cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethio Astronomy And Ancient History

ስለ ጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንታዊ የስነ ፈለክ እና የታሪክ መፅሃፍቶቿ፣ ቀደምት አባቶቿ ስለተራቀቁበት የእውቀት ማዕድ፣ ቀደምት እናቶቿ ተውበው ስላስዋቡባቸው ጥንታዊ ማዕድናት ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር አንድ ላይ የምናይበት ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ወደኋላ የምንመልስበት ጥበባትን የምንመረምርበት ቻናል ነው። ለሃሳብ እና አስተያየት: @T_F_A_P

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
320
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Who to Send Into Space: Dog or Monkey❓ When scientists were faced with this question, they chose dogs. Dogs are more unpretentious and easier to train.
Hammasini ko'rsatish...
Blue Is Not Always Water Scientists originally thought that life could exist on the exoplanet HD 189733 b, as the blue color could indicate the presence of water💦 As it turned out, the blue color did not mean water at all, but was direct evidence the planet's surface was constantly raining molten glass. The velocity of this glass downpour reached 6,500 km/h.
Hammasini ko'rsatish...
An animation showing what gravity really looks like According to the general theory of relativity, any massive body creates a kind of vortex in space-time. Bodies flying by change their trajectory according to the curvature of curved space.
Hammasini ko'rsatish...
Vantablack - The darkest material in the world. It absorbs nearly 99.965% of the light that enters the tube.
Hammasini ko'rsatish...
Eight stars skirt a black hole 1 million times the mass of the Sun in these supercomputer simulations. As they approach, all are stretched and deformed by the black hole’s gravity. Some are completely pulled
Hammasini ko'rsatish...
#ሌዘሮች📚📘📗📓📔 ሌዘሮች ስፔክቶሜትሮች በሚባሉ መሳሪያዎች ውስጥም ጥቅም ላይ ይውላሉ። ስፔክትሮሜትሮች ሳይንቲስቶች ከምን ነገሮች እንደተሠሩ ለማወቅ ይረዳሉ። ለምሳሌ፣ Curiosity rover በማርስ ላይ በተወሰኑ አለቶች ውስጥ ምን አይነት ኬሚካሎች እንዳሉ ለማየት ሌዘር ስፔክትሮሜትር ይጠቀማል። የናሳ ተልዕኮዎች በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ያሉትን ጋዞች ለማጥናት ሌዘር ተጠቅመዋል። የፕላኔቶችን፣ የጨረቃዎችን እና የአስትሮይዶችን ገጽታ በሚያሳዩ መሳሪያዎች ላይ ሌዘርም ጥቅም ላይ ውሏል። ሳይንቲስቶች ሌዘርን በመጠቀም በጨረቃ እና በምድር መካከል ያለውን ርቀት እንኳን ለክተዋል! የሌዘር ጨረር ወደ ጨረቃ እና ወደ ኋላ ለመጓዝ የሚፈጀውን ጊዜ በመለካት የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ምን ያህል ርቀት እንዳለ በትክክል ማወቅ ይችላሉ! ሌዘር በተቀሰቀሰ የጨረራ ልቀት አማካኝነት ወጥ የሆነ ሞኖክሮማቲክ ብርሃን የሚያመነጭ የኦፕቲካል መሳሪያ ነው። ሌዘር ብርሃን ከተራ ብርሃን የተለየ ነው። እንደ ወጥነት፣ ሞኖክሮማሲቲ፣ አቅጣጫዊ እና ከፍተኛ ጥንካሬ ያሉ የተለያዩ ልዩ ባህሪያት አሉት። በእነዚህ ልዩ ባህሪያት ምክንያት ሌዘር በተለያዩ ትግበራዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል። ሌዘር ለብዙ ቴክኖሎጂዎች እና መሳሪያዎች ጠቃሚ የሆነ በጣም ጠባብ የብርሃን ጨረር የሚፈጥር መሳሪያ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
[ኅዳር 24 የሥላሴን መንበር የሚያጥኑ የ24ቱ ካህናተ ሰማይ ዓመታዊ በዓልና የ24ቱ መላእክቱ ስማቸው] ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 💥 “በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሊቃናት ተቀምጠው ነበር።” — ራእይ 4፥4 💥 ዮሐንስ በራእዩ የጠቀሳቸው በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት የቆሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ማን ናቸው? የሚለውን በዝርዝር የሚያስረዱን የቤተ ክርስቲያን የሥነ ፍጥረት መጻሕፍት አሉን። ይኸውም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡- ✍️ “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” ይላል። 💥 ከሰራዊተ ሩፋኤል 24ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪) እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ብሏቸዋል። 💥 የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል። ♥ ቁጥራቸው 24 መኾኑም በ24ቱ ሰዓት ጸልየው አመስግነው በጸሎታቸው ሌላውን ጠብቀው የሚኖሩ ናቸውና ነው፨ ♥ ዮሐንስም በራእዩ “ሀያ አራቱ ሊቃናት በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።” ይላል። — ራእይ 4፥10-11 💥 እነዚኽ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል። 💥 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ምስጋናው ላይ እመቤታችን ምዕራገ ጸሎት ናትና በካህናተ ሰማይ ማዕጠንት መስሎ፦ ✍️"ናስተማስለኪ ኦ እግዝእትነ ማርያም በማዕጠንት ዘወርቅ ዘውስተ እደዊሆሙ ለሊቃነ ካህናት ሰማያውያን" (እመቤታችን ማርያም ሆይ የቅዱሳንና የምእመናንን ጸሎት ከምድር ወደ ሰማይ በሚያሳርጉ በሰማያውያን የካህናት አለቆች እጆች ውስጥ ባለ የወርቅ ማዕጠንት እንመስልሻለን) ይላታል። 💥 ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማሕሌተ ጽጌው ላይ፦ ✍️ "ማዕጠንተ ሱራፊ ዘወርቅ" (የሱራፊ የወርቅ ማዕጠንት) ይላታል እመቤታችንን። 💥 ጸሎት ሁሉ በመላእክት ማዕጠንት (ጽናሕ) ወደ ጌታ የሚቀርብ ነውና፦ ✍️ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” ይላል ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡ 💥 ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ፦ ✍️ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” ይላል። 💥 ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)፡፡ 💥 አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በኆኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ፡- ✍️ “ወይምጽኡ ካህናት ሰማያውያን፣ ልቡሳነ ብርሃን ወጸወርተ ዕጣን፣ እለ ያቈርቡ ቅድመ ምሥዋዒከ ጸሎተ ቅዱሳን፣ እለ ይቀውሙ ዐሠርቱ ወክልኤተ እምይምን ወዐሠርቱ ወክልኤቱ እምፅግም፣ ወፍያላተ ያቄርቡ ለስብሐተ መለኮትከ፤ ዕሥራ ወአርባዕቱ ኊልቆሙ ዕሥራ ወአርባዕቱ መናብርቲሆሙ፣ ዕሥራ ወአርባዕቱ አክሊላቲሆሙ፣ ዕሥራ ወአርባዕቱ ማዕጠንታቲሆሙ” (ብርሃንን የለበሱ ዕጣንንም የተሸከሙ የቅዱሳንን ጸሎት ወደ መሠዊያኽ ፊት የሚያቀርቡ ዐሥራ ኹለቱ ከቀኝ ዐሥራ ኹለቱ ከግራ የሚቆሙ ለጌትነትኽም ምስጋና ጽዋዎችን የሚያቀርቡ ሰማያውያን ካህናት ይምጡ፤ ቊጥራቸው ኻያ አራት ነው ወንበሮቻቸውም ኻያ አራት ናቸው፣ አክሊሎቻቸውም ኻያ አራት ናቸው፤ ማዕጠንቶቻቸውም ኻያ አራት ናቸው) በማለት ስለ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ አስተምሯል፡፡ 💥 ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተአምሆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ለኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰላምታ ሲያቀርብ፦ ✍️ "ሰላም ለ፳ወ፬ቱ ካህናት ሰማያውያን እለ ዐውደ መንበሩ ለአብ፡፡ ወሰላም ለማዕጠንት ዘውስተ እደዊሆሙ ወሰላም ለአክሊላት ዘዲበ አርዕስቲሆሙ፤ ወሰላም ለአስማቲሆሙ፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል”፡፡ (በአብ መንበር ዙሪያ ላሉ ለ፳፬ቱ ሰማያውያን ካህናት ሰላምታ ይገባል፤ በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም ሰላምታ ይገባል፤ በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል ለተባሉ ስሞቻቸውም ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል፨ [የልዑል እግዚአብሔርን ዙፋን የሚያጥኑ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በማዕጠንታቸው ጸሎታችንን ወደ ጸባኦት ዙፋን ያድርሱልን] ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የቴሌግራም ቻናል https://t.me/joinchat/AAAAAFTyR7tztt08pN9U-w
Hammasini ko'rsatish...
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

How to Identify that Light in the Sky
Hammasini ko'rsatish...
ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን መጫን በቂ ነው። ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
ክፈት
Open
خاصة ليوم الجمعة
Hammasini ko'rsatish...
Ethio space science🪐

Welcome to E.S.S channel!! Exploration of Astronomy For any suggestion @pupina16