኅራኄ አንዳች ትምህርት ያገኛል ብዬ ለጠፍኹት።

https://www.facebook.com/share/p/1JR7jm7PQS/ ለኅትመት የተዘጋጀውን "ጥላ እና አካል" የተሠኘውን ፪ኛውን መጽሐፌን መሠረት በማድረግ፥ ከ"ድንቅ ፍጻሜ" የቴሌቪዥንና ዩቲዩብ ቻናል ጋራ የተደረገው ውይይት ፪ኛ ክፍል ዕንኾ። "ጥላ እና አካል" የተሠኘውንና ለማኅበረ በኵር የወንጌል አገልግሎት የሚውለውን ይህን ዕትም ለማሳተም ዐብራችኹን እንድትቆሙ በሥራው ባለቤት በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጋብዛለን። Mahbere Bekur CBE 1000002276848

https://youtu.be/h-v1CziFJ_U?si=pWSH_37leMKtLvbg ለኅትመት የተዘጋጀውን "ጥላ እና አካል" የተሠኘውን ፪ኛውን መጽሐፌን መሠረት በማድረግ፥ ከ"ድንቅ ፍጻሜ" የቴሌቪዥንና ዩቲዩብ ቻናል ጋራ የተደረገውን ውይይት የመጀመሪያ ክፍል ታደምጡ ዘንድ ዕንኾ።

photo content

share share share
share share share

https://vt.tiktok.com/ZSXpHE8pG/ መሬት ላይ ያለው አጿጿም እንዲህም ነው።

"በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ" (ሐ.ሥ. 3፥6) ላለማለት "በናዝሬቱ በእግዚአብሔር ስም ተነሣና ተመላለስ" ይላል ያለው "ሰባኪ" ማን ነበር?

photo content

ዘሚካኤላውያን በዚህ [በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ] ዘመን ለውዝግብ ምክንያት የኾነው ሌላው ሃይማኖታዊ ጕዳይ የእነ አባ ዘሚካኤል የእምነት አቋም ነው። ከአባ ዘሚካኤል ጋራ ስማቸው ዐብሮ የሚነሣው ዋናዎቹ ሊቃውንት አባ ገማልያልና አባ ዐፅቃ ሲኾኑ፥ የተጕለት ሰዎች እንደ ኾኑ ይገመታል። እነዚህ አበው በትምህርት የበሰሉና በሚያራምዱት የእምነት አቋም ላይ አስተያየታቸው የላቀ ኾኖ ይታያል። ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጋራ ያጋጫቸው የእምነት አቋም የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔር እንደ ሰው መልክ ያለ መልክ የለውም፤ እግዚአብሔር የአዳምን የሚዳሰሰውንና የሚታየውን የሥጋውን መልክ በራሱ አርኣያና በአምሳሉ አልፈጠረውም። የእግዚአብሔር አርኣያና አምሳል የማይታየው በአዳም ገጽ ላይ የነፋው (እፍ ያለው) መንፈስ ነው። ዮሐንስ በወንጌሉ እንዳለው፥ እግዚአብሔርን ያየው ፈጽሞ የለም። (ያየው ፈጽሞ ከሌለ እዛዲያ (ታዲያ) ማንን ይመስላል እንበል?) እግዚአብሔር አይታይም፤ ሰው የሚያውቀው መልክም የለውም፤ መልኩን ራሱ ነው የሚያውቀው። [እንደዚሁ] ነፍስም ሰው የሚያውቀው መልክ የላትም፤ የእግዚአብሔር አምሳል ስለ ኾነች አትታይም። (ጌታቸው፣ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ገጽ 65።) ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ይህን ትምህርት በተመለከተ ትልቅ ጉባኤ አድርጎ ከእነዚህ ሊቃውንት ጋራ እንደ ተከራከረና “እግዚአብሔር የሰውን መልክ የሚመስል መልክ እንዳለው [በማስረዳት]” የረታው ርሱ እንደ ኾነ ተነግሯል (ጌታቸው፣ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ገጽ 65)። መቼም ይህ ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ በጕልበትና በኀይል የረታበት ካልኾነ በቀር፥ በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ያገኘው ድል እንዳልኾነ ይታወቃል። ሰው በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯል ሲባል፥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እንዳለው እግዚአብሔር እንደ ሰው ያለ የሚታይና የሚዳሰስ ግዙፍ አካል አለው ማለት አይደለም። ኾኖም መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ አንዳንድ ክፍሎች እግዚአብሔር የአካል ክፍሎች እንዳሉት የሚናገሩበት ኹኔታ አለና፥ እንደ እኛ ዐይነት ግዙፍ የሰውነት ክፍሎች ያሉት ሊመስለን ይችላል፤ ለምሳሌ በሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እግዚአብሔር፦ ·   ዐይኖች (ዘዳ. 1፥12፤ መዝ. 32/33፥18፤ 33/34፥15፤ ምሳ. 15፥3፤ 22፥12፤ ሕዝ. 8፥18፤ 20፥17፤ አሞ. 9፥8፤ ዘካ. 4፥10፤ 9፥1፤ 1ጴጥ. 3፥12)፤ ·   ጆሮዎች (መዝ. 33/34፥15፤ ኢሳ. 59፥1፤ ሕዝ. 8፥18፤ 1ጴጥ. 3፥12)፥ ·   እጅ (ዘፀ. 9፥3፤ ዘኍ. 11፥23፤ ዘዳ. 2፥15፤ ኢያ. 4፥24፤ ኢሳ. 4፥19፤ 59፥1፤)፤ ·   እግር (ኢሳ. 66፥1፤ ሕዝ. 43፥7፤ ናሆ. 1፥3፤ ማቴ. 5፥35፤ ሐ.ሥ. 7፥48-50፤ ዕብ. 10፥13) ወዘተ. እንዳሉት ተጽፎ እናነብባለን። ነገር ግን እንደ እኛ ያሉ፥ የሚታዩና የሚዳሰሱ፦ የሥጋ የኾኑ ግዙፍ ዐይኖች፣ ጆሮዎች፣ እጆችና እግሮች አሉት ማለት አይደለም። መንፈስ የኾነውን ትልቁን ጌታ እግዚአብሔርን፥ ኢምንት ለኾነው ሰው በሚገባው መንገድ ለመግለጥ መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀመበት ቋንቋ እንደ ኾነ የታመነ እውነት ነው። “እግዚአብሔር አያይም” ላሉት ኀጢአተኞች ዘማሪው ምላሽ የሰጠው፥ “ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዐይንን የሠራው አያይምን?” በማለት ነው (መዝ. 93/94፥7፡9)። ስለዚህ እግዚአብሔር ዐይኖች አሉት ማለት ያያል፥ ያስተውላል፥ ይመለከታል፤ ጆሮዎች አሉት ማለት ደግሞ ይሰማል፥ ያደምጣል ማለት ነው እንጂ፥ እንደ እኛ ዐይነት ግዙፍ ዐይኖችና ጆሮዎች አሉት ማለት አይደለም። በመጽሐፈ ኢዮብ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዲህ ይለዋል፥ “በውኑ የሥጋ ዐይን አለኽን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለኽን?” (10፥4)። በርግጥም እግዚአብሔር የሥጋ ዐይን የለውም፤ ሰው እንደሚያይም አያይም። የእይታውን መጠን ስፋቱንና ጥልቀቱን መናገር ያስቸግራል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን፥ “እኛን በሚቈጣጠር በርሱ ዐይኖቹ ፊት ኹሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም” በማለት ገልጦታል (ዕብ. 4፥13)። በውጭ ያለውና የሥጋ ዐይን የሚያየውን ብቻ ሳይኾን፥ እጅግ የጠለቀውንና የረቀቀውን በሰው ውስጥ ያለውን ኹሉ ያያል። “አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም ዕወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም ዕወቅ፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ” (መዝ. 139/140፥23-24)። ገና ሳይኾን ወደ ፊት የሚኾነውንም ቀድሞ ያያል። “እኔ በስውር በተሠራኹ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም። ያልተሠራ አካሌን ዐይኖችኽ አዩኝ” (ቍ. 16፡17)። እጆችና እግሮች አሉት ማለትም በተመሳሳይ መንገድ የሚተረጐም እንጂ፥ መንፈስ ለኾነው እግዚአብሔር ግዙፍ አካልን የሚያጐናጽፍ ቃል አይደለም። ይህን ዐሎ ብሎ (ክዶ) እንደ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በማሰብ፥ መንፈስ የኾነውን ጌታ እግዚአብሔርን ግዙፍ አካል ያለው አስመስሎ መናገር ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው። ሰው እግዚአብሔርን የመሰለበት መልኩ ሥጋዊ ወይም ግዙፍ ሳይኾን፥ መንፈሳዊ መኾኑን የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስም እንዲህ በማለት አስረድቷል። “በኦሪት የተጻፈውን ቃል ምክንያት አድርገው ለእግዚአብሔር ቀድሞ ሥጋ እንደ ነበረው የሚናገሩ፥ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰውን በእኛ አምሳል እንፍጠር አለ፤ በእኛ አምሳል ያለውም ስለ ሰው ሥጋ ነው የሚሉ አሉ (ዘፍ. ፩፥፳፯)። ነገር ግን እንዲህ አይደለም፤ ርሱ ስለ ውስጣዊ ሰውነታችን (ነፍስ) ተናገረ እንጂ፤ ርሱ ኹልጊዜ በመታደስ ጸንቶ ይኖራልና፤ አፍኣዊ ሰውነታችን (ሥጋ) ይሞት ዘንድ፥ እስኪነሣ ድረስም ይፈርስ፥ ይበሰብስ ዘንድ እንዳለው ነገሩ የታወቀ ነው፤ ውስጣዊ ግን አይሞትም፤ አይፈርስም፤ አይበሰብስም (፪ ቆሮ. ፬፥፲፮)።” (ሃይማኖተ አበው፣ ገጽ 263)። (ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና አባ እስጢፋኖስ ገጽ 232 የተወሰደ)

"ኢትእመኑ ሰብአ እንበለ ዋሕድ ሥላሴ በሳምናዊት ዘመን አምጣነ አልቦ መነኩሴ" የምትልና ከአበው የሰማኋት ጉባኤ ቃና ትዝ ብትለኝ ለጠፍኋት።

ዕድሜ ጠግብ የኾኑትን፣ በሌላቸውና ባልተጻፈላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ እየተቀባቡ፥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ ዘመን ዘለቅ የኾኑትን፥ ያለፈው ሳያንስ፥ አኹን ያለው ትውልድም ወደ ወንጌል እ
+2
ዕድሜ ጠግብ የኾኑትን፣ በሌላቸውና ባልተጻፈላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ እየተቀባቡ፥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ ዘመን ዘለቅ የኾኑትን፥ ያለፈው ሳያንስ፥ አኹን ያለው ትውልድም ወደ ወንጌል እውነት እንዳይደርስ ለማድረግ ዐልመው፥ በየጊዜው የሚነዙትን የስሕተት ትምህርቶች፥ እግር በእግር እየተከታተለ፥ ስሕተታቸውን ለማጋለጥ፥ የወንጌልን እውነት ደግሞ ለመግለጥ፥ እግዚአብሔር በሰጠው ሸክም ተግቶ በመሥራት በርካታ መጻሕፍትን ያበረከተልን ወንድማችን ቴዎድሮስ ደመላሽ፥ አኹንም፦ 1. ሃይማኖታዊ እንክርዳድ ቅጽ 2 2. ለሥዕሏ መስገድ ይገባልን? የተሠኙ ኹለት መጻሕፍትን አሳትሞ፥ መጻሕፍቱ በማተሚያ ቤት ይገኛሉ። “ዝናም የሌላት ደመና” በሚል ርእስ በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ዶ/ር መስከረም ሌቺሳ ለጻፈችው ማስረጃ አልባ መጽሐፍም ያዘጋጀውን ምላሽ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። የታተሙት ኹለቱ መጻሕፍት ከማተሚያ ቤት እንዲወጡና ወደ ተዘጋጀላቸው አንባቢ እንዲደርሱ፥ በቀጣይ ለሚያሳትመውም መጽሐፍ ከወንድማችን ጐን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንድናደርግና ዐብረነው እንድናገለግል እጋብዛለኹ። https://t.me/tewoderosdemelash

“በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፥ እንደ መንፈስ ቅዱስ ችላ የተባለ ወይም ያልታወቀ ከሦስቱ አካላት የለም። ለምሳሌ በአኹኑ ጊዜ (መጽሐፉ የታተመው በ1987 ዓ.ም. ነው)፥ በዐዲስ አበባ 56 አብያተ ክርስቲያናት አሉ። በመንፈስ ቅዱስ ስም የታነጸ ግን አንድም የለም። የሥላሴ 2፥ የእግዚአብሔር አብ 3፥ የመድኀኔ ዓለም 7፥ ይህም ከማርያም ስለ ተወለደ እንጂ ማን ዙሮ አይቶት አያ፥ በጠቅላላ በአስማተ ሠለስቱ ሥላሴ አሐዱ አምላክ 10 አብያተ ክርስቲያናት አሉ። የተቀረው ግን በማርያም፣ በመላእክት፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታት ስም ነው። ምስኪን የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ መንፈስ ቅዱስ ግን፥ አንድም እንኳ የለውም። ያመት እንጂ የወር በዓልም የለውም። ሰዎች ሲደነግጡ፥ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሲሉ በቀር፥ ስሙን ማን አንሥቶት አያ! ከእነዚሁም በጣም ካልደነገጡ በስመ አብ ብቻ ብለው ዝም የሚሉ አሉ።” (ዓለማየኹ ሞገስ፣ ኹሉም ኹሉን ይወቅ፣  ገጽ 140)።

Agizachew Tefera - Telegram kanali @agiztefera statistikasi va tahlili