cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Muslim profile picture

Your profile picture

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
333
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
#ችሎት በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረው በዒድ አል ፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ አካባቢ የአድማ ብተና የጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ፍርድ ቤት ቀረበ። የፌደራል ፖሊስ የ 'አድማ ብተና ዘርፍ አባል' የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በአ/አ በተከበረው የዒድ አል ፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ ከፈነዳው የአድማ በታኝ የጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውሎ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ቀርቧል። መርማሪ ፖሊስ ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በዓሉ ዕለት በተመደበበት ወንጀል የመከላከል ምደባ ላይ እያለ የታጠቀውን አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ በአግባቡ መታጠቅ ሲገባው በአግባቡ ባለመታጠቅ የጭስ ቦንቡ እንዲፈነዳና ሁከት እና ብጥብጥ እንዲፈጠር አድርጓል ያለው መርማሪ በዚህ በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ የመንግስትና የግለሰብ ንብረት ጉዳት መድረሱን አብራርቷል። በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል ለተጨማሪ ማስረጃ አሰባስቦ ለመቅረብ 14 ቀን እንዲሰጠው መርማሪው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በበኩሉ በዕለቱ አስቀድሞ በተመደበበት ቦታ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ እንደነበር እና በሰዓቱ በቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች ቁጥር መጨመርና መጨናነቁን ተከትሎ ከታጠቀው ሶስት አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ ውስጥ አንደኛው በማያውቀው ሁኔታ መሬት ላይ ወድቆበት በድንገት መፈንዳቱን ገልጿል። ሆኖም ምንም አይነት ተንኮልም ሆነ ክፋት በውስጤ አልነበረም ወድቆ ሲፈነዳ እኔ እራሴ ደንግጬ ነበር ሲል እያለቀሰ ሁኔታውን ለችሎቱ አስረድቷል። በተጨማሪም ተጠርጣሪው ወላጆቹን በሞት ማጣቱን ገልጾ እህትና ወንድሙን በሱ እርዳታ እያስተማራቸው እንደሆነ እና ከለሊት 7:00 ጀምሮ ለጥበቃ ስራ ከመሰማራቴ ውጪ ሌላ ክፋት በውስጤ የለም ሲል ለችሎቱ አብራርቷል። ጉዳዩን የተከታለው ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ 14 ቀን ፈቅዷል። ለግንቦት 10 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ @profileofmuslim
Hammasini ko'rsatish...
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፦ " . . . ልክ ወደ መጨረሻው ፕሮግራም ላይ ልንገባ ስንል ነው ድንገት ድምፅ ሰማን፤ እየተረበሸ እንደሆነ ተነገረን። ምንድነው ? ብዬ የሚመለከተው የመንግስት የስራ ኃላፊ ከፀጥታ መዋቅር ውስጥ አንዱ አመራር ጋር ደውዬ ስጠይቅ ያለው ነገር ' ሀያት ሬጀንሲ አካባቢ ጭስ ነው ' ይረጋጉ አሉኝ። ሰው ይረጋጋ ብዬ ለመድረክ አስተባባሪው ነገርኳቸው ፤ ሰውን አረጋጋነው ፤ መልሶ ግን ቀጠለ ረብሻው ፣ ድምፁም የሚረብሽ ስለነበር ትንሽ ጥሩ አልነበረምና ምንድነው በሚል ጉዳዮችን ለመከታተል ሞከርን። መልሼ ስጠይቅ ፤ ' አይ አስለቃሽ ጋዝ ከአንድ ፖሊስ በአጋጣሚ አምልጦት ፤ ድንገት ባርቆበት ' ተባለ ፤ ይህንን የሰማሁት ከፀጥታ መዋቅሩ ነው። ...በጣም ደስ የሚል እና ያማረ ፣ በጣም በጥሩ ሁኔታ ያሳለፍንበት ኢድ ነበር ነገር ግን ይሄ ክስተት መጥቶ ትንሽ ነገሮችን ረባበሻቸው። በትክክል ለማጣራት ሞክሪያለሁ አንድ የፀጥታ ኃላፊ ከሚመለከታቸው ኮሚሽነር ጋር ተነጋግሬ የነገሩኝ ' ፌዴራል ፖሊሱ ባርቆበት ነው ' አሉ። ከዛም ደግሞ በትክክል አካባቢው ላይ የመደብናቸው የእኛ አስተናጋጆች በአጋጣሚ ሴቶች ያሉበትና የሚሰግዱበት ቦታ ነበር። የ 'ሰማዕታት ሀውልት' አካባቢ ላይ ነው፤ ሚኒስትሮች ሳይቀሩ የመንግስት ሙስሊም ሴት ሚኒስትሮች ቦታው ላይ የነበሩ አግኝቻቸው ያዩትን ክፍተት ነግረውኛል። ከአንድ የ 'ፌዴራል ፖሊስ' ነው ተወርውሯል የሚሉት ምክንያቱም ፤ የሚባርቅ ነገር ዝም ብሎ የሚወድቅ አይደለም ፤ ተፈቶ መለቀቅ አለበት አስለቃሽ ጭሱ ፤ ተፈቶ ነው የተለቀቀው ወደ ሰው ነው የተጣለው። ሴቶችና ህፃናቶች ወዳሉበት ቦታ ነው የተወረወረው። ሰው በዛ ሰዓት ወደ መራባበሽ ስሜት ውስጥ ገባ ፤ ሴቶችም በድንጋጤ መሮጥ፤ መነሳት ያፍናል አይነት ሁኔታ ተፈጠረ። በዚህ ሂደት ላይ እያሉ ሰውን አትውጣ ወደዛ አትሂድ የሚለው ግፊት መጣ ፤ በዚህ መካከል ሰውየውንም ይዘውት ነበር ፤ የእኛ አስተባባሪዎች ከያዙት በኃላ ሌሎች ፌዴራል ፖሊሶች ልቀቁት ብለው ያስለቀቁት፤ እሱም ይቅርታ ጠይቋል ' እኔ ባርቆብኝ ነው፤ ሳላስብ ነው ' ብሎ ደንግጦ የተናገረበት ሂደት ነበር የነበረው። ያ ሁኔታ ተከሰተ ሰው ስሜት ውስጥ ገባ ፤ እንደገና መገፋት ፣ ወደዛ አትሄድም ወደዚህ አትመጣም ፣ ሶላት አልሰገደም በዚህ አይነት ነገር ውስጥ ሲገባ ተኩስ ተጀመረ ወደ አየር ፤ አስለቃሽ ጭሶች መሰል ነገራቶች እየተደረጉ ሲሄዱ አቅጣጫ ስተው ረብሻዎች ደስ የማይል ነገር ተከስቷል። እስካሁን ባለኝ መረጃ የሞተ ሰው የለም። የተጎዱ ሰዎች አሉ። የተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ የገቡ አይናቸው አካባቢ ተመተው...በተለያየ ነገር የተመቱ ሰዎች ሆስፒታል የገቡ አሉ። ይሄ ነው ክስተቱ። መጣራት አለበት ለምን ?፤ ማን ?፤ እንዴት ? የሚሉት ነገሮች መታየት አለባቸው። ይሄ በጣም ትልቅ የሆነ ታሪካዊ የሆነ፣ እንደ አትዮጵያ ያለ ሙስሊም የውጭ እንግዳ ጠርተን ፣ በልዩ ሁኔታ ያከበርነው ኢድ ስለነበር እነዚህ ነገሮች ከባድ ናቸው። " @profileofmuslim
Hammasini ko'rsatish...
⚠️ የረብሻው ትክክለኛ መነሻ ከቦታው ከመስቀል አደባባይ በቦሌ መስመር ከቀይ ሽብር ትንሽ ከፍ ብሎ ሀያት ሪጀንሲ በሚገኘው ቦታ ላይ ክስተቱ ሚጀምረው። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዒዱን እየተከታተለ ባለበት ሰዓት ፌደራል ፖሊስ ምንም ባልተፈጠረበት ሁኔታ ሰላም ቁጭ ብሎ የነበረው ሰጋጅ ላይ ከመስቀል አደባባይ በቦሌ መስመር ከቀይ ሽብር ከፍ ብሎ ሀያት ሪጀንሲ ጋር በሴቶች በኩል አስለቃሽ ጭስ ጣለ ወደ ሰጋጆችም በእግሩ ገፋ አደርጎ ወደ መሃል ከተተው ይህ በቦታው ከነበሩ በብረቱ አይናቸው ያዩት የአማኞች ምስክር ነው። ማህበረሰቡ በመዋከብ ግማሹ ፊኛ ነው ግማሹ ሽጉጥ ነው እያለ ባለበት ሁኔታ ጭሱ መውጣት ጀመረና አማኞችን ማቃጠል ሲጀምር ሴቶችም መሸሽ ጀመሩ ግርግር ተፈጠረ ፌደራል ፖሊሱ ለምን እንዳደረገ ሲጠየቅ አባርቆብኝ በስህተት ነው በማለት የመለሰ ቢሆንም በእግሩ ወደ ሰጋጆቹ ገፋ ሲያደርገው ያዩት ስለነበሩ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፌደራል ፖሊሱን ለመያዝ ጥረት ቢያረግም ፖሊሱን ለማዳን ወደ ቀይ ሽብር ግቢ ውስጥ ይዘውት ገቡ ! ሙስሊሙ ማህበረሰብም ከቀይ ሽብር ግቢ ውስጥ እንዲወጣ ጥያቄውን አቀረበ በዛ መሃል ወደ ቀይ ሽብር ፖሊሱን ለማውጣት በተደረገው ትግል ላይ ቀይ ሽብር ላይ አነስተኛ ጉዳት ደረሰ ከዛ ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተጨማሪ ቶክሶች አስለቃሽ ጭሶች ተቶከሱ በዒዱ ቀን ረበሹት በሰላም እንዳያከብር አደረጉት እውነተኛ እና ትክክለኛ የረብሻው መነሻ ይህ ነው ። ሆኖም ግን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የመንግስትም ሚድያዋች እንደዘገቡት ጥቂት አሸባሪዋች በፈጠሩት ሁከት ረብሻ ተነስቶ ነበር ብለው ዘግበዋል! ጥቂት አሸባሪ የተባለው አስለቃሽ ጭሱን የለቀቀው ፌደራል ፖሊስ ከሆነ ትክክለኛ ዘገባ ነው ፣ በሰላም የዒድ ሰላትን በመጠባበቅ ላይ የነበረውን አማኝ ከሆነ ጥቂት አሸባሪዋች ያሉት ? ትልቅ ውሸትን ዋሽተዋል እና ዘገባቸውን ያስተካክሉት። በዒዱ ቀን ተሰቃይቶም የውሸት ዘገባም የሰሩበትን ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ ሴት እህቶቻችና እናቶቻችንን በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ ! ፌደራል ፖሊሱም ተይዞ ይመርመር ተሳስቶ ሳይሆን ሆን ብሎ ረብሻ ለማስነሳት ያቀደው እቅድ እንጂ በስህተት የተፈፀመ አደለም ! ያ ቢሆን ቀላል መፍትሄዋችን መውሰድ ይቻል ነበር ቶሎ ከሰጋጁ ማሰወገድ እና ጉዳት ማይደርስበት ቦታ ማስቀመጥ ፣ ማፈን እና ወደ ምእመናኑ እንዳይደርስ ማድረግ ፣ እና መሰል መፍትሄዋችን ተጠቅሞ ማስቆም ይቻል ነበር። ያም ሳይሆን በእግሩ ወደ ሰጋጂች እንደገፋው በቦታው ላይ የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል። #ረበሹን_ከሰሱን 😢 እውነታን በማሰራጨት የውሸት ክሶችን እንቃወም መልአክቱን ሼር በማድረግ ስለ እውነት እንጩህ ! @profileofmuslim
Hammasini ko'rsatish...
09:43
Video unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና አዲስአበባ ለሶላት በወጡት ሙስሊሞች ላይ ታጣቂዎችህ በመተኮሱ ሶላቱ ተረብሿል። እስካሁን ድረስ 67 በላይ ሙስሊሞች ተገድሎዋል። @profileofmuslim
Hammasini ko'rsatish...
39.83 MB
Photo unavailableShow in Telegram
#ዘካተል_ፊጥር ‹‹ዘካተል ፊጥር›› የረመዷን ወር ፆም መጠናቀቅያ ላይ የሚሰጥ የምጽዋት ዓይነት ነው፡፡ ‹‹ሶደቀተል ፊጥር›› በመባልም ይታወቃል፡፡ #የሚሠጥበት_ጊዜ ፡- መሠጠት ያለበት እንደ ነገ ዒድ ሲል ፀሐይ ከጠለቀችበት ጊዜ ጀምሮ የዒድ ሶላት እስኪሰገድ ድረስ ባለው ጊዜ ዉስጥ ነው፡፡ ከዒድ በፊት ሁለትና ሦስት ቀን አስቀድሞ መስጠትም ይቻላል፡፡ #ዓላማው ፡- የዘካተ-ልፊጥር ዓላማውም ድሆች የሆኑ ሙስሊሞች በዒድ ዕለት ተደስተው እንዲውሉ፣ ተርበዉና ተከፍተው እንዳይውሉ ለማድረግ ነው፡፡ እንዲሁም ስለዋለለልን ዉለታ ሁሉ አምላካችን አላህን (ሱ.ወ.) ፀጋ የምናመሰግንበት ነው፡፡ ዘካተል- ፊጥር የፆመኛን ነፍስ ታጠራለች፣ በፆሙ ወቅት  በመጥፎ ሥራዎችና ቸልተኝነት ምክንያት በፆሙ ላይ የደረሱ የተለያዩ ጉድለቶችን ትጠግንለታለች፣ አማኝንም ወደ አምላኩ ታቃርባለች፡፡ #ዘካተል_ፊጥር_ግዴታነቱ_በነማን_ላይ_ነው? ዘካተል ፊጥር ሴት፣ ወንድ፣ ባል፣ ሚስት፣ ትንሽ ትልቅ… ሳይል በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ አንዳንድ ዑለሞች ሆድ ውስጥ ላለ ጽንስ ጭምር ዘካተል ፊጥር ማውጣት ግዴታ ነው ብለዋል፡፡ አባወራ ለሚያስተዳድራቸዉና ለሚቀልባቸው ሁሉ አስልቶ ዘካዉን መስጠት ይኖርበታል፡፡ አንድ ሰው ዘካተል ፊጥር ማውጣት ግዴታ ይሆንበት ዘንድ ቤተሰቦቹ ለአንድ ቀን ያክል መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት የሚችሉበት ገንዘብ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ #ለዘካተል_ፊጥር_የሚወጡ_የእህል_ዓይነቶችና_መጠኑ፡- ዘካተል ፊጥር ከስንዴ፣ ከገብስ ከተምር፣ ከዘቢብ፣ ከሩዝና ሌሎችም ቀለብ ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች አንድ ‹‹ሷዕ›› ይወጣል፡፡ አንድ ሰው ሀገሩ ላይ አብዛኛው ሰው ከሚመገበው ምግብ ለዘካተል ፊጥር መስጠት ይችላል፡፡ አንድ ‹‹ሷዕ/ቁና›› 3 ኪሎ ግራም አካባቢ ይሆናል ተብሏል፡፡ ሚዛን ወይም መስፈሪያ የሌላቸው ሰዎች በመካከለኛ ሰው እጆች አራት እፍሶች ማውጣት ይችላሉ፡፡ አንድ ‹‹ሷዕ›› ይሆንላቸዋል፡፡ ለዚህ ጥቂት ቢያክሉም መልካም ነው፡፡ አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ #የአወጣጡ_ስልት፡- ሰውየው ራሱን ጨምሮ ከሥሩ ያሉ የሚቀልባቸው ቤተሰቦቹን አባላት ቁጥር ያሰላል፡፡ ቁጥራቸዉን በ3 ኪ.ግ ያባዘዋል፡፡ አባዝቶ የሚያገኘውን ቁጥር ያክል ኪሎ ግራም እህል ወይም ተመኑን በገንዘብ ለ‹‹ዘካተል ፊጥር›› ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ ሰውየው በሥሩ 9 የቤተሰብ አባላት አሉት፡፡ ከራሱ ጋር ቁጥራቸው 10 ይሆናል፡፡ እናም፡- 10 x 3 ኪ.ግ = 30 ኪ.ግራም እህል ዋጋውን ለዘካተል ፊጥር ይሰጣል፡፡ የቤት ሠራተኞች፣ ዘበኞችና ሌሎች ቤት ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎች ከቤተሰብ አባላት ጋር አብረው ይቆጠራሉ፡፡ የዘካተል ፊጥር ዋና ዓላማው ድሆችን በዒድ ቀን ማስደሰት እስከሆነ ድረስ ለዕለቱ እንዲደርስላቸው ገንዘብ ይሁን እህል ለነርሱ የሚሻለዉን መስጠቱ መልካም ነው፡፡ ዘካተል ፈጥር የሚሰጣቸው ወገኖች፡- ዘካተል ፊጥር የሚሰጣቸው ሰዎች ዘካ እንዲሰጣቸው የተደነገገላቸው የኀብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ ግና ለድሆች ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ዑለሞች ያፀድቃሉ፡፡ የዘካ ድርሻ ለሌላቸው ሰዎች ዘካተል ፊጥርን መስጠት አይፈቀድም፡፡ ዘካተል ፊጥርን ሲሰጡ ለአካባቢ ድሆች ቅድሚያ መስጠት ይገባል፡፡   1 እና 2. ድሆች (ፉቀራእ)ና ሚስኪኖች የዘካ ዓይነተኛ ዓላማ ድህነትን ማስወገድ ነው፡፡ ኢብን ጀሪር እንዳሉት፡- ‹‹ድሃ (ፈቂር) ሰዎችን የማይጠይቅ ቁጥብ (ሙተዐፊፍ) ችግረኛ ሲሆን÷ ሚስኪን ደግሞ ሰዎችን የሚለምን ችግረኛ ነው፡፡ ለሀብታሞች ወይም ሠርተው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን መሠረታዊ ፍላጎት የማሟላት አቅሙ ላላቸው ሰዎች ከድሆች ድርሻ መስጠት አይፈቀድም፡፡ 3.  የዘካ አስተባባሪ ቡድን ከድሆችና ሚስኪኖች ቀጥሎ ዘካ የሚሰጣቸው ወገኖች የዘካን ገንዘብ በመሰብሰብ፣ በማስላትና በመሳሰሉት ተግባራት የተሰማሩ ወገኖች (የዘካ አስተባባሪ ቡድን ሠራተኞች) ናቸው፡፡ 4.  ‹‹ሙአልለፈህ ቁሉቡሁም›› (ኢስላምን እንዲላመዱ የሚከጀሉ ወገኖች) አዲስ ወደ ኢስላም የገቡ ሰዎች ከዘካ ድርሻ አላቸው፡፡ ኢስላም ላይ እንዲፀኑና እንዲላመዱ፡፡   5. ሰዎችን ከባርነት ነፃ ለማውጣት የዘካ ገንዘብ ሰዎችን ከባርነት ነፃ ለማውጣት ሲባልም ወጭ ይደረጋል፡፡ ኢስላም ባርነትን ከምድር ላይ ለማስወገድ ከተጠቀማቸው በርካታ ስልቶች ይህ አንዱ ነው፡፡ 6. ዕዳ ያለባቸው ሰዎች በዕዳ የተያዙና ለመክፈል የተቸገሩ ሰዎችም የዘካ ገንዘብ ባለመብቶች ናቸው፡፡  ዕዳቸውን መሸፈን የሚያስችላቸውን ያህል የዘካ ገንዘብ ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ 7. በአላህ መንገድ (ፊ ሰቢሊልላህ) ‹‹ፊ ሰቢሊልላህ›› ወደ አላህ ሊያደርስ፤ የአላህን እርካታ ለመጎናፀፍ የሚያስችል ማንኛውም መልካም ተግባር ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢስላምን መልዕክት ለሰዎች ማድረስ የሚያስችሉ የዳዕዋ ተቋማትንና ድርጅቶችን ማቋቋም፣ ሙስሊሞችን በትክክለኛ ኢስላማዊና ስብዕና መቅረጽ የሚያስችሉ፣ የተለያዩ ተያያዥ ተቋማትን መገንባትና መዶገም የመሣሠለው ሊሆን ችላል፡፡ 8. በጉዞ ላይ እክል የገጠመው መንገደኛ (ኢብኑ ሰቢል) ወደ ሀገሩ ለመግባት እክል ያጋጠመው መንገደኛ ገንዘብ የሚያገኝበት ሁኔታ የማይመቻችለት ከሆነ ሀገሩ ላይ ባለንብረት ቢሆንም እንኳ ዘካ ይሰጠዋል፡፡ @profileofmuslim
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.