cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
31 477
Obunachilar
-1624 soatlar
-1137 kunlar
-58030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
ከንቃትህ ወዲያ! ፨፨፨////////፨፨፨ ንቃተ ህሊና፣ ንቃተ ነፍስና ንቃተ አካለ ለተወሰነ ጊዜ አስፈላጊ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ያሰብክበት ለመድረስ ግን የምግባርን /Discipline/ ያክል የጎላ ድርሻ የላቸውም። ንቃት ጊዜያዊ ነው፤ ምግባር ዘላቂ ነው። ንቃት ቅፅበታዊ ነው፤ እንዲሁም የጠበቀ ህግና ስረዓት ላያስፈልገው ይችላል። ምግባር ግን የእራሱ ህግና ስረዓት እንዲሁም ቅድመተከለ አለው። ምግባር ሲኖርህ ተጨማሪ ህግና ስረዓት የማርቀቅ ግዴታ የለብህም። እራሱ ምግባርህ ህግህም ስረዓትህም ነው። ማንም ሰው ሁሌም እራሱን እያነቃቃ አይሰራም። ስራህ በእራሱ አነቃቂህ ካልሆነ ከባድ ችግር ውስጥ እንደሆንክ እወቅ። ምግባር ስቃይ አለው፣ ህመሙ ሙሉ ሰውነትን ይወራል፣ ውስጥን ያላውሳል ነገር ግን ውጤቱ ስሜትን ያድሳል፣ ሰውነትን ያሳርፋል፣ ውስጥን ያረካል። ተነቃቅቶ አንድ ሰሞን ሆ ብሎ ከመነሳት ይልቅ እራስን ገዝቶና እራስን አሳምኖ ስራውን በዘላቂነት ማስቀጠሉ እጅግ ትልቅ ፋይዳ አለው። በብዙዎች ዘንድ አንቱታን ያተረፉ ሰዎችን ተመልከት። መነቃቃት አስጀመራቸው እንጂ የዛሬው ከፍታ ላይ አላደረሳቸውም፣ የቀደመ ንቃታቸው መንገድ ጠቆማቸው እንጂ መንገዳቸውን በሙሉ አብሯቸው አልተጓዘም። አዎ! ጀግናዬ..! ከንቃትህ ወዲያ፣ ከስሜትህ ባሻገር፣ ከሁኔታዎች በላይ ምግባር ያስፈልግሃል። ቀጣይነት ያለው፣ የማይቋረጥ ሁሌም በተሻለ ደረጃ እየጨመረ የሚሔድ በቆራጥነት የተደገፈ የማይወላውል ምግባር። በስቃንም ሆነ በደስታው ጊዜ፣ በተመቻቸ ወቅትም ሆነ ነገሮች በተወሳሰቡ ሰዓት የማይወላውል እውነተኛ ምግባር። የጊዜ ገደቡ በዓመታት የሚለካ አልያም ከስራው ክብደትና ቅለት አንፃር ሊወሰን ይችላል። ሁሌም ምቾት የለም፣ ሁሌም መደላደል አይኖርም። ምናልባት ከባድ ሁኔታዎችን እየሸሸን ምቾትን በማሳደድ ብንጠመድ ግን የምንገነባው ማንነት ልፍስፍስና በቀላሉ የሚሰበር መሆኑ አይቀርም። ተስፈኞት ሁሌም በምግባራቸው ያምናሉ፣ ከሁኔታዎች በላይ የሚገዛቸው ፍላጎትና ምኞታቸው ነው። ንቃትህ ሁሌም አብሮህ ላይኖር ይችላል፤ ምግባር ግን ንቃት ባሌለበትም ሊኖር ይገባል። እድገትህ በምግባርህ ልክ በፅናትህ መጠን ነው። ውጤታማነትህ በአንድ ሰሞን መነቃቃትና ወከባ የሚፈጠር አይደለም። በምግባር የተቃኘ ወጥነት ያለው የማያቋርጥ ጥረት ያስፈልግሃል። አዎ! ብዙ የሚያነቃቁ ነገሮች አይተህ፣ ሰምተህ ለጊዜው ነቅተህ፣ ለትግበራም ተነሳስተህ ይሆናል። በነቃህ ሰዓት የጀመርካቸው ዛሬ ግን ያቋረጥካቸውን፣ የገባህ ሰዓት ለማቆም የወሰንከውና ለጊዜው ያቆምከው ዛሬ ግን ረስተሀው በነበርክበት የተገኘሀው፣ በሌሎች ተበራተህ ሌሎችን አይተህ ጉዞ ጀምረህ በምግባር እጦት፣ በፅናት እጥረት ምክንያት ከመሃል የቀረህባቸውን ሁነቶች አስታውስ። ንቃት እንድትጀምር ሊያደርግህ ይችላል፤ የሚያስፈፅምህ ግን ፅናትህ ነው። ስሜትህን የሚገልፅ፣ የሆድህን የሚያመላክት ንግግር በሰማህ ጊዜ የመረጋጋት ስሜት ሊሰማህ ይችላል። ዘላቂውና ፈዋሹ ስሜት ግን በቀጣይነት የምትገብረውና የምትኖረው የምግባር ህይወት ነው። ንቃት ይኑርህ፣ ብስለት አክልበት፣ ምግባርን ጨምርበት፣ ፅናትን አክልበት። በሚያንፁ ቃላት ተሞላ፣ በሚያረጋጉ ንግርቶች ተረጋጋ፤ እራስህን አንፅ፤ ተግባር ላይ አተኩር፣ በየጊዜውም መሻሻልህን ቀጥልበት።
Hammasini ko'rsatish...
👍 9 4
ለምን አላደርገውም? ፨፨፨፨/////////፨፨፨፨ ለምን አስፈለገ? መማር፣ ማንበብ፣ ማጥናት፣ ብሎም ጠንከሮ መስራት ለምን አስፈለገ? ለምን ይህን ያክል ትደክማለህ? ለምንስ አርፈህ ያገኘሀውን ተቀምጠህ አትበላም? እኮ ለምን? ለማን ሲባል ዋጋ ትከፍላለህ? ለምንስ እራስህን ታስገድዳለህ? እራስህን ታስጨንቃለህ? እራስህን ታደክማለህ? ህይወትህንስ ለምን ታወሳስባለህ? እኮ ለምን? ጥሩ ጥያቄ ነው። እርግጥ ነው፤ መጨናነቅ አያስፈልግም። ፈታ በሎ መኖር፣ ህይወትን ቀለል ማድረግ፣ እንደተመቸን መኖር ግድ ይለናል። እንግዲያውስ ይህን ሁሉ ነፃነት የሚሰጠንን ነገርስ ብናደርግ ምን ችግር አለው? ለምንስ አናደርገውም? አለማንበብ ትችላለህ ነገር ግን አዕምሮህን የእውቀት ድርቅ ታስመታዋለህ፤ አለማጥናት ትችላለህ ነገር ግን ፈተናህን መውደቅህ አይቀርም፤ ህልምህን አለመኖር ትችላለህ ነገር ግን ነፃ ልትወጣ አትችልም፤ ምክንያት በመደርደር ትችላለህ ነገር ግን በስተመጨረሻ ምክንያትህ ውጤት አይሆንህም። አዎ! ጀግናዬ..! ለምን አደርገዋለሁ? ብለህ ከጠየክ ቦሃላ ለምንስ አላደርገውም? በለህ እራስህን ጠይቅ። የምትፈልገውን አይነት ህይወት እንድትኖር የሚያደርግህ ከሆነ ለምን እራስህን አትገዛም? የአስተሳሰብ፣ የገንዘብና የተግባር ነፃነት የሚሰጥህ ከሆነ ስለምን ደጋግመህ እራስህ ላይ አትሰራም? ስለምን ጠንክረህ አትፋለምም? ስለምንስ እራስህን ነፃ አታወጣም? ስለምንስ ከሰዎች እጅ በመጠበቅ ጊዜህን ታጠፋለህ? በሂደት የተገነባውን ማንነትህን መመልከት አትፈልግምን? ከእራሱ በተሻለ ለሰዎች መትረፍ የሚችለውን፣ ለእራሱም ሆነ ለሌሎች ትርጉም ያለውን ህይወት ማጎናፀፍ የሚችለውን ሰው መሆን አትፈልግምን? ያንተ አለም ያንተ ነው፤ ማሟላት የሚገባህን ግብዓት በቅድሚያ የምታሟላው ለእራስህ ነው። አዎ! ለምን ማንበብ የሚገባህን መፅሐፍ አንብበህ እውቀትህን አትመዝንም? ለምን ወደፊት ተጉዛህ አዲስ ነገር አትመለከትም? ለምን አጥንተህ ፈተናህን አትሰራውም? ለምን የቻልከውን ሞክረህ ህይወትህን አትቀይርም? ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ምላሽ ሊኖርህ ይችሃል፤ ነገር ግን ምላሹን በሰጠህ ልክ ከደረጃህ በታች ለመኖር እራስህን ማዘጋጀት ይኖርብሃል። በእርግጥ አቅምህ ቁጭ ብሎ ያገኙትን እየበሉ መተኛት እንዳልሆነ ታውቀዋለህ፤ በአመለካከት ማደግና መቀየር እየቻሉ በወረደ አስተሳሰብ የችግር መንስኤ መሆን እንዳልሆነ ታውቃለህ፤ በእራስ ጥረት ከፍ ማለት እየተቻለ ከሰው እጅ መጠበቅ እንዳልሆነም ታውቃለህ። እንግዲያውስ "ለምን ትለፋለህ?" የሚለህን ሃሳብ አንተም "የተሻለ ህይወት ለመኖር ለምን አልለፋም? ለምን አልጥርም? ለምንስ በተለየ መንገድ አልሞክርም?" ብለህ ሞግተው። የእራስህን ንግግር፣ የውስጥ ጥያቄህን ስትመልስ ውጫዊው አለም ባንተ ቁጥጥር ስር እንደሚሆን አትጠራጠር።
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
ለአሁን ተገዛ! ፨፨፨////፨፨፨ መነሻህ የት ነበር? መሰረትህ የተጣለው የት ነው? የትናንትናህ ገፅ ምን ይመስላል? የታሪክህ መልክ ዛሬም በአይንህ ላይ እየመጣ ያስጨንቅሃልን? አልፏል፣ አብቅቷል ያልከው ያለፈ ክስተት አሁን እየመጣ ህይወትህን እያወከ ነውን? የሰው ልጅ ብርቱ ሰልፍ አለበት። በትናንቱ ጠባሳ ዛሬውን ያበላሻል፣ ለነገ ምኞቱ ብሎ አሁን በሃሳብ ይብሰለሰላል። ትናንትና ነገ ወደፊትና ወደኋላ እየጎተቱ ዛሬውን እንዲዘነጋ ያደርጉታል። የት ሆነህ እንደምትጨነቅ አስተውል። ታሪክህም ምኞትህም ታሪክና ምኞት መሆናቸው የታወቀው አሁን ነው። የትናንት ታሪክህ ትናንት ታሪክህ ሳይሆን ህይወትህ ነበር፣ የነገ ምኞትህ ነገ ምኞትህ ሳይሆን እውነታህ ወይም ባዶ ቅዠትህ ሊሆን ይችላል። ለጊዜው ገደብ ብናበጅም ትክክለኛው ነፍስ ያለው ተዓምረኛው ጊዜ ግን ዛሬና አሁን ብቻ ነው። ለአሁን ተገዛ፣ ለዛሬ እራስህን ስጥ። ትናንትና ነገ መሃል ሆነህ አትብሰልሰል፣ ባለፈ ጊዜና በመጪው ጊዜ ክስተቶች አዕምሮህን ሰላም አትንሳው። አርቀህ ብትቆፍር እንኳን ትናንትን ልታገኘው አትችልም፣ በላቀው ከፍታ ላይ ብትንሳፈፍም እንኳን ነገን ልትጨብጥ አትችልም። የትም ብትሔድ የምትኖረው ዛሬና አሁን ውስጥ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ለአሁን ተገዛ! ዛሬ ነገ ማለት ይብቃህ፣ ቀናንት ሳምንታት ወራት ዓመታትን መቁጠር አቁም። ጨከን ማለትን ተለማመድ፣ ዛሬ አሁን እራስህን ለመግዛት ተነስ፣ አሁን የእራስህ አለቃ ለመሆን ተዘጋጅ፣ አሁን ከሺህ እርምጃዎችህ አንዱን መራመድ ጀምር። የሁሉም ነገር ሚስጥር ትናንት ወይም ነገ ውስጥ ሳይሆን ዛሬና አሁን ውስጥ እንደሆነ አስተውል። ምድርን የሚመሩ ሰዎች ከዛሬያቸው ያተረፉ፣ አሁን አሻራቸውን ማስቀመጥ የቻሉ ሰዎች ናቸው። ድፍረት፣ ተነሳሽነት፣ ብርታት፣ እምነት ሁነኛ ስንቃቸው ነው። በሀሳብ ከመዋተት፣ በባዶ ምኞት ከመሰቃየት፣ በህልምና በቅዠት ብቻ ከመስከር ዛሬን ምርጫቸው ያደረጉ ሰዎች ናቸው። የሰው ልጅ ከፈጣሪው በታች የሚኖርባትን ምድር ይገዛ ዘንድ ስልጣኑ አለው። ስልጣኑን ለመጠቀምም ይብዛም ይነስም በሂደት ውስጥ የመሆን ግዴታ አለበት። ለሁሉም ሰው መንገድ አለ፣ የእውቀትና የብስለት መንገድ። ማንኛውም ሰው እራሱን የሚያበቃበት መንገድ አለው፣ እራስህን የመሆንና ስሜትን የመግዛት መንገድ። ብስሉን ከጥሬው፣ ብርቱውን ከሰነፉ፣ ስኬታማውንም ከአማራሪው የሚለየው ወንፊት የጊዜ አጠቃቀም ወንፊት ነው። የዛሬ ሰው መሆን ሲገባው ትናንት ውስጥ የሚጨፍር ሰው በወንፊቱ ቀዳዳ ወደ መሬት መውረዱ አይቀርም፣ እንዲሁ አሁን አብቦና ፈክቶ ነገውን በውብ ገፅታ መቀበል ሲኖርበት በነገ ምኞትና ቅዠት ዛሬውን በዋዛ ፈዛዛ፣ አሁኑን አቋራጭ መንገድ በማሳደድ የተጠመደው ሰውም ከወንፊቱ ላይ ንፋስ እንደወሰደው ብናኝ ቆሻሻ ነው። አዎ! ሀሳብ ካለህ ታዓምሩ በእጅህ ነው፣ እቅድ ካለህ ሃይሉ በሰውነትህ ውስጥ ነው። ወደድክም ጠላህም እምነትህ ሲገዛህ ኖሯል ወደፊትም ሲገዛህ ይኖራል። የምታውቀው ሌላ የምትኖረው ሌላ ቢሆንብህ፣ ምኞትህ ሌላ ተግባርህ ሌላ ሆኖ ካስቸገረህ ትግልና ጭንቀቱን አቁመህ የገዛ እምነትህን መርምር። "በእርግጥ ሀሳቤ አሳምኖኛልን? በእርግጥ አቅዴ ግልፅና ተግባራዊ ነውን?" ብለህ እራስህን ጠይቅ። አሁን የምታደርገው የትኛውም ተግባር ህይወትህ ነው። የምትመራት ትንሽዬ ዓለም በልብህ ውስጥ አለች፣ ትገዛት ዘንድ ፍቃድ የተሰጠህ የእራስህ የግል ደሴት አለችህ። ማንንም ጣልቃ ሳታስገባ፣ ማንም መሪዋን ሳይጨብጥ ብቻህን እየመራህ የምታሳካው ህልም አለህ። የተግባሩም ጅማሮ አሁን ነው፣ ትክክለኛው መነሻውም አሁን ነው። ቁጪት ትናንትን አይመልስም፣ ምኞትም ነገን ዛሬ አያደርገውም። ለአሁንህ ስልጣን ስጥ፣ ከዛሬህ በአግባቡ አትርፍበት። የትናንት ስህተትህን አሁን አርም፣ የነገ ምኞትህንም ዛሬ መገንባት ጀምር። "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ" ተብሎ የተተረተው ተረት ባንተም ሳይተረት ያልተጨበጠ ምኞትህን ትተህ ወደ ተጨባጭ ተግባር ግባ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
ምንድነው የምትሰጠው? ፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨ እንደ አንድ ጥሩ ሰው፣ እንደ አንድ ብርቱ ለሰው አዛኝ ሰው፣ እንደ አንድ ቅንና የዋህ ሰው ይበልጥ የሚያስጨንቅህ ነገር ምንድነው? የምትሰጠው ወይስ የምትቀበለው? የምታደርገው ወይስ የሚደረግልህ? የምታስገኘው ወይስ የምታገኘው? የምታስጨምረው ወይስ የሚጨመርልህ? ለየትኛው ይበልጥ ትኩረት ትሰጣለህ? ልብህ ለየትኛው ያደላል። መቀበል የለመደ ሰው ደስታው ሁሌም የሚሰጠውን ነገር በማሰብ የሚያገኘው ነው። መስጠትን የለመደ ደግሞ ሲሰጥ ብቻ የሚያገኘውን ደስታ በሚገባ ያውቀዋል። አዲስ ነገር ሲደረግልህ እንደምትደሰተው ሁሉ አዲስ ነገር ለሰዎች ማድረግም ደስታን ሊሰጥህ ይገባል። የጠበከው ነገር ሲከናወንልህ ልብህ ሃሴት ያደርጋል፤ ብዙዎች የሚጠብቁትም ባንተ በኩል ሲደረግላቸው ያንተን ስሜት አዳምጥ። አዎ! ጀግናዬ..! ምንድነው የምትሰጠው? እንደ ማንኛውም ሰው "ምን አለኝና" አትበል። ምንም ባይኖርህ መስጠት እንደምትችል መለማመድ ይኖርብሃል። ነገር ግን ማንም ምንም ሳይኖረው፣ ምንም ሳይሰጠው፣ ምንም የሚያካፍለው ሳይታደለው የተፈጠረ ሰው የለም። ትኩረታችን ሁሉ ሰዎች ላይ ሆኖ ያለንን ነገር ግን ማስተዋል ያልቻልን ብዙዎች ነን። ባለው ነገር የሚመካ፣ በተሰጠው ነገር ደረቱን የሚነፋ ሰው ቢኖር አለኝ የሚለው ነገር ሲጠፋ ተሽመድምዶ እንደሚቀመጥ ምንም ጥርጥር የለውም። ኩራትህ በተሰጠህ፣ ባገኘሀው ወይም በታደልከው ሳይሆን በምትሰጠው፣ በምታጋራውና በምታካፍለው ይሁን። የሚያኮራህ ነገር አንተ ጋር ያለ ነገር ሳይሆን ካንተ የሚወጣ ነገር ይሁን። አዎ! ሌላው ባይኖርህ ተስፋ አለህ፣ ብርታት አለህ፣ ቅንነት አለህ፣ ደግነት፣ መልካምነት፣ የዋህነት አለህ። ሰዎችን ከዚህ በላይ ለረጅም ጊዜ የሚጠቅማቸው ነገር የለም። የምትሰጣቸው ገንዘበ ለጊዜው ችግራቸውን ይፈታል፤ የምታጋረቸው ንብረት ለተወሰነ ጊዜ የተሻለ ህይወት ያሳያቸዋል፤ በየጊዜው የምትመግባቸው የተስፋ ቃል፣ እንደ ቀላል ጆሮ ሰተህ የምታዳምጣቸው፣ ሲፈልጉህ አለሁላችሁ የምትላቸው፣ ብርታትን የምታካፍላቸው ነገር ግን ከምታስበው በላይ ዋጋህን ይጨምራል። ሁሌም ቢሆን ከምትቀበለው የምትሰጠውን አስበልጥ፤ ከሚደረግልህ ለሰዎች የምታደርገውና የምታካፍለው ነገር ላይ አተኩር፤ መስጠትን፣ ማጋራትን ልመድ፤ ውስጥህንም በመትረፍረፍ ሙላው።
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
ለመልካም ሆነልኝ! ፨፨፨፨///////፨፨፨፨ ከራስ ጋር ንግግር፦ "ደክሞኝ ነበረ ድካሜ ግን ለበጎ ሆነልኝ፣ ጨንቆኝ ነበረ ጭንቀቴ ግን ለመልካም ሆነልኝ፣ ህይወት ከብዳኝ፣ መፈናፈኛ አሳጥታኝ፣ ልቤንም አውካት ነበረ ክብደቷ ግን አጠነከረኝ፣ መታወኬም አረጋጋኝ። ሰውነቴ ደካማ ነው። ይዝላል፣ ይታክታል፣ ይወድቃል። ነገር ግን በዛው ዝሎ አይቀርም፣ በዛው ወድቆ አይቀርም። እኔ መነሳት ባልችል የሚያነሳኝ የአምላኬ መንፈስ በውስጤ አለ፣ እኔ እራሴን ማሳረፍ ባልችል የሚያሳርፈኝ የፈጣሪዬ ሃይል በእኔ ላይ አለ። ለዘመናት በእራሴ ስታመን ኖሬያለሁ፣ ለዘመናት ክንዴን ተማምኜ ፈተና ውስጥ ገብቼያለሁ። የታመንኩበት ግን ፍፃሜዬን እንደጠበኩት አላደረገልኝም። የጠበኩት ሌላ የሆነልኝም ሌላ ሆኖብኛል፣ ተስፋዬ ሌላ የገጠመኝ ሌላ ሆኖብኛል። ቢረፍድም የቱጋር እንደሳትኩ አሁን ገብቶኛል። ብዙ እያጠፉ መመለሻ ከሌለው የጥፋትና የፈተና መንገድ የታደገኝ ማንም ሳይሆን ፈጣሪዬ ነው። በአጉል እምነት ከጠፋውበት ከዛ ከሳትኩበት ስውር የህይወት አቅጣጫ እርሱ ታደገኝ። እሔዳለሁ ነገር ግን የት እንደምሔድ አላውቅም፣ እሰራለሁ ነገር ግን ለምን እንደሆነ አላውቅም፣ ህይወቴ ሁሉ ትግል ነው ነገር ግን ትግሌ ማንን ለመጣል እንደሆነ አልተገለጠልኝም። አዎ! ጭንቀቴ ሁሉ ለመልካም ሆነልኝ፤ ስቃይ መከራዬ ሁሉ ለበጎ ሆነልኝ። የብዙዎችን የሞት ደብዳቤ ወደ ህይወት የቀየረ፣ የብዙዎችን የጠፋ ተስፋ ዳግም ያለመለመ፣ የብዙዎችን ምስቅልቅል ህይወት የታደገ አምላክ ለእኔም ደርሶልኛል። ማንም በሌለኝ ሰዓት እርሱ ነበረ። ለምድራዊ ፈተና የተወኝ መስሎኝ ነበር፣ በጥፋቴ ምክንያት በብቸኝነት እየቀጣኝ እንዳለ ተሰምቶኝ ነበር፣ የገጠመኝን የህይወት ውጣውረድ እየተመለከተ ችላ ያለኝ ፊቱንም ያዞረብኝ መስሎኝ ነበር። ነገር ግን ሁሉም የእኔ ሀሳብና አረዳድ እንጂ የእርሱ ማንነት አልነበረም። እርግጥ ነው የገባኝ ከረፈደ ነው ነገር ግን ትልቁ ደስታዬ የፈውስ እልፍኙ ሳይዘጋ ከደጁ መድረሴ ለመዳንም ወደ ውስጥ መግባት መቻሌ ነው። ማንም ሰው እስካልተገለጠለት ድረስ የእግዚአብሔር አሰራር አይገባውም። ምንም እንኳን ውጤቱ የሚገለጠው በገሃድ ቢሆንም አሰራሩ ግን በስውር ነው። በአጋጣሚ በውሃ የተሞላ ባልዲ ውስጥ ገብታ ለመውጣት እንደምትፍጨረጨረው ትንሽዬ የዶሮ ጫጩት እኔም እንዲሁ ሳላስበውና ሳላውቀው በገባሁበት የህይወት ፈተና ውስጥ ስፍጨረጨር ፈጣሪ ይመለከት ነበር። የእኔ ለቅሶና መከራ ፈፅሞ አልተሰወረበትም። እውቀትና ረቂቅነቱ በእርሱ አይን ከመጤፍ ከማትቆጠር ኢምንት አንድ የጤፍ ዘለላን በምታክል የእኔ ችግር የሚለካ አይደለም። እርሱ ስለሚችል ሁሉን ለመልካም አድርጎልኛልና ዘወትር ከልቤ አመሰግነዋለሁ፣ ያደረገልኝንም ደጋግሜ አወሳለሁ።" አዎ! ጀግናዬ..! መጥፎ የመሰለህ አጣብቂኝ ውስጥ ከሆንክ ጥሩ ነገር እየመጣ ነውና ታገስ፤ የማያልፍ የመሰለህ መከራ ከተደራረበብህ ከእርሱ ቦሃላ የሚበረከትልህ ሽልማት እንዳለ በልብህ እመን። የህይወት ፈተና በበዛ ትዕግስትና ፅናት መሳሪያነት የሚረታ ሁነኛ ጠላትህ እንጂ ዘመንህን በሙሉ እያሰቃየህ የሚኖር አይረቴ ባላንጣህ አይደለም። ቅዱሱ መጽሐፍም እንዲህ ይላል፦ "በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።" ወሰኙ የመከራህ ብዛት ወይም ክብደት ሳይሆን አብሮህ ያለው ፈጣሪህ ነው። ወፍጮ ቤት ብትገባ ዱቄት ይነካሃል በህይወት እስካለህም ፈተና ይገጥምሃል። በእይታህና በአረዳድህ ልክና መጠን ነገርን ሁሉ ለበጎ የማድረግ አቅሙ እንዳለህ አስተውል። ልክ ጠቢባን እንደሚያደርጉት ከመጥፎ አጋጣሚ ውስጥ በረከትህን መቁጠር ላይ በርታ፣ ልክ ብልሆች እንደሚያደርጉት ከፈተናው በላይ አስደሳቹ ውጤት ላይ አተኩር። የሆነብህ ክፉ ነገር ሁሉ ለመልካም ይሆንልህ ዘንድ ያንተ እምነትና አቀባበል ወሳኝ ነውና ከመጥፎ ውስጥ ጥሩውን ተስፋ አድርግ፣ ከስብራትህ ቦሃላም የሚያጠነክርህ ትዕግስት እንደሚሰጥህ እመን።
Hammasini ko'rsatish...
3👍 2
ሁሉም አይታመንም! ፨፨፨፨/////////፨፨፨፨ ዓለም ከእውነታው ይልቅ የሚጠቅማትን እንድታምንና እንድትቀበል ትፈልጋለች። ስለዚህ ከየአቅጣጫው እውነት የሚመስሉ፣ በአመኔታ ብንቀበላቸው የሚያተርፉልን፣ ብንጠቀማቸው የምንጠቀምባቸው የሚመስሉ እሳቤዎችን ልትጭንብን ትሞክራለች። ጥቅመኛ ሰውም ከዚህ የተለየ አላማ የለውም። በእራሱ ሃሳብ እንድታምን ያደርግሃል፤ የሚፈልገውን ያክል ይጠቀምብሃል ከዚም አርቆ ይጥልሃል። ብዙ የሽንገላ ቃላት ወዳንተ መጥተዋል፤ በተደጋጋሚ ተታለሃል፤ በንግግር ብቻ ትኩረትና እምነትህ ተወስዷል፣ በስሜት ብቻ እራስህን ሰተሃል። ነገር ግን እራስህን ከመስጠት ጀርባ ምን እንዳለ የምታውቀው ምን ነገር አለ? እንድታምንና እንድትቀበል የሚያደርግህ ላንተ ታስቦ መሆኑን እርግጠኛ ሁን። ሰው ተዋናይ ነው፤ መልኩን እንጂ ልቡን አታውቀውም፤ ንግግሩ እንጂ ሃሳቡ አይገባህም። ባንተ ደስተኛ የሆነ ቢመስልህም ከኋላ ሊያጠፋህ የሚያሴረው እራሱ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ። አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም አይታመንም! ሁሉም ሊጠቅምህ የመጣ አይደለም፤ ሁሉም ለውጥህን የሚፈልግ፣ መሻሻልህን የሚመኝ አይደለም። እምነት ማስረጃ ባይፈልግም አንዳንዴ ግን ጥልቅ አረዳድና የሰከነ አስተውሎት ያስፈልገዋል። ዛሬ ስለተነቃቃህ ህይወትህ አይቀየርም፤ አማኝ ነኝ ስላልክ ፍላጎትህ አይሳካም፤ የምትሰማው ሁሉ እውነትና ተጨባጭ ስለሆነ ህይወትህ ላይ ተፅዕኖ አይፈጥርም። ስለሰማሀው ሳይሆን ስላመንክበት ብቻ ህይወትህ ላይ አሻራውን ያሳርፋል። እምነት ተግባር ቢፈልግም ትርፍ አልባ እምነት ግን የውድቀት ምክንያት ይሆናል። በእራስህ መንገድ ስለሞከርክ፣ ኮፒ ስላላደረክ፣ በሌሎች ስኬት መጠራት ስላልፈለክ፣ እራስህን መሆን ስለመረጥክ እንደማይሳካልህ፣ እንደምትወድቅና እንደምትጎዳ ቢነገሩህ በፍፁም እንዳታምናቸው። አዎ! አዕምሮህ ሚዛን አለው፤ ጠቃሚውን ከጎጂው፣ ስንዴውን ከእንክርዳዱ፣ አሻጋሪውን ከአሰናካዩ፣ አበርታቹን ከአድካሚው በአስተውሎቱ ተጠቅሞ የመለየት አቅም አለው። ወደፊት መጓዝን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪነትን፣ ከፍታንንና ስኬትን የሚፈልግ ሰው ማንን ማመን ማንን አለማመን እንዳለበት ያውቃል። ከሁሉም በፊት በፈጣሪው ድንቅ ሃይል ያምናል፤ በመቀጠል ወደ ምድር መምጣቱ ለትርፍና ትልቅ ተዓምር ለመፍጠር እንደሆነ በሚገባ ያምናል። የማይናወጥ እምነትም በመሰረቱ ላይ የተደገፈ እምነት ነው፤ ይህም በአምላክ ድንቅ ሃይል ማመን ነው። ብዙ ተናጋሪ አለ፤ ብዙ ሞጋች አለ ሁሉም ግን የእውነት አሳማኝና ተጨባጭ ነገር አይናገርም፤ አይሞግተም። ከጥቅሙ አንፃር ሊያሳምንህ የሚጥርን ሰው ጥንቅቀህ እወቀው፤ ማመንህ ዝቅ የሚያደርግህ፣ አቅምህን የሚያሳንስ፣ ወደኋላ የሚያስቀርህና ተስፋ የሚያቆሮጥህ ከሆነ በቶሎ እይታህን አስተካክል። እምነትህ የመጣልም  የማንሳትም ሃይል እንዳለውም አስተውል።
Hammasini ko'rsatish...
1
ይበቁሃል! ፨፨////፨፨ የተለየ ትኩረት የሚፈልግ፣ በቂ ጊዜን የሚጠይቅ፣ በጊዜው መፍትሔ የሚያሻ ችግር አስቀምጠህ ስላልገጠመህና ስላልተከሰተው፣ ገና ለገና ይመጣል በሚል እሳቤ፣ ይፈጠራል በሚል ጥርጣሬ ባመጣሀው የተራዘመ ችግር አብዝተህ የምትጨነቅበት ምክንያት ምንድነው? የፈራሀው ቢፈጠር እንኳን ባልኖርከው ነገ በሚፈጠር ችግር ምክንያት የዛሬ እንቅልፍህን የምታጣው ስለምንድነው? ለእርሱስ ብለህ ዛሬ መኖር ያቆምከው፣ በስጋትና በፍረሃት የምትሰቃየው ለምን ይሆን? ዛሬ መፍታት ከምትችለው ተጨባጭ ችግር በላይ ላልደረሰብህና ላልሆነው ግምታዊ ችግር የበለጠ ትኩረት የምትሰጠው ለምንድነው? አዎ! ወደፊት ፈተና አለብህ ዛሬ ማንበብና መዘጋጀት ከቻልክ ግን ፈተናው ችግር ሊሆንብህ አይችልም። ወደፊት ውጤቴ ሊበላሽ ይችላል በሚል ሃሳብ ትጨነቃለህ፣ ዛሬ ግን እንዴት ማንበብ እንዳለብህ አታስብም፤ በምን መንገድ ውጤታማ እንደምትሆን ማሰላሰል አትፈልግም። ዛሬ የፈለከውን ባለማድረግህ፣ የመረጥከውንም ባለመኖርህ የነገ እጣፋንታህ ያሳስብሃል። ችግር እያለብህ ሌላ ተጨማሪና ያልተፈጠረ ችግር አትጥራ። መጪዎቹን ችግሮች ማስቀረትና ስጋታቸውን መቅረፍ ከፈለክ አሁን ያጋጠመህን፣ አሁን በእጅህ ላይ ያለውን ችግር ፍታው፣ ቅረፈው፣ መፍትሔ ስጠው። አዎ! ጀግናዬ..! ይበቁሃል! ያለህ ይበቃሃል ማለት ችግሮችህንም እንደሚያካትት አስታውስ። የዛሬዎቹ ችግሮችህ፣ የዛሬዎቹ ፈተናዎችህ ብቻቸውን አንተን ለማሳሰብና ለማስጨነቅ እጅጉን በቂ ናቸው። ነገ የባሰ ችግር ይዞ ይመጣል? ይምጣ! እስካሁን ግን የተለየ ነገር አልተመፈጠረምና ገና ለገና በሚፈጠር ችግር መጨነቅ አይኖርብህም። ዛሬ ችግር ውስጥ ከሆንክ ምርጫህ አንድ ነው፤ እርሱም በየትኛውም መንገድ የመፍትሔ ሰው መሆን። ወደፊት ግን ሁለት ምርጫ አለህ፤ እርሱም በችግሩ መኖርና አለመኖር የሚወሰን ሲሆን፣ የጠበከው ችግር ቢፈጠር እንኳን ያለጭንቀት የመፍትሔ ሃሳብ አዘጋጅቶ መጠበቅ፣ ችግሩም ካልተፈጠረ ተረጋግቶ ህይወትን ማጣጣም።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
በማያዋጣሽ እራስሽን አትግለጪ! ፨፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨፨ ቆንጆ ነሽ፤ ገፅሽ ውብ ነው፤ ደምግባትሽ ያስደንቃል፤ ተክለ ቁመናሽ ያምራል፤ አንደበትሽ ይማርካል፤ የተመልካችን ቀልብ በቀላሉ ትስቢያለሽ፤ ለሚያይሽ ሁሉ የውበት መለኪያ ነሽ። አምላክ በስራው ፍፁም ቢሆንም የሰው ልጅ ግን ህፀፅ ማውጣት ባይሳነውም ካንቺ ላይ ግን አንዳች እንከን አያገኝም። የፈጣሪን ድንቅ ስራ ቁልጭ አድርገሽ የምታሳይ፣ የእጅ ስራውን ፍፁምነት የምታስረጂ ነሽ። ነገር ግን አንቺን የማያረካሽ፣ የማያስደስትሽ፣ በእራስ መተማመን የማያድልሽ ውበት ምንድነው? ሰው የሚያይሽን ያክል እራስሽን እስከምን ትመለከቺያለሽ? ከቁንጅናሽ በላይ፣ ከውበትሽ ባሻገር ስላንቺ የገባሽ ነገር ምንድነው? በቁንጅናሽ ሽፋን የምታልፊው የሰውነት ሚዛን የለም። ማራኪ ሴት ልትሆኚ ትችያለሽ ልኬትሽ ግን ሰውነት ነው፤ መጨረሻሽ ግን እንደ ሰው ኖሮ እንደ ሰው ማለፍ ነው። አዎ! ጀግኒት..! በማያዛልቅሽ እራስሽን አትወክይ፤ በማያዋጣሽ እራስሽን አትግለጪ። አብዝቶ ስለ መልክና ቁመናሽ ማውራት የለመደው አንደበትሽ ቦሃላ እራሱን መግለፅ እንዳይከብደው ተጠንቀቂ። ስለ እራስሽ ስታስቢ የሚያምረው ገፅሽ፣ ማራኪው ቁመናሽና አማላዩ አረማመድሽ ብቻ የሚታወስሽ ከሆነ በቅጡ የማታውቂያት ሌላ ሴት በውስጥሽ አለችና እርሷን ፈልጊያት። ልኬትሽን በጊዜያዊ ነገር አትተመኚ፤ አንቺ ከእርሱ እንደምትበልጪ አስቢ። ያንቺ ያለሆነ ነገር የትምክህትሽ ምክንያት ሊሆን አይገባም። አንድ ሰሞን ያለኔ ሴት የለም ብትይም ከጊዜ ቦሃል ግን በመልክም ሆነ በቁመና የሚተካሽን ታገኚያለሽ። ከመልክ በላይ በላቀው መገለጫ ማንም ሰው የማይወክላትን ሴት መፍጠር እንደምትችይ አስቢ። የምትታወቂበት ልባምነት፣ የሚገልፅሽ መልካምነት፣ አንቺን የሆነው ውሳጣዊ ባህሪሽ አንቺ ባለሽበት ሁሉ ይኖራልና በእርሱ ተደገፊ፤ እርሱን ጠበቅ አድርገሽ ያዢ። አዎ! ጀግናዬ..! ከቁመናህ፣ ከመልከመልካምነትህ፣ ከእውቀትህ፣ ከስራህ፣ ከውሎህ፣ ከሃሳብህ የላቀ ማንነት እንዳለህ አስተውል። ልኬቴ ነው የምትለው ትንሽ ነገር አይወክልህም። የዛሬ ከብዙዎች አንሶ መገኘት፣ በችግር መዓበል መናጥ፣ የጭንቀት ቋት መሆን አይገልፅህምና አያሳስብህ። ማንነትህን አሳንሰህ፣ የማይገባህን ስም ለእራስህ ሰተህ፣ ያልሆንከውን ለመሆን እየጣርክ የምትቀዳጀው ድልም ሆነ የምትደርስበት ከፍታ አይኖርም። ለእራስህ መታመን ከቻልክ፣ እራስህን የሚወክል፣ የሚገልፅህ ትክክለኛ ገፅታ መገንባት አይከብድህም። እራስህን መልቀቅ ጀምር፣ ከፊቱ የሚታዩትን አስፈሪና እስጨናቂ ስጋቶች አርቅለት፤ እራሱን በጉልህ ያወጣው ዘንድ ነፃ አድርገው። የአምላክ ህግጋት የህይወት መርህ ናቸው፤ ያንተም የሰውነት ልኬት ህግጋቱን መጠበቅና ፍቃዱን መፈፀም ነው። ያንተ የሆነ አንዳች ነገር የለም፤ ሁሉም ተሰቶህ ለጊዜው አንተን ፈጠረ። በሂደትም እየተሻረና እየተቀየረ መሔዱ አይቀርም። ለኩራትና እራስን ለመውደድ አምላክ የሰጠህ ሰውነትና ውስጥህ ያስቀመጠው መንፈሱ በቂ ናቸው። እናም መመካትን በማይነጥፈው አምላካዊ ሃይልህ፣ ኩራትንም በሰውነትህ ላይ አድርግ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
ትግልህ ያገናኝሃል! ፨፨፨፨///////፨፨፨፨ ከታላላቆቹ፣ ከተፅዕኖ ፈጣሪዎቹ፣ ከዝነኞቹ፣ ከስኬታማዎቹ ትግልህ ያገናኝሃል፤ ፅናትህ፣ ብርታትህ፣ ልፋትህ፣ ላመንክበት ነገር እስከ ጥግ መፋለምህ ያመሳስልሃል። በእራስህ የፈጠርከው ደስታ፣ እራስህን ለማብቃት የምታደርገው ጥረት፣ የምትጓዝበት መንገድ ከእነርሱ ያቆራኝሃል። እንደ ማንም መደበኛ ሰው ሳትጀምር አታቆምም፤ ምንም ሳትጓዝ አትደናቀፍም፤ ሳትሰራ ውጤት አትጠብቅም፤ ሳትለፋ፣ ሳትተጋ ሸልሙኝ አትልም። ግዴታህን በሚገባ ተረድተሃልና እርሱን ለመወጣት ወደኋላ አትልም፤ ማንም ሊያደናቅፍህ ቢሞክር የምትሰማበት ጆሮ የለህም፤ አይንህ እርሱን አይመለከትም። የውስጥህን ለማውጣት የሚጥረው ማንነትህ እንኳን ለማይመለከትህ ውጫዊ ችግር ይቅርና ለግል ችግርህ እራሱ አይበገርም። አዎ! ጀግናዬ..! ትግልህ ያገናኝሃል! ፅናትህ፣ በእራስ መተማመንህ፣ ለምንም አለመበገርህ፣ በየጊዜው የሚጨምረው ፍላጎትህ፣ ካልኖርከው እንቅልፍ የሚነሳህ ህልምህ ያመሳስልሃል። በስራህ ብቻ ተመሳስለሃቸው፣ በማንነት ብቻ ተቆራኝተሃቸው አትቀርም፤ ውጤትህም ከእነርሱ ጋር ያገናኝሃል፤ በምታየው የሚያምር ፍሬም ትመሳሰላቸዋለህ፤ ከእነርሱ ትገናኛለህ፤ የተቀዳጁትን ድል አንተም ትቀዳጃለህ፤ ከመዳረሻቸው ትደርሳለህ፤ ድላቸው ያንተም ድል ይሆናል፤ ልክ እንደነርሱ በእራስህ ለመኩራት ምንም እስኪኖርህ አትጠበቅም። መንገዳችሁ አንድ ነውና በየመንጋዳችሁ እድሎችን መፍጠር የየለት ስራችሁ ነው፤ ከእራስ በላይ መኖር፣ ለሰዎች መትረፍ፣ ለወገን መድረስ የየለት ስራችሁ ነው።  ያላመኑብህ ሰዎች ጥረትህን አይተው ያምኑብሃል፤ ያልተቀበሉህ ሰዎች በውጤትህ ተገደው ይቀበሉሃል፤ የናቁህ ሁሉም የለውጥ ሂደትህን ተመልክተው ያከብሩሃል፤ ያነግሱሃል። አዎ! መንቃት ያለብህ ማንንም ለማስደነቅ  ባይሆንም ብዙዎችን ማስደነቅህን ግን አታቆምም፤ አንተ ሳትሆን ስራህ እጃቸውን በአፋቸው ያስጭናቸዋል፤ መቀየርህ ያስገርማቸዋል፤ እራሳቸውን እንዲመለከቱ፣ የተናገሩህ ነገር ስህተት መሆኑን፣ ስላላመኑብህ እንዲፀፀቱ ታደርጋቸዋለህ። ከእምነታቸው ውጪ ምንም አልጠየካቸውም ነበር ነገር ግን በምትኩ ሊጥሉህ ሲሞክሩ አይተሃል፤ እራስህ ላይ ያለህን በእራስ መተማመን ለማጥፋት ሲጥሩ ተመልክተሃል። ይህ ግን የታላላቆቹን መንገድ እንዳትከተል አላደረገህም፤ የስኬታማዎቹን ልማድ እንዳታዳብር አላደረገህም፤ በመረጥከው አዋጭ መንገድ እንዳትገፋ አላደገህም። የሚያዋጣህ ይህ መንገድ ነውና በፍፁም ጀርባህን እንዳታይ፤ የሚያደናቅፉ የአካባቢ ወሬዎችን እንዳትሰማ፤ መዳረሻህን ደጋግመህ ተመልከት፤ ህይወትህን እያጣጣምክ ህልምህን በነፃነት ኑረው።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.