cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኰኲሐ ሃይማኖት

📃📖ኰኲሐ ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙምአለት ማለት ነው ። ኮኩሐ ሃይማኖት ማለት ጠንካራ የሃይማኖት መሰረት ማለት ነው ። 📖📃 ✝ በያላችሁበት ሰላመ እግዚያብሔር አይለያችሁ፣ የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kukuha_Haymanot

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
370
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

❤ #_አርሴማ_ቅድስት_ሰማዕት #_አጠር_በጠር_ያለ_ታረኳ ሼር በማድረግ ለሰማዕቷ ለወዳጆችዋ አድርሱ! የወለላይቱ እመቤት ልጆች ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከሚያከብሩ ብሩካን ከሆኑ፤በጾም በጸሎት በስግደት በትጋት ከሚኖሩ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስ ከእናቷ ከቅድስት አትናስያና በጥር 6 ቀን የተወለደች ደገኛ የገድል አርበኛ ናት፡፡ በተለይ ስትወለድ ይህ ቀረሽ የማትባል እጅግ መልከኛ እና ግርማዋ የሚያስፈራ ነበር፡፡ እናት እና አባቷም በጾም በጸሎት በስዕለት ስላገኟት እስከ 3 ዓመት ካሳደግዋት በኃላ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም በተሰራች ቤተ ክርስትያን ታገለግል ዘንድ ሰጧት፡፡ እመቤታችንን 12 ዓመት አገልግላ ያለፈቃድዋ በቤተሰቦችዋ ግፊት በ15 ዓመቷ ዳሯት፡፡ ሰማዕቷ ግን ዓለማዊ ሕይወት ባለመፈለግዋ ወደ ገዳማዊ ምናኔ ህይወት ገብታለች፡፡ በዚያን ዘመን ብዙ ሰማዕታት ያስፈጀ ጨካኙ የሰው አውሬ ካሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ መላኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሴት ሊያገባ ሽቶ በየአገሩ ሁሉ ፈልገው መርጠው ያመጡለት አንድ አሽከሮቹን አዘዘ፡፡ እንግዲህ የሰማቷ አሳዘኝ የመከራ ሕይወት ከዚህ ነው የሚጀምረው፡፡ የዲዮቅልጥያኖስ ሠራዊቶች አርሴማ የምትባል ውብ ሴት በሮሜ በአንድ ገዳም እንዳለች ሰሙ፡፡ አዋቂዎችም የሰማዕቷን ውብ መልኳን ስለው ለንገሡ ለዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ስዕሏን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና በሥጋዊ ጋብቻ አብሯት ሊኖር እንዳሰበ ለመኳንንቱ ነግሮ ለሠርግ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ ቅድስት አርሴማ ይህንን በሰማች ባወቀች ጊዜ ከደናግሉ ጋር የንጉስ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነው አርመንያ አገር ሸሸች፡፡ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ የከበረች አርሴማን አስፈልጎ ባጣት ጊዜ በአርመንያ እዳለች ሰማ፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም ለአርመንያው ንጉሥ ለድርጣድስ ከእሱ ሸሽታ እንደሄደች እና ባስቸኳይ አስጠብቆ እንዲልክላት አዘዘው፡፡ ደናግሉ ይንን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሰወሩ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በክብር ያመጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ሰማዕቷም ወደ እርሱ መምጣትን እንቢ ባለች ጊዜ በመሬት እየጎተቱ ወደ ንጉሡ አቀረቧት፡፡ ድርጣድስ የቅድስት አርሴማን ደም ግባት እና ውበት ባየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ የመንፈስ እናቷን አጋታን አባብላ እሺ ታሰኛት ዘንድ አዘዛት፡፡ አጋታም ወደ ሰማዕቷ ሄዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት ‹‹እወቂ ይህ ርኩስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ምሽራሽን ክርስቶስን እንዳትተይ›› ብላ አጸናቻት፡፡ ንጉሥ ድርጣድስም ሰማዕቷን ይዞ ወደ እልፍኝ ሊያስገባት ከአደባባይ መካከል ተነስቶ ድንግል አርሴማ በእጁ ያዛት፡፡ በዚያን ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው፡፡ ድርጣድስም በጦትነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለነበር በታናሽ ብላቴና ስለተሸነፈ መኳንንቱ ፊት ስለተዋረደ አፈረ፡፡ ከዚህ በኃላ በሰው አንደበት ለመናገር የሚከብድ መከራና ስቃይ አጸናባት፡፡ ሰማዕቷም ከንጉሡና ከጋሻ ጃግሬዎቹ የሚደርስባትን መከራ በመታገስ በረታች፡፡ ንጉሥ ድጣድስ በሰማዕቷ ላይ የሚያደርሰውን ሥጋዊ መከራ የልቡ ስላልደረሰለት ጡቷን በማስቆረጥ ዓይኗን በወረንጦ በማስወጣት ቢያሰቃያትም ሰማዕቷ ይበልጥ በክርስቶስ ፍቅር ጸናች፡፡ በሚደርስባትም ነገር ደስ ተሰኘች፡፡ ወዳጆቼ እኛ በሚደረስብን ሥጋዊ ህመም ስቃይ መከራ ፈተና እንደሰታለን? አንደሰትም ይልቁንም እናማርራለን፡፡ ምንያቱም የክርስቶስ የመከራ ሕይወት ውስጣችን ስላልገባ ነው፡፡ ክርስቶስ ጋር ለመድረስ መንገዱ፣በአጋንንት እና በሥጋ እየተጎዱ መሆኑን ስለማንረዳ ነው፡፡ ብንረዳም የደስታ እንጂ የመከራ ትከሻ ስለሌለን ነው፡፡ የመከራ ትከሻ ቢኖረንም ትዕግስት ስለሌለን በመከራችን አንጸናም፡፡ በመጨረሻም ንጉሥ ድርጣድስ የሚያደርገውን ሲያጣ አንገቷን በሰይፍ ሊያስቆርጥ ወሰነ፡፡ ከዚህ በኃላ ንጉሥ ድርጣድስ ቡርክት ቅድስት አርሴማን ወደ መገደያ ወንዝ እንዲወስዷትና በዚያም የከበረ ራሷን ይቆርጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን ወታደሮች አንገቷን ሲቆርጧት ያይ ዘንድ ከእርሷ ጋር ወጣ፡፡ ሰማዕቷ በምትገደልበት ትይዩ ከሠራዊቱ ጋር ተቀመጠ፡፡ የእጃቸው ክንድ የበረታ ልባቸው ግን የጨከነ ሮማውያን ወታደሮች ሰይፍ ይዘው ወደ ሰማዕቷ ቀረቡ፡፡ ሰማዕቷ ሞቷ ሰማያዊ እረፍቷ ስለሆነ በደስታ ትመለከታቸው ነበር፡፡ ቅድስት አርሴማም ወታደሮቹን የጸሎት ጊዜ እንዲሰጧት ጠይቃቸው ፈጣሪዋን ካመሰገነች በኃላ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ ወገቧን ታጥቃ አንገቷን ከፍ አድርጋ ለሚቆርጧት ታመቻችላቸው ነበር፡፡ ቆራጮች ወታደሮች ከቅድስት አርሴማ ግርማ የተነሳ ደንግጠው ሰይፋቸውን እንደያዙ በምድር ላይ ወደቁ ሰይፋቸውንም ጣሉ፡፡ ሰማዕቷም እያበረታታች ‹‹የታዘዛችሁትን ፈጽሙ›› ትላቸው ነበር፡፡ ወታደሮቹም ‹‹እኛስ ወዳንቺ መቅረብ እና አንገትሽን መቁረጥ አልቻልንም በግንባርሽ ላይ ያለው ትዕምርተ መስቀል አስፈርቶና፤ግንባርሽን ካልሸፈንሽልን አንገትሽን ፈጽሞ ልንቆርጥ አንችልም›› አሏት፡፡ ሰማዕቷም ለወታደሮቹ ፊቴን የምሸፍንበት ቁራጭ ልብስ ወይም ቁራጭ ጨርቅ ስጡኝ አለቻቸው፡፡ እነሱም ቁራጭ ጨርቅ ጣሉላት እሷም ፊቷን ሸፈነች፡፡ ቅድስት አርሴማም ንጉሥ ድርጣድስ እና ሠራዊቱ ሕዝቡም እየተመለከቱ ምስከረም 29 ቀን አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ፡፡ ወዳጆቼ እኛን ጌታችን እንደ እነ ቅድስት አርሴማ፣ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ወዘተ አንገታችሁን ተቆረጡልኝ ሰማዕት ሁኑልኝ አላለንም፡፡ ኃጢአትን ከእናንተ ሰውነት ቆርጣችሁ ጣሉት ነው ያለን፡፡ የዝሙትን ፍላጎት ከሰውነታችሁ ቁረጡና ደም አላባ ሰማዕት ሁኑ ነው የተባልነው፡፡ የኃጢአቶችን ተቀጽላ ከሥጋችሁ ላይ ቁረጡና በንስሐ ጻድቅ ሁኑ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት በደማችሁ ዋጋ ገነት ግቡ ሳይሆን በደሜ ፈሳሽት መንግስቴን ውረሱ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት ጽኑ መከራን በሥጋችሁ ተቀበሉ ሳይሆን ቅዱስ ሥጋዬን ብሉና የርስቴ ተካፋይ ሁኑ ነው ያለን፡፡ ሰማዕት ሁኑ ሳይሆን በእኔ መስዋዕትነት ዳኑ ወደ መንግስቴ ጎዳና አቅኑ ነው ያለን፡፡ አወይ አለመጠቀማችን እንደ እኛ ያደለው ማን አለ? ቅድስት አርሴማም በሰይፍ ስትሰየፍ ከአንገቷም ደም፣ ውኃ፣ ወተትና ማር እንደ ክረምት ነጠብጣብ እየተንጠባጠበ መነጨ፡፡ ❤ ደም ከአንገቷ የመነጨው ስለ ሃይማኖትዋ ቆራጥነት ስለ ሞት አለመፍራት እና የጌታችንን መከራ ተሸክማ ሰማዕት ስለሆነች ነው፡፡ ❤ ውኃ የፈሰሰው ስለ ብዙ ጸሎትዋ፤ስለልመናዋና የቤተ ክርስትያን መጻሕፍትንና ምስጢራትን ሁሉ ልብ ስለምታደርግ ነው፡፡ ❤ ወተት የመነጨላት ስለ ክብሯ ስለ ከፍታዋ እና ንጽሃ ድግልናዋን ስለጠበቀች ነው፡፡ ማር የወረደው ስለሚያስደንቅ የፊቷ ወዝ፣ደም ግባቷ፣ስለ ጣፋጭ የከንፈሯ ቃልና የሰማዕታት ሁሉ እህት ስለሆነች ነው፡፡ ከዚህ በኃላ ብሩህ የሆነ የደመና አምድ ወረደና በላይዋ ጋረዳት፡፡ ወደ ሰማይም እንደ መብረቅ ሳባት፡፡ የቅዱሳን መላእክትም ማህበር ነፍሷን አሳረጓት፡፡ በክብር በእልልታ በዝማሬና በማህሌት ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አስገቧት፡፡ እርሷ እንደ ሞተች ባወቁ ጊዜ ወታደሮቹ ደናግሉን ሁሉ ጫማቸውን እየበሱ እራሳቸውን ቆረጡ፡፡ ቁጥራቸውም ሰባ ሁለት ነፍሳት ነበሩ፡፡ ❤ ቃል ኪዳንዋ ❤
Hammasini ko'rsatish...
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችን ምድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማዕቷ ለትውልድ የሚተላለፍ የዘላለም ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ መታሰብያዋን ያደረገ ስሟን የጠራ በስሟ ቤተ ክርስትያን የሠራ፣የተራበውን በስሟ ያበላ፣የተጠማውን በስሟ ያጠጣ፣የገድሏን መጽሐፍ የጻፈውን፣ያጻፈውን፣ያነበበውን፣የተረጎመውን፣ሰምቶም በልቡ ያኖረውን፣የልቡን መሻት እንደሚፈጽምለት እና በመንግስተ ሰማያት እንደ እርሷ የክብር አክሊል እንደሚያቀዳጀው፤ሥዕሏን አሥሎ በክብር በቤቱ አስቀምጦ ሽቶ እየረጨ ቢጸልይበት ጸሎቱ እንደሚሰማና ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ እንደሚያሸተው፣ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በስሟ የሰየመ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስም እንደሚሰጣቸው፣ዕጣን፣ስንዴና መብራትን፣ልብሰ ተክህኖ፣መጋረጃ ቢሰጥ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስ እንደሚለብስ፣ያለ ወቀሳ ያለከሳ ባህረ ሲኦልን ተሻግሮ መንግስቱን እንደሚወርስ ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ❤ ሰማዕቷን ከሌሎች ቅዱሳን ልዩ የሚያደርጋት ታሪክ ❤ በግብጽ አገር አርባ ዓመታት የነገሠ ባለ 12 ክንፉ ብጹአዊ አቡነ ሙሴ የሚባሉ ታላቅ ጻድቅ አሉ፡፡ እኝህ ጻድቅ ከንግስና ወደ ምንኩስና የተሸጋገሩ መንፈሳዊ አርበኛ ናቸው፡፡ ታድያ እኝህ ጻድቅ የቅዱሳን፣የሰማዕታትን ዓጽም እሰበሰቡ ደግላቸውን እያጻፉ፣ቤተ ክርስትያን በመስራት፣ታቦታቸውን በማክበር፣በበዓላቸውም ቀን ይቀድሱ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ታቦት ለማሰናዳት፣ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ በወርቅ የተለበጠ እና በላዩ በሮማይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት ያገኛሉ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰቡ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመሩ፡፡ ግን የቅድስት አርሴማን ግድልና የሞቷን ዜና አላገኙም፡፡ ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች እና የሰማዕትነቷን ሥራ ያስረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አመለከቱ፡፡ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለአቡነ ሙሴ ተገልጦ ‹‹ብጽአዊ ሙሴ ሆይ የብጽእት አርሴማን ሥራ እነግርህ ዘንድ ስማ፡፡ ይህቺ ሰማዕት ገና አልተጸነሰችም፣አልተወለደችም፤በወርቅ ዓምድ በሕይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ፡፡ ነብዩ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይጻፋል እንዳለ እርሷም በኋለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች፤በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል፡፡ ተአምሯ የሚነገረው በኢትዮጲያ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰብያ መጥራት አትተው፡፡ ጽላትዋም ከአንተ ጋር ይኑር፡፡ የመቅደስዋም ህንጻ በህንጻህ ቦታ ጎን ይኑር፡፡ ስምህ በተጠራበትም የስሟ መታሰብያ ይጠራል›› ብሎ መልአኩ ወደ ላከው እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡ አቡነ ሙሴም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ ሰማዕቷም ገና ሳትወለድ በፊት እንደ እመቤታችን በእግዚአብሔር ህሌና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ እኛም እንደ እንደ ጻድቁ አቡነ ሙሴ በሰማዕቷ ጸሎት እና ቃል ኪዳን ልንጠቀምባት ይገባል፡፡ ተወዳጆች ሆይ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዮንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶም ስለ ዮፍታሔ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነብያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና›› ነው ያለው፡፡ /ዕብ 11÷32/ እኔም ስለ እዚች ድንቅ ብርቅ እና ከወርቅ በላይ የከበረች ከአልማዝም በላይ የተወደደች ስለ ሰማዕቷ ለመተረክ ጊዜ ስለማይበቃን እዚህ ላይ ይብቃን፡፡ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ጸሎት፣በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት1.02 MB
ስንክሳር_ዘወርሃ_መስከረም_ሃያ_ሰባት_ሺህ_ዓ_ም_.mp37.08 MB
ASR_ድርሳነ_መድኃኔዓለም_ወገድለ_መብዓ_ጽዮን_ዘሰንበተ_ክርስቲያን_ቅድስት.mp31.40 MB
"እግርሽ_ጨረቃን_የሚጫማ"የጽጌ_መዝሙር_በበገና_በሠላምታ❤#yetsige_mezmur_egrsh_chereqan.m4a5.52 MB
የጽጌ_ጾም_ለምን_እንጾማለን_ምን_በማሰብ_ይጾማል128k.m4a3.95 MB
የጽጌ_መዝሙር–በብርሃን_ፀዳልYetsige_Mezmur_Bebirhan_Tsedal128k.m4a7.29 MB
''ክርስቲያን_ማለት_ምን_ማለት_ነው''.mp36.51 MB
ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው.mp37.05 MB
ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው.mp37.05 MB
''ክርስቲያን_ማለት_ምን_ማለት_ነው''.mp36.51 MB
የመስቀል_በዓል_መዝሙሮች_|_yemeskel_Mezmuroch_|_yemeskel_beal_mezmur_|_የመስቀል.m4a69.33 MB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.