cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ቻናል ነው 👉👉ለጠቅላላ @weldwahid 👉👉ለአብነት እና ግእዝ ቋንቋ ትምህርት @weldwahidabinet 👉👉 ለቤተ መጻሕፍት አገልግሎት @Abaiyesuslib 👉👉ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @mels_asteyayet

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 090
Obunachilar
+124 soatlar
+207 kunlar
+8830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 "ኑ ቅድስት ሐናን እናግናት ፤ እግዚአብሔር አግኗታልና ። በሥጋም አያቱ ናትና ። እርሷ ከወርቅና ከብር ትመረጣለች ፤ መልካቸው  የተለያየ ከሆኑ ከአስራ ሁለቱ ዕንቁዎችም ፈጽማ ትመረጣለችና።" 🌹 የቅዱስ ኢያቄም ወሐና የማክሰኞ ድርሳን🌹 🌹🌹🌹🌹✨✨✨🌹🌹🌹🌹
Hammasini ko'rsatish...
5👍 1
"ራስህን ለማየት ወደ መስታወት ብትመለከት ውበትህን ወይም ጉድለትህን ያሳይሀል። ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም ። ማንም ሊያመልጥበት በማይችለው በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል ።" ቅዱስ መቃርዮስ
Hammasini ko'rsatish...
" እምነት ባሕርን ከፍሎ ያሻግራል በበረሃ መካከል ከሚገኝ አለትም ውኃ አፍልቆ ያጠጣል:: ለዚህ ነው መጽሀፍ ቅዱስ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል የሚለው:: " ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ
Hammasini ko'rsatish...
7
" ሁልጊዜ የሚያመሰግን አንደበት ከልኡል እግዚአብሔር በረከትን ያገኛል:: " ማር ይስሀቅ
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 2
የ ጥያቄና መልስ ውድድር መክፈቻና የአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ቤተመጻሕፍት የመጻሕፍት ጉባኤ በድምቀት ተካሔደ:: 1ኛው ዙር የጥያቄና መልስ ውድድርና 2ኛው የ መጻሕፍት ጉባኤ በድምቀት ተካሔደ:: ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ : ወልድ ዋህድ ሚዲያ የዝግጅቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ዲ/ን ቢንያም አለባቸው  "ነገረ መንፈስ ቅዱስ" በተሰኘው የዲያቆን ልሳነ ጽድቅ ኪዳነ  መጽሐፍ ላይ እጅግ ጥልቅ ይዘት ያለው የመጽሐፍ ዳሰሳ አቅርበዋል:: በዕለቱ አንደኛ ለወጣው ቡድን በዕለቱ የተዳሰሳወን መጽሐፍ ነገረ መንፈስ ቅዱስ   የተሸለሙ ሲሆን ከዲ/ን በረከት አበበ  እጅ ተቀብለዋል:: መርሐ ግብሩ በዲ/ን ሰሎሞን ኢያሱ የተመራ ሲሆን የጥያቄና መልስ ውድድሩ በዲ/ን ኤርሚያስ ወንደሰን  አወዳዳሪነት ተካሒዶአል:: ዲ/ን ኤርሚያስ ወንደሰን ከጥያቄዎቹ በተጨማሪ ለታዳሚው  ግንዛቤ የሚሠጡ ታሪኮችን በመናገር በንቃት እንዲከታተል አድርጎል።  ውድድሩ የመጀመሪያ እንደመሆኑ  በስኬት ተጠናቅቋል:: በቀጣይ የአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ቤተመዳሕፍት የሚያዘጋጀው የመጻሕፍ ዳሰሳ  በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምና  ቀን ሐምሌ 21 ታኦዶክስ መጽሐፍ የሚዳሰስ ይሆናል ። ቀጣይ በጥያቄ እና መልስ ውድድሩ ለመሳተፍ ከመጽሐፍ ዳሰሳው ባሉት ሳምንታት ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:30 በሰንበት ትምህርት ቤታችን የቴሌግራም ቻናል ወልድ ዋህድ ሚዲያ(    https://t.me/weldwahid)የሚለቀቅ ሲሆን በድምር ውጤት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 6 ተወዳዳሪዎች በቀጥታ ተሳታፊ የሚሆኑ ይሆናል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 4 2
"መከራን በመከራነቱ ሳይሆን በመካሪነቱ ውደደው።"         ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የተጽፈውን ሁሉ አንብቡ በጥንቃቄም አስተውሉ ስትማሩና መጽሐፍትን ሳታነቡ የምታገኙት ዕውቀት አይኖርም ከሊቃውንት ተማሩ የመጽሐፍትንም ቃል አዳምጡ፡፡"     📖  መጽሐፈ ቀሌምንጦስ📖 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨       📖የመጻሕፍት ዳሰሳ ጉባኤ📖 ዛሬ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በምዕራፈ ጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ  መርሐግብራችንን ለመጀመር አስፈላጊውን ሁሉ አዘጋጅተን እየጠበቅናችሁ ነው። መጥታችሁ  ለሕይወት የሚበጀንን ቃል አብረን እንማማር። ጠሪ አክባሪያችሁ የውልድ ዋህድ ሰንበት ትምህርት ቤት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ቤተ መጻሕፍት። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
"በቤተ ከርስቲያን ውስጥ ስትቆም ከቅዱሳን መላእክት ጋር በገነት እንዳለህ ቁጠርና ከወንድሞቻችህ ጋር አብረህ መጸለይ የማይገባህ አድርገህ ራስህን አዋርድ። ወንድሞችህ እንዴት እንደ ቆሙ ወይም እንዴት እንደሚያዜሙ ለመመልከት ወደፊት እና ወደኋላ እንዳትገላመጥ በንቃት ቁም፡፡ ይልቁንም ራስህን፥ዜማህንና ኃጢአቶችህን ብቻ ተመልከት።" የሥነ መለኮት ሊቅ ቅዱስ ስምዖን
Hammasini ko'rsatish...
6👍 1
የማይቈጣጠሩትን ምላስ ያህል መጥፎ ፆር የለም፤እርሷ የፈተና ሁሉ እናት ናትና። ✨በበዓቴ የነበረችውን አልጋ ሳልጠቀምባት ከበዓቴ ወጣሁ፤ምክንያቱም በዚያ መኖሯን የነገረኝ ሰው አልነበረምና። ✨እኔ ማንንም አሳዝኜ ወደ መኝታዬ ገብቼ አላውቅም፤ማንም አሳዝኖኝ ወደ መኝታው እንዲሔድ አልተወውም። ✨ቍጡ ሰው ምንም እንኳ ሙት የማሥነሳት ችሎታ ቢኖረው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ✨ልቡን መቈጣጠር ራስንም ለእግዚአብሔር ሲሉ ከመሻቱ ማራቅ ጠባብ እና ከባድ በር ነው።"              አባ አጋቶን
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ቅዱሳት መጻሕፍትን ገንዘብ ማድረግ መልካል ነው። መጻሕፍትን አብዝተን በተመለከትን ቍጥር ወደ ኃጢአት ማዘንበላችን ይቀንሳል። በእምነት ጸንተን ጽድቅንም የበለጠ እንፈጽም ዘንድ ያነቃቁናል። ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ከኃጢአት ፍላጻ የመደበቂያ ጽኑ መከላከያ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍትን አለማወቅ በአዘቅት እና በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መኖር ነው።"           ቅዱስ ኤጲፋንዮስ 📖📖📖📖 1ቀን ቀረው📖📖📖📖
Hammasini ko'rsatish...
3😱 1