cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን መዝሙሮችን እንዲሁም ምክሮችን ያገኙበታል። ክርስቲያናዊ ሕይወትዎን ያዩበታል.......

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
653
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kunlar
-1030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🕊 † በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን ::  † [ ግንቦት ፳፮ [ 26 ] ] 🕊  † አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ †   🕊 እግዚአብሔር በ፲፫ [13ኛው] መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው:: እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ [ዳኅና] አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል:: ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን [ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው] ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ:: አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ:: በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው:: በአንዴም ከዳሞ [ትግራይ] ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ [ወሎ] አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ:: ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ [ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው] ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ:: በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው:: ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ:: ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል:: እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም:: "እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ:: መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል:: ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው [በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ] በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::} " ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! " " ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: " [፩ዼጥ. ፭፥፫ ] †  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።  † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
🕊 † በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን ::  † 🕊  † አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ †   🕊 እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል:: ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ [የራውዕይ] ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር:: ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች:: ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር:: የ ፭ [5] ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል:: ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም:: - ባሕር ውስጥ ሰጥመው ፭፻ [500] ጊዜ ይሰግዳሉ:: - በየቀኑ ፬ [4] ቱን ወንጌልና ፻፶ [150] መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (µ[መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው] - በ ፵ [40] ቀናት : ቀጥሎም በ ፹ [80] ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ:: - ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው:: - በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: [ካህን ናቸውና] - ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ:: - በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም:: በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው:: ፩. " ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: ፪. ስለ ምናኔሕ: ፫. ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: ፬. ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: ፭. ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: ፮. ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: ፯. ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ ፯ [7] አክሊላትን እሰጥሃለሁ::" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : ፭፻ [500] የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው:: ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: {ይህች ቀን [ግንቦት ፳፮ [26] ] ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::} አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን:: 🕊 "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .  ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፮፥፳፮-፴፩]   (36:28-31) †  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።  † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
🕊 [ ✞ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ] 🕊  †  ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ  †   🕊 ከ ፲፪ [12] ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል:: ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም [አልቦ ትንሳኤ ሙታን] የሚሉ ናቸው:: መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል:: ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: [ዮሐ.፲፩፥፲፮] (11:16) ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም :- ፩. ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው ፪. አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር:: ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ [ጌታየና አምላኬ]" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን [መለኮትን] ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች:: ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ [ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት]" ሲሉ ያከብሩታል:: ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል:: በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት :- "ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ: አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ:: በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል:: ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ፴፰ [38] ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: በመጨረሻም በ፸፪ [72] ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል:: እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ [ቶማስስ] ማለት ጸሐይ [ኦርያሬስ] እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: 🕊 [ †  ግንቦት ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ [ከ ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት] ፪. ቅድስት አርሶንያ [የቅዱስ ቶማስ ተከታይ] ፫. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ፪. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን ፫. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን " ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: " [ዮሐ.፳፥፳፮-፳፱]  (20:26-29) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]                 [   ክፍል - ፬ -  ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇
Hammasini ko'rsatish...